የያዕቆብ መልእክት 5
8፤ እናንተ ደግሞ ታገሡ፥ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።
James 5
8 You also be patient. Establish your hearts, for the coming of the Lord is at hand.
👉🏻 Follow @hymnsofmes

❤4👍1
የዮሐንስ ራእይ 22
20፤ ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ፡ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።
21፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።
#daily #bible
@hymnsofmes

❤3
ፍቃዳችሁ ከሆነ ይህንን ፀሎት አብረን እንፀልይ🙏🏾
የተወደድከው አባታችን ሆይ ፤
እኛ በሚያስደንቅ ሁኔታ የአንተን ኃይል እና መንፈስ እንፈልጋለን። በአማኞች መካከል ባለው ና በፈሰሰው የፍቅር እና የአንድነት መንፈስ እንድትሞላን እንጠይቃለን። ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በመተው ትልቁን ምክንያት የሆነውን የክርስቶስን ደም ዘውትር እንድንመለከት ዘንድ እንድትረዳን እንጠይቃለን። አባት ሆይ በእውነት በፍቅር እንድንኖር እርዳን። ይህ የሚቻለው በመንፈስህ ሃይል ብቻ መሆኑን ስለምናውቅ በተአምራዊ መንገድ ምድራችንን ፤ ቤተ ክርስቲያንን እንድታሻግር በአዲስ ሙላት እና ግንዛቤ ህዝቦቻችንን ወደ እናንተ እንድትመልስ እና ሌሎችም ይህንን እንዲያውቁህ ወደ እውነትህ እንድትስባቸው እንጠይቃለን። እኛን የሚመራንን የአንተ ጥበብን እንፈልጋለን፣ መንፈስህም እንዲመራን፣ እንፈልጋለን። ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ስለሆንክ እናመሰግናለን።
በኢየሱስ ስም አሜን።🙏🏻🙏🏻🙏🏻

❤8
የዕለቱ ሐሳብ
"በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው።"
(ምሳ 19፥21 አመት)
☞ አንድ ሰው በቀን በአማካኝ 70,000 ጊዜ ያህል ሐሳብ ያስባል ይባላል። ይህ 'ከምናስበው' በላይ እጅግ ብዙ ነው። ከዚህ ሁሉ መካከልም ፍሬ ያዘለ—ቁም ነገር የሆነ—ለውጤትም የሚበቃው ጥቂቱ ነው።
☞ ጠቢቡ እንዲህ አለ፤ "በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው" (19፥21)።
☞ ከእልፍ ሐሳብ መካከል አንድ ከተፈጸመ፣ ይህንንም ያንንም ማሰብ ትቶ፣ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለማግኘት ጸጥና ስክን ማለት ነው የሚያስፈልገው።
☞ የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚያደምጡም ሌላ ሌላውን ሁሉ የለጎሙ (ጸጥ ያሰኙ) ናቸው።
☞ ይህ ቀን ወደ እግዚአብሔር ሀሳብ ይበልጥ የምንጠጋበት ይሁንልን ፤ ተከናወኑ 🙏🏿

❤9
☞ የዕለቱ ቃል
"የማያወላውል ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ አዲስ መንፈስ በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ድንጋዩን ልብ ከውስጣቸው አወጣለሁ፤ ሥጋ ልብም እሰጣቸዋለሁ።"
(ሕዝ 11፥19 አመት)
————————————————
☞ ለአዲስ ነገር አዲስ መያዢያ (ማስቀመጪያ) ያስፈልጋል፤ አለበለዚያ ያልተጣጣመ ይሆንና የተፈለገው ውጤት አይመጣም።
☞ በቀደመው #ብሉይ_ኪዳን እግዚአብሔር #ከ613 ያላነሰ ሕግጋት ለሰዎች ሰጠ። ይህ ግን የልብ ለውጥ ወይም የሚፈለገውን የባሕርይ ለውጥ አላመጣም። ስለዚህም፣ በዚያው ኪዳን እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ "የማያወላውል ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ አዲስ መንፈስ በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ድንጋዩን ልብ ከውስጣቸው አወጣለሁ፤ ሥጋ ልብም እሰጣቸዋለሁ" (ሕዝ 11፥19)።
☞ ለ"አዲስ መንፈስ" አዲስ ልብ ያስፈልጋል፤ ይህ ልብ "የሥጋ" ሲሆን፣ ትርጕሙም የሚሠራ፣ የሚስተካከል፣ ሕይወትን የሚቀበልና የሚያስተናግድ ማለት ነው።
☞ በአዲሱ ኪዳን ውስጥ ላለን ለእኛም ይህ ልብ ተሰጥቶናል፤ ሠሪ ለሆነው አምላክ የሚመች ማንነት እንዲኖረንም አዲሱን ልብ ዕለት ዕለት #እናሠራው ።
☞ ከታች በምልከው voice record አብረን እንፀልይ🙏🏾
☞Join @hymnsofmes

❤3👍1
1 ዮሐንስ 4:19፤ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
:20፤ ማንም፦ “እግዚአብሔርን እወዳለሁ፥” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፥ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
21፤ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።

☞ ዳዊት ገና ወጣት እያለ፣ ዳዊት መንጋውን ሲጠብቅ አንበሳና ድብ እንዲገድል እግዚአብሔር አስችሎታል።
☞ ደግሞም በግዙፉ ጎልያድ ላይ ድልን ሰጠው (1ሳሙ 17፡34–37፣ 45–47)።
☞ በተጨማሪም፣ በመዝሙር 18፡32 ላይ፣ ዳዊት “መንገዱን” የጦር መንገዱን ጨምሮ እንከን የለሽ ያደረገው እግዚአብሔርን ሲያመሰግነው እናያለን።
☞ እኛም ክርስቲያኖችን ከዲያብሎስና ከጭፍሮቹ ጋር ለመዋጋት አዘጋጅቶናል፣ ይህም የእኛ እውነተኛ ውጊያዎች በ (ኤፌሶን 6፡) ላይ ተጠቅሰዋል። ኤፌሶን 6፡10–18 ያዘጋጀውን መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ እና ጠቃሚ የጦር ግብአቶች ይገልጻል። ከዚህ የጦር ትጥቅና ጸሎትም ከተጠቀምን “የዲያብሎስን አሳብ መቃወም እንችላለን” (ኤፌሶን 6፡11)።

🙏3❤2
የዕለቱ ቃል
☞ ይህ ሙሉ ምዕራፍ በተስፋ የተሞላ ነው…እና ወደዚህ ምዕራፍ መጨረሻ ስትደርሱ… ሞት በድል እንደሚዋጥ የድል አዋጅ ብቻ ታያላችሁ… ሞት ከእንግዲህ መውጊያ የለውም ፣ የሞት መውጊያ ፣ የኃጢአት ኃይል ሕግ ነው… ግን እግዚአብሔርን ይመስገን ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል #ድልን ሰጥቶናል ደግሞ በየዕለቱም ይሰጠናል።
☞ "በጌታ በኢየሱስ በኩል #ድልን" ያገኘና ድሉ የገባው ማኅበረሰብ ጸንቶ ለመቆም አይቸገርም። ጳውሎስ ያስገነዘበው ይህንኑ ነው፤ "ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። #ለጌታ_ሥራ_ዘወትር_የምትተ_ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት #በከንቱ_እንዳልሆነ ታውቃላችሁ" (1ቆሮ 15፥58)።
☞ በምንም ነገር አለመናወጥ እንዴት ይቻላል? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል።
☞ የክርስቶስ ትንሣኤ ያስገኘልን ውጤት ግን ለማረፍም ሆነ ለመበርታት፣ ለመሥራትም ሆነ ለመድከም አቅም ይሆናል።
☞ #የማይናወጥ ሕዝብ #ያረፈ_ብቻ_ሳይሆን #የሚተጋም_ነው።
☞ ድል ነሺው ጌታ ድሉ ውስን ወይም የአንድ ጊዜ አይደለም፤ የዘላለም እንጂ! ስለዚህም በርሱ የሚታመኑ በሁኔታዎች አካሄድ ወይም መወሳሰብ ወይም መባባስ አይናወጡም። ይልቁንም፣ እየታመኑ ይቀጥላሉ፤ እየቀጠሉም ይተጋሉ።
🙏ወዳጆቼ እግዚአብሔር ለመንግሥቱ ስራ በትጋት እንድንቀጥል እና ዘውትር በፀጋው እና በሀይሉ እንድንፀና ይርዳን !!!
አሜን !!

❤5
#የዕለቱ_ቃል
“ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።"
(ዮና 2፥7 አመት)
የዕለቱ ሐሳብ
☞ የእግዚአብሔር ምሕረት ነፍስን ያተርፋል።
☞ እግዚአብሔር ከ120 ሺ በላይ ነዋሪ የነበራትን ነነዌን ለማትረፍ ፈልጎ የንስሐ ስብከት እንዲሰብክ ነቢዩ ዮናስን ላከው።
☞ እርሱ ግን በድርጊቱ እምቢታውን ገለጠ፤ ወደ ተርሴስ ኮበለለ። ሁሉን የሚገዛ አምላክም በትልቅ ዓሣ ወደ ተልዕኮው አቅጣጫ መለሰው።
☞ በዚያም መካከል እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች" (2፥7)።
☞ ስለ ነነዌ ነፍስ ግድ ያላለው ነቢይ፣ በዓሣው ሆድ ሳለ ነፍሱ ዛለች፤ ምሕረቱ ለሁሉ የሚበቃውንም አምላክ ዐሰበ።
☞ አይገርምም ዩናስ ከመሬት ያቃተው ጸሎት ከባሕሩ ጥልቅ ወደ ሰማይ ዐረገ። በርግጥም፣ የዛለች ነፍስ በጸሎት ከዝለቷ ነፃ ትወጣላች፤ ጸሎቷም ሰማይ ድረስ 'መሄድ' ይችላል።
☞ እዚህ ላይ ሌላው መገንዘብ ያለብን ዩናስ እግዚአብሔር ያደረገለትን፣ ለሌሎች ያደረገውን፣ ምን ማድረግ እንደሚችል ና ለማድረግ ቃል የገባለትን አስታወሰ። ይህም ነፍሱ እንዳይዝል አድርጎታል።
☞ እናስተውል፣ መከራችን አምላክን እንድናስብና በዚህም ወደ እሱ እንድንጸልይ ያደርገናል። ነፍሳችን ስትደክም እግዚአብሔርን ማስታወስ አለብን ፤ እርሱንም ስናስታውስ ዘውትር ጸሎትን ወደእርሱ ማቅረብ አለብን።
☞ በተለያዩ ፈተና እና መከራ ውስጥ እያለፋችሁ የዛላችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ነፍሳችሁን ከዝለት ይጠብቃት!
አሜን!!
𓂀𝕊𝕙𝕒𝕣𝕖𝕤 𝕚𝕥 𝕨𝕚𝕥𝕙 𝕪𝕠𝕦𝕣 𝕗𝕣𝕚𝕖𝕟𝕕𝕤𓂀
°◤𝙅𝙤𝙞𝙣 @hymsofmes 𝙛𝙤𝙧 𝙢𝙤𝙧𝙚 𝘿𝙖𝙞𝙡𝙮 𝘿𝙚𝙫𝙤𝙩𝙞𝙤𝙣 𝙨𝙚𝙧𝙫𝙞𝙘𝙚 ◥°

❤7👍1
#የእግዚአብሔር _ቃል
"በምክርህ መራኸኝ፤ ኋላም ወደ ክብር ታስገባኛለህ።"
(መዝ 73፥24 አመት) ከቻልን ሙሉ ምዕራፉ ይነበብ)
☞ አሳፍ ለጌታ መገኘት ብቻ ሳይሆን ለመንግስተ ሰማያት ስላለው መመሪያ እና ማረጋገጫም አመስጋኝ ነበር። ከገጠመው #የእምነት_ቀውስ ወዲያውኑ እንዲያገግም የረዳው ያ መመሪያ ነው። በመዝሙር 73፡2–3 እንዲህ ብሎ ነበር ❝ እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ አረማመዴም ሊወድቅ ትንሽ ቀረ። የኃጢአተኞችን ሰላም አይቼ፡ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና ። ❞ ይላል !
☞ እግዚአብሔር #ከኀይሉ በፊት #ምክሩንና_ሐሳቡን ያስቀድማል። የግንኙነት አምላክ ስለሆነውም በምክሩ የሚመራ አምላክ ነው። በምሪቱ ውስጥም አቅርቦቱና ከለላነቱ አጃቢ ናቸው።
☞ እግዚአብሔር ሲመራ የሚመራው ወደ ራሱ ወደ መታወቁ ስለሆነ መድረሻው ወይም ግቡ የሚሰላው በምናከማቸው በስኬት ቅደም ተከተል አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት ተብሎ አይደለም፤ #በሕልውናውና #በክብሩ በመገኘት እንጂ።
☞ እንደ ሰው የምናስቀምጣቸው ግቦች አሉ፤ እነዚህ ጥሩ ናቸው፤ የሕይወት ምዕራፎች እንጂ ዋነኛ ፍጻሜዎች ግን አይደሉም፤ ሲደረስባቸው ሌላ ድጋፍ፣ ሌላ አቅርቦት፣ ሌላም ምሪት ይፈልጋሉና። ከጌታ ጋር የምናደርገውና በምክሩ የምናሳምረው ጕዞ መዳረሻ ግን ክብሩ ነው፤ እግዚአብሔር እየመራቸው ከክብሩ የሚጎድሉ የሉም።
⚠️ ወዳጆቼ የጌታን ፈቃድ እና ምክሩን በየዕለቱ እንድናውቅ ሰውነታችንን ሕያው ቅዱስና ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርገን ለጌታ እያቀረብን ፤ በአእምሮ መታደስ እየተለወጥን ፤ ዓለምን ለመምሰል እምቢ እያልን #ወጥነት እና #ፅናት ያለውን #ትጋት እና #ባህሪ እያሳየን ጌታ ባስቀመጠን ስፍራ በታማኝነት እንድናገለግለው ደግሞ እንድንኖር ይርዳን። አሜን !
Join @hymnsofmes

❤8👍1
ብጹዕ ሆኖ
በመንፈሱ ድኻ ... የመንግሥተ ሰማያት የእርሱ የሆነ፣ የሚገባ፣ ሌሎችን የሚያስገባ ድኻ
የሚያዝን... የሚጽናናና ሌሎችን አልቃሾች የሚያጽናና።
የዋሕ... በመስቀሉ ሞት ምድርን የሚወርስ፣ ቀሊል ቀንበሩን ሌሎች ላይ አድርጎ ራሳቸውን ወደመካድ የሚመራ ልዝብ፣ ልስልስ መሪ፣ ዓለምን የሚያንበረክክ ጽኑ ፍቅር።
ጽድቅን የሚራብ፣ የሚጠማ... የሞቱን ጽዋ ጨልጦ የራሱን ብቻ ሳይሆን የሌሎችን የጽድቅ ረሃብ የሚያረካ።
ምህረትን የሚያደርግ፣ ለጠላቶቹ የሚሞት ... በእግዚአብሔር አብ የትንሳዔን ምህረት የሚያገኝ፣ የትንሳዔን ምህረት የሚያስገኝ።
ሰላምን የሚያወርድ፣ ጨቋኞቹ እየሰቀሉት የሚመሰክሩለት ... "እውነትም ይኽ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነበር!" (ማቴ. 27፥54)
ስለጽድቅ ብሎ የተሰደደ ባለመንግሥት።
@hymnsofmes
_________________________
እኔ ደካማው ላይ በረከትህ ይውረድብኝ ጌታዬ! 🤲
©️sara a.

❤9👍1👏1🙏1