GLOW KG AND PRIMARY SCHOOL ADDIS ABABA ETHIOPIA.
1.42K subscribers
2.54K photos
306 videos
220 files
14 links
Always strive for Excellence!!
Download Telegram
ቀን፡ 16/12/2017ዓ.ም

ውድ ወላጆች፣  🫲🫲ሰላምታችን ይድረሳችሁ።


ለተማሪዎች ( ከቅድመ  አንደኛ እስከ 8ኛ ክፋል ) መጽሐፍ የከፈላችሁ ወላጆች ከዚህ በታች ባለው መርሃ ግብር መጽሐፍ ከትምህርት ቤት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን በትህትና  እንገልጻለን።

👉ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የተማሪዎች መጽሐፍ ሰኞ  ነሐሴ 19/2017 እና ማክሰኞ ነሐሴ 20/2017ዓ.ም   በስራ ሰዓት
መውሰድ የምትችሉ መሆኑን በትህትና  እናሳውቃለን ፡፡


🙏ትምህርት ቤቱ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ውድ የግሎው  ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንኳን ለ2018  ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ‼️     
            
   ዘመኑ የሰላም ፣ ፍቅር እንዲሁም የብልፅግና እንዲሆንላችሁ እየተመኘን  
በቅድሚያ የልጆቻችሁ ደህንነታቸው ተጠብቆ  በጥበብ፣ በእውቀት፣ የፈጠራ ክህሎትና በቴክኖሎጂ መብቃት፣በአካዳሚክ ውጤትና ስነምግባር መላቅ፣ እንድንዘራባቸው፣ተኮትኩተው እንዲያድጉ እና ብቁ እንዲሆኑ ትክክለኛ ምርጫችሁ አድርጋችሁ
❤️ግሎው ❤️ ት/ቤትን ስለመረጣችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ ልንላችሁ እንወዳለን፡፡

የ2018 ዓ.ም ትምህርት አጀማመር በተመለከተ የሚከተሉትን ጠቃሚ መረጃዎች እንድትገብሩ እንጠይቃለን፤

1.  የ2018 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምረው ሪቡዕ  መስከረም 07/2018 ዓ.ም ይሆናል፡፡

2.  ከምስከረም 07- 09/2018 ዓ.ም ትምህርት ለግማሽ  ቀን (እስከ 6፡00) ብቻ ይሰጣል፡፡


3.  ከነርሰሪ እስከ KG -3 ክፍል ላሉ ተማሪዎች የትምህርት ፅህፍት መሳሪያ የምንቀበለው  መስከረም ሰ
05 /2018 ዓ/ም እስከ ማክሰኞ 06/2018 ዓ.ም ነው፡፡ ተማሪዎች ይዘዋቸው የሚመጡ ማንኛውን ቦርሳ ፣ ምሳ እቃ እና የትምህርት ቁሳቁሶች  ላይ ስማቸውን  እንዲፃፍበት እናሳስባለን፡፡

4.  የተማሪ መታወቂያ ያልወሰዳችሁ የተማሪ ወላጆች አርብ 09/2018 ዓ.ም ጠዋት እንድትወሰዱ እያሳሰብን መታወቂያ ያልያዘ ወላጅ ለተማሪዎች ጥንቃቄ ሲባል ከሰኞ12/01/2018ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት መግባት እንደማይቻል ከወዲሁ እንዲታወቅ፡፡

5.  ሰርቪስ ለመጠቀም የምትፈልጉ ከዚህ በፊት ሲፈጠሩ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ሲባል ተቋማችን  ከትራንስፖርት
ለቤት ጋር ለመስራት  ስምምነት ስላደረግን በቀጣይ ቀናት  ዝርዝር መረጃዎችን የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ ፡-👇👇👇👇👇👇

ቀጣይ ከትምህርት አጀማመር  እና ሌሎች ጉዳዮች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ስለምንለቅ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን በንቃት እንድትከታተሉ እናሳስባለን ፡፡

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻