ነገን ስለማናውቅ⛅️🌧 ነገን በማወቅ ህይወትን የሚመራት ሰው ማን ነው??
ማንም፡፡ ነገን በተስፋ እንጂ በሙሉ ልብ ይሄ ይሆናል ያኛው
ደግሞ አይሆንም በማለት በዕርግጠኝነት የሚያውቅ ማንም
ፍጡር የሰው ልጅ የለም፡፡ ምክንያቱም ዓለም እርግጠኛ
ባለመሆን የተሞላች ናት እኛ ሰዎች ደግሞ የነገን የማወቅ
ስልጣን እና ክህሎት የሌለን ፍጡራን ነን ፡፡ እስኪ ከዚህ
በፊት ይሆናል… ይሳካል ….ይፈጸማል ብላችሁ ፍፁም
እርግጠኛ የሆናችሁበትን እና ያልተሳካበትን ሁኔታ
…….አልያም ከዚህ ሰው ጋር ብዙ እቆያለሁ ወይም ብዙ
እሰራለሁ ብላችሁ ያልሆነበትን ሁኔታ አስቡ እስኪ…….
አሁን ደግሞ ይህ የፈጠረባችሁን አሉታዊ ስነ-ልቡናዊ እና
አካላዊ ጉዳቶች ለአፍታ አስቧቸው፡፡ የተረሳ ዶሴ አስከፍቼ
ትካዜን ጫርኩኝ እንዴ?? እንግዲያውስ ይቅርታ
እጠይቃለሁ፡፡ ምናልባትም እስከ አሁን ድረስ ከእነዚህ
ጉዳቶች ጋር እየታገላችሁ የምትኖሩ ይሆናል፡፡ መቼም
ህይወት በአቀበት… በቁልቁለት እና ለጥ ባለ ለምለም
መስክ የተሞላች ናት፡፡ ባንዱ ሲሞላልን… በሌላው ሲጎልብን
….ባንዱ ስናጣ በሌላው ስናገኝ ….ባንዱ ስንደሰት በሌላው
ስናዝን እንኖራለን ፡፡ ባለፈው ስለ ይቅርታ በለጠፍነው ጽሁፍ
ላይ ህይወት የሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ሙሌት ናት ብለንም
የለ!! ስለዚህ በቅድሚያ የሆነ ነገር ለመፈጸም ስንነሳ
በአዕምሮአችን ይሳካል ብለን ማሰባችን መልካም እና
ለመስራት ላሰብነው ስራ አነቃቂ ቢሆንም፤ ላይሳካ ይችላል
የሚለውንም በመጠኑ ማየት ይኖርብናል። ለምን አላችሁኝ??
ምክንያቱም ጉዳታችን ከጥበቃችን እኩል ነውና ነው
መልሴ። ታላቁ የጥበብ ሰው ዊሊያም ሼክስፒር ባንድ ወቅት
ቅድመ ጥበቃ የጉዳት ምንጭ ነው (expectation is the
root of heartache) ብሎን ነበር፡፡
አብዝተን የሻትነው እና ጫፍ ለማድረስ የቋመጥንለት
ሳይሳካ ሲቀር በእራስ መተማመናችን ይሻክርብናል ፣
ለእራሳችን የሚኖረን ግምትና እውቀት አናሳ ይሆናል።
አካላችን እና አእምሮአችን እንደ አለቃና ምንዝር በሆነ
ግንኙነት ውስጥ ሰለሰለሚሰሩ አዕምሮአችን እነዚህን
አሉታዊ ስሜቶች ሲያስተናግድ የአካላችንን አምራችነት
በእጅጉ ያሳንሰዋል ። በተጨማሪም ለአዕምሮ መታወክ አንደ
ምክያትነት cognitive ሳይኮሎጂስቶች ከሚጠቅሱዋቸው
ነገሮችን አንዱ ሁኔታው ከመከሰቱ አስቀድሞ አብዝቶ
አልያም አሳንሶ መጠበቅ እንደሆነ ምን ያህሎቻችን እንገነዘብ
ይሆን?? ስለዚህ መፍትሄው ከላይ የጠቀስነው ነው።
አመክኖአዊ እና ነባራዊ የሆነ ቅድመ ግምት ለነገሮች
ሊኖረን ይገባል። ይህ ማለት ግን ቀድሞ አይሳካም ብሎ
በማሰብ ነገሮችን አለመፈጸም ሳይሆን አሁን የጀመርኩት
የሞከርኩት ነገር ባይሳካ ቀጣይ ዕቅዴ (plan B) ምንድንነው
ብሎ ማሰብ ነው፡፡ አልያም ደግሞ ሙከራችን አልተሳካም
ማለት ሰማይ ተደፋብን ፣ የዓለም ፍጻሜ ሆነ ማለት
እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ በመጨረሻም ሁልጊዜ
ቅድመ ጥበቃችን እና ጉዳታችን እኩል እንደሆነ ልንገነዘብ
ይገባል ፡፡ ምዕራባውያኖቹ እንደሚሉት
(expectation=disappointment) ነውና ጎበዛዝት ….ስለነገ
ስለማናውቅ ……ጠንቀቅ!! ብለን የዛሬን በዚሁ እንቋጨው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ….
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ማንም፡፡ ነገን በተስፋ እንጂ በሙሉ ልብ ይሄ ይሆናል ያኛው
ደግሞ አይሆንም በማለት በዕርግጠኝነት የሚያውቅ ማንም
ፍጡር የሰው ልጅ የለም፡፡ ምክንያቱም ዓለም እርግጠኛ
ባለመሆን የተሞላች ናት እኛ ሰዎች ደግሞ የነገን የማወቅ
ስልጣን እና ክህሎት የሌለን ፍጡራን ነን ፡፡ እስኪ ከዚህ
በፊት ይሆናል… ይሳካል ….ይፈጸማል ብላችሁ ፍፁም
እርግጠኛ የሆናችሁበትን እና ያልተሳካበትን ሁኔታ
…….አልያም ከዚህ ሰው ጋር ብዙ እቆያለሁ ወይም ብዙ
እሰራለሁ ብላችሁ ያልሆነበትን ሁኔታ አስቡ እስኪ…….
አሁን ደግሞ ይህ የፈጠረባችሁን አሉታዊ ስነ-ልቡናዊ እና
አካላዊ ጉዳቶች ለአፍታ አስቧቸው፡፡ የተረሳ ዶሴ አስከፍቼ
ትካዜን ጫርኩኝ እንዴ?? እንግዲያውስ ይቅርታ
እጠይቃለሁ፡፡ ምናልባትም እስከ አሁን ድረስ ከእነዚህ
ጉዳቶች ጋር እየታገላችሁ የምትኖሩ ይሆናል፡፡ መቼም
ህይወት በአቀበት… በቁልቁለት እና ለጥ ባለ ለምለም
መስክ የተሞላች ናት፡፡ ባንዱ ሲሞላልን… በሌላው ሲጎልብን
….ባንዱ ስናጣ በሌላው ስናገኝ ….ባንዱ ስንደሰት በሌላው
ስናዝን እንኖራለን ፡፡ ባለፈው ስለ ይቅርታ በለጠፍነው ጽሁፍ
ላይ ህይወት የሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ሙሌት ናት ብለንም
የለ!! ስለዚህ በቅድሚያ የሆነ ነገር ለመፈጸም ስንነሳ
በአዕምሮአችን ይሳካል ብለን ማሰባችን መልካም እና
ለመስራት ላሰብነው ስራ አነቃቂ ቢሆንም፤ ላይሳካ ይችላል
የሚለውንም በመጠኑ ማየት ይኖርብናል። ለምን አላችሁኝ??
ምክንያቱም ጉዳታችን ከጥበቃችን እኩል ነውና ነው
መልሴ። ታላቁ የጥበብ ሰው ዊሊያም ሼክስፒር ባንድ ወቅት
ቅድመ ጥበቃ የጉዳት ምንጭ ነው (expectation is the
root of heartache) ብሎን ነበር፡፡
አብዝተን የሻትነው እና ጫፍ ለማድረስ የቋመጥንለት
ሳይሳካ ሲቀር በእራስ መተማመናችን ይሻክርብናል ፣
ለእራሳችን የሚኖረን ግምትና እውቀት አናሳ ይሆናል።
አካላችን እና አእምሮአችን እንደ አለቃና ምንዝር በሆነ
ግንኙነት ውስጥ ሰለሰለሚሰሩ አዕምሮአችን እነዚህን
አሉታዊ ስሜቶች ሲያስተናግድ የአካላችንን አምራችነት
በእጅጉ ያሳንሰዋል ። በተጨማሪም ለአዕምሮ መታወክ አንደ
ምክያትነት cognitive ሳይኮሎጂስቶች ከሚጠቅሱዋቸው
ነገሮችን አንዱ ሁኔታው ከመከሰቱ አስቀድሞ አብዝቶ
አልያም አሳንሶ መጠበቅ እንደሆነ ምን ያህሎቻችን እንገነዘብ
ይሆን?? ስለዚህ መፍትሄው ከላይ የጠቀስነው ነው።
አመክኖአዊ እና ነባራዊ የሆነ ቅድመ ግምት ለነገሮች
ሊኖረን ይገባል። ይህ ማለት ግን ቀድሞ አይሳካም ብሎ
በማሰብ ነገሮችን አለመፈጸም ሳይሆን አሁን የጀመርኩት
የሞከርኩት ነገር ባይሳካ ቀጣይ ዕቅዴ (plan B) ምንድንነው
ብሎ ማሰብ ነው፡፡ አልያም ደግሞ ሙከራችን አልተሳካም
ማለት ሰማይ ተደፋብን ፣ የዓለም ፍጻሜ ሆነ ማለት
እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ በመጨረሻም ሁልጊዜ
ቅድመ ጥበቃችን እና ጉዳታችን እኩል እንደሆነ ልንገነዘብ
ይገባል ፡፡ ምዕራባውያኖቹ እንደሚሉት
(expectation=disappointment) ነውና ጎበዛዝት ….ስለነገ
ስለማናውቅ ……ጠንቀቅ!! ብለን የዛሬን በዚሁ እንቋጨው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ….
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ጠቢቡ ሰለሞን “ከሰማይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም”
ቢልም ቅሉ በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ግን በየጊዜው
አዲስ ነገር የመፍጠር ጉጉት ድምጽ ጎልቶ ይሰማል፡፡
ተዟዙረን ዓለምን ማየት፤ ያልሰራነውን መስራት፤ በጥቅሉ
ያለማቋረጥ መለወጥ እና ማደግ እንፈልጋለን፡፡
የማንፈልገው ፍላጎት አልባ መሆን ነው፡፡ የስነ-ልቡና
ሃኪሞችም ከሰማይ በታች ላለ ማንኛውም ነገር ፍላጎት
ማጣት የድብርት ህመም ግንባር ቀደም ምልክት ነውም
ይላሉ፡፡
ሁሉ በእጃቸው የሆነላቸው ሰዎች ላባቸው ጠብ እስኪል
ድረስ ይሰራሉ፡፡ ባለሃብቶች ማልደው ጠዋት
ከሰራተኞቻቸው ቀድመው ስራ ገበታቸው ላይ ይገኛሉ፡፡
በአንድ አጋጣሚ የተዋወኩት የአንድ ትልቅ ፋብሪካ ባለቤት
አንድም ቀን ሰራተኞቹ ቀድመውት ስራ ገበታቸው ላይ
እንደማይገኙ አጫውቶኛል፡፡ ከሳምንቱ ሰባት ቀናት ሌላ
ጉዳይ ከሌለው በስተቀር የፋብሪካው ዘበኞች ቢያንስ
አምስቱን ቀን ጠዋት ከሁሉም ሰራተኛ በፊት የአሰሪያቸውን
ፊት ነው የሚያዩት፡፡ ብዙ መጽሐፍትን ጽፈው ብዙ ትምህርት
የሰጡን እውቅ ሰዎች የዘመናቸው ጀምበር ጠልቃ
ህይወታቸው የሚያልፍበት አልጋ ላይ እንኳን ተኝተው ሁሉ
ይጽፋሉ፡፡ ከሃያ በላይ ዓለም አቀፍ ሬከርዶችን ሰባብሮ
ሚሊዮን ዶላሮችን ወደ ካዝናው ማስገባት የቻለው አትሌት
ኃይሌ ገ/ስላሴ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አንድ አንዴ ከህመም
ጋር ሁሉ እየታገለ ይሮጥ ነበር፡፡ በቅርቡ በሰጠው አንድ ቃለ
ምልልስ ላይም “ውድድር እንጂ ሩጫ አላቆምኩም”
ብሏል፡፡ አዲስ ነገርን ሁልጊዜም መፈለግ የሰው ልጅ
ተፈጥሮአዊ ባህሪ፣ ስነ-ልቡናችን የተገነባበት አሸዋና
ሲሚንቶ ነው፡፡ የበዛ የሰው ልጅ ስኬት ምስጢርም ይኸው
አዲስ ነገር ያለማቋረጥ መሻት ነው፡፡
መፈለግ ወደ መለወጥ የሚደረግ አንድ ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡
ቀጣዩ ምክንያታዊ እርምጃ ዕቅድ ማውጣት ነው፡፡ በህይወት
ጎዳና ላይ መነሳት መውደቃችን በአንድ ጎኑ የተደገፈው
አምድ ዕቅድ ነው፡፡ አቅደን ስንሰራ ይሳካልናል፤ ያለ ዕቅድ
ስንሰራ አንድም ስኬታችን የዘገየ ይሆናል፤ ሁለትም
ከነአካቴው የውሃ ሽታ ሆኖ ሊቀርም ይችላል፡፡ “አለማቀድ
ውድቀትን ማቀድ ነው” የሚባለው ከዚህ አኳያ ነው፡፡
ስቴቨን ኮቬይ በ “The 7 Habits of Highly Effective
People” ዝነኛ መጽሐፉ “Begin with the end in mind”
ይላል፡፡ የትኛውንም የህይወት ጉዞ ስትጀመሩ መድረሻችሁን
አውቃችሁ ጉዟችሁ ጀምሩ እንደ ማለት ነው፡፡ አለበለዚያ
ሁሉም መንገድ ደግም ክፉም ይሁን መንገዳችን ይሆናል፡፡
መርጠን ህይወታችን ካልመራን ባልመረጥነው እንመራለን፡፡
ስለዚህ ለውጥ ለማድረግ ስንነሳ አስቀድመን ምንድነው
የምፈልገው? የት ለመድረስ ነው የማስበው? ለሚሉ
ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ሊኖረን ይገባል፡፡
በተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች መንገድ ላይ ተሰነካክሎ
ወደ ኋላ መቅረት ቀላል ነው፡፡ የምንፈልገውን ካላወቅን
በሚፈልጉን ቁጥጥር ስር እንወድቃለን፡፡ ዝም ብሎ ቀን
ከሌት መስራት ብቻውን ውጤታማ አያደርግም፡፡
እዚህ ምድር ላይ ሁሉም ነገሮች ሁለት ጊዜ ነው
የሚፈጠሩት (All things are created twice) ይባላል::
የመጀመሪያው ፈጠራ አእምሯቸን ውስጥ የሚካሄደው ነው፤
አስበን፣ ተጨንቀን እና ተጠበን የምንወስነው ውሳኔ ሲሆን
ሲጀመር “በቃ እኔ ይኼንን ነው የምፈልገው” የምንለው ነው፤
መዝግበን የምናስቀምጠው ነው፡፡ ዕቅድን ማሰብ ብቻ
ሳይሆን ጽፎ ማስቀመጥም ቁልፍ ሚና ይጫወታል፤ “በቃል
ያለ ይረሳል በጽሑፍ ያለ ይወረሳል” እንዲሉ አበው፤
“ወረቀት ላይ አስቡ (Think on paper)” ይላል አንቶኒ
ሮቢንስም እንዲሁ፡፡
ሁለተኛው ፈጠራ በአእምሮአችን አውጥተን አውርደን
በወረቀት የመዘገብነውን የሚታይ ተጨባጭ እውነታ
ማድረግ ነው፡፡ መስራት፣ ማግኘት፣ መሆን የምንፈልገውን
መስራት፣ ማግኘት እንዲሁም መሆን ነው፡፡ የመጀመሪያው
ከሌለ ሁለተኛውም አይኖርም፡፡ ሳያስቡ እንደመናገር፣ ሳያጠኑ
ፈተና ላይ እንደመቀመጥ፣ የት መሄድ እንደሚፈልጉ ሳያውቁ
ጉዞ እንደመጀመር ነው፡፡
ሳይኮሎጂስቶች የምንፈልገውን ነገር ለማወቅ ይረዱናል
ብለው ያሰቧቸውን አንድ አንድ ስልቶች ቀይሰዋል፡፡ ከእነዚህ
ስልቶች ውስጥ አንዱ ለብቻችን ምንም ዓይነት ሃሳባችንን
የሚሰርቅ ነገር በሌለበት ስፍራ ቁጭ በማለት ከዚህ ዓለም
በሞት ከወዳጅ ዘመዶቻችን ስንለይ ለወዳጅ ዘመዶቻችን
እንዲነበብ የምንፈልገው የህይወት ታሪክ ምን ዓይነት ነው
ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ምን ሰርቶ አለፈ? ምን ዓይነት ሰው
ነበር? ምን ነበረው? ሰዎች ስለእሱ ምን ይላሉ? እነዚህ እና
መሰል ጥያቄዎችን ጸጥ ያለ ስፍራ ሆነን አእምሯችን ውስጥ
በማጉላላት አጠቃላይ የህይወት ግባችንን መለየት
አንችላለን፡፡ ቀጣዩ ስራ የሚሆነው የአጭር እና ረጅም ጊዜ
ዕቅድ ማውጣት ነው፡፡
ዝርዝር ዕቅድ ስናወጣ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን መሰረት
እንድናደርግ ይመከራል፡፡ አንድ በአንድ አጠር አድርጌ
እንደሚከተለው ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡
1. ለእኛ ትርጉም ያላቸው እና ፈታኝ ዕቅዶችን ማውጣት
የምንሰራው ስራ የምንወደው፣ ለእኛ ትርጉም ያለው፣
የልጅነት ህልማችን፣ ስሜት የሚሰጠን ወዘተ እንዲሆን
ይመከራል፡፡ የትኛው ያተርፋል? የትኛው ቀላል ነው?
ከማለት ይልቅ ምን ያስደስተኛል? ምን ውስጤን በሃሴት
ይሞላዋል? ምን እንድነቃቃ እና ድካምን እንድረሳ
ያደርገኛል? ብሎ ማሰብ ይበልጥ ጠቃሚ ነው፡፡ ሌላኛው
የምንነድፋቸው ግቦች ፈታኝ ግቦች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡
አቅማችንን አሟጠን እንድንጠቀም፣ ይበልጥ ተግተን
እንድንሰራ፣ የምንችለውን ድንጋይ በሙሉ እንድንፈነቅል
የሚያስገድዱንን ግቦችን መንደፍ ይመከራል፡፡ ፊት ለፊታችን
የምናስቀምጣቸው ግቦች በቀላሉ የምናሳካቸው፣ ከዚህ
በፊት ደግመን ደጋግመን የሰራናቸው ወዘተ ሲሆኑ የስራ
ተነሳሽነታችን ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ ፈተና ውስጣችን
የሚዘዋወረውን አድሬናሊን ሆርሞን መጠን ከፍ በማድረግ
ትኩረታችንን እንድንሰበስብ፣ እንድንተጋ፣ እንቅልፍን
እንድንረሳ፣ እንድንበረታ ወዘተ ይረዳናል፡፡ ስለዚህ የአጭርም
የረጅምም ጊዜ ዕቅድ ስናወጣ አንደኛው ማረጋገጥ ያለብን
ቁም ነገር ዕቅዳችን ከአቅማችን በታች እንዲሁም እጅግም
ከአቅማችን በላይም አለመሆኑን ነው፡፡ እንቁራሪት ዝሆንን
አክላለው ብላ ዓይነት መሆንም የለበትም፡፡
2. ግልጽ እና የማያሻማ ዕቅድ ማውጣት
በዚህ ጊዜ ውስጥ ይህንን ያህል ነገር አደርጋለሁ ማለት
ያስፈልጋል፡፡ የምንፈልገው ይህንን ነው ያንን ነው ብቻ ማለት
አሻሚ ነው፡፡ ግልጽ አይደለም፡፡ ምን? መቼ? ምን ያህል?
በምን ያህል ጊዜ ውስጥ? ወዘተ ዕቅዳችን ሊመልሳቸው
የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
3. ምክር መጠየቅ
ለመስራት በአሰብነው ስራ ዙሪያ ልምድም ዕውቀትም
ያላቸውን ቢያንስ ቢያንስ ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች ማማከር
ጥሩ ነው፡፡ አማካሪዎች ያላየነውን እንድናይ ይረዱናል፤
መቀነስ መጨመር ያለብን ነገር ካለ ጥቆማ ይሰጡናል፡፡
የግድ ወድቀን ወይም ተጋጭተን መማር የለብንም፡፡ ከገዛ
ራስ ተሞክሮ መማር አስፈላጊ የሆነውን ያህል ከሌሎችም
መማር እንዲሁ አስፈላጊ ነው፡፡
Join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ቢልም ቅሉ በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ግን በየጊዜው
አዲስ ነገር የመፍጠር ጉጉት ድምጽ ጎልቶ ይሰማል፡፡
ተዟዙረን ዓለምን ማየት፤ ያልሰራነውን መስራት፤ በጥቅሉ
ያለማቋረጥ መለወጥ እና ማደግ እንፈልጋለን፡፡
የማንፈልገው ፍላጎት አልባ መሆን ነው፡፡ የስነ-ልቡና
ሃኪሞችም ከሰማይ በታች ላለ ማንኛውም ነገር ፍላጎት
ማጣት የድብርት ህመም ግንባር ቀደም ምልክት ነውም
ይላሉ፡፡
ሁሉ በእጃቸው የሆነላቸው ሰዎች ላባቸው ጠብ እስኪል
ድረስ ይሰራሉ፡፡ ባለሃብቶች ማልደው ጠዋት
ከሰራተኞቻቸው ቀድመው ስራ ገበታቸው ላይ ይገኛሉ፡፡
በአንድ አጋጣሚ የተዋወኩት የአንድ ትልቅ ፋብሪካ ባለቤት
አንድም ቀን ሰራተኞቹ ቀድመውት ስራ ገበታቸው ላይ
እንደማይገኙ አጫውቶኛል፡፡ ከሳምንቱ ሰባት ቀናት ሌላ
ጉዳይ ከሌለው በስተቀር የፋብሪካው ዘበኞች ቢያንስ
አምስቱን ቀን ጠዋት ከሁሉም ሰራተኛ በፊት የአሰሪያቸውን
ፊት ነው የሚያዩት፡፡ ብዙ መጽሐፍትን ጽፈው ብዙ ትምህርት
የሰጡን እውቅ ሰዎች የዘመናቸው ጀምበር ጠልቃ
ህይወታቸው የሚያልፍበት አልጋ ላይ እንኳን ተኝተው ሁሉ
ይጽፋሉ፡፡ ከሃያ በላይ ዓለም አቀፍ ሬከርዶችን ሰባብሮ
ሚሊዮን ዶላሮችን ወደ ካዝናው ማስገባት የቻለው አትሌት
ኃይሌ ገ/ስላሴ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አንድ አንዴ ከህመም
ጋር ሁሉ እየታገለ ይሮጥ ነበር፡፡ በቅርቡ በሰጠው አንድ ቃለ
ምልልስ ላይም “ውድድር እንጂ ሩጫ አላቆምኩም”
ብሏል፡፡ አዲስ ነገርን ሁልጊዜም መፈለግ የሰው ልጅ
ተፈጥሮአዊ ባህሪ፣ ስነ-ልቡናችን የተገነባበት አሸዋና
ሲሚንቶ ነው፡፡ የበዛ የሰው ልጅ ስኬት ምስጢርም ይኸው
አዲስ ነገር ያለማቋረጥ መሻት ነው፡፡
መፈለግ ወደ መለወጥ የሚደረግ አንድ ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡
ቀጣዩ ምክንያታዊ እርምጃ ዕቅድ ማውጣት ነው፡፡ በህይወት
ጎዳና ላይ መነሳት መውደቃችን በአንድ ጎኑ የተደገፈው
አምድ ዕቅድ ነው፡፡ አቅደን ስንሰራ ይሳካልናል፤ ያለ ዕቅድ
ስንሰራ አንድም ስኬታችን የዘገየ ይሆናል፤ ሁለትም
ከነአካቴው የውሃ ሽታ ሆኖ ሊቀርም ይችላል፡፡ “አለማቀድ
ውድቀትን ማቀድ ነው” የሚባለው ከዚህ አኳያ ነው፡፡
ስቴቨን ኮቬይ በ “The 7 Habits of Highly Effective
People” ዝነኛ መጽሐፉ “Begin with the end in mind”
ይላል፡፡ የትኛውንም የህይወት ጉዞ ስትጀመሩ መድረሻችሁን
አውቃችሁ ጉዟችሁ ጀምሩ እንደ ማለት ነው፡፡ አለበለዚያ
ሁሉም መንገድ ደግም ክፉም ይሁን መንገዳችን ይሆናል፡፡
መርጠን ህይወታችን ካልመራን ባልመረጥነው እንመራለን፡፡
ስለዚህ ለውጥ ለማድረግ ስንነሳ አስቀድመን ምንድነው
የምፈልገው? የት ለመድረስ ነው የማስበው? ለሚሉ
ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ሊኖረን ይገባል፡፡
በተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች መንገድ ላይ ተሰነካክሎ
ወደ ኋላ መቅረት ቀላል ነው፡፡ የምንፈልገውን ካላወቅን
በሚፈልጉን ቁጥጥር ስር እንወድቃለን፡፡ ዝም ብሎ ቀን
ከሌት መስራት ብቻውን ውጤታማ አያደርግም፡፡
እዚህ ምድር ላይ ሁሉም ነገሮች ሁለት ጊዜ ነው
የሚፈጠሩት (All things are created twice) ይባላል::
የመጀመሪያው ፈጠራ አእምሯቸን ውስጥ የሚካሄደው ነው፤
አስበን፣ ተጨንቀን እና ተጠበን የምንወስነው ውሳኔ ሲሆን
ሲጀመር “በቃ እኔ ይኼንን ነው የምፈልገው” የምንለው ነው፤
መዝግበን የምናስቀምጠው ነው፡፡ ዕቅድን ማሰብ ብቻ
ሳይሆን ጽፎ ማስቀመጥም ቁልፍ ሚና ይጫወታል፤ “በቃል
ያለ ይረሳል በጽሑፍ ያለ ይወረሳል” እንዲሉ አበው፤
“ወረቀት ላይ አስቡ (Think on paper)” ይላል አንቶኒ
ሮቢንስም እንዲሁ፡፡
ሁለተኛው ፈጠራ በአእምሮአችን አውጥተን አውርደን
በወረቀት የመዘገብነውን የሚታይ ተጨባጭ እውነታ
ማድረግ ነው፡፡ መስራት፣ ማግኘት፣ መሆን የምንፈልገውን
መስራት፣ ማግኘት እንዲሁም መሆን ነው፡፡ የመጀመሪያው
ከሌለ ሁለተኛውም አይኖርም፡፡ ሳያስቡ እንደመናገር፣ ሳያጠኑ
ፈተና ላይ እንደመቀመጥ፣ የት መሄድ እንደሚፈልጉ ሳያውቁ
ጉዞ እንደመጀመር ነው፡፡
ሳይኮሎጂስቶች የምንፈልገውን ነገር ለማወቅ ይረዱናል
ብለው ያሰቧቸውን አንድ አንድ ስልቶች ቀይሰዋል፡፡ ከእነዚህ
ስልቶች ውስጥ አንዱ ለብቻችን ምንም ዓይነት ሃሳባችንን
የሚሰርቅ ነገር በሌለበት ስፍራ ቁጭ በማለት ከዚህ ዓለም
በሞት ከወዳጅ ዘመዶቻችን ስንለይ ለወዳጅ ዘመዶቻችን
እንዲነበብ የምንፈልገው የህይወት ታሪክ ምን ዓይነት ነው
ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ምን ሰርቶ አለፈ? ምን ዓይነት ሰው
ነበር? ምን ነበረው? ሰዎች ስለእሱ ምን ይላሉ? እነዚህ እና
መሰል ጥያቄዎችን ጸጥ ያለ ስፍራ ሆነን አእምሯችን ውስጥ
በማጉላላት አጠቃላይ የህይወት ግባችንን መለየት
አንችላለን፡፡ ቀጣዩ ስራ የሚሆነው የአጭር እና ረጅም ጊዜ
ዕቅድ ማውጣት ነው፡፡
ዝርዝር ዕቅድ ስናወጣ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን መሰረት
እንድናደርግ ይመከራል፡፡ አንድ በአንድ አጠር አድርጌ
እንደሚከተለው ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡
1. ለእኛ ትርጉም ያላቸው እና ፈታኝ ዕቅዶችን ማውጣት
የምንሰራው ስራ የምንወደው፣ ለእኛ ትርጉም ያለው፣
የልጅነት ህልማችን፣ ስሜት የሚሰጠን ወዘተ እንዲሆን
ይመከራል፡፡ የትኛው ያተርፋል? የትኛው ቀላል ነው?
ከማለት ይልቅ ምን ያስደስተኛል? ምን ውስጤን በሃሴት
ይሞላዋል? ምን እንድነቃቃ እና ድካምን እንድረሳ
ያደርገኛል? ብሎ ማሰብ ይበልጥ ጠቃሚ ነው፡፡ ሌላኛው
የምንነድፋቸው ግቦች ፈታኝ ግቦች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡
አቅማችንን አሟጠን እንድንጠቀም፣ ይበልጥ ተግተን
እንድንሰራ፣ የምንችለውን ድንጋይ በሙሉ እንድንፈነቅል
የሚያስገድዱንን ግቦችን መንደፍ ይመከራል፡፡ ፊት ለፊታችን
የምናስቀምጣቸው ግቦች በቀላሉ የምናሳካቸው፣ ከዚህ
በፊት ደግመን ደጋግመን የሰራናቸው ወዘተ ሲሆኑ የስራ
ተነሳሽነታችን ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ ፈተና ውስጣችን
የሚዘዋወረውን አድሬናሊን ሆርሞን መጠን ከፍ በማድረግ
ትኩረታችንን እንድንሰበስብ፣ እንድንተጋ፣ እንቅልፍን
እንድንረሳ፣ እንድንበረታ ወዘተ ይረዳናል፡፡ ስለዚህ የአጭርም
የረጅምም ጊዜ ዕቅድ ስናወጣ አንደኛው ማረጋገጥ ያለብን
ቁም ነገር ዕቅዳችን ከአቅማችን በታች እንዲሁም እጅግም
ከአቅማችን በላይም አለመሆኑን ነው፡፡ እንቁራሪት ዝሆንን
አክላለው ብላ ዓይነት መሆንም የለበትም፡፡
2. ግልጽ እና የማያሻማ ዕቅድ ማውጣት
በዚህ ጊዜ ውስጥ ይህንን ያህል ነገር አደርጋለሁ ማለት
ያስፈልጋል፡፡ የምንፈልገው ይህንን ነው ያንን ነው ብቻ ማለት
አሻሚ ነው፡፡ ግልጽ አይደለም፡፡ ምን? መቼ? ምን ያህል?
በምን ያህል ጊዜ ውስጥ? ወዘተ ዕቅዳችን ሊመልሳቸው
የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
3. ምክር መጠየቅ
ለመስራት በአሰብነው ስራ ዙሪያ ልምድም ዕውቀትም
ያላቸውን ቢያንስ ቢያንስ ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች ማማከር
ጥሩ ነው፡፡ አማካሪዎች ያላየነውን እንድናይ ይረዱናል፤
መቀነስ መጨመር ያለብን ነገር ካለ ጥቆማ ይሰጡናል፡፡
የግድ ወድቀን ወይም ተጋጭተን መማር የለብንም፡፡ ከገዛ
ራስ ተሞክሮ መማር አስፈላጊ የሆነውን ያህል ከሌሎችም
መማር እንዲሁ አስፈላጊ ነው፡፡
Join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች አሉት👌👇 ተፈጥሮ በኡደት (Process) የተመላች ናት፡፡ ዘመናትን በጊዜ
ቀመር አስልታ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላኛው ታሻግራለች፡፡
የኡደት ስሌትዋ ከትልቅ ወደ ትንሽ ሳይሆን ከትናንሽ ወደ
ትላልቅ የሚያመራ ነው፡፡
የሰው ልጅ የዕድገት ለውጥ ዓላማ በተፈጥሮ የወረሰውን
እምቅ ኃይል ከከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው፡፡ ኤልሳቤጥ
ሃርሎክ የተባለች የሳይኮሎጂ ምሁር እንደገለጸችው ሰዎች
በአእምሮ ፤ በአካል ከሌሎች የተሻሉ ሆነው ለመገኘት
የሚያደርጉት ጥረት ወደ ዕድገት ለውጥ ግብ ለመድረስ
የሚደርጉት ጥረት ስለሆነ እነዚህን ጥረቶቻቸውን እውን
ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሉ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ሰዎች እራሳቸውን ለማሻሻል እምቅ
አቅምና ችሎታ ካላቸው ከወዴት ነው የሚጀሚሩት የሚለው
ነው፡፡ ብዙዎቻችን በስራችንና በህይወታችን የምንፈልገውንና
የምንሻውን ያህል ውጤታማ መሆን ያልቻልነው
ዕቅዶቻችንንና ስኬቶቻችንን ከታች ከትንንሽ ነገሮች
ስለማንጀምራቸው ነው፡፡ ቀድሞ የሚታየን ትልቁ ስዕል እንጂ
ወደ ትልቁ የስኬት ጎዳና ለመድረስ ከትንሽ ነገር መጀመር
እንዳለብን አንገነዘብም፡፡ ከዚህ በታች ከትንንሽ ነገር
ተነስተን ወደ ትልቁ ስኬት ለመጓዝ የሚረዱንን ነጥቦች
እንመለከታለን፡፡
1.ትምህርት
የተሻለ የትምህርት ደረጃ ያለቻው ሰዎች ስራዎቻቸውን
የሚያከናውኑት ዕውቀትንና ዕቅድን መሰረት አድርገው ነው፡፡
በስራዎቻቸው ላይ ወሳኝ ጉዳዮችን በደንብ ስለሚያውቁ
ከሌላው ሰው በተሻለ ሃሳብና መረጃ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ
ዕውቀቶቻቸውን በመመንዘርና ማኅበራሰባቸውን በማገልገል
የተሻለና የተሳካ ህይወት (ገቢንም ጨምሮ) መኖር ይችላሉ፡፡
ዕውቀት በጨመረ ቁጥር የሰው አስተሳሰብ አድማሱ
ስለሚሰፋ ምን ሰርቶ ምን ማግኘትና የት እንደሚደርስ
አቅጣጫን ይጠቁማል፡፡ ትምህርት ስንል በአንድ የትምህርት
መስክ የምናገኛውን የሰርተፍኬት ብዛት ብቻ ሳይሆን
በህይወት ልምድና ተሞክሮ ያገኘነውን ዕውቀት ትርጉም
ባለው ስራ ላይ ማዋልና በትንሽ በትንሹ በመደበኛም ይሁን
ኢ-መደበኛ ትምህርት ታግዘን ህይወትን ለማሸነፍ
የምንሄድበትን የህይወት ጉዞን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡
2. ክህሎት
በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን ክህሎት የምናስመዘግበውን
ውጤት ብዛትና ጥራት ይወስናል፡፡ የምንሰራውን ስራ በደንብ
ካወቅነው በስራችን ቅልጥፍና ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ
በብቃት መሸጋገር እንችላለን፡፡ ከማናውቀው ነገር አንድ
ብለን ከመጀመር የምናውቀውን ነገር አሻሽሎ በመስራትና
ክህሎትን በማዳበር የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡
3. ግንኑነትን ማስፋት
በምንሰራው ስራ ላይ ብዙ ሰዎችን ለማወቅ ከጣርን
ግንኙነታችንን በማጠናከር አማራጮችን ማስፋት እንችላለን፡፡
ስለዚህ የግንኙነት አድማስን ለማስፋት ዘውትር ማኅበራዊ
ገመዶቻችንን በረጅሙ መዘርጋት አለብን፡፡
4. ጥሩ የስራ ልምድ
ጥሩ የስራ ልምድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስራዎችን
እንድንሰራ ይረዳናል፡፡ ይህን ለማድረግ ስራዎቻችንን በዕቅድ
መስራት አለብን፡፡ ጥሩ የስራ ልምድ አንድን ነገር
ከማከናወናችን በፊት አስቀድመን እንድናስብበት
ስለሚያስችለን ከስራው በኋላ የሚከሰቱትን ማንኛውንም
አወንታዊና አሉታዊ ውጤቶችን አስቀድሞ መገመት
ስለሚያስችል ኪሳራን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
6. አወንታዊ አመለካከት
የምንሰራው ስራ እኛነታችንን ስለሚገልጸው በስራችን ላይ
አወንታዊ አመለካከት ፤ በእራስ መተማመን ፡ ከስራ
ባልደረቦቻችን ጋር ጥሩ መስተጋብር ካለን ሁሌም መልካም
ነገር እንድናስብ ስለሚረዳን ወደ ምንፈልግበት ደረጃ
እንድንደርስ አወንታዊ አመለካከት የበኩሉን አስተዋጽኦ
ያበረክታል፡፡
7. ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ይኑረን
ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ወይም ምልከታ መያዝ
የምንፈልገውንና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረን ይረዳናል፡፡
ሰዎች በውጫዊ ገጽታችን ሊገምቱንና ሊፈርጁን ይችሉ
ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውጫዊ ምልከታ የእኛንም ሆነ የሌላውን
ስለማይገልጽ ስለእራሳችንም ሆነ ስለሌሎች ሰዎች ጥሩና
የተቃና አመለካከት ሊኖረን ይገባል፡፡
8. ፈጠራ
ፈጠራ አንድን ነገር ዘውትር በተሻለ ፍጥነት፤ ቅልጥፍና ፤
በቀላል አኳሃን እንድንተገብረው ይረዳናል፡፡ ፈጠራ አዲስ
ነገር ፈጥሮ ወይም ሰርቶ ማሳየት ብቻ ሳይሆን ነገሮችን
ከዚህ ቀደም ከምናያቸው ዕይታና ግንዛቤ በአዲስ መልኩና
በሌላ አቅጣጫ ማየትንም የሚያካትት ነው፡፡
9. ማንነት
እራስን መግራትና ግልጽነት ብዙ የስኬት በሮችን
እንድንከፍት ይረዳናል፡፡ መተማመን የግንኙነት ሁሉ መሰረት
ነው፡፡ ሰዎች የሚያውቁን በድርጊታችንና በቃላችን
የምንታመን ከሆነ ነገሮችን በፍጥነት በቀላልና በታማኝነት
በእኛ በኩል እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡ ይህም ብርታትና በራስ
መተማመንን ስለሚፈጥርልን ወደምንፈልገው ደረጃ
ለመድረስ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡
ዕቅድህ 15ኪሎ ክብደት መቀነስ ከሆነ በቀላሉ እንቅስቃሴ
ማድረግና አመጋገብህን በማስተካከል ከትንሹ መጀመር
ትችላለህ፡፡ ከዚያ ወደ ምትፈልገው ደረጃ ስትደርስ
እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች እንዳሉት
ትገነዘባለህ፡፡ ጀማል
መልካም ምሽት
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ቀመር አስልታ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላኛው ታሻግራለች፡፡
የኡደት ስሌትዋ ከትልቅ ወደ ትንሽ ሳይሆን ከትናንሽ ወደ
ትላልቅ የሚያመራ ነው፡፡
የሰው ልጅ የዕድገት ለውጥ ዓላማ በተፈጥሮ የወረሰውን
እምቅ ኃይል ከከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው፡፡ ኤልሳቤጥ
ሃርሎክ የተባለች የሳይኮሎጂ ምሁር እንደገለጸችው ሰዎች
በአእምሮ ፤ በአካል ከሌሎች የተሻሉ ሆነው ለመገኘት
የሚያደርጉት ጥረት ወደ ዕድገት ለውጥ ግብ ለመድረስ
የሚደርጉት ጥረት ስለሆነ እነዚህን ጥረቶቻቸውን እውን
ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሉ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ሰዎች እራሳቸውን ለማሻሻል እምቅ
አቅምና ችሎታ ካላቸው ከወዴት ነው የሚጀሚሩት የሚለው
ነው፡፡ ብዙዎቻችን በስራችንና በህይወታችን የምንፈልገውንና
የምንሻውን ያህል ውጤታማ መሆን ያልቻልነው
ዕቅዶቻችንንና ስኬቶቻችንን ከታች ከትንንሽ ነገሮች
ስለማንጀምራቸው ነው፡፡ ቀድሞ የሚታየን ትልቁ ስዕል እንጂ
ወደ ትልቁ የስኬት ጎዳና ለመድረስ ከትንሽ ነገር መጀመር
እንዳለብን አንገነዘብም፡፡ ከዚህ በታች ከትንንሽ ነገር
ተነስተን ወደ ትልቁ ስኬት ለመጓዝ የሚረዱንን ነጥቦች
እንመለከታለን፡፡
1.ትምህርት
የተሻለ የትምህርት ደረጃ ያለቻው ሰዎች ስራዎቻቸውን
የሚያከናውኑት ዕውቀትንና ዕቅድን መሰረት አድርገው ነው፡፡
በስራዎቻቸው ላይ ወሳኝ ጉዳዮችን በደንብ ስለሚያውቁ
ከሌላው ሰው በተሻለ ሃሳብና መረጃ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ
ዕውቀቶቻቸውን በመመንዘርና ማኅበራሰባቸውን በማገልገል
የተሻለና የተሳካ ህይወት (ገቢንም ጨምሮ) መኖር ይችላሉ፡፡
ዕውቀት በጨመረ ቁጥር የሰው አስተሳሰብ አድማሱ
ስለሚሰፋ ምን ሰርቶ ምን ማግኘትና የት እንደሚደርስ
አቅጣጫን ይጠቁማል፡፡ ትምህርት ስንል በአንድ የትምህርት
መስክ የምናገኛውን የሰርተፍኬት ብዛት ብቻ ሳይሆን
በህይወት ልምድና ተሞክሮ ያገኘነውን ዕውቀት ትርጉም
ባለው ስራ ላይ ማዋልና በትንሽ በትንሹ በመደበኛም ይሁን
ኢ-መደበኛ ትምህርት ታግዘን ህይወትን ለማሸነፍ
የምንሄድበትን የህይወት ጉዞን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡
2. ክህሎት
በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን ክህሎት የምናስመዘግበውን
ውጤት ብዛትና ጥራት ይወስናል፡፡ የምንሰራውን ስራ በደንብ
ካወቅነው በስራችን ቅልጥፍና ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ
በብቃት መሸጋገር እንችላለን፡፡ ከማናውቀው ነገር አንድ
ብለን ከመጀመር የምናውቀውን ነገር አሻሽሎ በመስራትና
ክህሎትን በማዳበር የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡
3. ግንኑነትን ማስፋት
በምንሰራው ስራ ላይ ብዙ ሰዎችን ለማወቅ ከጣርን
ግንኙነታችንን በማጠናከር አማራጮችን ማስፋት እንችላለን፡፡
ስለዚህ የግንኙነት አድማስን ለማስፋት ዘውትር ማኅበራዊ
ገመዶቻችንን በረጅሙ መዘርጋት አለብን፡፡
4. ጥሩ የስራ ልምድ
ጥሩ የስራ ልምድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስራዎችን
እንድንሰራ ይረዳናል፡፡ ይህን ለማድረግ ስራዎቻችንን በዕቅድ
መስራት አለብን፡፡ ጥሩ የስራ ልምድ አንድን ነገር
ከማከናወናችን በፊት አስቀድመን እንድናስብበት
ስለሚያስችለን ከስራው በኋላ የሚከሰቱትን ማንኛውንም
አወንታዊና አሉታዊ ውጤቶችን አስቀድሞ መገመት
ስለሚያስችል ኪሳራን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
6. አወንታዊ አመለካከት
የምንሰራው ስራ እኛነታችንን ስለሚገልጸው በስራችን ላይ
አወንታዊ አመለካከት ፤ በእራስ መተማመን ፡ ከስራ
ባልደረቦቻችን ጋር ጥሩ መስተጋብር ካለን ሁሌም መልካም
ነገር እንድናስብ ስለሚረዳን ወደ ምንፈልግበት ደረጃ
እንድንደርስ አወንታዊ አመለካከት የበኩሉን አስተዋጽኦ
ያበረክታል፡፡
7. ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ይኑረን
ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ወይም ምልከታ መያዝ
የምንፈልገውንና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረን ይረዳናል፡፡
ሰዎች በውጫዊ ገጽታችን ሊገምቱንና ሊፈርጁን ይችሉ
ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውጫዊ ምልከታ የእኛንም ሆነ የሌላውን
ስለማይገልጽ ስለእራሳችንም ሆነ ስለሌሎች ሰዎች ጥሩና
የተቃና አመለካከት ሊኖረን ይገባል፡፡
8. ፈጠራ
ፈጠራ አንድን ነገር ዘውትር በተሻለ ፍጥነት፤ ቅልጥፍና ፤
በቀላል አኳሃን እንድንተገብረው ይረዳናል፡፡ ፈጠራ አዲስ
ነገር ፈጥሮ ወይም ሰርቶ ማሳየት ብቻ ሳይሆን ነገሮችን
ከዚህ ቀደም ከምናያቸው ዕይታና ግንዛቤ በአዲስ መልኩና
በሌላ አቅጣጫ ማየትንም የሚያካትት ነው፡፡
9. ማንነት
እራስን መግራትና ግልጽነት ብዙ የስኬት በሮችን
እንድንከፍት ይረዳናል፡፡ መተማመን የግንኙነት ሁሉ መሰረት
ነው፡፡ ሰዎች የሚያውቁን በድርጊታችንና በቃላችን
የምንታመን ከሆነ ነገሮችን በፍጥነት በቀላልና በታማኝነት
በእኛ በኩል እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡ ይህም ብርታትና በራስ
መተማመንን ስለሚፈጥርልን ወደምንፈልገው ደረጃ
ለመድረስ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡
ዕቅድህ 15ኪሎ ክብደት መቀነስ ከሆነ በቀላሉ እንቅስቃሴ
ማድረግና አመጋገብህን በማስተካከል ከትንሹ መጀመር
ትችላለህ፡፡ ከዚያ ወደ ምትፈልገው ደረጃ ስትደርስ
እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች እንዳሉት
ትገነዘባለህ፡፡ ጀማል
መልካም ምሽት
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
መጋፈጥ ወይስ መሸሽ የግል፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና የመሳሰሉት ችግር
በሚያጋጥሙ ጊዜ፤ በተለያየ መንገድ ለችግሩ ምላሽ
እንሰጣልን፡፡ ስለተፈጠረው ችግር ማሰብ ከሚያስከትልብን
መጥፎ ስሜት ለመገላገል ስንል መፍትሄ ከማፈላለግ ይልቅ
ሽሽትን የምንመርጥ ልንኖር እንችላለን፡፡ መፍትሄ ሳናገኝ ሆነ
ብለን ወደ ጎን የምንተው ከሆነ፤ ከጊዜያዊ መጥፎ ስሜት
እራሳቸንን እየተከላከልን እንጅ ችግሩን እያባባስነው እንደሆነ
መገንዘብ ይገባል፡፡ ለምሳሌ አንድ ግለሰብ ጥንቃቄ
የጎደለው የግብረ-ስጋ ግንኙነት ፈጸመ እንበል፡፡ የደም
ምርመራ አድርጎ እውነታውን ከማወቅ ይልቅ፤ ያልፈለገው
ነገር ቢከሰት ሊያስከትልበት ከሚችለው የስነ-ልቡና ጫናና
እውነታ ለመሸሽ ሲል እድሜውን በሙሉ እነደተጨነቀ
ይኖራል፡፡ ስለዚህ ችግሮች በሚያጋጥሙ ጊዜ ከመሸሽ
ይልቅ በዘዴ መጋፈጥ ለዘለቄታዊ መፍትሄ ከሽሽት የተሻለ
መፍትሄ ነው፡፡
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
በሚያጋጥሙ ጊዜ፤ በተለያየ መንገድ ለችግሩ ምላሽ
እንሰጣልን፡፡ ስለተፈጠረው ችግር ማሰብ ከሚያስከትልብን
መጥፎ ስሜት ለመገላገል ስንል መፍትሄ ከማፈላለግ ይልቅ
ሽሽትን የምንመርጥ ልንኖር እንችላለን፡፡ መፍትሄ ሳናገኝ ሆነ
ብለን ወደ ጎን የምንተው ከሆነ፤ ከጊዜያዊ መጥፎ ስሜት
እራሳቸንን እየተከላከልን እንጅ ችግሩን እያባባስነው እንደሆነ
መገንዘብ ይገባል፡፡ ለምሳሌ አንድ ግለሰብ ጥንቃቄ
የጎደለው የግብረ-ስጋ ግንኙነት ፈጸመ እንበል፡፡ የደም
ምርመራ አድርጎ እውነታውን ከማወቅ ይልቅ፤ ያልፈለገው
ነገር ቢከሰት ሊያስከትልበት ከሚችለው የስነ-ልቡና ጫናና
እውነታ ለመሸሽ ሲል እድሜውን በሙሉ እነደተጨነቀ
ይኖራል፡፡ ስለዚህ ችግሮች በሚያጋጥሙ ጊዜ ከመሸሽ
ይልቅ በዘዴ መጋፈጥ ለዘለቄታዊ መፍትሄ ከሽሽት የተሻለ
መፍትሄ ነው፡፡
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
መቼ ላግባ❓❓ በተገቢው ዕድሜ ተገቢ እርምጃ መውሰድ
‹‹ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው››
በሰው ልጅ ዕድገት ውስጥ የህጻንነት፣ ልጅነት፣ ወጣትነት፣
ጎልማሳነትና የእርጅና ደረጃዎች አሉ፡፡ በእያንዳንዱ የዕድገት
ደረጃዎች ውስጥ መደረግ የሚገባቸው (አንድ ሰው
ሊያከናውናቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ)፡፡ እነዚህን ለዕድሜ
የሚመጥኑ ተግባራትን በተገቢው ዕድሜ አለማከናወን
በቀጣዮቹ ደረጃዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡
በልጅነት ጊዜ በአብዛኛው ራሳችንን ስለማንችል በብዙ ነገር
በወላጆቻችን ላይ ጥገኞች ሆነን እንኖራለን፡፡ ሆኖም በልጅነት
ጊዜ ለወጣትነት ጊዜ መልካም መሠረት የሚጥሉ
ሥራዎችን እንሠራለን (ለምሳሌ ትምህርት መማር፣ የተለያዩ
ክህሎትን ማጎልበት፣ …)፡፡ በወጣትነትና በጎልማሳነት
ጊዜም እንዲሁ የምንሰራቸው ስራዎች ይኖራሉ፡፡
ከወላጆቻችን ጋር በጥገኝነት የምንኖረው ለተወሰነ ጊዜ
ነው፡፡ እያደግን ስንሄድ፣ እነርሱን ትተን በራሳችን መኖር
መጀመር አለብን፡፡
ግን በስንት ዓመታችን?
ለሁሉም ነገር ጊዜ ስላለው፣ ነገሮች በተገቢ ጊዜያቸው
ሲከናወኑ ውበት ይኖራቸዋል፡፡ በሰው ልጅ ውስጥ ጊዜን
የማወቅ እምቅ ጥበብ አለ፡፡ በውስጣችን የተቀመጡ
ሆርሞኖችም ጊዜያቸውን ጠብቀው ስራቸውን ሲሰሩ የተለያዩ
እርምጃዎችን እንድንወስድ ያነሳሱናል፡፡ ተፈጥሮ ራሷ ሰዓት
አላት እንደ ማለት ነው፡፡
ሰውነታችንና አእምሮአችን ‹‹ለጋብቻ ደርሰሃል/ ደርሰሻል››
ብለው ሲደውሉ ማዳመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህን
ማዳመጥ ካልቻልን ደግሞ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ‹‹እንዴት
ነው አልደረሰም›› የሚል ሃሳብ ሲያቀርቡ ከመደንገጥ
ወይም ችላ ከማለት ቆም ብሎ በማሰላሰል አዎንታዊ
እርምጃ መውሰድ መልካም ነው!
ከጋብቻ በፊት ከሚጠየቁ መሠረታዊና አስፈላጊ ጥያቄዎች
መካከል አንዱ ‹‹መቼ ላግባ?” የሚለው ነው፡፡ ስለጋብቻ
ለሚያስቡ ወጣቶች ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን መልስ መስጠት
ቀላል እንዳልሆነ ይታሰባል፡፡
በአንዳንድ ባህሎች ውስጥ ወጣቶች መቼ ማግባት
እንዳለባቸው ከመጠየቃቸው በፊት ወላጆች
ይወስኑላቸዋል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ጋብቻ የሚወሰንላቸው
ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ የጉርምስና
ዕድሜያቸውን እንደ ጀመሩ ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው
በሁለንተናዊ ህይወታቸው ሙሉ ሰው ከመሆናቸው በፊት
ወደ ጋብቻ እንዲገቡ ማድረጋቸው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት
ነው፡፡ የልጅነት ወቅት የሚባለው በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ
እስከ 18 ዓመት ያለው ዕድሜ ነው፡፡
በልጅነት የሚደረግ ጋብቻ በልጆቹ ህይወት በተለይ በሴት
ልጆች ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳትን ያመጣል፡፡ ከዚህም
በላይ ለማኅብረተሰብም በርካታ ማኅበራዊ ቀውሶችን
ያስከትላል፡፡
እንግዲህ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የተለያዩ
መስፈርቶችን ማንሳት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ እነዚህን እንደ
መስፈርት ሆነው ሊያገለግሉ የሚችሉ ጥቂት ነጥቦችን
ከዚህ በታች ለመግለጽ እንሞክራለን፡፡
ለአካለ መጠን መድረስ
የዕድሜ መጨመር በሰውነት ላይ የሚያመጣቸው ለውጦች
አሉ፡፡ ዕድገት ከእናት ማህጸን ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ በተለይ
የአካል ዕድገት በልጅነት ወቅት ከነበረው ሁኔታ በወጣትነት
ወቅት የተለየ ገጽታ ይኖራል፡፡ የአካል ዕድገት በወጣትነት
ጊዜ ወደ ሙላት ይደርሳል፡፡ ከዚህ ዕድገት ጋር ተያይዞ
የተቃራኒ ጾታ ፍላጎትም ይጀምራል፡፡ ወንድና ሴት ለፍቅር
ግንኙነት ይፈላለጋሉ፡፡ ይህ ማለት በተፈጥሮ በሰውነታቸው
ውስጥ የተቀመጠው እምቅ የተቃራኒ ጾታ ፍላጎት ጊዜውን
ጠብቆ ብቅ ይላል ማለት ነው፡፡ ፍላጎቱ በራሱ ጤናማ
ነው፡፡
የፍቅር ፍላጎት መምጣትና የአካል ዕድገት መኖር ግን
ለብቻው ለጋብቻ ዝግጁ መሆንን አያመለክትም፡፡ ቢያንስ
ዕድሜያቸው 18ና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡ በመሠረተ
ሃሳብ ከዚህ ዕድሜ በፊት የሚመሠረት ጋብቻ በህግ ፊት
ተቀባይነት የለውም፡፡
የኢኮኖሚ አቅም መኖር
ጋብቻ በአካል ብቻ ሳይሆን በአእምሮ፣ በማኅበራዊ፣
በኢኮኖሚና በሌሎችም የህይወት ዘርፎች የበሰሉና ኃላፊነት
የሚወስዱ ወንድና ሴት የሚጣመሩበት ኅብረት ነው፡፡ በዚህ
ዕድሜ አካባቢ ታዳጊ ወጣቶች በአካላቸው ወሲብን
ለመፈጸም ደርሰዋል እንጂ በሌሎች የህይወት ገጽታዎች
ገና መብሰል ይቀራቸዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱን
የኢኮኖሚ ብስለትን እንውሰድ፡፡ 18 ዓመት ዕድሜ አካባቢ
ታዳጊ ወጣቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ
ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በኢኮኖሚ በወላጆቻቸው ላይ ጥገኞች
ናቸው፡፡ ከዚያም ኮሌጅ ገብተው ለመማር ከ3-7 ዓመት
ሊፈጅባቸው ይችላል፡፡ የኮሌጅ ትምህርት ካገኙና ሥራ ከያዙ
የራሳቸውን የገቢ ምንጭ ያገኛሉ፡፡ አንድ ወንድና አንዲት
ሴት ሁለቱም የገቢ ምንጭ ካላቸው ወይም የአንዱ የገቢ
ምንጭ ሁለቱን ማኖር የሚያስችል ከሆነ ማግባት ይችላሉ፡፡
በኢኮኖሚ ራስን መቻል የሚለው ሐሳብ አንጻራዊ ነው፡፡
በጋብቻ ሊጣመሩ ያሰቡ ወንድና ሴት ለመሠረታዊ
ፍላጎቶቻቸው የሚሆኑ ነገሮችን ማግኘት የሚያስችል ሁኔታ
ላይ መሆን ለጋብቻ ጅማሬ በቂ ነው፡፡ ጋብቻ ሃብታም
በመሆን የሚጀመር ሳይሆን በዝቅተኛ ገቢ ላይ ተጀምሮ
ሃብቱ ቀስ በቀስ በሁለቱ ጥረት ይመጣል፡፡
የአእምሮ ብስለትና ማኅ በራዊ ግንኙነት ክህሎት
ለጋብቻ ግንኙነት ዘላቂነት አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ነገሮች
መካከል አንዱ የጥንዶቹ (ወንድና ሴት) የአእምሮ ብስለትና
የማኅበራዊ ግንኙነት ክህሎት መኖር ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ
ብስለት ደግሞ ዕድሜ በመቁጠር ብቻ ላይመጣ ይችላል፡፡
ሆኖም ዕድሜ ራሱ ትምህርት ቤት በመሆኑ (የተለያዩ
ነገሮችን ከውጣ ውረድ ለመቅሰም ዕድል ስለሚሰጥ)
የዕድሜ መጨመር የአእምሮ ብስለትና የማኅበራዊ ግንኙነት
ክህሎትን ለማዳበር መልካም አጋጣሚዎች ይኖራሉ፡፡
በለጋ ዕድሜ ከማግባት በሃያዎቹ አጋማሽ አካባቢ ማግባት፣
የጋብቻ ግንኙነትን ለማጣጣምና ግንኙነቱን ዘላቂ ለማድረግ
አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ብቁ ያደርጋል፡፡
ልጅ ለመውለድና ለማሳደግ
ከአካል ዕድገት አንጻር ወንድና ሴት ከጉርምስና ዕድሜ
ጀምረው ልጅ መውለድ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከአካል ዝግጅት፣
ከጤንነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሌሎች ምክንያቶች
አንጻር በተለይ ለሴቶች ጥሩ ልጅ የመውለጃ ዕድሜ ከ18
እስከ 35 ዓመት መሃል ያለው ጊዜ ነው፡፡
እንግዲህ ከላይ በተጠቀሱ ነጥቦች ስር ወጣት ወንዶችና
ሴቶች በአብዛኛው እስከ 20ዎቹ አጋማሽ አካባቢ
በትምህርት ላይ ይሆናሉ፡፡ ራሳቸውን ችለው ቤተሰብ
ለመመስረት ሁለንተናዊ ብቃት የሚኖራቸው በዚህ ወቅት
ነው፡፡
ልጅ ከመውለድ አንጻር ከዝቅተኛ ተገቢ ዕድሜ 18 መጀመር
ቢመረጥም የሁኔታዎች አለመመቻቸት ስለሚኖር በዚህ ጊዜ
ማድረጉ ብዙ ተግዳሮቶች አሉት፡፡ ራስን የመቻል አቅም
ከመጣ በኋላ ግን ወደ ከፍተኛ ጫፍ (35) ከፍ ማድረጉ
አይመረጥም፡፡
ልጅ መውለድ ብቻ ሳይሆን የማሳደግም ኃላፊነት ስለሚኖር
ተጋቢዎቹ በለጋ የጎልማሳነት ዕድሜያቸው ልጆቹን ለማሳደግ
የአካል፣ ስሜትና ስነልቦናዊ ዝግጁነት ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ
አግብቶ ልጅ መውለድ ለሚፈልጉ ይህን ነጥብ ከግንዛቤ
ውስጥ ማስገባት ጠቃሚ ነው፡፡
በተገቢ ዕድሜ የማግባት ጥቅሞች
በሃያዎቹ አጋማሽ አካባቢ የሚያገቡ ወንዶችና ሴቶች
በጋብቻ ህይወታቸው ከሌሎቹ ይልቅ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡
በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገቡ ወንዶች ካላገቡ
ወንዶች ይልቅ ሃብት የማፍራት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
ያገቡ ወንዶች ገቢና ሃብት እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ለጤንነት አስጊ ለሆኑ ነገሮች የመጋለጥ ዕድል
ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ በወጣትነታቸው ወቅት ያገቡ
ወንዶችና ሴቶች ጤንነታቸውን ጠብቀው የመኖር
መልካም አጋጣሚዎችን ያገኛሉ፡፡
በወጣትነት (20ዎቹ አጋማሽ አካባቢ
‹‹ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው››
በሰው ልጅ ዕድገት ውስጥ የህጻንነት፣ ልጅነት፣ ወጣትነት፣
ጎልማሳነትና የእርጅና ደረጃዎች አሉ፡፡ በእያንዳንዱ የዕድገት
ደረጃዎች ውስጥ መደረግ የሚገባቸው (አንድ ሰው
ሊያከናውናቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ)፡፡ እነዚህን ለዕድሜ
የሚመጥኑ ተግባራትን በተገቢው ዕድሜ አለማከናወን
በቀጣዮቹ ደረጃዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡
በልጅነት ጊዜ በአብዛኛው ራሳችንን ስለማንችል በብዙ ነገር
በወላጆቻችን ላይ ጥገኞች ሆነን እንኖራለን፡፡ ሆኖም በልጅነት
ጊዜ ለወጣትነት ጊዜ መልካም መሠረት የሚጥሉ
ሥራዎችን እንሠራለን (ለምሳሌ ትምህርት መማር፣ የተለያዩ
ክህሎትን ማጎልበት፣ …)፡፡ በወጣትነትና በጎልማሳነት
ጊዜም እንዲሁ የምንሰራቸው ስራዎች ይኖራሉ፡፡
ከወላጆቻችን ጋር በጥገኝነት የምንኖረው ለተወሰነ ጊዜ
ነው፡፡ እያደግን ስንሄድ፣ እነርሱን ትተን በራሳችን መኖር
መጀመር አለብን፡፡
ግን በስንት ዓመታችን?
ለሁሉም ነገር ጊዜ ስላለው፣ ነገሮች በተገቢ ጊዜያቸው
ሲከናወኑ ውበት ይኖራቸዋል፡፡ በሰው ልጅ ውስጥ ጊዜን
የማወቅ እምቅ ጥበብ አለ፡፡ በውስጣችን የተቀመጡ
ሆርሞኖችም ጊዜያቸውን ጠብቀው ስራቸውን ሲሰሩ የተለያዩ
እርምጃዎችን እንድንወስድ ያነሳሱናል፡፡ ተፈጥሮ ራሷ ሰዓት
አላት እንደ ማለት ነው፡፡
ሰውነታችንና አእምሮአችን ‹‹ለጋብቻ ደርሰሃል/ ደርሰሻል››
ብለው ሲደውሉ ማዳመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህን
ማዳመጥ ካልቻልን ደግሞ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ‹‹እንዴት
ነው አልደረሰም›› የሚል ሃሳብ ሲያቀርቡ ከመደንገጥ
ወይም ችላ ከማለት ቆም ብሎ በማሰላሰል አዎንታዊ
እርምጃ መውሰድ መልካም ነው!
ከጋብቻ በፊት ከሚጠየቁ መሠረታዊና አስፈላጊ ጥያቄዎች
መካከል አንዱ ‹‹መቼ ላግባ?” የሚለው ነው፡፡ ስለጋብቻ
ለሚያስቡ ወጣቶች ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን መልስ መስጠት
ቀላል እንዳልሆነ ይታሰባል፡፡
በአንዳንድ ባህሎች ውስጥ ወጣቶች መቼ ማግባት
እንዳለባቸው ከመጠየቃቸው በፊት ወላጆች
ይወስኑላቸዋል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ጋብቻ የሚወሰንላቸው
ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ የጉርምስና
ዕድሜያቸውን እንደ ጀመሩ ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው
በሁለንተናዊ ህይወታቸው ሙሉ ሰው ከመሆናቸው በፊት
ወደ ጋብቻ እንዲገቡ ማድረጋቸው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት
ነው፡፡ የልጅነት ወቅት የሚባለው በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ
እስከ 18 ዓመት ያለው ዕድሜ ነው፡፡
በልጅነት የሚደረግ ጋብቻ በልጆቹ ህይወት በተለይ በሴት
ልጆች ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳትን ያመጣል፡፡ ከዚህም
በላይ ለማኅብረተሰብም በርካታ ማኅበራዊ ቀውሶችን
ያስከትላል፡፡
እንግዲህ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የተለያዩ
መስፈርቶችን ማንሳት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ እነዚህን እንደ
መስፈርት ሆነው ሊያገለግሉ የሚችሉ ጥቂት ነጥቦችን
ከዚህ በታች ለመግለጽ እንሞክራለን፡፡
ለአካለ መጠን መድረስ
የዕድሜ መጨመር በሰውነት ላይ የሚያመጣቸው ለውጦች
አሉ፡፡ ዕድገት ከእናት ማህጸን ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ በተለይ
የአካል ዕድገት በልጅነት ወቅት ከነበረው ሁኔታ በወጣትነት
ወቅት የተለየ ገጽታ ይኖራል፡፡ የአካል ዕድገት በወጣትነት
ጊዜ ወደ ሙላት ይደርሳል፡፡ ከዚህ ዕድገት ጋር ተያይዞ
የተቃራኒ ጾታ ፍላጎትም ይጀምራል፡፡ ወንድና ሴት ለፍቅር
ግንኙነት ይፈላለጋሉ፡፡ ይህ ማለት በተፈጥሮ በሰውነታቸው
ውስጥ የተቀመጠው እምቅ የተቃራኒ ጾታ ፍላጎት ጊዜውን
ጠብቆ ብቅ ይላል ማለት ነው፡፡ ፍላጎቱ በራሱ ጤናማ
ነው፡፡
የፍቅር ፍላጎት መምጣትና የአካል ዕድገት መኖር ግን
ለብቻው ለጋብቻ ዝግጁ መሆንን አያመለክትም፡፡ ቢያንስ
ዕድሜያቸው 18ና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡ በመሠረተ
ሃሳብ ከዚህ ዕድሜ በፊት የሚመሠረት ጋብቻ በህግ ፊት
ተቀባይነት የለውም፡፡
የኢኮኖሚ አቅም መኖር
ጋብቻ በአካል ብቻ ሳይሆን በአእምሮ፣ በማኅበራዊ፣
በኢኮኖሚና በሌሎችም የህይወት ዘርፎች የበሰሉና ኃላፊነት
የሚወስዱ ወንድና ሴት የሚጣመሩበት ኅብረት ነው፡፡ በዚህ
ዕድሜ አካባቢ ታዳጊ ወጣቶች በአካላቸው ወሲብን
ለመፈጸም ደርሰዋል እንጂ በሌሎች የህይወት ገጽታዎች
ገና መብሰል ይቀራቸዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱን
የኢኮኖሚ ብስለትን እንውሰድ፡፡ 18 ዓመት ዕድሜ አካባቢ
ታዳጊ ወጣቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ
ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በኢኮኖሚ በወላጆቻቸው ላይ ጥገኞች
ናቸው፡፡ ከዚያም ኮሌጅ ገብተው ለመማር ከ3-7 ዓመት
ሊፈጅባቸው ይችላል፡፡ የኮሌጅ ትምህርት ካገኙና ሥራ ከያዙ
የራሳቸውን የገቢ ምንጭ ያገኛሉ፡፡ አንድ ወንድና አንዲት
ሴት ሁለቱም የገቢ ምንጭ ካላቸው ወይም የአንዱ የገቢ
ምንጭ ሁለቱን ማኖር የሚያስችል ከሆነ ማግባት ይችላሉ፡፡
በኢኮኖሚ ራስን መቻል የሚለው ሐሳብ አንጻራዊ ነው፡፡
በጋብቻ ሊጣመሩ ያሰቡ ወንድና ሴት ለመሠረታዊ
ፍላጎቶቻቸው የሚሆኑ ነገሮችን ማግኘት የሚያስችል ሁኔታ
ላይ መሆን ለጋብቻ ጅማሬ በቂ ነው፡፡ ጋብቻ ሃብታም
በመሆን የሚጀመር ሳይሆን በዝቅተኛ ገቢ ላይ ተጀምሮ
ሃብቱ ቀስ በቀስ በሁለቱ ጥረት ይመጣል፡፡
የአእምሮ ብስለትና ማኅ በራዊ ግንኙነት ክህሎት
ለጋብቻ ግንኙነት ዘላቂነት አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ነገሮች
መካከል አንዱ የጥንዶቹ (ወንድና ሴት) የአእምሮ ብስለትና
የማኅበራዊ ግንኙነት ክህሎት መኖር ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ
ብስለት ደግሞ ዕድሜ በመቁጠር ብቻ ላይመጣ ይችላል፡፡
ሆኖም ዕድሜ ራሱ ትምህርት ቤት በመሆኑ (የተለያዩ
ነገሮችን ከውጣ ውረድ ለመቅሰም ዕድል ስለሚሰጥ)
የዕድሜ መጨመር የአእምሮ ብስለትና የማኅበራዊ ግንኙነት
ክህሎትን ለማዳበር መልካም አጋጣሚዎች ይኖራሉ፡፡
በለጋ ዕድሜ ከማግባት በሃያዎቹ አጋማሽ አካባቢ ማግባት፣
የጋብቻ ግንኙነትን ለማጣጣምና ግንኙነቱን ዘላቂ ለማድረግ
አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ብቁ ያደርጋል፡፡
ልጅ ለመውለድና ለማሳደግ
ከአካል ዕድገት አንጻር ወንድና ሴት ከጉርምስና ዕድሜ
ጀምረው ልጅ መውለድ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከአካል ዝግጅት፣
ከጤንነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሌሎች ምክንያቶች
አንጻር በተለይ ለሴቶች ጥሩ ልጅ የመውለጃ ዕድሜ ከ18
እስከ 35 ዓመት መሃል ያለው ጊዜ ነው፡፡
እንግዲህ ከላይ በተጠቀሱ ነጥቦች ስር ወጣት ወንዶችና
ሴቶች በአብዛኛው እስከ 20ዎቹ አጋማሽ አካባቢ
በትምህርት ላይ ይሆናሉ፡፡ ራሳቸውን ችለው ቤተሰብ
ለመመስረት ሁለንተናዊ ብቃት የሚኖራቸው በዚህ ወቅት
ነው፡፡
ልጅ ከመውለድ አንጻር ከዝቅተኛ ተገቢ ዕድሜ 18 መጀመር
ቢመረጥም የሁኔታዎች አለመመቻቸት ስለሚኖር በዚህ ጊዜ
ማድረጉ ብዙ ተግዳሮቶች አሉት፡፡ ራስን የመቻል አቅም
ከመጣ በኋላ ግን ወደ ከፍተኛ ጫፍ (35) ከፍ ማድረጉ
አይመረጥም፡፡
ልጅ መውለድ ብቻ ሳይሆን የማሳደግም ኃላፊነት ስለሚኖር
ተጋቢዎቹ በለጋ የጎልማሳነት ዕድሜያቸው ልጆቹን ለማሳደግ
የአካል፣ ስሜትና ስነልቦናዊ ዝግጁነት ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ
አግብቶ ልጅ መውለድ ለሚፈልጉ ይህን ነጥብ ከግንዛቤ
ውስጥ ማስገባት ጠቃሚ ነው፡፡
በተገቢ ዕድሜ የማግባት ጥቅሞች
በሃያዎቹ አጋማሽ አካባቢ የሚያገቡ ወንዶችና ሴቶች
በጋብቻ ህይወታቸው ከሌሎቹ ይልቅ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡
በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገቡ ወንዶች ካላገቡ
ወንዶች ይልቅ ሃብት የማፍራት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
ያገቡ ወንዶች ገቢና ሃብት እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ለጤንነት አስጊ ለሆኑ ነገሮች የመጋለጥ ዕድል
ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ በወጣትነታቸው ወቅት ያገቡ
ወንዶችና ሴቶች ጤንነታቸውን ጠብቀው የመኖር
መልካም አጋጣሚዎችን ያገኛሉ፡፡
በወጣትነት (20ዎቹ አጋማሽ አካባቢ
) የሚያገቡ ጥንዶች
መልካም የወሲብ ህይወት ይኖራቸዋል፡፡ በዚህ የትኩስ
ወጣትነት ጊዜ ወሲብን ሁልጊዜ የማግኘትና በፍቅር
ውስጥ ሆነው የመለማመድ ዕድል አላቸው፡፡ ዕድሜ
ሲጨምር የሰውነት ኃይልም እየቀነሰ ስለሚሄድ እንደ
ትኩስ የወጣትነት ጊዜ ወሲብን የመለማመድ ዕድሉ
ይቀንሳል፡፡
ጥንዶቹ በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረዶች (ከተቃራኒ ጾታ
ጋር ባለው የግንኙነት መፍረስ) ህይወታቸው ሳይቆስል
ወደ ጋብቻ ይገባሉ፡፡ ስለዚህ ከሌሎች ግንኙነቶች ወደ
ጋብቻ ይዘው የሚመጡት ‹‹ኮተት›› ላይኖር ይችላል፡፡
አንዱ ሌላውን የመቅረጽ ዕድሉ ይሰፋል፡፡ በዚህ
የወጣትነት ጊዜ ሁለቱም ተሰርተው ስላላለቁ፣
ይቀራረጻሉ፣ በረጅም ርቀት መልካም ጓደኛሞች ይሆናሉ፡፡
ጤናማ ልጆችን በጊዜ ወልዶ በጊዜ ለማሳደግ
መልካም ዕድል ይፈጥራል፡፡ ዕድሜ ከገፋ በኋላ ልጆችን
መውለድ የሚቻል ቢሆንም ወላጆች ልጆቹን ለማሳደግ
የሚኖራቸው ጉልበት ይቀንሳል፡፡ በወላጆችና በልጆች
መካከል የዕድሜ መራራቅም የትውልድ ክፍተትን በጣም
ይፈጥራል፡፡
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
መልካም የወሲብ ህይወት ይኖራቸዋል፡፡ በዚህ የትኩስ
ወጣትነት ጊዜ ወሲብን ሁልጊዜ የማግኘትና በፍቅር
ውስጥ ሆነው የመለማመድ ዕድል አላቸው፡፡ ዕድሜ
ሲጨምር የሰውነት ኃይልም እየቀነሰ ስለሚሄድ እንደ
ትኩስ የወጣትነት ጊዜ ወሲብን የመለማመድ ዕድሉ
ይቀንሳል፡፡
ጥንዶቹ በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረዶች (ከተቃራኒ ጾታ
ጋር ባለው የግንኙነት መፍረስ) ህይወታቸው ሳይቆስል
ወደ ጋብቻ ይገባሉ፡፡ ስለዚህ ከሌሎች ግንኙነቶች ወደ
ጋብቻ ይዘው የሚመጡት ‹‹ኮተት›› ላይኖር ይችላል፡፡
አንዱ ሌላውን የመቅረጽ ዕድሉ ይሰፋል፡፡ በዚህ
የወጣትነት ጊዜ ሁለቱም ተሰርተው ስላላለቁ፣
ይቀራረጻሉ፣ በረጅም ርቀት መልካም ጓደኛሞች ይሆናሉ፡፡
ጤናማ ልጆችን በጊዜ ወልዶ በጊዜ ለማሳደግ
መልካም ዕድል ይፈጥራል፡፡ ዕድሜ ከገፋ በኋላ ልጆችን
መውለድ የሚቻል ቢሆንም ወላጆች ልጆቹን ለማሳደግ
የሚኖራቸው ጉልበት ይቀንሳል፡፡ በወላጆችና በልጆች
መካከል የዕድሜ መራራቅም የትውልድ ክፍተትን በጣም
ይፈጥራል፡፡
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ሚዛናዊ ጤነኛ ሰው አለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO አለመታመም የጤነኝነት
ምልክት አይደለም ይልና ጤናን እንዲህ ሲል ይተረጉመዋል፡፡
ሙሉ (Complete) አካላዊ ፤ አእምሮአዊ ፤ ማኅበራዊ ፤
ውስጠ ስሜታዊ (Emotional) እና መንፈሳዊ ደህንነት ነው
ይለናል፡፡ ከተጠቀሱት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ ቢስተጓገል
የጤና መታወክ እንዳለም ያስረዳናል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እንዳሉ ሆነው የፖዘቲቭ
ሳይኮቴራፒ ጽንሰ-ሃሳብ አመንጪ ፕ/ር ኖስራት ፖዘሽኪያን
የሰው ልጅ ዕለት ተዕለት በሚኖረው ህይወት ውስጥና
በዚህች ምድር ላይ እስካለ ድረስ ጤናማ ፤ ደስተኛና
ስኬታማ ሆኖ እንዲኖር አራት መሰረታዊ ሚዛንነት ያላቸው
ጉዳዮች ያስፈልጉታል፡፡ ውጤታማ ለመሆንም ከአንዱ ደረጃ
ወደ ሌላው ሳይሸጋገር የምኞቱንና የፍላጎቱን ውጥን
ማሳካት ይችላል ይላል፡፡ ከአብርሃም ማስሎ የፍላጎት ደረጃ
በተቃራኒ (Hierarchy of needs)፡፡ አሁን ያለበትን ሁኔታ
ከግምት ውስጥ በማስገባት የአኗኗር ዘይቤን መቀየር ብቻ
ወሳኝ መሆኑን ያስረዳል፡፡ እሳቤውም ሰዎች የዛሬውን ድካም
፤ አለመሳካት ፤ ጭንቀት ፤ ሰላም ማጣትን ብቻ እንዲያስቡ
ሳይሆን የዛሬ አለመሳካትን ፤ ጭንቀትንና ጨለምተኝነትን
እንደ አንድ ግብአት በመውሰድ ኃይልና ብርታትን አግኝተው
ወደፊት ወይም ወደ ሚፈልጉበት አቅጣጫ መጓዝ
እንደሚችሉ ነው፡፡ የዛሬ የጭንቀት ፤ የድካምና የልፋት እሳት
የነገ ብርሃን እንደሆነ በማስረዳት፡፡
ፖዘቲቭ ሳይኮቴራፒ ሶስት መሰረታዊ የመርህ አምዶች
ሲኖሩት ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሚዛናዊነት መርህ ነው
(Principles of Balance)፡፡ ከተነሳንበት ነጥብ ጋር
ተያያዥነት ስላለው የሚዛናዊነት መርህ ምን እንደሆነ
በቀላሉ ለማስረዳት እሞክራለው፡፡
የሚዛናዊነት መርህ አራት ዋና ዋና ክፍሎችን በውስጡ
አካቶ ይይዛል (አካል ፤ ስኬት ወይም ስራ ፤ ማኅበራዊነትና
መንፈሳዊነት/ተስፍ)፡፡ አራቱም ክፍሎች በእኩል
ሚዛናዊነታቸውን ጠብቀው ያለተቃርኖ አንዱ አንዱን እያገዘና
እየደገፈ የግለሰቡን ማንነት ፤ ፍላጎት ፤ ደስታ ፤ ስኬት
ጤነኝነት…ወዘተ ያስገኙለታል፡፡
ሀ. አካል (Body)
ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ሮጦ ህይወትንና ኑሮን ለመምራት
አካላዊ ጤና ወሳኝነቱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ግን ስለ
አካልህ ምን ይሰማሃል (ወፍራም ፤ ቀጭን ፤ ረጅም
፤አጭር፤ ብርቱ ፤ ደካማ ፤ አካል ጉዳተኛ ፤ ጤናማ…ወዘተ)?
አካላዊ ማንነትህን ትቀበለዋለህ ወይስ የሆነ ለውጥ
እንደሚያስፈልግህ ታስባለህ? አካልህን ትንከባከበዋለህ
ወይስ ለዚህ ፈራሽ ገላ ብለህ ደንታ ቢስ ሆነሃል? ያገኘውትን
ልብላ ዛሬ የሆንኩትን ልሁን አካሌ ኖረ አልኖረም
አይደንቀኝም ትል ይሆናል፡፡ አካላዊ ሰላምና ጤና የሌለህ
(ጉዳትም ካለብህ እውነታውን ተቀበልና ባለህበት ደስተኛና
ውጤታማ መሆን ትችላለህ፡፡ በመጀመሪያ እራስህንና
ማንነትህን ተቀበለው) ቢሆን እንኳ ግድ የለህም እራስህን
መቀየርና መለወጥ ትችላለህ፡፡ አካላዊ ማንነትህ ሰላምና
ጤናማ ሲሆን አእምሮህም መልካም ነገር ማሰብና መስራት
ይጀምራል፡፡ ወይም በተቃራኒው እዩኝ ባይ ተሽቀርቃሪ
ለአካላዊ ማንነትህ የምትኖርና የምትጨነቅ ብቻ መሆን
የለብህም፡፡ አካልህ የማንነትህ አንድ መገለጫ እንጂ
ሁለንተናህ እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ በአጭሩ አካልህን ውደደው
ተቀበለው ተንከባከበው መቀየር ወይም መለወጥ ያለበት
አካላዊ ገጽታ ካለህ ጠንክረህ በመስራት ገጽታህን
ለውጠው (በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወይም ለጤናህ ቅድሚያ
በመስጠት)፡፡ አንተ ጡንቻ ብቻ ሳትሆን አእምሯዊ፤
መንፈሳዊ፤ ማኅበራዊም ሰው መሆንህን ልብ በል፡፡ ግን
አሁንም አካልህን መንከባከብን አትዘንጋ (በሚዛናዊነት)
ለ. ስኬት/ስራ (Achievement)
በምትሰራው ስራ ወይም በተሰማራህበት ነገር ሁሉ ስኬታማ
መሆንን ትሻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ህይወት ስኬት ብቻ
አይደለችም፡፡ የምትፈልገው የስኬት ወይም ውጤት ላይ
ስትደርስ ምናልባት አእምሮህ ፤ አካልህ ፤ ማኅበራዊነትህና
ተስፈኝነትህ ተዳክሞ ሊሆን ይችላል የደረስከው፡፡ ስለዚህ
ትክክለኛው ስኬት ላይ እንዳልደረስክ እወቅ፡፡ አንዱን
ለማግኘት ስትል ሌላው ማንነትህን አጥተሃልና፡፡ ዛሬ ለብር
ብቻ ብትሮጥ ብትለፍ ውሎ አድሮ ብርን ታገኝና በገንዘብህ
ደግሞ ጤናን ለመሸመት ወደ ኋላ መሄድህ አይቀርም፡፡ ስራ
መስራትና ገንዘብ ማጠራቀም ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እራስን
ጎድቶ ለገንዘብ ማደር ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ገንዘብህ ዋጋ
የሚኖረው መጀመሪያ አንተ ስትኖር ነው፡፡ አንዴ አንተ
ከጠፋህ ገንዘብ ሊያኖርህ አይችልም፡፡ ታመህ ጤናን
ለመሸመት ከመሯሯጥ ሳትታመም አስቀድመህ ባለህ ነገር
ጤናን መንከባከብ ይሻላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ስኬትንም
ለማግኘት ደፋ ቀና ስትል በሚዛናዊነት መሆን አለበት፡፡
ትምህርትን ስታስብ መማርህን ብቻ ሳይሆን እየተማርክ
በተጓዳኝ ማስኬድ ያለብህ ነገር ምን አንዳላ ተረዳና
ከውነው (ጊዜህን ሙሉ በትምህርት ብቻ አሳልፈህ ወደ ኋላ
ተመልሰህ ልታገኛቸው የማትችላቸው የህይወት ዘይቤዎቸ
ስላሉ አስተውላቸው) ስኬት አካላዊ ፤ አእምሮዊ
፤ማኅበራዊና መንፈሳዊ/ተስፍ ዕድገትን አካታ ካልተገኘች
ትናንት የቋመጥክለት ስኬት እርባና ቢስ ይሆንብሃል
(ቤተሰብ የመመስረቻ ጊዜ….በነገራችን ላይ ቤተሰብ
አለመመስረትም አንዱ የህይወት ዘይቤ ነው) ምክንያቱም
በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ሁሌም ዕድገትና ለውጥ ስላለ
የትናንት ወርቃማ መርሆችህና የኑሮ ዘይቤዎችህ ከአስር
ዓመት በኋላ ምንም ማለት እንዳልሆኑ ስትረዳው ትናት
ያባከንከው ጊዜና ኃይል መልሰህ ላታገኘው ነገር ይቆጭሃል
(Robert J. Havighurst’s Developmental Task)፡፡
ስለዚህ ለጊዜና ለስኬትህ ሚዛናዊነትን አስቀምጥ፡፡ ስኬት
ወይም ስራ አስፈላጊ ነው ነገር ግን በተጓዳኝ ምን
ያስፈልገኛል የሚለውን ባለመርሳት፡፡
ሐ.ማኅበራዊ (Social)
ሰውን ሰው ያሰኘው ስራው ብቻ ሳይሆን ማህበራዊነቱም
ጭምር ነው፡፡ አገርኛ ዘይቤው ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው
እንዲል፡፡ ያለ ማኅበራነት ህይወት ትርጉም ታጣለች፡፡
ስትደሰት ደስታህን ተካፍይና ስታዝን አጽናኝ ያስፈልግሃል፡፡
በብቸኝነት ደስታ ጤነኝነትንና እርካታን ማግኘት አይቻልም
ቢገኝም ጊዜአዊ ነው የሚሆነው፡፡ ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ
ደሴት አይደለም፡፡ ደሴት ደሴት ይባል ዘንድ ዙሪያውን በውሃ
አካል መከበብ አለበት፡፡ ማኅበራዊ ህይወት ስንል ሺህ
ሰማኒያውን ሰው ግር አድርጎ መጓተትና መግተልተል ሳይሆን
ጥራቱን ነው የምናወራውና ትኩረት የምንሰጠው፡፡ አንዳንድ
ጊዜ በብዙ ሰዎች ተከበህም ምንም የማይፈይዱህ ከሰው
ጋር ሆነህ ብቸኝነት እንዲሰማህ የሚያደርጉህ ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ህይወትህን ቀለል የሚያደርጉና ደስታና
ሃዘንህን ሊጋሩህ የሚችሉ ወዳጆች ያስፈልጉሃል፡፡ ጠንካራ
ማኅበራዊ ትስስር ያላቸው ሰዎች ደስተኛና ጤነኛ ይሆናሉ፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጥሩ ማኅበራዊ ህይወት
ያላቸው ሰዎች ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ፡፡ ከማኅበራዊ ሚዲያ
አምስት ሺህ ጓደኞችህ (በአወንታዊው መልኩ ይታይልኝ፡፡
የማኅበራዊ ሚዲያን ጓደኝነት ማሳነሴና ዋጋ ለማሳጣት
እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ እኛም በማኅበራዊ ሚዲያ አይደል
እየተማማርን ያለነው!) ይልቅ በሳምንት አንዴ በአካል
የምታገኘው ወዳጅህ ትልቅ አስተዋጽኦ ላንተነትህ አለው፡፡
ሳይበዛም ሳያንስም ማኅበራዊ ህይወት ደስታንና ሃሴትን
ከማጎናጸፉ ባሻገር የሌላውን ልምድና ተሞክሮ እንድንጋራ
ይረዳናል፡፡
መ. መንፈሳዊነት/ተስፍ (Spirit or Hope)
ትናንትን አትመልሰውም ወይም አትኖረውም፡፡ ግን ትልቅ
ምልክት አይደለም ይልና ጤናን እንዲህ ሲል ይተረጉመዋል፡፡
ሙሉ (Complete) አካላዊ ፤ አእምሮአዊ ፤ ማኅበራዊ ፤
ውስጠ ስሜታዊ (Emotional) እና መንፈሳዊ ደህንነት ነው
ይለናል፡፡ ከተጠቀሱት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ ቢስተጓገል
የጤና መታወክ እንዳለም ያስረዳናል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እንዳሉ ሆነው የፖዘቲቭ
ሳይኮቴራፒ ጽንሰ-ሃሳብ አመንጪ ፕ/ር ኖስራት ፖዘሽኪያን
የሰው ልጅ ዕለት ተዕለት በሚኖረው ህይወት ውስጥና
በዚህች ምድር ላይ እስካለ ድረስ ጤናማ ፤ ደስተኛና
ስኬታማ ሆኖ እንዲኖር አራት መሰረታዊ ሚዛንነት ያላቸው
ጉዳዮች ያስፈልጉታል፡፡ ውጤታማ ለመሆንም ከአንዱ ደረጃ
ወደ ሌላው ሳይሸጋገር የምኞቱንና የፍላጎቱን ውጥን
ማሳካት ይችላል ይላል፡፡ ከአብርሃም ማስሎ የፍላጎት ደረጃ
በተቃራኒ (Hierarchy of needs)፡፡ አሁን ያለበትን ሁኔታ
ከግምት ውስጥ በማስገባት የአኗኗር ዘይቤን መቀየር ብቻ
ወሳኝ መሆኑን ያስረዳል፡፡ እሳቤውም ሰዎች የዛሬውን ድካም
፤ አለመሳካት ፤ ጭንቀት ፤ ሰላም ማጣትን ብቻ እንዲያስቡ
ሳይሆን የዛሬ አለመሳካትን ፤ ጭንቀትንና ጨለምተኝነትን
እንደ አንድ ግብአት በመውሰድ ኃይልና ብርታትን አግኝተው
ወደፊት ወይም ወደ ሚፈልጉበት አቅጣጫ መጓዝ
እንደሚችሉ ነው፡፡ የዛሬ የጭንቀት ፤ የድካምና የልፋት እሳት
የነገ ብርሃን እንደሆነ በማስረዳት፡፡
ፖዘቲቭ ሳይኮቴራፒ ሶስት መሰረታዊ የመርህ አምዶች
ሲኖሩት ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሚዛናዊነት መርህ ነው
(Principles of Balance)፡፡ ከተነሳንበት ነጥብ ጋር
ተያያዥነት ስላለው የሚዛናዊነት መርህ ምን እንደሆነ
በቀላሉ ለማስረዳት እሞክራለው፡፡
የሚዛናዊነት መርህ አራት ዋና ዋና ክፍሎችን በውስጡ
አካቶ ይይዛል (አካል ፤ ስኬት ወይም ስራ ፤ ማኅበራዊነትና
መንፈሳዊነት/ተስፍ)፡፡ አራቱም ክፍሎች በእኩል
ሚዛናዊነታቸውን ጠብቀው ያለተቃርኖ አንዱ አንዱን እያገዘና
እየደገፈ የግለሰቡን ማንነት ፤ ፍላጎት ፤ ደስታ ፤ ስኬት
ጤነኝነት…ወዘተ ያስገኙለታል፡፡
ሀ. አካል (Body)
ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ሮጦ ህይወትንና ኑሮን ለመምራት
አካላዊ ጤና ወሳኝነቱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ግን ስለ
አካልህ ምን ይሰማሃል (ወፍራም ፤ ቀጭን ፤ ረጅም
፤አጭር፤ ብርቱ ፤ ደካማ ፤ አካል ጉዳተኛ ፤ ጤናማ…ወዘተ)?
አካላዊ ማንነትህን ትቀበለዋለህ ወይስ የሆነ ለውጥ
እንደሚያስፈልግህ ታስባለህ? አካልህን ትንከባከበዋለህ
ወይስ ለዚህ ፈራሽ ገላ ብለህ ደንታ ቢስ ሆነሃል? ያገኘውትን
ልብላ ዛሬ የሆንኩትን ልሁን አካሌ ኖረ አልኖረም
አይደንቀኝም ትል ይሆናል፡፡ አካላዊ ሰላምና ጤና የሌለህ
(ጉዳትም ካለብህ እውነታውን ተቀበልና ባለህበት ደስተኛና
ውጤታማ መሆን ትችላለህ፡፡ በመጀመሪያ እራስህንና
ማንነትህን ተቀበለው) ቢሆን እንኳ ግድ የለህም እራስህን
መቀየርና መለወጥ ትችላለህ፡፡ አካላዊ ማንነትህ ሰላምና
ጤናማ ሲሆን አእምሮህም መልካም ነገር ማሰብና መስራት
ይጀምራል፡፡ ወይም በተቃራኒው እዩኝ ባይ ተሽቀርቃሪ
ለአካላዊ ማንነትህ የምትኖርና የምትጨነቅ ብቻ መሆን
የለብህም፡፡ አካልህ የማንነትህ አንድ መገለጫ እንጂ
ሁለንተናህ እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ በአጭሩ አካልህን ውደደው
ተቀበለው ተንከባከበው መቀየር ወይም መለወጥ ያለበት
አካላዊ ገጽታ ካለህ ጠንክረህ በመስራት ገጽታህን
ለውጠው (በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወይም ለጤናህ ቅድሚያ
በመስጠት)፡፡ አንተ ጡንቻ ብቻ ሳትሆን አእምሯዊ፤
መንፈሳዊ፤ ማኅበራዊም ሰው መሆንህን ልብ በል፡፡ ግን
አሁንም አካልህን መንከባከብን አትዘንጋ (በሚዛናዊነት)
ለ. ስኬት/ስራ (Achievement)
በምትሰራው ስራ ወይም በተሰማራህበት ነገር ሁሉ ስኬታማ
መሆንን ትሻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ህይወት ስኬት ብቻ
አይደለችም፡፡ የምትፈልገው የስኬት ወይም ውጤት ላይ
ስትደርስ ምናልባት አእምሮህ ፤ አካልህ ፤ ማኅበራዊነትህና
ተስፈኝነትህ ተዳክሞ ሊሆን ይችላል የደረስከው፡፡ ስለዚህ
ትክክለኛው ስኬት ላይ እንዳልደረስክ እወቅ፡፡ አንዱን
ለማግኘት ስትል ሌላው ማንነትህን አጥተሃልና፡፡ ዛሬ ለብር
ብቻ ብትሮጥ ብትለፍ ውሎ አድሮ ብርን ታገኝና በገንዘብህ
ደግሞ ጤናን ለመሸመት ወደ ኋላ መሄድህ አይቀርም፡፡ ስራ
መስራትና ገንዘብ ማጠራቀም ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እራስን
ጎድቶ ለገንዘብ ማደር ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ገንዘብህ ዋጋ
የሚኖረው መጀመሪያ አንተ ስትኖር ነው፡፡ አንዴ አንተ
ከጠፋህ ገንዘብ ሊያኖርህ አይችልም፡፡ ታመህ ጤናን
ለመሸመት ከመሯሯጥ ሳትታመም አስቀድመህ ባለህ ነገር
ጤናን መንከባከብ ይሻላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ስኬትንም
ለማግኘት ደፋ ቀና ስትል በሚዛናዊነት መሆን አለበት፡፡
ትምህርትን ስታስብ መማርህን ብቻ ሳይሆን እየተማርክ
በተጓዳኝ ማስኬድ ያለብህ ነገር ምን አንዳላ ተረዳና
ከውነው (ጊዜህን ሙሉ በትምህርት ብቻ አሳልፈህ ወደ ኋላ
ተመልሰህ ልታገኛቸው የማትችላቸው የህይወት ዘይቤዎቸ
ስላሉ አስተውላቸው) ስኬት አካላዊ ፤ አእምሮዊ
፤ማኅበራዊና መንፈሳዊ/ተስፍ ዕድገትን አካታ ካልተገኘች
ትናንት የቋመጥክለት ስኬት እርባና ቢስ ይሆንብሃል
(ቤተሰብ የመመስረቻ ጊዜ….በነገራችን ላይ ቤተሰብ
አለመመስረትም አንዱ የህይወት ዘይቤ ነው) ምክንያቱም
በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ሁሌም ዕድገትና ለውጥ ስላለ
የትናንት ወርቃማ መርሆችህና የኑሮ ዘይቤዎችህ ከአስር
ዓመት በኋላ ምንም ማለት እንዳልሆኑ ስትረዳው ትናት
ያባከንከው ጊዜና ኃይል መልሰህ ላታገኘው ነገር ይቆጭሃል
(Robert J. Havighurst’s Developmental Task)፡፡
ስለዚህ ለጊዜና ለስኬትህ ሚዛናዊነትን አስቀምጥ፡፡ ስኬት
ወይም ስራ አስፈላጊ ነው ነገር ግን በተጓዳኝ ምን
ያስፈልገኛል የሚለውን ባለመርሳት፡፡
ሐ.ማኅበራዊ (Social)
ሰውን ሰው ያሰኘው ስራው ብቻ ሳይሆን ማህበራዊነቱም
ጭምር ነው፡፡ አገርኛ ዘይቤው ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው
እንዲል፡፡ ያለ ማኅበራነት ህይወት ትርጉም ታጣለች፡፡
ስትደሰት ደስታህን ተካፍይና ስታዝን አጽናኝ ያስፈልግሃል፡፡
በብቸኝነት ደስታ ጤነኝነትንና እርካታን ማግኘት አይቻልም
ቢገኝም ጊዜአዊ ነው የሚሆነው፡፡ ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ
ደሴት አይደለም፡፡ ደሴት ደሴት ይባል ዘንድ ዙሪያውን በውሃ
አካል መከበብ አለበት፡፡ ማኅበራዊ ህይወት ስንል ሺህ
ሰማኒያውን ሰው ግር አድርጎ መጓተትና መግተልተል ሳይሆን
ጥራቱን ነው የምናወራውና ትኩረት የምንሰጠው፡፡ አንዳንድ
ጊዜ በብዙ ሰዎች ተከበህም ምንም የማይፈይዱህ ከሰው
ጋር ሆነህ ብቸኝነት እንዲሰማህ የሚያደርጉህ ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ህይወትህን ቀለል የሚያደርጉና ደስታና
ሃዘንህን ሊጋሩህ የሚችሉ ወዳጆች ያስፈልጉሃል፡፡ ጠንካራ
ማኅበራዊ ትስስር ያላቸው ሰዎች ደስተኛና ጤነኛ ይሆናሉ፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጥሩ ማኅበራዊ ህይወት
ያላቸው ሰዎች ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ፡፡ ከማኅበራዊ ሚዲያ
አምስት ሺህ ጓደኞችህ (በአወንታዊው መልኩ ይታይልኝ፡፡
የማኅበራዊ ሚዲያን ጓደኝነት ማሳነሴና ዋጋ ለማሳጣት
እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ እኛም በማኅበራዊ ሚዲያ አይደል
እየተማማርን ያለነው!) ይልቅ በሳምንት አንዴ በአካል
የምታገኘው ወዳጅህ ትልቅ አስተዋጽኦ ላንተነትህ አለው፡፡
ሳይበዛም ሳያንስም ማኅበራዊ ህይወት ደስታንና ሃሴትን
ከማጎናጸፉ ባሻገር የሌላውን ልምድና ተሞክሮ እንድንጋራ
ይረዳናል፡፡
መ. መንፈሳዊነት/ተስፍ (Spirit or Hope)
ትናንትን አትመልሰውም ወይም አትኖረውም፡፡ ግን ትልቅ
ቤተ-መጽሐፍና ትምህርት ቤት ሊሆንህ ይገባል፡፡ የትላንት
መንነትህ ዛሬነትህን አይገልጸውም፡፡ ብትወድቅ ብትነሳ ፤
ህይወት ቢሰምርልህ ቢያማርርህ ትናንት ነበር ነው፡፡
ላትመልሰው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብቶህ ሄዶአል፡፡
ዛሬ የአንተ ናት በእጅህ ላይ ነው ያለችው፡፡ የስኬትንም
የውድቀትም ካርድ ልትመዝባት ትችላለህ፡፡ ግድ የለህም
ዛሬ እንኳ ባይሆንልህ ነገ ደግሞ አለልህ፡፡ ነገን ታስበው
ዘንድ ተስፍ የሚሉት ስንቅ ያስፈልግሃል፡፡እዚህ ላይ
መንፈሳዊነት/ተስፍ ስንል ሃይማኖተኝነትህን ለመግለጽ
ሳይሆን ዛሬን እንደ ግብአት ተጠቅመህ ነገን እንደምትኖር
ለማሳየት ነው፡፡ ተስፍ እንዲኖርህ ደግሞ መንፈሳዊ ሰው
መሆን አለብህ፡፡ ነገሮችን በቅንነት በመልካምነት
የሚመለከት አእምሮ ፤ የዛሬ ውድቀትህ ጠንክሮ በመስራት
ትምህርትና የነገ ስኬትህ እንደሚሆን የሚያስብ፡፡ እንዲያ
ሲሆን በአሉታዊ ህይወትና መንገድ ውስጥ አወንታዊ
የሆነውን ነገር ማየት ትችላለህ (አወንታዊ= ጠንካራ ጎን +
ደካማ ጎን )፡፡ ነገን ለማየት ግን ምንም ዋስትና ባይኖርህም
በተስፍ ታየዋለህ፡፡ ካለማመን ማመን ይሻላል ብለህ
ስለምታስብ ነገን በዛሬ መነጽር ታያትና ሐሴት ታደርጋለህ፡፡
ግላዊ እምነትህ ምንም ይሁን ምን ተስፈኝነትን/
መንፈሳዊነትን ከአንተ በፍጹም ማራቅ የለብህም፡፡ ሌሎች
“ተስፍ/መንፈሳዊነት የሞኞች መጽሐፍ ቅዱስ/ቁራን ነው”
ቢሉህ አትስማቸው፡፡ ሰው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም ኗሪ
ነው ፤ አንድም በምናብ አንድም በአካል፡፡ ታላቁ የሰላም
ታጋይ ማህተመ ጋንዲ ብዙ ጊዜ ስለ ሃይማኖቱ ሲጠየቅ
ምላሹ ስለዚህ ጉዳይ አስቤበት አላውቅም ነበር መልሱ፡፡
ከሃማኖተኝነቱ ይልቅ መንፈሳዊነቱ/ተስፈኝነቱ
ስለሚያደላበት፡፡ ያለተስፍ ሁሉም ነገር ከንቱና ብላሽ ነው፡፡
መሽቶ ስንተኛ ነግቶ ጠዋት እንደምንነሳ በተስፋ ነው፡፡ ሰው
እንስሳ ስላልሆነ ተስፍና ተስፈኝነት ያስፈልገዋል፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው አካል ፤ ስኬት/ስራ ፤
ማኅበራዊነትና መንፈሳዊነት/ተስፍ የፒራሚድ ቅርጽ
በመስራት አንዱ አንዱን ሳይጎዳና ሳይጫን በሚዛንነት
ተጠባብቀው የሚሄዱ ከሆነ ህይወት ቀላልና ምቹ
ትሆናለች፡፡ የሰው ጤነኛነቱም (From Positive
Psychotherapy point of view) በዚሁ ልኬት ይታያል
ይዳሰሳል፡፡ ስለዚህ ጤነኛና ደስተኛ ሰው የአራቱ ድምር
ውጤት ነው በእኩልነት (1+1+1+1=4 (ሙሉ ጤናማ
ሰው))፡፡ ከላይ በተቀመጡት መስፈርቶች አንተስ እንዴት ነህ
የጎደለህና ማስተካከል ያለብህ ነገር አለ? እንግዲያውስ
አትዘናጋ ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ስራህን በሚዛናዊነት
ለመከወን ተነሳ፡፡ ያን ጊዜ ጤነኛና ደስተኛ ሰው ትሆናለህ::
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
መንነትህ ዛሬነትህን አይገልጸውም፡፡ ብትወድቅ ብትነሳ ፤
ህይወት ቢሰምርልህ ቢያማርርህ ትናንት ነበር ነው፡፡
ላትመልሰው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብቶህ ሄዶአል፡፡
ዛሬ የአንተ ናት በእጅህ ላይ ነው ያለችው፡፡ የስኬትንም
የውድቀትም ካርድ ልትመዝባት ትችላለህ፡፡ ግድ የለህም
ዛሬ እንኳ ባይሆንልህ ነገ ደግሞ አለልህ፡፡ ነገን ታስበው
ዘንድ ተስፍ የሚሉት ስንቅ ያስፈልግሃል፡፡እዚህ ላይ
መንፈሳዊነት/ተስፍ ስንል ሃይማኖተኝነትህን ለመግለጽ
ሳይሆን ዛሬን እንደ ግብአት ተጠቅመህ ነገን እንደምትኖር
ለማሳየት ነው፡፡ ተስፍ እንዲኖርህ ደግሞ መንፈሳዊ ሰው
መሆን አለብህ፡፡ ነገሮችን በቅንነት በመልካምነት
የሚመለከት አእምሮ ፤ የዛሬ ውድቀትህ ጠንክሮ በመስራት
ትምህርትና የነገ ስኬትህ እንደሚሆን የሚያስብ፡፡ እንዲያ
ሲሆን በአሉታዊ ህይወትና መንገድ ውስጥ አወንታዊ
የሆነውን ነገር ማየት ትችላለህ (አወንታዊ= ጠንካራ ጎን +
ደካማ ጎን )፡፡ ነገን ለማየት ግን ምንም ዋስትና ባይኖርህም
በተስፍ ታየዋለህ፡፡ ካለማመን ማመን ይሻላል ብለህ
ስለምታስብ ነገን በዛሬ መነጽር ታያትና ሐሴት ታደርጋለህ፡፡
ግላዊ እምነትህ ምንም ይሁን ምን ተስፈኝነትን/
መንፈሳዊነትን ከአንተ በፍጹም ማራቅ የለብህም፡፡ ሌሎች
“ተስፍ/መንፈሳዊነት የሞኞች መጽሐፍ ቅዱስ/ቁራን ነው”
ቢሉህ አትስማቸው፡፡ ሰው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም ኗሪ
ነው ፤ አንድም በምናብ አንድም በአካል፡፡ ታላቁ የሰላም
ታጋይ ማህተመ ጋንዲ ብዙ ጊዜ ስለ ሃይማኖቱ ሲጠየቅ
ምላሹ ስለዚህ ጉዳይ አስቤበት አላውቅም ነበር መልሱ፡፡
ከሃማኖተኝነቱ ይልቅ መንፈሳዊነቱ/ተስፈኝነቱ
ስለሚያደላበት፡፡ ያለተስፍ ሁሉም ነገር ከንቱና ብላሽ ነው፡፡
መሽቶ ስንተኛ ነግቶ ጠዋት እንደምንነሳ በተስፋ ነው፡፡ ሰው
እንስሳ ስላልሆነ ተስፍና ተስፈኝነት ያስፈልገዋል፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው አካል ፤ ስኬት/ስራ ፤
ማኅበራዊነትና መንፈሳዊነት/ተስፍ የፒራሚድ ቅርጽ
በመስራት አንዱ አንዱን ሳይጎዳና ሳይጫን በሚዛንነት
ተጠባብቀው የሚሄዱ ከሆነ ህይወት ቀላልና ምቹ
ትሆናለች፡፡ የሰው ጤነኛነቱም (From Positive
Psychotherapy point of view) በዚሁ ልኬት ይታያል
ይዳሰሳል፡፡ ስለዚህ ጤነኛና ደስተኛ ሰው የአራቱ ድምር
ውጤት ነው በእኩልነት (1+1+1+1=4 (ሙሉ ጤናማ
ሰው))፡፡ ከላይ በተቀመጡት መስፈርቶች አንተስ እንዴት ነህ
የጎደለህና ማስተካከል ያለብህ ነገር አለ? እንግዲያውስ
አትዘናጋ ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ስራህን በሚዛናዊነት
ለመከወን ተነሳ፡፡ ያን ጊዜ ጤነኛና ደስተኛ ሰው ትሆናለህ::
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ፈገግታ😄 “ከእንስራ ሙሉ ሀሞት ይልቅ አንዲት ጠብታ ማር ንቦችን
ትስባለች”
ዴል ካርኔጊ
አንድ ሁለት ብለን ቆጥረን የማንጨርሳቸው “በእጅ የያዙት
ወርቅ” የሆኑብን የግልም የጋራም ሀብት አሉ፤ በእኛም ሆነ
በሌሎች ሰዎች ሕይወት ውስጥ ለውጥ መፍጠር የሚችሉ
ወርቆች፡፡ ዋጋቸውን ከአለመረዳት አንዳንዴ ግድየለሽ
በመሆንም እነዚህን ወርቆች መዳብ አስመስለናቸዋል፡፡
ፈገግታ አንዱ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ከቤት አባወራዎች ጀምሮ
እስከ ሀገር መሪዎች ድረስ በፈገግታ ድርቅ ተመትተናል፡፡
ኮስተር ማለት፣ ፊት መንሳት እንደውም የወንድነት፣
የጀግንነት፣ የጎበዝነት መገለጫም ነው፡፡ ኮስታራ ጀግና እና
ፊቱ የማይፈታ መሪ ብቻ ነው ያለን፡፡ “ወንድ ልጅ ኮስተር
ነው ማለት ያለበት” ሁሉ ይባላል፡፡ መሳቅ፣ መጫወት፣
ፈገግ ማለትን ከድካም ጋር አስተሳስረነዋል፡፡ የሚቀልድ
ሰው ቁምነገረኛ መሆን የሚችል አይመስለንም፡፡
ጉዳይ ለማስፈፀም በየቢሮው ስንገባ “የእግዜር ሰላምታ”
እንኳ በቅጡ አናቀርብም፡፡ አስተናጋጆቹም በበኩላቸው
ፊታቸው ሳይፈታ ያስተናግዱናል፡፡ ኮስትር ብለን የቤት
ሰራተኞቻችን እናዛለን ኮስትር ብለው በግዴታ ስሜት ብቻ
ስራቸውን ይወጣሉ፡፡ ፊትን በማኮሳተር ብቻ ብዙ ማከናወን
የምንችል ይመስለናል፡፡ እውነታው ግን ተቃራኒ ነው፡፡ ፊትን
በመፍታት እንጂ ፊትን በማኮሳተር ማንም ጥሩ መሪ፣ ጥሩ
አስተናጋጅ፣ ጥሩ ባለሀብት፣ ጥሩ ባል፣ ጥሩ ልጅ፣ ጥሩ
መምህር፣ ጥሩ ሾፌር ሊሆን አይችልም፡፡ ዴል ካርኔጊ
“ከእንስራ ሙሉ ሀሞት ይልቅ አንዲት ጠብታ ማር ንቦችን
ትስባለች” ይላል፡፡ ከሚኮሳተሩ ይልቅ በፈገግት የሚደምቁ
ገፆች ሰው ይስባሉ፡፡ ግንባራቸው ከማይፈታ ይልቅ ፈገግታ
የማይለያቸው መሪዎች በህዝብ ዘንድ ይወደዳሉ፡፡
የፈገግታ መልእክቱ “እውድሻለሁ/እወድሀለሁ”፣ “አንተ/
አንቺ በሕይወቴ ውስጥ ቦታ አለሽ/አለህ”፣ “ለእኔ ልዩ ነህ/
ነሽ”፣ “ስላየሁህ ደስ ብሎኛል”፣ “አከብርሀለሁ” ወዘተ ነው፡፡
ኮስታራ ገፅታ በአንፃሩ የዚህን ተቃራኒ መልእክት
ያስተላልፋል፡፡ “ጥፋ ከዚህ”፣ “አሁንስ አንተን የማላይበት
የት ልሂድ?”፣ “ደሞ መጣ” ወዘተ ዓይነት፡፡ በዚህ አስተሳሰብ
የተቃኙ ማኅበራዊ ግንኙነቶች ምን ያህል የምቾት ማጣት
እና ህመም ምንጭ እንደሚሆኑ መገመት ቀላል ነው፡፡
ፈገግታ የተዘጋ የልብን በር የሚከፍት ቁልፍ ነው፡፡
ሁላችሁም እስኪ ዘወትር ፊታቸው እንደ ተቋጠረ ውሎ እንደ
ተቋጠረ የሚያድር ሰዎችን በአእምሮአችሁ አስቡ፡፡ ምን
ያህል ከእነዚህ ሰዎች ጋር መስራት ትፈልጋላችሁ? እነዚህ
ሰዎች የብዙዎቻችን ቀዳሚ ምርጫ መሆን እንደማይችሉ
መገመት ይቻላል፡፡ ጥሩ ሰው ሁሉ ሊሆኑ ይችላል፡፡ ምንም
እንኳ ውስጣቸው ቅን ቢሆንም የማይፈታው ፊታቸው ግን
“አትድረሱብኝ” የሚል መልዕክት ስለሚያስተላልፍ እነዚህ
ሰዎች በተቻለ መጠን ለመቅረብ ሳይሆን በተቻለ መጠን
ለመራቅ እንሞክራለን፡፡
ፈገግታ የሀብት ምንጭ ነው፡፡ በቅጡ ፈገግ ማለት የሚችሉ
አስተናጋጆች ፊታቸው ከማይፈታ አስተናጋጆች የበለጠ “ቲፕ”
ያገኛሉ፡፡ ዩኒቨርስቲ ሶስተኛ ዓመት ተማሪ እያለሁ አንድ ፎቶ
ኮፒ ያደርግልን የነበረ ልጅ አስታውሳለሁ፡፡ ሁልጊዜ ፊቱ
በፈገግታ የተሞላ ነው፡፡ አንድም ቀን እንኳ አዝኖ የሚያውቅ
አይመስላችሁም፡፡ እሱ ባይኖር እንኳ እስኪመጣ ጠብቀን
ኮፒ እናደርጋለን፡፡ ሌላ የሚያስተናግድ ሰው ጠፍቶ
አይደለም፤ ሌሎች ኮፒ ቤቶችም ሞልተዋል፡፡ ብዙ ኮፒ
ቤቶች ቢኖሩም ከፈገግታ ጋር የሚያስተናግዱት ግን ጥቂት
ናቸው፡፡ ፈገግታ ገበያ ያደራል፡፡ ይህንን ቅርብ ጊዜ አግኝቼው
ሌላ ሰው መስሏል፡፡ ቻይና እየተመላለሰ እንደሚነግድ
አጫወተኝ፡፡ መኪና ይዟል፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ በብዙ
መልኩ ተቀይሯል፡፡ አሁንም ግን ያልተቀየረው የፊቱ ፈገግታ
ነው፡፡
ሌላ ማሳያ አሁንም ማንሳት እንችላለን፡፡ አንዳንድ ሰዎች
ጉዳይ በማስፈፀም ረገድ የሚስተካከላቸው የለም፡፡ ሰው
ስለሚያውቁ ላይሆን ይችላል፡፡ አንድ ሁለት እንደዚህ አይነት
ሰዎችን እኔ በግሌ አውቃለሁ፡፡ በቃ እነሱ ጠይቀው ማንም
“አይቻልም” አይልም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ታዲያ
“ግንባር አለው/አላት”፣ ባስ ሲል ደግሞ “የሆነ ነገር አለው/
አላት” ማለት የተለመደ ነው፡፡ ግንባር የሌለው ማን አለ?
ሁላችንም ግንባር አለን፡፡ አንድ አንዶቻችን እንደውም በሰው
መስፈሪያ በጣም ውብ ግንባር ሁሉ ሊኖረን ይችላል፡፡
ሁላችንም የሌለን ፈገግታ ነው፡፡ እነዚህ “ድንጋይ ዳቦ ነው”
ብለው ማሳመን የሚችሉ፣ እንደው የሚያገኛቸው ሰው
በሙሉ ቀና ቀና መልስ የሚመልስላቸው ሰዎች አንዱ ትልቁ
የጋራ መለያቸው ፈገግታቸው ነው፡፡ “አይሆንም ብያለሁ
አይሆንም” ብሎ የዘጋውን “ፋይል” በፈገግታ ቁልፍ
ይከፍቱታል፡፡ እርግጥ ነው “ቁልፉ ፈገግታ ብቻ ነው”
እያልኩ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ አንዱ ዋና ቁልፍ ፈገግት
ነው፡፡
ፈገግታ፣ ደስታ እና አንጎል
ደስታየፈገግታምንጭነው፡፡በአንፃሩፈገግታም የደስታ ምንጭ
ሊሆን ይችላል፡፡ ፈገግታ አንጎላችን ውስጥ የሚገኙ
“ኒውሮኖችን” ስለሚያነቃቃ እና ደስታችንን እና ጤናችንን
ለማሻሻል ይረዳል፡፡ ፈገግታ “Neuropeptides” የሚባሉ
ጥቃቅን ሞሎኪውሎች አንጎላችን ውስጥ እንዲለቀቁ
ያደርጋል፡፡ እነዚህ ሞሎኪውሎች በሌላ በኩል አንጎል ውስጥ
የሚገኙ “ኒውሮኖች” በሚገባ መልካም ግንኙነት እንዲፈጥሩ
በማድረግ ውጥረትን (Stress) ይቀንሳል፡፡
“Neuropeptides” ስንደሰት፣ ስንከፋ፣ ስንናደድ ወዘተ
መልእክት ከአንጎላችን ወደ አካላችን ያስተላልፋሉ፡፡
ውስጣችን አስደሳች ስሜት የሚያቀጣጥሉት ዶፓሚን፣
ኢንዶርፊን፣ ሴሮቶኒን ወዘተ የሚባሉ “ኔውሮትራንስሚተርስ”
ፈገግታ ፊታችንን በሚያጥለቀልቅበት ወቅት በብዛት
ይመነጫሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ሰውነታችን ዘና ይላል፡፡ ይህ
ብቻ ሳይሆን የልብ ምታችን እና የደም ግፊታችን የተረጋጋ
እና የተስተካከለ ይሆናል፡፡
“ኢንዶርፊን” የሚባሉት “ኔውሮትራንስሚተሮች” በበኩላቸው
የህመም ማስታገሻናቸው፡፡ ህመም ሲያጋጥመን
የምንውጣቸውየህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች የጎንዮሽ
ጉዳታቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ፈገግታ
የሚያመነጨው “ኢንዶርፊን” በሌላ በኩል ግን ሙሉ ለሙሉ
ተፈጥሮአዊ የሆነ የህመም ማስታገሻ ነው፡፡ ታማሚዎችሰው
አጠገባቸው ሆኖ ሲያጫውታቸው፣ ፈገግ ሲሉ፣ ሲስቁ “አይ
ደህና ነህ እኮ! ያመመህ አትመስልም እንደውም”ብለን
የምናውቅበት ጊዜ ሁሉ ይኖራል፡፡
ፈገግታ የሚያመነጨው ሌላኛው “ኒውሮትራንስሚተር”
“ሴሮቶኒን” ፍቱን የድብርት መድኃኒት ነው፡፡ የመድኃኒት
ፋብሪካዎች የሚያመርቷቸው “Anti-depressants”
አንጎላችን ውስጥ ገብተው የሴሮቶኒንን መጠን ነው ከፍ
የሚያደርጉት፡፡ ፈገግታ በአንፃሩ ያለ ምንም የጎንዮሽ ጉዳት
እና የሀኪም ትዕዛዝ የድብርት ሰሜትን ከውስጥ ጠራርጎ
ያስወጣል፡፡
ፈገግታ እና አካላችን
ፈገግታ ውበትን ይጨምራል፡፡ ፎቶ አንሺዎች “ትንሽ
ፈገግጋ… ትንሽ… አዎ…እንደሱ” ያላሉት ማን አለ?የፈገግታን
ምስጢር ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡ ፈገግታ ፊታችሁ ላይ
ሲታይ ሰዎች በጥሩሁኔታ ያስተናግዷችኋል፡፡ ይህ ሊሆን
የቻለበት ዋና ምክንያት የጥናት ውጤቶች እንደሚጠቁሙት
“ፈገግ በምንልበት ወቅት ሰዎች ማራኪ፣ እምነት
የሚጣልበት፣ ዘና ማለት የሚችል እና ቅን ሰው ነው/ናት”
ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡
በ2011 ዓ.ም ስኮትላንድ አበርደን ዩኒቨርስቲ ውስጥ
ከፈገግታ ጋር የተያያዘ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ የጥናቱ
ተሳታፊዎች ለፈገግታ እና ውበት ደረጃ ያወጡ ሲሆን
ብዙዎቹ ዓይን ዓይንን (Eye Contact) የሚያዩ እና ፈገ
ትስባለች”
ዴል ካርኔጊ
አንድ ሁለት ብለን ቆጥረን የማንጨርሳቸው “በእጅ የያዙት
ወርቅ” የሆኑብን የግልም የጋራም ሀብት አሉ፤ በእኛም ሆነ
በሌሎች ሰዎች ሕይወት ውስጥ ለውጥ መፍጠር የሚችሉ
ወርቆች፡፡ ዋጋቸውን ከአለመረዳት አንዳንዴ ግድየለሽ
በመሆንም እነዚህን ወርቆች መዳብ አስመስለናቸዋል፡፡
ፈገግታ አንዱ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ከቤት አባወራዎች ጀምሮ
እስከ ሀገር መሪዎች ድረስ በፈገግታ ድርቅ ተመትተናል፡፡
ኮስተር ማለት፣ ፊት መንሳት እንደውም የወንድነት፣
የጀግንነት፣ የጎበዝነት መገለጫም ነው፡፡ ኮስታራ ጀግና እና
ፊቱ የማይፈታ መሪ ብቻ ነው ያለን፡፡ “ወንድ ልጅ ኮስተር
ነው ማለት ያለበት” ሁሉ ይባላል፡፡ መሳቅ፣ መጫወት፣
ፈገግ ማለትን ከድካም ጋር አስተሳስረነዋል፡፡ የሚቀልድ
ሰው ቁምነገረኛ መሆን የሚችል አይመስለንም፡፡
ጉዳይ ለማስፈፀም በየቢሮው ስንገባ “የእግዜር ሰላምታ”
እንኳ በቅጡ አናቀርብም፡፡ አስተናጋጆቹም በበኩላቸው
ፊታቸው ሳይፈታ ያስተናግዱናል፡፡ ኮስትር ብለን የቤት
ሰራተኞቻችን እናዛለን ኮስትር ብለው በግዴታ ስሜት ብቻ
ስራቸውን ይወጣሉ፡፡ ፊትን በማኮሳተር ብቻ ብዙ ማከናወን
የምንችል ይመስለናል፡፡ እውነታው ግን ተቃራኒ ነው፡፡ ፊትን
በመፍታት እንጂ ፊትን በማኮሳተር ማንም ጥሩ መሪ፣ ጥሩ
አስተናጋጅ፣ ጥሩ ባለሀብት፣ ጥሩ ባል፣ ጥሩ ልጅ፣ ጥሩ
መምህር፣ ጥሩ ሾፌር ሊሆን አይችልም፡፡ ዴል ካርኔጊ
“ከእንስራ ሙሉ ሀሞት ይልቅ አንዲት ጠብታ ማር ንቦችን
ትስባለች” ይላል፡፡ ከሚኮሳተሩ ይልቅ በፈገግት የሚደምቁ
ገፆች ሰው ይስባሉ፡፡ ግንባራቸው ከማይፈታ ይልቅ ፈገግታ
የማይለያቸው መሪዎች በህዝብ ዘንድ ይወደዳሉ፡፡
የፈገግታ መልእክቱ “እውድሻለሁ/እወድሀለሁ”፣ “አንተ/
አንቺ በሕይወቴ ውስጥ ቦታ አለሽ/አለህ”፣ “ለእኔ ልዩ ነህ/
ነሽ”፣ “ስላየሁህ ደስ ብሎኛል”፣ “አከብርሀለሁ” ወዘተ ነው፡፡
ኮስታራ ገፅታ በአንፃሩ የዚህን ተቃራኒ መልእክት
ያስተላልፋል፡፡ “ጥፋ ከዚህ”፣ “አሁንስ አንተን የማላይበት
የት ልሂድ?”፣ “ደሞ መጣ” ወዘተ ዓይነት፡፡ በዚህ አስተሳሰብ
የተቃኙ ማኅበራዊ ግንኙነቶች ምን ያህል የምቾት ማጣት
እና ህመም ምንጭ እንደሚሆኑ መገመት ቀላል ነው፡፡
ፈገግታ የተዘጋ የልብን በር የሚከፍት ቁልፍ ነው፡፡
ሁላችሁም እስኪ ዘወትር ፊታቸው እንደ ተቋጠረ ውሎ እንደ
ተቋጠረ የሚያድር ሰዎችን በአእምሮአችሁ አስቡ፡፡ ምን
ያህል ከእነዚህ ሰዎች ጋር መስራት ትፈልጋላችሁ? እነዚህ
ሰዎች የብዙዎቻችን ቀዳሚ ምርጫ መሆን እንደማይችሉ
መገመት ይቻላል፡፡ ጥሩ ሰው ሁሉ ሊሆኑ ይችላል፡፡ ምንም
እንኳ ውስጣቸው ቅን ቢሆንም የማይፈታው ፊታቸው ግን
“አትድረሱብኝ” የሚል መልዕክት ስለሚያስተላልፍ እነዚህ
ሰዎች በተቻለ መጠን ለመቅረብ ሳይሆን በተቻለ መጠን
ለመራቅ እንሞክራለን፡፡
ፈገግታ የሀብት ምንጭ ነው፡፡ በቅጡ ፈገግ ማለት የሚችሉ
አስተናጋጆች ፊታቸው ከማይፈታ አስተናጋጆች የበለጠ “ቲፕ”
ያገኛሉ፡፡ ዩኒቨርስቲ ሶስተኛ ዓመት ተማሪ እያለሁ አንድ ፎቶ
ኮፒ ያደርግልን የነበረ ልጅ አስታውሳለሁ፡፡ ሁልጊዜ ፊቱ
በፈገግታ የተሞላ ነው፡፡ አንድም ቀን እንኳ አዝኖ የሚያውቅ
አይመስላችሁም፡፡ እሱ ባይኖር እንኳ እስኪመጣ ጠብቀን
ኮፒ እናደርጋለን፡፡ ሌላ የሚያስተናግድ ሰው ጠፍቶ
አይደለም፤ ሌሎች ኮፒ ቤቶችም ሞልተዋል፡፡ ብዙ ኮፒ
ቤቶች ቢኖሩም ከፈገግታ ጋር የሚያስተናግዱት ግን ጥቂት
ናቸው፡፡ ፈገግታ ገበያ ያደራል፡፡ ይህንን ቅርብ ጊዜ አግኝቼው
ሌላ ሰው መስሏል፡፡ ቻይና እየተመላለሰ እንደሚነግድ
አጫወተኝ፡፡ መኪና ይዟል፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ በብዙ
መልኩ ተቀይሯል፡፡ አሁንም ግን ያልተቀየረው የፊቱ ፈገግታ
ነው፡፡
ሌላ ማሳያ አሁንም ማንሳት እንችላለን፡፡ አንዳንድ ሰዎች
ጉዳይ በማስፈፀም ረገድ የሚስተካከላቸው የለም፡፡ ሰው
ስለሚያውቁ ላይሆን ይችላል፡፡ አንድ ሁለት እንደዚህ አይነት
ሰዎችን እኔ በግሌ አውቃለሁ፡፡ በቃ እነሱ ጠይቀው ማንም
“አይቻልም” አይልም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ታዲያ
“ግንባር አለው/አላት”፣ ባስ ሲል ደግሞ “የሆነ ነገር አለው/
አላት” ማለት የተለመደ ነው፡፡ ግንባር የሌለው ማን አለ?
ሁላችንም ግንባር አለን፡፡ አንድ አንዶቻችን እንደውም በሰው
መስፈሪያ በጣም ውብ ግንባር ሁሉ ሊኖረን ይችላል፡፡
ሁላችንም የሌለን ፈገግታ ነው፡፡ እነዚህ “ድንጋይ ዳቦ ነው”
ብለው ማሳመን የሚችሉ፣ እንደው የሚያገኛቸው ሰው
በሙሉ ቀና ቀና መልስ የሚመልስላቸው ሰዎች አንዱ ትልቁ
የጋራ መለያቸው ፈገግታቸው ነው፡፡ “አይሆንም ብያለሁ
አይሆንም” ብሎ የዘጋውን “ፋይል” በፈገግታ ቁልፍ
ይከፍቱታል፡፡ እርግጥ ነው “ቁልፉ ፈገግታ ብቻ ነው”
እያልኩ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ አንዱ ዋና ቁልፍ ፈገግት
ነው፡፡
ፈገግታ፣ ደስታ እና አንጎል
ደስታየፈገግታምንጭነው፡፡በአንፃሩፈገግታም የደስታ ምንጭ
ሊሆን ይችላል፡፡ ፈገግታ አንጎላችን ውስጥ የሚገኙ
“ኒውሮኖችን” ስለሚያነቃቃ እና ደስታችንን እና ጤናችንን
ለማሻሻል ይረዳል፡፡ ፈገግታ “Neuropeptides” የሚባሉ
ጥቃቅን ሞሎኪውሎች አንጎላችን ውስጥ እንዲለቀቁ
ያደርጋል፡፡ እነዚህ ሞሎኪውሎች በሌላ በኩል አንጎል ውስጥ
የሚገኙ “ኒውሮኖች” በሚገባ መልካም ግንኙነት እንዲፈጥሩ
በማድረግ ውጥረትን (Stress) ይቀንሳል፡፡
“Neuropeptides” ስንደሰት፣ ስንከፋ፣ ስንናደድ ወዘተ
መልእክት ከአንጎላችን ወደ አካላችን ያስተላልፋሉ፡፡
ውስጣችን አስደሳች ስሜት የሚያቀጣጥሉት ዶፓሚን፣
ኢንዶርፊን፣ ሴሮቶኒን ወዘተ የሚባሉ “ኔውሮትራንስሚተርስ”
ፈገግታ ፊታችንን በሚያጥለቀልቅበት ወቅት በብዛት
ይመነጫሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ሰውነታችን ዘና ይላል፡፡ ይህ
ብቻ ሳይሆን የልብ ምታችን እና የደም ግፊታችን የተረጋጋ
እና የተስተካከለ ይሆናል፡፡
“ኢንዶርፊን” የሚባሉት “ኔውሮትራንስሚተሮች” በበኩላቸው
የህመም ማስታገሻናቸው፡፡ ህመም ሲያጋጥመን
የምንውጣቸውየህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች የጎንዮሽ
ጉዳታቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ፈገግታ
የሚያመነጨው “ኢንዶርፊን” በሌላ በኩል ግን ሙሉ ለሙሉ
ተፈጥሮአዊ የሆነ የህመም ማስታገሻ ነው፡፡ ታማሚዎችሰው
አጠገባቸው ሆኖ ሲያጫውታቸው፣ ፈገግ ሲሉ፣ ሲስቁ “አይ
ደህና ነህ እኮ! ያመመህ አትመስልም እንደውም”ብለን
የምናውቅበት ጊዜ ሁሉ ይኖራል፡፡
ፈገግታ የሚያመነጨው ሌላኛው “ኒውሮትራንስሚተር”
“ሴሮቶኒን” ፍቱን የድብርት መድኃኒት ነው፡፡ የመድኃኒት
ፋብሪካዎች የሚያመርቷቸው “Anti-depressants”
አንጎላችን ውስጥ ገብተው የሴሮቶኒንን መጠን ነው ከፍ
የሚያደርጉት፡፡ ፈገግታ በአንፃሩ ያለ ምንም የጎንዮሽ ጉዳት
እና የሀኪም ትዕዛዝ የድብርት ሰሜትን ከውስጥ ጠራርጎ
ያስወጣል፡፡
ፈገግታ እና አካላችን
ፈገግታ ውበትን ይጨምራል፡፡ ፎቶ አንሺዎች “ትንሽ
ፈገግጋ… ትንሽ… አዎ…እንደሱ” ያላሉት ማን አለ?የፈገግታን
ምስጢር ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡ ፈገግታ ፊታችሁ ላይ
ሲታይ ሰዎች በጥሩሁኔታ ያስተናግዷችኋል፡፡ ይህ ሊሆን
የቻለበት ዋና ምክንያት የጥናት ውጤቶች እንደሚጠቁሙት
“ፈገግ በምንልበት ወቅት ሰዎች ማራኪ፣ እምነት
የሚጣልበት፣ ዘና ማለት የሚችል እና ቅን ሰው ነው/ናት”
ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡
በ2011 ዓ.ም ስኮትላንድ አበርደን ዩኒቨርስቲ ውስጥ
ከፈገግታ ጋር የተያያዘ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ የጥናቱ
ተሳታፊዎች ለፈገግታ እና ውበት ደረጃ ያወጡ ሲሆን
ብዙዎቹ ዓይን ዓይንን (Eye Contact) የሚያዩ እና ፈገ
ግታ
የሚሉ ሰዎች ሰዎች የተሻለ ማራኪ እንደሆኑ ተናግረው
ነበር፡፡
ፈገግታ እና አከባቢያችን
ፈገግታ ተላላፊ ስሜት መሆኑን ቀደም ሲል ገልፀናል፡፡
ስዊድን ውስጥ በተካሄደ ሌላ ጥናት አጥኚዎች የተወሰኑ
ሰዎችን ሰብስበው ፈገግ ያለ፣ የተቆጣ፣ የፈራ እና
የተኮሳተረ ሰው ፊት ስዕል አሳይተዋቸው ነበር፡፡ ፈገግ ያሉ
ሰዎችን ስዕል እየተመለከቱ ኮስተር ለማለት ተቸግረው
ነበር፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚጠቁመው ፈገግ ያለ ፊትን
እየተመለከቱ ኮስተር ማለት ከባድ ነው፡፡ ፈገግታ ስንመለከት
እኛም መልሰን ፈገግ እንድንል የሚያደርግ የአንጎላችን ክፍል
አለ፡፡ ፈገግታ የእኛን ብቻ ሳይሆን የሌሎችን የተናደዱ፣ ያዘኑ፣
ሰዎችን ስሜት ይቀይራል፡፡ ልጅ ያላችሁ መቼም ይህ
አጋጥሟችሁ ይሆናል፡፡ አንድ በንዴት የሚያጦፍ ስራ ልጃችሁ
ይሰራና “ቆይ ባልሰራለትን” ዝታችሁ፣ ከአሁን አሁን መጣ
እያላችሁ ትጠባበቁና ቤት ሲገባ ያንን አንጀት የሚባላ
ፈገግታ ወይም ሳቁን ያሳያችኋል፡፡ እሳት የነበረው
ስሜታችሁ በአንድ ጊዜ ቀዝቅዞ ውሀ ይሆናል፡፡ ከዛ ያ ሁሉ
ዛቻ ይረሳና “ለምን እንደዚህ አደረክ አቡሽዬ” የሚል ለስላሳ
የፍቅር ቃል ከአንደበታችሁ ይወጣል፡፡
ፈገግት እንግዲህ እነዚህ እና ከእነዚህም ውጪ ሌሎች
ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል፡፡ እኛንም ሆነ በዙሪያችን የሚገኙ
ሰዎችን ያስደስታል፡፡ በመሆኑም ትንሽ ትልቅ ወዘተ የሚል
ከፋፋይ ሀሳብ ውስጥ ሳንገባ ፈገግታችንን ለራሳችንም
ለሰዎችም እንለግስ የዛሬው መልእክቴ ነው፡፡
ቸር እንሰንብት!
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
የሚሉ ሰዎች ሰዎች የተሻለ ማራኪ እንደሆኑ ተናግረው
ነበር፡፡
ፈገግታ እና አከባቢያችን
ፈገግታ ተላላፊ ስሜት መሆኑን ቀደም ሲል ገልፀናል፡፡
ስዊድን ውስጥ በተካሄደ ሌላ ጥናት አጥኚዎች የተወሰኑ
ሰዎችን ሰብስበው ፈገግ ያለ፣ የተቆጣ፣ የፈራ እና
የተኮሳተረ ሰው ፊት ስዕል አሳይተዋቸው ነበር፡፡ ፈገግ ያሉ
ሰዎችን ስዕል እየተመለከቱ ኮስተር ለማለት ተቸግረው
ነበር፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚጠቁመው ፈገግ ያለ ፊትን
እየተመለከቱ ኮስተር ማለት ከባድ ነው፡፡ ፈገግታ ስንመለከት
እኛም መልሰን ፈገግ እንድንል የሚያደርግ የአንጎላችን ክፍል
አለ፡፡ ፈገግታ የእኛን ብቻ ሳይሆን የሌሎችን የተናደዱ፣ ያዘኑ፣
ሰዎችን ስሜት ይቀይራል፡፡ ልጅ ያላችሁ መቼም ይህ
አጋጥሟችሁ ይሆናል፡፡ አንድ በንዴት የሚያጦፍ ስራ ልጃችሁ
ይሰራና “ቆይ ባልሰራለትን” ዝታችሁ፣ ከአሁን አሁን መጣ
እያላችሁ ትጠባበቁና ቤት ሲገባ ያንን አንጀት የሚባላ
ፈገግታ ወይም ሳቁን ያሳያችኋል፡፡ እሳት የነበረው
ስሜታችሁ በአንድ ጊዜ ቀዝቅዞ ውሀ ይሆናል፡፡ ከዛ ያ ሁሉ
ዛቻ ይረሳና “ለምን እንደዚህ አደረክ አቡሽዬ” የሚል ለስላሳ
የፍቅር ቃል ከአንደበታችሁ ይወጣል፡፡
ፈገግት እንግዲህ እነዚህ እና ከእነዚህም ውጪ ሌሎች
ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል፡፡ እኛንም ሆነ በዙሪያችን የሚገኙ
ሰዎችን ያስደስታል፡፡ በመሆኑም ትንሽ ትልቅ ወዘተ የሚል
ከፋፋይ ሀሳብ ውስጥ ሳንገባ ፈገግታችንን ለራሳችንም
ለሰዎችም እንለግስ የዛሬው መልእክቴ ነው፡፡
ቸር እንሰንብት!
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ሰዎች ስለሚሉት ነገር ለምን ይጨነቃሉ❓❓❓ ‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ
አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው
ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ
ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ
በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና
ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና
እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ
ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን
ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር
ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!
1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡-
እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ
እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት
ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ
አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ
ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች
ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን
እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም
አንችልም፡፡
2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች
ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን
ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ
ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም
ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ
አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች
የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን
መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት
ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡
ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ
የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::
3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:-
እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ
ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን
የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን
የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን
ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም
ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/
ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡
4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን
ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው
የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን
ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ
ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን
ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን
እንችላለን፡፡
5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ
ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች
የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ
ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡
ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው
”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም
ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል
ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/
አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን
መረዳት ይጠበቅብናል::
6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን
ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን
ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን
እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም
በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ
በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ
የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን
በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡
7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች
አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን
የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ:
ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና
ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ
በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን
መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል
ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር
ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::
8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና
ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ)
በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው
እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡
9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች
ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ
ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን
(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም)
ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ
መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን
ልናጣ እንችላለንና፡፡
10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው
ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን
ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን
ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም
ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ
ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል
ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ
ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን
ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ
ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::
በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ
ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው
ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ
ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ
በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና
ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና
እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ
ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን
ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር
ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!
1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡-
እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ
እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት
ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ
አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ
ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች
ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን
እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም
አንችልም፡፡
2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች
ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን
ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ
ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም
ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ
አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች
የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን
መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት
ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡
ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ
የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::
3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:-
እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ
ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን
የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን
የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን
ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም
ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/
ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡
4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን
ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው
የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን
ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ
ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን
ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን
እንችላለን፡፡
5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ
ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች
የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ
ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡
ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው
”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም
ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል
ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/
አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን
መረዳት ይጠበቅብናል::
6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን
ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን
ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን
እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም
በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ
በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ
የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን
በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡
7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች
አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን
የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ:
ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና
ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ
በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን
መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል
ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር
ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::
8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና
ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ)
በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው
እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡
9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች
ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ
ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን
(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም)
ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ
መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን
ልናጣ እንችላለንና፡፡
10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው
ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን
ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን
ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም
ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ
ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል
ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ
ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን
ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ
ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::
በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ
ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ስኬት ምንድን ነው❓የስኬት ቁልፍስ❓❓🔑 ስኬታማ ሕይወት እንዴት ያለ ነው? ሰዎች “ለእኔ ስኬት
ማለት ይኼ ነው ይኼ ነው” ብለው ሀሳባቸውን
በሚገልፁበት ወቅት ስምም የሆነ አገላለፅ መስማት
የተለመደ አይደለም፡፡ ለአንዱ እንደ ስኬት የሚታይ ነገር
ለሌላው እዚህ ግባ የማይባል ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡
ቤተሰብ መስርቶ፣ ልጅ ወልዶ ወዘተ ማሳደግ ለአንድ አንድ
ሰዎች ትልቅ የሕይወት ስኬት ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ
ለሌሎች ዓለምን እየተዘዋወሩ ማየት የስኬት ሁሉ ስኬት
ሊሆን ይችላል፡፡ የትኛው ሕይወት ነው ስኬታማ ሕይወት
ከሚለው ጥያቄ ጀምሮ ወደዛ በስኬት አሸብርቋል
ወደምንለው ሕይወት የሚወስደን ጎዳናስ የትኛው ነው
የሚለው ጥያቄ መሰረታዊ ጥያቄ ነው፤ የታሰበበት እና
የተጠና ምላሽም ይፈልጋል፡፡
በስነ ልቡና ባለሙያዎች ዘንድ ከሞላ ጎደል የሚያግባባው
አንዱ ሀሳብ “ስኬታማ ሕይወት ሚዛናዊ ሕይወት ነው”
የሚል ነው፡፡ ሕይወት ብዙ ፈርጆች፣ ገፆች እና ጎኖች አሏት፡፡
ሁላችንም አነሰም በዛ እዚህ ምድር ላይ በምንኖርበት ወቀት
የተለያየ ሚና እንጫወታለን፤ የተለያየ ኃላፊነት እንሸከማለን፡፡
ታዲያ እነዚህ የተለያዩ የሕይወት ግፆችን ሚዛናዊ በሆነ
መልኩ በሕይወት ወጣ ገባ መንገድ ላይ መኖር መቻል
ስኬትም የስኬት ቁልፍም ነው፡፡ ዝነኛው ሳይኮሎጂስት
ሲግመንድ ፍሮይድ “ስራ እና ፍቅር የሰው ልጅ ሕይወት
የማዕዘን ራስ ናቸው (Love and work are the corner
stone of our humans)” ይላል፡፡ በአጭሩ እነዚህን ሁለት
የሕይወት ገፆች ፍሬያማ በሆነ መልኩ መኖር መቻል
ስኬትም የስኬትም ቁልፍ ነው፡፡ አንድ ሰው በስራው እጅግ
በጣም ውጤታማ ቢሆንና ለወዳጅ ዘመዶቹ ግን የረባ እንኳን
ጊዜ መስጠት ባይችል ይህ ሰው ሕይወትን በሙላት
እየኖራት እና እየተሳካለት ነው ማለት ይቸግራል፡፡
በዙሪያችን ከሚገኙ ሰዎች ጋር ፍቅር በፍቅር ሆነን
ውጤታማ ስራ መስራት ካልቻልንም ያው ነው፡፡ ስኬት
እነዚህን ሁለት የሕይወት ገፆች የሚጠይቁትን ጊዜ መስጠት
መቻል፣ ሁለቱም የሚያሸክሙንን ኃላፊነት በአግባቡ
መወጣት፣ በሁለቱም በኩል አትራፊ መሆን መቻል ነው፡፡
ሚዛናዊ ስለመሆን ስንነጋገር ከእኛ ውጪ ያሉ የሕይወት
ገፆችን ብቻ ሳይሆን እኛ ውስጥ የሚገኙ የማንነታችንን
ክፍልፋዮች ሚዛንም ሚዛን መጠበቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
አንድ ሰው አንድ ሰው ብቻ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ውስጡ
በሚገኙት የተለያዩ የማንነት ክፍሎች ምክንያት ብዙ ሰውም
ነው ማለት ይቻላል፡፡ እነዚህ የተለያዩ የማንነ ክፍሎች
የሚፈልጉትን እና የሚያስፈልጋቸውን ያህል ቦታ
ከሰጠናቸው፣ ከሰማናቸው፣ ፍላጎታቸውን ካሟላንላቸው፣
አንዱ ከአንዱ ጋር በስምምነት እንዲኖር መፍቀድ ከቻልን
ትልቅ ስኬትም የስኬት ቁልፍም ነው፡፡ በአንፃሩ አንዱን
ወደፊት አድርገን አንዱን ወደ ኋላ ከተውን፤ አንዱ ዘወትር
እንዳሻው እንዲሆን ፈቅደን አንዱ ላይ በር ከዘጋን፤ የአንዱን
ጥሪ አድምጠን ሌላውን ጆሮ ዳባ ልበስ ካልን ውስጣችን
(አእምሯችን፣ መንፈሳችን ወዘተ) እነዚህ የማንነታችን
ክፍሎች የሚራኮቱበት የጦር አውድማ ይሆናል፡፡ በዚህ
ምክንያት ልዩ ልዩ ስነ ልቡናዊ ችግሮችም ይፀነሳሉ፤
ይወለዳሉም፡፡ ኤሪክ በርኔ የተባለ ሳይኮሎጂስት የሰው ልጅ
ሰብዕና የሶስት ልዩ ልዩ ማንነቶች ጥምረት/ቅንጅት ውጤት
ይላል፡፡ የመጀመሪያው “ወላጅ (Parent)” ነው ይላል፡፡ ይህ
ክፍል ሁልጊዜ የሚመዝን፣ የሚቆጣጠር፣ እንከን የለሽ
ለመሆን ጥረት የሚያደርገው ጥንቁቁ የሰብዕናችን ክፍል
ነው፡፡ የዚህ የሰብዕና ክፍል መሰረት ራስ ወዳድነት፣
ደህንነት (security) እና ለሚደርገው ማናቸውም ነገር በቂ
ምክንያት (justification) መስጠት መቻል ነው፡፡ ሌላኛው
የሰብዕናችን ክፍል “አዋቂ (Adult)” ይባላል፡፡ ይህ የሰብዕና
ክፍል ምክንያታዊ፣ አመዛዛኝ እና ነገሮች ተግባራዊ ሊሆኑ
የሚችሉበትን መንገድ የሚያወቅ ይሆናሉ ወይስ አይሆኑም
የሚለውን ጨምሮ መቀየስ መረዳት የሚችለው ነው፡፡
የሚያደርገውን ማናቸውንም ነገር የሚያደርግበት ምክንያት
የውስጥ እርካታ፣ የመማር እና የማወቅ ፅኑ ፍላጎት ነው፡፡
ሶስተኛውና የመጨረሻው የሰብዕናችን ክፍል “ልጅ (Child)”
የሚል ስያሜ አለው፡፡ ይህ ክፍል በአንፃሩ የፈጠራ አቅሙ
የላቀ፤ ሰፊ ምናብ ያለው፤ ማደግ፣ መበልፀግ፣ መጫወት፣
ማጥፋት ወዘተ ነፍሱ የሆነ ነው፡፡ የሚፈልገውና
የሚያደርገው ነገር መሰረቱ ደስታ፣ እርካታና ጥፋት ነው፡፡
እነዚህ ሶስት የሰብዕና ክፍሎች አንዳቸው ያለአንዳቸው
እንዳሻቸው እንዲሆኑ ብንፈቅድላቸው በጎም በጎ ያልሆነም
ውጤት ያስከትላሉ፡፡ አንዱ የሰብዕና ክፍል ብቻውን ፈላጭ
ቆራጭ ሲሆን አሉታዊ ነገሮች ሕይወታችን ውስጥ
ይበረክታሉ፤ ደስታ ይርቀናል፤ እረፍት ከአድማስ ባሻገር ያለ
ሩቅ ሀገር ይሆንብናል፤ ስኬታማ እንደሆንን አይሰማንም፤
ስኬታማ ለመሆን የምናደርገው ትግልም በግጭት የታጀበ
ይሆናል፡፡ የደስታ፣ እረፍት፣ ሰላም ወዘተ በጥቅሉ የስኬት
ምንጭ እነዚህን ሶስት የሰብዕናችንን ክፍሎች አቻችሎ፣
አስማምቶ እና ሚዛን ጠብቆ ሕይወትን መምራት መቻል
ነው፡፡ አንዱን ጥሎ ሌላውን ብቻ አንጠልጥሎ መኖር
ተገቢም ገንቢም አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ጥልቅ ተፈጥሮአዊ
ፍላጎቱ ማደግ፣ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት እና እምቅ
ችሎታውን አውጥቶ መጠቀም መቻል ነው፡፡ ይህንን ፍላጎቱን
እያሟላ ለመኖር በእነዚህ ሶስት የሰብዕና ክፍሎች መካከል
እርቅ፣ ስምምነት እና ሚዛናዊ ግንኙነት ሊኖር ይገባል፡፡
ቅርብ ጊዜ አንድ ትልቅ ፓርቲ ላፍቶ ሞል የመታደም እድሉ
ገጥሞኝ ነበር፡፡ ዙሪያዬ ይገኙ የነበሩ ወጣቶች ጨዋታና
ቡረቃ ሌላ ነው፡፡ ይዘፍናሉ፤ ይደንሳሉ፤ የራሳቸውን ግጥምና
ዜማ እዛው ጭምር እየፈጠሩ ምን አለፋችሁ በቃ
ራሳቸውንም በአካባቢያቸው የሚገኘውንም ታዳሚ ዘና
ማድረግ ቻሉ፡፡ ምሽቱ እገፋ፣ ወደ ጉሮሮ የሚንቆረቆረው
መጠጥ መጠኑ እየጨመረ ሲሄድ ግን ሁኔታዎች
መልካቸውን ቀየሩ፡፡ ቅጥ ያጣ ዳንስና ልፊያ፤ የሌላውን
መብት የሚጋፍ ድርጊት መፈፀም ተጀመረ፡፡ ያስደሰቱት ሰው
ያዝንባቸው፣ ይታዘባቸው፣ ይናደድባቸው ገባ፡፡ ይህ
እንግዲህ ሚዛንን መጠበቅ ያለመቻል ውጤት ነው፡፡
መዝናናት እና መደሰት አስፈላጊና እጅግ ጠቃሚ ነገሮች
ነው፡፡ ሁሉም ሰው ማንነት ውስጥ መቦረቅ የሚፈልግ “ልጅ”
ማንነት አለ፡፡ ይሁን እንጂ ይሄ ማንነት ሙሉ ለሙሉ ወንበሩን
ያለ ኃይ ባይ ሲቆጣጠር ከሚለማው ይልቅ የሚጠፋው
ያመዝናል፡፡ ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት ታዲያ ሀይ ባዩ፣ ከልካዩ፣
ተቆጪው፣ ቆንጣጩ “ወላጅ” ማንነታችን አብሮን ሊኖር
ይገባል፡፡ “ይበቃል፤ እንዴ! ተው አንጂ፣ ሰው እኮ እየረበሽክ
ነው፣ ኋላ ችግር ውስጥ እንዳትገባ! ነግሬሀለሁ!” ወዘተ ሊል
ይገባል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን አመዛዛኙና አዋቂው ማንነታችንም
እንዲሁ ምንጊዜም አብሮን ሊሆን ይገባል፡፡ “እየመሸ ነው
ብንሄድ ሳይሻል አይቀርም፤ የጀመርካትን ጨርስና ጓደኞችህን
ተሰናበት፤ ስትጨፍር ሌላውን ላለመርገጥ ተጠንቀቅ፤
መጠጡንም ቢሆን ከዚህ በላይ አትውሰድ፣ ረሳኸው እንዴ
ነገ እኮ ስራ ገቢ ነህ ባለፈው ዓመት እንዲህ ስትጠጣና
ስትጨፍር አድረህ የሆንከው ጉድ ትዝ ይልሀል” ወዘተ እያለ
አዛዡን እና አማፂውን ማንነታችንን የሚያግባባ፤ ምክንያታዊ
እርምጃ እንድንወስድ የሚያግዘን አዋቂ ማንነታችንን ያለ
ልዩነት ሊጠነክር ይገባል፡፡ ሶስቱም የማንነት ክፍሎች ድምፅ
ኖሯቸው እንደ ዴሞክራሲያዊ ስርዐት “check and balance”
እየተደራረጉ ሲኖር ስኬታማ መሆን ይችላል፤ ተፈጥሮአዊ
እምቅ ችሎታን አውጥቶ ለመጠቀም የሚያስችል
ማለት ይኼ ነው ይኼ ነው” ብለው ሀሳባቸውን
በሚገልፁበት ወቅት ስምም የሆነ አገላለፅ መስማት
የተለመደ አይደለም፡፡ ለአንዱ እንደ ስኬት የሚታይ ነገር
ለሌላው እዚህ ግባ የማይባል ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡
ቤተሰብ መስርቶ፣ ልጅ ወልዶ ወዘተ ማሳደግ ለአንድ አንድ
ሰዎች ትልቅ የሕይወት ስኬት ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ
ለሌሎች ዓለምን እየተዘዋወሩ ማየት የስኬት ሁሉ ስኬት
ሊሆን ይችላል፡፡ የትኛው ሕይወት ነው ስኬታማ ሕይወት
ከሚለው ጥያቄ ጀምሮ ወደዛ በስኬት አሸብርቋል
ወደምንለው ሕይወት የሚወስደን ጎዳናስ የትኛው ነው
የሚለው ጥያቄ መሰረታዊ ጥያቄ ነው፤ የታሰበበት እና
የተጠና ምላሽም ይፈልጋል፡፡
በስነ ልቡና ባለሙያዎች ዘንድ ከሞላ ጎደል የሚያግባባው
አንዱ ሀሳብ “ስኬታማ ሕይወት ሚዛናዊ ሕይወት ነው”
የሚል ነው፡፡ ሕይወት ብዙ ፈርጆች፣ ገፆች እና ጎኖች አሏት፡፡
ሁላችንም አነሰም በዛ እዚህ ምድር ላይ በምንኖርበት ወቀት
የተለያየ ሚና እንጫወታለን፤ የተለያየ ኃላፊነት እንሸከማለን፡፡
ታዲያ እነዚህ የተለያዩ የሕይወት ግፆችን ሚዛናዊ በሆነ
መልኩ በሕይወት ወጣ ገባ መንገድ ላይ መኖር መቻል
ስኬትም የስኬት ቁልፍም ነው፡፡ ዝነኛው ሳይኮሎጂስት
ሲግመንድ ፍሮይድ “ስራ እና ፍቅር የሰው ልጅ ሕይወት
የማዕዘን ራስ ናቸው (Love and work are the corner
stone of our humans)” ይላል፡፡ በአጭሩ እነዚህን ሁለት
የሕይወት ገፆች ፍሬያማ በሆነ መልኩ መኖር መቻል
ስኬትም የስኬትም ቁልፍ ነው፡፡ አንድ ሰው በስራው እጅግ
በጣም ውጤታማ ቢሆንና ለወዳጅ ዘመዶቹ ግን የረባ እንኳን
ጊዜ መስጠት ባይችል ይህ ሰው ሕይወትን በሙላት
እየኖራት እና እየተሳካለት ነው ማለት ይቸግራል፡፡
በዙሪያችን ከሚገኙ ሰዎች ጋር ፍቅር በፍቅር ሆነን
ውጤታማ ስራ መስራት ካልቻልንም ያው ነው፡፡ ስኬት
እነዚህን ሁለት የሕይወት ገፆች የሚጠይቁትን ጊዜ መስጠት
መቻል፣ ሁለቱም የሚያሸክሙንን ኃላፊነት በአግባቡ
መወጣት፣ በሁለቱም በኩል አትራፊ መሆን መቻል ነው፡፡
ሚዛናዊ ስለመሆን ስንነጋገር ከእኛ ውጪ ያሉ የሕይወት
ገፆችን ብቻ ሳይሆን እኛ ውስጥ የሚገኙ የማንነታችንን
ክፍልፋዮች ሚዛንም ሚዛን መጠበቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
አንድ ሰው አንድ ሰው ብቻ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ውስጡ
በሚገኙት የተለያዩ የማንነት ክፍሎች ምክንያት ብዙ ሰውም
ነው ማለት ይቻላል፡፡ እነዚህ የተለያዩ የማንነ ክፍሎች
የሚፈልጉትን እና የሚያስፈልጋቸውን ያህል ቦታ
ከሰጠናቸው፣ ከሰማናቸው፣ ፍላጎታቸውን ካሟላንላቸው፣
አንዱ ከአንዱ ጋር በስምምነት እንዲኖር መፍቀድ ከቻልን
ትልቅ ስኬትም የስኬት ቁልፍም ነው፡፡ በአንፃሩ አንዱን
ወደፊት አድርገን አንዱን ወደ ኋላ ከተውን፤ አንዱ ዘወትር
እንዳሻው እንዲሆን ፈቅደን አንዱ ላይ በር ከዘጋን፤ የአንዱን
ጥሪ አድምጠን ሌላውን ጆሮ ዳባ ልበስ ካልን ውስጣችን
(አእምሯችን፣ መንፈሳችን ወዘተ) እነዚህ የማንነታችን
ክፍሎች የሚራኮቱበት የጦር አውድማ ይሆናል፡፡ በዚህ
ምክንያት ልዩ ልዩ ስነ ልቡናዊ ችግሮችም ይፀነሳሉ፤
ይወለዳሉም፡፡ ኤሪክ በርኔ የተባለ ሳይኮሎጂስት የሰው ልጅ
ሰብዕና የሶስት ልዩ ልዩ ማንነቶች ጥምረት/ቅንጅት ውጤት
ይላል፡፡ የመጀመሪያው “ወላጅ (Parent)” ነው ይላል፡፡ ይህ
ክፍል ሁልጊዜ የሚመዝን፣ የሚቆጣጠር፣ እንከን የለሽ
ለመሆን ጥረት የሚያደርገው ጥንቁቁ የሰብዕናችን ክፍል
ነው፡፡ የዚህ የሰብዕና ክፍል መሰረት ራስ ወዳድነት፣
ደህንነት (security) እና ለሚደርገው ማናቸውም ነገር በቂ
ምክንያት (justification) መስጠት መቻል ነው፡፡ ሌላኛው
የሰብዕናችን ክፍል “አዋቂ (Adult)” ይባላል፡፡ ይህ የሰብዕና
ክፍል ምክንያታዊ፣ አመዛዛኝ እና ነገሮች ተግባራዊ ሊሆኑ
የሚችሉበትን መንገድ የሚያወቅ ይሆናሉ ወይስ አይሆኑም
የሚለውን ጨምሮ መቀየስ መረዳት የሚችለው ነው፡፡
የሚያደርገውን ማናቸውንም ነገር የሚያደርግበት ምክንያት
የውስጥ እርካታ፣ የመማር እና የማወቅ ፅኑ ፍላጎት ነው፡፡
ሶስተኛውና የመጨረሻው የሰብዕናችን ክፍል “ልጅ (Child)”
የሚል ስያሜ አለው፡፡ ይህ ክፍል በአንፃሩ የፈጠራ አቅሙ
የላቀ፤ ሰፊ ምናብ ያለው፤ ማደግ፣ መበልፀግ፣ መጫወት፣
ማጥፋት ወዘተ ነፍሱ የሆነ ነው፡፡ የሚፈልገውና
የሚያደርገው ነገር መሰረቱ ደስታ፣ እርካታና ጥፋት ነው፡፡
እነዚህ ሶስት የሰብዕና ክፍሎች አንዳቸው ያለአንዳቸው
እንዳሻቸው እንዲሆኑ ብንፈቅድላቸው በጎም በጎ ያልሆነም
ውጤት ያስከትላሉ፡፡ አንዱ የሰብዕና ክፍል ብቻውን ፈላጭ
ቆራጭ ሲሆን አሉታዊ ነገሮች ሕይወታችን ውስጥ
ይበረክታሉ፤ ደስታ ይርቀናል፤ እረፍት ከአድማስ ባሻገር ያለ
ሩቅ ሀገር ይሆንብናል፤ ስኬታማ እንደሆንን አይሰማንም፤
ስኬታማ ለመሆን የምናደርገው ትግልም በግጭት የታጀበ
ይሆናል፡፡ የደስታ፣ እረፍት፣ ሰላም ወዘተ በጥቅሉ የስኬት
ምንጭ እነዚህን ሶስት የሰብዕናችንን ክፍሎች አቻችሎ፣
አስማምቶ እና ሚዛን ጠብቆ ሕይወትን መምራት መቻል
ነው፡፡ አንዱን ጥሎ ሌላውን ብቻ አንጠልጥሎ መኖር
ተገቢም ገንቢም አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ጥልቅ ተፈጥሮአዊ
ፍላጎቱ ማደግ፣ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት እና እምቅ
ችሎታውን አውጥቶ መጠቀም መቻል ነው፡፡ ይህንን ፍላጎቱን
እያሟላ ለመኖር በእነዚህ ሶስት የሰብዕና ክፍሎች መካከል
እርቅ፣ ስምምነት እና ሚዛናዊ ግንኙነት ሊኖር ይገባል፡፡
ቅርብ ጊዜ አንድ ትልቅ ፓርቲ ላፍቶ ሞል የመታደም እድሉ
ገጥሞኝ ነበር፡፡ ዙሪያዬ ይገኙ የነበሩ ወጣቶች ጨዋታና
ቡረቃ ሌላ ነው፡፡ ይዘፍናሉ፤ ይደንሳሉ፤ የራሳቸውን ግጥምና
ዜማ እዛው ጭምር እየፈጠሩ ምን አለፋችሁ በቃ
ራሳቸውንም በአካባቢያቸው የሚገኘውንም ታዳሚ ዘና
ማድረግ ቻሉ፡፡ ምሽቱ እገፋ፣ ወደ ጉሮሮ የሚንቆረቆረው
መጠጥ መጠኑ እየጨመረ ሲሄድ ግን ሁኔታዎች
መልካቸውን ቀየሩ፡፡ ቅጥ ያጣ ዳንስና ልፊያ፤ የሌላውን
መብት የሚጋፍ ድርጊት መፈፀም ተጀመረ፡፡ ያስደሰቱት ሰው
ያዝንባቸው፣ ይታዘባቸው፣ ይናደድባቸው ገባ፡፡ ይህ
እንግዲህ ሚዛንን መጠበቅ ያለመቻል ውጤት ነው፡፡
መዝናናት እና መደሰት አስፈላጊና እጅግ ጠቃሚ ነገሮች
ነው፡፡ ሁሉም ሰው ማንነት ውስጥ መቦረቅ የሚፈልግ “ልጅ”
ማንነት አለ፡፡ ይሁን እንጂ ይሄ ማንነት ሙሉ ለሙሉ ወንበሩን
ያለ ኃይ ባይ ሲቆጣጠር ከሚለማው ይልቅ የሚጠፋው
ያመዝናል፡፡ ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት ታዲያ ሀይ ባዩ፣ ከልካዩ፣
ተቆጪው፣ ቆንጣጩ “ወላጅ” ማንነታችን አብሮን ሊኖር
ይገባል፡፡ “ይበቃል፤ እንዴ! ተው አንጂ፣ ሰው እኮ እየረበሽክ
ነው፣ ኋላ ችግር ውስጥ እንዳትገባ! ነግሬሀለሁ!” ወዘተ ሊል
ይገባል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን አመዛዛኙና አዋቂው ማንነታችንም
እንዲሁ ምንጊዜም አብሮን ሊሆን ይገባል፡፡ “እየመሸ ነው
ብንሄድ ሳይሻል አይቀርም፤ የጀመርካትን ጨርስና ጓደኞችህን
ተሰናበት፤ ስትጨፍር ሌላውን ላለመርገጥ ተጠንቀቅ፤
መጠጡንም ቢሆን ከዚህ በላይ አትውሰድ፣ ረሳኸው እንዴ
ነገ እኮ ስራ ገቢ ነህ ባለፈው ዓመት እንዲህ ስትጠጣና
ስትጨፍር አድረህ የሆንከው ጉድ ትዝ ይልሀል” ወዘተ እያለ
አዛዡን እና አማፂውን ማንነታችንን የሚያግባባ፤ ምክንያታዊ
እርምጃ እንድንወስድ የሚያግዘን አዋቂ ማንነታችንን ያለ
ልዩነት ሊጠነክር ይገባል፡፡ ሶስቱም የማንነት ክፍሎች ድምፅ
ኖሯቸው እንደ ዴሞክራሲያዊ ስርዐት “check and balance”
እየተደራረጉ ሲኖር ስኬታማ መሆን ይችላል፤ ተፈጥሮአዊ
እምቅ ችሎታን አውጥቶ ለመጠቀም የሚያስችል
እድል
ይፈጠራል፡፡ አንዱ አንዱን ወርሶ ዙሪያ ገባውን ሲያጥር፤
አንዱ ብቻውን አድራጊ ፈጣሪ ሲሆን ግን ውጤቱ ጥፋት፣
ደስታ አልባ መሆን፣ ለመግባባት መቸገር ወዘተ ነው፡፡
ስለዚህ እንደየሁኔታው ሶስቱንም የሰብዕና ክፍሎች ቦታ
ሰጥቶ፣ አግባብቶና አቻችሎ፣ ሚዛን ጠብቆ፤ ጨዋታና
ጭፈራ አስፈላጊ የሆነበት ቦታ ተጫውቶና ጨፍሮ፣ ቁም
ነገር የሚቀድምበት ቦታም እንዲሁ ቁም ነገረኛ ሆኖ፣ ለነገና
ከነገ ወዲያም አስቦ፣ ተጠቦ እና ተጠንቅቆ እንደ ወላጅ፣
አዋቂና ልጅ መኖር ስኬትም ነው የስኬትም ቁልፍ ነው፡፡
ቸር እንሰንብት!
@httptelegramme81biniyamin
ይፈጠራል፡፡ አንዱ አንዱን ወርሶ ዙሪያ ገባውን ሲያጥር፤
አንዱ ብቻውን አድራጊ ፈጣሪ ሲሆን ግን ውጤቱ ጥፋት፣
ደስታ አልባ መሆን፣ ለመግባባት መቸገር ወዘተ ነው፡፡
ስለዚህ እንደየሁኔታው ሶስቱንም የሰብዕና ክፍሎች ቦታ
ሰጥቶ፣ አግባብቶና አቻችሎ፣ ሚዛን ጠብቆ፤ ጨዋታና
ጭፈራ አስፈላጊ የሆነበት ቦታ ተጫውቶና ጨፍሮ፣ ቁም
ነገር የሚቀድምበት ቦታም እንዲሁ ቁም ነገረኛ ሆኖ፣ ለነገና
ከነገ ወዲያም አስቦ፣ ተጠቦ እና ተጠንቅቆ እንደ ወላጅ፣
አዋቂና ልጅ መኖር ስኬትም ነው የስኬትም ቁልፍ ነው፡፡
ቸር እንሰንብት!
@httptelegramme81biniyamin
በራስ መተማመን ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና
እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self
confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን
አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው
ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን
ነው ?? በራስ መተማመንን የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ
ፍቺዎች ሰጠውታል ሆኖም ጭብታቸው ተመሳሳይ ሆኖ
ስላገኘሁት አንዱን ብቻ ልንገራችሁ፡፡ ጎልማን በራስ
መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ
ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ
በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ
ውሳኔዎችን መስጠት ነው ይለናል፡፡ በራስ መተማመን የራስ
እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን
የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ
በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy) ድምር ውጤት
ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ
ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ
የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን
ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk
taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ
የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ
ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው
ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣
ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣
አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች
ያሉት ነው፡፡
ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው
ነገሮች ለማውራት ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ
መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን አጠንክረን
እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ በራስ
መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?? የሚከተሉትን
ነጥቦች አብረን እንያቸው…… መልካም ንባብ ተመኘሁ፡-
1. በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ
አውጣ፡- በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣
አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ
አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች
የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ
ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን
ይሸረሽሩታል፡፡
2. አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ
የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ
ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣
እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች
ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ
ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡
3. አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ
አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው
ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡
ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት
ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር
ግባ፡፡ በዚህም ከሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ፣ ስትሳሳት
ይቅርታ ለማለት እና የማይሆን ነገር ሲመጣ ወይም
ስትጠየቅ በአክብሮት አይሆንም ለማለት አትፍራ፡፡
ሁልጊዜም ከዚህ በፊት ያሳካሃቸውን ነገሮች እና
ጠንካራ ጎኖችህን አስባቸው፡፡
4. ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ
ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን
እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ
ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና
ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች
እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ ካልሆነ ደግሞ
ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ነቀፌታቸውን ተመልከት፡፡
ለዚህ እንዲረዳህ ደግሞ የተወሰነ ጊዜ በመውሰድ
እነዚህን ሰዎች እና ድርጊቶች ለይተህ አውጣ፡፡
5. ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ
በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ
የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን
ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ
አድርገው፡፡ ተጨማሪ የሆኑ ጊዜህን የምታሳልፈበትና
ስኬታማ የምትሆንበትንም ነገሮች እግረ-ሃሳብህን
ለይተህ አውጣና ትኩረትህን ስጠው፡፡
6. በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት
ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡ ከሰዎች ጋር
ባለህ መልካም፣ ግንኙነት፣ አዳማጭ በመሆንህ፣
የሰውን ችግር መረዳት በመቻልህ፣ ውጥረትን
በመቋቋም ብቃትህ ፣ እስካሁን ባሳካሀቸው ስኬቶችህ
እና በመሳሰሉት ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ በማድረግ
ኩራትህን ጨምር፡፡
7. ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ
እራስህ ውሸት በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት
አትሞክር፡፡ ስለ ራስህ መዋሸት በወቅቱ ጥሩ ስሜት
ሊፈጥርልህ ይችላል ሆኖም ግን ወዳጄ ጊዜው ባለፈ
ቁጥር እውነቱ ከዛሬ ነገ ወጣ በማለት በስጋት
እንድትኖርና ሁሌም በእራስ በመተማመን እና በልበ
ሙሉነት እንዳትቀርብ ያረግሃል፡፡
8. አድናቆትን ተቀበል፡- ሰዎች ሲያደንቁህ እየዋሹኝ ነው….
ተሳስተዋል ወይም እየሸነገሉኝ ነው አትበል፣
አድናቆታቸውን ሙሉ ለሙሉ ተቀበለው ሆኖም ግን
አድናቆትን ከልክ በላይ የምትቀበለው ከሆነ የሌለህን
ያለህ፣ ያልሆንከውን የሆንክ አድርጎ እንዲሰማህ
ሊያደርግ ይችላል ስለዚህ ጥንቃቄ አድርግ፡፡
በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት
ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን
አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት ወይም ከመሞከር
ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ
በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ
እየሞከረ ራሱን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ
መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት ሚዛናዊ አድርጎ
መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡መልካም የእረፍት ግዜ ተመኘሁ ጀማል አህመድ❤️
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self
confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን
አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው
ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን
ነው ?? በራስ መተማመንን የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ
ፍቺዎች ሰጠውታል ሆኖም ጭብታቸው ተመሳሳይ ሆኖ
ስላገኘሁት አንዱን ብቻ ልንገራችሁ፡፡ ጎልማን በራስ
መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ
ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ
በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ
ውሳኔዎችን መስጠት ነው ይለናል፡፡ በራስ መተማመን የራስ
እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን
የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ
በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy) ድምር ውጤት
ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ
ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ
የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን
ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk
taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ
የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ
ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው
ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣
ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣
አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች
ያሉት ነው፡፡
ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው
ነገሮች ለማውራት ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ
መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን አጠንክረን
እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ በራስ
መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?? የሚከተሉትን
ነጥቦች አብረን እንያቸው…… መልካም ንባብ ተመኘሁ፡-
1. በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ
አውጣ፡- በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣
አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ
አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች
የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ
ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን
ይሸረሽሩታል፡፡
2. አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ
የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ
ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣
እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች
ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ
ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡
3. አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ
አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው
ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡
ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት
ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር
ግባ፡፡ በዚህም ከሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ፣ ስትሳሳት
ይቅርታ ለማለት እና የማይሆን ነገር ሲመጣ ወይም
ስትጠየቅ በአክብሮት አይሆንም ለማለት አትፍራ፡፡
ሁልጊዜም ከዚህ በፊት ያሳካሃቸውን ነገሮች እና
ጠንካራ ጎኖችህን አስባቸው፡፡
4. ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ
ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን
እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ
ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና
ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች
እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ ካልሆነ ደግሞ
ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ነቀፌታቸውን ተመልከት፡፡
ለዚህ እንዲረዳህ ደግሞ የተወሰነ ጊዜ በመውሰድ
እነዚህን ሰዎች እና ድርጊቶች ለይተህ አውጣ፡፡
5. ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ
በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ
የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን
ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ
አድርገው፡፡ ተጨማሪ የሆኑ ጊዜህን የምታሳልፈበትና
ስኬታማ የምትሆንበትንም ነገሮች እግረ-ሃሳብህን
ለይተህ አውጣና ትኩረትህን ስጠው፡፡
6. በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት
ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡ ከሰዎች ጋር
ባለህ መልካም፣ ግንኙነት፣ አዳማጭ በመሆንህ፣
የሰውን ችግር መረዳት በመቻልህ፣ ውጥረትን
በመቋቋም ብቃትህ ፣ እስካሁን ባሳካሀቸው ስኬቶችህ
እና በመሳሰሉት ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ በማድረግ
ኩራትህን ጨምር፡፡
7. ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ
እራስህ ውሸት በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት
አትሞክር፡፡ ስለ ራስህ መዋሸት በወቅቱ ጥሩ ስሜት
ሊፈጥርልህ ይችላል ሆኖም ግን ወዳጄ ጊዜው ባለፈ
ቁጥር እውነቱ ከዛሬ ነገ ወጣ በማለት በስጋት
እንድትኖርና ሁሌም በእራስ በመተማመን እና በልበ
ሙሉነት እንዳትቀርብ ያረግሃል፡፡
8. አድናቆትን ተቀበል፡- ሰዎች ሲያደንቁህ እየዋሹኝ ነው….
ተሳስተዋል ወይም እየሸነገሉኝ ነው አትበል፣
አድናቆታቸውን ሙሉ ለሙሉ ተቀበለው ሆኖም ግን
አድናቆትን ከልክ በላይ የምትቀበለው ከሆነ የሌለህን
ያለህ፣ ያልሆንከውን የሆንክ አድርጎ እንዲሰማህ
ሊያደርግ ይችላል ስለዚህ ጥንቃቄ አድርግ፡፡
በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት
ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን
አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት ወይም ከመሞከር
ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ
በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ
እየሞከረ ራሱን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ
መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት ሚዛናዊ አድርጎ
መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡መልካም የእረፍት ግዜ ተመኘሁ ጀማል አህመድ❤️
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ሠላም ወንድሜ m እባላለሁ በጣም ተናዳጅ ነኘ ትእግስት የለኘም ምን ትመክረኛለህ ስለንዴት፥ እርእስስ ብትፅፍልን ምስጋናየ ከልብ ነው♥ እኔም አመሠግናለሁ m ጥሩ ርእስ መርጠሀል እናም በዚህ መልክ ቀርቦልሀል ፥ አንዳንድ ሰዎች ምንም የሚያበሳጭና የሚያስቆጣ ነገር
ሳይኖር በትንሹ ይናደዳሉ ወይም ይቆጣሉ፡፡ ንዴት በመጠኑ
ሲሆን የጤናማ ባህርይ መገለጫ ነው ነገር ግን መጠኑን
ሲያልፍ ግንኙነትን ከማበላሸት ባሻገር ጤናንና አእምሮአዊ
ሰላምን ይነሳል፡፡ ንዴትን በፍጹም ማስወገድ ባይቻልም
ማስታገስና ማብረድ ይቻላል፡፡ ታዲያ ንዴትን እንዴት
ማብረድ ይቻላል? እነሆ!
1. ከመናገር በፊት ማሰብ፡- በቶሎ የሚናደዱ ሰዎች
አብዛኛውን ጊዜ አንድ ነገር ከመናገራቸው በፊት ጥንቃቄ
አያደርጉም፡፡ በሚናገሩት ነገር ሰዎችን ያስቀይሙና
“ምነው አፌን በቆረጠው!” ብለው ይጸጸታሉ፡፡
2. ስሜትን አረጋግቶ እራስን መግለጽ፡- ሳያስቡ መናገር
ጸጸትን እንደሚያመጣ ሁሉ የተናደዱበትን ምክንያት
ስሜትን አብርዶ አለማስረዳትና አለመናገር በእራሱ ሌላ
ንዴት ስለሚፈጥር እራስን መግለጽ ያስፈልጋል፡፡
3. መተንፈስ፡- በቀላሉ የሚናደዱ ሰዎች የንዴት ስሜት
በሚሰማቸው ሰዓት አንድ እጃቸውን ደረታቸው ላይ
አድርገው ቢያንስ ሶስቴ ዓየር በረጅሙ በአፍንጫቸው
መሳብና በአፋቸው ማስወጣት ስሜታቸውን ለማረጋጋት
ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡
4. ንዴትን ከሚቀሰቅሱ አካባቢዎች መራቅ፡- ንዴትን
በቀላሉ መቆጣጠር አስቸጋሪ ከሆነ የንዴት ስሜት
በሚፈጠርበት ወቅት አካባቢውን ለቆ መሄድ፡፡ ከቻልክ
አካባቢህን ቀይር አካባቢህን መቀየር ካልቻልክ እራስህን
ቀይር እንደሚባለው፡፡
5. መፍትሄ መፈለግ፡- የሚያበሳጨኝና የሚያናድደኝ ነገር
ምንድን ነው ብሎ ከማሰብ ይልቅ ንዴቴን እንዴት
መቆጣጠርና ማብረድ እችላለሁ ብሎ በራስ መፍትሄ
ማፈላለግ፡፡
6. ለራስ እውቅና መስጠት፡- ንዴትን በውስጥ አምቆ
ያልተናደዱ ከመምሰል ለአእምሮ ሰላምና እርፍት
ለመስጠት እንዲያስችል “አዎ እኔ ተናዳጅ ሰው ነኝ
ቢሆንም እራሴን መቀየር እችላለሁ“ ብሎ ለራስ ዕውቅና
መስጠት፡፡
7. ቂም አለመያዝ፡- ሰዎች የፈለጉትን የሚያናድድ ነገር
በእኛ ላይ ቢያደርጉ ይቅር የሚል አእምሮ ካለንና ቂም
የማንይዝ ከሆነ ንዴታችን በቀላሉ መቆጣጠር
እንችላለን፡፡
8. እውነታውን ለማወቅ መጣር፡- ስሜትን በንዴት
ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅረጋ ብሎ ስለሁኔታው
ማጤንና የሰከነ ውይይት ለማድረግ መሞከር፡፡
9. ትዕግስትን መለማመድ፡- የመጨረሻዋን የንዴት ጣሪያ
ላለመንካት ትዕግስተኛ መሆን፡፡ ይህንን ለማድረግ
ዘውትር ትዕግስተኝነትን መለማመድ፡፡
10. የሌሎች ዕርዳታን መሻት፡- አንዳንድ ጊዜ ለዘመናት
አብሮ የቆየን ንዴት በእራስ መንገድ ብቻ ለማብረድ
መሞከር አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሌሎች ሊያግዙን
የሚችሉ ሰዎችን ዕርዳታ መጠየቅ ትልቅ ብልሃት ነው፡፡
@httptelegramme81biniyamin
ሳይኖር በትንሹ ይናደዳሉ ወይም ይቆጣሉ፡፡ ንዴት በመጠኑ
ሲሆን የጤናማ ባህርይ መገለጫ ነው ነገር ግን መጠኑን
ሲያልፍ ግንኙነትን ከማበላሸት ባሻገር ጤናንና አእምሮአዊ
ሰላምን ይነሳል፡፡ ንዴትን በፍጹም ማስወገድ ባይቻልም
ማስታገስና ማብረድ ይቻላል፡፡ ታዲያ ንዴትን እንዴት
ማብረድ ይቻላል? እነሆ!
1. ከመናገር በፊት ማሰብ፡- በቶሎ የሚናደዱ ሰዎች
አብዛኛውን ጊዜ አንድ ነገር ከመናገራቸው በፊት ጥንቃቄ
አያደርጉም፡፡ በሚናገሩት ነገር ሰዎችን ያስቀይሙና
“ምነው አፌን በቆረጠው!” ብለው ይጸጸታሉ፡፡
2. ስሜትን አረጋግቶ እራስን መግለጽ፡- ሳያስቡ መናገር
ጸጸትን እንደሚያመጣ ሁሉ የተናደዱበትን ምክንያት
ስሜትን አብርዶ አለማስረዳትና አለመናገር በእራሱ ሌላ
ንዴት ስለሚፈጥር እራስን መግለጽ ያስፈልጋል፡፡
3. መተንፈስ፡- በቀላሉ የሚናደዱ ሰዎች የንዴት ስሜት
በሚሰማቸው ሰዓት አንድ እጃቸውን ደረታቸው ላይ
አድርገው ቢያንስ ሶስቴ ዓየር በረጅሙ በአፍንጫቸው
መሳብና በአፋቸው ማስወጣት ስሜታቸውን ለማረጋጋት
ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡
4. ንዴትን ከሚቀሰቅሱ አካባቢዎች መራቅ፡- ንዴትን
በቀላሉ መቆጣጠር አስቸጋሪ ከሆነ የንዴት ስሜት
በሚፈጠርበት ወቅት አካባቢውን ለቆ መሄድ፡፡ ከቻልክ
አካባቢህን ቀይር አካባቢህን መቀየር ካልቻልክ እራስህን
ቀይር እንደሚባለው፡፡
5. መፍትሄ መፈለግ፡- የሚያበሳጨኝና የሚያናድደኝ ነገር
ምንድን ነው ብሎ ከማሰብ ይልቅ ንዴቴን እንዴት
መቆጣጠርና ማብረድ እችላለሁ ብሎ በራስ መፍትሄ
ማፈላለግ፡፡
6. ለራስ እውቅና መስጠት፡- ንዴትን በውስጥ አምቆ
ያልተናደዱ ከመምሰል ለአእምሮ ሰላምና እርፍት
ለመስጠት እንዲያስችል “አዎ እኔ ተናዳጅ ሰው ነኝ
ቢሆንም እራሴን መቀየር እችላለሁ“ ብሎ ለራስ ዕውቅና
መስጠት፡፡
7. ቂም አለመያዝ፡- ሰዎች የፈለጉትን የሚያናድድ ነገር
በእኛ ላይ ቢያደርጉ ይቅር የሚል አእምሮ ካለንና ቂም
የማንይዝ ከሆነ ንዴታችን በቀላሉ መቆጣጠር
እንችላለን፡፡
8. እውነታውን ለማወቅ መጣር፡- ስሜትን በንዴት
ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅረጋ ብሎ ስለሁኔታው
ማጤንና የሰከነ ውይይት ለማድረግ መሞከር፡፡
9. ትዕግስትን መለማመድ፡- የመጨረሻዋን የንዴት ጣሪያ
ላለመንካት ትዕግስተኛ መሆን፡፡ ይህንን ለማድረግ
ዘውትር ትዕግስተኝነትን መለማመድ፡፡
10. የሌሎች ዕርዳታን መሻት፡- አንዳንድ ጊዜ ለዘመናት
አብሮ የቆየን ንዴት በእራስ መንገድ ብቻ ለማብረድ
መሞከር አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሌሎች ሊያግዙን
የሚችሉ ሰዎችን ዕርዳታ መጠየቅ ትልቅ ብልሃት ነው፡፡
@httptelegramme81biniyamin
ሀሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ለማድረግ የሚረዱ፥ ቀላል ስልቶች🤔 ከኔ ጋር ናቹሁ ❓እስኪ አንብቡት ሺ አመት አላወራ😳
“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት
ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡
ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ
መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ
ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ
ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ
ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው
የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡
ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት
ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን
ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም
ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡
ቅለት
ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና
አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ
ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ
ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት
ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም
እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ
የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን
ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ
ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡
ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ
“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ
ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን
ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ
ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን
ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡
በራስ መተማመን
አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ
ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን
ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ
ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት
ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ
የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ
የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ
ጉልበት አላቸው፡፡
በሌሎች ዓይን ማየት
ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ
አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣
ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ
ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ
የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ
ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት
ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ
የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን
እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን
የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል
ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ
መቼም አይጠፋም፡፡
ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ
መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን
ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ
መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን
ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው
የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ
የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን
ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ
ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም
ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡
እጥረትን መፍጠር
ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣
የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ
ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ
ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው
ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣
በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም
እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡
ዝግጅት
ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት
ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል
ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ
መተማመናችንንም ይገነባል፡፡
መልቀም የረፍት ቀን
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት
ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡
ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ
መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ
ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ
ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ
ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው
የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡
ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት
ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን
ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም
ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡
ቅለት
ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና
አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ
ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ
ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት
ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም
እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ
የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን
ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ
ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡
ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ
“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ
ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን
ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ
ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን
ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡
በራስ መተማመን
አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ
ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን
ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ
ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት
ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ
የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ
የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ
ጉልበት አላቸው፡፡
በሌሎች ዓይን ማየት
ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ
አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣
ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ
ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ
የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ
ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት
ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ
የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን
እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን
የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል
ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ
መቼም አይጠፋም፡፡
ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ
መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን
ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ
መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን
ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው
የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ
የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን
ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ
ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም
ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡
እጥረትን መፍጠር
ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣
የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ
ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ
ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው
ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣
በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም
እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡
ዝግጅት
ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት
ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል
ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ
መተማመናችንንም ይገነባል፡፡
መልቀም የረፍት ቀን
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
እራስን የማወቅ እና የመምራት ክህሎት👇 የሚከተሉት ነጥቦች አንድ ራሱን የሚያውቅ ሰው ሊኖሩት
የሚገባ ባህሪያትን ያሳዩናል::
ደካማና ጠንካራ ጎኑን ለይቶ ያውቃል
ለራሱ ህይወት ኃላፊነት ይወስዳል
ስለራሱ ያለው አመለካከት አዎንታዊ ነው
በራሱ ይተማመናል
ራሱን ለማሻሻል ይጥራል (በኢኮኖሚ በማኅበራዊ…)
የሚሄድበትን መንገድ ያውቃል/ራዕይ አለው
ለአላማው መሳካት መስዋትነትን ይከፍላል
ሌሎችን ለመሆን አይጥርም/በራሱ ማንነት ይተማመናል
ራሱን ያከብራል
የራስ ህይወት መሪ ለመሆን ደግሞ የሚከተሉት ሶስት
ነጥቦች አጋዥነት ይኖራቸዋል
ሀ. ለራስ ህይወት ኃላፊነት መውሰድ
ስለኛነታችን ልናውቃቸው የሚገቡ እውነታዎች
በዓለም ላይ አንተን የሚመስል ማንም እንደሌለ
በዓለም ላይ መኖራችን ለአንድ አላማ መሆኑ
ሃሳባችንን፤ ምኞታችንን፤ አመለካከታችንን መቆጣጠር
የሚያስችል ሃይል እንዳለን
የዛሬ አስተሳሰብ ለነገ ህይወታችን መሰረት እንደሆነ
የራስን ማንነት ለመፈተሽ የሚረዱ ጥያቄዎች
ጠንካራ ጎኔ ምንድን ነው?
ደካማ ጎኔ ምንድን ነው?
ለራሴ ያለኝ አመለካከት ምን ይመስላል?
ለህይወት ያለኝ አመለካከት ምን ይመስላል?
ለ. ዓላማ ያለው ህይወት መምራት
ልንሰራውና ልንሆን የምንፈልገውን ነገር ለይተን እንድናቅ
ይረዳና
የህይወት አስቸጋሪ ሁኔታዎች በድል የምንወጣበትን
ኃይል ይሰጠናል
ጤናማና ውጤታማ ሰዎች እንድንሆን ይረዳናል
ዓላማ ያለው ህይወት ለመምራት ምን ማድረግ
ይጠበቅብናል?
ዓላማ ያለው ህይወት ለመምራት ራስን ማዘጋጀት
እየኖርን ካለነው የተሻለ ህይወት መኖር እንዳለብን
ማመን
በመጀመሪያ በቀላሉ ልንተገብረው የምንችለውን ነገር
በማቀድና በመተግበር በዕቅድ መመራት/መሄድ
ከጎጂ ልምዶችና አስተሳሰቦች ራስን ማውጣት
ለራሳችን የምንገባውን ቃል ማክበር
ሽንፈትን በጸጋ አለመቀበል ይልቁንም ካለፈው
ስህተታችን በመማር የተሻለ ነገርን ማለም
በዓላማ መመራት ስንጀምር ሊያጋጥሙን የሚችሉ
እንቅፋቶች
ከራሳችን/ከውስጣችን የሚመነጭ
በአቅራቢያችን ካሉ ሰዎች የሚነሳ
የአካባቢያዊ ሁኔታዎች አለመመቸት🌒 መልካም ምሽት🌹
ሼር
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
የሚገባ ባህሪያትን ያሳዩናል::
ደካማና ጠንካራ ጎኑን ለይቶ ያውቃል
ለራሱ ህይወት ኃላፊነት ይወስዳል
ስለራሱ ያለው አመለካከት አዎንታዊ ነው
በራሱ ይተማመናል
ራሱን ለማሻሻል ይጥራል (በኢኮኖሚ በማኅበራዊ…)
የሚሄድበትን መንገድ ያውቃል/ራዕይ አለው
ለአላማው መሳካት መስዋትነትን ይከፍላል
ሌሎችን ለመሆን አይጥርም/በራሱ ማንነት ይተማመናል
ራሱን ያከብራል
የራስ ህይወት መሪ ለመሆን ደግሞ የሚከተሉት ሶስት
ነጥቦች አጋዥነት ይኖራቸዋል
ሀ. ለራስ ህይወት ኃላፊነት መውሰድ
ስለኛነታችን ልናውቃቸው የሚገቡ እውነታዎች
በዓለም ላይ አንተን የሚመስል ማንም እንደሌለ
በዓለም ላይ መኖራችን ለአንድ አላማ መሆኑ
ሃሳባችንን፤ ምኞታችንን፤ አመለካከታችንን መቆጣጠር
የሚያስችል ሃይል እንዳለን
የዛሬ አስተሳሰብ ለነገ ህይወታችን መሰረት እንደሆነ
የራስን ማንነት ለመፈተሽ የሚረዱ ጥያቄዎች
ጠንካራ ጎኔ ምንድን ነው?
ደካማ ጎኔ ምንድን ነው?
ለራሴ ያለኝ አመለካከት ምን ይመስላል?
ለህይወት ያለኝ አመለካከት ምን ይመስላል?
ለ. ዓላማ ያለው ህይወት መምራት
ልንሰራውና ልንሆን የምንፈልገውን ነገር ለይተን እንድናቅ
ይረዳና
የህይወት አስቸጋሪ ሁኔታዎች በድል የምንወጣበትን
ኃይል ይሰጠናል
ጤናማና ውጤታማ ሰዎች እንድንሆን ይረዳናል
ዓላማ ያለው ህይወት ለመምራት ምን ማድረግ
ይጠበቅብናል?
ዓላማ ያለው ህይወት ለመምራት ራስን ማዘጋጀት
እየኖርን ካለነው የተሻለ ህይወት መኖር እንዳለብን
ማመን
በመጀመሪያ በቀላሉ ልንተገብረው የምንችለውን ነገር
በማቀድና በመተግበር በዕቅድ መመራት/መሄድ
ከጎጂ ልምዶችና አስተሳሰቦች ራስን ማውጣት
ለራሳችን የምንገባውን ቃል ማክበር
ሽንፈትን በጸጋ አለመቀበል ይልቁንም ካለፈው
ስህተታችን በመማር የተሻለ ነገርን ማለም
በዓላማ መመራት ስንጀምር ሊያጋጥሙን የሚችሉ
እንቅፋቶች
ከራሳችን/ከውስጣችን የሚመነጭ
በአቅራቢያችን ካሉ ሰዎች የሚነሳ
የአካባቢያዊ ሁኔታዎች አለመመቸት🌒 መልካም ምሽት🌹
ሼር
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
💫እውነተኛ ፍቅር ማስመሠልን ሳይሆን መተግበርን ትሽለች✿ እስኪ አሁን ደግሞ በእዉነተኛ ታሪክ ላይ
የተመሰረተ ነጠመኝ ላካፍላችሁ፡፡
:
❀︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵❀
፡
አንድ ሰውዬ በአቅራቢያው ከሚገኙ በእድሜ ጠና ካሉ
አዛውንት ዘንድ ይሄድና ጋሼ ወደ እርሶ የመጣሁት በትዳሬ ችግር
ስለገጠመኝ እንዲረዱኝ ፈልጌ ነዉ አላቸው፡፡
፡
እሳቸውም እስቲ ምን ገጠመህ ንገረኝ አሉት።
፡
ሰውዬውም እንዲህ አላቸው፦
፡
➊.እኔ ከባለቤቴ ትዳር ከያዝን እነሆ ➐ ዓመታት አስቆጥረናል፡፡
:
➋.በዚህ መሃል ሁለት ልጆችም አፍረተናል፡፡
:
➌.ነገር ግን እኔና ባለቤቴ በአሁኑ ሰዓት ጥሩ ግንኙነትና ፍቅር
የለንም፡፡
:
➍.ሰላማችን አጥተናል፣
:
➎.ትዳራችንም ልናፈርስ ተዘጋጅተናል፣
፡
➏.ከሁሉም በላይ የሚያሳስበኝ ግን ልጆቼ ናቸዉ፡፡
፡
➐.ስለዚህ ከባለቤቴ ጋር አብረን እንድንቀጥል ምን ይመክሩኛል?”
ብሎ ጠየቃቸዉ፡፡
:
አዛውንቱም በአንዲት ቃል እንዲህ ሲል መለሰሉት “አፍቅራት”
አሉት፡፡
፡
ሰዉየዉ ወድያዉኑ "እንዴት ላፈቅራት እችላለሁ? እባክዎ
ይርዱኝ" ብሎ አዛውንቱን በመጠየቅ ወሬውን አያይዞ ቀጠለ....
:
➋.እሚገርምዎት ነገር ትዳር ሳንመሰርት በጣም ነበር
የምንዋደደዉ፡፡
፡
➌.እስዋ አጠገቤ ከሌለች በጣም ይጨንቀኝ ነበር፡፡ እሰዋም
እንዲሁ፡፡
:
➍.እስዋ ከሌለች ምግብ ሁላ አይበላልኝም ነበር፡፡
:
➎.ትዳር ከመሰረተንና ልጆች ከወለድን በሃል ግን ተደባብረናል፡፡
:
➏.ስለዚህ ምን ላርግ ነዉ እምልዎት፡፡”
፡
አዛውንቱም፦ አሁንም እነደበፊቱ በአንዲት ቃል “አፍቅራት”
ብሎ መለሰሉት፡፡
፡
ሰዉየዉ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እያሳየ “አባ እንግዲህ
እሚረዱኝ መስሎኝ ነበር ነገር ግን አይደሉም፡፡” አላቸዉ።
፡
☞አሁን አዛውንቱ በተረጋጋ መንፈስ እንዲህ ብሎ መለሰሉት፡፡
:
“በትክክል ተረድቼህ ከሆነ እያልከኝ ያለሀዉ በፊት አፈቅራት
ነበር ነገር ግን አሁን የፍቅር ስሜት የለኝም፤ እስዋም ስሜት
የላትም እያልከኝ ነዉ?” ብሎ ጠየቁት፡፡
፡
ሰዉየዉ በፍጥነት “አዎ አባ....በፊት የፍቅር ስሜት ነበረኝ፡፡
አሁን ግን የለኝም፡፡ እሳዋም ቢሆን እንዲሁ፡፡” ብሎ መለስላቸው፡፡
፡
አዛውንቱም ቀበል አደረጉና እንዲህ አሉት፦
፡
➊.“አንተ እያልከዉ ባለሀዉ መሰረት የፍቅር ትርጉም ስሜት ብቻ
ቢሆን ኑሮ 95% ያህል በአለም ላይ ትዳር እሚባል አይኖርም ነበር፡፡
፡
➋.ነገር ግን ፍቅር እንደዛ አይደለም፡፡
:
➌.እስኪ አሁንም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ "በአለም ላይ የፍቅር
ተምሳሌት የሚባሉ ንገረኝ" አሉት።
፡
ሰዉየዉ ትንሽ ካሰበ ቧሃላ ፈገግ አለና “እናት፡፡ እናት ፍቅር ናት
ይባላል” አለዉ፡፡
:
አዛውንቱም ቀበል አደረጉና ፈገግ እያሉ መልሶ “በጣም
ጎበዝ፣ ትክክል ብለሃል።
:
➊.እንዳልከዉ እናት የፍቅር ተምሳሌት ናት፡፡
:
➋.እናት ታድያ ለልጆችዋ ፍቅር እምታሳያቸዉ በተግባር እንጂ
በስሜት ብቻ አይደለም፡፡ ለምሳሌ፦
፡
►ልጆችዋ ሲታረዙባት ከየትም አምጥታ ታለብሳችዋለች እንጂ
ልጆቼ ታረዙ ብላ ዝም አትልም፡፡
:
►ልጆችዋ ሲራቡ ከየትም አምጥታ ትመግባችዋለች እንጂ ልጆቼ
ተራቡ ብላ ዝም አትልም፡፡
:
➌.ስለዚህ ልጄ አንተ እንዳልከዉ ፍቅር ስሜት ሳይሆን ተግባር
ነዉ፡፡
:
➍.ፍቅር ለፍጡራን የተሰጠ ውድ ገጸበረከት ሲሆን ፍቅርና
ማፍቀርን መቀበል ደግሞ የገጸበረከቱ በጽናት ፍጹም ታማኝ መሆን
ነው።
:
➎.ስለዚህ አንተም ሚስቴን አፈቅራታለው የምትል ከሆነ፦
:
√አሁኑኑ ሂድና የምትልህን አዳምጣት፣
፡
√አግዛት፣
፡
√ከጎኑዋ ሁን፣
፡
√ቅርህን በተግባር አሳያት፡፡” አሉት።
፡
ሰውዬውም የአዛውንቱን ማብራሪያ ካደመጠ ቧሃላ ስለፍቅር
ምንነት ለመጀመርያ ጊዜ ገባዉ፡፡ ወድያዉኑ ሳይዉል ሳያድር ሂዶ
ከሚስቱ ጋር ታረቀ ይባላል፡፡
:
❀︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵❀
:
# አዎን ወዳጆቼ፥
:
☞በእርግጥም እውነተኛ ፍቅር ማስመሰልን ሳይሆን መተግበርን
ትሻለች።
:
➊.ታዲያ እናንተስ ፍቅራችሁ እንዴት ነዉ እምትገልፁት?
:
➋.ፍቅራችሁ እምትገልፁት በተግባር ወይስ በስሜት?
:
➌.ጥሩ ትዳርና ፍቅር አላችሁ? ካላችሁ አምላክ ጨምሮ
ይበርካላችሁ፡፡
:
➎.ትዳርዎ ወይም ፍቅረኛዎ ላይ ችግር ካለዎት ወይንም ለማፍረስ
እያሰቡ ከሆነ ግን መልካም አይደለምና አሁኑኑ ሃሳብዎን ይቀይሩና
እንዲታረቁ በአላህ ስም ወይም በምያምኑት አምላክ ስም
እለምነዎታለሁ!
:
➏.በሌላ ጊዜ አንድ ተጨማሪ ለትዳር መፍረስ ምክንያት የሆኑትን
ለማቅረብ እሞክራለው! አመሰግናለው፡፡
፡
# አምላክ ከወረት የጸዳ ንጹሕ ፍቅር ለሁላችንም ያድለን!!(አሜን)
:
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
:
"በፍቅር ያቆየን"
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
የተመሰረተ ነጠመኝ ላካፍላችሁ፡፡
:
❀︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵❀
፡
አንድ ሰውዬ በአቅራቢያው ከሚገኙ በእድሜ ጠና ካሉ
አዛውንት ዘንድ ይሄድና ጋሼ ወደ እርሶ የመጣሁት በትዳሬ ችግር
ስለገጠመኝ እንዲረዱኝ ፈልጌ ነዉ አላቸው፡፡
፡
እሳቸውም እስቲ ምን ገጠመህ ንገረኝ አሉት።
፡
ሰውዬውም እንዲህ አላቸው፦
፡
➊.እኔ ከባለቤቴ ትዳር ከያዝን እነሆ ➐ ዓመታት አስቆጥረናል፡፡
:
➋.በዚህ መሃል ሁለት ልጆችም አፍረተናል፡፡
:
➌.ነገር ግን እኔና ባለቤቴ በአሁኑ ሰዓት ጥሩ ግንኙነትና ፍቅር
የለንም፡፡
:
➍.ሰላማችን አጥተናል፣
:
➎.ትዳራችንም ልናፈርስ ተዘጋጅተናል፣
፡
➏.ከሁሉም በላይ የሚያሳስበኝ ግን ልጆቼ ናቸዉ፡፡
፡
➐.ስለዚህ ከባለቤቴ ጋር አብረን እንድንቀጥል ምን ይመክሩኛል?”
ብሎ ጠየቃቸዉ፡፡
:
አዛውንቱም በአንዲት ቃል እንዲህ ሲል መለሰሉት “አፍቅራት”
አሉት፡፡
፡
ሰዉየዉ ወድያዉኑ "እንዴት ላፈቅራት እችላለሁ? እባክዎ
ይርዱኝ" ብሎ አዛውንቱን በመጠየቅ ወሬውን አያይዞ ቀጠለ....
:
➋.እሚገርምዎት ነገር ትዳር ሳንመሰርት በጣም ነበር
የምንዋደደዉ፡፡
፡
➌.እስዋ አጠገቤ ከሌለች በጣም ይጨንቀኝ ነበር፡፡ እሰዋም
እንዲሁ፡፡
:
➍.እስዋ ከሌለች ምግብ ሁላ አይበላልኝም ነበር፡፡
:
➎.ትዳር ከመሰረተንና ልጆች ከወለድን በሃል ግን ተደባብረናል፡፡
:
➏.ስለዚህ ምን ላርግ ነዉ እምልዎት፡፡”
፡
አዛውንቱም፦ አሁንም እነደበፊቱ በአንዲት ቃል “አፍቅራት”
ብሎ መለሰሉት፡፡
፡
ሰዉየዉ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እያሳየ “አባ እንግዲህ
እሚረዱኝ መስሎኝ ነበር ነገር ግን አይደሉም፡፡” አላቸዉ።
፡
☞አሁን አዛውንቱ በተረጋጋ መንፈስ እንዲህ ብሎ መለሰሉት፡፡
:
“በትክክል ተረድቼህ ከሆነ እያልከኝ ያለሀዉ በፊት አፈቅራት
ነበር ነገር ግን አሁን የፍቅር ስሜት የለኝም፤ እስዋም ስሜት
የላትም እያልከኝ ነዉ?” ብሎ ጠየቁት፡፡
፡
ሰዉየዉ በፍጥነት “አዎ አባ....በፊት የፍቅር ስሜት ነበረኝ፡፡
አሁን ግን የለኝም፡፡ እሳዋም ቢሆን እንዲሁ፡፡” ብሎ መለስላቸው፡፡
፡
አዛውንቱም ቀበል አደረጉና እንዲህ አሉት፦
፡
➊.“አንተ እያልከዉ ባለሀዉ መሰረት የፍቅር ትርጉም ስሜት ብቻ
ቢሆን ኑሮ 95% ያህል በአለም ላይ ትዳር እሚባል አይኖርም ነበር፡፡
፡
➋.ነገር ግን ፍቅር እንደዛ አይደለም፡፡
:
➌.እስኪ አሁንም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ "በአለም ላይ የፍቅር
ተምሳሌት የሚባሉ ንገረኝ" አሉት።
፡
ሰዉየዉ ትንሽ ካሰበ ቧሃላ ፈገግ አለና “እናት፡፡ እናት ፍቅር ናት
ይባላል” አለዉ፡፡
:
አዛውንቱም ቀበል አደረጉና ፈገግ እያሉ መልሶ “በጣም
ጎበዝ፣ ትክክል ብለሃል።
:
➊.እንዳልከዉ እናት የፍቅር ተምሳሌት ናት፡፡
:
➋.እናት ታድያ ለልጆችዋ ፍቅር እምታሳያቸዉ በተግባር እንጂ
በስሜት ብቻ አይደለም፡፡ ለምሳሌ፦
፡
►ልጆችዋ ሲታረዙባት ከየትም አምጥታ ታለብሳችዋለች እንጂ
ልጆቼ ታረዙ ብላ ዝም አትልም፡፡
:
►ልጆችዋ ሲራቡ ከየትም አምጥታ ትመግባችዋለች እንጂ ልጆቼ
ተራቡ ብላ ዝም አትልም፡፡
:
➌.ስለዚህ ልጄ አንተ እንዳልከዉ ፍቅር ስሜት ሳይሆን ተግባር
ነዉ፡፡
:
➍.ፍቅር ለፍጡራን የተሰጠ ውድ ገጸበረከት ሲሆን ፍቅርና
ማፍቀርን መቀበል ደግሞ የገጸበረከቱ በጽናት ፍጹም ታማኝ መሆን
ነው።
:
➎.ስለዚህ አንተም ሚስቴን አፈቅራታለው የምትል ከሆነ፦
:
√አሁኑኑ ሂድና የምትልህን አዳምጣት፣
፡
√አግዛት፣
፡
√ከጎኑዋ ሁን፣
፡
√ቅርህን በተግባር አሳያት፡፡” አሉት።
፡
ሰውዬውም የአዛውንቱን ማብራሪያ ካደመጠ ቧሃላ ስለፍቅር
ምንነት ለመጀመርያ ጊዜ ገባዉ፡፡ ወድያዉኑ ሳይዉል ሳያድር ሂዶ
ከሚስቱ ጋር ታረቀ ይባላል፡፡
:
❀︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵❀
:
# አዎን ወዳጆቼ፥
:
☞በእርግጥም እውነተኛ ፍቅር ማስመሰልን ሳይሆን መተግበርን
ትሻለች።
:
➊.ታዲያ እናንተስ ፍቅራችሁ እንዴት ነዉ እምትገልፁት?
:
➋.ፍቅራችሁ እምትገልፁት በተግባር ወይስ በስሜት?
:
➌.ጥሩ ትዳርና ፍቅር አላችሁ? ካላችሁ አምላክ ጨምሮ
ይበርካላችሁ፡፡
:
➎.ትዳርዎ ወይም ፍቅረኛዎ ላይ ችግር ካለዎት ወይንም ለማፍረስ
እያሰቡ ከሆነ ግን መልካም አይደለምና አሁኑኑ ሃሳብዎን ይቀይሩና
እንዲታረቁ በአላህ ስም ወይም በምያምኑት አምላክ ስም
እለምነዎታለሁ!
:
➏.በሌላ ጊዜ አንድ ተጨማሪ ለትዳር መፍረስ ምክንያት የሆኑትን
ለማቅረብ እሞክራለው! አመሰግናለው፡፡
፡
# አምላክ ከወረት የጸዳ ንጹሕ ፍቅር ለሁላችንም ያድለን!!(አሜን)
:
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
:
"በፍቅር ያቆየን"
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ፍቅር ምክንያቱ አይታወቅም♥ በትዳር መካከል የረዘመና መቋጫው የማይታወቅ
ጭቅጭቅ የሚፈጠር ከሆነ ምንም እንኩዋን
የተመሰረተው ትዳር ለረዥም ጊዜ እንደሚዘልቅ
ቢታሰብም ጭቅጭቁ እየዋለ እያደር ግን ትዳርን
አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ አስቀድሞውኑ ልብ
ሊባል ይገባል፡፡ ችግሮችን ቀለል አድርጎ ማየት፡-
በባለትዳሮች ዘንድ ለሚነሱ ጥቃቅን ለሚመስሉ
ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ነገ ዛሬ ማለት
እና ነገሮችን በአናሳነት በመፈረጅ መፍትሔውን
በፍጥነት አለመፈለግ አልፎ አልፎ ያጋጥማል፡፡
በሌላም በኩል ለተነሱ ነገሮች መፍትሔ
ለመስጠት በሚል አንዳቸው ከአንዳቸው ለጊዜው
እራቅ ወደ አለ ቦታ ዞር ማለትን የሚመርጡበት
ሁኔታ ይስተ ዋላል፡፡ ይህ ክስተት ምናልባት ነገሩን
በስፋት ለማሰብ እና እራስን ለማረጋጋት ለጊዜው
ይረዳ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለተነሳው
ጭቅጭቅ መፍትሔ የሚሻው ሌላኛው ወገን
በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ባለመሰጠቱ ለምን ይህ ሆነ
በሚል ቁጭትና ንዴትን እንዲያብ ሰለስል
እንዲሁም ወደከፋ ውሳኔ እንዲሄድ ሊያደርገው
ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በባልና ሚስቱ መካከል
ለተነሱ ጭቅጭቆች ወይንም አለመግባባቶች
መፍትሔ ተሰጥ ቶአቸው ያልተቋጩ ነገሮች
የተረሱ ቢመስሉም እንኩዋን ውለው አድረው ግን
ከሌላ ነገር ጋር ተያይዘው መነሳታቸው ስለማይቀር
ስር ለሰደደ መቃቃር ሊዳርግ ይችላል፡፡ ከላይ
ለተጠቀሱት አጋጣሚዎች በመፍትሔነት
የተጠቆሙት ባልና ሚስቱ አስቀድሞውን
ጋብቻ ከመመስረታቸው በፊት ነገሮችን በምን
መንገድ ሊያስተናግዱ እንደሚገባቸው ፕላን
ሊያደርጉ እንደሚገባቸው ነው ፡፡ በገንዘብ ጉዳይ...
ቤተሰብን በማስተዳደር ...ዘመድ አዝማድ
...ጉዋደኛን በምን መልክ ማስተናገድ እንደሚገባ
እንዲ ሁም ማንን መርዳት ...ማንን አለመርዳት...
የመሳሰሉት ሁሉ ለውይይት መቅረብ የሚገባቸው
እና ለተጋቢዎቹ ቀላል የማይባሉ ናቸው፡፡ ትዳር
ሲመሰረት ንብረት ስለማፍራት ፣ ኃብት
ስለማከማቸት ፣ልጅ ስለመውለድ የመሳሰሉት
ሲታቀዱ በባህርይ በኩል ያለው ነገር ግን ብዙ ጊዜ
ቸል የሚባል ነው፡፡ ነገር ግን ወደታቀደው ግብ
የሚያደርሰው በባህርይ መግባባት ሲኖር መሆኑ
ሊዘነጋ እንደማይገባው ምሁራኑ ያስረዳሉ፡፡ አቋምን
አለማስተካከልና ውበትን አለመጠበቅ፡-በትዳር
መካከል አለመግባባቶችን ሊፈጥሩ ከሚችሉ
መካከል የራስን አቋምና ውበትን
አለማስተካከል አንዱ ነው፡፡ ሰዎች በትዳር አለም
ለረዥም ጊዜያት ሲቆዩ አንዳቸው አንዳቸውን
በድርጊታቸው ፣በአለባበሳቸው ፣በአቋማቸው
ተጉዋዳኛቸውን ለመማረክ ሲጥሩ ሌላኛው ወገን
ደግሞ ከነጭርሱም ለራሳቸው ትኩረት ላይሰጡ
ይችላሉ፡፡ እንደተገኝ ለብሶ መውጣት፣ የገላን
ንጽህና አለመጠበቅ፣ የጸጉርን የመሳሰሉ ውበቶችን
አለመጠበቅ ሊኖር ይችላል፡፡ የእራስን ንጽህና
አለመጠበቅና አቋምን አለማስ ተካከል ባልታሰበ
ሁኔታ በትዳር ጉዋደኛ ዘንድ የመሰልቸት ሁኔታን
ይፈጥራል፡፡ በስራ ቦታ ፣በመዝናኛ ...ወዘተ
በመሳሰሉት ቦታዎች የሚታዩትን ሰዎችም
ወደህሳቤ ለማስገ ባትና ወደውጭ ለመሳብ
ሁኔታዎችን ሊያመቻች ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች
እንዲህ ይላሉ፡፡ እኔ የምፈልገው ሰው የዛሬውን
ሳይሆን የእኔን የጥንት ማንነት የሚረዳ እና
የሚያስታውሰውን ነው” በእርግጥ ይህ አባባል
ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ነገር ግን በራስ እምነት
ብቻ ተመስርቶ የሌላውን
ስሜት እና ፍላጎት መጉዳት አይገባም፡፡ እራስን
መጠበቅ ፣ጸድቶ መገኘት የግልን ጤናም
ከመጠበቅ እና የተጉዋዳኝን ስሜት ከመረዳት
አኩዋያ ትክክለኛ ድርጊት ስለሆነ ሁሉም
ሊተገብረው የሚገባው ነገር ነው፡፡ ለእራስ ክብር
አለመስጠት፡-አንድ ሰው እራሱን ባከበረ ቁጥር
የሌላውንም ክብር እንደሚጠብቅ እሙን ነው፡፡
በተለይም በባለትዳሮች ዘንድ እራስን ማክበር
ማለት የትዳር ጉዋደኛውን ክበር መጠበቅ መሆኑን
ሊገነዘብ ይገባል፡፡ በአነጋገር፣ በአለባስ፣ በስራ
ግንኙነት፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በታማኝነት ...ወዘተ
በመሳሰሉት ሁሉ የእራስን ክብር ለመጠበቅ
መሞከር ማለት... አብሮ ለሚኖር እንዲሁም በስራ
እና በሌላ አጋጣሚ ለሚያገኙዋቸው ሁሉ ክብርን
እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡ ግልጽነት አለመኖር፡-
ባለትዳሮች አንዳቸው ለአንዳቸው በግልጽ
አስተያየት በመስጠት የጎደለውን እንዲያሟሉ
እንዲሁም አንዳቸው ለአንዳቸው የሚያስፈልገውን
በማቅረብ እንዲረዳዱና ተመሳሳይ በሆነ አቋም
እንዲታዩ ግድ ይላል፡፡ ባል ወይንም ሚስት ከሁለት
አንዳቸው የሚፈልጉት ነገር ካለ በግልጽ እርስ
በእርሳቸው ሊነጋገሩበት ይገባል፡፡ ምንም እንኩዋን
ባልና ሚስት ከማንኛውም ሰው በላይ መናበብ
ይችላሉ ቢባልም አንዳንድ ጊዜ ድብቅነት ሊኖር
ስለሚ ችል ይህንን ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡
በግልጽ የመነጋገር ጥቅሙ አንዳቸው
ስለአንዳቸው ፍላጎት አስቀድሞ ለመረዳትና
ተፈላጊውን ነገር አስቀድሞ ለማድረግ
ይጠቅማል፡፡ ብ ልንላቸው የሚገቡ፡- በትዳር
መካከል የሚደረግን ንግግርን በጩኸት ሳይሆን
በእርጋታ ማድረግ ፣በፍቅር አብረው የሚኖሩ ሰዎች
መሞጋገስ ይገባቸዋል ፡፡ባል ሚስቱን ወይንም
ሚስት ባልዋን ሊያመሰግኑ ይገባል ፡፡ የትዳር
አጋርዎ ለሚያደርግልዎት ወይም ለምታደርግልዎት
ነገር ማመስገንና ማሞገስ እንዲሁም በእርጋት
ማነጋገር የፍቅር አጋርዎ በእርስዎ ውስጥ ምን
ያህል ቦታ እንዳለው /እንዳላት ያስረዳል፡፡
ምስጋናው ሲቀርብ ግን ከልብ በመነጭ ስሜት
እውነተኛው መሆን ይባዋል፡፡ ስለፍቅር አንዳንድ
ነጥቦች፡- G
ወዲያውኑ ካወቁት ሰው ነው፡፡ ፍቅር የሰውነት
መረጋጋትን ይጨምራራል፡፡ የነርቭ ሲስተምን
ያፋጥናል፡፡ እንደስነልቦና ተመራራማሪዎች ፍቅር
የጭንቀት ስሜትን የበለጠ እንዲጨምር
ያደርጋል፡፡ የአይን ብሌን መለጠጥን ያስከትላል፡፡
መዳፍ በላብ የመጠመቅ እንዲሁም የልብ ምት
መጨመርን ይፈጥራራል፡፡ በአለም እስከአሁን ድረስ
ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ትልቁ እና ውብ የሆነ የፍቅር
ስጦታ የታጅመሀል መስኪድ ነው፡፡ ይህ መስኪድ
የህንዱ ንጉስ shajam ለሚስቱ እንደመታሰቢያ
ያበረከተላት የፍቅር መግለጫ ነው፡፡ ዶቭ የተባሉት
የወፍ ዘሮች ለፍቅርቀን(valentine day) እንደበአል
ማድመቂያ ይቆጠራራሉ፡፡እነኚህ የወፍ ዘሮች
የእምነት እና የፍቅር መገለጫዎች ተደርገው
ይወሰዳሉ፡፡ ምክንያቱም የራራሳቸውን አጋር ካገኙ
ስለማይለያዩ ነው፡፡ አንድ ሰው ለምን ይፈቀራል?
በከንፈር፣ በአይን፣ በቁመና ..ወዘተ እንዳይባል ይሄ
ፍቅር ሳይሆን ምኞት ነው፡፡በጉብዝና፣ ስለህይወት
በሚኖር የጠለቀ ግንዛቤ ...ወዘተ እንዳይባል
ይሄም ፍቅር ሳይሆን አድናቆት ነው፡፡ፍቅር ማለት
አንድ ሰው ሌላውን ለምን እንደሚመርጥ ወይንም
በዚያ ሰው ለምን እንደሚመስጥ ሳይታወቅ ሲቀር
ነው፡፡
“ፍቅር የራሱ ምክንያት አለው፡፡ ያ ምክንያት ደግሞ
አይታወቅም” ቸር እንሰንብት
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ጭቅጭቅ የሚፈጠር ከሆነ ምንም እንኩዋን
የተመሰረተው ትዳር ለረዥም ጊዜ እንደሚዘልቅ
ቢታሰብም ጭቅጭቁ እየዋለ እያደር ግን ትዳርን
አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ አስቀድሞውኑ ልብ
ሊባል ይገባል፡፡ ችግሮችን ቀለል አድርጎ ማየት፡-
በባለትዳሮች ዘንድ ለሚነሱ ጥቃቅን ለሚመስሉ
ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ነገ ዛሬ ማለት
እና ነገሮችን በአናሳነት በመፈረጅ መፍትሔውን
በፍጥነት አለመፈለግ አልፎ አልፎ ያጋጥማል፡፡
በሌላም በኩል ለተነሱ ነገሮች መፍትሔ
ለመስጠት በሚል አንዳቸው ከአንዳቸው ለጊዜው
እራቅ ወደ አለ ቦታ ዞር ማለትን የሚመርጡበት
ሁኔታ ይስተ ዋላል፡፡ ይህ ክስተት ምናልባት ነገሩን
በስፋት ለማሰብ እና እራስን ለማረጋጋት ለጊዜው
ይረዳ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለተነሳው
ጭቅጭቅ መፍትሔ የሚሻው ሌላኛው ወገን
በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ባለመሰጠቱ ለምን ይህ ሆነ
በሚል ቁጭትና ንዴትን እንዲያብ ሰለስል
እንዲሁም ወደከፋ ውሳኔ እንዲሄድ ሊያደርገው
ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በባልና ሚስቱ መካከል
ለተነሱ ጭቅጭቆች ወይንም አለመግባባቶች
መፍትሔ ተሰጥ ቶአቸው ያልተቋጩ ነገሮች
የተረሱ ቢመስሉም እንኩዋን ውለው አድረው ግን
ከሌላ ነገር ጋር ተያይዘው መነሳታቸው ስለማይቀር
ስር ለሰደደ መቃቃር ሊዳርግ ይችላል፡፡ ከላይ
ለተጠቀሱት አጋጣሚዎች በመፍትሔነት
የተጠቆሙት ባልና ሚስቱ አስቀድሞውን
ጋብቻ ከመመስረታቸው በፊት ነገሮችን በምን
መንገድ ሊያስተናግዱ እንደሚገባቸው ፕላን
ሊያደርጉ እንደሚገባቸው ነው ፡፡ በገንዘብ ጉዳይ...
ቤተሰብን በማስተዳደር ...ዘመድ አዝማድ
...ጉዋደኛን በምን መልክ ማስተናገድ እንደሚገባ
እንዲ ሁም ማንን መርዳት ...ማንን አለመርዳት...
የመሳሰሉት ሁሉ ለውይይት መቅረብ የሚገባቸው
እና ለተጋቢዎቹ ቀላል የማይባሉ ናቸው፡፡ ትዳር
ሲመሰረት ንብረት ስለማፍራት ፣ ኃብት
ስለማከማቸት ፣ልጅ ስለመውለድ የመሳሰሉት
ሲታቀዱ በባህርይ በኩል ያለው ነገር ግን ብዙ ጊዜ
ቸል የሚባል ነው፡፡ ነገር ግን ወደታቀደው ግብ
የሚያደርሰው በባህርይ መግባባት ሲኖር መሆኑ
ሊዘነጋ እንደማይገባው ምሁራኑ ያስረዳሉ፡፡ አቋምን
አለማስተካከልና ውበትን አለመጠበቅ፡-በትዳር
መካከል አለመግባባቶችን ሊፈጥሩ ከሚችሉ
መካከል የራስን አቋምና ውበትን
አለማስተካከል አንዱ ነው፡፡ ሰዎች በትዳር አለም
ለረዥም ጊዜያት ሲቆዩ አንዳቸው አንዳቸውን
በድርጊታቸው ፣በአለባበሳቸው ፣በአቋማቸው
ተጉዋዳኛቸውን ለመማረክ ሲጥሩ ሌላኛው ወገን
ደግሞ ከነጭርሱም ለራሳቸው ትኩረት ላይሰጡ
ይችላሉ፡፡ እንደተገኝ ለብሶ መውጣት፣ የገላን
ንጽህና አለመጠበቅ፣ የጸጉርን የመሳሰሉ ውበቶችን
አለመጠበቅ ሊኖር ይችላል፡፡ የእራስን ንጽህና
አለመጠበቅና አቋምን አለማስ ተካከል ባልታሰበ
ሁኔታ በትዳር ጉዋደኛ ዘንድ የመሰልቸት ሁኔታን
ይፈጥራል፡፡ በስራ ቦታ ፣በመዝናኛ ...ወዘተ
በመሳሰሉት ቦታዎች የሚታዩትን ሰዎችም
ወደህሳቤ ለማስገ ባትና ወደውጭ ለመሳብ
ሁኔታዎችን ሊያመቻች ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች
እንዲህ ይላሉ፡፡ እኔ የምፈልገው ሰው የዛሬውን
ሳይሆን የእኔን የጥንት ማንነት የሚረዳ እና
የሚያስታውሰውን ነው” በእርግጥ ይህ አባባል
ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ነገር ግን በራስ እምነት
ብቻ ተመስርቶ የሌላውን
ስሜት እና ፍላጎት መጉዳት አይገባም፡፡ እራስን
መጠበቅ ፣ጸድቶ መገኘት የግልን ጤናም
ከመጠበቅ እና የተጉዋዳኝን ስሜት ከመረዳት
አኩዋያ ትክክለኛ ድርጊት ስለሆነ ሁሉም
ሊተገብረው የሚገባው ነገር ነው፡፡ ለእራስ ክብር
አለመስጠት፡-አንድ ሰው እራሱን ባከበረ ቁጥር
የሌላውንም ክብር እንደሚጠብቅ እሙን ነው፡፡
በተለይም በባለትዳሮች ዘንድ እራስን ማክበር
ማለት የትዳር ጉዋደኛውን ክበር መጠበቅ መሆኑን
ሊገነዘብ ይገባል፡፡ በአነጋገር፣ በአለባስ፣ በስራ
ግንኙነት፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በታማኝነት ...ወዘተ
በመሳሰሉት ሁሉ የእራስን ክብር ለመጠበቅ
መሞከር ማለት... አብሮ ለሚኖር እንዲሁም በስራ
እና በሌላ አጋጣሚ ለሚያገኙዋቸው ሁሉ ክብርን
እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡ ግልጽነት አለመኖር፡-
ባለትዳሮች አንዳቸው ለአንዳቸው በግልጽ
አስተያየት በመስጠት የጎደለውን እንዲያሟሉ
እንዲሁም አንዳቸው ለአንዳቸው የሚያስፈልገውን
በማቅረብ እንዲረዳዱና ተመሳሳይ በሆነ አቋም
እንዲታዩ ግድ ይላል፡፡ ባል ወይንም ሚስት ከሁለት
አንዳቸው የሚፈልጉት ነገር ካለ በግልጽ እርስ
በእርሳቸው ሊነጋገሩበት ይገባል፡፡ ምንም እንኩዋን
ባልና ሚስት ከማንኛውም ሰው በላይ መናበብ
ይችላሉ ቢባልም አንዳንድ ጊዜ ድብቅነት ሊኖር
ስለሚ ችል ይህንን ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡
በግልጽ የመነጋገር ጥቅሙ አንዳቸው
ስለአንዳቸው ፍላጎት አስቀድሞ ለመረዳትና
ተፈላጊውን ነገር አስቀድሞ ለማድረግ
ይጠቅማል፡፡ ብ ልንላቸው የሚገቡ፡- በትዳር
መካከል የሚደረግን ንግግርን በጩኸት ሳይሆን
በእርጋታ ማድረግ ፣በፍቅር አብረው የሚኖሩ ሰዎች
መሞጋገስ ይገባቸዋል ፡፡ባል ሚስቱን ወይንም
ሚስት ባልዋን ሊያመሰግኑ ይገባል ፡፡ የትዳር
አጋርዎ ለሚያደርግልዎት ወይም ለምታደርግልዎት
ነገር ማመስገንና ማሞገስ እንዲሁም በእርጋት
ማነጋገር የፍቅር አጋርዎ በእርስዎ ውስጥ ምን
ያህል ቦታ እንዳለው /እንዳላት ያስረዳል፡፡
ምስጋናው ሲቀርብ ግን ከልብ በመነጭ ስሜት
እውነተኛው መሆን ይባዋል፡፡ ስለፍቅር አንዳንድ
ነጥቦች፡- G
ወዲያውኑ ካወቁት ሰው ነው፡፡ ፍቅር የሰውነት
መረጋጋትን ይጨምራራል፡፡ የነርቭ ሲስተምን
ያፋጥናል፡፡ እንደስነልቦና ተመራራማሪዎች ፍቅር
የጭንቀት ስሜትን የበለጠ እንዲጨምር
ያደርጋል፡፡ የአይን ብሌን መለጠጥን ያስከትላል፡፡
መዳፍ በላብ የመጠመቅ እንዲሁም የልብ ምት
መጨመርን ይፈጥራራል፡፡ በአለም እስከአሁን ድረስ
ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ትልቁ እና ውብ የሆነ የፍቅር
ስጦታ የታጅመሀል መስኪድ ነው፡፡ ይህ መስኪድ
የህንዱ ንጉስ shajam ለሚስቱ እንደመታሰቢያ
ያበረከተላት የፍቅር መግለጫ ነው፡፡ ዶቭ የተባሉት
የወፍ ዘሮች ለፍቅርቀን(valentine day) እንደበአል
ማድመቂያ ይቆጠራራሉ፡፡እነኚህ የወፍ ዘሮች
የእምነት እና የፍቅር መገለጫዎች ተደርገው
ይወሰዳሉ፡፡ ምክንያቱም የራራሳቸውን አጋር ካገኙ
ስለማይለያዩ ነው፡፡ አንድ ሰው ለምን ይፈቀራል?
በከንፈር፣ በአይን፣ በቁመና ..ወዘተ እንዳይባል ይሄ
ፍቅር ሳይሆን ምኞት ነው፡፡በጉብዝና፣ ስለህይወት
በሚኖር የጠለቀ ግንዛቤ ...ወዘተ እንዳይባል
ይሄም ፍቅር ሳይሆን አድናቆት ነው፡፡ፍቅር ማለት
አንድ ሰው ሌላውን ለምን እንደሚመርጥ ወይንም
በዚያ ሰው ለምን እንደሚመስጥ ሳይታወቅ ሲቀር
ነው፡፡
“ፍቅር የራሱ ምክንያት አለው፡፡ ያ ምክንያት ደግሞ
አይታወቅም” ቸር እንሰንብት
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin