መነሳሳት🤔 በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ
ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም
ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ
ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት
መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች
ይተግብሯቸው፡፡
1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች
ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ
በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም
ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ
ያስፈልጋል፡፡
2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ
ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ
የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር
ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡
ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው
ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”
3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና
የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ
ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን
መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ
ስንቅ ነው፡፡
4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው
ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው
ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች
ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ
ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ
ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡
5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል
ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡
በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና
ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ
እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡
6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና
ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው
ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ
ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ
መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡
7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው
ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና
ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት
ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡
8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ
ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት
የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ
ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡
9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን
ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር
ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ
በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡
10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን
ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን
ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን
የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ
አለብን፡፡
መልካም ግዜ📌
@httptelegramme81biniyamin
ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም
ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ
ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት
መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች
ይተግብሯቸው፡፡
1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች
ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ
በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም
ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ
ያስፈልጋል፡፡
2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ
ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ
የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር
ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡
ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው
ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”
3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና
የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ
ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን
መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ
ስንቅ ነው፡፡
4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው
ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው
ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች
ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ
ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ
ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡
5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል
ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡
በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና
ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ
እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡
6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና
ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው
ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ
ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ
መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡
7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው
ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና
ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት
ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡
8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ
ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት
የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ
ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡
9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን
ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር
ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ
በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡
10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን
ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን
ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን
የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ
አለብን፡፡
መልካም ግዜ📌
@httptelegramme81biniyamin
የወሲብ ችግሮችና መንስኤ ስለ ወሲብ ችግሮች ከማውራታችን በፊት በቅድሚያ ጤናማ
የወሲብ ባህርይ እና ደረጃዎች ምንድን ናቸው የሚሉትን
ማየት መልካም ነው:: አያሌ ምሁራን ስለ ጤናማ የወሲብ
ባህርይ ብዙ ብለዋል ከነዚህም መካከከል ዊሊያም እና
ቨርጂኒያ የተባሉት ባለሙያዎች ጤናማ የወሲብ ባህርይ
ማለት አራቱን የወሲብ ደረጃዎች ጠብቀው የሚከሰቱ
የወሲብ ባህርይ ነው ይሉናል፡፡ የመጀመሪያው ደረጃ
መነቃቃት ሲሆን በዚህም አጠቃላይ የሆነ አካላዊና
አዕምሮዐዊ መነቃቃቶችን እና ዝግጁነትን ያመለክታል፡፡
ሁለተኛው ደረጃ ሙሉ ለሙሉ አካላችንም ሆነ አዕምሮአችን
በመጀመሪያው ደረጃ ላይ የተጀመሩት መነሳሳቶች ለወሲብ
ዝግጁ ሲሆን ማለት ሲሆን ይህም የአካልን እና የመራቢያ
ክፍሎችን የዝግጁነት ጥግ መድረስን ያመለክታል፡፡
ሶስተኛው እርካታ ሲሆን በዚህም በወንዶችም ሆነ በሴቶች
ላይ ያሉትን እርካታ ላይ የመድረሻ መንገዶች እና እርካታን
ያካትታል፡፡ አራተኛው መረጋጊያ ሲሆን በዚህም ለወሲብ
ተዘጋጅተው የነበሩ የሰውነት ክፍሎቻችን ወደ ቀድሞ
ይዞታቸው ይመለሳሉ እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ ለቀጣይ
ወሲብ ዝግጁ አይሆኑም ማለት ነው፡፡ አንዳንድ የጥናት
ጽሁፎች እዚህ ጋር ጾታን በተመለከተ ልዩነት አላቸው፡፡
በውጤታቸውም መሰረት ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ፍጥነት
ለሁለተኛ ወሲብ ዝግጁ ይሆናሉ ይሉናል፡፡ እናንተስ ምን
ትላላችሁ ?
የወሲብ ችግር ብዙዎቻችን የሚያጋጥመን ግን ባህልና ወግ
ሸብቦ ስለያዘን ደፍረን የባለሙያ እርዳታ እና ምክር
የማንጠይቅበት እክል ነው፡፡ በወሲብ አለመጣጣም የፍቅር
ግንኙነቶችን አቀዝቅዞ የፍቅር አጋሮችን የመለያየት አቅሙ
ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህም ሳይወሰን የወሲብ ችግር ትዳርን
አፋልሶ ቤተሰብንም ይበትናል፡፡ ስንቶቻችን የወሲብ እክል
አጋጥሞኛል እርዳታ እፈልጋለሁ ብለን እናውቃለን?
ስንቶቻችንስ ከፍቅር አጋራችን ጋር የወሲብ ችግርን
በተመለከተ በግልጽ እንነጋገራለን?
በወሲብ ችግር ምክንያት የፍቅር አጋርን አለማርካት ከፍተኛ
የሆነ በእራስ መተማመንን የሚቀንስ ውጤቱ አስከፊ የሆነ
ችግር ነው፡፡ ታዋቂው የስነ-ልቡና እና ስነ-ባህሪ ችግሮች
መመሪያ (Diagnostic statistical manual (DSM IV))
የወሲብ ችግሮችን በአራት ከፍሎ ያያቸዋል የወሲብ ፍላጎት
እክል፣ ለወሲብ መነቃቃት እክል፣ የእርካታ ችግር እንዲሁም
በወሲብ ጊዜ ህመም በማለት ይከፍላቸዋል፡፡ እስኪ ዛሬ
ከእነዚህ መካከል ስለ ጥቂቶቹ እናውራ፡-
1. የብልት መቆም ችግር፡- ይህ ችግር በወንዶች ላይ
የሚከሰት ነው፡፡ በዚህም ወንዱ ወሲብ ለማድረግ
በዝግጅት ውስጥ ባለበት ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች
ብልቱ ዝግጁ አልሆን ሲለው ማለት ነው፡፡ ከእነዚህም
ከተጠቀሱት ምክንያቶች መካከል አደንዛዥ ዕፆች፣
ብቃቱን በተመለከተ ፍርሓት (የስነ-ልቡና ችግር)…
የመሳሰሉት እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡
2. ቀድሞ መጨረስ፡- በወሲብ ወቅት ወንዱ ለሁለቱም
እርካታ ከሚጠበቀው አማካይ ጊዜ በፊት ባብዛኛው
የወሲብ እንቅስቃሴ በተጀመረ በ 1 ደቂቃ ውስጥ (DSM
V) አስቀድሞ ሲያጠናቅቅ ማለት ነው፡፡ባብዛኛው
ቀድሞ መጨረስ የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ የሆነ
የችግር ምንጭ ያለው የወሲብ እክል ነው፡፡ይህንንም
ስንል ወሲብን በግልፅነት ከታችኛው የትምህርት ደረጃ
እንዲሁም ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ጀምሮ መነጋገር
ወይም አብጠርጥሮ መማር አለመቻል እንደ አብነት
ይጠቀሳል፡፡ እንዲሁም በግለ ወሲብ (masturbation)
ጊዜ እንዳይደረስብኝ ብሎ ቶሎ መጨረስ እንደ ልምድ
ተይዞ በዋናው ወሲብ ጊዜ ችግር ይፈጥራል፡፡
3. ዘግይቶ መጨረስ፡- ይህ ደግሞ ቀድሞ ከመጨረስ
ፍፁም ተቃራኒ ሲሆን በዚህም ወንዱ የሚጨርስበት
ሰዓት ይረዝማል፡፡ ይህም አላፈስላጊ የሆኑ አካላዊም ሆነ
ሳይኮሎጂካዊ ችግሮችን በሁለቱም ላይ ያስከትላል፡፡
4. እርካታ ላይ አለመድረስ፡- ይህ ባብዛኛው ጥናት
በተደረገባቸው ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑ ሴቶች ላይ የታየ
ችግር ሲሆን በዚህም ሴቶች በወሲብ ጊዜ የፍቅር
አጋራቸው የወሲብ ብቃት አጠያያቂ ሳይሆን እርካታ ላይ
በተጠበቀው ጊዜ ያለመድረስ ነው፡፡
5. ውስን የወሲብ ፍላጎት፡- የወሲብ ፍላጎታችን እጅግ
ዝቅተኛ ወይም ከነጭራሹን አነስተኛ ሲሆን ማለት ነው፡፡
በዚህም ወሲብ የመፈፀም አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ
የተለያዩ ምክንያት በመደርደር ወሲብን አለማድረግ
ነው፡፡
ከላይ የተቀስናቸው የወሲብ ችግሮች መካከል ቢያንስ አንዴ
እንኳን በወሲብ ህይወታችን ያጋጥማሉ ተብሎ ይታሰባል
ሆኖም ግን እንደ ወሲብ ችግር አይወሰዱም ምክንያቱም
እንደ ችግር የምንወስደው በተደጋጋሚ መፈጠርና ወሲብን
ከመዝናኛነት አልፎ አታካች ስራ ሲያደርጉት ነው፡፡
የወሲብ ችግር መንስዔዎች
ተፈጥሯዊ (ሥነ-ህይወታዊ)
የጤና እክል (በሽታ) በተዘዋዋሪ መንገድ እንደ አንድ
የወሲብ ችግር የሚታይ ሲሆን ይህንንም ሰንል ለምሳሌ
በውስጣችን የደም ዝውውር ችግር የሚፈጥሩ የጤና
እክሎች በወሲብ ጊዜ ደም ተዘዋውሮ የወንዱ ብልት
እንዳይቆም ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ሌላው የልብ ችግር
ያለባቸው ሰዎች በቅድመ ወሲብ ጊዜ ከሚፋጠነው የልብ
ምት ጋር በተያያዘ የሚፈጠረውን ችግር ለማስቀረት እና
ተጓዳኝ ጉዳቱን በመፍራት ከወሲብ ይታቀባሉ፡፡ ተጨማሪ
አንዳንድ ለበሽታ ፈውስ ተብለው የምንወስዳቸው
መድኃኒቶችም ወሲብ ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ይኖራቸዋል፡፡
ሌላው ከእድሜ መጨመር ጋር የተያያዘ ችግር ሲሆን
በዚህም በሁለቱም ጾታ ላይ በተፈጥሯዊ ምክንያቶች
የወሲብ ፍላጎት እየቀዘቀዘ፣ እየቀነሰ እንዲሁም
ከእነጭራሱኑ እየጠፋ ይመጣል፡፡
የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ ነክ ችግሮች
እነዚህ ከተለያዩ አስተሳሰቦች እና እምነቶች ጋር የተየያዙ
የወሲብ ችግሮች ናቸው፡፡ ጥቂቶቹንም ስናይ በቅድሚያ
የምናገኘው ትኩረትን ከሚቀንሱት መካከል የተመደቡትን
ነው፡፡ እነዚህም …..በእራሱ ተክለሰውነት የሚያፍር ሰው
በወሲብ ጊዜ አጋሩ ስለ ሰውነቱ አስቀያሚነት የምታስብ
ስለሚመስለው ወሲብ ላይ ችግር ይፈጠራል፤ በወሲብ ጊዜ
ወሲብ ነክ ያልሆኑ ኃሳቦች በተደጋጋሚ ሲመጡብን፤ ከዚህ
በፊት ወሲብ ችግር ያጋጠመው ሰው ድጋሜ ይከሰትብኛል
ብሎ ከመስጋት ጋር በተያያዘ፤ ወሲብን እንደ መጥፎ ነገር
የሚታሰብበት እምነት እና ባህል ያለው ማህበረሰብ ውስጥ
ማደግ እንዲሁም ከዚህ በፊት በወሲብ ምክንያት ጥቃት እና
ጉዳት የደረሰብን ከሆነ እና በመሳሰሉት ወሲብ ላይ ችግር
ሊፈጠር ይችላል፡፡
የጥንዶች ግንኙነት
በጥንዶች መካከል የሚኖረው ጤናማ የወሲብ ባህርይ
በጥዶቹ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ይህም ጥንዶች
ምን ያህል የልብ ወዳጆች እንደሆኑ፣ ችግሮችና ግጭጦችን
በምን መልኩ እንደሚፈቱ፣ ውጥረትን እንዴት
እንደሚያስወግዱ፣ ፍላጎታቸውን እንዴት እንደሚገልፁ …
የመሳሰሉት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ውድ የዘ-ሳይኮሎጂ ቤተሰቦች መቼም በዚች ትንሽ ጽሑፍ
ይህን ሁዳድ የሆነ ርዕስ ለመዳሰስ መሞከር ዓባይን
በጭልፋ ነው ነገሩ፤ ሆኖም በር ከፋች ትሆንልን ዘንዳ ነው
እንጂ አላማዋ ሁሉንም መሸፈን አይደለም ስለሆነም
በቀጣይ ጽሁፌ ደግሞ በመፍትሔው ዙሪያ እንደምመለስበት
ቃል በመግባት የዛሬውን በዚሁ ልጨርስ፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ……
@httptelegramme81biniyamin
የወሲብ ባህርይ እና ደረጃዎች ምንድን ናቸው የሚሉትን
ማየት መልካም ነው:: አያሌ ምሁራን ስለ ጤናማ የወሲብ
ባህርይ ብዙ ብለዋል ከነዚህም መካከከል ዊሊያም እና
ቨርጂኒያ የተባሉት ባለሙያዎች ጤናማ የወሲብ ባህርይ
ማለት አራቱን የወሲብ ደረጃዎች ጠብቀው የሚከሰቱ
የወሲብ ባህርይ ነው ይሉናል፡፡ የመጀመሪያው ደረጃ
መነቃቃት ሲሆን በዚህም አጠቃላይ የሆነ አካላዊና
አዕምሮዐዊ መነቃቃቶችን እና ዝግጁነትን ያመለክታል፡፡
ሁለተኛው ደረጃ ሙሉ ለሙሉ አካላችንም ሆነ አዕምሮአችን
በመጀመሪያው ደረጃ ላይ የተጀመሩት መነሳሳቶች ለወሲብ
ዝግጁ ሲሆን ማለት ሲሆን ይህም የአካልን እና የመራቢያ
ክፍሎችን የዝግጁነት ጥግ መድረስን ያመለክታል፡፡
ሶስተኛው እርካታ ሲሆን በዚህም በወንዶችም ሆነ በሴቶች
ላይ ያሉትን እርካታ ላይ የመድረሻ መንገዶች እና እርካታን
ያካትታል፡፡ አራተኛው መረጋጊያ ሲሆን በዚህም ለወሲብ
ተዘጋጅተው የነበሩ የሰውነት ክፍሎቻችን ወደ ቀድሞ
ይዞታቸው ይመለሳሉ እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ ለቀጣይ
ወሲብ ዝግጁ አይሆኑም ማለት ነው፡፡ አንዳንድ የጥናት
ጽሁፎች እዚህ ጋር ጾታን በተመለከተ ልዩነት አላቸው፡፡
በውጤታቸውም መሰረት ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ፍጥነት
ለሁለተኛ ወሲብ ዝግጁ ይሆናሉ ይሉናል፡፡ እናንተስ ምን
ትላላችሁ ?
የወሲብ ችግር ብዙዎቻችን የሚያጋጥመን ግን ባህልና ወግ
ሸብቦ ስለያዘን ደፍረን የባለሙያ እርዳታ እና ምክር
የማንጠይቅበት እክል ነው፡፡ በወሲብ አለመጣጣም የፍቅር
ግንኙነቶችን አቀዝቅዞ የፍቅር አጋሮችን የመለያየት አቅሙ
ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህም ሳይወሰን የወሲብ ችግር ትዳርን
አፋልሶ ቤተሰብንም ይበትናል፡፡ ስንቶቻችን የወሲብ እክል
አጋጥሞኛል እርዳታ እፈልጋለሁ ብለን እናውቃለን?
ስንቶቻችንስ ከፍቅር አጋራችን ጋር የወሲብ ችግርን
በተመለከተ በግልጽ እንነጋገራለን?
በወሲብ ችግር ምክንያት የፍቅር አጋርን አለማርካት ከፍተኛ
የሆነ በእራስ መተማመንን የሚቀንስ ውጤቱ አስከፊ የሆነ
ችግር ነው፡፡ ታዋቂው የስነ-ልቡና እና ስነ-ባህሪ ችግሮች
መመሪያ (Diagnostic statistical manual (DSM IV))
የወሲብ ችግሮችን በአራት ከፍሎ ያያቸዋል የወሲብ ፍላጎት
እክል፣ ለወሲብ መነቃቃት እክል፣ የእርካታ ችግር እንዲሁም
በወሲብ ጊዜ ህመም በማለት ይከፍላቸዋል፡፡ እስኪ ዛሬ
ከእነዚህ መካከል ስለ ጥቂቶቹ እናውራ፡-
1. የብልት መቆም ችግር፡- ይህ ችግር በወንዶች ላይ
የሚከሰት ነው፡፡ በዚህም ወንዱ ወሲብ ለማድረግ
በዝግጅት ውስጥ ባለበት ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች
ብልቱ ዝግጁ አልሆን ሲለው ማለት ነው፡፡ ከእነዚህም
ከተጠቀሱት ምክንያቶች መካከል አደንዛዥ ዕፆች፣
ብቃቱን በተመለከተ ፍርሓት (የስነ-ልቡና ችግር)…
የመሳሰሉት እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡
2. ቀድሞ መጨረስ፡- በወሲብ ወቅት ወንዱ ለሁለቱም
እርካታ ከሚጠበቀው አማካይ ጊዜ በፊት ባብዛኛው
የወሲብ እንቅስቃሴ በተጀመረ በ 1 ደቂቃ ውስጥ (DSM
V) አስቀድሞ ሲያጠናቅቅ ማለት ነው፡፡ባብዛኛው
ቀድሞ መጨረስ የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ የሆነ
የችግር ምንጭ ያለው የወሲብ እክል ነው፡፡ይህንንም
ስንል ወሲብን በግልፅነት ከታችኛው የትምህርት ደረጃ
እንዲሁም ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ጀምሮ መነጋገር
ወይም አብጠርጥሮ መማር አለመቻል እንደ አብነት
ይጠቀሳል፡፡ እንዲሁም በግለ ወሲብ (masturbation)
ጊዜ እንዳይደረስብኝ ብሎ ቶሎ መጨረስ እንደ ልምድ
ተይዞ በዋናው ወሲብ ጊዜ ችግር ይፈጥራል፡፡
3. ዘግይቶ መጨረስ፡- ይህ ደግሞ ቀድሞ ከመጨረስ
ፍፁም ተቃራኒ ሲሆን በዚህም ወንዱ የሚጨርስበት
ሰዓት ይረዝማል፡፡ ይህም አላፈስላጊ የሆኑ አካላዊም ሆነ
ሳይኮሎጂካዊ ችግሮችን በሁለቱም ላይ ያስከትላል፡፡
4. እርካታ ላይ አለመድረስ፡- ይህ ባብዛኛው ጥናት
በተደረገባቸው ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑ ሴቶች ላይ የታየ
ችግር ሲሆን በዚህም ሴቶች በወሲብ ጊዜ የፍቅር
አጋራቸው የወሲብ ብቃት አጠያያቂ ሳይሆን እርካታ ላይ
በተጠበቀው ጊዜ ያለመድረስ ነው፡፡
5. ውስን የወሲብ ፍላጎት፡- የወሲብ ፍላጎታችን እጅግ
ዝቅተኛ ወይም ከነጭራሹን አነስተኛ ሲሆን ማለት ነው፡፡
በዚህም ወሲብ የመፈፀም አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ
የተለያዩ ምክንያት በመደርደር ወሲብን አለማድረግ
ነው፡፡
ከላይ የተቀስናቸው የወሲብ ችግሮች መካከል ቢያንስ አንዴ
እንኳን በወሲብ ህይወታችን ያጋጥማሉ ተብሎ ይታሰባል
ሆኖም ግን እንደ ወሲብ ችግር አይወሰዱም ምክንያቱም
እንደ ችግር የምንወስደው በተደጋጋሚ መፈጠርና ወሲብን
ከመዝናኛነት አልፎ አታካች ስራ ሲያደርጉት ነው፡፡
የወሲብ ችግር መንስዔዎች
ተፈጥሯዊ (ሥነ-ህይወታዊ)
የጤና እክል (በሽታ) በተዘዋዋሪ መንገድ እንደ አንድ
የወሲብ ችግር የሚታይ ሲሆን ይህንንም ሰንል ለምሳሌ
በውስጣችን የደም ዝውውር ችግር የሚፈጥሩ የጤና
እክሎች በወሲብ ጊዜ ደም ተዘዋውሮ የወንዱ ብልት
እንዳይቆም ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ሌላው የልብ ችግር
ያለባቸው ሰዎች በቅድመ ወሲብ ጊዜ ከሚፋጠነው የልብ
ምት ጋር በተያያዘ የሚፈጠረውን ችግር ለማስቀረት እና
ተጓዳኝ ጉዳቱን በመፍራት ከወሲብ ይታቀባሉ፡፡ ተጨማሪ
አንዳንድ ለበሽታ ፈውስ ተብለው የምንወስዳቸው
መድኃኒቶችም ወሲብ ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ይኖራቸዋል፡፡
ሌላው ከእድሜ መጨመር ጋር የተያያዘ ችግር ሲሆን
በዚህም በሁለቱም ጾታ ላይ በተፈጥሯዊ ምክንያቶች
የወሲብ ፍላጎት እየቀዘቀዘ፣ እየቀነሰ እንዲሁም
ከእነጭራሱኑ እየጠፋ ይመጣል፡፡
የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ ነክ ችግሮች
እነዚህ ከተለያዩ አስተሳሰቦች እና እምነቶች ጋር የተየያዙ
የወሲብ ችግሮች ናቸው፡፡ ጥቂቶቹንም ስናይ በቅድሚያ
የምናገኘው ትኩረትን ከሚቀንሱት መካከል የተመደቡትን
ነው፡፡ እነዚህም …..በእራሱ ተክለሰውነት የሚያፍር ሰው
በወሲብ ጊዜ አጋሩ ስለ ሰውነቱ አስቀያሚነት የምታስብ
ስለሚመስለው ወሲብ ላይ ችግር ይፈጠራል፤ በወሲብ ጊዜ
ወሲብ ነክ ያልሆኑ ኃሳቦች በተደጋጋሚ ሲመጡብን፤ ከዚህ
በፊት ወሲብ ችግር ያጋጠመው ሰው ድጋሜ ይከሰትብኛል
ብሎ ከመስጋት ጋር በተያያዘ፤ ወሲብን እንደ መጥፎ ነገር
የሚታሰብበት እምነት እና ባህል ያለው ማህበረሰብ ውስጥ
ማደግ እንዲሁም ከዚህ በፊት በወሲብ ምክንያት ጥቃት እና
ጉዳት የደረሰብን ከሆነ እና በመሳሰሉት ወሲብ ላይ ችግር
ሊፈጠር ይችላል፡፡
የጥንዶች ግንኙነት
በጥንዶች መካከል የሚኖረው ጤናማ የወሲብ ባህርይ
በጥዶቹ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ይህም ጥንዶች
ምን ያህል የልብ ወዳጆች እንደሆኑ፣ ችግሮችና ግጭጦችን
በምን መልኩ እንደሚፈቱ፣ ውጥረትን እንዴት
እንደሚያስወግዱ፣ ፍላጎታቸውን እንዴት እንደሚገልፁ …
የመሳሰሉት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ውድ የዘ-ሳይኮሎጂ ቤተሰቦች መቼም በዚች ትንሽ ጽሑፍ
ይህን ሁዳድ የሆነ ርዕስ ለመዳሰስ መሞከር ዓባይን
በጭልፋ ነው ነገሩ፤ ሆኖም በር ከፋች ትሆንልን ዘንዳ ነው
እንጂ አላማዋ ሁሉንም መሸፈን አይደለም ስለሆነም
በቀጣይ ጽሁፌ ደግሞ በመፍትሔው ዙሪያ እንደምመለስበት
ቃል በመግባት የዛሬውን በዚሁ ልጨርስ፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ……
@httptelegramme81biniyamin
ቅናት😳? ቅናት መጠኑ ይለያይ እንጅ በአብዛኛው ሰው ላይ የሚታይ
ባህርይ ነው፡፡ እኛ ሰዎች በሁለቱም ማለትም ባለንም
በሌለንም ቁሳዊም ሆነ ስነ-ልቡናዊ ጥቅሞች ባላቸው
ነገሮች ላይ እንቀናለን፡፡ በሌለን ነገር ላይ የምንቀናው ቅናት
(Envy) ሰዎች የሚፈልግቱንና እኛ የሌለንን ሲያገኙ ፣
ሲያሳኩ ወይም የሚያሳኩበትን የተስተካከለ መስመር ሲይዙ
የሚሰማን ምቾት የማጣት ስሜት ሲሆን፤ ባለን ነገር ላይ
ቅናት (Jealousy) ማለት ደግሞ ሌሎች እኛ ያለንን ቁሳዊ
አካል ወይም የስሜት ግኙነት የመሰረትንበትን ሰው
ሊያሳጧችሁ የሚመስል መጥፎ ስሜት በውስጣችሁ
ሲፈጠር ነው፡፡ በምሳሌ ለማስቀመጥም የፍቅር አጋርህን
ሌላ ወንድ ሲያናግራት ብታይ እና ሰላም የማጣት ስሜት
ሲሰማህ ቅናት (Jealousy) ሸነቆጠህ ማለት ነው፡፡ አልያም
ህፃናት አዲስ በተወለደው ወንድም ወይም እህት ምክንያት
የሚሰማቸው እናቴን ወይም አባቴን ተነጠኩኝ ዓይነት ስሜት
እና ባህርይ እንደ አብነት ማየት ይቻላል፡፡ ቅናት ገደቡን
ካለፈ በእኛም ላይ ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ስነ ልቡናዊ እና
አካዊ ጉዳቶችን ይፈጥራሉ፡፡ ሆኖም ግን ቅናትን በበጎ
መልኩ የምንጠቀምበት ከሆነ መልካም የሆነ ግንኙነትና እኛ
ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ወደተሸለ ደረጃ ወይም
የምንቀናባቸው ሰዎች ወዳሉበት የስኬት ማማ ላይ
ለመድረስ መንገዱን ይጠርግልናል፡፡
ከላይ እንደተገለጸው ቅናት የተለያዩ ስነ-ልቡናዊ እና አካላዊ
ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡ ቅናት ቤተሰብን ይበትናል፣ ፍቅረኞችን
ያለያያል፣ የስራ ባልደረቦችን ያጋጫል፣ ሰላማዊውን የሰው
ልጆች መስተጋብር ያፋልሳል …ባስም ሲል ቅናት ክቡር
የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትን ያስጠፋል (የዴዝዴሞና ታሪክ
ትዝ አላችሁ?) ስለዚህ መፍትሔው ምንድን ነው ??
መቅናትን እንዴት ማቆም እንችላለን??? እስኪ እነዚህን
የመፍትሔ አቅጣጫዎች አብረን እንዝለቃቸው………. በጾታዊ
ፍቅር ምክንያት ከሆነ ቅናት የሚይዘን በግልጽ መነጋገር፡፡ ይሄ
ደርጊትሽ(ህ) ጥሩ ያልሆነ ስሜት እየፈጠረብኝ ስለሆነ
መስተካከል ይኖርበታል ማለት አለብን፡፡ ማስተዋል ያለብን
ቀንቻለው ማለት የተሸናፊነት ምልክት ሳይሆን ግንኙነቱን
ዘላቂና ሰላማዊ ማድረግ እፈልጋለሁ ማለት እደሆነ ነው፡፡
( መተማመን) በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ዋናው የግንኙነት
መሰረቱ መተማመን ነው፡፡ የማይተማመን ባልንጀራ ካብ
ለካብ ይማማላል እንዲሉ አበው፤ መተማመን የሌለው
ጾታዊ ፍቅርም ለቅናት የተጋለጠ ነው፡፡ ሌላው መቼም
የምንቀናበት ሰው ፍጹም አይደለም፡፡ እሱ የሌለው እኛ ግን
ያለን ሌሎች ነገሮችም እንዳሉ መገንዘብ፡፡ሁልጊዜ ራስህን
በጥረት ውስጥ ማሳለፍ ይኖርብሃል፡፡ ምክንያቱም
የቻልከውን ያህል ስለታተርክ በቅናት ፋንታ እርካታን
ታገኝበታለህ፡፡ ከምንቀናባቸው ሰዎች ልምድ መቅሰም
አለብን፡፡ ይህም ማለት የቀናህበትን ነጥብ ነቅሰህ አውጣ
በዚህም አንተ ማግኘት ያቃተህ ሌሎች ግን ያሳኩት ከሆነ
እንዴት እንዳሳኩት በማወቅ ራስህን እንድታሻሽል ይረዳሀል፡፡
በመጨረሻም ሌሎች ሰዎች ላይ እና ያላቸው ነገሮች ላይ
ያለህን ፅንፍ የያዘ ትኩረትህን ቀንስ፡፡ ምክንያቱም
የአዕምሮህን የትኩረት አቅጣጫ በማስቀየር አቅምህን
ያሟጥብሀል፡፡ ስለሌለህ ሳይሆን ስላለህ ነገር በማሰብ
ለእራስህ እውቅና ስጥ በዚህም በጊዜ ሂደት በራስ
መተማመንን አዳብረህ ቅናትን ታስወግዳለህ፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ……
ሼርያድርጉት
join👇
@httptelegramme81biniyamin
ባህርይ ነው፡፡ እኛ ሰዎች በሁለቱም ማለትም ባለንም
በሌለንም ቁሳዊም ሆነ ስነ-ልቡናዊ ጥቅሞች ባላቸው
ነገሮች ላይ እንቀናለን፡፡ በሌለን ነገር ላይ የምንቀናው ቅናት
(Envy) ሰዎች የሚፈልግቱንና እኛ የሌለንን ሲያገኙ ፣
ሲያሳኩ ወይም የሚያሳኩበትን የተስተካከለ መስመር ሲይዙ
የሚሰማን ምቾት የማጣት ስሜት ሲሆን፤ ባለን ነገር ላይ
ቅናት (Jealousy) ማለት ደግሞ ሌሎች እኛ ያለንን ቁሳዊ
አካል ወይም የስሜት ግኙነት የመሰረትንበትን ሰው
ሊያሳጧችሁ የሚመስል መጥፎ ስሜት በውስጣችሁ
ሲፈጠር ነው፡፡ በምሳሌ ለማስቀመጥም የፍቅር አጋርህን
ሌላ ወንድ ሲያናግራት ብታይ እና ሰላም የማጣት ስሜት
ሲሰማህ ቅናት (Jealousy) ሸነቆጠህ ማለት ነው፡፡ አልያም
ህፃናት አዲስ በተወለደው ወንድም ወይም እህት ምክንያት
የሚሰማቸው እናቴን ወይም አባቴን ተነጠኩኝ ዓይነት ስሜት
እና ባህርይ እንደ አብነት ማየት ይቻላል፡፡ ቅናት ገደቡን
ካለፈ በእኛም ላይ ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ስነ ልቡናዊ እና
አካዊ ጉዳቶችን ይፈጥራሉ፡፡ ሆኖም ግን ቅናትን በበጎ
መልኩ የምንጠቀምበት ከሆነ መልካም የሆነ ግንኙነትና እኛ
ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ወደተሸለ ደረጃ ወይም
የምንቀናባቸው ሰዎች ወዳሉበት የስኬት ማማ ላይ
ለመድረስ መንገዱን ይጠርግልናል፡፡
ከላይ እንደተገለጸው ቅናት የተለያዩ ስነ-ልቡናዊ እና አካላዊ
ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡ ቅናት ቤተሰብን ይበትናል፣ ፍቅረኞችን
ያለያያል፣ የስራ ባልደረቦችን ያጋጫል፣ ሰላማዊውን የሰው
ልጆች መስተጋብር ያፋልሳል …ባስም ሲል ቅናት ክቡር
የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትን ያስጠፋል (የዴዝዴሞና ታሪክ
ትዝ አላችሁ?) ስለዚህ መፍትሔው ምንድን ነው ??
መቅናትን እንዴት ማቆም እንችላለን??? እስኪ እነዚህን
የመፍትሔ አቅጣጫዎች አብረን እንዝለቃቸው………. በጾታዊ
ፍቅር ምክንያት ከሆነ ቅናት የሚይዘን በግልጽ መነጋገር፡፡ ይሄ
ደርጊትሽ(ህ) ጥሩ ያልሆነ ስሜት እየፈጠረብኝ ስለሆነ
መስተካከል ይኖርበታል ማለት አለብን፡፡ ማስተዋል ያለብን
ቀንቻለው ማለት የተሸናፊነት ምልክት ሳይሆን ግንኙነቱን
ዘላቂና ሰላማዊ ማድረግ እፈልጋለሁ ማለት እደሆነ ነው፡፡
( መተማመን) በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ዋናው የግንኙነት
መሰረቱ መተማመን ነው፡፡ የማይተማመን ባልንጀራ ካብ
ለካብ ይማማላል እንዲሉ አበው፤ መተማመን የሌለው
ጾታዊ ፍቅርም ለቅናት የተጋለጠ ነው፡፡ ሌላው መቼም
የምንቀናበት ሰው ፍጹም አይደለም፡፡ እሱ የሌለው እኛ ግን
ያለን ሌሎች ነገሮችም እንዳሉ መገንዘብ፡፡ሁልጊዜ ራስህን
በጥረት ውስጥ ማሳለፍ ይኖርብሃል፡፡ ምክንያቱም
የቻልከውን ያህል ስለታተርክ በቅናት ፋንታ እርካታን
ታገኝበታለህ፡፡ ከምንቀናባቸው ሰዎች ልምድ መቅሰም
አለብን፡፡ ይህም ማለት የቀናህበትን ነጥብ ነቅሰህ አውጣ
በዚህም አንተ ማግኘት ያቃተህ ሌሎች ግን ያሳኩት ከሆነ
እንዴት እንዳሳኩት በማወቅ ራስህን እንድታሻሽል ይረዳሀል፡፡
በመጨረሻም ሌሎች ሰዎች ላይ እና ያላቸው ነገሮች ላይ
ያለህን ፅንፍ የያዘ ትኩረትህን ቀንስ፡፡ ምክንያቱም
የአዕምሮህን የትኩረት አቅጣጫ በማስቀየር አቅምህን
ያሟጥብሀል፡፡ ስለሌለህ ሳይሆን ስላለህ ነገር በማሰብ
ለእራስህ እውቅና ስጥ በዚህም በጊዜ ሂደት በራስ
መተማመንን አዳብረህ ቅናትን ታስወግዳለህ፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ……
ሼርያድርጉት
join👇
@httptelegramme81biniyamin
💫ከትዳር በፊት ምን እናድርግ❓❓❓እኔም ልጅ አንቺም ልጅ ተጋቡ ይሉናል
የተሰቀለውን ማን ያወርድልናል
ከላይ እንደ መግቢያ የተጠቀምኩበት የግጥም ስንኝ
ከሙሉቀን መለሰ ዘፈን ላይ የተወሰደ ነው፡፡ ግጥሙ ሰምና
ወርቅ አለው ቅኔውን ፍታው የምትሉኝ ከሆነ ለእናንተ የቤት
ስራ ሰጥቼ አልፋለሁ፡፡ ሆኖም ግን የስንኙ ፍካሬያዊ ፍቺ
እንደሚለን ከሆነ ከመጋባታችን በፊት ከግምት ውስጥ
አስገብተን በጥንቃቄ ልናያቸው የሚገባን ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
እርግጥ ከዚህ በፊት ስለ ጤናማ ትዳርና የትዳር ወሰንን
መጠበቅ በሚል ርዕስ ስር ስለ ትዳር ህይወት አንዳንድ
ነጥቦችን ጠቅሰን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከትዳር በፊት ማየት
የሚገባንን ነጥብ ብለን ስንመጣ ከፈረሱ ጋሪው ቀድሞ ነበር
ካላችሁን ትክክል ናችሁ ሆኖም ግን ያን ያህል ብዙ የረፈደ
አልመሰልንም እና ከመጋባታችን በፊት እነዚህን ነጥቦቸ
እንመልከት ብለን ተነሳን፡-
1. ቅድመ ጋብቻ ምክክር (pre-marital counseling)
ከትዳር በፊት ከሳይኮሎጂ ባለሙያ ጋር ስለ ትዳር ውይይት
ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ አሁን አሁን ብቅ እያሉ ያሉ
የሳይኮሎጂ የምክክር አገልግሎት ተቋማት እየበዙ ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህን ተቋማት ከትዳር በፉት መጎብኘት አስፈላጊ
ነው፡፡ ይህን ስንል ግን የግድ ከባለሙያዎች ጋር ብቻ
ምክክሩ መሆን አለበት ሳይሆን በስኬታማ ትዳር ውስጥ
ረጅም ጊዜ ካሳለፉ ዕድሜ ጠገብ ባለትዳሮች ጋር ምክክሩ
መሆን ይችላል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንዳመለከቱት ከሆነ
ቅድመ ጋብቻ ምክክር አድርገው ወደ ትዳር የገቡ ተጋቢዎች
ምክክር ካላደረጉት የበለጠ ተግባቦት (communication) ፣
የረዘመ የትዳር ጊዜ እና ደስተኛ ቤተሰብ እንደሚኖራቸው
ተረጋግጧል፡፡
2. ኢኮኖሚያዊ ችግር
ትዳር ተቋም ነው፡፡ ይህን ተቋም ደግሞ በጽኑ መሰረት ላይ
ለመመስረት እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ግብዓት ከሆኑት
መካከል አንዱ የአኮኖሚ አቋም ነው፡፡ በዚህም ባል እና
ሚስት ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት ከኑሮው ደረጃ ጋር
ተመጣጣኝ የሆነ የፋይናንስ ምንጭ ወይም አቅም
ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በትዳር ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ
ከሚይዙ የግጭት መንስዔዎች መካከል ኢኮኖሚያዊ አቅም
አንዱ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡
3. ትክክለኛ ምክንያት
ትዳር የምንይዘው ለምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ
በተገቢው መልክ ካልመለስስን ትዳር የማንወጣው አዘቅት
ነው የሚሆንብን፡፡ ትክክለኛ ካልሆኑ ምክንያቶች መካከል
ከትዳር በፊት የሚመጣ ልጅ አንዱ ነው ፡፡ ከትዳር በፊት
ወልጄ ቤተሰቦቼን ከማሰድብ ይልቅ የመጣው ይምጣ ወደ
ትዳር እገባለሁ የሚል ድምዳሜ፣ ከሀገር ለመውጣት ቪዛ
ለማግኘት ሲባል እንዲሁም የተለያዩ ቁሳዊ ጥቃሞቶችን
ከትዳር አጋራችን ለማግኘት ሲባል ወደ ትዳር መግባት
ከጥቅሙ ጉዳቱ ነውና የሚበልጠው ጥንቃቄ ማድረግ
አስፈላጊ ነው፡፡
4. ሌሎች የቤተሰብ አባላት እና ጓደኞችን በተመለከተ
የትዳር አጋሮቻችን ቤተሰቦች እና ጓደኞች (በተለይ የልብ)
ጋር የሚኖረን ግንኙነት ከትዳር በፊት ጥሩ ቢሆን ይመከራል
ምክንያቱም ሰሚ ጆሮና አዳማጭ ልቦናን ከሰጠናቸው
ጣልቃ እየገቡ ትዳራችንን የሚበጠብጡበት አጋጣሚ ሰፊ
ነው፡፡
5. ጓደኛ መሆን እንችላለን??
ከትዳር አጋር በተጨማሪ ጓደኛ መሆን ይኖርብናል፡፡ እንደ
ጓደኛ የፈለኩትን ከአጋሬ ጋር ማውራት እችላለሁ ወይ??
ወይስ እየመረጥኩኝ ነው የማወራው የሚለውን አበክረን
ማየት አለብን፡፡ ምክንያቱም በብዛት በጓደኝነት ጊዜ
ተግባቦታችን እስከምን ድረስ መዝለቅ አለበት የሚለው
ወሳኝ ነጥብ ነው፡፡ ሳንግባባ መጋባት መጨረሻው ፍቺ እና
የቤተሰብ መበተን ነው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ
ምንጭ:- psychology today & Psych central
join👇
@httptelegramme81biniyamin
የተሰቀለውን ማን ያወርድልናል
ከላይ እንደ መግቢያ የተጠቀምኩበት የግጥም ስንኝ
ከሙሉቀን መለሰ ዘፈን ላይ የተወሰደ ነው፡፡ ግጥሙ ሰምና
ወርቅ አለው ቅኔውን ፍታው የምትሉኝ ከሆነ ለእናንተ የቤት
ስራ ሰጥቼ አልፋለሁ፡፡ ሆኖም ግን የስንኙ ፍካሬያዊ ፍቺ
እንደሚለን ከሆነ ከመጋባታችን በፊት ከግምት ውስጥ
አስገብተን በጥንቃቄ ልናያቸው የሚገባን ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
እርግጥ ከዚህ በፊት ስለ ጤናማ ትዳርና የትዳር ወሰንን
መጠበቅ በሚል ርዕስ ስር ስለ ትዳር ህይወት አንዳንድ
ነጥቦችን ጠቅሰን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከትዳር በፊት ማየት
የሚገባንን ነጥብ ብለን ስንመጣ ከፈረሱ ጋሪው ቀድሞ ነበር
ካላችሁን ትክክል ናችሁ ሆኖም ግን ያን ያህል ብዙ የረፈደ
አልመሰልንም እና ከመጋባታችን በፊት እነዚህን ነጥቦቸ
እንመልከት ብለን ተነሳን፡-
1. ቅድመ ጋብቻ ምክክር (pre-marital counseling)
ከትዳር በፊት ከሳይኮሎጂ ባለሙያ ጋር ስለ ትዳር ውይይት
ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ አሁን አሁን ብቅ እያሉ ያሉ
የሳይኮሎጂ የምክክር አገልግሎት ተቋማት እየበዙ ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህን ተቋማት ከትዳር በፉት መጎብኘት አስፈላጊ
ነው፡፡ ይህን ስንል ግን የግድ ከባለሙያዎች ጋር ብቻ
ምክክሩ መሆን አለበት ሳይሆን በስኬታማ ትዳር ውስጥ
ረጅም ጊዜ ካሳለፉ ዕድሜ ጠገብ ባለትዳሮች ጋር ምክክሩ
መሆን ይችላል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንዳመለከቱት ከሆነ
ቅድመ ጋብቻ ምክክር አድርገው ወደ ትዳር የገቡ ተጋቢዎች
ምክክር ካላደረጉት የበለጠ ተግባቦት (communication) ፣
የረዘመ የትዳር ጊዜ እና ደስተኛ ቤተሰብ እንደሚኖራቸው
ተረጋግጧል፡፡
2. ኢኮኖሚያዊ ችግር
ትዳር ተቋም ነው፡፡ ይህን ተቋም ደግሞ በጽኑ መሰረት ላይ
ለመመስረት እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ግብዓት ከሆኑት
መካከል አንዱ የአኮኖሚ አቋም ነው፡፡ በዚህም ባል እና
ሚስት ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት ከኑሮው ደረጃ ጋር
ተመጣጣኝ የሆነ የፋይናንስ ምንጭ ወይም አቅም
ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በትዳር ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ
ከሚይዙ የግጭት መንስዔዎች መካከል ኢኮኖሚያዊ አቅም
አንዱ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡
3. ትክክለኛ ምክንያት
ትዳር የምንይዘው ለምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ
በተገቢው መልክ ካልመለስስን ትዳር የማንወጣው አዘቅት
ነው የሚሆንብን፡፡ ትክክለኛ ካልሆኑ ምክንያቶች መካከል
ከትዳር በፊት የሚመጣ ልጅ አንዱ ነው ፡፡ ከትዳር በፊት
ወልጄ ቤተሰቦቼን ከማሰድብ ይልቅ የመጣው ይምጣ ወደ
ትዳር እገባለሁ የሚል ድምዳሜ፣ ከሀገር ለመውጣት ቪዛ
ለማግኘት ሲባል እንዲሁም የተለያዩ ቁሳዊ ጥቃሞቶችን
ከትዳር አጋራችን ለማግኘት ሲባል ወደ ትዳር መግባት
ከጥቅሙ ጉዳቱ ነውና የሚበልጠው ጥንቃቄ ማድረግ
አስፈላጊ ነው፡፡
4. ሌሎች የቤተሰብ አባላት እና ጓደኞችን በተመለከተ
የትዳር አጋሮቻችን ቤተሰቦች እና ጓደኞች (በተለይ የልብ)
ጋር የሚኖረን ግንኙነት ከትዳር በፊት ጥሩ ቢሆን ይመከራል
ምክንያቱም ሰሚ ጆሮና አዳማጭ ልቦናን ከሰጠናቸው
ጣልቃ እየገቡ ትዳራችንን የሚበጠብጡበት አጋጣሚ ሰፊ
ነው፡፡
5. ጓደኛ መሆን እንችላለን??
ከትዳር አጋር በተጨማሪ ጓደኛ መሆን ይኖርብናል፡፡ እንደ
ጓደኛ የፈለኩትን ከአጋሬ ጋር ማውራት እችላለሁ ወይ??
ወይስ እየመረጥኩኝ ነው የማወራው የሚለውን አበክረን
ማየት አለብን፡፡ ምክንያቱም በብዛት በጓደኝነት ጊዜ
ተግባቦታችን እስከምን ድረስ መዝለቅ አለበት የሚለው
ወሳኝ ነጥብ ነው፡፡ ሳንግባባ መጋባት መጨረሻው ፍቺ እና
የቤተሰብ መበተን ነው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ
ምንጭ:- psychology today & Psych central
join👇
@httptelegramme81biniyamin
ህይወት ከውስልትና ቡሀላ🙈
ሰላም ወዳጆች፤ ከዚህ በፊት በጾታዊ የፍቅር ግንኙነት ዙሪያ
አያሌ ጉዳዮችን ተወያይተናል፤ ምናልባትም ደግሞ እሰከዛሬ
ያልተነሳው ነጥብ ከላይ በርዕሱ ላይ ያነበባችሁት ነው፡፡
እርግጥ ነው ቃሉ ያስጠላል (ከድርጊቱ ባይብስም) ሆኖም
ግን ማለዘቢያ የሚሆን ምትክ ቃል ማግኘት ስላልቻልን
እንደወረደ cheating የሚለውን እንግሊዝኛ ቃል
ተርጉመናዋል ደግሞም ግንባርን ግንባር ካላልነው ምን
ልንለው ነው? የብዙ ጥንዶች የፍቅር ግንኙነት በውስልትና
ምክንያት ተቋርጧል፣ ቤተሰብ ተበጥብጦ ልጆች
ተበትነዋል፤ ሆኖም ግን በእንደዚህ ዓይነት ከባድ የፍቅር
ግንኙነት አደጋ ውስጥ ለማለፍ ጥቂት ጥቆማዎች ብሎ
ሳይኮሎጂ ቱደይ የተባለው ድህረ-ገጽ ያወጣውን አንድ
ጽሑፍ ይዘንላችሁ ቀርበናል መልካም ንባብ፡-
1. ከእኔ ምን ጎድሎባት ነው ሌላ ሰው ጋር የሄደችው
የሚለውን ጥያቄ እራስህን ጠይቅ ምናልባትም ጉዳዩን
በተሻለ መንገድ መረዳት ትችል ይሆናል፡፡
2. ወዲያው ወደ ማኅበራዊ ድህረ-ገጾች በመሄድ
ያደረሰብሽን በደል እና ጉዳት፣ ጭካኔውን በንዴት እና
በስሜት ተገፋፍተሸ ይፋ አታድርጊው፤ ምላሾችሽ በሙሉ
በተቻለ መጠን ከስሜታዊነት የጸዱ እና ማስተዋል
የታከለባቸው ይሁኑ፡፡
3. በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ለማሰብ እንኳን የሚከብድ
ቢመስልህና ፈጽሞ አይሞከርም ብትልም እንደው
ምናልባት ያሁኑን በደልና ጉዳት ይቅር ብዬ ይቅርታ
አድረጌላት አብረን እንቀጥል ይሆናል ብለህ አስብ፤
ለዚህም ያመችህ ዘንድ ለሁሉም ጓደኞችህ እና ቤተሰብ
ያለውን በሙሉ ዝርግፍ አድርገህ አትንገር ምክንያቱም
ከይቅርታ በኋላ ለሚመጣው ህይወት ተጽእኖ
ሊያሳድሩብህ ይችላሉ፡፡
4. ከላይ ለሁሉም ቤተሰቦችሽ እና ጓደኞችሽ መናገር ጥሩ
ውጤት አይኖረውም ቢባበልም ግን ሚስጥርሽን
ልታጋሪው የምትችይው ሁነኛ የልብ ወዳጅ
ያስፈልግሻል፡፡ ከዛ በኋላ ያለው ግንኙነትሽ ተስተካከለም
አልተስተካከለም የልብሽን የምታዋይው፣ስሜትሽን
የምትገልጭለት እና ጭንቀትሽን የምተነፍሽበት አንድ
ሰው ያስፈልግሻል፤ ግን ይሄን ሰው በጥንቃቄ ምረጪ፡፡
5. ባንድ ጊዜ ወስነህ ሁሉን ነገር ጠቅለህ አትውጣ፤
በአንድ ጣሪያ ስር እንኳን ቆይተህ በአጽንኦት ማሰላሰል
ካቃተህ ለተወሰነ ጊዜ የሆነ ቦታ ሁን እና ከስሜት በጸዳ
መልኩ ጉዳዩን እያወጣህ አውርድ፡፡
6. በቀል ነገሮችን አያስተካክልም፡፡ ስሜታዊ እና አካላዊ
የሆነ ጥቃቶችን ለጎዳን ሰው መሰንዘር ወደፊት
ለሚኖራችሁ ግንኙነቶች (በነበራችሁም ነገር ላይ
ለመቀጠል ወይም እንደ ጓደኛ ለመሆን) ችግር
ይፈጥራል ስለዚህ ከእነዚህ መራቅ አስፈላጊ ነው፡፡
7. በማኅበራዊ ድህረ-ገጽ ላይ የጎዳሽን ሰው አትከታተይው
ሲንግል ብሎ ጽፏል ወይስ በግንኙነት ውስጥ ነው፣ ማን
ታግ አድርጋዋለች፣ የማንን ፎቶ ወድዷል ማንስ ላይ
ኮሜንት አድርጓል እና የመሳሰሉ ነገሮችን አትከታተይ
እንደዚህ ዓይነት ነገሮች የጊዜ እና ጉልበት መጨረሻዎች
ናቸውና ተያቸው፡፡
8. ልጆች ካሏችሁ ደግሞ የበለጠ ጥንቃቄ አድርጉ፤ አንቺን
ሊበድልሽ ፣ ሊያዛንሽ እና በላይሽ ላይ ሄዶ ሊሆን
ይችላል ሆኖም ግን ለልጆቹ አሁንም አባታቸው ነው
ስለዚህ ስለ እርሱ የምታወሪው ነገር አነሱን እንዳይጎዳ
ጥንቃቄ አድርጊ፡፡
በእነዚህ ነጥቦች ብቻ ህይወት እንደበፊቱ ትቀጥላለች ብለን
መደምደም አንችልም፤ ከውስልትና በኋላ ግንኙነት ሊቀጥል
ይችላል ካልሆነም ዓይንህ/ዓይንሽ ላፈር ሊባልም ይችላል፡፡
በመጨረሻም እንዲህ ዓይነት ችግሮች ሲፈጠሩ ለእራሳችን
ከማዘን እና እራሳችንን መውቀስ ትተን በበለጠ እራሳችንን
ለመረዳት በቂ ጊዜ እና አማራጮች እንስጥ;፡፡
join👇
@httptelegramme81biniyamin
ሰላም ወዳጆች፤ ከዚህ በፊት በጾታዊ የፍቅር ግንኙነት ዙሪያ
አያሌ ጉዳዮችን ተወያይተናል፤ ምናልባትም ደግሞ እሰከዛሬ
ያልተነሳው ነጥብ ከላይ በርዕሱ ላይ ያነበባችሁት ነው፡፡
እርግጥ ነው ቃሉ ያስጠላል (ከድርጊቱ ባይብስም) ሆኖም
ግን ማለዘቢያ የሚሆን ምትክ ቃል ማግኘት ስላልቻልን
እንደወረደ cheating የሚለውን እንግሊዝኛ ቃል
ተርጉመናዋል ደግሞም ግንባርን ግንባር ካላልነው ምን
ልንለው ነው? የብዙ ጥንዶች የፍቅር ግንኙነት በውስልትና
ምክንያት ተቋርጧል፣ ቤተሰብ ተበጥብጦ ልጆች
ተበትነዋል፤ ሆኖም ግን በእንደዚህ ዓይነት ከባድ የፍቅር
ግንኙነት አደጋ ውስጥ ለማለፍ ጥቂት ጥቆማዎች ብሎ
ሳይኮሎጂ ቱደይ የተባለው ድህረ-ገጽ ያወጣውን አንድ
ጽሑፍ ይዘንላችሁ ቀርበናል መልካም ንባብ፡-
1. ከእኔ ምን ጎድሎባት ነው ሌላ ሰው ጋር የሄደችው
የሚለውን ጥያቄ እራስህን ጠይቅ ምናልባትም ጉዳዩን
በተሻለ መንገድ መረዳት ትችል ይሆናል፡፡
2. ወዲያው ወደ ማኅበራዊ ድህረ-ገጾች በመሄድ
ያደረሰብሽን በደል እና ጉዳት፣ ጭካኔውን በንዴት እና
በስሜት ተገፋፍተሸ ይፋ አታድርጊው፤ ምላሾችሽ በሙሉ
በተቻለ መጠን ከስሜታዊነት የጸዱ እና ማስተዋል
የታከለባቸው ይሁኑ፡፡
3. በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ለማሰብ እንኳን የሚከብድ
ቢመስልህና ፈጽሞ አይሞከርም ብትልም እንደው
ምናልባት ያሁኑን በደልና ጉዳት ይቅር ብዬ ይቅርታ
አድረጌላት አብረን እንቀጥል ይሆናል ብለህ አስብ፤
ለዚህም ያመችህ ዘንድ ለሁሉም ጓደኞችህ እና ቤተሰብ
ያለውን በሙሉ ዝርግፍ አድርገህ አትንገር ምክንያቱም
ከይቅርታ በኋላ ለሚመጣው ህይወት ተጽእኖ
ሊያሳድሩብህ ይችላሉ፡፡
4. ከላይ ለሁሉም ቤተሰቦችሽ እና ጓደኞችሽ መናገር ጥሩ
ውጤት አይኖረውም ቢባበልም ግን ሚስጥርሽን
ልታጋሪው የምትችይው ሁነኛ የልብ ወዳጅ
ያስፈልግሻል፡፡ ከዛ በኋላ ያለው ግንኙነትሽ ተስተካከለም
አልተስተካከለም የልብሽን የምታዋይው፣ስሜትሽን
የምትገልጭለት እና ጭንቀትሽን የምተነፍሽበት አንድ
ሰው ያስፈልግሻል፤ ግን ይሄን ሰው በጥንቃቄ ምረጪ፡፡
5. ባንድ ጊዜ ወስነህ ሁሉን ነገር ጠቅለህ አትውጣ፤
በአንድ ጣሪያ ስር እንኳን ቆይተህ በአጽንኦት ማሰላሰል
ካቃተህ ለተወሰነ ጊዜ የሆነ ቦታ ሁን እና ከስሜት በጸዳ
መልኩ ጉዳዩን እያወጣህ አውርድ፡፡
6. በቀል ነገሮችን አያስተካክልም፡፡ ስሜታዊ እና አካላዊ
የሆነ ጥቃቶችን ለጎዳን ሰው መሰንዘር ወደፊት
ለሚኖራችሁ ግንኙነቶች (በነበራችሁም ነገር ላይ
ለመቀጠል ወይም እንደ ጓደኛ ለመሆን) ችግር
ይፈጥራል ስለዚህ ከእነዚህ መራቅ አስፈላጊ ነው፡፡
7. በማኅበራዊ ድህረ-ገጽ ላይ የጎዳሽን ሰው አትከታተይው
ሲንግል ብሎ ጽፏል ወይስ በግንኙነት ውስጥ ነው፣ ማን
ታግ አድርጋዋለች፣ የማንን ፎቶ ወድዷል ማንስ ላይ
ኮሜንት አድርጓል እና የመሳሰሉ ነገሮችን አትከታተይ
እንደዚህ ዓይነት ነገሮች የጊዜ እና ጉልበት መጨረሻዎች
ናቸውና ተያቸው፡፡
8. ልጆች ካሏችሁ ደግሞ የበለጠ ጥንቃቄ አድርጉ፤ አንቺን
ሊበድልሽ ፣ ሊያዛንሽ እና በላይሽ ላይ ሄዶ ሊሆን
ይችላል ሆኖም ግን ለልጆቹ አሁንም አባታቸው ነው
ስለዚህ ስለ እርሱ የምታወሪው ነገር አነሱን እንዳይጎዳ
ጥንቃቄ አድርጊ፡፡
በእነዚህ ነጥቦች ብቻ ህይወት እንደበፊቱ ትቀጥላለች ብለን
መደምደም አንችልም፤ ከውስልትና በኋላ ግንኙነት ሊቀጥል
ይችላል ካልሆነም ዓይንህ/ዓይንሽ ላፈር ሊባልም ይችላል፡፡
በመጨረሻም እንዲህ ዓይነት ችግሮች ሲፈጠሩ ለእራሳችን
ከማዘን እና እራሳችንን መውቀስ ትተን በበለጠ እራሳችንን
ለመረዳት በቂ ጊዜ እና አማራጮች እንስጥ;፡፡
join👇
@httptelegramme81biniyamin
ውድ የትዳርና የፍቅር ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ ??
ለሁላችሁም ባላችሁበት ጤና፣ ፍቅር ፣ ሰላምና እና ደስታን
ተመኘሁላችሁ፡፡ በባለፈው ጽሁፌ ስለ ወሲብ ችግሮች
እንዲሁም መንስዔዎች ጥቂት አውርተን ለመፍትሄዎቹ
ደግሞ በቀጠሮ ተለያይተን እንደነበር ይታወሳል ሰለሆነም
በቀጠሮአችን መሰረት ከተፍ ብያለሁ፡፡ (በነገራችን ላይ
የባለፈውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም አስታውሶ ከዚህኛው ጋር
በማሰናሰል ለመቀጠል ለምትሹ ገጻችንን ወደ ኋላ ተጉዞ
በመጎበኘት የወሲብ ችግሮችና መንስዔዎች የሚለውን
ማየት እንደምትችሉ እንገልጻለን) ስለዚህ ችግር ካለ
መፍትሄ አለው ያለው ማን ነበር?? ያለፈው ጽሁፍ ላይ
እንዳነበባችሁት የተለያዩ የወሲብ ችግሮችን እና
መንስዔዎቻቸውን እያነሳን ስንጥል ነበር… እህሳ
መፍትሄውስ እንደምትሉ አንጠራጠርም ደግሞም በግበረ
መልስም እንዲሁም በውስጥ መልዕክትም ብላችሁን ነበር፡፡
ስለዚህ ጥቂት የመፍትሄ ሃሳቦችን እንካችሁ ብለናል፡-
1. ሳይኮሎጂካዊ መፍትሄ
እንደው በደምሳሳው ሳይኮሎጂካዊ መፍትሄ ስንል
የወሲብ ችግር ለሚያጋጥማቸው ሰዎች sex therapy
ወይም cognitive behavioral therapy በግርድፉ
አማርኛ ትርጉሙ የአስተሳሰብና የጠባይ ነክ የምክክር
አገልግሎት ይመከራል፡፡ በዚህም ሰዎችን ስለ ወሲብ፣
ጤናማ የወሲብ ባህርይ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ
ከባለሙያ ጋር ምክክር በማድረግ በተለይ ደግሞ
በባለፈው ጽሁፍ የጠቀስናቸውን በወሲብ ጊዜ የሚመጡ
ወሲብ ነክ ያልሆኑ ሀሳቦችን የመቀየሪያ ወይም
የማጥፊያ መንገዶችን በማሳየት ረገድ ዓይነተኛ ሚና
ይጫወታል፤ cognitive behavioral therapy እነዚህን
ሃሰቦች እንዴት መለወጥ እንደምንችል ያመላክተናል፡፡
ለአብነት ያህልም በወሲብ ጊዜ በተደጋጋሚ
የሚመጡብንን ወሲብ ነክ ያልሆኑ ሀሳቦች በሚከሰቱበት
ጊዜ አዕምሮአችንን በወሲቡ ወደ ሚገኘው ደስታ እና
እርካታ በማሰብ እንዲሁም በመምራት ይህን እንዴት
ማስቀረት እንደምንችል ያሳየናል፡፡ ለዚህም ደግሞ
የሳይኮሎጂስት ወይም የሳይካትሪስት እርዳታ መጠየቅ
ይኖርብናል፡፡
ቀድሞ የመጨረስ ችግር (premature ejaculation)
ቃሉን ለዘብ ሲያደረጉት ደግሞ (Early ejaculation)
ይሉታል፡- በባለፈው ጽሁፋችን ላይ እንደገለጽነው በርካታ
ችግሮችን ያስከትላል ከእነዚህም መካከል በራስ
መተማመንን ይሸረሽራል፣ የፍቅር ግንኙነቶችን ያቋርጣል፣
ከእኔ ውጪ እርካታን ፍለጋ ትሄድ ይሆን በማለት
የመተማመን ችግርን ያመጣል፣ እንዲሁም ቀጣይ
የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር እክል መሆን ጥቂቶቹ
ናቸው፡፡
ቀድሞ የመጨረስ ችግር ያለብን ሰዎች ካለን ደግሞ ለዚህ
መፍትሄ የሚሆነን በወሲብ ጊዜ ይህ የሚከሰትበትን ወቅት
መለየት የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን ይህም ማለት የዘር
ፈሳሽ ከሚወጣበት ቅጽበት ትንሽ ቀደም ብሎ ያለው እና
መመለስ የማንችልበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ነው ፡፡
ቀጥሎም ከፍቅር አጋራችን ጋር በተያያዘ ጥቂት ሀሳቦችን
ማሰብ ለምሳሌ የት እንደተገናኛቹ፣ የምትወደው ምግብ
ወይም ደግሞ አንተ የምትወደው የእግር ኳስ ቡድን
የመጨረሻ ግጥሚያውን እንዴት እንደተወጣው ማስታወስ
የመሳሰሉትን ለቅጽበት ማሰብ ቀድሞ መጨረስን
ሊከላከልልን ይችላል፡፡ እዚህ ጋር ዋናው ነጥብ አዕምሮህን
ከወሲቡ በጥቂቱም ቢሆን ሰርቆ መውሰድና ቀድሞ
መጨረስን ማዘግየት ነው፡፡ ሆኖም ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን
ሀሳባችን ቅጽበታዊ መሆን አለበት ካልሆነ ሌላ ችግር
ያመጣብናል፡፡ ሌላው ወሲብ የሚፈጸምበትን አካሄድ
(position) እየቀያየሩ መሞከር ይመከራል ይህንንም ስንል
ሴቷ ከላይ በመሆን ፍጥነቱን እየተቆጣጠረች በመቀጠል
ችግሩን መቀነስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የፍቅር አጋራችን
ከፍተኛው የእርካታ ደረጃ ላይ እስክትደርስ ድረስ ማነቃቃት
(Warming up) እና ወደ ዋናው ተግባር መግባት እንደ አንድ
መንገድ ይጠቀሳል፡፡ ሴቶች እንደዚህ ዓይነት ችግር
ያለባቸው ወንዶችን መረዳት እና ችግሩ ጊዜያዊና
አስፈላጊውን ሂደት ከተሄደበት እንደሚሰተካከል በማመን
የፍቅር አጋራቹ የሚደርስበትን የስነ-ልቦና ጉዳት መቀነስ
ወይም ማጥፋት እንደሚቻል ማመን ፣ አብሮነት እና ድጋፍን
ማሳየት አስፈላጊ ነው፡፡
ለብልት አለመቆም ችግር እና ለውስን የወሲብ ፍላጎት
እንደመፍትሄ ከተጠቆሙት ነጥቦች መካከል
የመጀመሪያውን ደረጃ የያዙት ሰለ እራሳችን ሰነ-ልቦናዊ
እና አካላዊ ማንነት አዎንታዊ አመለካከትን ማዳበር፣
የኑሮ ዘዬን መለወጥ ለምሳሌ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን
ማዘውተር፣ አልኮል መጠጥን አዘውትሮ ወይም ከመጠን
አሳልፎ አለመጠቀም፣ ሲጋራ ማጨስ ማቆም
የመሳሰሉት የተጠቀሱ ሲሆን በተጨማሪም ጥንዶች ወደ
ባለሙያ በመሄድ የምክክር አገልግሎት የሚያገኙበትን
መንገድ ማመቻቸት ዓይነተኛ መላ ነው፡፡
ግለ ወሲብ (masturbation)፤ በነገራችን ላይ ግለ
ወሲብ የሚለውን ቃል በተለምዶ ስለተዘወተረ ነው
እንጂ masturbation ለሚለው እንግሊዝኛ ቃል እንደ
ዓይነተኛ ፍቺ ሆኖ አያገለግልም ምክንያቱም በሁለት
ተጓዳኞች መካከል እርስ በእርስ የመራቢያ
አካላቶቻቸውን እየነካኩ እርካታ ላይ መድረስም mutual
masturbation ይባላል፡፡ ስለዚህም masturbation
ለብቻ የሚደረግ የወሲብ እርካታ ጋር መድረሻ መንገድ
ብቻ አይደለም፡፡
ግለ ወሲብ በተለያዩ ባህል ባላቸው የዓለማችን ክፍሎች
እንዲሁም ሰዎች የሚፈጽሙት ተግባር ነው ሆኖም ግን
ገደቡን ያልፍና ሱስ የሚሆንበት እንዲሁም ማቆም
የማንችልበት ደረጃ ላይ ያደርሰናል፡፡ በዚህም ማህበራዊ
ህይወታችንን በማቃወስ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይከተናል፡፡
ስለዚህ ግለ ወሲብን ለማቆም ወይም ድግግሞሹን
ለመቀነስ ጥቂት እንበል… የመጀመሪያው ከግለ ወሲብ
በኋላ የሚፈጠረውን የጥፋተኝነት ስሜት ማሰወገድ
እንዲሁም ችግሩን መቀበል አለብን ምክንያቱም እንደዚህ
ዓይነት ስሜቶች ድርጊቱን በተደጋጋሚ እንድንፈጽመው
ይገፋፉናል፣ ወሲብ ቀስቃሽ ነገሮችን ማስወገድ ለምሳሌ
ወሲባዊ መጽሄቶች፣ ፊልሞች ፣ምስሎች እንዲሁም ድህረ
ገጾችን ማስወገድ፣ ማህበራዊ ግንኙነትን መጨመር እና
እራሳችንን በስራ መወጠር ይህም ብቻችንን የምንሆንበትን
ጊዜ በመቀነስ ግለ ወሲብን ይቀንሳል፣ ምስጢር ጠባቂ ሰው
ፈልገን ችግራችን እናካፍል፣ ሌላው ቁርጠኝነት ሲሆን ይህም
ግለ ወሲብን ለማቆም ከወሰንን በኋላ ቁርጠኝነት ፣ትዕግስት
እና ጽናት ያስፈልጋል፡፡
የጥንዶች ምክክር (Couples therapy)
በዚህም ጥንዶች ግጭቶችን በሚፈቱባቸው፣
ውጥረቶችን በሚያስተናግዱባቸው፣ ልባዊ ጓደኝነትን
በሚያጠናክሩበት፣ የህይወት ዘያቸውን በሚቀይሩበት፣
ተግባቦታቸውን በሚጨምሩበት እና በመሳሰሉት ላይ
ምክክር በማድረግ በወሲብ ችግር ላይ መፍትሄ ላይ
ለመድረስ ይቻላል፡፡
በባለትዳሮች መካከል የሚፈጠርን የወሲብ ፍላጎት
ችግር ለማጥፋት ወይም … ለመቀነስ ከሚመከሩት
ነጥቦች መካከል መኝታ ቤትን ለእይታ ቀለል ባለ ቀለም
መቀባት እና ትኩረትን የሚሰርቁ ጽሁፎችና ምስሎችን
በብዛት አለመስቀል ወይም አለመለጠፍ፣ አልጋችን ላይ
የህፃናት ልጆቻችን መጫወቻዎች መሳሰሉት እንዳይኖሩ
ማድረግ፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉትን
የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመኝታ ቤት ውስጥ ያለ
አጠቃቀም መገደብ የመሳሰሉትን በባለትዳሮች መካከል
ያለን የወሲብ ህይወትን ከማጣፈጫ መንገዶች መካከል
ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
2. በህክምና ባለሙያ የሚታዘዙ መድኃኒቶች
ለወሲብ ችግር እንደተጨማሪ የመፍትሔ አቅጣጫ
የሚቀመጠው በህክምና በባለሙያዎች የሚታዘዝ
መድኃኒት ነው፤ ሆኖም ግን እነዚህን መድኃኒቶች
ደጋግሞ መጠቀም የመድሃኒቶቹን
ለሁላችሁም ባላችሁበት ጤና፣ ፍቅር ፣ ሰላምና እና ደስታን
ተመኘሁላችሁ፡፡ በባለፈው ጽሁፌ ስለ ወሲብ ችግሮች
እንዲሁም መንስዔዎች ጥቂት አውርተን ለመፍትሄዎቹ
ደግሞ በቀጠሮ ተለያይተን እንደነበር ይታወሳል ሰለሆነም
በቀጠሮአችን መሰረት ከተፍ ብያለሁ፡፡ (በነገራችን ላይ
የባለፈውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም አስታውሶ ከዚህኛው ጋር
በማሰናሰል ለመቀጠል ለምትሹ ገጻችንን ወደ ኋላ ተጉዞ
በመጎበኘት የወሲብ ችግሮችና መንስዔዎች የሚለውን
ማየት እንደምትችሉ እንገልጻለን) ስለዚህ ችግር ካለ
መፍትሄ አለው ያለው ማን ነበር?? ያለፈው ጽሁፍ ላይ
እንዳነበባችሁት የተለያዩ የወሲብ ችግሮችን እና
መንስዔዎቻቸውን እያነሳን ስንጥል ነበር… እህሳ
መፍትሄውስ እንደምትሉ አንጠራጠርም ደግሞም በግበረ
መልስም እንዲሁም በውስጥ መልዕክትም ብላችሁን ነበር፡፡
ስለዚህ ጥቂት የመፍትሄ ሃሳቦችን እንካችሁ ብለናል፡-
1. ሳይኮሎጂካዊ መፍትሄ
እንደው በደምሳሳው ሳይኮሎጂካዊ መፍትሄ ስንል
የወሲብ ችግር ለሚያጋጥማቸው ሰዎች sex therapy
ወይም cognitive behavioral therapy በግርድፉ
አማርኛ ትርጉሙ የአስተሳሰብና የጠባይ ነክ የምክክር
አገልግሎት ይመከራል፡፡ በዚህም ሰዎችን ስለ ወሲብ፣
ጤናማ የወሲብ ባህርይ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ
ከባለሙያ ጋር ምክክር በማድረግ በተለይ ደግሞ
በባለፈው ጽሁፍ የጠቀስናቸውን በወሲብ ጊዜ የሚመጡ
ወሲብ ነክ ያልሆኑ ሀሳቦችን የመቀየሪያ ወይም
የማጥፊያ መንገዶችን በማሳየት ረገድ ዓይነተኛ ሚና
ይጫወታል፤ cognitive behavioral therapy እነዚህን
ሃሰቦች እንዴት መለወጥ እንደምንችል ያመላክተናል፡፡
ለአብነት ያህልም በወሲብ ጊዜ በተደጋጋሚ
የሚመጡብንን ወሲብ ነክ ያልሆኑ ሀሳቦች በሚከሰቱበት
ጊዜ አዕምሮአችንን በወሲቡ ወደ ሚገኘው ደስታ እና
እርካታ በማሰብ እንዲሁም በመምራት ይህን እንዴት
ማስቀረት እንደምንችል ያሳየናል፡፡ ለዚህም ደግሞ
የሳይኮሎጂስት ወይም የሳይካትሪስት እርዳታ መጠየቅ
ይኖርብናል፡፡
ቀድሞ የመጨረስ ችግር (premature ejaculation)
ቃሉን ለዘብ ሲያደረጉት ደግሞ (Early ejaculation)
ይሉታል፡- በባለፈው ጽሁፋችን ላይ እንደገለጽነው በርካታ
ችግሮችን ያስከትላል ከእነዚህም መካከል በራስ
መተማመንን ይሸረሽራል፣ የፍቅር ግንኙነቶችን ያቋርጣል፣
ከእኔ ውጪ እርካታን ፍለጋ ትሄድ ይሆን በማለት
የመተማመን ችግርን ያመጣል፣ እንዲሁም ቀጣይ
የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር እክል መሆን ጥቂቶቹ
ናቸው፡፡
ቀድሞ የመጨረስ ችግር ያለብን ሰዎች ካለን ደግሞ ለዚህ
መፍትሄ የሚሆነን በወሲብ ጊዜ ይህ የሚከሰትበትን ወቅት
መለየት የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን ይህም ማለት የዘር
ፈሳሽ ከሚወጣበት ቅጽበት ትንሽ ቀደም ብሎ ያለው እና
መመለስ የማንችልበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ነው ፡፡
ቀጥሎም ከፍቅር አጋራችን ጋር በተያያዘ ጥቂት ሀሳቦችን
ማሰብ ለምሳሌ የት እንደተገናኛቹ፣ የምትወደው ምግብ
ወይም ደግሞ አንተ የምትወደው የእግር ኳስ ቡድን
የመጨረሻ ግጥሚያውን እንዴት እንደተወጣው ማስታወስ
የመሳሰሉትን ለቅጽበት ማሰብ ቀድሞ መጨረስን
ሊከላከልልን ይችላል፡፡ እዚህ ጋር ዋናው ነጥብ አዕምሮህን
ከወሲቡ በጥቂቱም ቢሆን ሰርቆ መውሰድና ቀድሞ
መጨረስን ማዘግየት ነው፡፡ ሆኖም ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን
ሀሳባችን ቅጽበታዊ መሆን አለበት ካልሆነ ሌላ ችግር
ያመጣብናል፡፡ ሌላው ወሲብ የሚፈጸምበትን አካሄድ
(position) እየቀያየሩ መሞከር ይመከራል ይህንንም ስንል
ሴቷ ከላይ በመሆን ፍጥነቱን እየተቆጣጠረች በመቀጠል
ችግሩን መቀነስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የፍቅር አጋራችን
ከፍተኛው የእርካታ ደረጃ ላይ እስክትደርስ ድረስ ማነቃቃት
(Warming up) እና ወደ ዋናው ተግባር መግባት እንደ አንድ
መንገድ ይጠቀሳል፡፡ ሴቶች እንደዚህ ዓይነት ችግር
ያለባቸው ወንዶችን መረዳት እና ችግሩ ጊዜያዊና
አስፈላጊውን ሂደት ከተሄደበት እንደሚሰተካከል በማመን
የፍቅር አጋራቹ የሚደርስበትን የስነ-ልቦና ጉዳት መቀነስ
ወይም ማጥፋት እንደሚቻል ማመን ፣ አብሮነት እና ድጋፍን
ማሳየት አስፈላጊ ነው፡፡
ለብልት አለመቆም ችግር እና ለውስን የወሲብ ፍላጎት
እንደመፍትሄ ከተጠቆሙት ነጥቦች መካከል
የመጀመሪያውን ደረጃ የያዙት ሰለ እራሳችን ሰነ-ልቦናዊ
እና አካላዊ ማንነት አዎንታዊ አመለካከትን ማዳበር፣
የኑሮ ዘዬን መለወጥ ለምሳሌ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን
ማዘውተር፣ አልኮል መጠጥን አዘውትሮ ወይም ከመጠን
አሳልፎ አለመጠቀም፣ ሲጋራ ማጨስ ማቆም
የመሳሰሉት የተጠቀሱ ሲሆን በተጨማሪም ጥንዶች ወደ
ባለሙያ በመሄድ የምክክር አገልግሎት የሚያገኙበትን
መንገድ ማመቻቸት ዓይነተኛ መላ ነው፡፡
ግለ ወሲብ (masturbation)፤ በነገራችን ላይ ግለ
ወሲብ የሚለውን ቃል በተለምዶ ስለተዘወተረ ነው
እንጂ masturbation ለሚለው እንግሊዝኛ ቃል እንደ
ዓይነተኛ ፍቺ ሆኖ አያገለግልም ምክንያቱም በሁለት
ተጓዳኞች መካከል እርስ በእርስ የመራቢያ
አካላቶቻቸውን እየነካኩ እርካታ ላይ መድረስም mutual
masturbation ይባላል፡፡ ስለዚህም masturbation
ለብቻ የሚደረግ የወሲብ እርካታ ጋር መድረሻ መንገድ
ብቻ አይደለም፡፡
ግለ ወሲብ በተለያዩ ባህል ባላቸው የዓለማችን ክፍሎች
እንዲሁም ሰዎች የሚፈጽሙት ተግባር ነው ሆኖም ግን
ገደቡን ያልፍና ሱስ የሚሆንበት እንዲሁም ማቆም
የማንችልበት ደረጃ ላይ ያደርሰናል፡፡ በዚህም ማህበራዊ
ህይወታችንን በማቃወስ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይከተናል፡፡
ስለዚህ ግለ ወሲብን ለማቆም ወይም ድግግሞሹን
ለመቀነስ ጥቂት እንበል… የመጀመሪያው ከግለ ወሲብ
በኋላ የሚፈጠረውን የጥፋተኝነት ስሜት ማሰወገድ
እንዲሁም ችግሩን መቀበል አለብን ምክንያቱም እንደዚህ
ዓይነት ስሜቶች ድርጊቱን በተደጋጋሚ እንድንፈጽመው
ይገፋፉናል፣ ወሲብ ቀስቃሽ ነገሮችን ማስወገድ ለምሳሌ
ወሲባዊ መጽሄቶች፣ ፊልሞች ፣ምስሎች እንዲሁም ድህረ
ገጾችን ማስወገድ፣ ማህበራዊ ግንኙነትን መጨመር እና
እራሳችንን በስራ መወጠር ይህም ብቻችንን የምንሆንበትን
ጊዜ በመቀነስ ግለ ወሲብን ይቀንሳል፣ ምስጢር ጠባቂ ሰው
ፈልገን ችግራችን እናካፍል፣ ሌላው ቁርጠኝነት ሲሆን ይህም
ግለ ወሲብን ለማቆም ከወሰንን በኋላ ቁርጠኝነት ፣ትዕግስት
እና ጽናት ያስፈልጋል፡፡
የጥንዶች ምክክር (Couples therapy)
በዚህም ጥንዶች ግጭቶችን በሚፈቱባቸው፣
ውጥረቶችን በሚያስተናግዱባቸው፣ ልባዊ ጓደኝነትን
በሚያጠናክሩበት፣ የህይወት ዘያቸውን በሚቀይሩበት፣
ተግባቦታቸውን በሚጨምሩበት እና በመሳሰሉት ላይ
ምክክር በማድረግ በወሲብ ችግር ላይ መፍትሄ ላይ
ለመድረስ ይቻላል፡፡
በባለትዳሮች መካከል የሚፈጠርን የወሲብ ፍላጎት
ችግር ለማጥፋት ወይም … ለመቀነስ ከሚመከሩት
ነጥቦች መካከል መኝታ ቤትን ለእይታ ቀለል ባለ ቀለም
መቀባት እና ትኩረትን የሚሰርቁ ጽሁፎችና ምስሎችን
በብዛት አለመስቀል ወይም አለመለጠፍ፣ አልጋችን ላይ
የህፃናት ልጆቻችን መጫወቻዎች መሳሰሉት እንዳይኖሩ
ማድረግ፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉትን
የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመኝታ ቤት ውስጥ ያለ
አጠቃቀም መገደብ የመሳሰሉትን በባለትዳሮች መካከል
ያለን የወሲብ ህይወትን ከማጣፈጫ መንገዶች መካከል
ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
2. በህክምና ባለሙያ የሚታዘዙ መድኃኒቶች
ለወሲብ ችግር እንደተጨማሪ የመፍትሔ አቅጣጫ
የሚቀመጠው በህክምና በባለሙያዎች የሚታዘዝ
መድኃኒት ነው፤ ሆኖም ግን እነዚህን መድኃኒቶች
ደጋግሞ መጠቀም የመድሃኒቶቹን
ፈዋሽነት ቀስ በቀስ
ይቀንሱታል፡፡ በተጨማሪም ለወሲብ ተብለው
ከሚወሰዱ መድኃኒቶች መካከል የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸው
እንዳሉ ልብ ይሏል፡፡ ከእነዚህም ጉዳቶች መካከል
ከወሲብ በኋላ ለረጅም ጊዜ ብልት ወደ ቀደሞ ቦታው
ላይመለስ ይችላል ይህም ከፍተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊና
አካላዊ ጉዳቶችን ይፈጥራል፡፡
ከላይ የጠቀስናቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች በተለይ
ሳይኮሎጂካዊው እኛ ሀገር በሰፊው የተለመደ ስላልሆነ
እነዚህን የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደ መነሻ በማድረግ
ችግራችንን ወደ ራሳችን ዘዬ ለውጠን (contextualized
manner) ማየት ይኖርብናል፡፡
ሰላማቹሁ ይብዛ
@httptelegramme81biniyamin
ይቀንሱታል፡፡ በተጨማሪም ለወሲብ ተብለው
ከሚወሰዱ መድኃኒቶች መካከል የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸው
እንዳሉ ልብ ይሏል፡፡ ከእነዚህም ጉዳቶች መካከል
ከወሲብ በኋላ ለረጅም ጊዜ ብልት ወደ ቀደሞ ቦታው
ላይመለስ ይችላል ይህም ከፍተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊና
አካላዊ ጉዳቶችን ይፈጥራል፡፡
ከላይ የጠቀስናቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች በተለይ
ሳይኮሎጂካዊው እኛ ሀገር በሰፊው የተለመደ ስላልሆነ
እነዚህን የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደ መነሻ በማድረግ
ችግራችንን ወደ ራሳችን ዘዬ ለውጠን (contextualized
manner) ማየት ይኖርብናል፡፡
ሰላማቹሁ ይብዛ
@httptelegramme81biniyamin
ስራ ፍቅርና ተስፋ👍 ባለቅኔው ጆን ባሮውስ መስኮቱ ላይ ቆም ብሎ ሲቃኝ አንድ
ጎረቤቱ በቤቱ ጥግ ሲያልፍ ተመለከተ፡፡ ሰውዬም በደስታና
በርካታ መንፈስ ሳይሆን በትካዜና በጭንቀት አቀርቅሮ ነበር
የሚንገላወደው፡፡
ለዚህ ሁኔታው ያበቃው ምን እነደሆነ ጆን ባሮውስ ተረዳለት፡፡
ሰውዬው የሚወደውና የሚመስጠው ጊዜውን ትርጉምና
አቅጣጫ የሚሰጥለት ምንም ዓይነት ሥራ አልነበረውም፡፡
ሥራ ያጣ ሰው ለሥቃይ የተዳረገ ነው ሲል ባሮውስ
ማሰላሰል ያዘ፡፡ የደመቀ የወፎች ኅብረ ዝማሬን እያዳመጠና
ለስላሳ የነፋስ ሽውታ እየተመገበ ባሮውስ በጉዳዩ ላይ
ሲያስብበት ቆየ፡፡
የሥራን ክቡርነትና ህይወት አዳሽነት ከእርሱ ወዲያ
የተገነዘበ አልነበረም፡፡ በአንድ ወቅት እርሱም ራሱ በሥራ
አጥነት ለሥቃይ ከተዳረጉት ምስኪኖች መኻል አንዱ
አልነበር? ያኔ ህይወት ጣዕሟን ነፍጋዋለች ፤ ባዶና ግትር
ሆናበታለች፡፡ ያኔ መብላትም ሆነ መተኛት ፣ መጫወትም ሆነ
መግባባት ተስኖት ነበር፡፡
ሥራ ነፍስ ዘራለት — እርሻ ላይ የመማሰን ፣ የማረስና
የመጎልጎል ፣ የመዝራትና የመትከል ፣ የማረምና የመኮትኮት
… ተግባራት ፣ ለም አፈር ጨብጦ በጣቶቹ መኻል
የመናኘት ሥራ እርሱነቱን ከሚኖርባት ዓለም ጋር
እንዳዋሐደለት በሚገባ ያውቀዋል፡፡
ደስታ ፣ እንደ ህልም ቦግ እልም የማትልና ዘወትር
ከአጠገብ የምትገኝ መሆኗን ለሰዎች ለማስረዳት ምንኛ
ተጣጣረ! ግን ፣ በዙሪያው የነበሩት ሁሉ ተስፋ
በሚያስቆርጥ መንገድ እየዋተቱ ህይወታቸውን ሲከትሩት
መመልከቱ አላስችል ብሎት የደስታ ምንጩ ሥራ ፣
መንፈስን የሚመስጥ ሥራ መሆኑን ለማስገንዘብ ቆርጦ
ተነሣ፡፡
ከማንኛውም ነገር ሁሉ በላቀ ሁኔታ ደስታን የሚለግስ አንድ
ነገር አለ ፤ ምን ይሆን?… በጣም ቀላልና በእጅ የሚገኝ
ነው፡፡ ይህን ምስጢር ለጨረታ ላቀርበው ብችል ምን ያህል
ሰው በጎረፈ! ዋጋውም ምንኛ በናረ! ብልሆች ብቻ ናቸው
ምንነቱን የሚገምቱት፡፡ አንዳንዶቹ ጤንነት ፣ ወይም ገንዘብ
፣ ወይም ባልንጀራ ፣ ወይም ይህን ወይ ያን ሃብት ይሉ
ይሆናል፡፡ ግን ፣ እነዚህ ሁሉ ተሟልተው ደስታ አትኖርም፡፡
ዝናና ሥልጣንም ደስታን አያስገኙም፡፡ ጤንነት ፣ ገንዘብ ፣
ባላንጀራ ፣ የሞቀ ቤት … ሁሉም አስፈላጊ ቢሆኑም ደስታ
አያጎናጽፉምና ከእነዚህ ሁሉ የሚልቅ አንድ ነገር አለ፡፡ ያ
ነገር — ምን ይሆን? ህመምተኛው ጤና ፣ ድሃው ሃብት ፣
ምሁሩ ዕውቀት ፣ እልቅና የሚሻው ሥልጣን ፣ የደከመው
ደግሞ ዕረፍትን ይል ይሆናል በማለት ባሮውስ ማስተማሩን
ጀመረ፡፡
ዓይነተኛውን የደስታ ምንጭ ምንነት አሁን ስነግራችሁ ቅር
ትሰኙ ይሆናል ይላል ባሮውስ፡፡ የተለመደ ፣ በቅርብ ያለ ፣
ብዙ ሰዎች በእጃቸው ያስገቡት ፣ ግን አስደሳችነቱን
ያልተገነዘቡት ጉዳይ ነው፡፡ ወይ ከአቅማቸው በላይ
ሆኖባቸዋል፣ ወይ የሚጥማቸው ሆኖ አላገኙትም፡፡ ጅረት
የሚሻው ዋነኛው ነገር ምንድን ነው? ሳያቋርጥ መንኳለሉን
ይሆናል፡፡ ከተከተረ ጣጣ ይወስዳል፡፡ ሰውም እንዲሁ
የማያቋርጥ እንቅስቃሴን ይሻል — የአካል ፣ የመንፈስ ፣
የጭንቅላት፡፡ ስለዚህ የደስታ ምንጩ ሥራ ፣ የሚጥም ሥራ
ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ ከሥራ ቢታገዱ ዓለማችን ምንኛ የሥቃይ
ቋት በሆነች!
ሥራ የደስታ ምንጭ መሆኑን ፣ በእርሱም በመጠመዳቸው
ህልውናቸውን ከመገዝገዝ መቆጠባቸውን የሚገነዘቡ
በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ደስታ የምትቀርበው አጥብቀው
የሚሿትን ፣ ስለርሷ የሚያብጠለጥሉትን አይደለም — አመች
ሁኔታን በመፍጠር እንጂ፡፡ መከተልን እንጂ መምራትን
አታውቅም፡፡ ፊት ካለችም እርሷን ለመቅደም መሞከሩ
አይበጅም፡፡
በሙሉ ልብ ተመስጦ ፣ ያለ የሌለ ኃይሉን በሚጥመው
ሥራ ላይ የሚያውል ሰው ምንኛ የታደለ ነው! እያለ ባሮውስ
የፍልስፍና አቅጣጫውን ጠቆመ፡፡
በምንወደው ሥራ ተጠምደን ደስታና እርካታን ማግኘት
ከቻልን ሁላቸንም ስለፍቅር በገባን ጥልቀት እናሰባለን፡፡ እንደ
ማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት ሁሉ ለልብ ወዳጅነትም
ዋናው መመሪያ ለመወደድ ከፈለክ ሰው ወዳድ ሁን
የሚለው ነው፡፡ ፍቅርን ልትላበስ ከፈለክ ይላል ዴል
ካርኒጊም በበኩሉ ብቸኛው መንገድ እንዲያፈቅሩህ
መወትወትህን ትተህ ፍቅርህን ለግስ ፣ ፍቅርን ስትሰጥ ብቻ
ነው ፍቅርን የምታገኘው፡፡
ደግነትና መተሳሰብ አስፈላጊ ባሕርያት መሆናቸው
የተዘነጋበት ዘመን ከቶ አይገኝም፡፡ ስለራሱ ብቻ የሚያስብ
ሰው ፣ ራሱን በራሱ የጠቀለለ ኢምንት ቋጠሮ ነው ያለው
ሃሪ ፎስዲክም ይህንኑ እውነታ ከልብ በማጤን ነው፡፡
ብዙ ጊዜ ፍቅር ሰጥቶ መቀበል ነው ሲባል እንሰማለን፡፡
ለራስህ እንዲደረግልህ የምትሻውን ለሌላውም አድርግ
የሚለው አባባል ፣ የሰዎችን ግንኙነት ከሚያዳብሩ ጥንታዊና
ጊዜ የማይሽራቸው ድንጋጌዎች መኻል አንዱ ሲሆን ፣
በግብረ-ገብ መመሪያነቱ ዛሬም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
ኢመርሰን ጓደኛ ለማፍራት ጓደኛ ሁን በማለት ይህንኑ ሃቅ
አስተጋብቷል፡፡
እንግዲህ ይህን ስናደርግ ማናችንም ስለ ነገ የተስፋ
ወኔአችንን ከሌሎች ጋር ብንካፈል ምንኛ መልካም ነው፡፡
እርግጥ ነው እንደ ሲድኒ ዳርክ አባባል፤ ቀደም ያሉት
አባቶቻችን የመኖርንና የመሞትን ምንነት አስተምረውናል፡፡
እኛም ወራሾቻቸው መሆናችንን አንዘንጋ፡፡ ወደ ጦር ግንባር
የሚሄድ ወታደር ጦር ሜዳ መሞት እንዳለ ልቦናው
ቢያውቅም እንኳን በድል ብስራት ዜና ከጓዶቹ ጋር
እንደሚመለስ ያስባል፡፡ ተስፋ የትም አለ፡፡
ለህይወት አስፈላጊዎቹ ቁም ነገሮች ሥራ ፣ ፍቅርና ተስፋ
ናቸው –ጆሴፍ ኤድሰን፡፡
ሼር
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ጎረቤቱ በቤቱ ጥግ ሲያልፍ ተመለከተ፡፡ ሰውዬም በደስታና
በርካታ መንፈስ ሳይሆን በትካዜና በጭንቀት አቀርቅሮ ነበር
የሚንገላወደው፡፡
ለዚህ ሁኔታው ያበቃው ምን እነደሆነ ጆን ባሮውስ ተረዳለት፡፡
ሰውዬው የሚወደውና የሚመስጠው ጊዜውን ትርጉምና
አቅጣጫ የሚሰጥለት ምንም ዓይነት ሥራ አልነበረውም፡፡
ሥራ ያጣ ሰው ለሥቃይ የተዳረገ ነው ሲል ባሮውስ
ማሰላሰል ያዘ፡፡ የደመቀ የወፎች ኅብረ ዝማሬን እያዳመጠና
ለስላሳ የነፋስ ሽውታ እየተመገበ ባሮውስ በጉዳዩ ላይ
ሲያስብበት ቆየ፡፡
የሥራን ክቡርነትና ህይወት አዳሽነት ከእርሱ ወዲያ
የተገነዘበ አልነበረም፡፡ በአንድ ወቅት እርሱም ራሱ በሥራ
አጥነት ለሥቃይ ከተዳረጉት ምስኪኖች መኻል አንዱ
አልነበር? ያኔ ህይወት ጣዕሟን ነፍጋዋለች ፤ ባዶና ግትር
ሆናበታለች፡፡ ያኔ መብላትም ሆነ መተኛት ፣ መጫወትም ሆነ
መግባባት ተስኖት ነበር፡፡
ሥራ ነፍስ ዘራለት — እርሻ ላይ የመማሰን ፣ የማረስና
የመጎልጎል ፣ የመዝራትና የመትከል ፣ የማረምና የመኮትኮት
… ተግባራት ፣ ለም አፈር ጨብጦ በጣቶቹ መኻል
የመናኘት ሥራ እርሱነቱን ከሚኖርባት ዓለም ጋር
እንዳዋሐደለት በሚገባ ያውቀዋል፡፡
ደስታ ፣ እንደ ህልም ቦግ እልም የማትልና ዘወትር
ከአጠገብ የምትገኝ መሆኗን ለሰዎች ለማስረዳት ምንኛ
ተጣጣረ! ግን ፣ በዙሪያው የነበሩት ሁሉ ተስፋ
በሚያስቆርጥ መንገድ እየዋተቱ ህይወታቸውን ሲከትሩት
መመልከቱ አላስችል ብሎት የደስታ ምንጩ ሥራ ፣
መንፈስን የሚመስጥ ሥራ መሆኑን ለማስገንዘብ ቆርጦ
ተነሣ፡፡
ከማንኛውም ነገር ሁሉ በላቀ ሁኔታ ደስታን የሚለግስ አንድ
ነገር አለ ፤ ምን ይሆን?… በጣም ቀላልና በእጅ የሚገኝ
ነው፡፡ ይህን ምስጢር ለጨረታ ላቀርበው ብችል ምን ያህል
ሰው በጎረፈ! ዋጋውም ምንኛ በናረ! ብልሆች ብቻ ናቸው
ምንነቱን የሚገምቱት፡፡ አንዳንዶቹ ጤንነት ፣ ወይም ገንዘብ
፣ ወይም ባልንጀራ ፣ ወይም ይህን ወይ ያን ሃብት ይሉ
ይሆናል፡፡ ግን ፣ እነዚህ ሁሉ ተሟልተው ደስታ አትኖርም፡፡
ዝናና ሥልጣንም ደስታን አያስገኙም፡፡ ጤንነት ፣ ገንዘብ ፣
ባላንጀራ ፣ የሞቀ ቤት … ሁሉም አስፈላጊ ቢሆኑም ደስታ
አያጎናጽፉምና ከእነዚህ ሁሉ የሚልቅ አንድ ነገር አለ፡፡ ያ
ነገር — ምን ይሆን? ህመምተኛው ጤና ፣ ድሃው ሃብት ፣
ምሁሩ ዕውቀት ፣ እልቅና የሚሻው ሥልጣን ፣ የደከመው
ደግሞ ዕረፍትን ይል ይሆናል በማለት ባሮውስ ማስተማሩን
ጀመረ፡፡
ዓይነተኛውን የደስታ ምንጭ ምንነት አሁን ስነግራችሁ ቅር
ትሰኙ ይሆናል ይላል ባሮውስ፡፡ የተለመደ ፣ በቅርብ ያለ ፣
ብዙ ሰዎች በእጃቸው ያስገቡት ፣ ግን አስደሳችነቱን
ያልተገነዘቡት ጉዳይ ነው፡፡ ወይ ከአቅማቸው በላይ
ሆኖባቸዋል፣ ወይ የሚጥማቸው ሆኖ አላገኙትም፡፡ ጅረት
የሚሻው ዋነኛው ነገር ምንድን ነው? ሳያቋርጥ መንኳለሉን
ይሆናል፡፡ ከተከተረ ጣጣ ይወስዳል፡፡ ሰውም እንዲሁ
የማያቋርጥ እንቅስቃሴን ይሻል — የአካል ፣ የመንፈስ ፣
የጭንቅላት፡፡ ስለዚህ የደስታ ምንጩ ሥራ ፣ የሚጥም ሥራ
ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ ከሥራ ቢታገዱ ዓለማችን ምንኛ የሥቃይ
ቋት በሆነች!
ሥራ የደስታ ምንጭ መሆኑን ፣ በእርሱም በመጠመዳቸው
ህልውናቸውን ከመገዝገዝ መቆጠባቸውን የሚገነዘቡ
በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ደስታ የምትቀርበው አጥብቀው
የሚሿትን ፣ ስለርሷ የሚያብጠለጥሉትን አይደለም — አመች
ሁኔታን በመፍጠር እንጂ፡፡ መከተልን እንጂ መምራትን
አታውቅም፡፡ ፊት ካለችም እርሷን ለመቅደም መሞከሩ
አይበጅም፡፡
በሙሉ ልብ ተመስጦ ፣ ያለ የሌለ ኃይሉን በሚጥመው
ሥራ ላይ የሚያውል ሰው ምንኛ የታደለ ነው! እያለ ባሮውስ
የፍልስፍና አቅጣጫውን ጠቆመ፡፡
በምንወደው ሥራ ተጠምደን ደስታና እርካታን ማግኘት
ከቻልን ሁላቸንም ስለፍቅር በገባን ጥልቀት እናሰባለን፡፡ እንደ
ማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት ሁሉ ለልብ ወዳጅነትም
ዋናው መመሪያ ለመወደድ ከፈለክ ሰው ወዳድ ሁን
የሚለው ነው፡፡ ፍቅርን ልትላበስ ከፈለክ ይላል ዴል
ካርኒጊም በበኩሉ ብቸኛው መንገድ እንዲያፈቅሩህ
መወትወትህን ትተህ ፍቅርህን ለግስ ፣ ፍቅርን ስትሰጥ ብቻ
ነው ፍቅርን የምታገኘው፡፡
ደግነትና መተሳሰብ አስፈላጊ ባሕርያት መሆናቸው
የተዘነጋበት ዘመን ከቶ አይገኝም፡፡ ስለራሱ ብቻ የሚያስብ
ሰው ፣ ራሱን በራሱ የጠቀለለ ኢምንት ቋጠሮ ነው ያለው
ሃሪ ፎስዲክም ይህንኑ እውነታ ከልብ በማጤን ነው፡፡
ብዙ ጊዜ ፍቅር ሰጥቶ መቀበል ነው ሲባል እንሰማለን፡፡
ለራስህ እንዲደረግልህ የምትሻውን ለሌላውም አድርግ
የሚለው አባባል ፣ የሰዎችን ግንኙነት ከሚያዳብሩ ጥንታዊና
ጊዜ የማይሽራቸው ድንጋጌዎች መኻል አንዱ ሲሆን ፣
በግብረ-ገብ መመሪያነቱ ዛሬም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
ኢመርሰን ጓደኛ ለማፍራት ጓደኛ ሁን በማለት ይህንኑ ሃቅ
አስተጋብቷል፡፡
እንግዲህ ይህን ስናደርግ ማናችንም ስለ ነገ የተስፋ
ወኔአችንን ከሌሎች ጋር ብንካፈል ምንኛ መልካም ነው፡፡
እርግጥ ነው እንደ ሲድኒ ዳርክ አባባል፤ ቀደም ያሉት
አባቶቻችን የመኖርንና የመሞትን ምንነት አስተምረውናል፡፡
እኛም ወራሾቻቸው መሆናችንን አንዘንጋ፡፡ ወደ ጦር ግንባር
የሚሄድ ወታደር ጦር ሜዳ መሞት እንዳለ ልቦናው
ቢያውቅም እንኳን በድል ብስራት ዜና ከጓዶቹ ጋር
እንደሚመለስ ያስባል፡፡ ተስፋ የትም አለ፡፡
ለህይወት አስፈላጊዎቹ ቁም ነገሮች ሥራ ፣ ፍቅርና ተስፋ
ናቸው –ጆሴፍ ኤድሰን፡፡
ሼር
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
የዕለት ተዕለት ግጭት ከሚፈጠርባቸው ምክንያቶች አንዱ
ሰዎች ለሚፈጠር ችግር መንስዔውን በትክክል አለመረዳት
ላይ ነው። ሶሻል ሳይኮሎጂስቶች ለሰዎች ባህሪ የሚሰጡ
ምክንያቶችን በሁለት ዘርፍ ያስቀምጧቸዋል። የመጀመሪያው
ሁኔታዎችን እንደመንስዔ መውሰድ ወይም situational
causes of behavior ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሰዎችን እንደ
መንስዔ መውሰድ ወይም dispositional causes of
behavior ነው፡፡ ይህም ለሚፈጠሩ ችግሮች መንስዔያቸው
የሰዎች ፀባይና ማንነት ነው የሚል ነው። እስኪ በምሳሌ
እንየው፤ ከጠዋቱ 2:30 የስራ የመግቢያ ሰዓት ሆኖ እያለ
2:45 ወደ ስራ አንድ ሰራተኛ ገባ እንበል፡፡ በዚህም የቅርብ
አለቃው አንተ ያረፈድከው እንቅልፍህን ተኝተህና የስራ
ተነሳሽነት ስለሌለህ ነው ብሎ ከሰራተኛው ጋር ተጣላ።
ዋናው አለቃ ደግሞ ሰራተኛው ያረፈደው የትራንስፖርት
እጥረት አጋጥሞት ነው በሚል የሰርቪስ አገልግሎት
እንዲጀመር አደረገ። የቅርብ አለቃው በሰውየው ወይም
dispositional causes of behavior ሲሆን፤ ዋናው አለቃ
ደግሞ ሁኔታዎችን ማለትም situational causes of
behavior ከግምት ውስጥ አስገብቷል፡፡ በዚህም ግጭትን
ማስወገድ ችሏል።
አኛስ አዘውትረን የምንጠቀመው የመንስዔ ዓይነት የትኛው
ነው???ነገ የግጭት አፈታቱን ይዘን እንቀርባለን ሼር ማድረግዎን አይዘንጉ
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ሰዎች ለሚፈጠር ችግር መንስዔውን በትክክል አለመረዳት
ላይ ነው። ሶሻል ሳይኮሎጂስቶች ለሰዎች ባህሪ የሚሰጡ
ምክንያቶችን በሁለት ዘርፍ ያስቀምጧቸዋል። የመጀመሪያው
ሁኔታዎችን እንደመንስዔ መውሰድ ወይም situational
causes of behavior ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሰዎችን እንደ
መንስዔ መውሰድ ወይም dispositional causes of
behavior ነው፡፡ ይህም ለሚፈጠሩ ችግሮች መንስዔያቸው
የሰዎች ፀባይና ማንነት ነው የሚል ነው። እስኪ በምሳሌ
እንየው፤ ከጠዋቱ 2:30 የስራ የመግቢያ ሰዓት ሆኖ እያለ
2:45 ወደ ስራ አንድ ሰራተኛ ገባ እንበል፡፡ በዚህም የቅርብ
አለቃው አንተ ያረፈድከው እንቅልፍህን ተኝተህና የስራ
ተነሳሽነት ስለሌለህ ነው ብሎ ከሰራተኛው ጋር ተጣላ።
ዋናው አለቃ ደግሞ ሰራተኛው ያረፈደው የትራንስፖርት
እጥረት አጋጥሞት ነው በሚል የሰርቪስ አገልግሎት
እንዲጀመር አደረገ። የቅርብ አለቃው በሰውየው ወይም
dispositional causes of behavior ሲሆን፤ ዋናው አለቃ
ደግሞ ሁኔታዎችን ማለትም situational causes of
behavior ከግምት ውስጥ አስገብቷል፡፡ በዚህም ግጭትን
ማስወገድ ችሏል።
አኛስ አዘውትረን የምንጠቀመው የመንስዔ ዓይነት የትኛው
ነው???ነገ የግጭት አፈታቱን ይዘን እንቀርባለን ሼር ማድረግዎን አይዘንጉ
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ግጭት ጥልቅ ውስጣዊ ስሜቶች አደባባይ ላይ ወጥተው
እንዲሰጡ ያደርግል፡፡ በዚህ ጊዜ በእውናችን ቀርቶ
በህልማችን እንኳን አልመን የማናውቀውን ነገር ራሳችንም
ሌሎችም ሲያደርጉ አስተውለን ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች
ለመስማት የሚከብድ ወንጀል ፈጸመው ወዳጅ ዘመዶቻቸው
ስለእነዚሁ ሰዎች ጠባይ ሲጠየቁ “እሱ እኮ ሰውም ቀና
ብሎ አይመለከት፣ ታላቁን አክባሪ፤ አንገት ደፊ ወዘተ ነበር”
ሲሉ ይደመጣል፡፡ እንደተባለውም እነዚህ ሰዎች ሰው
አክባሪ፣ ካልደረሱባቸው ሰው ላይ የማይደርሱ ይሆናሉ፡፡
መስካሪዎቹ ፊት ለፊት ያዩትን ነው የመሰከሩት፡፡ ነገር ግን
እነዚህ መስካሪዎች አይተውት የማያውቁት አጥፊ ስሜት
እነዚህ ሰዎች ውስጥ ይኖራል፤ ተመልካች ይቅርና
ባለቤቱም ራሱ አያውቀው ይሆናል፤ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው
እንዲሉ፡፡ይህ ማለት ግን በስሜት ተገፋፍተን በፈጸምነው
ድርጊት ተጠያቂ አንሆንም ማለትም አይደለም፡፡ ዞሮ ዞሮ
ስሜቶቻችንም የገዛ ራሳችን ንብረት እንጂ የማንም
አይደሉም፡፡
ግጭት የሚያስከትለውን ውድመት የበዛ የሚሆንበት ዋነኛ
ምክንያት ከመፈጠሩ በፊት ለመከላከልም ሆነ ከተፈጠረ
በኋላ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዕውቀት
እና ክህሎት እጦት ነው፡፡ በትንሽ በትልቁ ብስጭት የሚሉ
ሰዎችን ታውቁ ይሆናል፤ ለምን ቀና ብላችሁ በሙሉ
ዓይናችሁ ተመለከታችሁኝ ብለው ችግር የሚፈጥሩ እና
ችግር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በምዕራቡ
ዓለም ለእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ‹ንዴትን መቆጣጠር›
የሚችሉበት የተለየ ስልጠና ቁጭ ብለው እንዲወስዱ
ይደረጋል፡፡ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ግጭትን መከላከልም ሆነ
መፍታት በስልጠና ሊደረጅ የሚችል ችሎታ ነው፡፡ በዚህ
ጽሑፍ ግጭትን ለመከላከል እና ለመፍታት የሚረዱ
ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡
1. ስናዳምጥ ‹ጥቃትን› አናዳምጥ
ጥቃት እየተፈጸመብን ነው ብለን ከአሰብን አጸፋዊ መልስ
ለመስጠት አናቅማማም፡፡ ክፉ ደግ መነጋገር ደግሞ
ምክንያታዊ ውይይት ድራሹ እንዲጠፋ ያደርጋል፡፡ በተለይ
ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ማንኛውም ዓይነት ንግግር ሲደረግ
‹ይህ ሰው በትክክል ምን እያለ ነው?›፣ ‹ምን ዓይነት መረጃ
ነው በመተላለፍ ላይ የሚገኘው?›፣ ‹ምንድነው የተከፋበት
ምክንያት? ለምን ተቆጣ? ለምን ክፉ ተናገረ?› ወዘተ
በማለት በስሜት ታጅበው ከሚፈሱት ቃላት ጀርባ ያለውን
መልዕክት ለይቶ ማወቅ ጥሩ ነው፡፡ ይህንን ከአደረግን ራስን
ለመከላከል ከፍ ሲልም መልሶ ወደ ጥቃት ወደ መሰንዘሩ
ከመኬዱ በፊት መግባባት እንዲነግስ ያደርጋል፡፡
2. ደመ ነፍሳዊ ግፊት አደብ እንዲገዛ ማድረግ
የምንፈልገው እንዳልተሟላ፣ ፍትህ እንደጎደለ፣ ውሸት
እንደከበረ፣ መስማት የማንፈልገው ጥያቄ እንደቀረበ ወዘተ
ስናስብ እጥፍ ድርቡን መልሳችሁ አከናንቡ የሚል ውስጣዊ
ደመ ነፍሳዊ ግፊት ይቀሰቀሳል፡፡ እስከ ዶቃ ማሰሪያው፣
አፍንጫው ድረስ፣ ልክ ልኩን ወዘተ ነገረው ዓይነት ፈሊጣዊ
አገላለጾቻችን ‹ክፉ ነገርን ልክ የለሽ በሆነ ክፍት መመከትን›
እንደምናበረታታ ፍንጭ የሚሰጡ ናቸው፡፡ አጥቂ ምክንያታዊ
ይሁንም አይሁንም፣ ደግ ይሁንም አይሁንም አበጀህ የማለት፣
እንደ ጀግና ከፍ አድርጎ የመመልከት ባህል ሊወገድ
ይገባል፡፡
በግጭት ወቅት ‹እንዲህ በል፣ እንዲያ በል፣ የት አባቱ
ወዘተ› ዓይነት ውስጣችን የሚፈሉ የደመ ነፍስ ግፊቶችን
ማቀዛቀዝ ግጭትን ለመፍታት ይረዳል፡፡ ደመ ነፍሳዊ
ምሪትን ከአስቆምን በኋላ ተረጋግቶ በማሰብ መናገር
የምንፈልገውን ‹እኔ› በማለት መናገርም እንዲሁ
ይመከራል፡፡ ለምሳሌ፣ በቤት ውስጥ የትዳር አጋር ስራ
አላግዝ ብሎ አስቸግሮ ከሆነ ‹አንተ ድሮም ሰነፍ ነህ፣
ምንትስ ነህ› ከማለት ይልቅ ‹እኔ ስራ ካላገዝከኝ/ካላገዝሽኝ
ቅር ይለኛል፤ ተጋግዘን ልንሰራ ይገባል፤ ይኼ እኮ የጋራ
ህይወት ነው› ማለት ግጭት ላይ አርቆ ማጠሪያ ስልት
ነው፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ውስጣችን አሉታዊ ስሜት
ሲጸነስ እንደመጣልን ከመናገር እንቆጠብ፡፡ ‹ከአፍ የወጣ
አፋፍ› አይደል ከነአባባሉስ፡፡ ንግግር የፈሰሰ ውሃ ነው፡፡
እንደ ደራሽ ውሃ ፈሶ ያለ የሌለውን ጠራርጎ ከሄደ በኋላ
ሁኔታዎችን ወደ ነበሩበት መመለስ ፈታኝ ነው፡፡ ስለሆነም
ንግግር ሲያደርጉ ማመዛዘን እንዲሁም ከአንደበታችን
የሚወጡ ቃላት ግጭቱ ላይ ሄደው ሲያርፍ የቤንዚን ነው
ወይስ የውሃ ሚና የሚጫወቱት የሚለውን ቀድሞ ማሰብ
ተገቢ ነው፡፡
3. የሰዎችን በጎ ጎን ማነጋገር
100 % አጥፊ፣ ምንም ነገር የማይገባው፤ ውስጡ
እንጥፍጣፊ መልካምነት የሌለው ወዘተ ሰው አይኖርም፡፡
የትኛውም ሰው መልካም ማንነት የማንነቱ አካል ነው፡፡ እርስ
በእርስ ስንነጋገር አንዳችን የአንዳችንን ይህንን መልካም ጎን
ለማነጋገር ጥረት እናድርግ፡፡ ‹ጅኒ› ገለመሌ የሚል አጓጉል
ፍረጃ ውስጥ ሳንገባ መልአኩን ማንነት እናወያየው፡፡የሰው
የእምነቱ መነሻ ስረ መሰረት የአንድም ይሁን የብዙ የሰው
ልጅ ፍቅር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድ ድፍን ያለ ‹ነጭ›
አለያም ደግሞ ድፍን ያለ ‹ጥቁር› ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡
ፈረንጆቹ እንዲህ ዓይነቱን ጠርዘኛ አመለካከት ‹‹either/or
thinking›› ይሉታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ራስንም ሆነ
ሌሎችን አውዳሚ ነው፡፡ ከ‹ሰይጣን› ሌላ ሙሉ ለሙሉ
‹ሰይጣን› የሆነ ፍጥረት የለም፡፡
4. ለሰዎች ስሜት ቦታ እንስጥ
ስሜቶቻችን ጠቋሚ ምልክት ናቸው፡፡ ለራሳችንም ሆነ
ለሌሎች ስሜት ደንታ ቢስ መሆን ተገቢ አይደለም፡፡ የሰዎችን
ስሜት መረዳት የተፈጠረው ግጭቱ መንስኤ ምን እንደሆነ
ለማወቅ ይረዳል፡፡ ችግር ችግር ሆኖ የሚዘልቀው መንስኤው
እስኪታወቅ ድረስ ነው፡፡ የራስንም ሆነ የሌላውን ስሜት
አይቶ እንዳላዩ ማለፍ ግን ግጭትን ይወልዳል፤
ያባብሳልም፡፡ ‹ዶርማንት› የሚባል የእሳተ ገሞራ ዓይነት
አለ፡፡ መገለጫው ውሎ አድሮ አንድ ይደርሳል ብለን
ሳናስበው የደረስንበት ቀን ላይ መፈንዳት ነው፡፡ ያኔ ታዲያ
እዚያ አካባቢ ያለን ምንም ነገር አያደርጋችሁ፡፡ የነበረውን
እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ ሰሚ ጆሮ ተነፍጎ የከረመ ስሜትም
እንዲሁ ቋት ሲሞላ አንድ ቀን ያፈነውን ክዳን አሽቀንጥሮ
ሲወጣ ብዙ ሳይሰባብር አይበርድም፡፡ ‹አይመጣምን ትተሸ
ይመጣልን አስቢ› ትልቅ ቁም ነገር አዘል መልዕክት ነው፡፡
በእንቁላል ዕድሜ ላይ የሚገኙ ስሜቶችን ስራዬ ብሎ
መስማት፣ ቦታ መስጠት እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት
ከሰማይ በታች ማድረግ የሚቻለውን ነገር ሁሉ ማድረግ
ግጭትን በሩቅ ያስቀራል፤ ድንገት ቢቀሰቀስ እንኳን ያለ ብዙ
ኪሰራ ይቀዘቅዛል፡፡ ሳይኮሎጂቶች ቅጣትን የማያበረታቱት
ለዚህ ነው ለጊዜው ቀጪ ዱላውን ጨብጦ ዙሪያቸው ሲገኝ
ልጆች ታዛዥ እንዲሆኑ ያደርጋል እንጂ ዘላቂ የሆነ የጠባይ
ለውጥ ግን ጨርሶ አያመጣም፡፡ ስለዚህ በግለሰብም ሆነ
በማኅበረሰብ ደረጃ ግጭትን አስቀድሞ ለመከላከልም ሆነ
አንድ ጊዜ ከተፈጠረ በኋላ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ለማረጋጋት
ለሰዎች ስሜት ቦታ መስጠት፣ እንደተረዳናቸው ማስረዳት፣
ቁስላቸው እንደተሰማን መግለጽ ይመከራል፡፡
5. መስማት እና መስማማት መካከል ያለውን ልዩነት
መገንዘብ
የተጋጨን ሰው ቅሬታውን መስማታችንን ማወቅ አለበት፡፡
የሰው ልጅ አለመግባባት ሲፈጠር ቀዳሚ ፍላጎቱ መሰማት
ነው፡፡ መስማማት ቀጥሎ የሚመጣ ሌላ ሂደት ነው፡፡ በቂ
ጊዜ ሰጥተን ሰምተናል ማለት በተባለው ሁሉ ተስማምተናል
ማለት አይደለም፡፡ በሁሉ ነገርም መስማማት አይቻልም፡፡
መደማመጥ ግን ቁልፍ ሚና ሊጫወት እና በቀላሉ
ልንተገብረው የምንችለው የግጭት መፍቻ መመሪያ ነው፡፡
ከሁሉ በፊት ምንአልባትም ከሁሉ በላይም አቁሳዩ ጥይት
አድማጭ ማጣት ነው፡፡ ሰውን ጆሮ ዳባ ል
እንዲሰጡ ያደርግል፡፡ በዚህ ጊዜ በእውናችን ቀርቶ
በህልማችን እንኳን አልመን የማናውቀውን ነገር ራሳችንም
ሌሎችም ሲያደርጉ አስተውለን ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች
ለመስማት የሚከብድ ወንጀል ፈጸመው ወዳጅ ዘመዶቻቸው
ስለእነዚሁ ሰዎች ጠባይ ሲጠየቁ “እሱ እኮ ሰውም ቀና
ብሎ አይመለከት፣ ታላቁን አክባሪ፤ አንገት ደፊ ወዘተ ነበር”
ሲሉ ይደመጣል፡፡ እንደተባለውም እነዚህ ሰዎች ሰው
አክባሪ፣ ካልደረሱባቸው ሰው ላይ የማይደርሱ ይሆናሉ፡፡
መስካሪዎቹ ፊት ለፊት ያዩትን ነው የመሰከሩት፡፡ ነገር ግን
እነዚህ መስካሪዎች አይተውት የማያውቁት አጥፊ ስሜት
እነዚህ ሰዎች ውስጥ ይኖራል፤ ተመልካች ይቅርና
ባለቤቱም ራሱ አያውቀው ይሆናል፤ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው
እንዲሉ፡፡ይህ ማለት ግን በስሜት ተገፋፍተን በፈጸምነው
ድርጊት ተጠያቂ አንሆንም ማለትም አይደለም፡፡ ዞሮ ዞሮ
ስሜቶቻችንም የገዛ ራሳችን ንብረት እንጂ የማንም
አይደሉም፡፡
ግጭት የሚያስከትለውን ውድመት የበዛ የሚሆንበት ዋነኛ
ምክንያት ከመፈጠሩ በፊት ለመከላከልም ሆነ ከተፈጠረ
በኋላ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዕውቀት
እና ክህሎት እጦት ነው፡፡ በትንሽ በትልቁ ብስጭት የሚሉ
ሰዎችን ታውቁ ይሆናል፤ ለምን ቀና ብላችሁ በሙሉ
ዓይናችሁ ተመለከታችሁኝ ብለው ችግር የሚፈጥሩ እና
ችግር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በምዕራቡ
ዓለም ለእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ‹ንዴትን መቆጣጠር›
የሚችሉበት የተለየ ስልጠና ቁጭ ብለው እንዲወስዱ
ይደረጋል፡፡ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ግጭትን መከላከልም ሆነ
መፍታት በስልጠና ሊደረጅ የሚችል ችሎታ ነው፡፡ በዚህ
ጽሑፍ ግጭትን ለመከላከል እና ለመፍታት የሚረዱ
ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡
1. ስናዳምጥ ‹ጥቃትን› አናዳምጥ
ጥቃት እየተፈጸመብን ነው ብለን ከአሰብን አጸፋዊ መልስ
ለመስጠት አናቅማማም፡፡ ክፉ ደግ መነጋገር ደግሞ
ምክንያታዊ ውይይት ድራሹ እንዲጠፋ ያደርጋል፡፡ በተለይ
ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ማንኛውም ዓይነት ንግግር ሲደረግ
‹ይህ ሰው በትክክል ምን እያለ ነው?›፣ ‹ምን ዓይነት መረጃ
ነው በመተላለፍ ላይ የሚገኘው?›፣ ‹ምንድነው የተከፋበት
ምክንያት? ለምን ተቆጣ? ለምን ክፉ ተናገረ?› ወዘተ
በማለት በስሜት ታጅበው ከሚፈሱት ቃላት ጀርባ ያለውን
መልዕክት ለይቶ ማወቅ ጥሩ ነው፡፡ ይህንን ከአደረግን ራስን
ለመከላከል ከፍ ሲልም መልሶ ወደ ጥቃት ወደ መሰንዘሩ
ከመኬዱ በፊት መግባባት እንዲነግስ ያደርጋል፡፡
2. ደመ ነፍሳዊ ግፊት አደብ እንዲገዛ ማድረግ
የምንፈልገው እንዳልተሟላ፣ ፍትህ እንደጎደለ፣ ውሸት
እንደከበረ፣ መስማት የማንፈልገው ጥያቄ እንደቀረበ ወዘተ
ስናስብ እጥፍ ድርቡን መልሳችሁ አከናንቡ የሚል ውስጣዊ
ደመ ነፍሳዊ ግፊት ይቀሰቀሳል፡፡ እስከ ዶቃ ማሰሪያው፣
አፍንጫው ድረስ፣ ልክ ልኩን ወዘተ ነገረው ዓይነት ፈሊጣዊ
አገላለጾቻችን ‹ክፉ ነገርን ልክ የለሽ በሆነ ክፍት መመከትን›
እንደምናበረታታ ፍንጭ የሚሰጡ ናቸው፡፡ አጥቂ ምክንያታዊ
ይሁንም አይሁንም፣ ደግ ይሁንም አይሁንም አበጀህ የማለት፣
እንደ ጀግና ከፍ አድርጎ የመመልከት ባህል ሊወገድ
ይገባል፡፡
በግጭት ወቅት ‹እንዲህ በል፣ እንዲያ በል፣ የት አባቱ
ወዘተ› ዓይነት ውስጣችን የሚፈሉ የደመ ነፍስ ግፊቶችን
ማቀዛቀዝ ግጭትን ለመፍታት ይረዳል፡፡ ደመ ነፍሳዊ
ምሪትን ከአስቆምን በኋላ ተረጋግቶ በማሰብ መናገር
የምንፈልገውን ‹እኔ› በማለት መናገርም እንዲሁ
ይመከራል፡፡ ለምሳሌ፣ በቤት ውስጥ የትዳር አጋር ስራ
አላግዝ ብሎ አስቸግሮ ከሆነ ‹አንተ ድሮም ሰነፍ ነህ፣
ምንትስ ነህ› ከማለት ይልቅ ‹እኔ ስራ ካላገዝከኝ/ካላገዝሽኝ
ቅር ይለኛል፤ ተጋግዘን ልንሰራ ይገባል፤ ይኼ እኮ የጋራ
ህይወት ነው› ማለት ግጭት ላይ አርቆ ማጠሪያ ስልት
ነው፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ውስጣችን አሉታዊ ስሜት
ሲጸነስ እንደመጣልን ከመናገር እንቆጠብ፡፡ ‹ከአፍ የወጣ
አፋፍ› አይደል ከነአባባሉስ፡፡ ንግግር የፈሰሰ ውሃ ነው፡፡
እንደ ደራሽ ውሃ ፈሶ ያለ የሌለውን ጠራርጎ ከሄደ በኋላ
ሁኔታዎችን ወደ ነበሩበት መመለስ ፈታኝ ነው፡፡ ስለሆነም
ንግግር ሲያደርጉ ማመዛዘን እንዲሁም ከአንደበታችን
የሚወጡ ቃላት ግጭቱ ላይ ሄደው ሲያርፍ የቤንዚን ነው
ወይስ የውሃ ሚና የሚጫወቱት የሚለውን ቀድሞ ማሰብ
ተገቢ ነው፡፡
3. የሰዎችን በጎ ጎን ማነጋገር
100 % አጥፊ፣ ምንም ነገር የማይገባው፤ ውስጡ
እንጥፍጣፊ መልካምነት የሌለው ወዘተ ሰው አይኖርም፡፡
የትኛውም ሰው መልካም ማንነት የማንነቱ አካል ነው፡፡ እርስ
በእርስ ስንነጋገር አንዳችን የአንዳችንን ይህንን መልካም ጎን
ለማነጋገር ጥረት እናድርግ፡፡ ‹ጅኒ› ገለመሌ የሚል አጓጉል
ፍረጃ ውስጥ ሳንገባ መልአኩን ማንነት እናወያየው፡፡የሰው
የእምነቱ መነሻ ስረ መሰረት የአንድም ይሁን የብዙ የሰው
ልጅ ፍቅር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድ ድፍን ያለ ‹ነጭ›
አለያም ደግሞ ድፍን ያለ ‹ጥቁር› ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡
ፈረንጆቹ እንዲህ ዓይነቱን ጠርዘኛ አመለካከት ‹‹either/or
thinking›› ይሉታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ራስንም ሆነ
ሌሎችን አውዳሚ ነው፡፡ ከ‹ሰይጣን› ሌላ ሙሉ ለሙሉ
‹ሰይጣን› የሆነ ፍጥረት የለም፡፡
4. ለሰዎች ስሜት ቦታ እንስጥ
ስሜቶቻችን ጠቋሚ ምልክት ናቸው፡፡ ለራሳችንም ሆነ
ለሌሎች ስሜት ደንታ ቢስ መሆን ተገቢ አይደለም፡፡ የሰዎችን
ስሜት መረዳት የተፈጠረው ግጭቱ መንስኤ ምን እንደሆነ
ለማወቅ ይረዳል፡፡ ችግር ችግር ሆኖ የሚዘልቀው መንስኤው
እስኪታወቅ ድረስ ነው፡፡ የራስንም ሆነ የሌላውን ስሜት
አይቶ እንዳላዩ ማለፍ ግን ግጭትን ይወልዳል፤
ያባብሳልም፡፡ ‹ዶርማንት› የሚባል የእሳተ ገሞራ ዓይነት
አለ፡፡ መገለጫው ውሎ አድሮ አንድ ይደርሳል ብለን
ሳናስበው የደረስንበት ቀን ላይ መፈንዳት ነው፡፡ ያኔ ታዲያ
እዚያ አካባቢ ያለን ምንም ነገር አያደርጋችሁ፡፡ የነበረውን
እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ ሰሚ ጆሮ ተነፍጎ የከረመ ስሜትም
እንዲሁ ቋት ሲሞላ አንድ ቀን ያፈነውን ክዳን አሽቀንጥሮ
ሲወጣ ብዙ ሳይሰባብር አይበርድም፡፡ ‹አይመጣምን ትተሸ
ይመጣልን አስቢ› ትልቅ ቁም ነገር አዘል መልዕክት ነው፡፡
በእንቁላል ዕድሜ ላይ የሚገኙ ስሜቶችን ስራዬ ብሎ
መስማት፣ ቦታ መስጠት እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት
ከሰማይ በታች ማድረግ የሚቻለውን ነገር ሁሉ ማድረግ
ግጭትን በሩቅ ያስቀራል፤ ድንገት ቢቀሰቀስ እንኳን ያለ ብዙ
ኪሰራ ይቀዘቅዛል፡፡ ሳይኮሎጂቶች ቅጣትን የማያበረታቱት
ለዚህ ነው ለጊዜው ቀጪ ዱላውን ጨብጦ ዙሪያቸው ሲገኝ
ልጆች ታዛዥ እንዲሆኑ ያደርጋል እንጂ ዘላቂ የሆነ የጠባይ
ለውጥ ግን ጨርሶ አያመጣም፡፡ ስለዚህ በግለሰብም ሆነ
በማኅበረሰብ ደረጃ ግጭትን አስቀድሞ ለመከላከልም ሆነ
አንድ ጊዜ ከተፈጠረ በኋላ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ለማረጋጋት
ለሰዎች ስሜት ቦታ መስጠት፣ እንደተረዳናቸው ማስረዳት፣
ቁስላቸው እንደተሰማን መግለጽ ይመከራል፡፡
5. መስማት እና መስማማት መካከል ያለውን ልዩነት
መገንዘብ
የተጋጨን ሰው ቅሬታውን መስማታችንን ማወቅ አለበት፡፡
የሰው ልጅ አለመግባባት ሲፈጠር ቀዳሚ ፍላጎቱ መሰማት
ነው፡፡ መስማማት ቀጥሎ የሚመጣ ሌላ ሂደት ነው፡፡ በቂ
ጊዜ ሰጥተን ሰምተናል ማለት በተባለው ሁሉ ተስማምተናል
ማለት አይደለም፡፡ በሁሉ ነገርም መስማማት አይቻልም፡፡
መደማመጥ ግን ቁልፍ ሚና ሊጫወት እና በቀላሉ
ልንተገብረው የምንችለው የግጭት መፍቻ መመሪያ ነው፡፡
ከሁሉ በፊት ምንአልባትም ከሁሉ በላይም አቁሳዩ ጥይት
አድማጭ ማጣት ነው፡፡ ሰውን ጆሮ ዳባ ል
በስ ብሎ ማለፍ
ክብረ ነክ ድርጊት ነው፤ ንቀት ነው፤ ‹ምን ታመጣላችሁ?›፣
‹የራሳችሁ ጉዳይ› ወዘተ ማለት ነው፡፡ እነዚህ
የአመለካከከት እና ድርጊት መስመሮች በራሳቸው ግጭትን
ይቀሰቅሳሉም፤ ያባብሳሉም፡፡ አንድን ሰው እህ ብሎ
መስማት፣ ሃሳቡን በሚገባ እንዲገልጽ ዕድል መስጠት፣
እየተባለ ያለውን ፍሬ ነገር በገዛ ራስ ትርጉምና ፍረጃ
ሳይጀቡኑ ለመረዳት ጥረት ማድረግ፣ ሳይኮሎጂስቶች
‹‹already listening›› የሚሉት አለ (የሚመልሱትን መልስ
እያውጠነጠኑ መስማት ማለት ነው)፣ እንደዚህ ካለው
የማይበጅ የህሊና ድምጽን ዝም አሰኝቶ የሌላውን ህሊና
የቅሬታ ድምጽ መስማት ግጭትን ይቀንሳል፤ ይፈታልም፡፡
ተደማመጥን ማለት ተስማማን ማለት አይደለም፤ ሰሚ ጆሮ
መስጠት መሸነፍ አይደለም፡፡ መደማመጥ እስካለ ድረስ
በአልተስማሙበት ጉዳይ ላይም በልዩነት መስማማት
ይቻላል፤ ‹ላለመስማማት መስማማት› እንዲሉ፡፡
6. ስናዳምጥ አስሬ ጣልቃ እየገባን አስተያየት አንስጥ
ይኼም እንዲሁ ለንግግር አድራጊው ያለንን ዝቅተኛ ክብር
አስረጂ ነው፡፡ የሚከባበሩ ሰዎች ግጭት ውስጥ
የሚገቡበት ዕድል አነስተኛ ነው፡፡ አይበለውና ግጭት ቢነሳ
እንኳን በሰለጠነ መንገድ መፍታት አስቸጋሪ አይሆንም፡፡
አንድ ከዚህ በፊት በሌላ አንድ ጽሑፌ ላይ ያነሳሁት ገጠመኝ
አለኝ፡፡ እዚህ ጋርም ቢነሳ አስተማሪነቱ የጎላ ሊሆን
ስለሚችል ደግሜ ላንሳው፡፡ በነጋ በጠባ አንድንዴ አገር ጉድ
እስኪል ድረስ የሚጣሉ ጥንዶች ቤት በአንድ አጋጣሚ
ተገኘሁና አንድ ርዕሰ ጉዳይ ተነስቶ ሃሳብ መቀያየር ጀመርን፤
ይመስለኛል ክርክር ቢጤም ነው፡፡ ሚስት ሃሳቧን ሳትጨርስ
ባል ደጋግሞ ያቋርጣል፡፡ ሚስት ታዲያ መሃል ላይ ወደ እኔ
አንገቷን አዙራ በቅሬታ ድምጽ ‹ተመልከተው አያዳምጠኝም
እኮ› አለችኝ፡፡ ቅሬታዋ ‹ለምን በእኔ ሃሳብ አልተስማማም›
አይደለም፡፡ ቅሬታዋ ‹ለምን ስናገር አታዳምጠኝም› ነው፡፡
ስንወያይ ሃሳብ የማስጨረስ ልምድ ይኑረን፡፡ ማንም ‹ዓመት›
አያወራም፡፡ የቤተሰብ ውይይት ይባልናም በመመገቢያ
ጠረጴዛ ዙሪያ ተሰባስበን የወላጅን የትዕዛዝ ዝርዝር
የመስማት ትዕግስት እንዲኖረን እንጂ የራሳችንን ሃሳብ
እንድንገልጽ አንበረታታም፡፡ አምባገነኖችን በዚህ መልኩ ነው
በየቤቱ የምንፈጥራቸው፡፡ ሳይደመጥ ያደገ ልጅ ነገ
አድማጭ መሪ የሚሆንበት ዕድል ጠባብ ነው፡፡ በተቋማት
ውስጥም ተመሳሳይ ችግር አለ፡፡ ውይይት ማለት በአንድ
አቅጣጫ ብቻ ከአሰሪ ወደ ሰራተኛ የሚዥጎደጎድ ምክር
ይመስለናል፡፡ ሃሳብን ማስጨረስ ይልቁንም ‹እንዲህ
ለማለት ፈልገህ ነው ወይ?› የሚል ጥያቄ በንግግር
መጨረሻ በመጠየቅ በትክክል የተባለውን ለመረዳት
መጣር፣ ስንነጋገር ከተናጋሪ ጋር ቀጥታ የዓይን ግንኙነት
ማድረግ፣ በየመሃሉ ‹አሃ› ማለት ወዘተ ተናጋሪ እየተደመጠ
እንደሆነ ስለሚያስገነዝበው መከባበር የሰፈነበት አየር
እንዲኖር ያደርጋል፤ መከባበር ወደ መስማማት
የማይወስድበትም ምንም ምክንያት የለም፡፡
7. ግምታችንን ገልጸን ግምታችን ስህተት ከሆነ ለመታረም
ፈቃደኛ መሆን
‹ግምቶች ብዙ ጊዜ ከእውነታ የራቁ ናቸው› ይላል አንድ
ወዳጄ፡፡ ለእውነት የቆመ ሰው ‹ከአፈርኩ አይመልሰኝ› ከሚል
ድርቅና የጸዳ ነው፡፡ ‹በዚህ ሰዓት ነበር አይደል ቤት
የገባኸው?› ብለን ‹አይደለም፤ በዚህ ሰዓት ነው› የሚል
የተለየ መልስ ከተሰጠን፣ ማረጋገጥም ከቻልን ሃሳባችንን
እንቀይር፡፡ አንድ ጊዜ የተናገሩትን ላለመሻር በስህተት ላይ
ስህተትን እየከመሩ የመሄድ አዚማችን ራስን እያረሙ፣ ወደ
እውነት እየተቃረቡ፣ ከእውነት ጋር በእውነት እየተመሩ
ከመኖር ይልቅ ሚዛን ይደፋል፡፡ በታሪክም በአመክንዮም
ስህተት ስህተትን አርሞ አያውቅም፡፡ ከሰው ስህተት ከብረት
ዝገት አይጠፋም፡፡ መሳሳትን ማመን የመንፈስ ከፍታ ነው፡፡
ራስን ማረም ትልቅነት ነው፡፡ ‹ይቅርታ አድርጉልኝ› ማለት
ህይወት ውድድር ነው ብለን ብናምን እንኳን በልጦ መገኘት
ነው፡፡ እንደ ግለሰብ ለመታረም ፈቃደኛ ያለመሆን ድርቅና
ያጠቃናል፡፡ ይኼንን የስነ ልቡናችንን ጎን አፍርሶ መስራት
ጠቃሚ ነው፡፡ በአንድ ወቅት አንድ አባ ወራ ከሚስቱ ጋር
ተጋጭቶ ለማስማማት ጥረት በምናደርግበት ወቅት ‹እኔ
ምንም ስህተት የለብኝም፤ 100 % ልክ ነኝ› የሚል መልስ
ይሰጠናል፡፡ የሰው ልጅ በዚህ ደረጃ ልክ ሆኖ አያውቅም፤
ወደፊትም የሚሆን አይመስለኝም፡፡ የዚህ አባ ወራ ምላሽ
‹ስህተትን ማመን ሞት ነው› የሚል የጸና እምነት እንዳለን፣
ድርቅናችን ጥጉ የት ድረስ እንደሆነ የሚጠቁም ነው፡፡
8. ውስብስብ ነባራዊ ሁኔታዎችን ለመረዳት እንትጋ
አለማወቅ የብዙ ችግር ምንጭ ነው፡፡ ማወቅ ትዕግስትን፣
ጥረትን፣ ተነሳሽትን ወዘተ ይጠይቃል፡፡ ድምዳሜ ላይ
ከመድረሳችን በፊት የግጭቱን ቀስቃሽ መንስኤዎች
ለመረዳት መጓጓት ግጭትን በመፍታት ሂደት ውስጥ ገንቢ
ሚና ይጫወታል፡፡
9. ‹ገንቢ ውይይት ማድረግ ይቻላል› የሚል እምነት ይኑረን
የአትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የ‹ይቻላል› መርህ በግጭት
አፈታት ውስጥም ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ አስቀድሞ
‹መግባባት አይቻልም› የሚል እምነት ውስጣችንን ከሞላው
ለመግባባት ምንም ጥረት አናደርግም፡፡ ጥረት ብናደርግ
እንኳን ለይስሙላ ይሆናል፡፡ የተዘጋ የአይቻልም አስተሳሰብ
ወደ መቻል የሚወስዱንን መንገዶች ለመስራት መፈንቀል
ያለብንን ድንጋይ በሙሉ እንዳንፈነቅል ጋሬጣ ይሆንብናል፡፡
ከአንጀት ካለቀሱ እንባ መቼም ቢሆን አይገድም፡፡
10. ግጭቱ እንዲባባስ እያደረግን ከሆነ ከድርጊታችን
እንቆጠብ
ባልና ሚስት ፍቅራቸው ሳይጠፋ አንድ ጣሪያ ስር አብረው
የሚኖሩት አንዱ እሳት ሲሆን ሌላኛው አፈር ከሆነ ብቻ ነው ፡፡
እሳትን በእሳት ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም፡፡
11. ጥፋቱ የማን እንደሆነ ሳይሆን መንስኤው ምን እንደሆነ
ለማወቅ መሞከር
ጣት መጠቆም የረባ ለውጥ አያመጣም፡፡ ኮሽ ሲል
ተወንጃይ ፍላጋ መሯሯጥ ዘላቂ ለውጥ አያመጣም፡፡
ማውገዝ ረጅም መንገድ አያስኬድም፡፡ መወነጃጀል ግጭትን
መፍታት የማይችል ቀሽም ስትራቴጂ ነው፡፡ ግጭት
ሲቀሰቀስ ጥፋተኛውን ሳይሆን መንስኤውን ለማወቅ መጣር
ግጭቱ ዳግም እንዳይፈጠርም ሆነ አንድ ጊዜ ከተፈጠረ
በኋላም እንዲበርድ ለማድረግ ያግዛል፡፡ እውነቱን ለመናገር
በየትኛውም ዓይነት ግጭት ውስጥ ሁሉም ወገን
የሚጫወተው ሚና ይኖራል፡፡ ስለዚህ ‹ይኼ ግጭት
እንዲቀሰቀስ እንዲሁም እንዲባባስ ምን ዓይነት ሚና
ተጫውቻለሁ?› ብሎ ራስን መጠየቅ እና የራስን ቤት ከሁሉ
በፊት መፈተሽ ግጭትን ይከላከላል፤ ያበርዳልም፡፡
12. ስምምነትን ግልጽ ማድረግ
በግልጽ ያልተቀመጡ ስምምነቶች ዛሬም ሆነ ነገ ግጭት
እንዲፈጠር በር መክፈታቸው አይቀርም፡፡ ፍላጎትን በቀጥታ
በመናገር ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበትን አማራጭ ተግባራዊ
የሚያደርግ፣ ዳግመኛ ለጥል መጋበዝ እንዳይመጣ
የሚያደርግ ግልጽ ስምምነት ላይ መድረስ ብልህነት ነው፡፡
በግለሰቦች ሌላው ቀርቶ በባለ ትዳሮች መካከል እንኳን
በተደጋጋሚ ቅራኔ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ካሉ በሚገባ
ከተነጋገሩ በኋላ የመፍትሄ ስምምነቱን በወረቀት ጭምር
አስፍሮ ማስቀመጥ ወደፊት ግጭት ሊፈጠር የሚችልበትን
ዕድል ይቀንሳል፡፡ ሰው ሊረሳ፣ ቃሉን ሊያጥፍ፣ ፍላጎቱ
ሊለወጥ ወዘተ ይችላል፡፡
13. ግጭት ወደፊትም ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ እና
አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ
ዛሬ ተነጋግረን የፈታነው ጉዳይ ነገም ሌላ ቁጥር አንድ
አወዛጋቢ አጀንዳ ሆኖ ብቅ ሊል ይችላል፡፡ በጥንዶች መካከል
ዛሬ ተስማምተንበታል የሚሉት ጉዳይ ነገ ሰላምን ከቤታቸው
ገፍትሮ ሊያስወጣ ይችላል፡፡ ዛሬም ነገም ከነገ ወዲያም
የተቋጨ ግጭት እንደ አዲስ ሊያገረሽ እን
ክብረ ነክ ድርጊት ነው፤ ንቀት ነው፤ ‹ምን ታመጣላችሁ?›፣
‹የራሳችሁ ጉዳይ› ወዘተ ማለት ነው፡፡ እነዚህ
የአመለካከከት እና ድርጊት መስመሮች በራሳቸው ግጭትን
ይቀሰቅሳሉም፤ ያባብሳሉም፡፡ አንድን ሰው እህ ብሎ
መስማት፣ ሃሳቡን በሚገባ እንዲገልጽ ዕድል መስጠት፣
እየተባለ ያለውን ፍሬ ነገር በገዛ ራስ ትርጉምና ፍረጃ
ሳይጀቡኑ ለመረዳት ጥረት ማድረግ፣ ሳይኮሎጂስቶች
‹‹already listening›› የሚሉት አለ (የሚመልሱትን መልስ
እያውጠነጠኑ መስማት ማለት ነው)፣ እንደዚህ ካለው
የማይበጅ የህሊና ድምጽን ዝም አሰኝቶ የሌላውን ህሊና
የቅሬታ ድምጽ መስማት ግጭትን ይቀንሳል፤ ይፈታልም፡፡
ተደማመጥን ማለት ተስማማን ማለት አይደለም፤ ሰሚ ጆሮ
መስጠት መሸነፍ አይደለም፡፡ መደማመጥ እስካለ ድረስ
በአልተስማሙበት ጉዳይ ላይም በልዩነት መስማማት
ይቻላል፤ ‹ላለመስማማት መስማማት› እንዲሉ፡፡
6. ስናዳምጥ አስሬ ጣልቃ እየገባን አስተያየት አንስጥ
ይኼም እንዲሁ ለንግግር አድራጊው ያለንን ዝቅተኛ ክብር
አስረጂ ነው፡፡ የሚከባበሩ ሰዎች ግጭት ውስጥ
የሚገቡበት ዕድል አነስተኛ ነው፡፡ አይበለውና ግጭት ቢነሳ
እንኳን በሰለጠነ መንገድ መፍታት አስቸጋሪ አይሆንም፡፡
አንድ ከዚህ በፊት በሌላ አንድ ጽሑፌ ላይ ያነሳሁት ገጠመኝ
አለኝ፡፡ እዚህ ጋርም ቢነሳ አስተማሪነቱ የጎላ ሊሆን
ስለሚችል ደግሜ ላንሳው፡፡ በነጋ በጠባ አንድንዴ አገር ጉድ
እስኪል ድረስ የሚጣሉ ጥንዶች ቤት በአንድ አጋጣሚ
ተገኘሁና አንድ ርዕሰ ጉዳይ ተነስቶ ሃሳብ መቀያየር ጀመርን፤
ይመስለኛል ክርክር ቢጤም ነው፡፡ ሚስት ሃሳቧን ሳትጨርስ
ባል ደጋግሞ ያቋርጣል፡፡ ሚስት ታዲያ መሃል ላይ ወደ እኔ
አንገቷን አዙራ በቅሬታ ድምጽ ‹ተመልከተው አያዳምጠኝም
እኮ› አለችኝ፡፡ ቅሬታዋ ‹ለምን በእኔ ሃሳብ አልተስማማም›
አይደለም፡፡ ቅሬታዋ ‹ለምን ስናገር አታዳምጠኝም› ነው፡፡
ስንወያይ ሃሳብ የማስጨረስ ልምድ ይኑረን፡፡ ማንም ‹ዓመት›
አያወራም፡፡ የቤተሰብ ውይይት ይባልናም በመመገቢያ
ጠረጴዛ ዙሪያ ተሰባስበን የወላጅን የትዕዛዝ ዝርዝር
የመስማት ትዕግስት እንዲኖረን እንጂ የራሳችንን ሃሳብ
እንድንገልጽ አንበረታታም፡፡ አምባገነኖችን በዚህ መልኩ ነው
በየቤቱ የምንፈጥራቸው፡፡ ሳይደመጥ ያደገ ልጅ ነገ
አድማጭ መሪ የሚሆንበት ዕድል ጠባብ ነው፡፡ በተቋማት
ውስጥም ተመሳሳይ ችግር አለ፡፡ ውይይት ማለት በአንድ
አቅጣጫ ብቻ ከአሰሪ ወደ ሰራተኛ የሚዥጎደጎድ ምክር
ይመስለናል፡፡ ሃሳብን ማስጨረስ ይልቁንም ‹እንዲህ
ለማለት ፈልገህ ነው ወይ?› የሚል ጥያቄ በንግግር
መጨረሻ በመጠየቅ በትክክል የተባለውን ለመረዳት
መጣር፣ ስንነጋገር ከተናጋሪ ጋር ቀጥታ የዓይን ግንኙነት
ማድረግ፣ በየመሃሉ ‹አሃ› ማለት ወዘተ ተናጋሪ እየተደመጠ
እንደሆነ ስለሚያስገነዝበው መከባበር የሰፈነበት አየር
እንዲኖር ያደርጋል፤ መከባበር ወደ መስማማት
የማይወስድበትም ምንም ምክንያት የለም፡፡
7. ግምታችንን ገልጸን ግምታችን ስህተት ከሆነ ለመታረም
ፈቃደኛ መሆን
‹ግምቶች ብዙ ጊዜ ከእውነታ የራቁ ናቸው› ይላል አንድ
ወዳጄ፡፡ ለእውነት የቆመ ሰው ‹ከአፈርኩ አይመልሰኝ› ከሚል
ድርቅና የጸዳ ነው፡፡ ‹በዚህ ሰዓት ነበር አይደል ቤት
የገባኸው?› ብለን ‹አይደለም፤ በዚህ ሰዓት ነው› የሚል
የተለየ መልስ ከተሰጠን፣ ማረጋገጥም ከቻልን ሃሳባችንን
እንቀይር፡፡ አንድ ጊዜ የተናገሩትን ላለመሻር በስህተት ላይ
ስህተትን እየከመሩ የመሄድ አዚማችን ራስን እያረሙ፣ ወደ
እውነት እየተቃረቡ፣ ከእውነት ጋር በእውነት እየተመሩ
ከመኖር ይልቅ ሚዛን ይደፋል፡፡ በታሪክም በአመክንዮም
ስህተት ስህተትን አርሞ አያውቅም፡፡ ከሰው ስህተት ከብረት
ዝገት አይጠፋም፡፡ መሳሳትን ማመን የመንፈስ ከፍታ ነው፡፡
ራስን ማረም ትልቅነት ነው፡፡ ‹ይቅርታ አድርጉልኝ› ማለት
ህይወት ውድድር ነው ብለን ብናምን እንኳን በልጦ መገኘት
ነው፡፡ እንደ ግለሰብ ለመታረም ፈቃደኛ ያለመሆን ድርቅና
ያጠቃናል፡፡ ይኼንን የስነ ልቡናችንን ጎን አፍርሶ መስራት
ጠቃሚ ነው፡፡ በአንድ ወቅት አንድ አባ ወራ ከሚስቱ ጋር
ተጋጭቶ ለማስማማት ጥረት በምናደርግበት ወቅት ‹እኔ
ምንም ስህተት የለብኝም፤ 100 % ልክ ነኝ› የሚል መልስ
ይሰጠናል፡፡ የሰው ልጅ በዚህ ደረጃ ልክ ሆኖ አያውቅም፤
ወደፊትም የሚሆን አይመስለኝም፡፡ የዚህ አባ ወራ ምላሽ
‹ስህተትን ማመን ሞት ነው› የሚል የጸና እምነት እንዳለን፣
ድርቅናችን ጥጉ የት ድረስ እንደሆነ የሚጠቁም ነው፡፡
8. ውስብስብ ነባራዊ ሁኔታዎችን ለመረዳት እንትጋ
አለማወቅ የብዙ ችግር ምንጭ ነው፡፡ ማወቅ ትዕግስትን፣
ጥረትን፣ ተነሳሽትን ወዘተ ይጠይቃል፡፡ ድምዳሜ ላይ
ከመድረሳችን በፊት የግጭቱን ቀስቃሽ መንስኤዎች
ለመረዳት መጓጓት ግጭትን በመፍታት ሂደት ውስጥ ገንቢ
ሚና ይጫወታል፡፡
9. ‹ገንቢ ውይይት ማድረግ ይቻላል› የሚል እምነት ይኑረን
የአትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የ‹ይቻላል› መርህ በግጭት
አፈታት ውስጥም ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ አስቀድሞ
‹መግባባት አይቻልም› የሚል እምነት ውስጣችንን ከሞላው
ለመግባባት ምንም ጥረት አናደርግም፡፡ ጥረት ብናደርግ
እንኳን ለይስሙላ ይሆናል፡፡ የተዘጋ የአይቻልም አስተሳሰብ
ወደ መቻል የሚወስዱንን መንገዶች ለመስራት መፈንቀል
ያለብንን ድንጋይ በሙሉ እንዳንፈነቅል ጋሬጣ ይሆንብናል፡፡
ከአንጀት ካለቀሱ እንባ መቼም ቢሆን አይገድም፡፡
10. ግጭቱ እንዲባባስ እያደረግን ከሆነ ከድርጊታችን
እንቆጠብ
ባልና ሚስት ፍቅራቸው ሳይጠፋ አንድ ጣሪያ ስር አብረው
የሚኖሩት አንዱ እሳት ሲሆን ሌላኛው አፈር ከሆነ ብቻ ነው ፡፡
እሳትን በእሳት ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም፡፡
11. ጥፋቱ የማን እንደሆነ ሳይሆን መንስኤው ምን እንደሆነ
ለማወቅ መሞከር
ጣት መጠቆም የረባ ለውጥ አያመጣም፡፡ ኮሽ ሲል
ተወንጃይ ፍላጋ መሯሯጥ ዘላቂ ለውጥ አያመጣም፡፡
ማውገዝ ረጅም መንገድ አያስኬድም፡፡ መወነጃጀል ግጭትን
መፍታት የማይችል ቀሽም ስትራቴጂ ነው፡፡ ግጭት
ሲቀሰቀስ ጥፋተኛውን ሳይሆን መንስኤውን ለማወቅ መጣር
ግጭቱ ዳግም እንዳይፈጠርም ሆነ አንድ ጊዜ ከተፈጠረ
በኋላም እንዲበርድ ለማድረግ ያግዛል፡፡ እውነቱን ለመናገር
በየትኛውም ዓይነት ግጭት ውስጥ ሁሉም ወገን
የሚጫወተው ሚና ይኖራል፡፡ ስለዚህ ‹ይኼ ግጭት
እንዲቀሰቀስ እንዲሁም እንዲባባስ ምን ዓይነት ሚና
ተጫውቻለሁ?› ብሎ ራስን መጠየቅ እና የራስን ቤት ከሁሉ
በፊት መፈተሽ ግጭትን ይከላከላል፤ ያበርዳልም፡፡
12. ስምምነትን ግልጽ ማድረግ
በግልጽ ያልተቀመጡ ስምምነቶች ዛሬም ሆነ ነገ ግጭት
እንዲፈጠር በር መክፈታቸው አይቀርም፡፡ ፍላጎትን በቀጥታ
በመናገር ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበትን አማራጭ ተግባራዊ
የሚያደርግ፣ ዳግመኛ ለጥል መጋበዝ እንዳይመጣ
የሚያደርግ ግልጽ ስምምነት ላይ መድረስ ብልህነት ነው፡፡
በግለሰቦች ሌላው ቀርቶ በባለ ትዳሮች መካከል እንኳን
በተደጋጋሚ ቅራኔ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ካሉ በሚገባ
ከተነጋገሩ በኋላ የመፍትሄ ስምምነቱን በወረቀት ጭምር
አስፍሮ ማስቀመጥ ወደፊት ግጭት ሊፈጠር የሚችልበትን
ዕድል ይቀንሳል፡፡ ሰው ሊረሳ፣ ቃሉን ሊያጥፍ፣ ፍላጎቱ
ሊለወጥ ወዘተ ይችላል፡፡
13. ግጭት ወደፊትም ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ እና
አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ
ዛሬ ተነጋግረን የፈታነው ጉዳይ ነገም ሌላ ቁጥር አንድ
አወዛጋቢ አጀንዳ ሆኖ ብቅ ሊል ይችላል፡፡ በጥንዶች መካከል
ዛሬ ተስማምተንበታል የሚሉት ጉዳይ ነገ ሰላምን ከቤታቸው
ገፍትሮ ሊያስወጣ ይችላል፡፡ ዛሬም ነገም ከነገ ወዲያም
የተቋጨ ግጭት እንደ አዲስ ሊያገረሽ እን
ደሚችል ማሰብ፣
የቅድመ መከላከል ስራ መስራት እንዲሁም ገፍቶ መጥቶ
ግጭቱ ሲፈጠርም የበዛ ጥፋት እና ውድመት ሳይደርስ
መርገብ የሚቻልበትን ስልት መንደፍ ይመከራል፡፡ ትላንት
ያደናቀፍን ድንጋይ ዛሬም መልሶ ሊያደናቅፈን አይገባም፤
ቢቻል በቀላሉ አስቀድሞ መገመት የሚቻለውን ይቅርና
በቀላሉ ለማይገመተውም ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ይገባል፡፡
ቸር እንሰንብት!
Join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
የቅድመ መከላከል ስራ መስራት እንዲሁም ገፍቶ መጥቶ
ግጭቱ ሲፈጠርም የበዛ ጥፋት እና ውድመት ሳይደርስ
መርገብ የሚቻልበትን ስልት መንደፍ ይመከራል፡፡ ትላንት
ያደናቀፍን ድንጋይ ዛሬም መልሶ ሊያደናቅፈን አይገባም፤
ቢቻል በቀላሉ አስቀድሞ መገመት የሚቻለውን ይቅርና
በቀላሉ ለማይገመተውም ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ይገባል፡፡
ቸር እንሰንብት!
Join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
እንዴት ናቹሁ ወደጆቼ ዛሬም ይዤ የቀረብኩት ስለግጭት ነው ምነው ግጭት አበዛክ ልትልኘ ትችላላቹህ ከምንም በላይ ሰላም ይቀድማል ብየ ስላሰብኩ ነው እናም ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚል ርእስ ይዤ ቀርብያለሁ ያነቡት ዘንድ በአክብሮት ጋብዣለሁ መልካም ንባብ ግጭት የአንድ ሰው ድርጊት ወይም አመለካከት ሌላውን
ሲረብሽ የሚፈጠር ሲሆን ይህም በቤተሰብ ፤ በጓደኛ ፤
በስራ ቦታ፤ በጋብቻ.. ወዘተ መካከል ሊከሰት ይችላል፡፡
የግጭቱ ሁኔታ መክረር ወይም በቀላል መፈታት
እንደተጋጪዎቹ ባህርይ ፤ግንኙነትና የግጭቱ ዓይነት
ይለያያል፡፡ የተለያዩ የግጭት ዓይነቶችን በአራት ከፍሎ
ማየት ይቻላል፡፡
1. ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት (Intra-personal)
ምንም እንኳን የተለያዩ የግጭት ዓይነቶች ቢኖሩም
በማኅበረሰባችን ውስጥ የላቀ ትኩረት የሚሰጣቸው
ከውጫዊ አካላት ጋር ለሚፈጠሩ ግጭቶች ነው፡፡ ይሁንና
ሰው ከራሱ ጋር የሚፈጥረው ግጭት ከሌሎች ግጭቶች
በተለየ መልኩ አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን
እንደሚያስከትል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ከራስ ጋር የሚፈጠር
ግጭት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእነዚህም
ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው ሰው በህይወት ዘመኑ
በሚፈጽማቸው ስህተቶች ከህሊናው ጋር የሚፈጥረው
ግጭት ነው፡፡
2. ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር ግጭት (Inter-personal)
በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የግጭት ዓይነት ከሌላ ሰው
ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ሲሆን ይህም በተለያዩ
ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዋነኛዎቹ የዚህ ግጭት
መንስኤዎች መካከል በሃሳብ አለመግባባት ፤ ግትርነት ፤
ነገሮችን በትዕግስት አለማሳለፍ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡
3. በአንድ ቡድን አባላት መካከል የሚፈጠር (Intra-
group)
ይህ የግጭት ዓይነት በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠር ሳይሆን
ለአንድ ዓላማ በተመሠረተ ቡድን ውስጥ ባሉ አባላት
መካከል ምክንያታዊና ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች የራስን
አቋም በማጣት የሌላውን ሃሳብ ተከትሎ በመሄድና የተዛባ
መረጃ በመያዝ ከሌሎች የቡድን አባላት ጋር የሚፈጠር
የግጭት ዓይነት ነው፡፡
4. በቡድኖች መካከል የሚፈጠር ግጭት (Inter-group)
የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሁለትና ከዚያም በላይ
የሆኑ ቡድኖች በሚያገናኟቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተው
መስራት ሳይችሉ ሲቀር ወይም አንዱ ሌላውን በበላይነት
ማስተዳደር ሲፈልግ የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው የግጭት ዓይነቶች
በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
የአመለካከት ልዩነት
የባህል ፤ አስተዳደግ ፤ የባህርይ ልዩነት
የዓላማ እና የፍላጎት ልዩነት
የስልጣን/የኃይል ልዩነት
እውነታና ፍላጎት አለመስማማት
የግጭት አፈታት ዘዴዎች
ማንኛውም ዓይነት ግጭት ለማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ
ሊዳርግ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ በመሆኑም
በማንኛውም ጊዜ የሚያጋጥሙትን ለግጭት የሚዳርጉ
ሁኔታዎችን ከግጭት በራቀ መልኩ የመፍታት ክህሎትን
ማዳበር ስኬታማ የሆነ ህይወት ለመምራት ትልቅ
አስተዋጽኦ አለው፡፡
ግጭትን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ
ነጥቦች
1. የግጭቱን መንስኤ ለይቶ ማወቅ፡–
ግጭቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ መንስኤያቸውን ለይቶ ማወቅ
ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግና በቀላሉ መፍትሄ
ለማፈላለግ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ ግጭት በሃሳብ
አለመግባባት ቢፈጠር ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው ተጋጪው
ካለው የአስተሳሰብ፤ የባህል ፤ የአስተዳደግ ፤ ወይም
ከግለሰቡ የግል ባህርይ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ
መቻል ግጭቱን በቀላሉ ለመፍታት ይረዳል፡፡
2. አማራጭ መፍትሄዎችን ማየት
ለተከሰተው የሃሳብ ልዩነት ወይም ግጭት እንደመፍትሄ
ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጭ መንገዶችን ማየት ግጭትን
በቀላሉ ለመፍታት ያስችላል፡፡
3. ስሜታዊነትን ማስወገድ
አብዛኛውን ጊዜ በስሜታዊነት የሚወሰዱ እርምጃዎች
ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው የጎላ ነው፡፡
በመሆኑም ግጭት በሚነሳበት ወቅት እራስን ለመቆጣጠር
እና ከስሜታዊነት የጸዳ ውሳኔ ለመወሰን ይቻል ዘንድ
ግጭቱ ከተነሳበት አካባቢ በመራቅ ረጋ ብሎ ማሰብ
ያስፈልጋል፡፡
4. ስምምነት መፍጠር
የተፈጠረውን አጋጣሚ አንስቶ ፊት ለፊት በግልጽ
በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት
ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እንደ አስፈላጊነቱ
ሌላ ሦስተኛ አካል ገብቶ የሚያነጋግርበትን መንገድ
በመፈለግ ከግጭት ይልቅ ስምምነት የሚፈጥርበትን ሁኔታ
ማመቻቸት ይገባል ፡፡ መልካም ምሽት❤️
ሼር ያድርጉት
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ሲረብሽ የሚፈጠር ሲሆን ይህም በቤተሰብ ፤ በጓደኛ ፤
በስራ ቦታ፤ በጋብቻ.. ወዘተ መካከል ሊከሰት ይችላል፡፡
የግጭቱ ሁኔታ መክረር ወይም በቀላል መፈታት
እንደተጋጪዎቹ ባህርይ ፤ግንኙነትና የግጭቱ ዓይነት
ይለያያል፡፡ የተለያዩ የግጭት ዓይነቶችን በአራት ከፍሎ
ማየት ይቻላል፡፡
1. ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት (Intra-personal)
ምንም እንኳን የተለያዩ የግጭት ዓይነቶች ቢኖሩም
በማኅበረሰባችን ውስጥ የላቀ ትኩረት የሚሰጣቸው
ከውጫዊ አካላት ጋር ለሚፈጠሩ ግጭቶች ነው፡፡ ይሁንና
ሰው ከራሱ ጋር የሚፈጥረው ግጭት ከሌሎች ግጭቶች
በተለየ መልኩ አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን
እንደሚያስከትል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ከራስ ጋር የሚፈጠር
ግጭት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእነዚህም
ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው ሰው በህይወት ዘመኑ
በሚፈጽማቸው ስህተቶች ከህሊናው ጋር የሚፈጥረው
ግጭት ነው፡፡
2. ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር ግጭት (Inter-personal)
በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የግጭት ዓይነት ከሌላ ሰው
ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ሲሆን ይህም በተለያዩ
ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዋነኛዎቹ የዚህ ግጭት
መንስኤዎች መካከል በሃሳብ አለመግባባት ፤ ግትርነት ፤
ነገሮችን በትዕግስት አለማሳለፍ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡
3. በአንድ ቡድን አባላት መካከል የሚፈጠር (Intra-
group)
ይህ የግጭት ዓይነት በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠር ሳይሆን
ለአንድ ዓላማ በተመሠረተ ቡድን ውስጥ ባሉ አባላት
መካከል ምክንያታዊና ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች የራስን
አቋም በማጣት የሌላውን ሃሳብ ተከትሎ በመሄድና የተዛባ
መረጃ በመያዝ ከሌሎች የቡድን አባላት ጋር የሚፈጠር
የግጭት ዓይነት ነው፡፡
4. በቡድኖች መካከል የሚፈጠር ግጭት (Inter-group)
የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሁለትና ከዚያም በላይ
የሆኑ ቡድኖች በሚያገናኟቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተው
መስራት ሳይችሉ ሲቀር ወይም አንዱ ሌላውን በበላይነት
ማስተዳደር ሲፈልግ የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው የግጭት ዓይነቶች
በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
የአመለካከት ልዩነት
የባህል ፤ አስተዳደግ ፤ የባህርይ ልዩነት
የዓላማ እና የፍላጎት ልዩነት
የስልጣን/የኃይል ልዩነት
እውነታና ፍላጎት አለመስማማት
የግጭት አፈታት ዘዴዎች
ማንኛውም ዓይነት ግጭት ለማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ
ሊዳርግ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ በመሆኑም
በማንኛውም ጊዜ የሚያጋጥሙትን ለግጭት የሚዳርጉ
ሁኔታዎችን ከግጭት በራቀ መልኩ የመፍታት ክህሎትን
ማዳበር ስኬታማ የሆነ ህይወት ለመምራት ትልቅ
አስተዋጽኦ አለው፡፡
ግጭትን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ
ነጥቦች
1. የግጭቱን መንስኤ ለይቶ ማወቅ፡–
ግጭቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ መንስኤያቸውን ለይቶ ማወቅ
ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግና በቀላሉ መፍትሄ
ለማፈላለግ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ ግጭት በሃሳብ
አለመግባባት ቢፈጠር ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው ተጋጪው
ካለው የአስተሳሰብ፤ የባህል ፤ የአስተዳደግ ፤ ወይም
ከግለሰቡ የግል ባህርይ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ
መቻል ግጭቱን በቀላሉ ለመፍታት ይረዳል፡፡
2. አማራጭ መፍትሄዎችን ማየት
ለተከሰተው የሃሳብ ልዩነት ወይም ግጭት እንደመፍትሄ
ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጭ መንገዶችን ማየት ግጭትን
በቀላሉ ለመፍታት ያስችላል፡፡
3. ስሜታዊነትን ማስወገድ
አብዛኛውን ጊዜ በስሜታዊነት የሚወሰዱ እርምጃዎች
ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው የጎላ ነው፡፡
በመሆኑም ግጭት በሚነሳበት ወቅት እራስን ለመቆጣጠር
እና ከስሜታዊነት የጸዳ ውሳኔ ለመወሰን ይቻል ዘንድ
ግጭቱ ከተነሳበት አካባቢ በመራቅ ረጋ ብሎ ማሰብ
ያስፈልጋል፡፡
4. ስምምነት መፍጠር
የተፈጠረውን አጋጣሚ አንስቶ ፊት ለፊት በግልጽ
በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት
ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እንደ አስፈላጊነቱ
ሌላ ሦስተኛ አካል ገብቶ የሚያነጋግርበትን መንገድ
በመፈለግ ከግጭት ይልቅ ስምምነት የሚፈጥርበትን ሁኔታ
ማመቻቸት ይገባል ፡፡ መልካም ምሽት❤️
ሼር ያድርጉት
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
በመጀመሪያ ሰው ላመነበት ነገር ባሪያ ነው አራት ነጥብ፡፡
ምንም ብትተቸው ብትነቅፈው አመለካከቱ/እይታው በእራሱ
መነጸር ትክክል ነው ለድርድር አይቀርብም (ትክክል
አለመሆኑን ህሊናው ነግሮት ወይም በነጽሮት እራሱን
ለለውጥ እስካላዘጋጀ ድረስ)፡፡ (ለዚህም ነው በህክምና
ዘርፍ የአእምሮ ህሙማን በጥንቃቄ ሊያዙና እንክብካቤ
ሊደረግላቸው እንደሚገባ ምክር የሚለገሰው፡፡ ምክንያቱም
ባጋጠማቸው የጤና መታወክ ደረጃ አስተሳሰባቸው
እራሳቸውንና ሌላውን እስካልጎዳ ድረስ ጤናማ ናቸው
ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ልብ ይሎአል፡፡
ግን በጣም ታመውም ምንም አንዳልሆኑና እንዳልታመሙ
ሆነው ሊከራከሩና ከህክምና ሊርቁም ስለሚችሉ የሌሎች
ዕርዳትና እገዛ የሚያስፈልጋቸው፡፡ እንደው በአጋጣሚ
አነሳውት እንጂ ሃሳባችንና ትኩረታችን “ጤናማ ሰው” ብለን
የምናስበውን ነው፡፡) ይህ ማለት ግን የአንዱ እውነት ወይም
የሌላው ምልከታ በሌሎች አረዳድና ግንዛቤ ትክክልና ቀቡል
ነው ማለት አይቻልም ሊሆንም አይችልም፡፡ እዚህ ጋ የአንዱ
እውነት/ሐሰት ለሌላው ሐሰት/እውነት ሊሆን የሚችለው
በንጽጽር መልኩ ካየነው ብቻ ነው፡፡ ያለ ንጽጽር እውነትም
ሐሰት ነው ሐሰትም እውነት ነው፡፡ ለብቻው ቀጥ ብሎ
የሚቆምና የሚኖር እስካልሆነ ድረስ፡፡
ታዲያ እኔ ከአንተ በሃሳብ ልስማማምና ላልስማማም
እንደምችል ካወቅህ አንተም በራስ መንገድ አሸናፊ ነህ
እኔም እንደዚያው፡፡ ግን የአንድን ነገር እውነታ በንግግርና
በክርክር እንግለጸው ካልክ ሁለታችንም እውነት ነው ብለን
ካመንበትና ከተነሳንበት የእይታ ስፍራ ያደረግነውን መነጽር
ማውለቅ አለብን፡፡ ምክንያቱም አሁን ልንነጋገር
እየተንደረደርን ያለነው ስለ አንጻሪዊ እውነትነት ወይም
ሐሰትነት ሳይሆን በሁለታችን መሃል ስላለው ተቀባይነት
ነው፡፡ ስለዚህ በሃሳብ መቀመሪችን እንነጋገራለን እንፋጫለን
(ከስሜት በጸዳ መልኩና በምክንያት) ልኬቱ በተስተካከለ ፤
በሰከነ ፤ በአስተዋይነት ፤ ዕውቀትንና ቅንነትን መሰረት
ያደረገ አመለካከት ከሆነ መቁረጫው ቀላል ነው
የሚሆነው፡፡ የሃሳቡን መቁረጫ ልኬት ወደ አወንታዊነት
ስለሚቀይረው፡፡ እንደ እኔ እይታና አረዳድ አወንታዊነት
(positivity) የአንድን ነገር መልካም ጎን ብቻ መመልከት
ሳይሆን ደካማውን አካቶ ሚዛናዊ የሆነውን መያዝ ነው፡፡
የአወንታዊ ምልከታው በሃምራዊ መነጸር እይታ የተጋረደ
መሆን የለበትም፡፡ መነጽሩ የሚያሳየን ማየት የምንፈልገው
ነገር ብቻ ስለሆነ:: በአስቀመጥነው የሃሳብ/አመለካከት
ልኬት ለመቁረጥ መነጽሩ መውለቅ አለበት በሁሉም
አቅጣጫ ለማየት እንዲያስችለን፡፡ ከዚያ በኋላ ውጤቱ
ምንም ይሁን ምን ሁለታችንም አሸናፊዎች ስለሆንን
በልዩነትና በመከባበር እናልፈዋለን፡፡ ለዘለፋና ለትችትም
አጋልጦ አይሰጠንም፡፡ ስለዚህ የእኛ የሃሳብ ልኬት
በእራሳችን ወይስ በሌሎች ንጽጽር መለካት/መቆረጥ
ያለበት? በሁለቱም እንደ ነገሮች ሁኔታ ቢለያይም፡፡
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ምንም ብትተቸው ብትነቅፈው አመለካከቱ/እይታው በእራሱ
መነጸር ትክክል ነው ለድርድር አይቀርብም (ትክክል
አለመሆኑን ህሊናው ነግሮት ወይም በነጽሮት እራሱን
ለለውጥ እስካላዘጋጀ ድረስ)፡፡ (ለዚህም ነው በህክምና
ዘርፍ የአእምሮ ህሙማን በጥንቃቄ ሊያዙና እንክብካቤ
ሊደረግላቸው እንደሚገባ ምክር የሚለገሰው፡፡ ምክንያቱም
ባጋጠማቸው የጤና መታወክ ደረጃ አስተሳሰባቸው
እራሳቸውንና ሌላውን እስካልጎዳ ድረስ ጤናማ ናቸው
ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ልብ ይሎአል፡፡
ግን በጣም ታመውም ምንም አንዳልሆኑና እንዳልታመሙ
ሆነው ሊከራከሩና ከህክምና ሊርቁም ስለሚችሉ የሌሎች
ዕርዳትና እገዛ የሚያስፈልጋቸው፡፡ እንደው በአጋጣሚ
አነሳውት እንጂ ሃሳባችንና ትኩረታችን “ጤናማ ሰው” ብለን
የምናስበውን ነው፡፡) ይህ ማለት ግን የአንዱ እውነት ወይም
የሌላው ምልከታ በሌሎች አረዳድና ግንዛቤ ትክክልና ቀቡል
ነው ማለት አይቻልም ሊሆንም አይችልም፡፡ እዚህ ጋ የአንዱ
እውነት/ሐሰት ለሌላው ሐሰት/እውነት ሊሆን የሚችለው
በንጽጽር መልኩ ካየነው ብቻ ነው፡፡ ያለ ንጽጽር እውነትም
ሐሰት ነው ሐሰትም እውነት ነው፡፡ ለብቻው ቀጥ ብሎ
የሚቆምና የሚኖር እስካልሆነ ድረስ፡፡
ታዲያ እኔ ከአንተ በሃሳብ ልስማማምና ላልስማማም
እንደምችል ካወቅህ አንተም በራስ መንገድ አሸናፊ ነህ
እኔም እንደዚያው፡፡ ግን የአንድን ነገር እውነታ በንግግርና
በክርክር እንግለጸው ካልክ ሁለታችንም እውነት ነው ብለን
ካመንበትና ከተነሳንበት የእይታ ስፍራ ያደረግነውን መነጽር
ማውለቅ አለብን፡፡ ምክንያቱም አሁን ልንነጋገር
እየተንደረደርን ያለነው ስለ አንጻሪዊ እውነትነት ወይም
ሐሰትነት ሳይሆን በሁለታችን መሃል ስላለው ተቀባይነት
ነው፡፡ ስለዚህ በሃሳብ መቀመሪችን እንነጋገራለን እንፋጫለን
(ከስሜት በጸዳ መልኩና በምክንያት) ልኬቱ በተስተካከለ ፤
በሰከነ ፤ በአስተዋይነት ፤ ዕውቀትንና ቅንነትን መሰረት
ያደረገ አመለካከት ከሆነ መቁረጫው ቀላል ነው
የሚሆነው፡፡ የሃሳቡን መቁረጫ ልኬት ወደ አወንታዊነት
ስለሚቀይረው፡፡ እንደ እኔ እይታና አረዳድ አወንታዊነት
(positivity) የአንድን ነገር መልካም ጎን ብቻ መመልከት
ሳይሆን ደካማውን አካቶ ሚዛናዊ የሆነውን መያዝ ነው፡፡
የአወንታዊ ምልከታው በሃምራዊ መነጸር እይታ የተጋረደ
መሆን የለበትም፡፡ መነጽሩ የሚያሳየን ማየት የምንፈልገው
ነገር ብቻ ስለሆነ:: በአስቀመጥነው የሃሳብ/አመለካከት
ልኬት ለመቁረጥ መነጽሩ መውለቅ አለበት በሁሉም
አቅጣጫ ለማየት እንዲያስችለን፡፡ ከዚያ በኋላ ውጤቱ
ምንም ይሁን ምን ሁለታችንም አሸናፊዎች ስለሆንን
በልዩነትና በመከባበር እናልፈዋለን፡፡ ለዘለፋና ለትችትም
አጋልጦ አይሰጠንም፡፡ ስለዚህ የእኛ የሃሳብ ልኬት
በእራሳችን ወይስ በሌሎች ንጽጽር መለካት/መቆረጥ
ያለበት? በሁለቱም እንደ ነገሮች ሁኔታ ቢለያይም፡፡
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
እራስን ማክበር 🙏እውነት ነው እኛ ኢትዩጵያውያን ሰው አክባሪዎች ነን፡፡ግና
ሰው ማለት ማን ነው? ሌሎች ሰዎች? ወይስ እኔ እራሴ?
እርግጥ ነው አምናለሁ እኛ ኢትዩጵያውያን እንግዳ
አክባሪዎች ነን ፤በዕድሜ ጠና ያሉ አባቶችን እና እናቶችን
እናከብራለን ከመቀመጫጭን ብድግ ብለን “ኖሩ አባቴ”
ብለን ወንበራችን እንለቃለን፡፡አሪፍ ባህል! ባህል እንግዲህ
አንጻራዊ አይደል… እዚህ ለፈረንጆቹ ብድግ ብላችሁ
ተቀመጡ ብትሏቸው ምላሹ ተቃራኒ ነው፡፡ በእኔ እይታ
እንደተረዳሁት ከሆነ አረጋውያንን ለመርዳት ብትሞክሩ
ውጤቱ እንደ ሀገራቸን “ተባረኩ“ “ክፉ አይንካችሁ” ሳይሆን
ግልምጫ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም መረዳታቸውን
ከጥገኝነት ጋር ስለሚያይዙት፡፡ ሁሉም ግን እንደዚህ ያስባሉ
ማለት አይለደም፡፡ እንዲያው በዚያው ወግ ቢጤ አሰኝቶኝ
ነው እንጅ የዛሬ ትኩረቴስ ሌላ ነው… እነሱም
ጥገኝነታቸውን ያባሩ እኛም መልካም ባህላችንን
እናበለጽግ፡፡ እንከባበር…ተባረኩ!
ሌሎችን ማፍቀር ከእራስ ማፈቀር ይጀምራል እንደሚባለው፤
ሌሎችን ማክበር እራስን ከማክበር ይጀምራል ብየ
አምናለሁ፡፡ እራስን ማክበር ከእራስ ጋር ለመስማማት፤ ስለ
እራስ መልካም አመለካከትና ስሜት ለማዳበር መሰረታዊ
ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌጨው
ባለዕዳ አይቀበለውም ይሉ አይደል አበው ሲተርቱ፡፡ ብዙ
ጊዜ “እራስ” የሚል ጽንሰ ሃሳብ በጽሁፎቼ በተደጋጋሚ
እጠቀማለሁ ምክኒያቱም የሁሉም ፀባይና ባህርይ
መጀመሪያ እራሳችን ስለሆን፡፡ ደስ የሚለው ነገር እራሳችሁን
ሁሌም ታገኙታላችሁ በቁጥጥራችሁ ውስጥ ስለሆነ
መልካሙን አሊያም አሉታዊውን ነገር ማስረጽት ችላላቸሁ፡፡
ስለዚህ ለሚሰማን፣ለምናስበው፣ለምንተገብረውና
ለአጠቃላይ ማንነታችን የላቀ ሀላፊነት አለን ማለት ነው፡፡
የችግሩ መንስኤ ሌላ ሰው ነው ብለን ምናምን ከሆነ ግን
የቁጥጥር መጠናችን አናሳ ነው፡፡ የምንፈልገውን ለመሆን
እራሳችን ላይ እንጀምር…
በአጭር አገላለጽ እራሳችን ማክበር እንለማመድ
ምክኒያቱም ከሌሎች ግለሰቦች ጋር በሰላም ለመኖር
መከባባር እንደሚያስፈልግ ሁሉ ከእራሳችን ጋር መልካም
ግንኑነት ለመፍጠር እራሳችን ማክበር ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ወዳጃችሁ በሆነ ባልሆነ በእራሱ ጥፋት
ከፍቅረኛው ጋር እየተጋጨ እንደሆነ ቢያማክራችሁ…
በአብዛኛው እንዴት እንደዚህ አይነት ጥፋት ታጠፋለህ
ብላችሁ አትቆጡትም፡፡ በእርጋታና በአክብሮት ትሰሙታላችሁ
እንጅ፡፡ እናንተ ይህ ወዳጃችሁ ያጠፋውን ጥፋት ብትፈጽሙ
ከእራሳችሁ ጋር እንዴት ባለ መንፈስ ነው የምትነጋገሩት?
በአክብሮት ልክ ሌሎች ግለሰቦችን እንደምታዋዩ ? ወይስ
በብስጭትና በቁጣ? ስለማንኛውም ጉዳይ ከእራሳችን ጋር
በምንነጋገርበት ጊዜ በአክብሮት መንፈስ ከሆነ ለነገሩ ተገቢ
መፍትሄ እንዲሁም በጉዳዩ ምክኒያት የሚሰማንን መጥፎ
ስሜት ይቀንሰዋል፡፡ ማድረግ የሌለብንን ነገር ስንፈጽም
እራሳችንን በትሁት መንፈስ የማውራታችንን ጥቅም
ለመረዳት ቆም ብላችሁ “ይህን የፈጸምኩትን ጉዳይ አከሌ
ቢፈጽመው እንዴት ብዬ አዳምጠውና ምክር እለግሰው
ነበር?” ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ይህ ባልንጀራችሁ ብትበሳጩበት
እንዴት ነገሩን እንደሚያባብስበት መረዳት ቀላል ነው፡፡
ስለዚህ እራሳችን በሆነ ባልሆነው የምናመናጭቅ ከሆነ
እንደዚሁ ለችግሩ መፍትሄ ከስጠት ይልቅ ሚዛናዊ
አስተሳሰባችን በማሳት የበለጠ ችግሩን እናባብሳለን፡፡
ሌሎችን ማክበር እራስን ከማክበር ይጀምራል ! ማራኪ እሁድ ተመኙሁ 💓
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
ሰው ማለት ማን ነው? ሌሎች ሰዎች? ወይስ እኔ እራሴ?
እርግጥ ነው አምናለሁ እኛ ኢትዩጵያውያን እንግዳ
አክባሪዎች ነን ፤በዕድሜ ጠና ያሉ አባቶችን እና እናቶችን
እናከብራለን ከመቀመጫጭን ብድግ ብለን “ኖሩ አባቴ”
ብለን ወንበራችን እንለቃለን፡፡አሪፍ ባህል! ባህል እንግዲህ
አንጻራዊ አይደል… እዚህ ለፈረንጆቹ ብድግ ብላችሁ
ተቀመጡ ብትሏቸው ምላሹ ተቃራኒ ነው፡፡ በእኔ እይታ
እንደተረዳሁት ከሆነ አረጋውያንን ለመርዳት ብትሞክሩ
ውጤቱ እንደ ሀገራቸን “ተባረኩ“ “ክፉ አይንካችሁ” ሳይሆን
ግልምጫ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም መረዳታቸውን
ከጥገኝነት ጋር ስለሚያይዙት፡፡ ሁሉም ግን እንደዚህ ያስባሉ
ማለት አይለደም፡፡ እንዲያው በዚያው ወግ ቢጤ አሰኝቶኝ
ነው እንጅ የዛሬ ትኩረቴስ ሌላ ነው… እነሱም
ጥገኝነታቸውን ያባሩ እኛም መልካም ባህላችንን
እናበለጽግ፡፡ እንከባበር…ተባረኩ!
ሌሎችን ማፍቀር ከእራስ ማፈቀር ይጀምራል እንደሚባለው፤
ሌሎችን ማክበር እራስን ከማክበር ይጀምራል ብየ
አምናለሁ፡፡ እራስን ማክበር ከእራስ ጋር ለመስማማት፤ ስለ
እራስ መልካም አመለካከትና ስሜት ለማዳበር መሰረታዊ
ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌጨው
ባለዕዳ አይቀበለውም ይሉ አይደል አበው ሲተርቱ፡፡ ብዙ
ጊዜ “እራስ” የሚል ጽንሰ ሃሳብ በጽሁፎቼ በተደጋጋሚ
እጠቀማለሁ ምክኒያቱም የሁሉም ፀባይና ባህርይ
መጀመሪያ እራሳችን ስለሆን፡፡ ደስ የሚለው ነገር እራሳችሁን
ሁሌም ታገኙታላችሁ በቁጥጥራችሁ ውስጥ ስለሆነ
መልካሙን አሊያም አሉታዊውን ነገር ማስረጽት ችላላቸሁ፡፡
ስለዚህ ለሚሰማን፣ለምናስበው፣ለምንተገብረውና
ለአጠቃላይ ማንነታችን የላቀ ሀላፊነት አለን ማለት ነው፡፡
የችግሩ መንስኤ ሌላ ሰው ነው ብለን ምናምን ከሆነ ግን
የቁጥጥር መጠናችን አናሳ ነው፡፡ የምንፈልገውን ለመሆን
እራሳችን ላይ እንጀምር…
በአጭር አገላለጽ እራሳችን ማክበር እንለማመድ
ምክኒያቱም ከሌሎች ግለሰቦች ጋር በሰላም ለመኖር
መከባባር እንደሚያስፈልግ ሁሉ ከእራሳችን ጋር መልካም
ግንኑነት ለመፍጠር እራሳችን ማክበር ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ወዳጃችሁ በሆነ ባልሆነ በእራሱ ጥፋት
ከፍቅረኛው ጋር እየተጋጨ እንደሆነ ቢያማክራችሁ…
በአብዛኛው እንዴት እንደዚህ አይነት ጥፋት ታጠፋለህ
ብላችሁ አትቆጡትም፡፡ በእርጋታና በአክብሮት ትሰሙታላችሁ
እንጅ፡፡ እናንተ ይህ ወዳጃችሁ ያጠፋውን ጥፋት ብትፈጽሙ
ከእራሳችሁ ጋር እንዴት ባለ መንፈስ ነው የምትነጋገሩት?
በአክብሮት ልክ ሌሎች ግለሰቦችን እንደምታዋዩ ? ወይስ
በብስጭትና በቁጣ? ስለማንኛውም ጉዳይ ከእራሳችን ጋር
በምንነጋገርበት ጊዜ በአክብሮት መንፈስ ከሆነ ለነገሩ ተገቢ
መፍትሄ እንዲሁም በጉዳዩ ምክኒያት የሚሰማንን መጥፎ
ስሜት ይቀንሰዋል፡፡ ማድረግ የሌለብንን ነገር ስንፈጽም
እራሳችንን በትሁት መንፈስ የማውራታችንን ጥቅም
ለመረዳት ቆም ብላችሁ “ይህን የፈጸምኩትን ጉዳይ አከሌ
ቢፈጽመው እንዴት ብዬ አዳምጠውና ምክር እለግሰው
ነበር?” ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ይህ ባልንጀራችሁ ብትበሳጩበት
እንዴት ነገሩን እንደሚያባብስበት መረዳት ቀላል ነው፡፡
ስለዚህ እራሳችን በሆነ ባልሆነው የምናመናጭቅ ከሆነ
እንደዚሁ ለችግሩ መፍትሄ ከስጠት ይልቅ ሚዛናዊ
አስተሳሰባችን በማሳት የበለጠ ችግሩን እናባብሳለን፡፡
ሌሎችን ማክበር እራስን ከማክበር ይጀምራል ! ማራኪ እሁድ ተመኙሁ 💓
join👇👇👇
@httptelegramme81biniyamin
የውለታ ባንክ 🏦ታዋቂው ብራዚላዊ ደራሲ ፓውሎ ኮሊዮ ዘ ዛሂር በተሰኘው
ረጅም ልቦለዱ ላይ በአንድ ገፀ-ባህሪ አማካኝነት ስለ
ውለታ ባንክ (favor bank) እንዲህ ይለናል፡፡ አንድ ሰው
ጥሩ ስራ ለሌላው ሰው ሲሰራ ውለታ የሰራለት ሰው ላይ
የቁጠባ ሂሳብ ከፍቶ ውለታን አንድ ብሎ ይቆጥባል በዚህም
ውለታ አድራጊው (ቆጣቢው) በሌላ ጊዜ ከዛኛው ሰው
እርዳታ ሲፈልግ ሄዶ ይጠይቃል፤ የቆጠበውን እንደማውጣት
ማለት ነው፡፡ ያኛው ሰውም፣ ውለታ የተደረገለት (ባንኩ)
ያለፈውን ውለታ በመቁጠር መልሶ ውለታውን ይከፍላል፡፡
ስለዚህ በገፀ-ባህርይዋ አመለካከት አንድ ሰው ለሌላ ሰው
መልካም ስራን የሚሰራው ተረጂው ሰው ስለሚያስፈልገው
ብቻ ሳይሆን ረጂው በራሱ ከዚህ ሰው (ከተረጂው) በሌላ
ጊዜ የሚፈልገው እርዳታ ስላለ ነው ወይም ወደፊት
ስለሚኖር ነው ማለት ነው፡፡
የሰው ልጅ መልካም ግንኙነቶች ካረፈባቸው ዋልታዎች
መካከል አንዱ ለሰዎች መልካም ስራን መስራት ነው፡፡
መልካም ስራ (Prosocial behavior) በማህበረሰቡ እንደ
በጎ ስራ የተያዘ፤ ለግለሰብ ወይም ለማህበረሱ ጥቅም
የሚሰራ አድራጎት ማለት ሲሆን፣ ግለሰባዊ መልካም ስራ
(Altruism) ማለት ደግሞ ሌሎችን የመርዳትን አላማን
በውስጡ ያነገበ ራስን መስወዕት እስከ ማድረግ የሚደርስ
ባህርይ ማለት ነው፡፡ሌላን ሰው ለመርዳት በሚነድ ቤት
ውስጥ ገብተው እሳት ለማጥፋት ራሳቸውን አደጋ ላይ
የሚከቱ ሰዎች እንደምሳሌ መጥቀስ እንችላለን፡፡
በድንገተኛ አደጋ ውስጥ ገብተው ሌሎችን የሚረዱ ሰዎች
ከማይረዱ ሰዎች የተለየ የስብዕና መገለጫ (personality
traits) አላቸው ከነዚህም መካከል በራስ መተማመን፣
አዛኝነት (sympathetic)፣የሌላን ስሜት መረዳት የሚችሉ
(understanding) እንዲሁም የሰዎችን ችግር እንደራሳቸው
የሚያዩ (empathetic) ናቸው፡፡ አንዳንድ የማህበረሰብ
ሳይኮሎጂስቶች ግን በነዚህ ነጥቦች አይስማሙም
መከራከሪያቸውም ሰው በአደጋ ያለን ሌላን ሰው የሚረዳው
በጊዜው ባለው ስሜት (mood) ነው የሚል ነው፡፡ ባጠቃላይ
እራሳችንን አደጋ ውስጥ ከተን ሰዎችን ስንረዳና የሌሎችን
ጥቅም ብቻ ስናስቀድም ድርጊቱ ወይም ባህርዩ
(Altruism) ሲባል ድርጊቱን ፈጻሚው ደግሞ (Altruist)
ይባላል፡፡ ብዙዎቻችን በተለያዩ መንገዶች ሌላን ሰው ወይም
ማህበረሰቡን ለመጥቀም የምንሰራው ስራ ደግሞ
(Prosocial behavior) እንለዋለን፡፡
ግን ምን ያህሎቻችን ነን የሰውን ጥቅም ብቻ በማስቀደም
መልካም ስራን የምንሰራው ?? መልካም ስራ ስንሰራስ
ለእኛ ምን አለው የሚለውን የማንጠብቅ?? በተለምዶ
ውለታ መላሽ ያድርገኝ ወይም ወሮታውን እከፍላለው ስንባል
እውነት ከዛ ሰው የውለታ ባንክ ውስጥ ቆይቶ የሚከፈል
ውለታ እንዳስቀመጥን እርግጠኛ የማንሆንስ ስንቶቻችን
ነን?? ብዙዎቻችን የእነሱ እርዳታ ባስፈለገን ጊዜ
እንደሚረዱን እርግጠኛ እንሆናለን ምክንያቱም ያስቀመጥነው
ውለታ አለና፡፡ ስለዚህ እነዚን ነገሮች እያሰብን የምንሰራው
ስራ ለሌላው የተደረገ መልካም ስራ ይሆናል?? ውድ
የሳይኮሎጂ ቤተሰቦች ጥያቄ አነሳሁኝ እንጂ ድምዳሜ ላይ
እንዳልደረስኩኝ አፅንኦት ሰጡልኝ፡፡
ከላይ ባስቀመጥነው ምሳሌ መሰረት መልካም ስራ
የሚደረግለት ሰው ባንክ ሲሆን መልካም ስራ ሰሪው ደግሞ
ብር አስቀማጭ ደንበኛ ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም ባንኩ
ገንዘቡን በማንቀሳቀስ ይሰራበታል ቆጣቢው በጠየቀው ጊዜ
ደግሞ ገንዘቡን አውጥቶ ይሰጠዋል ፡፡በጎ ስራ የሚደረግለት
ሰው ውለታን በውለታ ይመልሳል ልክ ዕዳውን እንደመክፈል
ማለት ነው፡፡ መልካም ስራ ምንድን ነው ?? መልካም ስራ
የሚያስብሉትስ መሰረታዊ መገለጫዎች ምንድን ናቸው??
እስኪ ሁላችንም ባለንበት እንወያይበት፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ…….
@httptelegramme81biniyamin
ረጅም ልቦለዱ ላይ በአንድ ገፀ-ባህሪ አማካኝነት ስለ
ውለታ ባንክ (favor bank) እንዲህ ይለናል፡፡ አንድ ሰው
ጥሩ ስራ ለሌላው ሰው ሲሰራ ውለታ የሰራለት ሰው ላይ
የቁጠባ ሂሳብ ከፍቶ ውለታን አንድ ብሎ ይቆጥባል በዚህም
ውለታ አድራጊው (ቆጣቢው) በሌላ ጊዜ ከዛኛው ሰው
እርዳታ ሲፈልግ ሄዶ ይጠይቃል፤ የቆጠበውን እንደማውጣት
ማለት ነው፡፡ ያኛው ሰውም፣ ውለታ የተደረገለት (ባንኩ)
ያለፈውን ውለታ በመቁጠር መልሶ ውለታውን ይከፍላል፡፡
ስለዚህ በገፀ-ባህርይዋ አመለካከት አንድ ሰው ለሌላ ሰው
መልካም ስራን የሚሰራው ተረጂው ሰው ስለሚያስፈልገው
ብቻ ሳይሆን ረጂው በራሱ ከዚህ ሰው (ከተረጂው) በሌላ
ጊዜ የሚፈልገው እርዳታ ስላለ ነው ወይም ወደፊት
ስለሚኖር ነው ማለት ነው፡፡
የሰው ልጅ መልካም ግንኙነቶች ካረፈባቸው ዋልታዎች
መካከል አንዱ ለሰዎች መልካም ስራን መስራት ነው፡፡
መልካም ስራ (Prosocial behavior) በማህበረሰቡ እንደ
በጎ ስራ የተያዘ፤ ለግለሰብ ወይም ለማህበረሱ ጥቅም
የሚሰራ አድራጎት ማለት ሲሆን፣ ግለሰባዊ መልካም ስራ
(Altruism) ማለት ደግሞ ሌሎችን የመርዳትን አላማን
በውስጡ ያነገበ ራስን መስወዕት እስከ ማድረግ የሚደርስ
ባህርይ ማለት ነው፡፡ሌላን ሰው ለመርዳት በሚነድ ቤት
ውስጥ ገብተው እሳት ለማጥፋት ራሳቸውን አደጋ ላይ
የሚከቱ ሰዎች እንደምሳሌ መጥቀስ እንችላለን፡፡
በድንገተኛ አደጋ ውስጥ ገብተው ሌሎችን የሚረዱ ሰዎች
ከማይረዱ ሰዎች የተለየ የስብዕና መገለጫ (personality
traits) አላቸው ከነዚህም መካከል በራስ መተማመን፣
አዛኝነት (sympathetic)፣የሌላን ስሜት መረዳት የሚችሉ
(understanding) እንዲሁም የሰዎችን ችግር እንደራሳቸው
የሚያዩ (empathetic) ናቸው፡፡ አንዳንድ የማህበረሰብ
ሳይኮሎጂስቶች ግን በነዚህ ነጥቦች አይስማሙም
መከራከሪያቸውም ሰው በአደጋ ያለን ሌላን ሰው የሚረዳው
በጊዜው ባለው ስሜት (mood) ነው የሚል ነው፡፡ ባጠቃላይ
እራሳችንን አደጋ ውስጥ ከተን ሰዎችን ስንረዳና የሌሎችን
ጥቅም ብቻ ስናስቀድም ድርጊቱ ወይም ባህርዩ
(Altruism) ሲባል ድርጊቱን ፈጻሚው ደግሞ (Altruist)
ይባላል፡፡ ብዙዎቻችን በተለያዩ መንገዶች ሌላን ሰው ወይም
ማህበረሰቡን ለመጥቀም የምንሰራው ስራ ደግሞ
(Prosocial behavior) እንለዋለን፡፡
ግን ምን ያህሎቻችን ነን የሰውን ጥቅም ብቻ በማስቀደም
መልካም ስራን የምንሰራው ?? መልካም ስራ ስንሰራስ
ለእኛ ምን አለው የሚለውን የማንጠብቅ?? በተለምዶ
ውለታ መላሽ ያድርገኝ ወይም ወሮታውን እከፍላለው ስንባል
እውነት ከዛ ሰው የውለታ ባንክ ውስጥ ቆይቶ የሚከፈል
ውለታ እንዳስቀመጥን እርግጠኛ የማንሆንስ ስንቶቻችን
ነን?? ብዙዎቻችን የእነሱ እርዳታ ባስፈለገን ጊዜ
እንደሚረዱን እርግጠኛ እንሆናለን ምክንያቱም ያስቀመጥነው
ውለታ አለና፡፡ ስለዚህ እነዚን ነገሮች እያሰብን የምንሰራው
ስራ ለሌላው የተደረገ መልካም ስራ ይሆናል?? ውድ
የሳይኮሎጂ ቤተሰቦች ጥያቄ አነሳሁኝ እንጂ ድምዳሜ ላይ
እንዳልደረስኩኝ አፅንኦት ሰጡልኝ፡፡
ከላይ ባስቀመጥነው ምሳሌ መሰረት መልካም ስራ
የሚደረግለት ሰው ባንክ ሲሆን መልካም ስራ ሰሪው ደግሞ
ብር አስቀማጭ ደንበኛ ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም ባንኩ
ገንዘቡን በማንቀሳቀስ ይሰራበታል ቆጣቢው በጠየቀው ጊዜ
ደግሞ ገንዘቡን አውጥቶ ይሰጠዋል ፡፡በጎ ስራ የሚደረግለት
ሰው ውለታን በውለታ ይመልሳል ልክ ዕዳውን እንደመክፈል
ማለት ነው፡፡ መልካም ስራ ምንድን ነው ?? መልካም ስራ
የሚያስብሉትስ መሰረታዊ መገለጫዎች ምንድን ናቸው??
እስኪ ሁላችንም ባለንበት እንወያይበት፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ…….
@httptelegramme81biniyamin
ለምን እንዎሻለን ❓❓❓ ሰላም ለእናንተ
ከሜክሲኮ ወደ አራት ኪሎ ለመሄድ የታክሲ ሰልፍ
መጨረሻ ላይ ተሰልፌያለሁ፡፡ መቼም የስራ መውጫ ሰዓት
ስለነበር የሰልፉን እርዝመት ልነግራችሁ አልችልም ደግነቱ
የታክሲው ቶሎ ቶሎ መምጣት በጊዜ ወደ ቤት የመግባት
ተስፋዬን አለምልሞታል፡፡ ከኋላዬ አንዲት ወጣት ሴት ልጅ
መጥታ ተሰለፈች በስልኳ እያወራች ነበር ልጅቷ
የምታወራውን የጽሁፌ መነሻ ስለሆነ እነግራችኋለሁ በስልኩ
በዛኛው ጫፍ ሆኖ የሚያወራውን ወዳጅዋን ደግሞ
የሚመልሰውን መልስ ከእርሷ መልስ ጋር እያሰናሰልኩኝ
በምናቤ እመልሳለሁ፡፡
ልጅቷ፡- በጣም ነው የደከመኝ ብታይ በጊዜ ነው ወደ ቤት
የምገባው
ልጁ፡- ትንሽ አንቆይም ናፍቀሽኛል እኮ
ልጅቷ፡- Me too ግን ደክሞኛል እረፍት እፈልጋለሁ የት ነህ
አሁን??
ልጁ፡- (የሆነ ቦታ ይላታል)
ልጅቷ፡- አሪፍ፣ እዛው ነሀ ከ 25 ደቂቃ በኋላ እደርሳለሁ
ስልኩ ይዘጋል የታክሲ ተራችንም ይደርስና ሶስተኛው ወንበር
ላይ ጎን ለ ጎን ተቀምጠን ጉዞ ወደ አራት ኪሎ፡፡ እንቅስቃሴ
የሚበዛበት ሰዓት ስለነበር መንገዱ በመጠኑም ቢሆን
ተዘጋግቷል፡፡ ፓርላማ አካባቢ ስንደርስ ስልኳን አውጥታ
መልሳ ደውላ ደርሼያለሁ ትለዋለች፡፡ እሱም ምን እንዳላት
በእርግጠኝነት ባላውቅም ከመልሷ ግን መረዳት የቻልኩት
ልጁ በቦታው አልነበረም፡፡ ቆይ ግን መዋሸት ምን
አስፈለገህ ?? መቼ ነው ይሄን ውሸትህን የምታቆመው ??
ብላ ስልኩን ድርግም፡፡ ስልኳ በተደጋጋሚ ቢጠራም መልሳ
አላነሳችም፡፡ መጨረሻቸው እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
የእነሱን ጉዳይ እንተውና እስኪ ስለ ውሸት ትንሽ እናውራ፡-
ውሸትን የተለያዩ ምሁራን ትርጓሜና እና ማብራሪያ
ሰጥተውበታል በዚህም ነጋሪውን ለመጥቀም የታሰበ
ሐሰታዊ የሆነ ግንኙነት(ሚሼል) የሚለው መጀመሪያው ሲሆን
ይህም ብዙ ውዝግቦችን አስነስቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም
ነጋሪውን ብቻ ለመጥቀም ውሸት አይነገርም የሚሉ፣ ውሸት
ሆን ተብሎ የሚደረግ እውነትን የመደበቅ ስራ ነው ብለው
መልስ የሰጡ ብዙ ወገኖች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የውሸት
ማብራሪያ ወይም ፍቺ መሰረትም ሰዎች ሳያውቁት የተሳሳተ
መረጃ ከተናገሩ እንደ ውሸት አይቆጠርም ማለት ነው፡፡
በርገን እና ቡለር የተባሉ ሁለት ምሁራን ደግሞ ውሸት
ማለት መልዕክት ላኪው ለመልዕክት (መረጃ) ተቀባዩ ሆን
ብሎ የተሳሳተ መረጃ በማቀበል መልዕክት ተቀባዩን
መጉዳት ነው ይሉናል፡፡ እኛ ደግሞ የእራሳችን የሆነ የውሸት
ትርጉም ወይም ፍቺ ይኖረናል፡፡
ውሸት ብዙ ጊዜ በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም
በድርጊትም ጭምር እንጂ ለምሳሌ ያልተጎዳ አትሌት
እግሩን እንደተጎዳ አድርጎ እያነከሰ ከውድድር ወይም
ከስልጠና ካቋረጠ ዋሽቷል ማለት ነው፡፡ መረጃን ሆን ብሎ
መደበቅ ለምሳሌ የገቢን መጠን በመደበቅ ግብርን
ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትም ውሸት ነው፡፡ እኛ ሰዎች
ውሸትን ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእራሳችንም እንዋሻለን
ለአብነትም ማሳካት የፈለግነውን ነገር በራሳችን በሆነ
ምክንያት ካላሳካን ችግሩን በውጪ ኣካል በማሳበብ
(Externalize) ለራሳችን ውሸት እንነግራለን፡፡ እንደ
ዲፓውሎ እና ሌሎችም ምሁራን መሰረት ሶስት የውሸት
ዓይነቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው outright lie (falsification)
ሲሆን በግርድፉ አማርኛ ፍጹም ውሸት የሚባለው ነው
ይህም ውሸት ተናጋሪዎች ከእውነታው ፍጹም ተቃራኒ የሆነ
መረጃን ወይም መልዕክት ይናገራሉ ወይም ያስተላልፋሉ፡፡
ሁለተኛው Exaggeration ወይም ማጋነን ሲሆን በዚህም
ውሸት ተናጋሪዎች እውነታውን በማጋነን ያቀርባሉ ለምሳሌ
ቀጠሮ ላይ አርፎዶ የሚመጣ ተቀጣሪ የመንገዱን መዘጋጋት
ከዕውነታው በተጋነነ መልኩ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ሶስተኛው
የውሸት ዓይነት subtle lie ሲሆን በዚህም የሚነገረው
የውሸት ዓይነት ጥቂት ሆኖ ከብዙ እውነታዎች ጋር
በማቅረብ ሰዎችን ለማማሳት የምንጠቀምበት ነው፡፡
ለምን እንዋሻለን ??
ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡– ለምሳሌ ለስራ ስንውዳደር
ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን
የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡
ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ
ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡
ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች
ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣
ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ
እና እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ (self oriented)
ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው ተብለው የሚዋሹ
ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-
ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት
ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ
እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡
ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት
እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን ምግብ ጣት
ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን
ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡
ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ
ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ
ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን 83% የሚሆኑ የጥናት
ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት
አይቆጥሩትም፡፡ ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ 40% የሆኑት
የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው
ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ
አረጋግጠዋል፡፡ ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ
የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር
ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች
ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ
ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡
ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ
የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም
ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው
የበለጠ ይዋሻል?? ወንድ ወይስ ሴት?? መልሱን ለእናንተ
ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው
ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert)
ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡ውሸትን
እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ
ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ
ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን
ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን
አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ
ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ
የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤
ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው
የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን
ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ
ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት
እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን
እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
ስሜታዊነትን (emotional state)፣ የወሬያቸውን
(የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity) እና ባህርይን
ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral
control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት
ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት
ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ
ከሜክሲኮ ወደ አራት ኪሎ ለመሄድ የታክሲ ሰልፍ
መጨረሻ ላይ ተሰልፌያለሁ፡፡ መቼም የስራ መውጫ ሰዓት
ስለነበር የሰልፉን እርዝመት ልነግራችሁ አልችልም ደግነቱ
የታክሲው ቶሎ ቶሎ መምጣት በጊዜ ወደ ቤት የመግባት
ተስፋዬን አለምልሞታል፡፡ ከኋላዬ አንዲት ወጣት ሴት ልጅ
መጥታ ተሰለፈች በስልኳ እያወራች ነበር ልጅቷ
የምታወራውን የጽሁፌ መነሻ ስለሆነ እነግራችኋለሁ በስልኩ
በዛኛው ጫፍ ሆኖ የሚያወራውን ወዳጅዋን ደግሞ
የሚመልሰውን መልስ ከእርሷ መልስ ጋር እያሰናሰልኩኝ
በምናቤ እመልሳለሁ፡፡
ልጅቷ፡- በጣም ነው የደከመኝ ብታይ በጊዜ ነው ወደ ቤት
የምገባው
ልጁ፡- ትንሽ አንቆይም ናፍቀሽኛል እኮ
ልጅቷ፡- Me too ግን ደክሞኛል እረፍት እፈልጋለሁ የት ነህ
አሁን??
ልጁ፡- (የሆነ ቦታ ይላታል)
ልጅቷ፡- አሪፍ፣ እዛው ነሀ ከ 25 ደቂቃ በኋላ እደርሳለሁ
ስልኩ ይዘጋል የታክሲ ተራችንም ይደርስና ሶስተኛው ወንበር
ላይ ጎን ለ ጎን ተቀምጠን ጉዞ ወደ አራት ኪሎ፡፡ እንቅስቃሴ
የሚበዛበት ሰዓት ስለነበር መንገዱ በመጠኑም ቢሆን
ተዘጋግቷል፡፡ ፓርላማ አካባቢ ስንደርስ ስልኳን አውጥታ
መልሳ ደውላ ደርሼያለሁ ትለዋለች፡፡ እሱም ምን እንዳላት
በእርግጠኝነት ባላውቅም ከመልሷ ግን መረዳት የቻልኩት
ልጁ በቦታው አልነበረም፡፡ ቆይ ግን መዋሸት ምን
አስፈለገህ ?? መቼ ነው ይሄን ውሸትህን የምታቆመው ??
ብላ ስልኩን ድርግም፡፡ ስልኳ በተደጋጋሚ ቢጠራም መልሳ
አላነሳችም፡፡ መጨረሻቸው እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
የእነሱን ጉዳይ እንተውና እስኪ ስለ ውሸት ትንሽ እናውራ፡-
ውሸትን የተለያዩ ምሁራን ትርጓሜና እና ማብራሪያ
ሰጥተውበታል በዚህም ነጋሪውን ለመጥቀም የታሰበ
ሐሰታዊ የሆነ ግንኙነት(ሚሼል) የሚለው መጀመሪያው ሲሆን
ይህም ብዙ ውዝግቦችን አስነስቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም
ነጋሪውን ብቻ ለመጥቀም ውሸት አይነገርም የሚሉ፣ ውሸት
ሆን ተብሎ የሚደረግ እውነትን የመደበቅ ስራ ነው ብለው
መልስ የሰጡ ብዙ ወገኖች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የውሸት
ማብራሪያ ወይም ፍቺ መሰረትም ሰዎች ሳያውቁት የተሳሳተ
መረጃ ከተናገሩ እንደ ውሸት አይቆጠርም ማለት ነው፡፡
በርገን እና ቡለር የተባሉ ሁለት ምሁራን ደግሞ ውሸት
ማለት መልዕክት ላኪው ለመልዕክት (መረጃ) ተቀባዩ ሆን
ብሎ የተሳሳተ መረጃ በማቀበል መልዕክት ተቀባዩን
መጉዳት ነው ይሉናል፡፡ እኛ ደግሞ የእራሳችን የሆነ የውሸት
ትርጉም ወይም ፍቺ ይኖረናል፡፡
ውሸት ብዙ ጊዜ በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም
በድርጊትም ጭምር እንጂ ለምሳሌ ያልተጎዳ አትሌት
እግሩን እንደተጎዳ አድርጎ እያነከሰ ከውድድር ወይም
ከስልጠና ካቋረጠ ዋሽቷል ማለት ነው፡፡ መረጃን ሆን ብሎ
መደበቅ ለምሳሌ የገቢን መጠን በመደበቅ ግብርን
ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትም ውሸት ነው፡፡ እኛ ሰዎች
ውሸትን ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእራሳችንም እንዋሻለን
ለአብነትም ማሳካት የፈለግነውን ነገር በራሳችን በሆነ
ምክንያት ካላሳካን ችግሩን በውጪ ኣካል በማሳበብ
(Externalize) ለራሳችን ውሸት እንነግራለን፡፡ እንደ
ዲፓውሎ እና ሌሎችም ምሁራን መሰረት ሶስት የውሸት
ዓይነቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው outright lie (falsification)
ሲሆን በግርድፉ አማርኛ ፍጹም ውሸት የሚባለው ነው
ይህም ውሸት ተናጋሪዎች ከእውነታው ፍጹም ተቃራኒ የሆነ
መረጃን ወይም መልዕክት ይናገራሉ ወይም ያስተላልፋሉ፡፡
ሁለተኛው Exaggeration ወይም ማጋነን ሲሆን በዚህም
ውሸት ተናጋሪዎች እውነታውን በማጋነን ያቀርባሉ ለምሳሌ
ቀጠሮ ላይ አርፎዶ የሚመጣ ተቀጣሪ የመንገዱን መዘጋጋት
ከዕውነታው በተጋነነ መልኩ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ሶስተኛው
የውሸት ዓይነት subtle lie ሲሆን በዚህም የሚነገረው
የውሸት ዓይነት ጥቂት ሆኖ ከብዙ እውነታዎች ጋር
በማቅረብ ሰዎችን ለማማሳት የምንጠቀምበት ነው፡፡
ለምን እንዋሻለን ??
ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡– ለምሳሌ ለስራ ስንውዳደር
ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን
የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡
ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ
ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡
ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች
ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣
ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ
እና እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ (self oriented)
ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው ተብለው የሚዋሹ
ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-
ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት
ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ
እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡
ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት
እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን ምግብ ጣት
ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን
ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡
ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ
ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ
ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን 83% የሚሆኑ የጥናት
ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት
አይቆጥሩትም፡፡ ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ 40% የሆኑት
የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው
ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ
አረጋግጠዋል፡፡ ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ
የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር
ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች
ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ
ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡
ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ
የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም
ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው
የበለጠ ይዋሻል?? ወንድ ወይስ ሴት?? መልሱን ለእናንተ
ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው
ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert)
ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡ውሸትን
እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ
ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ
ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን
ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን
አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ
ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ
የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤
ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው
የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን
ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ
ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት
እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን
እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
ስሜታዊነትን (emotional state)፣ የወሬያቸውን
(የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity) እና ባህርይን
ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral
control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት
ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት
ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ
ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት
ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን
በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት
ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ
በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና
ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ
ተቀምጠዋል፡፡
የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት
እንችላለን ዲፓውሎ እና ሮዘንሀል በጥናታቸው
እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት
ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን
የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን
ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ
ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ
በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት
የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት
እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና ፀጉራቸውን
ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ
ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን
እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ
ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……
ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣
ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም
ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡
ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን
ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው
ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን
ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን
እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር
ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars
(ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና
ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች)
ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ
እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ………
@httptelegramme81biniyamin
ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን
በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት
ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ
በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና
ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ
ተቀምጠዋል፡፡
የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት
እንችላለን ዲፓውሎ እና ሮዘንሀል በጥናታቸው
እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት
ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን
የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን
ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ
ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ
በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት
የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት
እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና ፀጉራቸውን
ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ
ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን
እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ
ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……
ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣
ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም
ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡
ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን
ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው
ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን
ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን
እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር
ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars
(ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና
ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች)
ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ
እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ………
@httptelegramme81biniyamin
ትዳርና ፍቅር
ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡ የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን ዲፓውሎ እና ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት…
የስነ-ልቦና ጥያቄ፣ አስተያየት ወይም ትምህርት
እንዲሰጥበት የምትፈልጉት ርዕሰ ጉዳይ ካለ የሚከተለውን
አድራሻ ተጠቀሙ፡፡
+251931698282
Email☞biniyaminjemal82@gmail.com
imo +251966988181
እንዲሰጥበት የምትፈልጉት ርዕሰ ጉዳይ ካለ የሚከተለውን
አድራሻ ተጠቀሙ፡፡
+251931698282
Email☞biniyaminjemal82@gmail.com
imo +251966988181