World Fun Facts in Amharic 😱😱
154 subscribers
162 photos
5 links
All Kinds of Funny Surprising🤠 Scary😮 Unbelievable🙀 but Real 👌Facts in this world will be posted on this channel. Stay Safe😷
Just Share and Join 🙏
For any Suggestion, Comment,Promotions,or any thing about this channel
Download Telegram
All world fun facts with pictures will be posted in this Channel
Every day Fun facts or Amazing pictures will be posted


Don't mute this channel!!!
👉 በመካከለኛው ክፍለ ዘመን በጀርመን ፀበኛ ባልና ሚስቶች በተዘጋጀላቸው ቦታ በመፋለም ፀባቸውን ማጣጣም ይችሉ ነበር ፡፡ ይሄ ፍልሚያ ግን የራሱ ህግ ነበረው ህጉም ፦ ባለልየው እስከወገቡ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አንድ እጁ ወደ ጀርባው ይታሰራል ሴትዋ ደሞ እንደፈለገች መንቀሳቀስና በድንጋይ የተሞላ ከረጢት መታጠቅ ትችላለች ! !
#ዴቪልስ_ትሪያንግል👆👆👆 ወይም በሌላኛው አጠራሩ #ቤርሙዳ_ትሪያንግል በጥቂቱ

በምድር ላይ ካሉት ሚስጥራዊ ስፍራዎች አንዱ የቤርሙዳ ትሪያንግል ነው ቤርሙዳ ትሪያንግል ነው ፡፡ ቤርሙዳ ትሪያንግል በአትላንቲክ ውቅያኖሶች ውስጥ ይገኛል ፤ ከአሜሪካ ፍለሎሪዳ ግዛት ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በስተደቡብ በኩል ካሪቢያን ደሴት ያዋስነዋል ፡፡

ቤርሙዳ ትሪያንግልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየው ክርስቶፈር ኮሎምበስ ሲሆን ዘመኑም በ1449 ነበር ፡፡ ተጓዡ ክርስቶፈር ዓለምን በሚያስስበት ወቅት በዚህ ስፍራ ደርሶ አንድ ነገር ተመለከተና በማስታወሻው እንዲህ ሲል ፃፈ

"በአድማስ ላይ የሚደንስ እንግዳ የሆነ የብርሃን ጮራ ፤ በሰማይ ላይ የነገሰ የእሳት ነበልባል ፤ የአቅጣጫ መጠቆሚያን ኮመምፓስን የሚያመሰቃቅል ሀይል" ብሎት ነበር ፡፡

እንደ ብዙዎች አነጋገር ከዛ ከቤርሙዳ ትሪያንግል ቡሃላ ያለውን የምድር ክፍል አዲስ አለም ወይም አዲስ ምድር ብለው ይጠሩታል

ቤርሙዳ ትሪያንግል ባለልታወቀ ሚስጥር በርካታ መርከቦች እና የሰውን ልጅ ህይወት እና ሀብት እንደያዙ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ጠፍቷል ! በአለማችን ላይ ከፍተኛ የመርከብና የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴ የሚደረግበት በዚህ ስፍራ ላይ እንዲ አይነት እንቅስቃሴ ወይም እንግዳ የሆነ እና ሁሉን ውጦ የሚያስቀር ገደል መገኘቱ የሰውን ልጅ እስካሁን ግራ አጋብቷል ፡፡

በቤርሙያ ትሪያንግል አካባቢ እንደ ወጡ ከቀሩት ውስጥ በጥቂቱ በ1812 ቲዎዶስያ በር አልስተን የተባለች የወቅቱ የአሜሪካን ም/ፕሬዝደንት የነበሩት የአሮን በር ልጅ ዲሴምበር 30 በተጠቀሰው አመት ፓትሮዎት በተባለች መርከብ ስትጓዝ በዚያው ቀርታለች ፡፡ በ1945 ፍላይት 19 የተባለች አውሮፕላን ከ14 ተጓዥ ጋር ጠፍታለች ፡፡ በዛኑ ወቅት ፍላይት 19 ፍለጋ የተላኩ 6 አውሮፕላኖች እና 27 ሰዎች እንደወጡ በዛው ቀርተዋል ፡፡ በ1948 ስታር ታይገር 19 የተባለች አውሮፕላን ከ6 አብራሪዎች እና ከ25 ተሳፋሪዎች ጋር ልትጠፋም ችላለች ፡፡ ከ65 አመታትቶች በፊት በዚ በቤርሙዳ ተትሪያንግል በየእለቱ 5 አውሮፕላኖች በዚህ አካባቢ ላይ ሲያልፉ የመስመጥ አደጋ ደርሶባቸዋል መስመጥ ብቻ ሳይሆን ደብዛቸውም ጠፍቷል ብዙ መርከቦች ከነተሳፋሪያቸው ላይመለሱ ቤርሙዳ ትሪያንግል ውስጥ ሊሰምጡ ችለዋል !!

ለቤርሙዳ ትሪያንግል እንዲ መሆን ብዙ መላምቶች ተቀምጠዋል በጥቂቱ

1, ከፍተኛ የማግኔት እና የኤሌክትሮኒክስ ሃይል ያለው ደመና በአካባቢው ሰማይ ላይ መኖር የመርከቦችንና የአውሮፕላኖችን እንቅስቃሴ ያግዳል

2,ያልታወቁ በራሪ ፍጥረታት (UFO) በአካባቢው ሰፍረዋል

3, ሁሪካን የሚባለው ሃይለኛ አውሎ ንፋስ በአካባቢው ሊኖር ይችላል

4,በውቅያኖሱ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት የሚጓዝ አደገኛ ወንዝ ስላለ መርከቦችን እና ፕሌኖችን ጠራርጎ ይወስዳል

5, ሚቴን ሃይድሬት የተባለ ንጥረ ነገር በባህር ውስጥ በከፍተኛ መጠን ስላለ የውሃውን እፍጋት (ዴንሲቲ) ይቀንሰዋል የውሃው ዴንሲቲ በሚቀንስበት ወቅት መርከቦችን የመሸከም አቅሙ ስለሚወርድ መርከቦቹ በቀላሉ ይሰምጣሉ ፡፡

6,ሰይጣናዊ ቦታ ነው ተብሎም ይገመታል ! ! !
Channel name was changed to «World Fun Facts😱😱»
ሚስጥራዊው የኮካ-ኮላ ፎርሙላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዶ/ር ጆን ፔንበርተን የተባለ አሜሪካዊ ፋርማሲስት አማካኝነት በአሜሪካ አትላንታ ጆርጂያ ግዛት ውስጥ በ1886 ዓ.ም ተሰራ ፡፡ ጆን ስሚዝ ፔንበርተን በ1856 አሜሪካ እርስ በርስ ጦርነት ላየይ ጉዳት ስለደረሰበት ህመሙን ለማስታገስ ሞርፊን የተባለ አደንዛዥ መድሃኒት ለመጠቀም ተገዶ ነበር ፡፡ በመጨረሻም የዚህ መድሃኒት ሱሰኛ በመሆን በበለጠ አደጋ ላይ ወደቀ ፡፡ በሙያው ፋርማሲስት ነበርና ካጋጠመው የመድሃኒት ሱስ ለመላቀቅ የሚያስችሉትን መድሃኒቶችን ለማግኘት ከፍተኛ ምርምር ሲያካሄድ #ኮካዋ እና #ኮላዋይን የተባሉ እፅዋቶችን በማደባለቅ #ፔንበርተን_ፈሬንች_ዋይን_ኮላ የተባለ ፈሳሽ ፈጠረ ፡፡ ለሃንግ ኦቨር እና ለራስ ምታት ፈዋሽ መድሃኒት እንደሆነም ተገነዘበ ፡፡ ቀስ በቀስ ግኝቱን በማሻሻል ባደረገው ጥረት በአለማችን ቁጥር አንድ የተባለውን የለስላሳ መጠጥ ሰራ ፡፡ ለራሱ መድሃኒትን ፍለጋ የያደረገው ጥረት ከራሱ አልፎ የሰው ልጆችን የሚያዝናና መጠጥ ሆኖ ተገኘ ፡፡ በ1886 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በገበያ ላይ ሲውል በመጀመሪያው አመት የተሸጠው 50 ዶላር ብቻ ነበር ፡፡ ይሄን የ50 ዶላር ገቢ ለማግኘት ሲል ለማስታወቂያ ብቻ ያወጣው 70 ዶላር በመሆኑ ፔንበርተን በመጀመሪያው አመት የ20 ዶላር ክስረት አጋጠመው ፡፡ ይሄም በመሆኑ ዶነን ፔንበርተን በአመቱ የዚህን ድንቅ ግኝቱን ሚስጥራዊ ቀመር ወይን ፎርሙላ #_አሣ_ግሪግስ_ካንድለር ለተባለ ባለሃብት አሳልፎ ሸጠ ፡፡ የተሸጠበትም ዋጋ 2360 ዶላር ብቻ ነበር !!

ሻጩ የፈጠራው ባለቤት ከገቢው ተጠቃሚ አነበረም ማለት ነው ፡፡ ገዢው #ካንድለር ግን በጥቂት ንዋየይ በገዛው ፎርሙላ ታዋቂ የኮካ-ኮላ አምራት ካምፓኒ በመፍጠር የአለምን ገበያ ከመቆጣጠሩም አልፎ ከዚህ ባገኘው ትርፍ የግል ባንኮችን በመክፈት ፣ የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶችን በማቋቋም ፣ ሌሎች ታላላቅ ካምፓኒዎችን በመመስረት በመላው አለም እጅግ በጣም የታወቀ ቱጃር ለመሆን ቻለ ፡፡

ፎርሙላውን የሸጠው ፋርመማሲስቱ እድለ ቢሱ ጆኀን ቤንበርተን ግን 2360 ዶላሩን በተቀበለ በአመቱ ከዚህች አለም በሞት ተለየ ፡፡ እድለኛው ካንድለር ካዝናው በገንዘብ ብዛተት ከመጨናነቁ የተነሳ ፊቱን ወደ እርዳታ ልገሳ በማዞር በሚልየኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለዩኒቨርስቲዎች እና ለሆስፒታሎች በመለገስ በበጎ አድራጎት ተግባር ስሙን በሰፊው አስጠራ ፡፡ በአነስተኛ ዋጋ የተገዛው ይህ ፎርሙላ ስፍር ቁጥር የሌለው ሀብት ሊያመጣ ቻለ ፡፡ ካንድለር በ1917 ዓ.ም የራሱን አብዛኛውን ድርሻ ለልጆቹ ቢያወርስም ልጆቹ ግን በ1919 ዓ.ም #አርነስት_ውድሮፍ ለተባለ ባለሀብት እነና ለንግድ ሸርኮቹ ሸጡት ፡፡ ውድሮፍ ሌሎች ባለአክስዮኖች ጋር በመሆን ፎር ሙላውን ከገዛ ቡሃላ እነርሱም በተራቸው የናጠጠ ባለ ፀጋ ሆነዋል

የኮካ-ኮላ ፎርሙላ በሚስጥር የተቀመጠው ሰን ትረስት ባንክ በተባለ የአሜሪካ ታዋቂ ካዝና ውስጥ ነው ፡፡ ባለቤቶቹ ፎርሙላውን ለልጅ ለልጆቻቸው በማውረስ አሁን #አራተኛው_ትውልድ ላየይ ደርሷል ፡፡ በአንድ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የዚህን ፎርሙላ ሚስጥር የሚያውቁት #ሁለት_ሰዎች ብቻ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሰዎች በማንኛውም መልኩ በስልክም በአካልም እንዳይገናኙ ከፍተኛ ጥበቃ እና ክትትል ይደረግባቸዋል ፡፡ ሁለቱ ደግሞ የሚያውቁት እያንዳንዳቸው ግማሹን ፎርሙላ ብቻ ነው ፡፡ ሁለቱ የሚያውቁት ግማሽ ፎርሙለላ ሲዋሃድ ሙሉ ፎርሙላ ይሆናል ፡፡ ሰን ትረስት የተባለው ባንክ ይህንን ሚስጥር በጥብቅ ታማኝነት በመጠበቅ ብቻ ከኮካ-ኮላ ሽያጭ ትርፍ ላይ በዓመት 3.56 ፐርሰንት የክብር ክፍያ ያገኛል ።
👉 በማዳጋስካር አቋራጭ የብልጽግና መንገድ የሚባለው ሙስና ሳይሀሆን አውራ ዶሮዎችን ለዶሮ ፍልሚያ (Cock fight) አሰልጥኖ ለውድድር ማብቃትና ዶሮዎቹን ማፋለም ነው ! ! በዚ ውድድር የዶሮ ባሉካዎች በጣም ተጠቃሚዎች ናቸው!!!
​​👉 ከአዕዋፋት ሁሉ በጣም ሰነፍ የምትባለዋ "ካው በርድ" ☝️☝️ናት ፡፡ ይቺ የወፍ ዝርያ ስራ ከመጥላትዋ የተነሳ የጣለችውን እንቁላልን እንኳን ታቅፋ ማስፈልፈል አትፈልግም ፡፡ ካው በርዶች የራሳቸውን ጎጆ መስራት አይወዱም ፡፡ ጫጩቶቻቸውንም አያሳድጉም ወይም አይንከባከቡም ፡፡ ሴቷ ካው በርድ እንቁላል ከጣለች ቡሃላ አሳቻ ሰአት ጠብቃ የሌላ ዝርያ ያላት አዕዋፍ ጎጆ በመሄድ የራሷን እንቁላል ታስቀምጥና የዚያችኛዋን ወፈእንቁላል ትሰርቃታለች ፡፡ የተታለለችዋ ወፍ የአታላዯን እንቁላል ታቅፋ ታስፈለፍልና መብረር እስኪችሉ ድረስ ይንከባከቧቸዋል ፡፡ እስከ 144 የወፍ ዝርያዎች ባለማወቅ የካው በርድን እንቁላል በጉዲፈቻነት ታቅፈው ያስፈለፍላሉ ፡፡ የሚገርመው ግን ጫጩቶቹ ከተፈተፈሉ ቡሃላ ወደ ቤተሰቦቻቸው ካው በርዶች አውቀዋቸው ይመለሳሉ ! ! !
👉 ስቴፈን ኪንግ አለማችን ላይ እጅግ አስፈሪ ሆረር ፊልሞችን በመፃፍ ታዋቂ ነው ይህ ደራሲ ስለራሱ ሲናገር ማታ መብራት ካልበራ በተአምር እንቅልፍ መተኛት አይችልም ! !
👉 በኢትዮጵያ በ1947 ዓ.ም ላይ ት/ቤት ውስጥ የጥጥ መፍተል ራሱን የቻለ ትምህርት ይሰጥ ነበር የሚገርመው ተማሪዎች ጥጥ በሚፈትሉበት ጊዜ እናቶች ወደ ትምህርት ቤት ሄደው ነበር ተማሪዎችን እንደ መምህር ሆነው ሚያስተምሯቸው የነበረው !