የሐምዛ ዲናዊ ምክሮች{وصايا حمزة}
532 subscribers
68 photos
17 videos
1 file
69 links
ይህ ቻናል የሀምዛ 【أسد الله】ዲናዊ ምክሮች ብቻ ናቸው የሚለቀቁበት ተከታተሉት።

@Habshey
@Habshey


ማንኛውም ሀሳብና አስተያየት ካለዎት ያድርሱኝ።
Download Telegram
#የኔ ምክሮች

معنى " اللهمَّ صَلِّ على مُحَمَّد " : اللهُمَّ زِدْ مُحَمَّداً شَرَفاً وَتَعظيماً

🪀አሏሁመሶሊ ዓላ ሙሀመድ ብሎ ማለት 【ሶሊ】ማለት ትርጉሙ አሏህን እየለመንነው ነው ትርጉሙም፦【አሏህ ሆይ ለሰይዳችን ሙሀመድ በልቅና ላይ ልቅናን በደረጃ ላይ ደረጃን ጨምርላቸው ማለት ነው】አሚን
🤲

https://t.me/hamzaasedullah
9
#የኔ ምክሮች

الناس اذا دخلوا الجنة يكونون على صورة سيدنا يوسف عليه السلام ، أما سيدنا محمد صلى الله عليه وسلم فيكون أجمل.


🪀ሰዎች ጀነት ሲገቡ ሁሉም በዩሱፍ ዓለይሂ ሰላም መልክ (ውበት)ሆነው ነው ሚገቡት ነገር ግን ሰይዳችን ሙሀመድ ሷለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እጅጉን ውብ ነው ሚሆኑት።


ለሰዎች ሊንኩን ሼር አድርጉ ውዶች

https://t.me/hamzaasedullah
7
#የኔ ምክሮች

الـإسـراء والـمـعـراج السابع

ኢስራእ_እና_ሚዕራጅ ሰባት


#ነብዩ_ሙሐመድ_ﷺ በሚዕራጅ ካዩዋቸው #አስገራሚ ነገራት መካከል የተወሰኑትን እንመልከት፦

#በይተል_መእሙር:-ይህ የተቀደሰ ቤት
ሲሆን ለሰው ልጆች ካእባ እንደምንለው ሁሉ
ለመላኢካዎች እንደዛው የተቀደሰ ቦታ ነው።

#ጀነት:ከሰባት ሰማያት በላይ ስትሆን
#ነብዩ_ሙሐመድ_ﷺ እንዲህ
ብለዋል“ጀነትን ተመለከትኩኝ ፣አብዛኛው
ባለቤቶቿ ድሆች ሆነው
አገኝቻቸዋለሁ” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ዘግበውታል::አሏህ ከጀነት ሰዎች ያድርገን
አሚን
#ሑረልዒን:-ረሱል ጀነት ውስጥ ሑረልዒኖችን
አይተዋል ጂብሪልም ለነዚህ ሰላምታ
እንዲያቀርቡላቸው አዝዟቸው እነሱም
አሉ“እኛ መልካምና ቆንጆ የሆንን አሏህ
ላከበራቸው
#ሚስቶች ነን”።

#ሰይዱና_ጅብሪልን በትክክለኛ
አፈጣጠራቸው ተመልክተዋል።

#ነቢያችን_ﷺ ለመጀመሪያ ጊዜ ጂብሪልን በትክክለኛ አፈጣጠራቸው የተመለከቷቸው #በመካ_አጅያድ በምትባል ቦታ ሲሆን በተመለከቷቸውም ጊዜ ራሳቸውን ስተው ነበር::በዚህ በተባረከች ሌሊት #ለሁለተኛ ጊዜ በትትክክለኛ አፈጣጠራቸው በተመለከቷቸው ሰዐት ግን እራሳቸውን ስተው #አልወደቁም ነበር።ይህም ጥንካሬና ችሎታ ስለተጎናጸፉ ነበር። #ከዛስ_ምን_ተከሰተ.....

🪀የሚለውን በቀጣይ ክፍል እናየዋለን ሼር አድርጉት

https://t.me/hamzaasedullah
4👍2
#የኔ ምክሮች

قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ :
«بلِّغوا عنِّي ولو آيةً»
رواه البخاري.

🪀የአሏህ መልክተኛ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–

«ከእኔ የሰማችሁትን አንዲትም አያት(አንቀፅ) ብትሆን አድርሱ(አስተላልፉ» አሉ። ቡኻሪ ዘግበውታል



https://t.me/hamzaasedullah
6
#ከአዕምሮዪ የማይጠፉ አባባሎች

قال أحدٌ لصاحبِهِ؛ صفْ لي نعيم الجنة
قال فيها رسولُ الله.

🪀አንዱ ለጓደኛው እንዲህ አለው እስቲ የጀነትን ፀጋ ግለፅልኝ አለው እርሱም አለው፦【እርሷ ውስጥ የአሏህ መልዕክተኛ አሉ።


https://t.me/hamzaasedullah
5
#የኔ ምክሮች


َحْرُمُ_هَجْرُ_الْمُسْلِمِ أَخَاهُ الْمُسْلِم فَوْقَ ثَلاَثٍ إِنْ كَانَ الْهَجْرُ بِغَيْرِ عُذْرٍ شَرْعِيٍّ، قَالَ رَسُولُ اللـهِ صَلَّى اللـهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: “لاَ يَحِلُّ لِمُسْلِمٍ أَنْ يَهْجُرَ أَخَاهُ فَوْقَ ثَلاَثِ لَيَالٍ يَلْتَقِيَانِ فَيُعْرِضُ هَذَا وَيُعْرِضُ هَذَا، وَخَيْرُهُمَا الَّذِي يَبْدَأُ بِالسَّلاَمِ” رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ.

#ሙስሊም የሆነን ሰው ያለምንም ሸሪዓዊ ምክኒያት ከ3 ቀን በላይ ማኩረፍ ሀራም ነው አይፈቀድም።
ነቢያችን ዐለይሂ ሷላቱ ወሰላም ምን አሉ «ለአንድ ሙስሊም ሙስሊም የሆነን ወንድሙን ከ3ቀን በላይ ማኩረፍ አይፈቀድለትም፣ይገናኛሉ ያ ወደዛ ይዞራል(ይተወዋል) ይሄም ወደዛ ይዞራል(ይተወዋል)፣ ነገር ግን ከሁለቱ ሰዎች በላጩ ሰላምታን ቀድሞ የሚለው ነው» አሉ ቡኻሪ ዘግበውታል።



https://t.me/hamzaasedullah
5
👉#ጠቃሚ ነጥቦቼ

#البراق بعدما ركبه الرسول عاد إلى الجنة، الرسول ركب البراق في ذهابه من مكة إلى المسجد الأقصى، أما في الرجوع رجع بطريق خرق العادة بدون البراق

#ቡራቅ ነብዩ ከጋለቡት ቡሀሏ ወደ ጀነት ተመልሷል የአሏህ መልዕክተኛ ቡራቅን ከመካህ ወደ መስጂደል አቅሷ ሲጓዙ ጋልበውታል።ነገር ግን ሲመለሱ ያለ ቡራቅ ተለምዶን በተቃረነ መልኩ ደርሰዋል

https://t.me/hamzaasedullah
ሊንኩን ለጓደኞቻችሁ በየግሩፑ ሼር አድርጉት።

ከወደዱት የውዴታ ምልክቱን ይጫኑት።
👇👇👇👇
6
#የኔ ምክሮች


فــــــــائـــــــدة
قال البغوي
‏"رُويَ أنّ موسى -عليه السلام- لمّا أراد أن يفارقه الخضر -عليه السلام- قال له: أوصني.
‏قال له: يا موسى، لا تطلبِ العلمَ لتحدِّث به، واطلبه لتعملَ به.

በገውይ አሉ፦

ከሰይዱና ሙሳ እንደተዘገበው ከኽዲር ዐለይሂ አሰላም ጋር መለየት በፈለጉ ግዜ ምከረኝ አሉት ፡

ሰይዱና ኽዲርም አሉ ሙሳ ሆይ፦

【እውቀትን ለመናገር አትፈልገው

【ይልቅንስ ልትሰራበት ዘንዳ ፈልገው
6👎1
#የኔ ምክሮች

قال أحمد المرزوقي رحمه الله :" وكل ما أتى به الرسولُ فحقُهُ التسليمُ والقبولُ "،

ታላቂ ዐሊም አህመዱል መርዙቅይ ይህን አሉ፦【ረሱል ይዘውት በመጡበት ነገር ሁሉ ሀቁ እጅ ሰጥቶ መቀበል ነው】

ተቃውሞን አይሻም ሰይዲ የመጡበት እምነት


https://t.me/hamzaasedullah
🥰4🔥1
#የኔ ምክሮች


قال عبد القادر الجيلاني : «إياكم أن تحبوا أحدا أو تبغضوه إلا بعد عرض أفعاله على الكتاب والسنة. حتى لاتحبوه بالهوى وتبغضوه بالهوى واعلموا أنه لايجوز لكم هجر أحد على الظن والتهمة»
-----
#ታላቁ ወልይ ሸይኽ_አብዱል-ቃዽር አልጂይላንይ እንድህ ይላሉ፦
«አደራችሁን!!! አንድን ሰው ልትወዱትም ሆነ ልጠሉት የሚገባው በሸሪዓ ሚዛን ላይ ስራውን ካቀረባችሁት በኃላ መሆን አለበት፤ በስሜት ተነሳስተህ እንዳትወዳቸውና አንዳጠላቸው።
#እወቅ አንድንም ሰው በጥርጣሬ ልትኮረፍው አይበቃልህም።»
*-*-*-*-*-*

•ሰዎችን ዝም ብለን በስሜት ተገፋፍተን ልንጠላቸው ወይም ልንወዳቸው አይገባም ይልቁንስ የኛ ዋናው መስፈርት የሚሆነው ከሐቅ ጐን ለቆመና ሀቅን ለተከተለ መሆን አለበት።

°【ሰው ተከታይ ሳይሆን ሀቅን ተከታይ መሆን ነው ያለብን】
5
#የኔ ምክሮች

#قال الحسَنُ البِصريُّ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ: "الفَهمُ وِعاءُ العِلمِ، والعِلمُ دلِيلُ العمَلِ، والعمَلُ قائدُ الخَيرِ، والهوَى مَركِبُ المَعاصِي، والمَالُ داءُ المُتكبِّرين، والدُّنيا سُوقُ الآخِرةِ، والوَيلُ كُلُّ الوَيلِ لِمَنَ قَوِيَ بنِعَمِ اللهِ على مَعاصِيهِ

ታላቁ ታብዕይና ሱፊይ የሆኑት ሀሰኑል ቢስርይ እንዲህ አሉ፦መረዳት የእውቀት እቃ ነው¹እውቀት የስራ ማስረጃ ነው² ስራ የመልካም ነገር መሪ ነው³የአእምሮ ግምት ወደ ወንጀል ጋላቢ ነው⁴ገንዘብ የኩራተኞች መድሀኒት ናት⁵ ዱንያ የአኺራ ሱቅ ናት⁶ ወየሁለት ለእርሱ አሉ ንግግራቸውን ሲያጠናቅቁ ከአሏህ ፀጋ ይልቅ በእርሱ ላይ በመወንጀል ለበረታ አሉ⁷።
رضي الله عنه

#¹ማለትም መረዳት ሚባለው ነገር ለእውቀት በእቃ መልኩ መገለፁ መረዳት የሚባለው ነገር ለእውቀት ትልቅ መሳርያ መሆኑን እንረዳለን ማለትም ያለ መረዳት እውቀት ለተለያዩ አዘቅት ውስጥ ለመግባት ምክንያት ስለሚሆነን ማለት ነው።
#²እንዲሁ የሰውዪው አዋቂነት የስራ ሰው እንደሆነ አመላካች የሆነ ይሆናል ማለት ነው ምክንያቱም ሰዎች እውቀትን በጨመሩ ቁጥር ማንነታቸውን የሚያልቅ ምልክት ስለሚሆናቸው።
#³ማለትም በመልካም እውቀት የሰራው ስራ መልካም ነውና መልካም ሰራው ለጥሩ ነገሮች የመሪነትን ሚና ይጫወትለታል ማለት ነው።
#⁴ሰዎች እንዲሁ ያለ እውቀት በመጣላቸው ነገር ሚናገሩና ምላሳቸውን ሚሰነዝሩ ከሆነ ወደ ወንጀል ለመሄድ ፈጣን አድራሻቸው ይሆናል።
#⁵እንዲሁ ገንዘብ ደሞ ኩራት ያለባቸው ሰዎች መድሀኒት ናት ነብዩ عليه الصلاة والسلام እንዳሉት የኔ ኡመት ፈተናዎች ገንዘብና ሴቶች ናቸው እንዳሉት ነው እንዳንድ አዋቂዎችም እንዲህ ብለዋል ገንዘብ ያሳብዳል ብለዋል።
#⁶ዱንያ ደሞ ለአኺራ ተስራርተንባትና አምርተንባት የምናልፍባት ሀገር ናት ልክ እንደ ግብይት ስፍራ።
#⁷በመጨረሻ የማስጠንቀቅያ መልእክታቸውን ሰነዘሩ ወየሁለት አሉ አሏህ በሰጠው ፀጋዎች እርሱን በመታዘዝ መጠንከርን በመተው አሏህን በመወንጀል የሚጠነክር ሰው የአሏህን ቅጣት ይፍራ እንዳሉ ነው።
3
#የኔ ምክሮች

عن أبي هريرة قال الرسول صلى الله عليه وسلم؛الرّجل على دين خليله فلينظر أحدكم من يخالل. حديث حسن


📥ከአቡ ሁረይራ አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ብለው አወጉ፦

📌"
#የሰው ልጅ ባህሪው¹ ሚቀዳው ከ ጓደኛው ነው ከመካከል አንዳችሁ ይመልከት² ጓደኛ ማንን አድርጎ መያዝ እንዳለበት³"።

¹ ባህሪው ብቻ ሳይሆን በነገሮች ላይ የሚጓዝበት መንገዱ …

² ማለትም ያስተንትን ያስተውል ።

³ ጓደኛ አርጎ የሚይዘው ሰው በባህሪው መልካም ሚባልና በሸሪዐ የተወደደለት ከሆነ ጓደኛ አርጎ ይያዘው ካልሆነ ግን ይጠነቀቀዋል።
4
#የኔ ምክሮች

ባለ አንድዮ ምላስ፣ ባለ ሁለት ጆሮ
ሆነህ መፈጠርህ
ጥቂት እንዲሆን ነው የምላሱ ግብርህ

እውነትን እንጂ ውሸትን በማያወሩት፣ ከወሕይ እንጂ ከረእይ (ከግምት) በማይናገሩት ትልቁ ሰው አንደበት እንደተላለፈልን
أكثر خطايا ابن آدم من لسانه
«የአደም ልጅ ብዙ ስሑቱ (ስህተትም ወንጀሉ) ከምላሱ ነው።»

አንዱ ጠቢብ ንግግርን ሲያበዛ ወዳስተዋሉት ወጣት ቀረብ ብለው እንዲህ አሉት

"إن الله تعالى إنما خلق لك أذنين ولسانا واحداً، ليكون ما تسمعه ضعف ما تتكلم به"

«አሏህ ሁለት ጆሮዎችንና አንድ ምላስን የፈጠረልህ የምትሰማው ከምትናገረው በላይ እጥፍ ሊሆን ዘንድ ነው»

ጠቢቡ በጠቢብ ሾሬ «ንግግርህን ቆጥብ፣ አሳንስ
ብዙ አድማጭ እንጂ ብዙ ተናጋሪ አትሁን» እያሉት ነው።

ከተናገርን ስለ ጠቃሚነቱ ተጨንቀን ይሁን፣ አሊያ ግን «
#ዝም ያለ ነፃ ወጣ» ነውና ሐዲሱ ዝም እንበል።
3
#የኔ ምክሮች

الـإسـراء والـمـعـراج الثامن

ኢስራእ_እና_ሚዕራጅ ስምንት

በደንብ ልናውቅ የሚገባው
#ነብዩ_ሙሐመድ_ﷺ ወደ ሰባቱ ሰማያት ያደረጉት ጉዞ በጭራሽ እንዲህ የሚልን “የአሏህን መኖር ወደ ሚጠናቀቅበት ቦታ መድረስን ነው”የሚልን #በጭራሽ አልተፈለገበትም። ይልቁንስ እንዲህ ብሎ ያመነ ሰው የካዳ [የከፈር] ይሆናል የነብዩ ﷺ የጉዞው አላማም ይህ አልነበረምና።

#የጉዞው_አላማ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ የላይኛውን ዓለም ተዓምራት በማሳየት ለማላቅ [ ለማክበር]ነው።

#ነብዩ_ሙሐመድ_ﷺ ጅብሪልን ለሁለተኛ ግዜ በትክክለኛ አፈጣጠሩ በሲደረተል ሙንታሀ አይተውታል በዚህ ሰዐትም ነቢዩ ﷺ እራሳቸውን አልሳቱም ነበር።በቁርአንም እንደተገለጸው

قال تعالى؛[ولقد رءاه نزلة أخرى عند سدرة المنتهى]

#ትርጉሙ “በእርግጥ ተመለከተው ለሁለተኛ ጊዜ ሲድረቱል ሙንተሀ ዘንድ”(የነጅም ምዕራፍ 14)::

ስለዚህ👆የቁርአን አንቀፅ
#ሰይዲቲ_ዓኢሻ እንዲህ አሉ“ ከዚች ኡማ ስለዚህ አንቀጽ ማለትም (ከማንጋ እንደተገናኙ) የመጀመሪያዋ ጠያቂ እኔ ነኝ #ነቢዩም " ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ነው። " ብለው መለሱልኝ አለች ። [ ሙስሊም] ዘግበውታል።

መላኢካው ጂብሪል
#ለነቢዩ_ﷺካለው ፍቅር እና ናፍቆት እንዲሁም ደስታ ወደ ነቢዩ ﷺ ተጠጋ። በመካከላቸውም #ሁለት_ክንድ ወይንም ከዛም ያነሰ በሆነ እርቀት ቀርባቸው::

እዚህ ላይ እንደዚህ ብሎ “አሏህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ከነቢያችን ጋር ተቀራረበ”ብሎ ማመን ጨርሶ የማይፈቀድ ሲሆን የተጥራራው ጌታችን እንዳለው፦

قال تعالى؛ ثم دنا فتدلى ﻓﻜﺎﻥ ﻗﺎﺏ ﻗﻮﺳﻴﻦ ﺃﻭ ﺃﺩﻧﻰ ” صدق الله العظيم


በዚህ የቁርአን አንቀጽ ላይ የተጠቀሰው «የሁለት ክንድ ወይንም ከዛ ባነስ እርቀት ተቀራረቡ» የሚለው የተፈለገበት
#ጂብሪል ዐለይሂ ሰላምን ነው ።

እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች
#እንደሚዋሹት አይደለም እንዲህ ይላሉ«አሏህ በዛቱ ከሙሐመድ ጋር ተቀራረበ በመካከላቸውም ያለው እርቀት በሁለት ቅንድቦች መካከል እንዳለው እርቀት ሆነ ወይም ሁለት ክንድ ሆነ» ይላሉ ይህ አሏህን ከፍጥረታት ጋር ማመሳሰል ነው::እንዲሁም ለአሏህ ቦታን ማስጠጋት ነው ምክንያቱም እርቀትን ማስጠጋት ያው ቦታን ማስጠጋት ስለሆነ።አሏህ ደግሞ ያለ ቦታ ያለ ነው::

ይቀጥላል

https://t.me/hamzaasedullah
2👎1
@Habshey
@Habshey
👆👆👆👆

ላለዎት ማንኛውም ሀሳብና አስተያየት፣ምክር እቀበላለው ውዶቼ።

ሊንኩን ለ10 ሰው በመላክ እናሳድገው።
#የኔ ምክሮች


الهوى يدعو إلى اللذة الحاضرة من غير فكر في عاقبة ويحث على نيل الشهوات عاجلا وإن كانت سببا للألم والأذى في العاجل فأما العاقل فإنه ينهى نفسه عن لذة تعقب ألما وشهوة تورث ندما.


#ስሜት ያለ ምንም ስለ ዘውታሪ ነገር ያለማሰብ ወደ ግዜያዊ ፍላጎት ይጣራል በፍጥነት ወደ ግዜያው ስሜቶችን ወደ ማግኘት ይገፋፋል ይህች ስሜት ለህመም እንዲሁ ለመቸገር የፍጥነት ምክነያት ናት። ነገር ግን ጤነኛ ሰው እርሱ ነው ነፍሱን ከዘውታሪ የስሜት ህመም የሚጠብቅ …

ስሜት ፀፀትን ታወርሳለች ።
👍3
#የኔ ምክሮች

#ኢማሙ_አቡ_ጀዕፈር አጧሐዊይ የአህለሱና ወልጀማዓ እምነትን በሚጠቅሱባት ኪታብ እንድህ አሉ፦

"تَعالى عَنِ الْحُدُودِ وَالْغَاياتِ والأَرْكَانِ والأعْضَاءِ والأَدَواتِ لا تَحْويِهِ الْجِهَاتُ السِّتُّ كَسَائِرِ الْمُبْتَدَعَاتِ".
«አሏሕ ከመጠን፣ ከመጨረሻ፣ ከማዐዘናት፣ ከትላልቅ የሰውነት ክፍሎችና ከትናንሽ የሰውነት ክፍሎች የተጥራራ ነው። በስድስቱም አቅጣጫ እንደፍጡራን አይገለፅም።»

•ሁዱድ ማለት መጠነቁስ ሲሆን አሏሕ መጠነቁስን ፈጣሪ እንጅ እርሱ (አሏሕ) መጠነቁስ አይደለም።

•መህዱድ (መጠነቁስ) ደግሞ በሸሪዐና በቋንቋ ሊቃውንቶች ዘንድ ማንኛውም መጠን ያለው ነገር ትንሽም ይሁን ትልቅ መህዱድ ይባላል።

•ጛያት ማለት መጨረሻ ሲሆን እርሱም የፍጡር ባህሪ ነው።

•አርካን ማለት ጐን ማለት ሲሆን እሱም የፍጡር መገለጫ ነው።

•አእዷዕ ማለት ትላልቅ የሰውነት ክፍሎች እንደ እጅ፣ እግርና ፊትን ይመስል።

•አድዋት ማለት ትናንሽ የሰውነት ክፍሎች እንደ አይን፣ ምላስ እና ድድ ይመስል

وقَوْلِهِ "لا تَحْويهِ الْجِهَاتُ السِّتُّ":
°ትርጉሙ፦አሏሕ ያለ ቦታ ያለ አቅጣጫ ያለ ነው ማለት ነው።

°አቅጣጫዎች ስድስት ሲሆኑ እነሱም ላይ፣ ታች፣ ቀኝ፣ እግራ፣ ፊት፣ ኃላ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ አሏሕ በአንዱም አይገለፅም በታች ነው እንደማይባለው ሁሉ በላይ ነው አይባልም።


https://t.me/hamzaasedullah
5
#የኔ ምክሮች

📌 አሏሕ በአካሎች ከመገለፅ የተጥራራ ጌታ ነው አሏሕን በአካል መግለፅ ከፍጡራን ጋር ማመሳሰል ነው! ይህ ደግሞ ጥርጥር የሌለበት ክህደት ነው!!

📌 ኢማሙ ዓልይ ረድየሏሁ ዓንሁ እንዳሉት፦
قال الإِمام علي رضي الله عنه "من زعم ان الهنا محدود فقد جهل الخالق المعبود"رواه ابو نعيم في حلية اَلأَولياء

“ጌታችን መጠን (ማለትም አካል) ነዉ ብሎ የሚያምን ሰዉ ካለ ይህ በርግጥ ጃሂል ነዉ የሚገዛዉን ጌታ አላወቀም።”

© አቡ ኑዓይም አል’ስባሀንይ ከኑዕማን ብኑ ሰኢድ ይዘው ሒሊየቱ-ል-አውሊያእ ላይ ዘግበውታል።


https://t.me/hamzaasedullah
👍32
#የኔ ምክሮች

📌 ኢብኑ ሙዐሊሙ’ል’ቁረይሽ ነጅሙል ሙህተድ ወረጅሙል ሙዕተድ 588 ገፅ ላይ እንደጠቀሱት፦

{عن عَليّ رضيَ اللهُ عنهُ قَالَ:
سَيَرجِعُ قَومٌ مِنْ هَذِهِ الأُمّةِ عِندَ اقتِرَابِ السّاعَةِ كُفّارًا.
📌 ሰይዱና ዐልይ አሁንም እንድዚህ አሉ፦
«ከዚች ኡማ የውመል ቂያማ ሲቀርብ ሰዎች ወደ ክህደት ይገባሉ።»
قَالَ رَجُلٌ: يَا أَمِيرَ المؤمنينَ كُفرُهُم بماذَا أَبِالإحْدَاثِ أَم بِالإنْكَارِ؟
•በዚህን ጊዜ አንድ ሰው « አንቱ የመዕመናን አዛዥ ሆይ!!! ክህደታቸው በምንድ ነው? አድስ በመፍጠር ነው ወይስ ያለውን በመካድ ነው?»
فَقالَ: "بل بالإنكَارِ يُنْكِرُونَ خَالِقَهُم فيَصِفُونَه بالجِسمِ والأَعضَاء".
«በመካድ ነው። ፈጣሪያቸውን ክደው በአካል እና በክፍለ አካል ይገልፁታል።»


አሏህ ይጠብቀንና።


https://t.me/hamzaasedullah
3
#የኔ ምክሮች

قال إمام أبو حنيفة في كتاب الفقه الأكبر؛

روية الله في الاخرة
وكان الله تعالى خالقا قبل ان يخلق ورازقا قبل ان يرزق والله تعالى يرى في الآخرة ويراه المؤمنون وهم في الجنة بأعين رؤوسهم بلا تشبيه ولا كيفية ولا يكون بينه وبين خلقه مسافة

ታላቁ ኢማም አቡሀኒፋህ በፊቅሁል አክበር ላይ እንዲህ አሉ፦

አሏህን በአኺራ ስለማየት፦

👉አሏሁ ተዕላ ፍጡርን ሳይፈጥር በፊት በፈጣሪነት ይገለፅ ነበር እንዲሁ ሲሳይን ሳይለግስ በለጋሽነት ይገለፅ ነበር አሏሁ ተዕላ በመጨረሻው ዓለም ይታያል አማኞች ያዩታል እነርሱ በጀነት ውስጥ ሆነው በአናታቸው ላይ ባለው አይን አሏህን ያለ ማመሳሰል ያለ እንዴታ እንዲሁ በእነርሱና በአሏህ መካከል የቦታ እርቀት ሳይኖር አሏህን ያዩታል አሉ።

ምክነያቱም አሏህ በቦታ ስለማይገለፅ።


https://t.me/hamzaasedullah