የሐምዛ ዲናዊ ምክሮች{وصايا حمزة}
532 subscribers
68 photos
17 videos
1 file
69 links
ይህ ቻናል የሀምዛ 【أسد الله】ዲናዊ ምክሮች ብቻ ናቸው የሚለቀቁበት ተከታተሉት።

@Habshey
@Habshey


ማንኛውም ሀሳብና አስተያየት ካለዎት ያድርሱኝ።
Download Telegram
🪀ውዶቼ ረመዷንን ልንዘልቀው በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ቀርተውታል።

🪀ሀምዛ ነኝ ሰው ነኝ ያውም በዳይ ባርያ ከኔ ስህተት አለመጠበቅ ሞኝነት ነው ሰው ነኝና እሳሳታለው ውዶች ግን አንድ ነገር አውቃለው እናንተ ከኔ የተሻላችሁ እንደሆናችሁ ይቅር በሉኝና በሰላም ሸህሩል ሙባረክ ረመዷንን እንቀበለው ።

👉በተፈጥሮዪ ስህተት ካለ ዱዓ አድርጉልኝ በእናንተ ምክር ሰበብ የሚስተካከል ከሆነ ደግሞ ምከሩኝ የተሻለው ባርያ ከስህተቱ የተመለሰ ነውና።

شهر صفاء الروح
🥰6👍1
#የኔ ምክሮች


قال أحدٌ من زمرة العلماء؛: الذي تَسَلَّطَ عَلَيْهِ الكَسَلُ إذا توضأ يَخفُ عنهُ ، والذي أعياهُ التعب من السيرِ إذا توضأ يذهبُ عنهُ جُزءٌ من التعبِ أو كُلُّهُ.

ከዑለማዎች ጎራ የሆኑት አንድ ዓሊም እንዲህ አሉ፦

"ስልችት ያደረገበት ሰው ውዱእ ካደረገ ይህ ስልቹነቱ ይቀንስለታል ድካም ያደከመው ሰው ደግሞ በጉዞ ውዱእ ካደረገ ከድካሙ ከፊሉ አልያ ሙልእ ድካሙ ከእርሱ ይሄድለታል
"
7
#የኔ ምክሮች

حسن الخلق

َال رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيهِ وَسَلَّمَ: "اتَّقِ اللَّهَ حَيثُمَا كُنتَ" المعنَى أَنَّ الإنسَانَ حَيثُمَا كَانَ عَلَيهِ أَن يَتَّقِيَ اللَّهَ ...

#ሰይዱና ሙሀመድ ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም እንዲህ አሉ፦"#የትም ብትሆን አሏህ ፍራ"

ማለትም አንድ ሰው የትም ቢሆን አሏህን መፍራት ይገባዋል።
7
#የኔ ምክሮች


#قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: "كلمتان خفيفتان على اللسان، ثقيلتان في الميزان، حبيبتان إلى الرحمٰن: سبحان الله وبحمده سبحان الله العظيم"★ رواه البخاري ومسلم


#ረሱል ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ምን አሉ"ሁለት ቃላት ለምላስ ቀላል፣ሚዛን ላይ ከባድ፣አሏህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ናቸው" እነሱም"ሱብሀነሏህ ወቢሀምዲሂ ሱብሀነሏሂል ዐዚም"★ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበዋል።
5👍4
#የኔ ምክሮች

ባለ አንድዮ ምላስ፣ ባለ ሁለት ጆሮ
ሆነህ መፈጠርህ
ጥቂት እንዲሆን ነው የምላሱ ግብርህ

እውነትን እንጂ ውሸትን በማያወሩት፣ ከወሕይ እንጂ ከረእይ (ከግምት) በማይናገሩት ትልቁ ሰው አንደበት እንደተላለፈልን
أكثر خطايا ابن آدم من لسانه
«የአደም ልጅ ብዙ ስሑቱ (ስህተትም ወንጀሉ) ከምላሱ ነው።»

አንዱ ጠቢብ ንግግርን ሲያበዛ ወዳስተዋሉት ወጣት ቀረብ ብለው እንዲህ አሉት

"إن الله تعالى إنما خلق لك أذنين ولسانا واحداً، ليكون ما تسمعه ضعف ما تتكلم به"

«አሏህ ሁለት ጆሮዎችንና አንድ ምላስን የፈጠረልህ የምትሰማው ከምትናገረው በላይ እጥፍ ሊሆን ዘንድ ነው»

ጠቢቡ በጠቢብ ሾሬ «ንግግርህን ቆጥብ፣ አሳንስ
ብዙ አድማጭ እንጂ ብዙ ተናጋሪ አትሁን» እያሉት ነው።

ከተናገርን ስለ ጠቃሚነቱ ተጨንቀን ይሁን፣ አሊያ ግን «
#ዝም ያለ ነፃ ወጣ» ነውና ሐዲሱ ዝም እንበል
6
#የኔ ምክሮች


روى الإمام مالك في مُوَطئه أَنَّ رَسُولَ اللهِ ﷺ قَالَ: "إِذَا تَوَضَّأَ الْعَبْدُ الْمُؤْمِنُ فَتَمَضْمَضَ خَرَجَتِ الْخَطَايَا مِنْ فِيهِ وَإِذَا اسْتَنْثَرَ خَرَجَتِ الْخَطَايَا مِنْ أَنْفِهِ فَإِذَا غَسَلَ وَجْهَهُ خَرَجَتِ الْخَطَايَا مِنْ وَجْهِهِ حَتَّى تَخْرُجَ مِنْ تَحْتِ أَشْفَارِ عَيْنَيْهِ فَإِذَا غَسَلَ يَدَيْهِ خَرَجَتِ الْخَطَايَا مِنْ يَدَيْهِ حَتَّى تَخْرُجَ مِنْ تَحْتِ أَظْفَارِ يَدَيْهِ فَإِذَا مَسَحَ بِرَأْسِهِ خَرَجَتِ الْخَطَايَا مِنْ رَأْسِهِ حَتَّى تَخْرُجَ مِنْ أُذُنَيْهِ فَإِذَا غَسَلَ رِجْلَيْهِ خَرَجَتِ الْخَطَايَا مِنْ رِجْلَيْهِ حَتَّى تَخْرُجَ مِنْ تَحْتِ أَظْفَارِ رِجْلَيْهِ".

#ኢማሙ ማሊክ በዘገቡት ሀዲስ ላይ ነብያችን ዐለይሂ ሷላቱ ወሰላም እንዲህ ይላሉ፦

«ሙዕሚን የሆነ የአሏህ ባሪያ ዉዱዕ ሲያደርግ አሉ ሲጉመጠመጥ በአፉ የሰራው ሀጢያት ባጠቃላይ ከውሀው ጋር አብሮ ይወገዳል ይጠረግለታል፣ በአፍንጫው ውሀን ሲስብ ደግሞ በአፍንጫው የሰራው እንዲሁም ፊቱን ሲያጥብ በአይኑ የሰራው ሀጢያት ባጠቃላይ አብሮ ይታጠብለታል፣እጁን ሲያጥብ በእጁ የሰራው ወንጀል አብሮ ይታጠብለታል ይሰረዝለታል፣እራሱን ሲያብስ እንደዛው በጆሮው የሰራው ሀጢያት ሳይቀር ይታበስለታል እንዲሁም እግሩን ሲያጥብ በእግሩ የሰራው ሀጢያት ማለትም ትናንሽ ወንጀሉ አብሮ ይታጠብለታል፣ይሰረዝለታል»አሉ
👍52
#የኔ ምክሮች

لله تعالى
التوحيد: ‏إفراد القديم من المُحدث"
•ተውሒድ ማለት፦ጅማሪ የሌለውን ከፍጡር ለይቶ ማወቅ ነው።

والقديم هنا أي الله الذي لا ابتداء له، كان
قبل ‏المكان والزمان،

•ቀድም እዚህ ዘንድ ጅማሪ የሌለው፣ ከቦታና ከዘመናት በፊት የነበረውን አሏሕ ነው።

والمُحدث أي المخلوق وهو كل ما سوى الله تعالى
•ሙህደስ ማለት ፍጥረታት ማለት ነው እሱም ከአሏሕ ውጭ ያሉ ነገራቶች በሙሉ
6
👉እስቲ ውዶቼ እናንተ ደሞ ምከሩኝ ብዪ ወደ እናንተው ጎራ ልበል ዛሬ የእናንተን የግላችሁን ምክር እከጅላለው።

አሏህም እንዳለው፦

አሏህ በሀዲሱል ቁድስይ ላይ እንዲህ አለ አሉ፦

ውዴታዪ ተረጋግጣላቸዋለች እርስ በእርስ ለሚመካከሩ ለሆኑት】

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم قال الله عز وجل ؛【حقت محبتي للمتناصحين فيّ 】


@Habshey
@Habshey
👆👆👆

ምክራችሁን በዚህ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ።
4👍2👏1
#የኔ ምክሮች

وعن ابن عباسٍ رضي الله عنهما، قَالَ: مرَّ رسول الله صلى الله عليه وسلم بِقُبورٍ بالمدِينَةِ فَأقْبَلَ عَلَيْهِمْ بِوَجْهِهِ، فَقَالَ: ((السَّلامُ عَلَيْكُمْ يَا أهْلَ القُبُورِ، يَغْفِرُ اللهُ لَنَا وَلَكُمْ، أنْتُمْ سَلَفُنَا وَنَحنُ بالأثَرِ)). رواه الترمذي، وقال: (حَدِيثٌ حَسَنٌ).
في هذه الحديث: استحباب زيارة القبور والدعاء لأهلها.
👉 ከዓብዱሏህ ኢብን ዓባስ ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መዲና ውሰጥ ካሉ ቀብሮች ስያልፉ ሳለ ወደ መቃብሩ ፊታቸውን በማቀጣጨት እንዲህ አሉ፦【እናንተ የዚህ ቀብር ባልተቤቶች ሆይ የአሏህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ፡አሏህ ለእናንተም ለኛም ይማረን፡ እናንተ ቀዳሚዎች ናችሁ እኛ እንዲሁ ተከታዮቻችሁ ነን አሉ】

ቲርሚዚይ ይህን ሀዲስ ሀሰን(ጥሩ) ነው ብለውታል።

ኢማም አነወውይ ይህንን ሀዲስ አስቀምጠው ከጨረሱ ቡሀላ እንዲህ አሉ፦

ከዚህ ሀዲስ የምንማረው ቀብርን መዘየር እንዲሁ ለሟቾችም ዱዓ ማድረግ የተወደደ እንደሆነ እንማራለን አሉ።
5🎉1
#የኔ ምክሮች

فائدة؛ فقديما كانت الأمة إذا فعلوا شيئا من المعاصي يكتب على بابهم بأنه عصى الله تلك الليلة ولا يستطيع أن يحذفه يا أحبابي والله تعالى رحمنا ولو لا رحمة الله لنا لهلكنا لملئت الأبواب بكتابة الذنوب.

#በበፊት ኡመቶች ዘመን አንድ ሰው በቤቱ ወንጀልን የፈፀመ እንደሆነ በዛች ለሊት የወነጀለ እንደሆነ በቤቱ በር ላይ ወንጀለኛ ተብሎ ይፃፍበት ነበር ያንንም ፁሁፍ መፋቅ አይችልም ነበር ውዶቼ ወሏህ ነው ምላችሁ አሏህ ምሮናል የኛም ሁኔታ እንደነዛ ህዝቦች ቢሆን በወንጀላችን በጠፋን እንዲሁ ወንጀሎቻችን ተፅፈው በሮቻችንን በሞሉት ነበር።
😢5😱1
#የኔ ምክሮች


أَحِبَّ المساكينَ وجالِسْهُم ولا تَنْظُرْ إلى من هوَ فَوْقَكَ وانْظُر إلى من هوَ دُونَك واشكر الله.

#"ምስኪኖችን ውደድ ከነርሱ ጋርም ተቀማመጥ ካንተ በላይ ስላለ ሰው አትመልከት ካንተ በታች ስላለ ሰው ተመልከት አሏህንም አመስግን"
6
#የኔ ምክሮች

#قال مالك بن دينار
"إذا طلبَ العبدُ العلمَ ليعمل به به كسره علمه وإذا طلبه لغير العمل زاده كبرا"
رواه البيهقي

#ማሊክ ኢብን ዲናር የተባሉ ታላቅ ዓሊም እንዲህ አሉ፦"አንድ ባርያ እውቀትን የፈለገው ባወቀው ነገር ሊሰራበት እንደሆነ ይህ ሰው እውቀቱ መተናነስ እና አለመኩራራትን ይጨምርለታል አሉ፤ነገር ግን ይህን እውቀት ላይሰራበት ከሆነ የፈለገው ኩራትን ነው የሚጨምርበት አሉ።

"በይሀቅይ ዘግበውታል"
👍6
#ልዩ ፕሮግራም

👉አሰላሙ ዓለይኩም ውዶቻችን ረመዷን ከ3 ሳምንት ያነሰ ግዜ ቀርቶታል እናም ይቅርታ ማለት የምትፈልጉት አልይ ውዴታዎን አልያም ናፍቆትዎን ለመግለፅ ለምትሹት ወዳጅ ፣ጓደኛ ቤተሰብ ካለ ከታች በምታዩት ሊንክ ላኩልን እኛ በቻናላችን የምንለቀው ይሆናል።

@Habshey
@Habshey
@Habshey
👆👆👆👆
👍5
#ከወንድማችን ሙሀመድ አደም


#ምስጋና

#ዱባይ ለምትኖረው ወድ እህቴ ጦይባ አደም እንድሬ

#እህቴ ለዋልሽልኝ ውለታ አሏህ ጀዛሽን እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈልሽ እያልኩኝ፤በጣም እወድሻለሁ አሏህ አፍያና ጤና ሰጥቶሽ ለመገናኘት ያብቃን ናፍቀሽኛል፤አሏህ ሀሣብሽን አሟልቶልሽ ደስታሽ ደስታየነውና ከደስታሽ መካፈል እፈልጋለሁ።
ረመዷንም የሠላም፣የጤና እንድሁም የኢባዳ ወር አሏህ ያድርግልሽ

#እናቴም ኑሪልኝ እወድሻለሁ መልካም የረመዷን ወር ይሁንልሽ።

#ጆርዳን ላለችው በጣም ለምወዳት ኢማን አህመድ ይመር ኑሪልኝ
መልካም የረመዷን ወር ከአፍያና ከኢባዳ ጋር እመኝልሻለሁ።

#በተጨማሪም ለሙስሊሙ በአጠቃላይ ለወዚር ጀማልና ለኡስታዞች ፣በተለያዩ ቦታ ሁነው ለሚፆሙ እህት ወንድሞች እንኳን አደረሳችሁ
የሠላም የፍቅር የዒባዳና የጤና ረመዷን አሏህ ያድርግልን አሚን።
6
#የኔ ምክሮች

#الدّنيا والأخرة مثل المشرق والمغرب إذا اقتربت من واحدة ابتعدت عن الأخرى

(المشرق) (المغرب)
☝️ ☝️

🤔

انظر أين أنت وإلى أين تريد الذًهاب...........

#ዱንያ እና #አኺራ ልክ እንደ ምስራቅና ምዕራብ ናቸው አሉ ከእነርሱ መካከል ወደ አንዳቸው ስትቃረብ ከአንዳቸው እየራቅክ ትመጣለህ።

ምስራቅ ምዕራብ
☝️ ☝️

👌ተመልከት አንተ የት እንደሆንክ ወደምንስ መሄድ እንደምትፈልግ?
6
#የኔ ምክሮች

(مَنْ عَرَفَ قَدْرَ الآخِرَةِ هَانَ عَلَيْهِ التَّعَبُ)

"የአኺራን ልክ ያወቀ ሰው ድካሙ ከአሁኑ ይጀምራል"


🙏ይሄን ፖስቸር ለሰራህልኝ ወንድሜ ቢላል ባረከሏሁ ፊከ አሏህ ይስጥህ ብያለው ሹክረን።

https://t.me/hamzaasedullah
👍5
#የኔ ምክሮች

🧕
#ያለኝ እውቀት ለምክር ባያበቃኝም ውድ እህቴ ነገር ግን ትንሽ ልበልሽ፦

🙏
#እህቴ ለመጣው ሁሉ ውድ አካልሽን አታሳይ፡

👍
#የመጣው ሁሉ እያየሽ የሚሄድ ቡቲክ ውስጥ የተሰቀለ ልብስ አይደለሽም እና፡ልልሽ የፈለኩት፡

🧕
#እንቁዋ የኢስላም ፈርጥ አንቺ ነሽ ጀግናዬ በሂጃብ የተሰተርሺዋ በክብርሽ የጸናሺው አንቺ ነሽ፡

💃💃
#ምስል ላይ ምታያት ሴት ስለ ሴት ነፃነት ብላ ራቆቷን ሆና ትወጣለች አንቺን ለማሳቀቅ… ሚገርመው ግን ነገ ነገ

🤦‍♀🤦‍♀😭
#በምታያት መልኩ ተደፍራ ወንድ ተጫውቶባት የስነ ልቦና ተጠቂ ሆኖ ታገኛታለሽ አሏህ ይጠብቀን ነገር ግን በቀጣዩም ግዜ ለሴት ነፃነት ይሉና ራቆትን ነፃነት ይሉታል ይወጣሉ ቀጣይኛዋ ትደፈራለች ሁሌም እንደዚ ይቀጥላል…

🧕
#ሁሌ አንድ አይነት ህይወት እንዳትኖሪ ኢስላማዊ የህይወት ዘይቤ ልመጂ ውድ እህቴ…
5
#የኔ ምክሮች

#إذا تحدثنا عن التواضع
فقل سيد المتواضعين محمد

#ስለ መተናነስ ካወራን
ብለህ በል የተናናሾች አለቃ ሙሀመድ ናቸው

#إذا تحدثنا عن الحلم
فقل سيد الحلماء محمد

#ስለ ብልሀት ካወራን
ብለህ በል የብልሆች አለቃ ሙሀመድ ናቸው።

#إذا تحدثنا عن الأمانة
فقل سيد الأمناء محمد

#ስለ ታማኝነት ካወራን
ብለህ በል የታማኞች አለቃ ሙሀመድ ናቸው።

#إذا تحدثنا عن الشجاعة
فقل سيد الشجعان محمد

#ስለ ጀግንነት ካወራን
ብለህ በል የጀግኖች አለቃ ሙሀመድ ናቸው።

عليه وعلى آله وعلى أتباعه صلوات ربي وسلامه
8