💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
8.72K subscribers
1.56K photos
549 videos
136 files
5.84K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
قال رسول الله ﷺ : "أربعٌ إذا كُنّ فيك فلا عليك ما فاتك من الدنيا
". تعليق الشيخ/ سليمان الرحيلي( حفظه الله )
﴿ يَـٰعِبَادِ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمُ الْيَوْمَ وَلَآ أَنْتُمْ تَحْزَنُونَ ﴾
- إبراهيم محمد
( ياحي ياقيوم برحمتك أستغيث أصلح لي شأني كله ولا تكلني إلى نفسي طرفة عين )
19
قناة ابن محمد الولوي (abu abdirehman)
🔖 አዲስ የቂርአት ፕሮግራም!
     ➖➖➖➖➖➖

👉የኪታቡ ርዕስ
  ➫➫➫➫➫➫

🌐 «ما هي السلفية
➡️
(ክፍል አስራ  ዘጠኝ   )

⭕️የመጨረሻ ክፍል


🎙በኡስታዝ  አቡ አብዲላህ ተውፊቅ

t.me/ibnumohammedyimer
t.me/ibnumohammedyimer

📚 የኪታብን Pdf ለማገኘት ⤵

t.me/ibnumohammedyimer/1319
🌷ለፈገግታ☝️

♦️ባል:- ባለቤቴን ሱብሒ ስቀሰቅሳት አትሰማም፤
መተኛት ሆነ ሥራዋ እንደው ምን ላድርግ ያሸይኽ ብሎ ጠየቀ?

♦️ሸይኽ:- በሌላ ሴት ስም ጠርተህ ቀስቅሳት፤
«የማን ስም ነው ?» ብላ ብድግ ትላለች!
👍5
👉ሴት ልጅ ለባሏ ሀያዕ ሊኖራት ይገባል!!አሁን ላይ በግልባጩ ሁኖል ለውጭ ስው አይን አፋር ናቸው?ለባሏ ደግሞ ጋጠውጥ ናቸው !

t.me/https_Asselfya
👍4
ከትላልቅ የፍቅር ማሳያዎች አንዱ፦ ወንድ ልጅ ለባለቤቱ ያለው ቅናት፣ በክብርና በሀያዕ እንድትኖር ያለው ጽኑ ፍላጎት፣ ከሰው ሁሉ ዓይን ሊሰውራት እና ስሟን ከሰዎች ጆሮ ሊያርቀው የሚመኘው ምኞት ነው።

የሴት ክብርና ሀያዕ ሙሉ ከሚሆንባቸው ነገሮች አንዱ፦ ባሏ በሂጃብና በክብር እንድትጠበቅ የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥንቃቄ ተቆጥታ አለመናደዷ ነው።

ወንዶች የሌሎችን ወንዶች እይታና አስተሳሰብ የተሻለ ያውቃሉና! ከዚህም በላይ፣ ከዲኗ እና ከሀያዕ ፍጹም የተነሳ ሂጃብ ግዴታና የአምልኮ ትዕዛዝ መሆኑን በማመን በመጀመሪያ በራሷ ተነሳሽነት ልትንከባከበውና ልትተገብረው ግድ ነው።

ከሴትነቷ ውበትና ፍጹምነቷ አንዱ ደግሞ፦ በባሏ ቅናት ውስጥ የልብ እረፍትን እና ሰላምን ማግኘት እንጂ በዚህ ነገር ፈጽሞ ልትበሳጭ አይገባም።

♛...
https://t.me/Qudwatii1
👍5
5 أسباب للغاية من الزواج:

1- أن تأنس ويُؤنس بك؛ وتأمن ويُؤمن بك
2- أن يباع كل شيء ويشترى خاطرك
3- أن يكتفى بوجودك؛ فيهون كل شيء ولا تهون أنت
4- أن تباركك علاقةً؛ وتزيدك امتنانًا لخالقك
5- أن تتكئ للمرة الأولى وأنت لا تخشى السقوط، أن تحب نفسك مجددًا وتراها أهلاً للمحبة.
🔖ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

ቀልብ ቀጥ አለች (ተስተካከለች) የሚባለው፦
①) በአላህ ውዴታ የተሞላች ስትሆን
②) አላህን መታዘዝ ስትወድና
③) አላህን ማመፅ ስትጠላ ነው።

【جامع العلوم والحكم】


t.me/https_Asselfya
🔖ባልን መታዘዝና የእሱን መብት ማሟላት ወላጆችን ከመታዘዝና
መብታቸውን ከማሟላት ይቀድማል።
ለዚህ ሲባል ስለ አንዲት ሴት፣ ባልና የታመመች እናት ስላላት ሴት ኢማሙ
አህመድ እንድህ አሉ፤ “
ባሏን መታዘዝ ከእናቷ ይበልጥ ግዴታይሆንባታል።”

~የባልን ሀቅ መወጣት የአላህን ትእዛዝ የመወጣት መንገድ ነው።
የአላህ መልእክተኛ እንድህ አሉ፤ “ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ፦
አንዲት ሴት የባሏን ሀቅ እስካልተወጣች ድረስ የጌታዋን ሀቅ አልተወጣችም። በግመል (ኮርቻ) ላይ ሆና እንኳን ነፍሷን ቢፈልጋት አትከልክለው።”ኢብኑ ማጂህ ዘግበውታል፤አልባኒም ሶሒሕ ብለውታል።
የባልን ሀቅ መወጣት የጀነት መግቢያ ምክንያት ነው።
የአላህ መልእክተኛ  እንዲህ ብለዋል፤ “አንዲት ሴት አምስቶቿን
ከሰገደች ፣ ወሯን ከጾመች፣ ብልቷን ከጠበቀች፣ ባሏን ከታዘዘች፣
በፈለግሽው በር ወደ ጀነት ግቢ! ትባላለች።

”አህመድ ዘግበውታል፤
👍2
خطبة الجمعة - الفرقان بين أولياء الرحمن وأولياء الشيطان- لسماحة…
سماحة الشيخ محمد الإمام
خطبة الجمعة

በአሏህ ወልዮች እና በሽይጧን ወልዮች መካከል ያለው ልዩነት

للشیخ العلامة محمد بن عبدالله الإمام
☀️ የአያሙል ቢድ (የነጫጭ ቀናት) ጾም ማስታወሻ!

የአላህ መልክተኛ ﷺ በየወሩ 13፣ 14 እና 15ኛ ቀናትን እንድንጾም ይመክሩን ነበር። የዚህ ወር የአያሙል ቢድ ጾም ነገ ይጀመራል፤ የቻለ ይፁም፣ ያልቻለ ደግሞ ሌሎችን በማስታወስ የአጅሩ ተካፋይ ይሁን!
⇛ አያሙል ቢድ — ቅዳሜ (13)
⇛ አያሙል ቢድ — እሁድ(14)
⇛ አያሙል ቢድ — ሰኞ (15)

🔸 قال ﷺ: «إذا صمت من الشهر ثلاثًا، فصم ثلاث عَشْرَةَ، وأربع عَشْرَةَ، وخمس عَشْرَةَ.»


t.me/SleSlkachin
﴿فَوَرَبِّكَ لَنَسْأَلَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ ۝ عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ﴾

ይህ የቁርኣን አንቀጽ ትርጉም በልብ ውስጥ በትክክል ቢሰርጽ፣ አንድን ባሪያ ከብዙ የሥራ ጉድለቶችና ወንጀሎች ለመጠበቅ በቂ ሰበብ ይሆን ነበር። ጉዳዩ ቀናት እያለፉ መጨረሳቸው ብቻ አይደለም፤ እያንዳንዱ የሚያልፍ ቀን በአላህ ፊት ለምንቀርብበትና ለምንጠየቅበት ታላቅ ጥያቄ ወደ እኛ እያቀረበን ነው።
ስለ ሥራዎቻችን፣ ስለ ንግግሮቻችን፣ ዕድሜያችንን በምን እንዳሳለፍንና በእጃችን ያሉትን ጸጋዎች እንዴት እንደተጠቀምን እንጠየቃለን።
አስተዋይ የሆነው ሰው ይህንን ጥያቄ በልቡ ውስጥ ሁልጊዜ የሚያስታውሰው ነው። ከመጠየቁ በፊት ራሱን ይመረምራል፤ በቻለውም ያህል ራሱን ያስተካክላል። መልካም ሥራ ብቻ በሚጠቅምበት ቀን ከመድረሱ በፊት መልካም ሥራን ይሠራል።
ስለዚህ አላህ ጉድለቶችህን በመሸፈኑ ወይም እድሜህ በማራዘም አትታለል። በአላህ ፊት መቆም እውነት ነው፤ መጠየቅም በእርግጥ የሚመጣ ነው። ለዚያ ቀን ራሱን ያዘጋጀና አላህ በእርሱ የሚወድድበትን ሥራ የሠራ ሰው ዕድለኛ ነው።
Audio
የጁሙዓ ኹጥባ
📖ርዕስ: የዲጂታል ሪያዕ አደገኛነት እና የኢኽላስ አስፈላጊነት.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

📍ቦታ፦አ/አ
🌇መስጂድ፦ሂጅራ መስጅድ
🎙 በሸይኽ ሰዒድ አቡ አህመድ
👉የኔ ወርቅ ድክም ሲልሽ ልብሽን ያዝ አድርገሽ አላህዬ እዘንልኝ በይው!  ወደርሱ ጥግት በይ እደማትወድቂ እርግጠኛ ሁነሽ ድግፍ በይው በጌታዬ ይሁንብኝ  አይተሽ የማታውቂውን እረፍት እና ደስታ ታገኛለሽ ።

~
👍13
🌷 እድለኛዋ ሴት🌹

🌿 የሰዎችን እይታ ሳትፈልግ፣ ሀያእዋን ጠብቃ፣ ዲኗን ተምራ፣ በዒባዳዋ ጸንታ የምትኖር ሴት በእውነት እድለኛ ናት።

💎 የእሷ ውበት ሰዎች በሚያዩት ፊቷ ሳይሆን፣ አላህ በሚያየው ልቧ ነው።

🌷 እህቴ! የሰዎችን ውዴታ ከመፈለግ ይልቅ የአላህን ውዴታ ፈልጊ፤ ያኔ እውነተኛዋ እድለኛ ትሆኛለሽ።🌿
Š
👍6
ዑመር ብኑል ኸጣብ የደካሞች ጋሻ!
~
አገሩ ወዲያ ነው - ከመካ በረሃ
ክንዱ የሚፋጀው - የሚያሰኘው ውሃ!
.
ዑመር ብኑል ኸጣብ ከመስለማቸውም በፊት በሃይለኝነታቸው በአይበገሬነታቸው የሚታወቁ ነበሩ። አቡ ጀህልም እንዲሁ ነበር። አቡ ጀህል ስሙ ዐምር ብኑ ሂሻም ብኒል ሙጊራ አልመኽዙሚይ ይባላል። ነብዩ ﷺ የነዚህን ሁለት ሰዎች መስለም በእጅጉ ይፈልጉ ነበር። ይህም የሆነው በጊዜው እንግዳ ለሆነው ኢስላም ክብርና አይደፈሬነትን ይሰጣል በሚል መነሻ ነበር። ለዚህም ነበር የአላህ መልእክተኛ ﷺ “አምላኬ ሆይ! ኢስላምን ከነዚህ ሁለት ሰዎች አንተ ዘንድ በተወደደው አስከብረው'' ማለታቸው። በአቡ ጀህል ወይም በዑመር ብኑል ኸጣብ! ከሁለቱ እሱ ዘንድ የተወደደው ዑመር ሆነ፡፡ [ቲርሚዚይ፡ 3681]

ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ዑመር እስከሚሰልም ድረስ ከዕባ አካባቢ መስገድ አንችልም ነበር፡፡ ዑመር ሲሰልም ግን ቁረይሾችን ተፋለማቸው፡፡ ከዚያም ከዕባ ዘንድ ሰገደ፡፡ ከሱም ጋር ሰገድን።” “ዑመር ብኑል ኸጣብ ከሰለመ ጀምሮ የተከበርን ሆነናል፡፡” [ቡኻሪይ፡ 3684]

ኡሙ ዐብዲላህ ቢንት አቢ ሐስማህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች:- “ወላሂ ወደ ሐበሻ ምድር ልንሰደድ እየተዘጋጀን ነበር፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሆነ ጉዳያችንን ሊፈፅም ወጥቶ ሳለ ዑመር መጣና ቆመ፡፡ በሺርኩ ላይ እንዳለ ነው፡፡ ከሱ ፈተናና ስቃይ ይደርስብን ነበር፡፡ ከዚያም፡

* “የምርም መጓዛችሁ ነው ኡሙ ዐብዲላህ?” አለኝ፡፡
- “አዎ ወላሂ! አላህ መውጫ እስከሚያደርግልን ድረስ ከአላህ ሀገሮች ወደ አንዱ እንወጣለን፡፡ አስቸገራችሁን አሰቃያችሁን!” አልኩት፡፡
* “አላህ አብሯችሁ ይሁን” አለ፡፡
ቀድሜ አይቸው የማላውቀው መቆርቆር አየሁበት፡፡ ከዚያም ተመልሶ ሄደ፡፡ ሳስበው መውጣታችን በርግጥም አሳዝኖታል፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሄደበትን ጉዳያችንን ፈፅሞ ሲመጣ፡

- “የአብደላህ አባት ሆይ! እንዲያው ዑመርን ቅድም ብታየው፣ ለኛ መቆርቆሩንና ማዘኑን” አልኩት፡፡
* “ይሰልማል ብለሽ ከጀልሽ እንዴ?” አለኝ፡፡
- “አዎ” አልኩት፡፡
* “የኸጣብ አህያ ሳይሰልም ያ ያየሽው ሰውዬ አይሰልምም!” አለኝ፡፡ “በኢስላም ላይ የሚያደርሰውን ጭካኔና ድርቅና በማየት ተስፋ ቆርጦ ነው።”

ዐብዱላህ ብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡-

“ዑመር ሲሰልም ቀድሞ በክህደት የተቀመጠባቸውን ስብሰባዎች አንድም ሳያስቀር መስለሙን ሊያውጅባቸው ለነብዩ ﷺ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ እናም በሰለመ ጊዜ፡
- 'ከቁረይሽ እጅግ ወሬ አራጋቢ የሆነው ማነው?' ሲል ጠየቀ፡፡
* 'ጀሚል ብኑ መዕመር ነው' አሉት፡፡
ቀጥታ ወደሱ ሄደ፡፡ ምን እንደሚሰራ ለማየት ከስር ከስሩ ተከትየው ሄድኩኝ፡፡ በጊዜው የማየውን ሁሉ በደንብ የማስተውል ልጅ ነበርኩ፡፡ ጀሚል ጋ መጣና፡
- 'ጀሚል ሆይ! መስለሜን አወቅክ ወይ? ወደ ሙሐመድ ሃይማኖት ገባሁ'ኮ!' አለው፡፡

ወላሂ ከዚያ በኋላ ጀሚል ለዑመር አልመለሰም፡፡ ቀጥታ ኩታውን እየጎተተ ወጣ፡፡ ዑመር ተከተለው፡፡ እኔም ዑመርን ተከተልኩት፡፡ ጀሚል ከመስጂዱ በር ቆመና ድምፁን በጣም ከፍ አድርጎ ጮኸ፡-

* 'የቁረይሽ ህዝብ ሆይ! አዋጅ! የኸጣብ ልጅ አፈንግጧል' አለ፡፡ በከዕባ ዙሪያ ተሰብስበው ነበር፡፡ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ከኋላው እየተከተለ፡
- “ዋሸ! ባይሆን እኔ በርግጥም ሰልሜያለሁ፡፡ ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆነ መስክሬያለሁ” አለ።

ዑመርን ሮጠው ከበቡት። ሲታገላቸው ሲታገሉት እኩለ ቀን ሆነ፡፡ ዑመር አቃተውና ቁጭ አለ፡፡ በራሱ ላይ ወጡበት፡፡ እሱ ይህኔ
* “የታያችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ በአላህ እምላለሁ! በርግጠኝነት ሶስት መቶ ወንዶች ብንሆን መካን ወይ እንተውላችኋለን፣ ወይ ትተውልናላችሁ!” አላቸው። ከሁለት አንዳችን ይወጣል እያላቸው ነው።

በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አንድ የቁረይሽ ሽማግሌ መጣ፡፡ የተቀለመ ሙሉ ልብስ ለብሷል፣ ቀሚስ ጋር፡፡ ቀጥታ ካጠገባቸው ቆመና፡
- “ምን እየሆናችሁ ነው?” አላቸው፡፡
* “ዑመር አፈንግጦ ነው” አሉት፡፡
- “ቢሆንስ?! እረፉ! አንድ ሰው ለራሱ የሆነ ነገር መረጠ፡፡ ታዲያ ምንድን ነው የምትፈልጉት? ይህን ሰውዬ እንዲህ ስታደርጉት የዐዲይ ጎሳዎች ዝም የሚሉ መሰላችሁ? ከሰውየው ዞር በሉ!” አላቸው፡፡
ከዚያም በአላህ ይሁንብኝ ልክ ከላዩ ላይ እንደተገፈፈ ልብስ ሆኑ! (ባንዴ ለቀቁት)፡፡ አባቴ ወደ መዲና ከተሰደደ በኋላ:
* “አባዬ ሆይ! ያኔ መካ የሰለምክ እለት እነዚያን ሲታገሉህ የነበሩትን ሰዎች የተቆጣቸው ሰውዬ ማነው?” አልኩት፡፡
- “ያማ አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚ ነው የኔ ልጅ” አለኝ፡፡ (አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚ ማለት የብልሁ ፖለቲከኛ የዐምር ብኑል ዓስ አባት ነው።)
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 1/2006)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor