💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.03K subscribers
1.41K photos
525 videos
128 files
5.49K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🔖የአረፋ ቀን የሚባል ዱዓ ..!
       ~ ~

~የአላህ መልእክተኛ  እንድ ብለዋል

እኔና ከኔ በፊት ካሉ ነብያቶች ሁሉ  ካልነዉ  በላጩ ዱአ፦

قال الرسول ﷺ :" خيرُ الدعاءِ دعاءُ يومِ عرفَةَ وخيرُ ما قلْتُ أنا والنبيونَ من قبلي لا إلهَ إلَّا اللهُ وحدَه لا شريكَ له له الملكُ وله الحمدُ وهو على كلِّ شيءٍ قديرٌ

➡️ከአላህ በስተቀር በሀቅ (በእዉነት) የሚመለክ አምላክ የለም ።በብቸኝነት ለሱም እሚጋራዉ የለም።  ስልጣንም ንግስናም  ባጠቃላይ  የሱ ነዉ። ምስገና ባጠቃላይ ለሱ ነዉ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነዉ
~
         t.me/https_Asselfya
👍1
كان السَّلف يدّخرون حاجاتهم ليومِ عرفة فيسألونَ الله ويتضرَّعون ليحقق اللهُ لهم مرامهم ومرادهم، فلا تشغلنَّكم الملاهي ؛ فتكونَ العبد اللَّاهي السَّاهي!

انتبه.. فيوم عرفة لا عوض له!
“ዱዓን አጥብቀህ ያዝ፤ ተስፋ አትቁረጥ፣ አትሰላች፣ አትቸኩልም። አላህ ፍላጎቶችን የሚፈጽም፣ ዱዓዎችን የሚመልስ መሆኑን እርግጠኛ ሁን። ሁሉም ነገር በእጁ ውስጥ ነው፤ መልካሙም ሁሉ በእርሱ እጅ ነው። ክፉን ከአንተ የሚያስወግድልህም ከእርሱ በቀር ሌላ የለም፤ እርሱም ከሁሉ በላይ ለመጠየቅ የተገባ፣ በፍጥረት ሁሉ ውስጥ ከሁሉ በላይ ሀብታም ነው። 🤲
​=
አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ

https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
የአረፋ ቀን እውነተኛዉ ከሳሪ ማን ነው?

قال عبد الله بن المبارك رحمه الله:

«جئتُ إلى سفيان الثوري عشية عرفة وهو جاثٍ على ركبتيه وعيناه تذرفان، فالتفتَ إليّ فقلت له: أتدري من الخاسر اليوم؟

قال: الذي يظن أن الله لا يغفر له.»

​المصدر: لطائف المعارف ابن الجوزي، ص (310)

​ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ዐብዱላህ ኢብኑል ሙባረክ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፡-

«በአረፋ ቀን አመሻሽ ላይ ሱፍያን አሰውሪ ዘንድ መጣሁ፤ እሱም በሁለት ጉልበቶቹ ተንበርክኮ አይኖቹ በእንባ ይፈሱ ነበር። ወደ እኔ ዘወር ሲል "ዛሬ በእውነቱ የከሰረው (ተሸናፊው) ማን እንደሆነ ታውቃለህ?" አልኩት።

​ሱፍያንም ሲመልሱ፡ "አላህ አይምረኝም ብሎ የሚያስብ ሰው ነው!" አሉኝ።»

​ያሸባበ ኢስላም

​ሞት ሳያሳውቀን ድንገት ከመምጣቱ በፊት፣ የንስሐ በር ሳይዘጋና ምላሳችን መናገር ሳይሳነው በፊት ወደ ጌታችን እንሩጥ። የአረፋ ቀን የዕንባና የተውባ ቀን ነው፤ አንዲት ንጹህ ዕንባ በአላህ እዝነት የጀሃነምን እሳት የማጥፋት አቅም አላት።

​ወንጀላችን ምንም ያህል ቢበዛም በግልፅም ይሁን በድብቅ አብዝተን ብናስቆጣዉም ተስፋ አንቁረጥ! ሸይጧን ትልቁን ድል የሚያገኘው ወንጀል ላይ ሲጥለን ሳይሆን፣ "አላህ አይምርህም" ብሎ ተስፋ ሲያስቆርጠን ነው። ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ ከወንጀሉ የከፋ ወንጀል መሆኑን አንዘንጋ።

​የጀነትና የጀሀነም ፈጣሪ፣ ሁሉ ነገር በእጁ የሆነው ጌታ "ጌታዬ ሆይ በድያለሁ!" ስትለው፤ "ባሪያዬ ሆይ ምሬሃለሁ!" ለማለት ወደ ቅርቢቷ ሰማይ የሚወርድ አዛኝ ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን እንጠብቃለን? የነፍሳችን ሰላም የሚገኘው በሱጁድ ውስጥ በሚፈስ ዕንባ እንጂ በኃጢአት ጊዜያዊ ደስታ ውስጥ አይደለም።

አላህን በሚያስቆጣ ወንጀል ላይ የከረምን ወንድሞች እና እህቶች ​በዚህ ታላቅ ቀን የራሳችንን ታሪክ እንቀይር፤ ካለንበት የጨለማ ጉድጓድ ወጥተን ወደ አላህ የይቅርታ ብርሃን እንሻገር።

​ዛሬ ካልተመለስን መቼ ልንመለስ ነዉ ?

https://t.me/durusuabihizam
👍4
🔖 እህቴ ሆይ አደራ !!

ለዒባዳና ወደ አላህ ለመቃረብ ከቤት ስትወጪ አላህን ከማስቆጣትና ሸሪዓውን ከመጣስ ተጠንቀቂ!

የአላህ ውዴታ እሱን በማመጽ አይገኝም።

~
       t.me/https_Asselfya
~ዉድ የቻናላችን ቤተሠቦች .....!

ኢድ ሙባረክ تقبل الله منا ومنكم 

ኢዳችሁ የተባረከ ይሁን
Audio
🔖ከቤተሰብ ፣ከዘመድ አዝማድና ከምትወዱት ሰው ርቃችሁ ኢድ ለምታሳልፋ ተጋበዙ
👍9
ነፍስ በ3 መንገዶች ስኬታማና፤ የጠራች ትኾናለች።

قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ۝١٤ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ۝١٥

የተጥራራ ሰው በእርግጥም ዳነ፤ የጌታውንም ስም ያወሳ፤ የሰገደም። [አል‒አዕላ (14—15)]
-

➀. እንዳትቆሺሽ ተገቢውን ክትትል በማድረግ፤

➁. የአላህን ስም ያለማቋረጥ በማውሳት እና፤
➂. ነፍስን በሶላት ጊዜ ከአላህ ጋር በማስተሳሰር።

t.me/https_Asselfya
🔖 አንድ ሰው ወደ ሀሰነል በስርይ መጣና፦ የሰኢድ አባት ሆይ ቀልቤ ደርቋል ምን ላድርግ ብሎ ስሞታ አቀረበ። እሳቸውም በዚክር ስርአት አሲዛት አሉት።

[ ذم الهوى: 69 ]
t.me/https_Asselfya
👍6
🌷 ሰው በውበቱ አይከበርምበኢማኑና በአክላቁ ነው የሚያምር።
ልብሽን በሀያእ፣ አንደበትሽን በዚክር፣ ሕይወትሽንም በሶላት አሳምሪ። 🌸

~ያኔ ሁሉም ቦታ ቦታውን ይይዛል!!

t.me/https_Asselfya
Forwarded from ስለ ስልካችን
👈 وَكُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ وَلَا تُسْرِفُوٓا۟ ۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلْمُسْرِفِينَ
ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ (አላህ ሱብሀነሁ ተአላ) አባካኞችን አይወድምና፡፡
~
🔖የጁሙዓ ቀን ሱናዎች!

①) ገላን መታጠብ
②) ሲዋክ መጠቀም
③) ጥሩ ልብስ መልበስ
④) ሱረቱል ከህፍን መቅራት
⑤) ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)
➅) በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
➆) በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት
⓼) ዱአ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት መጠባበቅ

t.me/https_Asselfya
الخطب المنبرية 5 التحذير من ذنوب الخلوات!! الأستاذ أبو مسلم عمر…
በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁሏህ)
🫵 የጁሙዓ_ኹጥባ (ምክር) - 5

•التحذير_من_ذنوب_الخلوات!!

•  
ከድብቅ_ወንጀሎች_ማስጠንቀቅ!!
   

🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Mp3
t.me/AbumuslimAlarsi/14106
       
          •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)
እህቴ ሞደልሽ ይህች ነች!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

እናታችን አዒሻ እንዲህ ነበረች፦

➩«በቤታችሁ ውስጥ ተሰተሩ(እርጉ)»የሚለውን አንቀፅ ስታነብ«መሸፋፈኛዋ» እስኪረጥብ ድረስ ታለቅስ ነበር።

رواه البخاري(4467)

فما بال نساء المسلمين
في الأسواق يزاحمن
الرجال .....
በየገበያው ውስጥ ከብዙ
ወንዶች.....ጋር #የሚጋፉት የኛዎቹ ሙስሊም ሴቶችስ..!?
👍2
ያ አሏህ!
ከቅናቻ በኋላ አታንሸራተን፡፡
ከታጠብን በኋላ አታጨቅየን፡፡
ከተነሳን በኋላ አትጣለን፡፡
ከቶበትን በኋላ አትመልሰን፡፡
ካንተ ጋር የሕይወትን ጥፍጥና
ከቀመስንና ካጣጣምን በኋላ አትጣላን፡፡
👍13
👉እናቷን እንዲህ አለቻት  እናቴ ለምን
ከቤት ስንወጣ ሽቶ ከለከልሽኝ?

🌸እናቷም፦

አበቦች ሽቶ አያስፈልጋቸውም።
🌹 በባልሽ ዘንድ ተወዳጅና የተከበርሽ ለመሆን ከፈለግሽ ⁉️

በባልሽ ዘንድ ሁልጊዜም ተወዳጅ፣ የተከበርሽና የልቡ ንግሥት ሆነሽ መኖር ትፈልጊያለሽ? እንግዲያውስ ይህንን ትልቅ የትዳር ሚስጥር በተግባር አሳይው።

🌹 ባልሽን መከባከብና እሱን ማስደሰት እንዲሁ ተራ ተግባር ሳይሆን፣ አላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝ "ዒባዳ" መሆኑን እወቂ።

🌹 ባልሽን እንደ ባል አክብሪው  አላህ ለወንዶች የሰጠውን የኃላፊነት ቦታ (ቀዋሚነት) እወቂለት። እሱን ማክበርሽ አንቺን ዝቅ አያደርግሽም፤ ይልቁንም በዓይኑ ላይ ትልቅ ያደርግሻል። አላህን በማመፅ እስካላዘዘሽ ድረስ የታዛዥነትሽን  ልብ ስጪው።

🌹 የቤትሽ "ሰከን" (መረጋገጫ) ሁኚለት ከውጭ በስራና በኑሮ ደክሞት ሲመጣ፣ ቤትሽ የሰላም ወደብ ይሁንለት። ንጭንጭንና ጭቅጭቅን አስወግጂ። በለሰለሰ ንግግርና በፈገግታ ተቀበዪው። ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት፦ "ምርጥ ሴት ማለት ስትመለከታት ደስ የምታሰኝህ ናት ብለዋልና።"

🌹 እልክና ፉክክርን ተዪ  ትዳር የሁለት ተፋቃሪዎች መርከብ እንጂ የፉክክር ሜዳ አይደለም።ከባልሽ ጋር እልህ ውስጥ አትግቢ፣ ለባልሽ ንቀት አታሳይ። ስህተቱ የሱ ቢሆንም እንኳ  በትህትናና በጥበብ ለማሳመን ሞክሪ እንጂ በባልሽ ላይ ድምፅሽን ከፍ አታድርጊ።

🌹 የትዳር ሀቁን ጠብቂለት የባልሽን ስሜት መጠበቅና በሐላል ደስተኛ እንዲሆን ማድረግ የአንቺ ትልቁ ኃላፊነት ነው። በዚህ ረገድ አትዘንጊ፣ አትለግሚ። እሱ ካንቺ ዘንድ እርካታን ካገኘ፣ ልቡ ሙሉ በሙሉ የአንቺ ይሆናል።

🌹 ቤትሽንና ራስሽን ጠብቂ፦ ቤቱን በንጽህና ያዢ፣ ለአንቺም እንዲመቸው አድርጊው። ለባልሽ በሚያምር ሁኔታ ተዘጋጂ። ይህ ማድረግሽ ለሱ ያለሽን ፍቅርና ክብር መግለጫ ነው።

🌹 ይህንን ሁሉ ስታደርጊ ለዱንያ ጥቅም ብቻ ሳይሆን የአላህን ውዴታ ፍለጋ ይሁን። "ባሌን ካስደሰትኩ አላህ ይወደኛል" ብለሽ ነይቺ። ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዲት ሴት አምስት ወቅት ሶላቷን ሰግዳ፣ የረመዳንን ወር ጾማ፣ ብልቷን ጠብቃና ባሏን ታዛ ከሞተች፤ ከፈለግሽበት የጀነት በር ግቢ ትባላለች።" (ኢማም አሕመድ ዘግበውታል)

እህቴ ሆይ! ባልሽን ለአላህ ብለሽ ካከበርሽው፣ አላህ በእሱ ልብ ውስጥ ያንቺን ፍቅርና ክብር ይዘራዋል። ትዳርሽን በኢማንና በጥሩ ስነ-ምግባር አድምቂው።

ያንችው ወንድም አቡ ሒበቲላህ
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
👍3