💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
8.72K subscribers
1.56K photos
549 videos
136 files
5.84K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
تزكية النفس
شيخ سيد بن محمد (أبو محمد الفاتح)
የጁመአ ኹጥባ (በኮምቦልቻ አንሷር መስጂድ) በኹጥባው ላይ የተወሱት ነጥቦች

​የኹጥባው ርዕስ፦ «تزكية النفس (የነፍስ ንጽህና)»

◈ ​የነፍስ ንጽህና ትርጉም፦ ነፍስን ከሽርክ፣ ከቢድዓ፣ ከማዕሲያ (ከሃጢያት) እና ከመጥፎ ስነ-ምግባሮች ማጽዳት፤ እንዲሁም በኢማን፣ በታንት እና በበጎ ስነ-ምግባር ማሳደግ።

◈ ​እውነተኛው የነፍስ ንጽህና መንገድ፦ ሰው ውጫዊ አካሉን ብቻ ሳይሆን ልቡን፣ ሰብዕናውን እና ሃሳቡን ከኩራት፣ ከሐሰድ (ከምቀኝነት)፣ ከውሸት እና ከግልጽ/ስውር ኃጢያቶች መጠበቅ እንዳለበት።

◈ ​የሰው ልጅ ስኬት በልብ ንጽህና ላይ የተመሰረተ መሆኑ፦ በአኼራ ከሰዎች ንብረት እና ብዛት ይልቅ «ከሰላም ጋር ከመጣ አላህ ዘንድ የሚጠቅመው ንጹህ ልብ ያለው ሰው ብቻ ነው» የሚለው ነጥብ።

◈​ የስኬት መለኪያ ገንዘብ ወይም መስተካከል አለመሆኑ፦ አላህ ዘንድ ደረጃ የሚሰጠው በውጫዊ ገጽታ፣ በሀብት ብዛት ወይም በዘር ከፍታ ሳይሆን በልብ እና በስራ ንጽህና መሆኑ።

​በሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ (አቡ ሙሐመድ አልፋቲሕ)
https://t.me/kombolcha_Ansuarmesjid_channel
.             10 ምክር ለእንስቶች        .
         እህቴ  ጀግና ሴት ነኝ ካልሽ

1ኛ: ከሚያናግርሽ ወንድ ሁሉ ጋር አትሳቂ። አንዳንዴ መኮሳተር ጥሩ ነው። ድንበር የሌለው ፈገግታና ሳቅ ከመንገድሽ ያዘገይሻል።

2ኛ: በኢስላምሽ ጉዳይ አትደራደሪ፣ ምክንያቱም ኢስላምሽ ከህይወትሽ በላይ ውድ ነው።  አንችን ከመከራ፣ ከስቃይ አውጥቶሻል።  ከነ ህይወትሽ በሚቀብሩሽ ሰኣት ‘ለምን!?’ ብሎ ጠበቃ ሆኖ ለነፃነት አብቅቶሻል።

3ኛ: በእምነትሽ አትፍሪ፣ ረጋ ብለሽ  ተጓዥ። ባለሽ ነገር ተብቃቂ። ኩርምት አትበይ። ከእምነትሽ ያፈነገጠ አለባበስና ፋሽን ተከታይ አትሁኚ አደራ። ኢስላምሽ ሰማያዊ እንጂ ዘመናዊ አይደለም።


4ኛ: ወደ ዝሙትና ወደ ወንጀል ከሚጋብዙ  ነገሮች ሁሉ ራቂ። ‘ኢስላማዊ’ የሚለው ስም እንዳይሸውድሽ አደራ። ኢስላማዊ ፊልም፣ ኢስላማዊ ነሺዳ።

5ኛ: በቦርሳሽ ውስጥ የኮስሞቲክስ ነጋዴ ይመስል የቻይና እቃ ይዘሽ አትዙሪ። ይልቁንስ የእምነትሽን መመሪያ ቁርኣን መያዝን አትርሺ። ቦርሳሽ ውበት የሚኖራት ያኔ ነው።

6ኛ: ድንግልናሽን ጠብቂው። ለምታገቢው ብቻ አስቀምጪ። አላህ ካልፈቀደው ነገር ሁሉ ራቂ። ያኔ  ደስተኛ  ህይወትን ትኖሪያለሽ።

7ኛ: ሁሌም የምትሰሪውን ስራ አስተውይው። ሙስሊም እንስት የምትፈፅመውን እንጂ አትስሪ።

8ኛ: ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! አንቺኮ ምርጥ ነሽ። ወንድ ሁሉ ይፈልግሻል። የሚያገባሽ እንዴት ታድሏል። ተፈላጊ መሆንሽን አትርሺ። ግን ለሚያገባሽ እንጂ ለሚፈልግሽ ሁሉ አትገኚ።

9ኛ: ሁሌም እምነቴ ኢስላም ነው ብለሽ ስታስቢ በሀሴት ልትረኪ ይገባል። ምክንያቱም የጀነት እጩ ተወዳዳሪ ነሽ። ውድድሩን ለማሸነፍ መዝሀበ ሰለፍን ተከተይ አደራሽን።

10ኛ: የመጨረሻው መልእክቴ - ተውሒድና ሱናን ባገኘሽው አጋጣሚ ሁሉ ለእህቶችሽ ስበኪ። ያኔ ውበትሽ ይደምቃል።©
👍8
~አላህ መልካም የሻለትን ሰዉ ድኑን ያስገነዝበዋል።በተቃራኒዉ ሼር የሻበትን ሠዉድንን አያዉቅም።ዲንን  ለማወቅ ችልተኛ ይሆናል።

~
👍6
የሀይድን ጉዳይ እያስተዋልኩ ነበር…  ብዙ ሴቶች በሀይድ ወቅት ራስ ምታት፣ ሆድ ቁርጠትና የጀርባ ህመም ያጋጥማቸዋል … አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት በከፍተኛ ድብርትና  የስሜት መገለባበጥ ውስጥ ይመላለሳሉ ምናልባትም አንዳንዴ ማልቀስ…

ይህ ሁሉ ሲሆን ዓለም ለነርሱ ብሎ ለደቂቃ እረፍት አይሰጣቸውም …  መደበኛ ትምህርቶች አይቋረጡም፣ ፈተናዎች አይዘዋወሩም፣ ስራም ለነርሱ ብሎ የተለየ ፈቃድ አይሰጥም…  አላህ ሲቀር… ወዱድ ሲቀር…

እርሱ ይወዳቸዋልና እንዲንገላቱ አልፈቀደም… ልዩ የህይወት ፈቃድ ሰጣቸው … በዚያ ወቅት  ሰላትን አነሳላቸው … ፆም እንዳይፆሙ ከለከላቸው…  “ነብዩ እኔ ሀይድ ላይ ሆኜ እቅፌ ውስጥ ይደገፉና ቁርአን ይቀሩ ነበር።" ትላለች አዒሻ…  ክብር ተመልከቱ… በነብዩ የህይወት ትምህርት ውስጥ ወንድ ልጅ በየትኛውም ሁኔታ ባለቤቱን ካላከበራት ክብር የለውም  "ከናንተ ውስጥ ምርጡ…  ለባለቤቱ ምርጥ የሆነው ነው" እንዲሉ  … ከዚያ አንዳንዶች ይመጡና እስልምና ሴትን ልጅ በድሏል ይላሉ…    ሀሻ ወከላ…

نقل
👍25
ለራስሽ የማተገብሪውን ነገር ለሰው አትምከሪ..!
ሰው ለሌላ ሰው አርአያ ሊሆን የሚችለው  ለራሱ የተግባር ሰው  ሲሆን ነው...!
ለመሆን እንጅ ለመምሰል አትሞክሪ..!
ምክኒያቱም ጠንካራዋ እንስት የተግባር ሰው እንጅ የወሬ ሰው አይደለችምና...!
👍8
ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል
~
ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች። ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች - ክፉ የሸር መፈልፈያ። ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለ ኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል። ተንቀሳቃሽ ሙት! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሂወት እንዳለው ያስባል፡፡

ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ!

(أَفَلَمۡ یَسِیرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبࣱ یَعۡقِلُونَ بِهَاۤ أَوۡ ءَاذَانࣱ یَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ)

"ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም። ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡" [አልሐጅ፡ 46]

በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በተቅዋ ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ!

ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና! አቡበክር ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች በተለየ የላቁት በሶላትና በፆማቸው ብዛት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ልባቸው ውስጥ በፀደቀ ነገር ነበር። ኢማን! የቀልብ ልዩ ክብር!

ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው? በሽተኛ ነው? ወይስ ሞቷል? ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ "ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም" አይደል ያለው ኻሊቁ?

አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ አዙርልን። በዲንህም ላይ አፅናን፡፡ አላሁመ ኣሚን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ 2001)
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🌸ኡክቲዬ🍒

--»አንቺ ሷሊህ  ከሆንሽ ሀቅ የምጠብቂ
--»ባል አጣሁኝ ብለሽ አትጨናነቂ
--»መልካም ለመልካሞች መሆኑን እወቂ
--»ወቅቱ ቢዘገይም እንዳትበሳጪ...
--»በሶብር ጠብቂ ሷሊሁን አታጪ።
©
👍15
ትዳር የዘገየባት ኒቃቢስት ካየህ እርሷ ወንድ ሳይሆን ያጣችው ሸሪዓዊ መስፈርቷን የሚያሟላ ሰለፊይ ባል የሚሆናትን ወንድ ነው።

አላህ ያበርታት🤲
👍24
أسباب نزع البركات من الأرزاق
خطبة الشيخ أحمد شملان
🔸أسباب نزع البركات من الأرزاق

#خطبة الجمعة
بدار الحديث بوادي بنا- السدة
🎙للشيخ الفاضل|
أحمد بن أحمد شملان
   حفظه الله تعالى

🗓 بتاريخ ٠٥ جمادى الأولى ١٤٤٨ه‍
┈┉┅━━•❁•━━┅┉┈
◢للمزيد| قناة الخطباء
➢https://t.me/ooooh5
👉በዲንሽና  በዒባዳሽ  ላይ ባለሽ ጥንካሬ ልክ በዚህች ሀያት ደስታን ታገኛለሸ...!

t.me/https_Asselfya
👍1
🔖ኢብኑ በጣል አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።
~
👉ሚስጥር አማና ነው። መጠበቁ ግዴታ ነው። ይህም የሙእሚኖች ባህሪ ነው። ነብዩን አስር አመት ኻድሚያለሁ። "ሚስጥሬን ጠብቅ ሙእሚን ትሆናለህ" ብለውኛል የሚል ዘገባ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ተወርቷል።
📚شرح صحيح البخاري (9/64) :

~
t.me/https_Asselfya
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
قال رسول الله ﷺ : "أربعٌ إذا كُنّ فيك فلا عليك ما فاتك من الدنيا
". تعليق الشيخ/ سليمان الرحيلي( حفظه الله )
﴿ يَـٰعِبَادِ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمُ الْيَوْمَ وَلَآ أَنْتُمْ تَحْزَنُونَ ﴾
- إبراهيم محمد
( ياحي ياقيوم برحمتك أستغيث أصلح لي شأني كله ولا تكلني إلى نفسي طرفة عين )
19
قناة ابن محمد الولوي (abu abdirehman)
🔖 አዲስ የቂርአት ፕሮግራም!
     ➖➖➖➖➖➖

👉የኪታቡ ርዕስ
  ➫➫➫➫➫➫

🌐 «ما هي السلفية
➡️
(ክፍል አስራ  ዘጠኝ   )

⭕️የመጨረሻ ክፍል


🎙በኡስታዝ  አቡ አብዲላህ ተውፊቅ

t.me/ibnumohammedyimer
t.me/ibnumohammedyimer

📚 የኪታብን Pdf ለማገኘት ⤵

t.me/ibnumohammedyimer/1319
🌷ለፈገግታ☝️

♦️ባል:- ባለቤቴን ሱብሒ ስቀሰቅሳት አትሰማም፤
መተኛት ሆነ ሥራዋ እንደው ምን ላድርግ ያሸይኽ ብሎ ጠየቀ?

♦️ሸይኽ:- በሌላ ሴት ስም ጠርተህ ቀስቅሳት፤
«የማን ስም ነው ?» ብላ ብድግ ትላለች!
👍5
👉ሴት ልጅ ለባሏ ሀያዕ ሊኖራት ይገባል!!አሁን ላይ በግልባጩ ሁኖል ለውጭ ስው አይን አፋር ናቸው?ለባሏ ደግሞ ጋጠውጥ ናቸው !

t.me/https_Asselfya
👍4
ከትላልቅ የፍቅር ማሳያዎች አንዱ፦ ወንድ ልጅ ለባለቤቱ ያለው ቅናት፣ በክብርና በሀያዕ እንድትኖር ያለው ጽኑ ፍላጎት፣ ከሰው ሁሉ ዓይን ሊሰውራት እና ስሟን ከሰዎች ጆሮ ሊያርቀው የሚመኘው ምኞት ነው።

የሴት ክብርና ሀያዕ ሙሉ ከሚሆንባቸው ነገሮች አንዱ፦ ባሏ በሂጃብና በክብር እንድትጠበቅ የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥንቃቄ ተቆጥታ አለመናደዷ ነው።

ወንዶች የሌሎችን ወንዶች እይታና አስተሳሰብ የተሻለ ያውቃሉና! ከዚህም በላይ፣ ከዲኗ እና ከሀያዕ ፍጹም የተነሳ ሂጃብ ግዴታና የአምልኮ ትዕዛዝ መሆኑን በማመን በመጀመሪያ በራሷ ተነሳሽነት ልትንከባከበውና ልትተገብረው ግድ ነው።

ከሴትነቷ ውበትና ፍጹምነቷ አንዱ ደግሞ፦ በባሏ ቅናት ውስጥ የልብ እረፍትን እና ሰላምን ማግኘት እንጂ በዚህ ነገር ፈጽሞ ልትበሳጭ አይገባም።

♛...
https://t.me/Qudwatii1
👍5