💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
13.6K subscribers
4.95K photos
2.24K videos
164 files
13.3K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ
↓↓↓↓↓↓
@Ass_Selefyaa1bot
@Ass_Selefyaa1bot
Download Telegram
🛍🍂በትዛዝ የተሰሩ ባለ ሂጃብ የሶላት ሸርሸፎች 🩵
ዋጋ የአዋቂ 1400 የህፃን 1000 ብር!

📲 0929438806

https://t.me/reemjilibab
👍12
የሶላት ሸርሸፍ ....
የፕሮግራም ቀሚሶች....
ከቱርክ የመጡ የመኚታ ልብሶች ታገኛላችሁ! ከታች ባለዉ ስልክ ቁጥር ይደዉሉልን🌺

0985597464 0985597464

___
👍4
ሴት ልጆቻችሁ ውጭ የሚሆኑትን ብታዩ ኖሮ፣ ባል ሲመጣ “ምን አለው?” ብላችሁ አትጠይቁም ነበር። ቤት ውስጥ መልካምና ጨዋ ናት ብላችሁ የምታምኗት ልጃችሁ፣ ከዓይናችሁ ስትርቅ ምን ያህል እንደምትታለል፣ በዝሙትና በሀራም ፈተናዎች ውስጥ ምን ያህል እንደምትወድቅ ብታውቁ ኖሮ፣ ትዳር ሲመጣላት በገንዘብ መስፈርት ብቻ አትመልሱም ነበር። “የኔ ልጅ ጥሩ ናት” ብላችሁ ብቻ አታስቡ፤ “ልትሳሳትም ትችላለች” ብላችሁ አስቡ!።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
👍36👎3
ዕድል ሙሉ ሆና አታውቅም፤ ተፈጥሮዋም አይደለም። ሁለንተናዊ ምሉዕነትም… የሁልጊዜ ጎዶሎነትም የለም። በመንገድህ የሆኑ ፀጋዎች ላንተ ተፅፈዋል፤ አያመልጡህም። የሆኑ ፀጋዎች ደግሞ ካንተ ተከልክለዋል፤ ሰማይን ብትቧጭር አታገኛቸውም። አየህ? እዚህ ነው ህይወትህ የሚጀምረው ወይም ፍፃሜውን የሚያውቀው። በእጅህ ያለውን ፀጋ እያተለቅክ የጌታህን ስጦታ ወድደህ ትኖራለህ፤ አልያም የተከለከልከውን ፍለጋ መዳፍህን ታገላብጣለህ። ከዚያስ? በዚህ የማትጨብጠው ዓለም ውስጥ ከርታታ ትሆንና መኖር የሚገባህን ህይወት ያመልጥሃል። ፀጋህን አመስግን።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
👍17
🌿 ውድ እህቴ!

በእውነት የሚወድሽ ሰው፣ በተጫዋችነትና በሐሰተኛ ቃላት ልብሽን አይዝም፤ ከቤተሰብሽ ፈቃድ ጠይቆ፣ በሀላል የኒካህ መንገድ እንዲያገባሽ ወደ ቤተሰብሽ ይመጣል። ነገር ግን ለጨዋታና ለጊዜያዊ ደስታ የሚፈልግሽ ሰው፣ በጋብቻ ተስፋ ሊያታልልሽ፣ በጣፋጭ ቃላትም ሊያሳስትሽ ይችላል። ስለዚህ ቃሉን ሳይሆን ተግባሩን ተመልከቺ።

እህቴ! ልብሽን ለማንም አትስጪ፤ ክብርሽን፣ ንጽሕናሽን ጠብቂ። ፍቅር አላህን ወደ ማይታዘዙበት መንገድ እንዲወስድሽ አትፍቀጂ።
የሚገባሽን ሰው በሐላል መንገድ አግኚ፤ የአላህን ውዴታ ከጊዜያዊ የሰው ፍቅር አስቀድሚ። አላህ በዲንሽ የሚረዳሽ፣ ክብርሽን የሚጠብቅልሽና ወደ ጀነት የሚያቀርብሽ መልካም ባል ይወፍቅሽ። አሚን! 🤲🏻


=
t.me/https_Asselefya1
👍31
" የፍቅር ከፍተኛው ጥግ መረዳዳት ነው። ሰዎች ካልተረዱህ በእውነት አልወደዱህም ማለት ነው፤ የፍቅርን ስም ተጠቅመው አታለሉህ እንጂ፣ ቅርበትንም እንደ ማታለያ ተጠቀሙበት ማለት ነው። በዚያን ጊዜ ከእነርሱ መራቅና ልብህን፣ ስሜትህንና ባሕርይህን ከሚረዱ ሰዎች ጋር መቀራረብ ለክብርህ የሚገባ ነው። ካልሆነ ግን በመካከላቸው እንግዳ እንደሆንክ ከሚሰማህ፣ ልብህ ከማይረጋባቸውና ማንነትህን ከማይረዱ ሰዎች ጋር በመቆየት ልብህን አታባክን። ራስህን በሚጎዳ ግንኙነት ውስጥ ማስቀመጥ በራስህ ላይ በደል መፈጸም ነው።
"አንዳንድ ጊዜ ከአንዳንድ ሰዎች መራቅ ኪሳራ አይደለም፤ የልብን ሰላም መጠበቅ ነው።

=
t.me/https_Asselefya1
👍25👎2
" ለአላህ ብለህ የተውከው ነገር አይጠፋም! ልቡን ከሐራም ግንኙነት በመጠበቅ፣ የአላህን ውዴታ ከጊዜያዊ የሰው ፍቅር አስቀድሞ የሚኖር ሰው፣ የአላህን ረህመት ተስፋ ያድርግ። አላህ እርሱን የሚፈሩትን፣ በትእዛዙ ላይ የሚጸኑትን አያሳፍርም።

ያረብ! ለልባችን ሰላም፣ ለዓይናችን ማረፊያ፣ ለዲናችን ረዳት የሚሆኑንን መልካም የሕይወት አጋሮች ለግሰን።

آمين يا رب العالمين 🤲🏻
=
👍20
" መልካም የትዳር አጋር ማለት…

መልካም የትዳር አጋር ማለት በደስታ ጊዜ ከጎንህ የሚቆም ብቻ ሳይሆን፣ በፈተና ጊዜም አላህን የሚያስታውስህ ሰው ነው።
ስትጨነቅ በሰብር የሚያጽናናህ፣ ስትደክም በዱዓ የሚደግፍህ፣ የዱንያን ጭንቀት በተወኩል እንድትቀበል የሚያስታውስህ፣ የአኺራንም ጉዳይ እንዳትዘነጋ የሚመክርህ ነው።
ትዳር ማለት ሁለት ሰዎች በአንድ ቤት መኖር ብቻ አይደለም፤ አንዱ ሌላውን ወደ አላህ የሚያቀርብበት፣ በኢማን የሚተጋገዙበት ነው።

🌷 ያረብ! ትዳራችንን የሰላም፣ የመውደድና የረህመት ምንጭ አድርግልን። እርስ በርሳችንም ወደ ጀነት የምንመራራበት አጋሮች አድርገን።

آمين يا رب العالمين 🤲🏻
=
t.me/https_Asselefya1
👍24
"አስታውሺ! ቁርአን የልብሽ መርጊያ፣ የልብሽ ብርሃንና የሕይወትሽ መረጋጋት ነው። በደረቀው ልብሽ ላይ እንደ ረጋ ዝናብ የሚዘንብ፣ ነፍስሽን በእምነት የሚያለመልም፣ ልብሽንም በአላህ ዚክር የሚያረጋጋ የአላህ ቃል ነው።

ቁርአንን ከሕይወትሽ አትለዪው፤ በንባቡ ልብሽን አብሪ፣ በትርጉሙ አስተውዪ፣ በትምህርቱም ሕይወትሽን አስተካክዪ። የአላህ ቃል የዱንያ መንገድሽ ብርሃን፣ የልብሽ መድኃኒትና ወደ አላህ የሚያቀርብሽ መንገድ ነው።

=
👍27
‏قال بؚ؜ السلف:
‏"ؼذا أعاد الله -عزَّ وجلَّ- بعبده خيرًا
‏جعل له واعظًا من قلبه يأمره وينهاه".
=
👍6
اللَّهُمَّ اهْدِنا وسَدِّدْنا، اللَّهُمَّ إنَّا نسْألُكَ الْهُدى، والسَّدَادَ... 🌸
👍16
« የሚያስፈልገው ብዙ መልካም ሥራ መሥራት ብቻ ሳይሆን፣ ሥራውን ለአላህ ብሎ በንጹሕ ልብና በነቢዩ ﷺ ፈለግ መሠረት መፈጸም ነው። «አንዳንድ ትንሽ የሚመስል መልካም ሥራ፣ በንጹሕ ኒያ ምክንያት በአላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ሊያስገኝ ይችላል፤ በተቃራኒውም ትልቅ የሚመስል ሥራ በተበላሸ ኒያ ምክንያት ዋጋ ሊያጣ ይችላል።
ስለዚህ የሥራ ትልቅነት የሚለካው በብዛቱ ሳይሆን፣ በኢኽላሱና በሱና መሠረት በመፈጸሙ ነው።

=
t.me/https_Asselefya1
« አንድ ሰው ለዓመታት ሁሉ ዲግሪና ማዕረግ ለማግኘት፣ ከፍተኛ የሥራ ቦታ ለመያዝና በሰዎች ዘንድ የሚያምር ገጽታ ለመፍጠር ሲሮጥ መኖሩ አሳሳቢ ነው። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ሩጫ መካከል ልቡን ለማስተካከልና ሥነ-ምግባሩን ማሳደግ እንደሚገባው ይረሳል! አንድ ሰው የትምህርት ከፍተኛ ማዕረግ ለመድረስ ዕድሜውን ሙሉ ጥረት ሲያደርግ፣ ከዚያ ጥረት ትንሽ እንኳን ቆርሶ በመልካም ሥነ-ምግባር ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ አለመጣሩ ያሳዝናል።
ሁሉንም ነገር ይማራል፤ ነገር ግን እንዴት ጥሩ ሰው መሆን እንዳለበት ሳይማር ይቀራል!ሰው በሌሎች ፊት የሚታየውን ገጽታ ማሳመር በደንብ እየተካነ ሲሄድ፣ በተቃራኒው ግን እውነተኛውን ማንነቱንና የልቡን ሁኔታ ችላ ማለቱ እጅግ የሚያስፈራ ነው።የእውነተኛ ስኬት መለኪያ የተማርነው ትምህርት፣ የያዝነው ማዕረግ ወይም በሰዎች ዘንድ ያለን ዝና ብቻ አይደለም፤ እውነተኛ ስኬት በእውቀታችን ልክ በሥነ-ምግባራችን፣ በንግግራችንና በተግባራችንም መታየት አለበት።

~
አስታውሱ፦ እውቀት የሰውን አእምሮ ያበራል፤ መልካም ሥነ-ምግባር ግን የሰውን ማንነት ያሳምራል። አላህ ከእውቀታችን ጋር መልካም ሥነ-ምግባርን ይስጠን።

=
👍7
الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
ወንድሞች ሰርተው እዳይተዳደሩ? ሰርተው ሚስት እዳያገቡ ከማድረግ ተቆጠቡ✅ ደረሳ ነው) ደረሳ አይስራ ያለው ማነው። ሸይኽ ነው) ሸይኹ አይስሩ ያለው ማነው። "እስኪ አንዳድ ጊዜ አፈር እያልን!! ዛሬ በርብርብ ትዳር የጀመረ) ዛሬ በእርዳታ የፈራረሸ ነገ መውለድ ሲጀምር ማን ሊረዳው ነው። በወጣትነቱ .ይሄንን የለመደ እድሜው. ከገፋ ቡሀላ እውነት ሊሰራ ነውን?? ገና ለገና ደረሳ ነው) ኡስታዝ ነው)…
100% የምደግፈዉ ሀሳብ!!
👍3
~ ውድ ባለቤቴ!

በኸይር መንገድ ላይ በጽናት ቀጥል። ዲንን መጠበቅ ፍም እሳትን በእጅ እንደመያዝ አስቸጋሪ በሆነበት በዚህ ዘመን፣ ዲንህን በጽናት ይዘሃል።
ብዙዎች በዱንያ ጉዳይ በተጠመዱበት፣ አንተ ግን የዐቂዳን ትክክለኛነትና የነቢዩን ﷺ ሱና ለመጠበቅ ትጋለህ። የአላህን ቃል ታስታውሳለህ፣ የነቢዩን ﷺ ሐዲስ ታስተላልፋለህ፤ ሌሎች ግን በገበያ ዋጋ መጨመርና መቀነስ ተጠምደዋል።
ስለዚህ በአላህ እገዛ መንገድህን ቀጥል። እኔም በአላህ ፈቃድ በመልካም ሥራ እደግፍሃለሁ፤ ለሶላት፣ ለዚክር፣ ለቁርአን ንባብና ለሱና መከተል እንድትተጋ ከጎንህ እሆናለሁ።

ለምን መሰለህ?
እኔ የዲንን መልዕክት ለማስተላለፍ የምትተጋ፣ የአላህን ውዴታ የምትፈልግ፣ የአኺራን ስኬት ከዱንያ ጌጥ የምታስበልጥ ሚስት ነኝና።

~ የጋራ ዓላማችን የአላህን ውዴታ ማግኘት፣ በኢማንና በሱና ላይ መጽናት፣ በአላህ እዝነት ጀነተል ፊርደውስን መውረስ ነው።

~ ከአረበኛ የተወሰዴ¡


=
t.me/https_Asselefya1
👍7
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
~ ውድ ባለቤቴ! በኸይር መንገድ ላይ በጽናት ቀጥል። ዲንን መጠበቅ ፍም እሳትን በእጅ እንደመያዝ አስቸጋሪ በሆነበት በዚህ ዘመን፣ ዲንህን በጽናት ይዘሃል። ብዙዎች በዱንያ ጉዳይ በተጠመዱበት፣ አንተ ግን የዐቂዳን ትክክለኛነትና የነቢዩን ﷺ ሱና ለመጠበቅ ትጋለህ። የአላህን ቃል ታስታውሳለህ፣ የነቢዩን ﷺ ሐዲስ ታስተላልፋለህ፤ ሌሎች ግን በገበያ ዋጋ መጨመርና መቀነስ ተጠምደዋል። ስለዚህ በአላህ እገዛ…
አረበኛ ቻናል አገኘሁትና እንድህ በግርድፍ ለመተርጎም ሞክሪያለሁ......ይመቻችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ.....
👍7