💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
13.8K subscribers
4.94K photos
2.24K videos
164 files
13.3K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ
↓↓↓↓↓↓
@Ass_Selefyaa1bot
@Ass_Selefyaa1bot
Download Telegram
-
በእርግጥም ወላጆቻችን
ከአሏህ የተሰጡን እዝነትና ፍቅር ናቸው..!!

اللَّهُمَّ جَازِهِمْ عَنَّا خَيرَ الجَزَاء.!


♛...
https://t.me/Qudwatii1
ሁሉም ነገር ባለበት ይቀጥላል ብለህ አታስብ… የወጣ ሁሉ ይወርዳል … የኖረ ሁሉ ይሞታል… የማይነጋ ጨለማም አይኖርም… የሆነ ቀን ፀሃይ ራሱ ህጉን ጥሶ፣ ፍፃሜን ለመግለፅ ከምዕራብ የሚወጣበት ጊዜ አለ። የሰዎች ህይወትና የግንኙነት ሂደት ባልታሰበ ሁኔታ ሊለወጥ ይችላል። በጣም የወደደህ በመጨረሻ በጣም ይጠላህ ይሆናል። በጣም የጠላህ ደግሞ በጣም ይወድህ ይሆናል።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
" አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት አይቻልም፤ ለማብራራት ብትሞክርም ለዚያ ሰው ምክንያታዊ ላይሆንለት ይችላል፡፡

=
ሰለዋት ማብዛት…  የእድሜና የስራ በረካን ያመጣል፣ ለብዙ አህዋሎች መስተካከልም ምክንያት ይሆናል።

ኢብኑል ቀይዪም "ጀላኡል-አፍሀም" በተሰኘው መፅሃፋቸው 245 ገፅ ላይ ይህንን ሀሳብ አስፍረዋል።

አስበህው ታውቃለህ..? ነብይህ ላይ የምታወርደው ሰለዋት… በስምህ ሲደርሳቸው… እገሌ የእገሌ ልጅ ተብሎ … አላህም በአስር እጥፍ አንተ ላይ እዝነቱን ሲያሰፍን… ደስ የሚል ስሜት አለው… ነብይህ  በሰለዋት ብዛት ያውቁህ ይሆን?
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
« ሴት ሆይ፣ ምናልባት ዛሬ የምትያዪው ሁሉ ጨለማ ይሆናል፤ ግን ጨለማው የመጨረሻሽ አይደለም። ትዕግስትሽን አጠንክሪ፣ ዱዓሽን አትተዪ፣ በአላህም ላይ ያለሽን ተስፋ አትስበሪ። አንድ ቀን ዛሬ ያስለቀሰሽን ነገር በልብሽ ላይ ምስጋናን እንዲያመጣ አላህ ይለውጠዋል። 🤲🏻🌷

=
«አላህ ከፍ ሊያደርግህ ሲፈልግ ምቀኛን ይልክልሃል» ይላል ዛሬ ያነበብኩት የ አረብኛ ጥቅስ።

በነገራችን ላይ ምቀኛ ከሌላችሁ አታድጉም። በህይወታችሁ ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩና ስኬታችሁን የማይወዱ ሰዎች መኖራቸው የተሻለ ደረጃ ላይ እንድትደርሱ የሚገፋፋችሁ ትልቁ ሞተር ነው።

የእነሱ ትችት እና ምቀኝነት እናንተን ወደ ኋላ ከመጎተት ይልቅ፣ የበለጠ ጠንክራችሁ እንድትሰሩና አላህ ወዳዘጋጀላችሁ ከፍታ እንድትወጡ መንገድ ጠራጊ ይሆናል።
t.me/AbuSufiyan_Albenan
👍1
« እህቴለአላህ ብዬ እወድሻለሁ ተብለዉ በonline የሚጀምሩ ዉደታዎች አብዘሀኞቹ ከonline ጠፋ ሲባል ተቆርጠዉ ይቀራሉ! እና ብዙ ልባችሁ አትክፈቱ ለማለት ያክል ነዉ! ዉደታ የልባሞች ስራ ብቻ ነች። የምላሰኞች አይደለችም።»

=
t.me/https_Asselefya1
" ተፅዕኖ ፈጣሪ፣ አስተዋይ፣ የተማረች፣ በሥራ የምትተጋ፣ ቅን፣ አማኝ፣ ጠንካራ፣ ውድና ራሷን የምታውቅ ሴት ሁኚ።
ውበትሽ በፊትሽ ብቻ እንዲወሰን አትፍቀጂ፤ በባዶ ሙገሳና በርካሽ ሽንገላ የምትማረክ ሴት ብቻ አትሁኚ።ዕውቀትሽን አሳድጊ፣ ማንነትሽን ገንቢ፣ እሴትሽን ጠብቂ፤ በክብርሽና በማንነትሽ የምትታወቂ ሴት ሁኚ። አንቺ ውብ ፊት ብቻ ሳይሆን፣ ውብ አእምሮ፣ ጠንካራ ማንነትና የተከበረ ልብ ያለሽ ሴት ነሽ።

=
t.me/https_Asselefya1
አስተውሎትና ነገሮችን በጥልቀት ማየት አንዳንዴ ውጤቱ በባዶ መብሰልሰልና እንደ እሳት መንደድ ብቻ ነው(ሰኪናን ያነሳል)። ብትፈልግ እንኳን ተመልሰህ የበፊቱ አለማስተዋል ውስጥ መግባት አትችልም። እና አንዳንድ ነገሮችን በጥልቀት አለማየትና ብዙም ቦታ አለመስጠትን መለማመድ ጥሩ ነው። የዓረቡ ዓለም ጉምቱ ገጣሚ ሙተነቢ እንዲህ ብሎ ገልፆት ነበር…
ذو العَقلِ يَشقى في النَعيمِ بِعَقلِه
وَأَخو الجَهالَةِ في الشَقاوَةِ يَنعَمُ
👍1
Forwarded from *
ጓደኝነት
🖊  ጓደኛ ያለው ሰው ትርፉ የበዛ ይሆናል ጓደኝነት እና ጤና አንድ ናቸው ሁለቱንም ስናጣቸው ነው የሚገባን ።
መልካም ጓደኛ ከትላልቅ የአላህ ፀጋወች አንዱ ነው ።እውነተኛ ጓደኛችሁን በሁለት  እጃችሁ ያዙት ሁላችንም የሆነቦታ ስንሄድ በሀሳባችን ይዘነው የምንሄደው ጓደኛ ይኑረን ።
እውነተኛ ጓደኛ ማለት የሁለት ሰው አንድልብ እንደባለት ነው።
እውነተኛ ጓደኛ አለም ሁሉ ጀርባዋን ስታዞርብህ  ፊቱን ወደ አንተ የሚያዞር ነው ።ሁሉም ሰው የሚሰማ ቢሆንም እንካ ማለት የፈለከውን የሚያውቅ ብቻ ነው ።
ጓደኛችሁን እወድሀለሁ ካላችሁት ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ልታሳዩቸው ይገባል ።
አንዱ ለጓደኛቹ ያለውን ውደታ ሲገልፅ እንድህ ይላል ፦ጓደኛቸ እራሳቸውን ከፎቅ ለመወርወር ቢዘጋጁ  እኔ አብሬቸው አልወረወርም ምክንያቱም ከፎቁ ላይ ወርጀ እመሬት ላይ እጠብቃቸዋለሁ ይላል ። ሌላኛው ደግሞ ለጓደኛው እንድህ ሲል
ፍቅሩን ይገልፃል በምድር ላይ መቶ አመት ብትኖር  ከአንተ ያነሰ እድሜ ቢኖረኝ አመኛለሁ ምክንያቱም ካንተ የተለየ አንድ ቀን እንኳን መኖር ስለማልፈልግይለዋል ።
ጓደኝነት ትልቅ ነገር ነው በተለይ በቀጥተኛው መስመር ላይ ሲፀና አላህን ፈሪ እና መልካም የሆነ ጓደኛ  ለቤተሰቦቹም ለአንተም ቤተሰብ ጭምር አሳቢ የሆነ ትልቅ ዋጋ ያለው ጓደኛ ነው
የሰው ልጅ ብቻውን መቸም ሊኖር አይችልም ደካማ ነው ምን አልባች እንኳን እረፍትን ፈልጎ ለ2 ለ3 ቀን ብቻውን ሊሆን ይችላል ከዛብሗላ ግን የጓደኛ ምንነት ይገባዋል ጭርታና ብቸኝነት ሲያጨናንቀው ሰው ይፈልጋል ። ምክንያቱም ሰው ለሰው ከጭንቅ መውጫ ሰበብ ነው በተለይ መልካም ሰው ከሆነ ።
ጥሩ ጓደኛ ማለት በእስልምና ላይ ያገኘኸው ወንድምህ ወይንም አህትሽ ናት ። 
ወንድማማችነት እስልማናውስጥ  ከሌሎች ጋር ባለው የባህሪ ትስስር የተመሰረተ ነው    .......     .... .
ብቻ በቀላሉ እንኳን አናውራ ከተባለ ስለጓደኝነት ብዙማለት ይቻላል ግን እንደቀላል ባናየው ጥሩነው ።
ከወደድ ነው ለአሏህ ብለን ከውስጣችን እንውደደው ከላሆነ ግን ከምናስመስልበት ብንተወው የተሻለ ነው
ምክንያቱም እሱጋር እውነተኛ ውደታ ሊኖር ስለሚችል በኛ  ማስመሰል እና ጥቃቅን ተግባራት ስንሰራ ልቡ ሊሰበር ይችላል እና  ።
ያአሏህ ለጓደኞቻችን መልካም አድርገን ለኛም መልካም ጓደኛን ወፍቀን  ውደታችንንም ሆነ መለያየታችንን በአንተ መንገድ ላይ ለአንተ ሀያልነት ብቻ አድርግልን ያረብ !
"‏أدعوك بكل ذرة في كياني أن تكفيني هم الدنيا والآخرة وألا تكلني إلى نفسي طرفة عين، أن تقيني شر نفسي وأن ترزقني قرة عين لا تنقطع، أدعوك أن ترضى عني وترزقني الرضا وتجبر قلبي، أدعو بالمغفرة أن تغفر ذنوبي وتقبل توبتي وزلاتي، أدعوك دعوة من تيقن أنه سينال ما يرجوه إذ يدعوك".
🤲
👍1
«በዚህ ዘመን፣ በድኗ ላይ ጸንታ የምትኖር ሴት ልዩ በሆነ ውበት ትታያለች፤ ውበቷም በቁጥብነቷ፣ (በአይነፋርነቷ)፣ በሀቅ ላይ ባላት ጽናት እና በስውርም ሆነ በግልጽ ሁኔታ አላህን በመፍራቷ ይገለጣል።
እንደ ዘመኗ ሴቶች ለመሆን አትጥርም፤ ከዚያ ይልቅ አላህ ከሚወዳቸው ባሮቹ መካከል እንዲያደርጋት ትለምነዋለች። »

=
t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ሴትነት ከምንም አያግድም! ይች ማሳዉ ላይ የምታጭደዉ ጀግኒት ሴት ነች! ባሏ በቅርቡ ወደ አኼራ የሄዴ ሶስት ነፍስ ያላወቁ ህፃኖች ጥሎ የሞተ ግን እሷ ልጆቼ ፆም አያድሩም ብላ ይሄዉ እንደምታይዋት አጨዳዉን ይዛዋለች ብርቱ ሴት በርችልኝ ጀግኒት💪👈

=
« ከአንድ ወንድ ጋር የሚኖርሽ ጋብቻ ማለት በሕይወት ጉዞ ውስጥ አጋር ማግኘት ብቻ አይደለም፤ በአላህ ፈቃድ አንዱ ለሌላው ሰላም፣ መጠጊያና ድጋፍ መሆን ነው። በደስታሽ ከአንቺ ጋር የሚደሰት፣ በችግርሽ ከጎንሽ የማይርቅ፣ ስትደክሚ በርኅራኄ የሚደግፍሽ፣ ስትጨነቂም በጥሞና የሚያዳምጥሽ ባል ማግኘት ነው።
አላህን የሚፈራ፣ በአንቺ ላይ ያለውን አደራ የሚያውቅ፣ መብትሽን የሚጠብቅ፣ በክብርና በመልካም አያያዝ የሚኖር ወንድ። እንከን የለሽ ሰው ሳይሆን፣ ስህተት ሲፈጽም ይቅርታ የሚጠይቅ፣ ሲሳሳት ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመመለስ የሚጥር፣ በችግርም ጊዜ ከአላህ ጋር ተያይዞ ከአንቺ ጋር የሚታገስ ሰው።
በዓይኑ ውስጥ ክብርሽን የሚያይ፣ በልቡ ውስጥ ፍቅርሽን የሚያሳድር፣ በቤቱም ውስጥ ሰላምና ምሕረትን አብሮ የሚገነባ። አብሮ መኖርን ብቻ ሳይሆን፣ በኢማን አብሮ ማደግን፣ አንዱ ሌላውን ወደ መልካም ሥራ መጋበዝንና በአላህ ፈቃድ ወደ ጀነት አብሮ ለመድረስ መተጋገዝን የሚመኝ የሕይወት አጋር።

ምክንያቱም አላህ በቁርአን ላይ እንዲህ ይላል፦
«وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً»

«ከተዓምራቱም መካከል ከነፍሳችሁ የሆኑ ሚስቶችን ለእናንተ መፍጠሩ፣ ወደእነርሱም ሰላምን እንድታገኙ ነው። በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን አደረገ።»
(ሱረቱ አር-ሩም፣ 30፡21)

«የሚያምር ጋብቻ ማለት አንዱ በሌላው ውስጥ ሰላምን ማግኘት፣ በፍቅር መኖር፣ በእዝነት መተያየትና አላህን በመታዘዝ አብሮ ወደ ጀነት የሚያደርስ ጉዞ መጓዝ ነው።

=
t.me/https_Asselefya1
👍6
" የልብሽን ሰላም እንዲያውክ ለማንኛውም ነገር ዕድል አትስጪ። በሕይወትሽ ላይ መልካም ነገር የማይጨምሩትን ከሕይወትሽ አስወግጂ፤ የሚጎዱሽን ግንኙነቶች፣ ተስፋሽን የሚያስቆርጡ ንግግሮችንና ከአእምሮ ሰላምሽ የሚያርቁሽን ሁሉ ተይ።
ምክንያቱም ሁሉም ነገር በሕይወታችን ውስጥ መቆየት አይገባውም፤ አንዳንድ ነገሮችን መተው ራሱ ትልቅ እፎይታና የልብ ሰላም ነው።

=
t.me/https_Asselefya1
👍20
" አንዳንዴ አላህን የማያውቁ፣ ወደ እርሱም መመለስን የማያውቁ ሰዎች የሕይወትን ፈተና እንዴት እንደሚቋቋሙ እገረማለሁ ልባቸው በሐዘን ሲሰበር፣ መንገዳቸው ሲጠብ፣ ዓለም በሙሉ የተዘጋባቸው ሲመስላቸው ወደ ማን ይሸሻሉ? በድካም የተሞላው ቀናቸው ሲያበቃ ልባቸውን በማን ፊት ያስቀምጣሉ? ማንስ ያዳምጣቸዋል ማንስ ያረጋጋቸዋል?እኛ ግን ምንኛ ዕድለኞች ነን! በማንም ፊት ማስረዳት የማንጠብቅበት፣ በእንባ ብቻ እንኳን የልባችንን ቋንቋ የሚረዳ፣ የምንጠራውን የሚሰማን ጌታ አለን!

"ሌሊት ሁሉም ሲተኛ «ያ ረቢ፣ እኔ ደክሞኛል፣ አንተ ግን ሁሉን ታውቃለህ» ብለን ልባችንን ለእርሱ ማውራት እንችላለን። ሰዎች ቢተዉንም አላህ አይተወንም፤ በሮች ቢዘጉም የእርሱ በር ክፍት ነው።

አልሐምዱሊላህ አላኒዕማተል ኢማን! አላህን ማወቅ፣ እርሱን መውደድና በእርሱ መተማመን ከዱንያ ሀብቶች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ፀጋ ነው። አላህ ከሚያስታውሱት፣ በእርሱ ከሚተማመኑትና በዚክር ልባቸው ከሚረጋጋው ባሮቹ ያድርገን። አሚን ያ ረበል ዓለሚን!


=
👍8