💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ዒልም
Daru tewhid
እውቀትን ከመፈለግ ከሚያግዱን ነገራቶች በጥቂቱ ....?

🎙በኡስታዝ አቡል አባስ ሓፊዘሁላህ

t.me/Darutewhide
قهر الهوىٰ= الجنَّة.

﴿وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى ۝ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَى﴾ .
👍7
✅ ነፍሱ ከዒባዳ መሰላቸቷን ያስተዋለ፤ኢስቲግፋር ያብዛ። ማንኛውም ሰው ዒባዳን መፈፀም የሚሳነው በሰራው ወንጀል ምክንያት ነው።
أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ الْعَظِيمَ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ، وَأَتُوبُ إِلَيْهِ.
~
t.me/https_Asselfya
👍5
ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
👍14
ለ ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ባለቤቶች

የሱና ቻናል ተደራሽነት ይበልጥ ይሰፋ ዘንድ
የቻናል ሊንክ መላክ ትችላላችሁ  ⚡️

✍️መስፈርት 1/ :- የሱና ቻናል ሊሆን ስለማጣራ⚫️
✍️መስፈርት2/ ከ1k member በላይ 🔤 ከዛበታች ❌
✍️መስፈርት 3/:-  ቻናሉን አይቼ አሳውቃቹኋለሁ

🚫ግሩፕ አልቀበልም❌

⭐️ @twhidfirst1 ✅
🌟 @twhidfirst1 ✅
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5
🌻فَإِنَّ اصِّدْقَ طُمَأنينة وإِنَّ الكزِب رِيبة
📚رواه الترمزي

~እዉነት የአእምሮ እርፈት እና መረጋጋትን ይሠጣል። ዉሸት ደግሞ የአእምሮ መረበሸ እና መጥፎ ጥርጣሬን ያስከትላል።

t.me/https_Asselfya
👍8
ሙሓደራ 215 ምክር ለ ቁርዓን ሓፊዞች.mp3
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ሙሐደራ 215 

ለ ቁርዓን ሓፊዦች የተደረገች ምክር

🚦🚦 አሸዋሜዳ በሚገኘው የ ወንድማችን ሳዳት ከማል የ ቁርዓን ሒፍዝ ማእከል ላይ የተደረገ  ነሲሃ ነው  ።

🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/UstazKedirAhmed
ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَطۡمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكۡرِ ٱللَّهِۗ أَلَا بِذِكۡرِ ٱللَّهِ تَطۡمَئِنُّ ٱلۡقُلُوبُ (الرعد ٢٨)


እነዚያ ያመኑት አላህን በማዉሳት ልቦቻቸው ይረጋሉ። አዋጅ ንቁ!

አላህን በማዉሳት ልብ ትረጋጋለች!
«سُبْحَانَ اللهِ ،
وَالحَمْدُ للهِ ،
وَلَا إلَهَ إلَّا اللهُ
، وَاللهُ أكْبَرُ
، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ»


       t.me/https_Asselfya
👍2
قال تعالى :
{وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُمْ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ}.
[سُورَةُ الرُّومِ: ٢٥] .

فَجَعَلَ الْمَرْأَةَ سَكَنًا لِلرَّجُلِ، يَسْكُنُ قَلْبُهُ إِلَيْهَا، وَجَعَلَ بَيْنَهُمَا خَالِصَ الْحُبِّ، وَهُوَ الْمَوَدَّةُ الْمُقْتَرِنَةُ بِالرَّحْمَةِ.

[الداء والدواء ٢٣٧].

t.me/https_Asselfya
👍6
🔖እውቀትን መፈለግ ያለው ቱርፋት
~ ~
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
፦

👉እዉቀትን በመፈለግ ላይ የተጓዘ ሰዉ አላህ  ለሹ የጀነትን መንገድ ያገራለታል ።

~የአላህ መልክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል፣

~አላህ መልካም የሻለት የሆነ ሰው ድኑን ያስገነዝበዋል።

👉በተቃራኒዉ ሟር የሻበትን ሠዉ ድንን አያዉቅም።ዲንን  ለማወቅ ችልተኛ ይሆናል።

t.me/https_Asselfya
👍5
በስደት ያላችሁ በተለይ ሴቶች ወላሒ በጣም ተጠንቀቁ በጣም ነገሩ ከሚባለውም በላይ እጅግ የከፋና የከረፋ ሆኗል።

.....ዝሙት⁉️

ነቄነት ተደርጎ ዝሙት እንደ ሀላል፡
መብቴ ነው ሲባል እንደምን ያስጠላል!?
ጥርስን ካልሸፈነ ምን ይሰራል ከንፈር፡
ነውራችን ከረፋ ኸረ ተው እንፈር⁉️
ማን ከማን ተሽሎ ማንን ነው ምታሙት፡
የእለት ከእለት ስራ ሰርክ ሆኗል ዝሙት‼️

.......✍️ኑር

ትላንት ከዝሙት ስለመጠንቀቅ ማሳሰቢያ የፃፍኩት ዐረብ ሃገር ላይ እየተፈፀሙ ስላሉ ጥፋቶች የሚገልፁ አስደንጋጭ ጥቆማዎችን ከተለያዩ ወንድሞች ስላየሁ ነው። ከላይ ያያያዝኩት መልእክት ወንድማችን ከኔ ፖስት ስር ያስቀመጠው እጅግ አስደንጋጭ ትዝብት ነው። እንዲህ አይነት ወጥመዶች ወንጀሉ መቋጫ እንዳይኖረው ነው የሚያደርጉት። የመፍትሄው ሁሉ ቁንጮ አላህን መፍራት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
👍4
الإكثار من المال والرزق - الرحيلي
t.me/al3olma
☑️ አላህን መፍራት የሪዝቅ መሠረት ነዉ።
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
🔍
ሀሳቡና ጭንቁ ዱንያ ብቻ የሆነ ሰው፣ ጉዳዩን አላህ ይበታትንበታል፣ ድህነቱን በዓይኑ መሀል ያደርግበታል፣ ከዱንያም የተቀደረለት እንጂ አይመጣለትም።

🔍 ሀሳቡና ጭንቀቱ አኼራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃትን በቀልቡ ያደርግለታል። ጉዳዩን ይሰበስብለታል። ዱንያ የግዷ ወደሱ ትመጣለች።

አድምጧት ጣፋጭ ምክር !
=
t.me/https_Asselfya
👍7
🔖ሀሰነል በስርይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብሏል።

አላህን ሳይታመፅበት ያለፈ ቀን ሁሉ ኢድ ነው። አንድ ሙእሚን አላህን በመታዘዝ፣ እሱን በመዘከርና በማመስገድ ያሳለፈው ቀን በሙሉ ኢዱ ነው።
📚لطائف المعارف لابن رجب

=
t.me/https_Asselfya
👍2👎1
🔖ኢማም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

"وقـد ضمـن اللَّـه سبحانـه لڪلّ مـن عمـل صالحـا أن يحييـه حيـاة طيبـة وهـو صـادق الوعـد لا يخلـف وعـده".

አላህ መልካምን ለሰራ ሰው ሁሉ ያማረ ህይወት እንደሚያኖረው ዋስትና ሰጥቶታል የእሱ ቃል እውነት ነው ቃሉን አያፈርስም።

📚[አዳእ ወደዋእ]
👍9
~"አላህ ከከለከለው ነገር እይታን ዝቅ ማድረግ፣ የአላህን ዉዴታ ይወርሳል።"

=
وخَيرا في كل أمرٍ ننتظِرُه يا الله!
🔖አላህ ዘንድ ሰዎች የበላይ የሚሆኑበት የእውቀት ዘርፍ# ሸሪዓዊ እውቀት ነው።

ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ دَرَجَٰتٍۢ ۚ

አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡

(ሙጃዲላ 11)

t.me/https_Asselfya
👍5