💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
"እኔ" ገደል እንዳይከተን
~
"እኔ እኔ" ሲበዛ ለሰሚው ያቅለሸልሻል። ድንበርም ያስታል። ለራስ የተጋነነ ግምት ማሳደር ጎንበስ ብሎ ለመማር እንቅፋት ይሆናል። በ "እኔ" የተለከፈ ማንነት ከኢኽላስ ጋር የመጣላቱ እድል ሰፊ ነው። እዚህ ላይ አንድ የሚደንቅ የሶሐቦች ስብእና አለ። ከሚያስተላልፏቸው ገድሎች ውስጥ የራሳቸው ሲሆን ጊዜ "አንድ ሰው እንዲህ አድርጎ" በማለት እንደዋዛ የአንድ ማንነቱ የማይታወቅ ሰው ጉዳይ በሚመስል መልኩ የሚያቀርቡበት ሁኔታ አለ። ታሪኩ በሌላ አቅጣጫ ሲፈተሽ ግን የራሳቸው ገድል ሆኖ ይገኛል። ሱብሓነላህ!

ኢኽላስን ለማረጋገጥ፣ ስግብግብ ነፍስያን ለማሸነፍ፣ በራስ ፍቅር ክንፍ ከማለት ለመዳን "እኔ፣ እኔ" በሚል ክፉ ስሜት ላይ ጦርነት ማወጅ ያስፈልጋል። ነፍሲያን ጉሮሮዋን አንቆ መያዝ። የኢኽላስ ነገር ለነፍሲያ ፈተና ነው። የአንድ ሸይኽ ደርስ ላይ የሚገርም ገጠመኝ ሰማሁኝ። የሆነ ሰው ሌሊት እየተነሳ ሶላት መስገዱ ማንም ዘንድ አለመታወቁ ይከነክነዋል። እና በብልሃት ሰጋጅነቱን ማሳወቅ ፈለገ። ፋርማሲ ገባና

* "በሌሊት ሶላት ምክንያት ለሚሰማ ድካም የሚሆን መድሃኒት አለህ ወይ?" ብሎ ይጠይቃል።
- "የለኝም" አለው።
* "እሺ ሷሊሖችን ትውዳለህ'ንዴ?" ብሎ ይጠይቀዋል።
- ፋርማሲስቱ ነገሩ ቢገርመው አሳለፈው።
* "ለማንኛውም ሷሊሖችን ውድድ አላህ ይወድሃል" ብሎት ወጣ።

"እኔ" ይሉኝታ ያሳጣል።
"የኔ" ስግብግብ ያደርጋል።
"እኔ ዘንድ" ትእቢት ያወርሳል።

እነዚህ ስሜቶች ልባችንን እንዳይቆጣጠሩ መጠንቀቅ ይገባል። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
" 'እኔ'፣ 'የኔ' እና 'እኔ ዘንድ' ማለት ድንበር እንዳያልፍብህ መጠንቀቅ ይገባል። እነኚህ ሶስት ቃላት ኢብሊስ፣ ፊርዐውን እና ቃሩን ተፈትነውባቸዋል።
👉🏾 'እኔ ከሱ በላጭ ነኝ' የሚለው የኢብሊስ ነው።
👉🏾 'የግብፅ ግዛት የኔ ነው' የሚለው የፊርዐውን ነው።
👉🏾 '(ሀብቱን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው' የሚለው የቃሩን ነው።

➡️ 'እኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'እኔ ባሪያ ነኝ'፣ 'እኔ አጥፊ ነኝ'፣ 'እኔ ምህረትን ለማኝ ነኝ'፣ 'እኔ ወንጀለኛነቴን የማምን ነኝ'፣ ... በሚለው የባሪያ ንግግር ውስጥ ነው።
➡️ 'የኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'የኔ ወንጀል'፣ 'የኔ ውርደት'፣ 'የኔ ድህነት' በሚለው ውስጥ ነው።
➡️ 'እኔ ዘንድ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ ደግሞ 'ምሬንም ሆነ ቀልዴን፣ ስህተቴንም ሆነ አውቄ የፈፀምኩኑን ምህረት አድርግልኝ። ይሄ ሁሉ እኔ ዘንድ አለና' በሚለው ውስጥ ነው።"

📖 [ዛዱል መዓድ]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
~ምቀኝነት ከእውቀት ማነስ የሚመነጭ
ትልቅ የአዕምሮ ድህነት ነው!

~
هل يوجد فرق بين مشركي زماننا و المشركين الأولين ‼️
Anonymous Quiz
87%
نعم
13%
كلا
አንድ ሰው እንደት እንደዚህ ደስተኛ ሂዎት ሊኖርህ ቻለ ተብሎ ሲጠየቅ
አላህን በድብቅ ማመጽ ትቸ ብሎ መለሰ!
ብዙዎችን የከበደው. ይህ ነው።

~
سعادة المرأة في تغطية الوجه!!
Audio
ወንጀሎችን መራቅ ተውሂድን ከማረጋገጥ ውስጥ ነው

አጭር ምክር ሙሐመድ ሲራጅ
https://t.me/MedrestuImamuAhmed

https://t.me/Muhammedsirage
Forwarded from أَبُوْ سَهْلَة مُصْطَفَى سَعِيْدٍ الْجُنَيْدِي
ቆንጆ ግጥም ማሻአላህ

#አስመሳይ #አግብቼ

አስመሳይ አግብቼ ግራ ከምጋባ፣
ተደብቄ ልኑር ልቅር ሳላገባ።
ተመሳሳይ ኮፒ በመቅረቷ አልባባም፣
እምነት አሰዳቢ ፍፁም አላገባም።
የአላህን ትዕዛዝ ሂጃቧን አድርጋ፣
ከተጨማለቀች ከአጂነብይ ሰው ጋ፣
እሷን አላገባም ከቶ ቁሜ ልቅር፣
በብቻየ አለም ውስጥ ተደብቄ ልኑር።

አቂዳየ እያለ ምን አለው ካለችኝ፣
እስልምናየን ይዤ ድሃ ካረገችኝ፣
መስፈርቷ ከሆነ ቤት ና መኪና፣
ኒቃቢስትም ብትሆን ብትሄድ ተሸፍና፣
ትቅርብኝ ይች ልጂ እኔ አላገባትም፣
ኪታቤን አዝየ ሄዳለሁ የትም።

እውቀት ፍለጋየን አቀጣጥላለሁ፣
እምነት አሰዳቢ ለምን አገባለሁ።
ጀግና የጀግና ልጂ በመንሀጂ ያደገች፣
በሰለፎች አሰር አምራ የደመቀች፣
አላህ ከገጠመኝ ውብ ትዳር ፈላጊ፣
አስተዋይ መካሪ ንደት አረጋጊ፣
የሙብተዲ ጥላት ጦረኛ ተዋጊ፣

ሽርክን አፈራራሽ የተውሂድ ምርኮኛ፣
የቢድአ ካንሰር የሱና ሱሰኛ፣
እምነቷ ሲደፈር የሚያንዘረዝራት፣
ከእግር እስከ ራሷ ንደት የሚወራት፣
በአቂዳዋ ታጋይ ጀግና አርቆ አሳቢ፣
የእህቶቿ ሞደል በሂጃብ ተዋቢ፣

ከመጥፎ ከልክላ በመልካም ላይ አዛዢ፣
ውዲ ባልተቤቷን በፍቅር አደንዛዢ።
ለረጂሙ ጉዞ ስንቋን የሰነቀች፣
በተውሂድ በሱና በሀቅ የደመቀች።
ከመንሀጀ ሰለፍ ሁሌ የማትለወጥ፣
ያወራ ቢያወራ ልቧን የማትሰጥ።

ይህችን መሳይ ሞደል ታስፈልገኛለች፣
እህትም ፣ባልተቤት እናት ትሆናለች።
ችግሩ እሷ ግን የት አለች የት አለች፣
ልፈልግ በዱኣ ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም፣
እምነት አሰዳቢ አልለማመጥም፣
ተውሂድ ያልገባት ልጂ አርፋ አትቀመጥም።

ያ አላህ
እኔንም አድርገኝ ከነጓደኞቼ፣
ቀጥ ብየ የምሄድ አንተኑ ፈርቼ።
ሀቅ የምገልፅበት ስጠኝ እምቅ ወኔ፣
ተውሂድ ላስተምረው ይጠቀም ወገኔ።
ጀግናይቱ የት አለች ለባሽ ጥቁር ካባ፣
ብቸኝነት ይብቃኝ አትፈትነኝ ላግባ።
.     ╭─•••─═••••••═─•••─╮
.    🌺 እንኳን ደህና  መጡ 🌺     
.     ╰─•••─═••••••═─•••─╯
❝አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ❞

«ስለ ቀልባችን» የቻናሉ ዓላማ ምንድን ነው?
|
~በዚህ ዘመን በብዙ የዓለም አካባቢዎች ላይ በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ የአላህ ፍራቻ ሁኔታ ወርዶ ታይቷል፡፡ የዚህ ሁሉ መንስኤው የግሎባላይዜሽንና ቴክኖሎጂ ተጽእኖ ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ የኢንተርኔት መስፋፋት፣ በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል የሰዎች በእጅጉ መቀራረብ ደግሞ ጉዳዩን የበለጠ አወሳስቦታል፡፡ በዚህም ምክንያት የብዙው ሰው ቀልብ አደገኛ በሆነ የኢማን ድርቅ በመመታቱ መጥፎና ጥሩን መለየት ተስኖታል፡፡ ይህ ሁኔታ ወደፊትም በዚሁ መልኩ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይመስላል፡፡

•የዚህ ቻናል ዓላማውም ይህን ድርቀቱን ለመቋቋምም ሆነ ለማከም ሰበብ ይሆን ዘንድ አላህ ያገራልንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከ ቁርኣን እና ከሀድስ መድሐኒቱን ለመጠቆም ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው።

Ⅱ-ስለሆነም በዚህ ቻናል ላይ፦
➜ ልብ የሚያረጥቡ አጫጭር ፁሁፎች፣
➜ ከ ቀልባችን ጋር የተያያዙ የሙሓደራ ፕሮግራሞች፣
➜ ከ ረቃኢቅ እና ከ አደብ ጋር የተያያዙ የቂርኣት ደርሶች፣
➜ አጫጭር የሆነ የሰለፎች ንግግር ከነ ትርጉሙ፣
➜ አጫጭር የቀደምቶች ታሪኮች፣
➜  በቻናሉ በቀጥታ ስርጭት ብሮድካስት የሚደረጉ መሰናዶዎች…

☞እንድሁም የተለያዩ ቁም ነገር አዘል ፕሮግራሞችን በሰፊው ለመስራት አስበናል።―ኢንሻ አላህ!―
t.me/Sle_Qelbachn
t.me/Sle_Qelbachn
👆አስተማማኝ ሂፍዝ ለመሀፈዝ
ከሚረዱን ነገሮች 5ቱን
ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ ٱللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ ٱللَّهِ تَطْمَئِنُّ ٱلْقُلُوبُ
~እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

👉እርካታ ሲለካ በዚክር ነዉ ለካ!!

=
~ትዳር ማለት ከመጥፎ ነገር  ከዝሙት ያልተፈቀደ ከማየት ያልተፈቀደ ከመንካት የምንቆጠብበት የአላህን ድንጋጌእንጂ!ሚስትህን እያስቀየምክ በሚዲያ እየዋሸህ ሌሎችን ልብ እምሠርቅበት የስዳዶች መድረክ አይደለም።

~ትዳር ማለት እሾህ ያለዉ አበባ ነዉ።ፍሬ እንዲያፈራልህ ከፈለክ የእሾሁን ዉጋት መታገስ አለብህ።እሾሁ አንዳንዴ ያለመግባባት ሲሆን ያኔ ታጋሸ ሁን። አበባ እዉነተኛ ፍቅር ሲሆን እዉነተኛ ባልሆነ አበባዉን ቅዘም ፍሬዉ የአብራክህ ክፋይ ልጆች ሲሆኑ ለልጆችህ እዉነተኛና ጀግና አባት ሁነህ በተርቢያ አሳድገህ የፍሬዉ ባለቤት ሁን።

=

t.me/https_Asselfya
~ኑ እንተዋወስ .
መልካም እንጋራ .
ድናችንን እንወቅ.
አለብን አደራ!!

~
~ኢማንህ ከፍ ሲል ከአላህ እርዳታ ዉጭ አንድም ነገር ሊሳካ እንደማይችል ሲገባህ ሁሉን ነገር ለፈጣሪህ ለአላህ ሱብሀነሁ ተአላ ትሠጣለህ።የማትችለዉንም የምችለዉንም ሁሉ አንድ ሳታስቀር ታስረክባለህ። ገር ነገር ጭምር ሊገራልህ የሚችለዉ አላህ ሲያገራልህ ብቻ ነዉ።

~መጥፎዉን ነገር ልትጠላ የምችለዉ አላህ ያንን ነገር ያስጠላህ እንደሆነ ብቻ ነዉ። አላህ ካላስጠላህ ወንጀሉ ፅድቅ መጥፎ ነገር ጥሩ መስሎ ይታይሀል። ለዚህም...

وَكَرَّهَ إِلَيْكُمُ الْكُفْرَ وَالْفُسُوقَ وَالْعِصْيَانَ ۚ
ክህደትንና አመጽንም እንቢተኛነትንም ወደናንተ የተጠላ አደረገ፡፡

~ወንጀልን ሲጥልብህ መዉደቅን ሲሻብህ ፅድቅ ወንጀልን ያጎራብተሀል።ከበጎ አዉጥቶ ወንጀልን ያዛምድሀል።መልካም አስጠልቶ ቆሻሻን ያስወድድሀል።#ቀልብህ ሲደነድን የትም ይሁን የትም አላህን አፈራም።በመስጅድ ይሁን በተቀደሠዉ ምድር ድንበርን አታከብርም።ሰዉንም ሆነ ፈጣሪህን አታፍርም።#በእርግጥ ወንጀል ምን ያህል እንደሚያደነድን የሚገባህ #የአላህን ቤት ካእባን ለመዘየር #ለሐጅ ብለዉ የሄዱትን ሴቶች የአላህን ባሪያዎች ጠዋፍ ላይ የሚጓነትሩትን ስታይ ነዉ።

አንተ ልብን እንደፈለክ የምታገላብጥ ጌታ ሆይ ! ልቤን በዲነል ኢስላም አፅናልኝ!!
=
t.me/https_Asselfya
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎

ዉድ የተከበራቹህ ወንድምና እህቶች በአሏህ ፍቃድ አዲስ ተከታታይ ትምህርት በቅርቡ እንጀምራለን። سلسلة الأخلاق الإسلامية ተከታታይ ኢስላማዊ ሦነ-ምግባሮች

በትምህርቱ የሚዳሱ የሦነ-ምግባር ርዕሶች ለሁለት እንከፍላቸዋለን ¹መልካም ሦነ-ምግባር እሱም 53 ርዕሶች አሉት↓
1 إحسان 2 ألفة 3 أمانة 4 إيثار 5 بر 6 بشاشة 7 التأني 8 التضحية 9 التعاون 10 التواضع 11 التودد 12 الجود والكرم والسخاء والبذل 13 حسن الظن 14 حكمة 15 حلم 16 حياء 17 رحمة 18 رفق 19 ستر 20 سكينة 21 سلامة الصدر 22 سماحة 23 شجاعة 24 الشفقة 25 الشهامة 26 صبر 27 صدق 28 صمت 29 عدل 30 عزة 31 العزم والعزيمة 32.العفة 33 العفو والصفح 34 علو الهمة 35 الغيرة 36 الفراسة 37 الفصاحة 38 الفطنة والذكاء 39 القناعة 40 كتمان السر 41 كظم الغيظ 42 المحبة 43 المدارة 44 المروء 45 المزاح 46 النبل 47 النزاهة 48 النشاط 49 النصرة 50 النصيحة 51 الورع 52 الوفاء بالعهد 53 الوقار
²መጥፎ ሦነ-ምግባር እሱም 47 ርዕሶች አሉት↓
1 الإساءة 2 الإسراف والتبذير 3 الافتراء والبهتان 4 إفشاء السر 5 الانتقام 6 البخل والشح 7 البغض والكراهة 8 التجسس 9 التعسير 10 التقليد والتبعية 11 التنفير 12 الجبن 13 الجدال والمراء 14 الجزع 15 الجفاء 16 الحسد 17 الحقد 18 الخبث 19 الخداع 20 الخذلان 21 الخيانة 22 الذل 23 السخرية والاستهزاء 24 السفه والحمق 25 سوء الظن 26 شماتة 27 الطمع 29 الظلم 30 العجب 31 العدوان 32 الغدر 33 الغش 34 الغصب 35 الغيبة 36 الفتور 37 الفجور 38 الفحش والبذاءة 39 القسوة والغلظة والفظاظة 40 الكبر 41 الكذب 42 الكسل 43 اللؤم 44 المكر والكيد 45 نقض العهد 46 النميمة 47 الوهن

በአሏህ ፍቃድ እነዚህን ርዕሶች በአጫጭር ደቂቃዎች አጠር መጠን ባለ መልኩ በሙሀደራ መልክ አቀርብላቹሃለሁ።

ወንድማችሁ አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/9544
t.me/abu_reyyis_arreyyis/9544