💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.68K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
~ ሶለተል ለይል የሚሠግዱ ሠዎች የአላህ እዝነት"""" ተዉፊቅ"""ማግኘት የሚገባቸዉ ምርጥ ሰዎች መሆናቸዉ። ▪️إِنَّ ٱلْمُتَّقِينَ فِى جَنَّٰتٍۢ وَعُيُونٍ አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ ▪️ءَاخِذِينَ مَآ ءَاتَىٰهُمْ رَبُّهُمْ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَبْلَ ذَٰلِكَ مُحْسِنِينَ ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን…
☑️  የሰጠህን አመስግነህ በፀጋ ተቀበል


📩 لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ
◼️የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡
📩 يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ
◼️ከነገራቶች የሚሻውን ይፈጥራል፡፡
📩يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا
◼️ለሚሻው ሰው ሴት ልጆችን ይሰጣል፡፡
📩وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ
◼️ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡
📩 أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا
◼️ወይም ወንዶችና ሴቶችን ቀላቅሎ ይሰጣል፡፡
📩 وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيمًا
◼️የሚሻውንም ሰው መውለድ እንዳይችል ያደርገዋል፡፡
📩إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ
◼️እርሱ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡

📚(ሱረቱ አል-ሹራ 49 - 50)

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/https_Asselfya
بسم الله الرحمن الرحيم، الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على رسول الأمين، وعلى آله واصحابه اجمعين.
اما بعد:-
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته!


~በጥያቄ ልጀምርረመዳን እንዴት ነዉ እህቴ? ወይኔ ምንም ሳልጠቀምበት ሊያልቅብኝ ነዉ እያልሽ ነዉ ወይስ ምነዉ ቶሎ አያልቅም እንዴ ብለሽ ተሰላችተሻል?
ኢባዳ ፈፅመሽ ፈፅመሽ ከበደሽ እንዴ እህቴ? ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማለት፣ ዱዓ ማድረግ ደከመሽ?

ይሀዉ ልብሽን ላፅናናዉ መጥቻለሁ።


ምንም ያህል ቢደክምሽም፣ ብርታትሽ ቢዝልም እሷ ራሷ ዉስን ቀናት ናትና አትድከሚ እህቴ!

ምኞቱ ጀነት የሆነ ሙእሚን ሰዉ ድካሙን ተቋቁሞ እንደ በረታ ነዉ መቀጠል ያለበትሀሳቡና ግቡ ጀነት የሆነ ሰዉ በጭራሽ ሊደክም አይገባዉም።


እህቴ! ነፍስሽን ኢባዳ ሲከባዳት ልብሽን መታ አድርጊና ‘ጀነትን አትፈልጊም እንዴ?’ በያት። ‘ያቺ ነቢይሽ ያሉባት ሀገር አትናፍቅሽም እንዴ?’ በያት። ‘የነ አዒሻ፣ የነ መርየም፣ የነ ኣሲያ፣ የነ ከዲጃ፣ የነ ፋጢማ ጎረቤት መሆን አያምርሽም እንዴ?’ በያት።

እህቴ ነፍስሽን  ኢባዳ ሲከብዳት ልብሽን መታ
አድርጊና ‘ያን ዉቡን የአላህን ፊት ማየት አይናፍቅሽም እንዴ?’ በያት።
‘አይዞሽ ጥቂት ቀናት ነዉ ከዚያም አላህ ካለ ኺታሙ ጀነት ነዉ።’ በያት።


እህቴ! ያለፈዉ አልፏል። በኢባዳ ጠነከርሽም ተሳነፍሺም የፈፀምሺዉን ይዞ ሂዷል። አሁን የቀረዉ ደግሞ ካለፉት በሙሉ የሚበልጥና በብዙ እጥፍ የሚሻል ነዉ። እናም ከየትኛዉም ጊዜ በላይ መበርታት አለብሽ።

የመጨረሻዎቹ አስርቱ ቀናት ዉስጥ አላህ ለኛ ያስቀመጠለን እጅግ ምርጥ አጋጣሚ አለ። አላህ በአንዲት ሌሊት ዉስጥ ምትፈፀምን ኢባዳ 1000 ወር ከሚፈፀም ኢባዳ በላጭ አድርጓታል። አላህ ብሎ ያቺን ቀን የተወፈቀ ሰዉ በርግጥም መልካም ነገርን ተወፍቋል።

~በምሳሌ ላስረዳሽ…
እንበልና በዚያች ሌሊት ዉስጥ 1ጁዝ ቁርኣን ከቀራሽ ለ1000 ወር 1ጁዝ ከመቅራት በላይ ኸይር ይፃፍልሻል። ከጨመርሽ ይጨመርልሻል።

እንበልና በዚያች ሌሊት ዉስጥ ሁለት ረከዓ ከሰገድሽ ለ1000 ወር ከሰገድሺዉ ሁለት ረከዓ በላይ አጅር ታገኚያለሽ። ከጨመርሽ ይጨመርልሻል።

እንበልና በዚያች ሌሊት ዉስጥ ዚክር ካደረግሽ
ለ1000 ወር ዚክር ከምታረጊዉ በላይ ምንዳ ይፃፍልሻል

እንበልና በዚያች ሌሊት 1ፆመኛን ካስፈጠርሽ ለ1000 ወር ፆመኛን ካስፈጠርሺዉ በላይ ምንዳ ታገኚያለሽ። ከጨመርሽ ይጨመርልሻል።


ባጭሩ እህቴ በቀሩት ቀናቶች ተጠናከሪ በርች ። እንዲሁም በአስርቱ ቀናት ዉስጥ ነፍስያችንን አሸንፈን ከየትኛዉም ጊዜ በላይ በኢባዳ መጠንከር አለብን። አላህ እኔንም፣ አንቺንም፣ አባቶቻችንንም፣ እናቶቻችንንም፣ መላዉ ወዳጆቻችንንም በዚህ ወር ከእሳት ነፃ የተባሉ ሰዎች ያድርገን!

በፆሙ ስላስረዘምኩኝ አዉፍ በዪ!!


በዉስጥ መስመር ከአንድ እህቴ ተልኮልን ነዉ ።ልንጠቀምበት ዘንድ !


t.me/https_Asselfya
ፀሐይ ለመጥለቅ ስታዘቀዝቅ እኛ ሙስሊሞች ደስታ እየጠበቀን መሆኑን እናውቃለን ። አምላካችን ሆይ !  ደስታችንን የተሟላ አድርግልን። አዛኝ ነህና እዘንልን።
أَڪۡثِرُواۡ الاِسۡتِغفَارَ فِي رَمَضَان🌙
ذُبَـٰالَةُۦالقِنۡدِيٖلِ٭🕊
أڪۡثِرُواْ الاِسْتِغفَارَ فِي رَمَضَان


🎙الشَّيۡخ عَبدُ السَّلاَم الشۡوِيعَر حَفِظَه اللَّهُ.

t.me/https_Asselfya
▪️فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّٰجِدِينَ
~ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው ከሰጋጆቹም ኹን፡፡

▪️وَٱعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ ٱلْيَقِينُ
~እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡

📚ሱረቱል አል ሒጅር

=
🔖አማናን መጠበቅ!!

    
👉 የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡‐

“አንድ ሰው ግራ ቀኙን ተመልክቶ የሆነ ወሬ ከነገረህ አማና (ሚስጥር) ነው ማለት ነው።” ጠብቅለት!!

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል

t.me/https_Asselfya
Audio
ቀልብን ለማስተካከል የሚጠቅሙ አንዳንድ ነገሮች

ዛሬ ረፋድ ላይ በሰልሰቢል መስጂድ የተሰጠ ትምህርት

https://t.me/Muhammedsirage
ሰባቱ አጥፊ ወንጀሎች
ኢብኑ/ሙነወር
“ሰባቱ አጥፊ ወንጀሎች”
~
ረመዷን 14/1445 በፉሪ ሰልሰቢል መስጂድ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
ኢብኑ/ሙነወር – ሰባቱ አጥፊ ወንጀሎች
~አስፈላጊ ነገሮች ተጠቅሶበታልስራችንን እየሠራን ብዙ ነገር ማድመጥ እንችላለን ።በርቱ ....

ትንሽ ቁጭ ስንል ቁርአናችንን እንቀራለን አላህ ያግዛችሁ በስተመጨረሻ ጣፋጭ ቁርአን አመጣለሁ

~
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
ኢብኑ/ሙነወር – ሰባቱ አጥፊ ወንጀሎች
~ቀደምቶች ከአላህ ዉጭ ባለነገር በእዉነት ከምምል በዉሸት በአላህ ስም ብምል ይሻለኛል ይሉ ነበር ።

~አሁን ግን በእዉነት በአላህ ስም ተምሎለት አያምንም።እዉነት የሚመስለዉ ከአላህ ዉጭ ባለነገር ሲማልለት ቢሆን እንጅ አጀብ!! ወዳጀ!! አላህን በማመጽ ፍጡርን መታዘዝ የለም ።

....
~ ብስራት ለዉዷ እህቴ !!!


~ ትንሸ ስራ ትልቅ ምንዳ ማለት ይህ ነዉ ...
     
🔖«ከተዉሂድ ቀጥሎ ....ሴት ልጅ አምስት አውቃት ሰላቶቿን ከሰገደች፣
🔖የረመዳንን ወር ከፆመች፣
🔖ብልቷን ከጠበቀች፣
🔖ባለቤቷን ከታዘዘች በምትፈልጊዉ የጀነት በር ግቢ ትባላለች»።

📒ኢብኑ ሂባን በሰሂህ ዘግበዉታል

=
t.me/https_Asselfya
Audio
🛑👉በረመዷን በተቀሩት ቀናቶች ላይ ነፍስን ማስታገስ ....!!

«تصبير النفس فيما بقي من رمضان»


ክፍል ⓵

🎙በአቡ አዩብ ሙሀመድ ሰይድ

=
https://telegram.me/abutoiba