💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
አብዝቶ የሚታገስ
በዉሳኔዉ አይፀፀትም።

~
~ለምን የለይል ሶላት ሲቆም አያድርም ። ምቀኝነት ያለበት ሰው ሰላም የለዉም ።

~
t.me/https_Asselfya
~ወንድ ልጅ ቤት ሊሠራ ይችላል።
ምቹ መኖሪያ የምታደርገዉ ግን ሴት ልጅ ናት።

~
t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
⭕️👉ተከታታይ ስለ ረመዷን አህካም ዳሰሳ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 #ህፃን (ለአቅመ አዳም) ያልደረሰ ልጅና ፃም ↪️ ክፍል ሶስት《0⃣3⃣》 ✅ ህጻን ልጅ ብሉግ (አቅመ አዳም) እስኪደርስ ድረስ ፃም ግደታ አይሆንበትም። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋልና። رُفِع القلم عن ثلاَثَةٍ عَنِ النَّاءِم حتَّ يَستيْقِظ وعنٍِ الصغيرِ يكبُرَ وعنِ المجنُونِ…
⭕️👉ተከታታይ ስለ ረመዷን አህካም ዳሰሳ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
#አቅመ አዳም (بلوغ) የመድረሻ ምልክቶች

↪️{ ክፍል አራት《0⃣4⃣》

📍በወንድም ሆነ በሴት ላይ ማንኛውም የሸሪአ ድንጋጌ ግዴታ (ዋጂብ) የሚሆነው አቅመ አዳም ወይም ብሉግነት ደረጃ ላይ ከደረሱ በኋላ ነው። ብዙ ሰዎች ለአቅመ አዳምነት ደርሰው ነገር ግን ምልክቶቹ በደምብ ካለማወቃቸው የተነሳ ገና ህፃን ነኝ በሚል እሳቦት ሶላት ፃምና ሌሎችም ግዴታ የሆኑ ኢባደዎች ላይ ሲዘናጉ ይታያሉ። በአላህ ፍቃድ እነዚህን ምልክቶች በቅደም ተከተል የምንቃኝ ይሆናል።

💠 ወንድ ልጅ አቅመ አዳም (ብሉግ) መድረሱ የምናውቅባቸው መንገዶች

◼️አንድኛ፦ መንይ (የዘር ፈሳሽ)

~አንድ ሰው ተኝቶም ይሁን ሳይተኛ በየትኛውም መልኩ መንይ (የዘር ፈሳሽ) ከወጣው ከዛን ሰአት ጀምሮ የሸሪዓ ድንጋጌዎች በሱ ላይ ግዴታ ይሆንበታል። ምክንያቱም ይህ ሰው አቅመ አዳም መድረሱ ከሚያሳዩ ምልክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የዘር ፈሳሽ ተገኝቶበታልና።

⭕️👉 ለዚህም መረጃው የአሏህ ሱብሀነሁተአላ ንግግር ነው።
📌وَإِذَا بَلَغَ ٱلْأَطْفَٰلُ مِنكُمُ ٱلْحُلُمَ فَلْيَسْتَـْٔذِنُوا۟ كَمَا ٱسْتَـْٔذَنَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ
ከእናንተም ሕፃናቶቹ ኢህቲላም (የዘር ፈሳሽ ሚያዩበት) ጊዜ ከደረሱ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት (ታላላቆቹ) እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ፡፡
📚 ሱረቱ አኑር (59)

🔹በሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
غُسلُ الجُمُعَةِ واجبٌ على كُلِّ مُحتلمٍ
ኢህቲላም (የዘር ፈሳሽ) የማየት ደረጃ ላይ በደረሱ ሁሉ የጁሙዓ ትጥበት ግዴታ ነው።

📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

◾️ሁለተኛ፦ "ብልት አካባቢ ፀጉር ማብቀሉ"

~ይህ ፀጉር ከርዳድ ያለ ልስላሴ የሌለው ብልት አካባቢ የሚበቅል ሲሆን ይህም አንዱ ቡሉግነት የመድረሻ ምልክት ተደርጎ ይቆጠራል።

⭕️👉 ለዚህ መረጃው አጢያ አልቁረዝይ ፡፡የተባለው ሰሀብይ የተናገረው ንግግር ነው። እሱም እንዲህ አለ፦ "የቁረይዛ ዘመቻ ግዜ በመልእክተኛው ላይ ቀረብን የዘር ፈሳሽ ማየት ደረጃ ላይ የደረሰ ወይም ብልቱ አካባቢ ፀጉር ያበቀለ ሰው ይገደል ነበር ብልቱ አካባቢ ፀጉር ያላበቀለ ሰው ይተው ነበር።
📕ኢማሙ አሕመድና ነሳዒይ የዘገቡት ሶሂህ ሀዲስ ነው።

⭕️👉በኑ ቁረይዛዎች ከየሁድ ጎሳ የሆኑ አደገኛ የኢስላም ጠላቶች ነበሩ። በዚህ በበኑ ቁረይዛ ዘመቻ ጊዜ የተማረኩት እንዲገደሉ ተወስኖ ስለነበረ ለአቅመ አዳምነት ያልደረሱት ግን ይተው አይገደሉም ነበር። ለአቅመአዳምነት ለመድረስ በብልቱ ላይ ፀጉር ማብቀሉ ያለማብቀሉ ታይቶ ካበቀለ ትልቅ ስለሆነ ይገደላል። ካላበቀለ ደሞ ህፃን ነውና ይተው ነበር።

◾️ሶስተኛ፦ አስራ አምስት {15} አመት መሙላት

ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች ውስጥ አንዱ ካልታየ አስራ አምስት አመት እስኪሞላው የሚጠበቅ ይሆናል። ይህ እድሜ ላይ ሲደርስ ግን ቡሉግነቱ ስለሚረጋገጥ በሸሪአ ዋጂብ የተደረጉ ኢባዳዎችን የመስራት ግዴታ ይኖርባቸዋል።

▪️ ለዚህም መረጃው፦
⭕️👉አብደላህ ኢብኑ ኡመር እንድ አለ:- የእሁድ ዘመቻ ጊዜ በዘመቻው ላይ እንድሳተፍ መልእክተኛው ሰለሏሁአለይሂ ወሰለም ዘንድ ቀረብኩኝ። የዛኔ እድሜዬ 14 ነበር። ነገር ግን ለጅሀድ መልእክተኛው አልፈቀዱልኝም። በቀጣዩ አመት ላይ የኸንደቅ ዘመቻ ግዜ መልሽ ቀረብኩኝ። የዛኔ አስራ አምስት አመት ሞልቶኝ ነበርና ዘመቻ ላይ ተፈቅዶልኝ ተሳተፍኩ።
📚( ቡኻሪ ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል።)

~ሴት ልጅ አቅመ አዳም (ብሉግ) መድረሷ የምናውቅባቸው ምልክቶች፦

◼️አንድኛ፦ መንይ (የዘር ፈሳሽ)
◾️ሁለተኛ፦ "ብልት አካባቢ ፀጉር ማብቀሏ"
◾️ሶስተኛ፦ አስራ አምስት {15} አመት መሙላት
◾️አራተኛ፦ ሀይድ (የወር አበባ) ማየት

~ ከላይ ያየናቸው ወንድ ልጅ አቅመ አዳም (ብሉግ) መድረሱ ከሚጠቁሙ ምልክቶች ውስጡ አንዱን ካየች ቡሉግ መድረሷ የሚታወቅ ሲሆን ከወንድ በተጨማሪ ሀይድ ማየት ይገኝበታል።

⭕️👉አንድ ሴት ልጅ በየትኛውም የእድሜ ክልል ደረጃ ላይ ሀይድ ካየች ብሉግነት የመድረሷ ምልክት ስለሆነ በግዴታነት የተደነገጉ የተለያዩ የኢባዳ አይነቶች መፈፀም በሷ ላይ ግዴታ ይሆናል።

⭕️👉ማሳሰቢያ!!
     〰〰〰〰〰
①)–አንድ ሰው ብሉግ ደረጃ ደረሰ ለማለት የግድ ሁሉንም ምልክቶች መታየት አለባቸው አይባልም። ይልቁንስ አንዱን ምልክት ከታየ በቂ ማረጋገጫ ነውና በኢባዳ ላይ የተገደደ ይሆናል።
②)–አንድ ሰው አቅመ አዳምነት ደረሰ ለማለት የግድ አስራ አምስት አመት የሚጠብቁ አሉ ይህ ስህተት ነው። አንድ ሰው የዘር ፈሳሽ ካላየ፣ ፀጉር ካላበቀለ፣ ሴቷም ሀይድ ካላየች ያለው አማራጭ አስራ አምስት አመት መጠበቅ ነው። ነገር ግን በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ አንዱን ምልክት ቀድሞ ከታየ ያ በቂ ነውና ብሉግ ደረሰ ይባላል።
③)–አንድ ሰው ረመዷን ውስጥ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ብሉግ መድረሱን ካረጋገጠ መጀመርያውኑ ፃሞ ከነበረ በዛው ፃሙን ይቀጥላል። ፃመኛ ካልነበረ ደሞ ከዛ ሰአት ጀምሮ ከምግብና መጠጥ መታቀብ ይኖርበታል ነገር ግን ቀዷ የማውጣት ግዴታ የለበትም።
            ፧              ፧
            ፧              ፧
    t.me/https_Asselfya
   
t.me/https_Asselfya
~ጣፋጭ ቲላዋ

በቁርአን እንገሠፅ

~
ውድ ወንድሞችና እህቶች መቸም አዝካረ ሶባህ እንደማትረሱ ተስፋ አለኝ ።
ዚክር የደረቀችን ልብ ያረጥባል የረጠበች ልብ ይበልጥ ወደ አላህ እንድትቀርብ ያደርጋታል።


🖊ወንድማችሁ አቡ ዓኢሻ ነኝ
https://t.me/Abuebrahim22322
~አላህ ጋ መገናኘትን የወደደ አላህ ከሱ ጋ መገናኘትን ይወዳል።ከአላህጋ መገናኘትን የጠላ አላህም ከሱጋ መገናኘትን ይጠላል።

የአላህ መልእክተኛ ይሄን ሲሉ እናታችን አኢሻ እንድህ አለች ፦ሞት ጥላቻ ነዉን?ሁላችንም ሞትን እንጠላለን አለቻቸዉ የአላህ መልእክተኛ ይህ አይደለም አሏት።ነገር ግን አማኝ ጣራ ሞት ሲደርስ በአላህ ራህመት ፦በአላህ ዉዴታ በጀነት እፊቱ ተመስሎለት ቁጭ ይልለታል።ስለዚህ አላህን መገናኘት ይወዳል። በዚህ ተቃራኒ ጠማማዉ ጣራሞት ሲደርስ ፊለፊቱ ጀሀነም የአላህ ቁጣ ቅጣት ስለዚህ አላህን መገናኘት ይጠላል።አላህም ከሱጋ መገናኘትን ይጠላል።

إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُوا۟ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسْتَقَٰمُوا۟ تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا۟ وَلَا تَحْزَنُوا۟ وَأَبْشِرُوا۟ بِٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ

~
~የኪስ አውላቂን ሌባ ከምንጠነቀቀው በላይ ,የአቂዳን አውላቂ  ተሽሎክሏኪ ሌባን እንጠንቀቅ።

t.me/https_Asselfya
⭕️👉ተከታታይ ፅሁፍ ስለረመዷን አህካም ዳሰሳ...!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
【ክፍል አንድ】
t.me/https_Asselfya/8066
t.me/https_Asselfya/8066

【ክፍል ሁለት】
t.me/https_Asselfya/8074
t.me/https_Asselfya/8074

【 ክፍልሶስት】
t.me/https_Asselfya/8084
t.me/https_Asselfya/8084

【ክፍል አራት】
t.me/https_Asselfya/8097
t.me/https_Asselfya/8097

~አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰዉ ያደርጋል።
🍃 يَا مَرْيَمُ اقْنُتِي لِرَبِّكِ وَاسْجُدِي وَارْكَعِي مَعَ الرَّاكِعِينَ

«መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፡፡ ስገጂም፡፡ ከአጎንባሾቹም ጋር አጎንብሺ፡፡»

                  አል-ኢምራን (43)

t.me/https_Asselfya
🔖የቻለ ከነገ ሀሙስ ጀምሮ ... እስከ ሰኞ ይፁም ።
➀الخميس
➁الجمعة 13
⓷السبت 14
➃الأحد 15
➄الإثنين
لمن استطاع صيامهم

~አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና ኢባዳን በማሳመር ላይ አግዘኝ"።

~