💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Photo
📍የሒጃብ ጥፍጥና⁾
                { እና }
⁽❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾

👉🔖ክፍል አንድ

▪ስለሒጃብ የመጀመሪያው ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ

⓵.
የእኔ ንፅሕና እና መልካም ስራዬ የሚገለፀው ሒጃብ በማድረጌ ሣይሆን በአለኝ ጥሩ ፀባይ ነው። ለምሣሌ፦ ብዙ ሂጃብ . ኒቃብ .ጅልባብ የሚያደርጉ ታላላቅ የሚባሉ ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሴቶች ያሉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሒጃብ ሣያደርጉ/ሣይለብሱ ጥሩ ፀባይ እና ከፍተኛ ስነምግባር ያላቸው ሴቶች አሉ! የሚል አስተሣሰብ አራማጅ መሆን ነው።

↘️ይህ አይነት እስተሳብ ላለን እህቶች መልስ፦
▪
ሂጃብ መልበስ ንፅህናና ጨዋነት ተጠቃለው የሚሟሉበት ደንብ ወይም ህግ አይደለም ። ንፅህናና ጥሩ ስነ-ምግባር በኢስላማዊ ሸሪዓ ግደታወች ሲሆኑ በዚህም ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ሊያሟሉዋቸውና ሊተገብራቸው ግድ ነው።ሆኖም እነዚህን የማሟላቱ ሂደት ሂጃብ በመልበስ እና ባለመልበስ ላይ የተመካ አይደለም።ስለሆነም ሂጃብ የለበሰች እንስት መጥፎ ነገር ⁽⁽ወንጀል⁾⁾ ብትሰራና ያለበሰችዋ ቁጥብ ልትሆን ብትችል አያስገርምም።በእርግጥ ሂጃብ የለበሰች እንስት ከማትለብሰው ለተሻሉ የስነ- ምግባር እሴቶች የቀረበች መሆኑን ሊጤን የሚገባው መሆኑ እንዳለ ነው።

●በሌላ በኩል ደግሞ ሂጃብን መልበስ ውጫዊ የሆነና ሴቶች ብቻ ሊያሟሉት የሚገባ #መለኮታዊ ትእዛዝ ነው ። ንፅህና እና ጨዋነት ሂጃብ ለመልበስ እንደ ብቸኛ ቅድመ ሁኔታ መታየት እንደሌለባቸው ሁሉ ሂጃብ መልበስም ለንፅህናና ጨዋነት ቅድመ ሁኔታ ሆኖ ሊቀርብ አይገባም።ነገር ግን #ሂጃብ_መልበስ_በንፅህና_ለመቆየትና_ለጨዋነት_ለመልካም ስነ -ምግባር የመጀመሪያው  ደረጃ ነው ማለት እንችላለን።

●ከዚህም በተጨማሪ ሂጃብ ወንዶች# የሴቶችን ውበት እንዳይመለከቱና በተለይ ደግሞ የተለያዩ ሴት ልጅ ምትጠቀምባቸውን መዋቢያወች (cosmetics) ጌጣጌጦች እንድሁም አላስፈላጊ አለባበሶች በማየት ወደ መጥፎ ሁኔታ እንዳይገቡ የሚከላከል መሆኑን መገንዘብ አለብን።

زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ ٱلشَّهَوَٰتِ مِنَ ٱلنِّسَآءِ وَٱلْبَنِينَ وَٱلْقَنَٰطِيرِ ٱلْمُقَنطَرَةِ مِنَ ٱلذَّهَبِ وَٱلْفِضَّةِ وَٱلْخَيْلِ ٱلْمُسَوَّمَةِ وَٱلْأَنْعَٰمِ وَٱلْحَرْثِ )آل عمران14
«ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆችም፣ ከወርቅና ከብር፣ ከተካመቹ ገንዘቦችም፣ ከተሰማሩ ፈረሶችም፣ ከግመል ከከብትና ከፍየልም፣ ከአዝመራም የኾኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመ፡፡»

●ሴቶችን መውደድ በመጀመሪያ የተጠቀሰበት ምክኒያት የሴቶች ውበት አላህﷻ በወንድ ልጅ መንገድ ላይ ያስቀመጠው የመጀመሪያው የፈተና መሰናክል በመሆኑ እንጂ በሌላ አይደለም ። ለዚ ታላቅ የሆነ ፈተና ያለው ብቸኛ መፍትሄ ሴቶች ሂጃብ እንዲለብሱ ማድረግ ሲሆን ይህም ወንዶችንና ሴቶችን እኩል በሆነ ሁኔታ የሚጠበቅባቸው መለኮታዌ እንክብካቤ ነው።ሴት ልጅ ደንቡን ጠብቃ ሂጃቧን ምትለብስ ከሆነ በማህበረሰቡ ውስጥ ለፆታዌ ፍንገጣ የሚደረጉ ወንዶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ የሥነ -ምግባር ዝቅጠትን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና መጫወት ትችላለች ።
منقول
📝ይ.ቀ.ጥ.ላ.ል.......
𝐓𝐞»t.me/https_Asselfya
Forwarded from 20 ሞክሮች ለእህቴ ከማግባትዋ በፊት
ባል እሺ የምትልና ከሱ ሀሳብ  ቀደም ቀደም የማትልን ሚስት ይበልጥ  ይወዳል

ስለዚህ ሚስት ሆይ እሺ ማለትን ሊመጂ ትዳርሽ ሰላም ይሆናል
ሙሐደራ 189 ረድ በወሰን ተላላፊዎች ላይ ክፍል 1
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ሙሓደራ ክፍል 189

አዲስ ሙሓደራ ክፍል 01

ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ

የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇

““የ አብዱል ሀሚድ አልለተሚይ እና  ሁሰይን ሙሀመድ ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““

🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed
✅ እንዴት ነው ውጤታማ የምትሆኑት?

~.በጥቂቱ አውሪ
~.በደንብ አስተውሉ
~.ተረጋጉ
~.ቁጥብ ሁኑ
~.ከመናገራችሁ
በፊት አስተውሉ
~.ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙ
~.ሌሎችን አክብሩ
~.ለመታየት አትቸኩሉ

~
t.me/https_Asselfya
~አንድ ቀን በእድሜው እጅግ የገፋ፣ሽፋሽፍቱ የወረደ፣ወገቡ የጎበጠ፣ሽማግሌ ዱላውን ተደግፎ እየተጎተተ የአላህ መልእክተኛ(ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጣና «የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ትንሽ ትልቅ ሳይል ወንጀልን የተባለን በሙሉ አንድም ሳያስቀር የሠራ ሰው እጣ ፈንታው ምንድነው?» አላቸው፡፡ ቀጠል አደረገና «ወንጀሉ በምድር ላይ ላሉ ሰዎች በሙሉ ቢከፋፈል ሰዎችን የሚያጠፋ ዓይነት የዚህ ዓይነቱ ሰው ተውባ ይኖረዋልን? የአላህንስ ምህረት ያገኛልን?» አላቸው፡፡ ነቢዩም (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ) «ሰልመሃልን?» አሉት፡፡ ሰውየውም «እኔማ ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ አምላክ የሌለ ስለመሆኑና አንቱም የአላህ መልእክተኛ መሆንዎትን እመሰክራለሁ፡፡» አላቸው፡፡

እርሳቸውም «መልካምን ነገር ትሰራለህ፤ ከመጥፎ ነገር ትርቃለህ፤ በዚህም አላህ ሁሉንም ነገር በመልካም መዝገብ ላይ ይፅፍልሃል፡፡» አሉት፡፡ ሰውየውም «ክህደቴንና ጥመቴን ሁሉ!» አላቸው፡፡ እርሳቸውም «አዎን ክህደትህንና ጥመትህን ሁሉ!» አሉት፡፡ ሰውየው ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስተኛ ሆኖ «አሏሁ አክበር! አሏሁ አክበር!» እያለ ሄደ፡፡ ከርሣቸው ዐይን እስኪሰወር ድረስ ይህንኑ ቃል ይደጋግም ነበር፡፡

•አሁን ጭንቀታችሁ ሲረግብ ይታየኛል፡፡ ኢንሻአላህ ይረግባል፡፡ አላህ ሆይ ጭንቀትን አርቅልን፡፡የደስታ ኑሮም አኑረን!
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan
አንዳንድ የ አረቦች ቂቢላ ዘንድ ተለምዶ የሆነ ሰው ሲጠራቸው አቤት ሲሉ " ለቤህ " እሚባል አቤት አባባል አለ

እዚህ ላይ ተጠንቀቁ እህቶች ይህ ለ ሙህሪም እና ሴት ለሴት ብቻ ነው መባባል እሚቻለው

ምክንያቱም የ ውዴታ መግለጫ አቤት አባባል ስለሆነ

ይህን አረቦቹ ያውቁታል ስለዚህ የውጭ ሴቴች ለውጭ ወንዶች አይጠቀሙትም " ሰም ወይም ስሚ " ነው እሚሉት

የኛወቹ እንታረም
قال العلامة مقبل الوادعي ࢪحمه الله :

لو ڪان الطلاق بأيدي بعض النِّساء لطلقت زوجها في اليو۾ عشࢪين مـࢪة.

[ ڪتاب غاࢪة الأشࢪطة ٢/ ٢١٨].🌱
~የማይጠቅሙሸ ነገሮቾ ላይ ትኩረት ስታደርጊ ላንች ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ታጫለሸ

~ስለዚህ በሚጠቅምሽ ላይ ትኩረት አድርጊ።

~
t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
📍የሒጃብ ጥፍጥና⁾                 { እና } ⁽❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾ 👉🔖ክፍል አንድ ▪ስለሒጃብ የመጀመሪያው ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ ⓵.የእኔ ንፅሕና እና መልካም ስራዬ የሚገለፀው ሒጃብ በማድረጌ ሣይሆን በአለኝ ጥሩ ፀባይ ነው። ለምሣሌ፦ ብዙ ሂጃብ . ኒቃብ .ጅልባብ የሚያደርጉ ታላላቅ የሚባሉ ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሴቶች ያሉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሒጃብ ሣያደርጉ/ሣይለብሱ…
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Photo
📍የሒጃብ ጥፍጥና⁾
                { እና }
⁽❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾

👉🔖ክፍል ሁለት

▪️ስለሒጃብ በሁለተኛ ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ

➥
ሌለኛዋ እህት ደግሞ ፦ "ለምን ነገሮችን  እናከባብዳቸዋለን ኢስላም ገር የሆነ ሀይማኖት ነው {ነአም ገር ነው } ። ታዲያ ሰወች ለምን አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርጉታል ? ሂጃብ ሴትን ልጅ ከሚያስጨንቋት ነገሮች አንዱ በመሆኑ  ለምን እንድትቸገር ይደረጋል? 
ጌታችን (ሱብሀነሁ ወተዓላ) እንድህ ሲል በቁርአኑ ተናግሮ የለምን ? "አላህ በናተ ላይ ገሩን ነገር ይሻል በእናተም ችግር እንድገጥማችሁ አይሻም ..." ትላለችም !

➥
እንግድህ እዲ አይነት ሃሳቦች በስብእናሽ ላይ ለተንሰራፋብሽ እህቴ ሚኖረኝ ምላሽ ፦ ውድ እህቴ ! ሀያሉ ፈጣሪያችን አንችን ሂጃብ እንድታደርጊ ሲያዝሽ ህይወትሽ ቀላልና ያልተጨናነቀ #እንድሆን ፈልጎ ነው ፤ እርሱ በእውቀቱ ምሉዕ በመሆኑ የባሮቹን ሁኔታ ጠንቅቆ ያውቃልና ።

➥
ሂጃብ ማለት ፦ለመተግበር በጣም ቀላልና ከብዙ ነገሮች የሚጠብቅሽ ነው። አወ! ሂጃብ እንደምታስቢው ከባድ ሳይሆን የማያጨናንቅ ነው ፤ ምክንያቱም በሂጃብ ያማረ ገላሽን መሰተር የቻልሽ ጊዜ ሰወች በሂጃብሽ ውስጥ ያለውን ክቡር ገላሽን ልክ ጌጣጌጥ ማስቀመጫ ሙዳይ እንደተቀመጠ የከበረ ሉል ወይም እንቁ መቁጠር ይጀምራሉና ነው ፤  ይህም ክቡር ሰውነትሽ ለአንድ እምነቱ የፀና እንድሁም የሚያፈቅርሽን ሚንከባከብሽ ወንድ ( ባልሽ) ተቆጥቦ የተቀመጠ እንደመሆኑ ገልጦ እንድመለከተው የሚፈቀድለት ለእርሱ ብቻ ነው ።

◎ሂጃብ አላህ ላገራለት ቀላልና የማያጨናንቅ ነው ፤ ሂጃብ መልበስሽ የአላህን ውደታ የሚያስገኝልሽ ሲሆን የመልእክተኛውን (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) የባልደረቦቻቸውን ቀኑን መንገድ የተከተሉን የሰማእታትን ጉርብትና በመጨው ዓለም ያገናፅፍሻል ።
አላህ እንድህ ይላል ፦
▪️وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ مَعَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ وَٱلصِّدِّيقِينَ وَٱلشُّهَدَآءِ وَٱلصَّٰلِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُو۟لَٰٓئِكَ رَفِيقًۭا
~አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ፡፡
(
አኒሳእ 69)

◎ሂጃብ ማድረግሽን ወደ ጎን ማለትሽ በራስሽ ላይ ብዙ ችግሮችን መጋበዝሽ እንደሆነ ልትረጅው ይገባል ፤እንድሁም ሂጃብ እንዳትለብሽ የሚገፋፉሽ ሀይሎች በአንቺ ላይ ብዙ መዘዞችና መጥፎ ሁኔታወች እንድፈጠሩብሽ እያደረጉ መሆናቸውን አስተውይ ። ይህን በተለመለከተ አላህ ሱብሀነሁ ተአላ እንድህ በማለት በቁርአን ይገልፃል !
▪️وَٱللَّهُ يُرِيدُ أَن يَتُوبَ عَلَيْكُمْ وَيُرِيدُ ٱلَّذِينَ يَتَّبِعُونَ ٱلشَّهَوَٰتِ أَن تَمِيلُوا۟ مَيْلًا عَظِيمًۭا
◎አላህም በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል፡፡ እነዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት (ከውነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ፡፡
▪️يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُخَفِّفَ عَنكُمْ ۚ وَخُلِقَ ٱلْإِنسَٰنُ ضَعِيفًۭا
አላህ ከእናንተ ሊያቃልልላችሁ ይሻል፡፡ ሰውም ደካማ ኾኖ ተፈጠረ፡፡
(
አል ኒሳእ 27~28)

◎ከላይ የተጠቀሰው የቁርአን አንቀፅ ጉዳዪን ከሸሪአ አንፃር ነው የሚዳስሰው ፤ ማንኛውም ወንድና ሴት አማኞች ይህን ሀቅ ያለማስታረቅ ይቀበላሉ 

◉ይህን ታላቅ የሆነ ጉዳይ ከአለማዌ የአኗኗር ስረአት ጋር ብናነፃፅረው ምን ይህል ጊዜ ጉልበትና ገንዘብ ለመገላለጥና ለእርቃናዌነት ትዕይንት (ተበሩጅ) እንደሚባክን ሁላችንም አናውቅም ? መልሱ ግልፅ ነው ፤ ቀላሉ መንገድ የትኛው እንደሆነ ተለይቷል ። ሆኖም ሰወች በራሳቸው ላይ ፍትሀዌ ብያኔን የመስጠት የሞራል ብቃት የላቸውም ።
منقول
📝ይ.ቀ.ጥ.ላ.ል.......
𝐓𝐞»t.me/https_Asselfya
ለጮኸዉ  ሁሉ  ምላሽ  ከሰጠሽ  ያወራን  ሁሉ  ካዳመጥሽ  እመኝኝ  የህይወትሽን  ትርጉም አታዉቂዉም!

ራሥሽን ሁኚ
ለጮኸ ሁሉ አይመለስም  መናገርሽ ለዉጥ ካላመጣ  ዝምታ ጌጥ ነዉ

ያወሩሽን ሁሉ አትቋጥሪ
አይቶ ማለፍ ሰምቶ  ማፍሰስ  ይልመድብሽ  በጆሮሽ  እንጂ በልብ ጆሮሽ  አትስሚያቸዉ።
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Photo
ዉዶች እስከመጨረሻ እልከዉናበ pdf መልኩ ላዘጋጀዉ ፈልጌ ነዉ ኢንሻአላህ

~