💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
~በአላህ ላይ ሙሉ እምነት መጣል ሠበብ ማድረስ መነጣጠል የለባቸዉም። በአላህ ላይ ተመካና ስበብ አድርስ።ሠበብና ተወኩል አንድ ላይ ሲኖሩ የርዝቅ ሠበብ ይሆናል።

~
ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ወርቃማ ንግግሮች ውስጥ፣

~ወጣት ሆይ ወጣትነትህን ተጠቀም። እራስህን አድን። ሀላፊነትህን ተወጣ። አርአያዎችህን ለይ።

~ቀና_በል_በተውሂድ። ከሺርክ ሰፈር አትልከስከስ!!

~ወጣት ሆኖ ለሺርክ ጠበቃ ለተውሂድ ግን ጠላት ሲሆን ማየት ምነኛ ልብ የሚያደማ ነው ?!ምነኛ የሚያሳፍር ነው ⁉️

📚 ተውሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ" ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ!!


t.me/https_Asselfya
~ፈገግ በሉ

ፈገግታ ሱና ነዉ።

ሌባና ሴቶች ዘዴ አያጡም ይላል ያገሬ ሰዉ...የሌባዉ ግን አትሻብኝ
~ውዷ  እህቴ  ሆይ!  ባለሽ ተብቃቂ።
#አመስጋኝ ሁኝ  ከበላይሽ ያሉትን ሳይሆ በታችሽ  ያሉትን  ተመልከቺ ! 

~አንቺ  ያገኝሺውን  ያላገኙ አሉና።
ባለቤትሽ ምን ላደረገልሽ  ሁሉ  አመስግኝው


ምን አድርገህልኛልና  አትበይው ልብ በይ..

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ።

ባሏን የማታመሰግንና በሱ የማትብቃቃ ሴት የውመልቂያማ አላህ ወደሷ አይመለከትም።

📚صحيح الترغيب - رقم: (1944)
~
t.me/https_Asselfya
የለተሞ መንጋ
~
እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ! ምናልባትም እንዲህ ዓይነቱ ቡድንተኝነት የወለደው ከንቱ ሙገሳ ይሆናል ልባቸውን አሳብጦ ገደል እየከተታቸው ያለው። አንደኛውንም "ሸይኹል ኢስላም" እያሉት እንደሆነ ሰምቼ ነበር። እውነት ይሆን?
ከቅጥፈቱ በላይ የገረመኝ ጠሀ ኸዲር ይህንን አሳፋሪ ወሬ ቁም ነገር አድርጎ መለጠፉ ነው። ሰዎቹ ግን እኛ ከምንገምታቸውም በጣም የራቁ ናቸው።
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
‏ﻗﺎﻝ ﺍﻟﺤﺎﻓﻆ ﺍﻟﻤﺰﻱ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :

"ﻭﻟﻮ ﺳﻜﺖ ﻣﻦ ﻻ ﻳﺪﺭﻱ ﻻﺳﺘﺮﺍﺡ ﻭﺃﺭﺍﺡ ﻭﻗﻞ ﺍﻟﺨﻄﺄ ﻭﻛﺜﺮ ﺍﻟﺼﻮﺍﺏ"
تهذيب ﺍﻟﻜﻤﺎﻝ (362/4)


~አላዋቂ ዝም ቢል ኖሮ ለራሱም አርፎ ሰዎችንም ያሳርፍ ነበር እንዲሁም ትክክለኛው በዝቶ ስህተቱ ያንስ ነበር።

~
~አላህ ሆይ!!
~መልካም ነገር ሲያገኙ ከሚያመሠግኑ
~ችግር ሲገጥማቸዉ ከሚታገሱ

~ወንጀል ላይ ሲወድቁ ፈጥነዉ ምህረት ከሚጠይቁ ባሮችህ አድርገኝ።

~
#ተበድሎና ተገፍቶም ፈገግታው ከፊቱ
የማይጠፋ ሰው በጣም ጠንካራ ነው!
~
ተጋበዙልኝ ከማስተንተን ጋ

~
የእናትሸ ልጅ የማያዉቀዉን ሚስጥር ለባእድ ወንድ ስነግሪ የዛኔ ነዉ የረከሸዉ !!
⭕️👉ይድረስ እንደ <መርየም መመረጥን> ለምትሹ ለውድ ሙእሚን እህቶቸ ሁሉ....!

~እኔ እንዴት እንደመርየም እመረጣለሁ ብለሽ እያሰብሽ ነው አይደል??? አንቺ ያለአባት ልጅ ትወልጃለሽ ማለት አይደለም። ወይም ኢሳ ዐለይሂ ሰላም ባንቺ ማህፀን ድጋሚ ይወላዳል ማለት አይደለም ነገር ግን እንደ መርየም የአላህ ሱብሀነሁ ተአላ ምርጥ ባሪያ ሆነሽ መመረጥ ትችያለሽ!!

~#ውዷ እህቴ አትጠራጠሪ ጌታሽ ዘንድ ምርጥ ባሪያው ሆነሽ መመረጥ ትችያለሽነገር ግን ምርጫው በዘፈቀደ ሳይሆን በመስፈርት ነው።መስፈርቱ ምን ይሆን???
ቀድመን የጌታችንን ቃል እንመልከት፦

▪️ﻭَﺇِﺫْ ﻗَﺎﻟَﺖِ ﭐﻟْﻤَﻠَٰٓﺌِﻜَﺔُ ﻳَٰﻤَﺮْﻳَﻢُ ﺇِﻥَّ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﭐﺻْﻄَﻔَﻯٰﻚِ ﻭَﻃَﻬَّﺮَﻙِ ﻭَﭐﺻْﻄَﻔَﻯٰﻚِ ﻋَﻠَﻰٰ ﻧِﺴَﺂﺀِ ﭐﻟْﻌَٰﻠَﻤِﻴﻦَ @ ﻳَٰﻤَﺮْﻳَﻢُ ﭐﻗْﻨُﺘِﻰ ﻟِﺮَﺑِّﻚِ ﻭَﭐﺳْﺠُﺪِﻯ ﻭَﭐﺭْﻛَﻌِﻰ ﻣَﻊَ ﭐﻟﺮَّٰﻛِﻌِﻴﻦَ

# <መላእክትም ያሉትን (አስታዉስ)
መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጸሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡# መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፡፡ ስገጂም፡፡ ከአጎንባሾቹም ጋር አጎንብሺ፡፡»

{ኢምራን ፡42-43}


በአለም ላይ መርየምን የሚያክል እንስት የለም።የእንስቶች ሁሉ አውራ ናት። እዚህ ደረጃ ላይ እንዴት ልትደርስ ቻለች? ምክንያቶቹ ሁለት አንደሆኑ ዑለሞች ተናግረዋል፦

አላህን በፅናት የምታመልክ መሆኗ
➋ ራሷን ከብልግና ተግባራት የጠበቀች መሆኗ ነው።


~#እህቴ ሆይ! እንደመርየም የተመረጥሽ እንስት ለመሆን በነዚህ ሁለት ባህሪያት አርአያነቷን ተከተይ። በዒባዳሽ ላይ በርቺ ብልትሽንም ከሀራም ጠብቂ።
አላህ ኢንዲመርጥሽ ከፈለግሽ በፅናት አምልኪው።ከሰጋጆች ጋር አብረሽ ስገጂ። ዒባዳ ላይ በርቺ። በጎ ስራን አብዢ። ጊዜሽን ፤ጉልበትሽን ፤እውቀትሽንና ገንዘብሽን አላህ ለሚወደው ተግባር አውዪ።
#መርየም የተመረጠችበት ሁለተኛው መስፈርት በቀጣዩ የቁርአን አንቀፅ ውስጥ ሰፍሯል፦

▪️ﻭَﻣَﺮْﻳَﻢَ ﭐﺑْﻨَﺖَ ﻋِﻤْﺮَٰﻥَ ﭐﻟَّﺘِﻰٓ ﺃَﺣْﺼَﻨَﺖْ ﻓَﺮْﺟَﻬَﺎ ﻓَﻨَﻔَﺨْﻨَﺎ ﻓِﻴﻪِ ﻣِﻦ ﺭُّﻭﺣِﻨَﺎ ﻭَﺻَﺪَّﻗَﺖْ ﺑِﻜَﻠِﻤَٰﺖِ ﺭَﺑِّﻬَﺎ ﻭَﻛُﺘُﺒِﻪِۦ ﻭَﻛَﺎﻧَﺖْ ﻣِﻦَ ﭐﻟْﻘَٰﻨِﺘِﻴﻦَ

~#የዒምራንን ልጅ መርየምን ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች(አመነች)፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡

{ተህሪም ፡12}


~ስለዚህ በአላህ ለመመረጥ ብልትሽን ከዝሙት መጠበቅ ይገባሻል ። ምክንያቱም ንፅህና ወሳኝና የማንነት መገለጫ ነውና!!!

t.me/https_Asselfya
ስኬት ማለትከችግር ቡሃላ ድሎት መኖሩን ማረጋገጥ ነዉ።

~
ዐይንህ ሲደርቅ በቁርአን አርሰው፣
ወገብህ ሲገር በሱጁድ አለስልሰው፣
ቀልብህ ሲደርቅ በሞት አስታውሰው።

.
ከቁርአን ጋር ያረጀች ዐይን አቤት ማማሯ!
ከቁርአን ጋር የኖረች ዐይን አቤት ብርሃኗ!
በቁርአን የተኳለች ቅንድብ አቤት ዉበቷ!
.
t.me/https_Asselfya
Audio
AudioLab
🍃▫️ آيات السكينة ▫️🍃
👉ከቁርአን በላይ ጣፋጭ የለም

~