💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.68K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
«በፂም ያሳመረን»
---------------------
ይድረስ ትውስታዬ ፂም ለሚጋጥጡ፡
ሲመክሯቸው ደግሞ እጂግ ለሚቆጡ፡
ሸይጧን ለመከተል ለሚቀላውጡ፡
በጥመት ላይ ሆነው እጂግ ለሚቀብጡ፡
መልዕክቴን አድርሱ በባቡር በፈረስ፡
ፂም የላጩ ሰወች እስኪሰሙ ድረስ፡
------------------------
ሙስሊሞች አድርጎ በፂም ላሳመረን፡
ፂምን አሳድጉ ብሎ ላስተማረን፡
ሙሉ በሆነ ህግ ሁሉን ለነገረን፡
አልሀምዱ ሊላሒ እኛን ለፈጠረን፡
----------------------------
ወንድ ልጅ ተወልዶ ፂሞቹን ከላጨ፡
ፊቱ ዱባ መስሎ ከተቁለጨለጨ፡
ፂሙን ለማፋፋት ከተሙለጨለጨ፡
ጥርጥር የለውም ከአሏህ ጋር ተጋጨ፡
--------------------------
ከኋላ ከፊቱ ሀራም ስዕል ስሎ፡
ሙሀመድ ነኝ ካለ ሙሽሪኮችን መስሎ፡
ወንጀል ነው ተግባሩ በጣም ተሳስቷል፡
የነብዩን መስመር ሱናውን ረስቷል፡
----------------------------
ወንድ ነኝ እያለ ጥምጣም ከወደደ፡
አቡ-ፉላን ሆኖ ፂሙን እየላጨ ከተረማመደ፡
ምኑን ወንድ ሆነ ሴት መስሎ እየሔደ፡
---------------------
ወንድሜ ተመከር ተከልከል ከምላጭ፡
ውበትህ ነውና ፂምህን አትላጭ፡
ወንድ ሁን እባክህ ጀግንነት ይሰማህ፡
የልብህን እምነት ሸይጧን እንዳይቀማህ፡
ስልጣኔ መስሎህ ፂምህን አትጣል፡
ወንጀል ነው እወቀው አሏህን ያስቆጣል፡
------------------------
ያስከብራል እንጂ ፂም አያዋርድም፡
ሱናውን የተወ ነብዩን አይወድም፡
ፊዳከ በማለት ሁሌ ብታቅራራ፡
በየሚዲያው ላይ ሁሌ ብታወራ፡

የፊትህ ገፅታ ሀቅን ካልተጣራ፡
የማይተገበር ወሬ ምን ይሰራል፡
አታላዩ በዛ ከማን ጋር ይኖራል፡
የተቦጫጨቀ ሱሪ እየገተተ፡
የነጮችን ፈለግ ከተመለከተ፡
የጀነቱን መሪ ነብዩን ከረሳ፡
እርቃኑን ከቆመ ከሆነ እንደ እንሰሳ፡
ተንቀሳቃሽ በድን ይባላል ሬሳ፡
---------------------------
ፊዳከ የሚል ጌጥ ፕሮፋይል ሰቅሎ፡
ልብሱን ከገተተ ፂሙን ተጎንድሎ፡
ይህ ሰው ሙሉ አይደለም ይባላል ጎደሎ፡
ፂማችን ውበት ነው ድንቅ መከበሪያ፡
የነብዩን ፈለግ ግሩም መተግበሪያ፡
ውበቱን ግርማውን ሆኖ መተግበሪያ፡
---------------------------
ምን ወንጀል ቢበዛ ሀቁን ባንወጣም፡
በፂማችን ብቻ አጂር ግን አናጣም፡
ምስጋና ይገባው በተውሒድ ያነፀን፡
እኔን ተከተሉ ብሎ ለቀረፀን፡
በአንድ አሏህ እመኑ ብሎ ላስተማረን፡
ጀነት አለላችሁ ብሎ ላበሰረን፡
የአሏህ ሰላም ይሁን በነቢ ሙሀመድ፡
በሀቁ ዘበኛ በኢማኑ ገመድ፡
አወ አልሀምዱ ሊላህ በኢስላም ላኖረን፡
በውት አከናንቦ በፂም ላሳመረን፡
-----------------------------
«በኑረዲን አል አረብ»
---------------------------
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
አንዳዴ  ያሠኛል  መኖር ተደብቆ
ከሰዉም  ከወሬ  ከሁሉም እርቆ

🍁አንዳዴ ደግሞ

በሰማይ  መንሳፈፍ እንደ ወፍ  መብረር
አይቻለንም እንጂ የሚቻል  በነበር
ያምራታል  ነፍሳችን  መሸሽ ከፍጥረታት
በራሧ አለም  ሆና  ስለሌላ መርሳት
የራሧ ልብ ጋር  ማዉራት  መወያዬት
ማንነቷን ማወቅ  በራሧዉ
ጥራት
الهي
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያአላህ ምን ልበል!!

ጌታችንጋ እንዲህ ብናወራኮ.......
اللَّهُمَّ يَا مُقَلِّبَ القُلُوبِ ثَبِّتْ قُلُوبَنَا عَلَى دِينِكَ.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
~ሰበሐል ኸይር !
.
🔍አስባቹህታል ግን.....
ዱንያ እንዲህ ያማረች አይን አይታዉ ጆሮ ሰምታዉ በሰዉ ልጅ ልብ ዉል ብላ የማታዉቀዉ ጀነት እንዴት ትሆንን......ኢላሂ ያለምንም ምርመራ ጀነትህን አደራ!
~አላህ ከከለከላቸዉ ነገሮች ከተከለከልክ ሽርክን ፦ወንጀልን ከራክ ላንተ መፋዛ አለልህ!!

إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ مَفَازًا
ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡.

📚ሱረቱል ነበእ 31

አላህ  ሆይ !  አንተ  ልብን  እንደፈለክ  የምታገላብጥ  ነህና  ልቤን  በዲነል  ኢስላም  አፅናልኝ።

✍️ሰላም ዋሉልኝ ...
~ከምሬ ነዉ የምላችሁ

ገንዘብ ደስታን አይገዛም!
እዉነተኛ ደስታ የሚገኘዉ ከጌታችንጋ በመተሳሠር ብቻ ነዉ።

~
🔖መልካም ሚስት በጅንጀና አትገኝም።

📍ኢብኑል አረብይ አልማሊኪይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

«መልካም ሚስት የምትገኘው ባንተ ጥረት አይደለም። እሷ ማለት አላህን ለሚፈራ ሰው የምትሰጥ የአላህ  ሲሳይ (ሪዝቅ) ናት።»

📖أحكام القرآن (1/536)
=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
☑️ ቀልባችን እንዲደርቅ፣ እንዲበታተንና እንዲደክም ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋናው የሀራም እይታ ነው።

قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ

"ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው"


t.me/https_Asselfya
~ካነበብኩት ላካፍላችሁ

✅ ለስኬታማ ህይወት ...

1. አመስጋኝ ልብ ፦ የተሻለ ለማግኛት የሚጥር እና ባለው ነገር ፈጣሪውን የሚያመስገን፤ ትንሽ ነገሮች ውስጥ ያለው ዋጋ የሚያውቅ የሚረዳ፤ ሁሉም በጊዜው እንደሚሆን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤ ባጣው ነገር ልቡን ከሚያመው ባለይ በቀረው ነገር የሚደሰት ነው። መማር የማያቆም ልብ አለው።

2. ይቅር የሚል ልብ ፦ ትላንትናው ላይ በሆነበት ነገር ቂም ያልያዘ እና ልቡን ዝግ ያላደረገ። በተቻለው መጠን እነዚያ ሰዎች ሰው እንደሆነ የሚገነዘብ ነው። ይሄ ማለቴ ሰው ስህተት ይሰራል ያንን ደግሞ መሻር የማይችለው የህይወት እዉነት እንደሆነ ጠንቅቆ የሚያውቅ። ስለዚህ ይቅር እያለ፤ ይቅርታ እያጠየቀ፤ ከትላንት ስህተት በመሻል የዛሬው ህይወት የሚመራ ነው። ነገ በመነፈቅ ያልተጠናወዘ፤ ትላንት በማሰብ ኖሮ እኮ ትላንት ቀረ የማይል፤ ህይወት አሁን ያለው ነገር በጣም ወሳኝ እንደሆነ በማሰብ ያንን በማጣጣም የሚኖር ነው።

3. ትግስተኛ የሆነ ልብ ፦ ትግስት እንደ ኮሶ የምትመር እንደ ወይን ጣፈጭ የሆነ ውጤት የምትሰጥ መሆኖን ጠንቅቆ የተረዳ። ነገሮች በጉልበት ከመጣል ይልቅ በትግስት እና በትጋት እንደሚያሸነፍ የሚያውቅ ሰው ነው።

4. የማይሰብር ቅስም ያለው፦  መሞከር የማያቆም፤ ከትላንትናው ስህተት ተምሮ ለዛሬው ሾል የተሻለ ለመሞከር የሚጥር። ነቀፋ እና ትችትን የሚቀበል፤ገንቢ የሆኑ ተግሳፅዎች የሚቀበል፤ ከስድብ ውስጥ ትምህርት የሚወስድ ፤ በደገፊዎች ሙቀት ምን ማድረግ እንዳለበት የማይረሰ፤ አይኑን ህልሙና ግቡ ላይ የሚያደርግ ነው። በተቺዎቹ ስድብ እና ያልተገባ ቃላት ለልሹ ያለው ቦታ እንዳንቀንስ ንግግራቸው ወደ፥ ውስጥ የማያስገባ። ጠንከር አስተያያት የማድመጥ እና የመቀበል አቅም ያለው።

t.me/https_Asselfya
አስተዋይ የሆነ ሰዉ ፎሎዎር ለማብዛት ጧት ማታ አይለፋም፡፡
ዳታ በከፈተ ቁጥርም ተከታዮቼ ጨመሩ ወይንስ ቀነሱ እያለ አይጨነቅም ፡፡

ምክኒያቱም ተከታዮቹ በጨመሩ ቁጥር ተጠያቂነቱም በዛዉ ልክ ይጨምራልና ፡፡
አነሰም በዛም በምንለቃቸዉ ነገሮች መጠየቃችን የማይቀር ነዉ፡፡

ስለዚህ በየ ደቂቃዎች ልዩነት ቻናላችን ጨመረ ወይንስ ቀነሰ እያልን ከምንፈትሽ በየደቂቃዉ ኢማናችንን እንፈትሽ እላለሁ፡፡

አላህ ከአስተዋዩች ያድርገን!

✍አብዱ ሽኩር