💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.73K subscribers
1.27K photos
494 videos
123 files
5.14K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
☑️ ተቅዋ ማለት የሠዉ ልጅ የተፈጠሩለት አላማነዉ።
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
🔖ተቅዋ የአላህን ነስር (ድልን )ያስገኛል።
🔹إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوا۟ وَّٱلَّذِينَ هُم مُّحْسِنُونَ
አላህ ከእነዚያ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነሱ መልካም ሠሪዎች ከኾኑት ጋር ነውና፡፡

🔖ተቅዋ ከሸር ፦ከጥፋት ከተንኮሎች ለመጠበቅ ስበብ ነዉ።
🔹وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا لَا يَضُرُّكُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئًا ۗ
ብትታገሱና ብትጠነቀቁም(አላህን ብትፈሩ)የነሱ ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም፡፡

🔖ተቅዋ ለጭንቅ ከመከራ  መዉጫ ስበብ ነዉ።
🔹وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجْعَل لَّهُۥ مَخْرَجًۭا
አላህን የሚፈራ የሆነ ሠዉ መዉጫ ቀዳዳን ያደርግለታል።

🔖ተቅዋ የሪዝቅ ስበብ ነዉ ።
🔹وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ
ካላሠበዉ አቅጣጫ አላህ ሲሳይን ይሠጠዋል።

🔖ተቅዋ  አላህን መፍራት እንዲኖረን ስራዎቻችንን እንዲስተካከሉ ያግዘናል።

🔹يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ يُصْلِحْ لَكُمْ أَعْمَالَكُمْ
እናንተ እመኑ በተባላችሁበት ያመናችሁ ሆይ!አላህን ፍሩ።ስራዎቻችሁን ያስተካክልላችኋል።

🔖ተቅዋ ምህረትን ማገኛ ስበብ ነዉ
🔹وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ
ወንጀላችሁን ይምርላችኋል።

🔹قال عمر بن عبدالعزيز: ليس تقوى الله بصيام النهار، ولا بقيام الليل، والتخليط فيما بين ذلك، ولكن تقوى الله ترك ما حرّم الله،

☑️ አላህን መፍራት ማለት ለሊት መስገድ ቀኑን መጾም አደለም እንዲሁም በመካከላቸዉ ሁሉንም መቀላቀል አይደለም።ይልቁንም ተቅዋ ማለት አላህ ግደታ ያደረገዉን መፈጸም አላህ እርም ያደረገዉን መተዉ ነዉ።

t.me/https_Asselfya
👍9
🔍ጊዜ ለሁሉም ማህበረሰብ የተሰጠው ሀብት❗️❗️
ምንም እንኳን የሰው ልጅ አለማወቅ ሁኖ ይህን ሀብት በአግባቡ ባይጠቀምበትም ይህ እድል ግን እስከ ግለሰቡ እልፈተ_ሒዎት ድረስ አብሮት አለ።

ታዳ ይህ ግለሰብ ለምን ሀብቱን በአግባቡ አይጠቀምበትም?ነው ወይስ ነገ ተጠያቂነትን ማፍራት ነው የሚፈልገው? አይ የሰው ልጅ ሀብቱን ጥሎ ሀብት ፍለጋ!!ለነገሩ ያለማዎቅ ትርፉ ይሄ አይደል።

ጊዜ"አዎ!እውነትም ሀብት ነው!ምናልባት ስለሀብት ሳወራ ዱኒያዊ ቁሳቁስ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጋችሁ ከነበረ እሱ ትልቅ ስህተት ነው።
ጌዜ"ጊን ለሰው ልጅ በዕጁ ላይ ያለ ትልቁ ሀብቱ ነው።

ዛሬ በአግባቡ ከያዝከው እውነትም ብልጥ ነህ።ነገ በጊዜ ውስጥ:የተራመድከው፣እረፍት ያደረከው፣በስራ ያሳለፍከው፣በግዴለሽነት ያሳለፍከው ከንቱ ተግባርህ ሁሉ ነገ ማመን በሚከብድ ሁኔታ የስራ መዝገብ ሁኖ ይመጣል።ስለዚህ ዛሬ በለሀብት ነህ የቻልከውን ያክል ትጋ። አዎ ባለ ሀብት ነህ።
👍8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☑️ áŒŁá‹áŒ­ የምሽት ስንቅ
{ إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا  }
👍7
~አይቶ እንደመራመድ
መርጦ እንደመናገር
ታግሶ እንደመኖር
መልካም ነገር የለም።

=
መልካም ...
👍14
አሰላሙአለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
ይህ ቻናል የተከፈተው ቁርኣንን ፀጥ ብሎ በማዳመጥ እና ቁርኣን ይዞ የሚቀሩትን ኡስታዞች በመከታተል አቀራራችንን በአላህ ፍቃድ እንድናስተካክል ነው፡፡
አንዱ የድምፅ ፋይል በአላህ ፍቃድ ግማሽ ጁዝ የተቀራበት ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ድምፅ ፋይል ኬት ሱራ እንደሆነ፣ ከስንተኛው አንቀፅ እስከ ስንተኛው እንደሆነ በአላህ ፍቃድ ይጠቀስበታል፡፡

https://t.me/Tilawa_Quran
https://t.me/Tilawa_Quran
👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
~ከሀሜትና ነገር ከማመላለስ ምላስን መያዣዉ መንገድ
~የሚስጥርሽሁሉ ሚስጥር ተካፋይ  ባልሽነው¡

ከባልሽ በላይ ትልቅ ሚስር ተካፋይ የለም።  እና  ሚስጥርሽን በማካፈል ላይ ቅድሚያ  ቦታ ሊይዝ የሚገባው ንጉስሽ ነውና   በማካፈል  ላይ በርች እያልኩሽ ነው።

ኡሙ   _ዑበይዳ

በሉ ደህና ክረሙ


t.me/yesunawakonjobetwuhidyabebech
~የሙስሊሞች ምሳሌያቸዉ እርስ በርስ ያላቸዉ መዋደድ፦መተዛዘን አንዱ ለሌላዉ መራራት ሁኔታቸዉ ልክ እንደ አካል ነዉ።ከፊሉ ሠዉነት ሲታመም ከፊሉ እንቅልፍ ሠላም ያጣል። ከፊሉ ትኩሳት ይሠማዋል። አንዱ ለሌላዉ መቆርቆር ማሠብ እራሱን የቻለ ኢማን ነዉ።

~የእዉነት ከልብ አንዳችን ለአንዳችን መልካም ነገር የሚያሳስበን ወይም የሌላዉ መከፋት የሚያስከፋን ከሆነ እዉነተኛ የሆነ ኢስላማዊ ወንድማማችነት እህትማማችነት አለ።

t.me/https_Asselfya
እኛ ኢልም ገበታ ላይ ተጥደን ሌላኛዋ እህታችን ወንድማችን በሌላ በማይጠቅም ነገር ቢዚ ሆና በማይጠቅም ነገር ቢዚ ሆኖ ስናያቸዉ እማንቆረቆር ከዚያ ካሉበት ነገር የማንመልሳት የማንመልሠዉ ከሆነ እዉነተኛ እህትማማችነት (ወንድማማችነት)ላይ ነን ?

ሁላችንም የተዘናጋንበት ነገር ...

የቤት ስራ ይሁነን
👍3
በተለይ ወንድሞች አስቡበት ወንዶች እሚያቀራቸዉ ጠፍቶ ሴቶችን አስተምሩን ማለት ደረጃ ደርሠዋል።ሴቶች ለሴቶች እንኳን ይጠነካከራሉ ።እናንተ እርስበርሳችሁ የማትጠናከሩበት ምክንያት ምን ይሆን?!
👍5
ቲሸርት ማሳተም
Daru tewhid
ወዳጅ የሆነ ሰው ለሚወደው አካል ታዛዥ ነው !!

🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ

t.me/Darutewhide
🔹يا مُعاذ إني احُبك ..
صالح الفوزان- حَفظُه الله
ሐያእ ለሴት ልጅ ዉበት ነው
ለወንድ ልጅ ደግሞ ሞገስ ነው።
☑️ ለባል እና ለሚስት ጠቃሚ ሀዲስ!!
      〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ከእለታት አንድ ቀን ልጃቸው ፋጢማ ቤት ሄዱ ባሏን አልይን አላገኙትም ነበር እሳቸውም ያጎትሽ ልጅ የት ነው አሏት? እሷም በኔና በሱ መካከል የሆነ ነገር ነበርና ተኮራርፈን ወቶ ሄደ አለቻቸው።

(📚ቡኻሪይ ዘግበውታል)

🔍ከሃዲሱ የምንወስደው  ፅንስ ሀሳብ🔍
       ~     ~   ~
①➴ በዚህ ሃዲስ ፋጢማ በተቆጣችበት ሁኔታ በሷ አና በአልይ መካከል ያለውን የፀብ ምክኒያት ለነብዩ ግልፅ አላደረገችም ነገር ግን (የሆነ ነገር ነበር )ነው ያለችው ከዚህ የምንረዳው አንዲት ሚስት ምንም እንኳ ከባሏ ጋር ቅር ብትባባል ሚስጥር ማውጣት እንደለለባት ነው።

🔖አሁን ላይ የብዙ ሴቶች ተጨባጭ‼️

በአሁን ግዜ አሏህ ያዘነላቸው ሴቶች ሲቀሩ ከባላቸው ጋ ትንሽ ፅብ ከተፈጠረ የባጡን የቆጡን እያነሱ መውቀስ እና መናገር ልማድ ሆኗል በዚህም ምክኑያት ትንሽ ፅብ የተባለው በነገር ብዛት ወደ ትልቅ ፀብ ዙሮ ለመፋታት ያደርሳል❗️

~ስለዚህ አንቺ የአሏህ እንስት ሆይ! መጣላት አይቀርም እና ከባልሽ ጋ ቅር ከተባባልሽ ፋጢማን ተምሳሌትሽ አድርጊ

② ➴ ሁለተኛውም ከዚህ ሃዲስ የምንወስደው ቁም ነገር ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ተኮራርፈን ወቶ ሂዷል ስትላቸው ዝርዝር አልጠየቁም ስለዚህ የልጅ አባት የሆነ ሰው በባልና በሚስት መካከል እሳትን ሊጭር አይገባውም ተምሳሌቱ ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሊሆኑ ይገባል።

③ ➴ከዚህ ሃዲስ የምንወስደው ቁም ነገር
አልይ ረዲየሏሁ አንሁ በተቆጣ ግዜ ጉዳዩ እንዳይሰፋ ቤቱን ጥሎ መሄዱ ትልቅ ቁም ነገርን ያስጨብጠናል።

🔖በአሁን ግዜ በባል እና በሚስት መካከል ቅሬታ ሲፈጠር መኮብለል የሚባል ነገር እንደ ባህል ተደርጎ ይታያል።

🔍ጉዳዩን ለማብረድ ከቤት መውጣት ያለበት ወንዱ ነው ።እንጂ ሴቷ የምትወጣ ከሆነ እህያ ወደ ቤት ዉሻ ወደ ግጦሽ እንደሚባለው ነው የሚሆነው ።
ወንዶች ወንድነታቸው በመላሸቁ የተነሳ ያለ ፍቃዱ ኮብልላ ለተወሰነ ግዜ ቤት ጠባቂ ሆኖ ይቆያል ።

   t.me/https_Asselfya
~አዉርዱት ሁለየ ሰአቱ ሲደርስ ያስታዉሳችኋል።

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.azkarsabahmasaa


~ዚክር የልብ ሀይል የአካል ብርታትና የትኛውንም ጣዕም የማይስተካከለው የቀልብ ምግብ ነው።
👎1
- انَشروا الع

ِلم انَشروا السُنة ..
🎤محمد رمزان الهاجري- حَفظُه الله.

.
ሁሉም በቋንቋው ያስተምር
~
ህዝባችን በስራ፣ በትምህርት፣ በሌሎችም ምክንያቶች ከትውልድ አካባቢው ርቆ በተለያዩ አካባቢዎች ይኖራል።
ሳዑዲ ውስጥ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ኢስላምን በቋንቋቸው የሚያስተምሩባቸው ጃሊያዎች አሉ። በቋንቋቸው ደዕዋ ያዘጋጃሉ። መጻህፍት ያሰራጫሉ። ወዘተ. ዐረቦቹ "በገዛ ሃገራችን ላይ ከ0ረብኛ ውጭ ማንም በሌላ ቋንቋ እንዳያስተምር" አላሉም። ይልቁንም ተቋም አደራጅተው፣ በጀት በጅተው ሃይማኖትህን በቋንቋህ እንድታስተምር ከጎንህ ይቆማሉ።
እኛ ዘንድ ደግሞ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ጀማዐዎች ውስጥ፣ በአንዳንድ መስጂዶች ጭምር ሰዎች በቋንቋቸው ኢስላምን እንዳያስተምሩ እንቅፋት የሚሆኑ አሉ። ይሄ ፈፅሞ መሆን የሌለበት ነው። መስጂዶቻችንን ከፖለቲከኞች እና ፖለቲካዊ ዝንባሌ ከሚታይበት አካሄድ እናፅዳ። አማራ ክልል ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተመደበ የኦሮሞ ተማሪ በኦሮምኛ ለማስተማር ቢፈልግ ከጎኑ ነው መቆም ያለብን። ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተመደበ አማርኛ ተናጋሪ ተማሪ በአማርኛ ለማስተማር ቢፈልግ ከጎኑ ነው መቆም ያለብን። ሌላውም እንደዚሁ። እንዲያውም በራሳችን ተነሳሽነት ሌሎችን መቀስቀስ ነው የሚገባን። ዲናችን እንዲያብብ፣ ሰዎች እምነታቸውን እንዲገነዘቡ አንፈልግም እንዴ? መስጂዶችንና የደዕዋ መድረኮችን ፈፅሞ ፖለቲካው ጥላውን እንዲያጠላባቸው ልንፈቅድ አይገባም።

Ibnu Munewor
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
* ኡማ ላይፍ፦ https://ummalife.com/IbnuMunewor
☑️ በቀደር ማመን ቆራጥ ደፋር ያደርጋል።

አላህ ከቀደረዉ ዉጭ የሚደርስብኝ ነገር የለም ብሎ ስለሚያምን ስለሚመጣዉ ነገር አይፈራም።

~አላህ ከቀደረዉ ወደየት እሽሻለሁ
~አላህ ካልቀደረዉ ለምን እሸ ሻለሁ ይላሉ ።
አልይ ረዲየሏሁ አንሁ

በቀደር ማመን ሠዎች ከተለያዩ ነገር አጉል ቁጭት ዉስጥ የሸይጧን መጠቃቀሚያ ከመሆን ይጠብቃቸዋል።

~
t.me/https_Asselfya