💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🛑👉 ትዳርን ካንድም ሁለት ጊዜ ሞክረው ያልተሳካላቸው አልያም ትዳር ለመያዝ በተሳሳተ መንገድ ተጉዘው ብዙ ጥረት አድርገው የተበላሸባቸው ወይም ከመሰረቱ ለትዳር ያላቸው አመለካከት የተበላሸና የተሳሳተ ለትዳር ምንም ቦታ የሌላቸው አንዳንዶች ትዳርን ስቃይ የተሞላበት እስር ቤት አስመስለው የሚያቀርቡልሽና ተልካሻ ምክንያት እየጠቀሱ ትዳርን እንድትፈሪ አልያም ከትዳር እንድትሸሺ አልፎም ለትዳር መጥፎ አመለካከት እንዲኖርሽ የሚያደርጉ የመሀይማን ንግግር ትተሽ የነዚህ እንቁ የሱና ኡለማዎች ንግግር በደምብ አዳምጪ።

🛑👉 እህቴዋ ትዳር አለም ነው ወደ ትዳር ሩጪ። የነሱ ህይወት አንቺ አትኖሪውም። ለነሱ የገጠማቸው ፈተና ሁሉ ላንቺ አይገጥምም። ተገቢው ጥንቃቄ ከማድረግሽ ጋር ወደ ትዳር አምሪ። ከነሱ ትምህርት ውሰጂ እንጂ በፍፁም እንዳትከተይ። ሞዴልሽ በትዳር ላይ የገፋፍሽ ነብዩን እንጂ እነዚህን አታድርጊ። ትዳር ሪዝቅ ነው። የሁሉም ሪዝቅ ደግሞ ይለያያል። ጎረቤትሽ ድሀ ስለሆነና ስለቸገረው አንቺም ድሀ ትሆኛለሽ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ትዳርም እንዲሁ ነው። ለአንዱ ካልተሳካ ለሌላውም አይሳካም ማለት አይደለም። አላህ ከመልካሙ ጋር እንዲገጥምሽ አበክረሽ ለምኚ። ለትዳር ምንም ግድ የሌላት ችለተኛና ዝንጉ ሴት አትሁኚ። ለትዳር ተገቢው ቦታና ክብር ስጪ። የሴት ልጅ ክብሯ ትዳሯ ውስጥ ነው። እድሜ ቆሞ አይጠብቅሽም። እናት አባትሽ ቤት ደልቶሽ ሁሉ ነገር ተሟልቶልሽ ከምትኖሪ እየቸገረሽም ቢሆን ሷሊህ ልጆች ወልደሽ እየሳምሽ ትዳር ውስጥ መሆንና መሰተርን ምረጪ።

🛑👉 ከዚህ የከፋው ደግሞ የሱና ሰው እንዳታገቢ እውቀት ያለው ተጠንቀቂ ጃሂልም ቢሆን የሚያከብርሽን አግቢ እያሉ የሚዘባርቁ አልያም ወደዚህ የሚያግደመድሙት አደራ አደራ በመቶ ሜትር ከተቻለም ከዛ በላይ ራቂያቸው። አንዳንዶችማ በግልፅ አፋቸው ሞልተው ላንቺ ውዴታ ይኑረው ያክብርሽ እንጂ የሱና ሰው ባይሆንም ብታገቢው ችግር የለውም የሚሉ ገልቱዎች አልጠፋም። እነዚህ ትዳር ውስጥ ከሚገኘው ከአሄራው ይልቅ የዱንያው ጥቅም የሚያስበልጡ ናቸው። እህቴ ከሱና ሰው ውጪ ማንንም አታግቢ። እውቀት ያለው እያለ ጃሂል አትምረጪ። አስተምሬ እመልሰዋለሁ። ቀስ ብዬ እቀይረዋለሁ ብለሽ ያልሆነ ቦታ እንዳትወድቂ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀይሮሽ ነው ቁጭ የሚለው። ከትዳር በፊት በኒቃብ የደመቁ ያልሆነ ቦታ ወድቀው ኒቃብ ያሆለቁ፤ ከትዳር በፊት በሱናና በእውቀት ጠንካራ የነበሩ ባልሆነ ሰው ወድቀው ከሱና አልፎም ከኢልም የሸሹ እጅግ ብዙዎች አሉ። ብዙ የሱና እህቶች እመልሰዋለሁ እቀይረዋለሁ በሚል የቢድአ ሰው አግብተው አልያም ስለዲኑ ምንም የማያውቅ ጃሂል ላይ ወድቀው ትዳሩ ስቃይ የሆባቸው አሉ። አይተውት ነገር ትዳር ነው በዛ ላይ ወልደዋል። መሄጃም የሌላቸው አሉ። በዛ ላይ ብዙዎቹ ከቤተሰብ ተጣልተው ነው የሚያገቡት። አይፈቱ ነገር ለፍች የሚጠይቁዋቸው ብር ብዙ ነው። በዛ ላይ ፍቹ በሱ እጅ ነው። ታግሰው አይኖሩት ስቃይ ነው። ከመከራ ወደ መከራ እየተሸጋገሩ ዝም ብለው ይኖራሉ። ከንዲህ አይነቱ ትዳር አላህ ይጠብቅሽ።

🛑👉 ጃሂል አልያም ሙብተዲእ አግብተሽ ከምትነፍሪና ዘርሽ ከምታበላሺ አደራ ቢበድልሽ እንኳ ሱንዩን አግቢ። በሱ ላይ ታገሺ። ዱንያዊ ፍላጎትሽ ባያሟላና ባያስደስትሽ እንኳ አሄራሽ አያበላሽብሽም። ስትወጪ ስትገቢ በቤትሽ የሱና ሽታ ታሸቻለሽ። ቤተሰብ ጓደኛ ዘመድ አዝማድ ቢመጣ አታፍሪም። ጫት የለ ነሺዳ መንዙማ ዘፈን የለ ፊልም የለ ወንድና ሴት ቅልቅል የለ መገላለጥ የለ። እንደው ለዚህ ስትይ ከሱና ሰው ውጪ ማንም እንዳታገቢ። ቤትሽ በቢድአና በሁራፋት የሞላ ሆኖ የተደላደለ ህይወት ከምኖሪ ከሽርክ ከቢድአና ከሑራፋት የፀዳ ሆኖ አንዳንድ ነገር እየጎደለሽም ቢሆን እየሶበርሽ የሱና ህይወት ብትኖሪ ላንቺ የተሻለ ነው።

🛑👉 አንዳንዶቹ ደፍረው የሱና ሰው አታግቢ ላይሉሽ ይችላሉ። ነገር ግን አንዳንድ የሱና ሰዎች አይብ በመጥቀስ እንድትጠያቸው ያደርጋሉ። ስንትና ስንት በሱና ላይ ያሉ የሰመረ ትዳር የሚመሩ ብዙዎች እያሉ እገሌና እገሊት አታይም እንዴ እያሉ አንድ ሁለት ያልተሳካ ትዳር ይጠቅሳሉ። ደፍረው እውቀት ያለውን ትተሽ ጃሂል አግቢ ላይሉሽ ይችላሉ። ነገር ግን የነሱ መጥፎነት በመጥቀስ እንድትጠያቸው ያደርጋሉ። ስልታቸው ብዙ ቢሆንም አደራ ተጠንቀቂያቸው። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት ብሂላቸው ወደ ጎን ተይው።

🛑👉 ደግሞ በሁሉ ነገር የተዋጣለትና ሁሉ ነገር ያሟላ ትዳር አትጠብቂ። ትዳር ውስጥ ብዙ ችግርና ፈተና አለ። በሶብርና በትእግስት ግን ሁሉም ያልፋል። ትዳር ማለት ያንዱን ጉድለት ሌላው የሚደፍንበት የጋራ መድረክ እንጂ ሁሉ ነገር ያሟላና የተስተካከለ መዝናኛ ወይም መናፈሻ አይደለም። በሁለት ባለትዳሮች መካከል የጠበቀ ግኑኝነት፣ የረዘመ ወዳጅነትና የሚያስቀና ፍቅር በመካከላቸው የሚኖረው ሁሉ ነገር ስለተሟላላቸው አይደለም። ምንም አይነት ግጭት፣ ስህተት ወይም ቅራኔ በመካከላቸው ስለማይከሰት አይደለም። ሚስጥሩ የፈለገ ነገር ቢፈጠር በመተሳሰብ፣ በመነጋገር፣ በመተላለፍ፣ በመመካከር፣ በመተዛዘንና ይቅርታ በመባባል ችግራቸውን ስለሚፈቱና የአንዱ ችግር አንዱ ስለሚሸፍን ነው። ዋናው  ያንዱን አይብ ሌላው ስለሚሰትር ነው። ስለዚህ ትዳርን አትፍሪ። ተገቢውን ሰበቡ አድርሺ። ከዛ በኋላ በጌታሽ ተመኪ።

🔖 ለሁሉም ላላገቡ ሙስሊም ወንድም እህቶቻችን ያማረና የሰመረ ትዳር አላህ ይወፍቃቸው። ከዱንያም ሆነ ከትዳር ፈተና አላህ ይጠብቃቸው። ያገቡትም ትዳራቸው ይባርክላቸው ለኡማው የሚጠቅም ሷሊህ ልጅም ይስጣቸው።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
👍1
አል ካፊያ ሸሪዓዊ ሩቃ ቤት

ሸሪዓውንና ሱናን በጠበቀ መልኩ የቁርአን ህክምና የሚሰጥበት አል ካፊያ ሩቃ ቤት በመምጣት በአሏህ ፍቃድ ሰበብ እንሆነዎታለን።

አድራሻ
አድራሻ ኮ/ቻ ቀበሌ 08 ድልድዩን ተሻግሮ ሁለተኛው ቅያስ ገባ ብሎ። ወይም ከሩሃማ መስጂድ በቀኝ በኩል ዝቅ ብሎ

ስልክ ቁጥር
0960243692
0915508640
ለማንኛውም ጥያቄ
@abureyyis
@abureyyis

https://t.me/al_kafia_ruqyeh_bet
https://t.me/al_kafia_ruqyeh_bet
ክብርሽን ጠብቂ ዋጋ ቢያስከፍልሽ እንኳን‼️

በማያገባሽ አትግቢ በየ ቦታው አትገኝ ድብቅ እንስት ሁኝ ከቀይ ወርቅ በላይ የተወደድሽ ነሽና

ንግግርሽ ያነሰ ተግባርሽ የበዛ ይሁን
ሁሉም ጥሎህ ሲሄድ ከቀብርህ ስፍራ
ካንተው ጋር ይቀራል የሰራኸው ስራ
🔖 ኢስላም ውስጥ አምስት አንገብጋቢ ጉዳዪች !!
➀/ድን

➁/አቅል

➂/ነፍስ

➃/ገንዘብ

➄ /ክብር

👉እነዚህ አምስት ነገሮች በሸሪአችን ትልቅ ትኩረት የተሰጣቸው አንገብጋቢ ጉዳዪቸ ናቸው።

https://t.me/https_Asselfya
Audio
የአደም ልጅ ሆይ !ሀይልህ:ሆነ ብልሀትህ አይጠቅምህም ..በጌታህ ተውፊቅን መገጠም ቢሆን እንጅ

‏الشيخ ‌ #صالح_اللحيدان ⁩ رحمه الله

t.me/https_Asselfya/6823
🌸ውዷ እህቴ 🌸
〰️〰️〰️
#ጓደኛ_ስትይዥ

🔖ትርቂያት  የምትናፍቅሸ
🔖ስትዘናጊ የምታነቃሽ
🔖ዱዓእ ስታደርግ የማትረሳሽ
🔖የህይወት መእበል መንገድ ስትስቺ
የምተመራሽ 
🔖ለአላህ ብላ ብቻ ና ብቻ የምትወድሽ
🔖አይብሽን የምደብቅ ሚስጥርሽን የምጠብቅ የአኼራ ጔደኛ ያዥ
አለበለዚያ ከዚህ ውጭ ያሉት ላች አይበጁሽም


https://t.me/https_Asselfya
ያረቢ አንተን መገናኘት የምናፍቅበትን ዓይነት "ኢማን" ወፍቀኝ !
ጀግና ሴት በዲኖ ብርቱ በመንሀጇ ነብር የወሬ ሳይሆን የተግባር ንቁ ናት

ከትርምስ ቦታ ጫወታ ጫጫታ ከአልቧልታ ወሬ  ምንም አትገኘም

ነገሮች ቢጠሙ ቢያምሩ ቢኮመሩ ቢጠፉ ቢያብቡ ቢለሙ ለሷ ግን አንድ ነው ምንም ፈርቅ የለውም


ጀግና ሴት ዘወትር  አላማዋ በመንሀጅ ሰለፍ ፀታ እና ታጀባ ጀነትን ማግኘት ነው


✍️የኻሊድ ማሚ
ከጠቢባን_አንደበት__!!
قال بعض الحكماء :

إياك والمشي في غير أدب
والضحك من غير سبب .

ያለ ስርዐት ከመራመድ ተቆጠብ
ያለ ምክንያት ከመሳቅም ተአደብ

📚 الآداب الشرعية (٢٢٣/٢).

╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
t.me/https_Asselfya
ይህ ግሩፕ የአረብ ሀገርን ሴት ክብር ማስከበሪያ ግሩፕ ሳይሆን ‼️

ወንድና ሴቱን ባንድ አምገው(ቀላቅለው) እንካስላንቲያ በማለት  ፈሳድ እሚያሰራጩበት ግሩፕ ስልሆነ ሁላችሁም እዚህ ያላችሁ የሱና እህቶች አላህን ፈርታችሁ ውጡ ‼️

በአረብ ሀገር ያሉ እህቶችም ሆነ በአለም ላይ ያሉ ሙስሊም እህቶቻቸው ክብራቸው የሚከበረው መጀመሪያ ራሳቸውን ሲያከብሩ ነው። ራሴን አስከብራለሁ ተብሎ ከወንድ ጋር ተሰልፎ ማውራት ይህ ራስን ማስረከብ ነው ። ሰምታቸኋል‼️
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
ይህ ግሩፕ የአረብ ሀገርን ሴት ክብር ማስከበሪያ ግሩፕ ሳይሆን ‼️ ወንድና ሴቱን ባንድ አምገው(ቀላቅለው) እንካስላንቲያ በማለት  ፈሳድ እሚያሰራጩበት ግሩፕ ስልሆነ ሁላችሁም እዚህ ያላችሁ የሱና እህቶች አላህን ፈርታችሁ ውጡ ‼️ በአረብ ሀገር ያሉ እህቶችም ሆነ በአለም ላይ ያሉ ሙስሊም እህቶቻቸው ክብራቸው የሚከበረው መጀመሪያ ራሳቸውን ሲያከብሩ ነው። ራሴን አስከብራለሁ ተብሎ ከወንድ ጋር ተሰልፎ…
ሢጣሩ ሠምቸ  እያሉ ኑግቡ፣
ምክራቸውን ልቀስም ገባሁ ከግሩቡ፣
ጀግኖችንም አየሁ  የተሠበሰቡ፣
በሳል እህቶቸን ሱናን ያነገቡ፣

ደሥ አለኝ በሩቁ ርእሱን አንብቤ፣
እጠባበቅ ጀመር ተግሳፅን ተርቤ፣


ሰአቱ ደረሠ  ማስታወስ  ጀመሩ፣
በሴቶች ተመራ ወንዶች ተሠተሩ፣
እንቁ የተማሩት  ብዙወቹ አፈሩ፣
ግራ በመጋባት ጥያቄ አሠፈሩ፣
መልስ ሣያገኙ  ወጡ ተባረሩ፣


ቃላታቸው እሬት ወሬያቸው መራራ፣
ስራቸው አያምር  ከአደብ የጠራ፣
ውይይት በሚልሥም ካጂነብይጋራ፣
ትመላለሣለች  ሴት ልጅ በደበፈራ፣
ታይ ለምን ስትባል ድምፄ አይደለም አውራ፣
አውቃለሁ ባይ ሆነች ከሷጋ ማን ያውራ፣
ስርዓት የጣሠ  መሠረቱ ደራ፣
እኔን አሳቀቀይ የያዙት ፉከራ፣


የሡናዋ እህቴ የምልሽ አደራ፣
ፈጥነሽ ተለያቸው አያጋቡሽ ግራ፣
ሀሣብሽ ቢገለፅ እሮሮሽ ቢወራ፣
ያሣለፍሽው ችግር  ያገኘሽ መከራ፣
1.    2  .ብለው ቢጠቅሱ በተራ፣
ቢያሥቡ ቢያሠሉ ትርፍ ከኪሣራ፣
ትተሽ ገለል በይ ሚሥጥሩ እስኪጣራ፣

🤙ውይይት ከተባለ ቅዲሚያ  የሠወችን ሀሣብ ለመቀበል ፍቃደኛ ሁኖ መገኘት ግድ ይላል። በተለይ የሡና እህቶቻችን የሡና ወንድሞቻችን  ለሚናገሩን ንግግር የተለየ ቦታ ሠጥተን በጥሞና አዳምጠን   ለሀሣባቸው ምላሽ መሥጠት እዳለብን  ማሥተዋል ለሚችል ሠው የሚሠወር አይደለም።

👍ለየት ያደረገው ነገር ቢኖር   እኔም በጣም የደነቀኝ ነገር እደት የሡና እህት ወንድሞችን በዚህ መልኩ እናያቸዋለን  ለምን ጥቅር ብሎ አይቀርም  እዲህ አይነቱ ምክር  እህቶቸ   ከእነኝህ ኸይርን አጠብቁ  እዳውም ተማሪን እና አስተማሪን ሊለያዩበት የተሤረ ሴራ ይመሥላል። በብዙ ርዕስ ብዙ ጊዜ ተመክረናል  እዲህ አይነት ጉዲ አላየንም።


🤙በቦት ከደረሰኝ  ምርጥ ግጥም በጥሞና አንብቧት!!  እህታችን አህሰንቲ 👍


=
  የተከበሩ ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን  ሀፊዘሑላህ  የ What Sapp ግሩፕ በመቀላቀል ተጠቃሚ ይሁኑ  ::
➷➷➷➷➷
https://chat.whatsapp.com/LyGimlbL7qk7Ia9dXgEQts


📍ሸር በማድረግ የኸይር ሰበብ ይሁኑ !!
#قـال العلامـة مقبـل بـن هـادي الوادعـي رحمه الله :

‌⁩ هل تعلمين أن عائشة رضي الله عنها لم تنجب ولم يكن لها ذرية، ومع ذلك لم يوجد أثر في كتب السنة النبوية أن عائشة قالت: يا رسول الله إدع الله لي بالذرية .

‌⁩وهل تعلمين أن النبي صلى الله عليه وسلم مات عنها وعمرها ١٨سنة، وكان شديد الحب لها، وكانت شديدة الغيرة، أي عاشت بعده ٤٧سنة، ومع ذلك لم تتحسر على الزواج.

لكنها إشتغلت بالعلم والعبادة وكانت معلمة ومثقفة ومفتيه لكبار الصحابة.
لن تتوقف الحياة:

على الإنجاب.
ولا على الزواج.
ولا على البيت.
ولا على الضرة -الزوجة الثانية-.
ولا على المال.
ولا على موت الوالدين، أو فقد الأبناء!!

ما أخذ الله شيئًا إلا وعوض خيرًا منه، والدنيا دار ابتلاء لم تكمل لأحد أبدًا.

#إملئي قلبك بالإيمان والرضا وحسن الظن بالله، ووقتك بطلب العلم والعمل في كل ما ينفع نفسك ومجتمعك.

#اجعلي الصبر زادك، والقرآن صاحبك:
﴿مَا أَنْزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَى﴾.

لاينبغي للإنسان أن يكون فارغًا؛ لأن الشيطان يتسلط عليه بخواطر السوء، فخير له أن يشغل نفسه بما ينفعه كي لاتشغله نفسه بما يضره.

ختامًا:

# أنصح المرأة الصالحة أن تحرص على مجالسة النساء الصالحات فإنها بهذا تزداد إيمانًا وتزداد علمًا وتزداد بصيرة.


📚 ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﻏﺎﺭﺓ ﺍﻷﺷﺮﻃﺔ ‏( 474/2 ‏) .
"ከቀደምቶች ምክር!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️
የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ አር ራዚይ እንዲህ ይሉ ነበር፦

"ዱንያ የሸይጣን ኸምር -አስካሪ መጠጥ፣ናት እሷን ጠጥቶ የሰከረ ሰው ከስካሩ የሚነቃው ከሙታን እና ከከሳሪዎች ጋር በቁጭት ተሞልቶ የተገናኘ ዕለት ነው"

  📚ጃሚዐልዑሉም ወልሒከም:381

"ከዲንና ከፅናት የማፈንገጥ ዋነኛ ምክንያት በድብቅ የሚሰሩ ወንጀሎች ሲሆኑ በዲን ላይ የመፅናት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ለአላህ ተብሎ በድብቅ የሚሰሩ መልካም ስራዎች ናቸው"

  ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ

t.me/https_Asselfya
👍1