💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🔗 በኢልም የታነፀች የአሊም ቀልብ ሁሌም በብርሀን እና በኑር ላይ ሲሆን!

🔗 ከእውቀት የራቀው የጃሂል ቀልብ ሁሌም በጨለማ ላይ ነው።
Audio
📍خطبة الجمعة
📍የጁሙዓ ኹጥባ
↓↓↓
🌐 الحذر من الفتن

🌐 ከፊትና መጠንቀቅ

🕌 ደሴ አል-አዝሓር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/2969
t.me/abu_reyyis_arreyyis/2969
Audio
◼️እውቀት እና ጅህልና‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖

✅የእውቀት አስፈላጊነትና አሳሳቢነት

✅እውቀት የሁለት ሀገር የስኬት ዋነኛው ቁልፍ

✅እውቀት ወደ አላህ መቃረቢያ ኢባዳ ስለመሆኑ

✅እውቀት መፈለግ ከነዋፊል ኢባዳ መብለጡ

✅የጅህልና አስከፊነትና አደገኝነት

✅ጅህልና የጨለማው የጀሀነም ጉዞ

♨️ጠቃሚ ነጥቦች የተወሳበት ምክር

🔻العلم قبل القول والعمل

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
#በላጭ_ሴት__!!
▬▬▬▬▬▬▬▬
በተውሒድ በሱና የማትደራደር፡
ፈገግታ የሞላት የማትዞር መንደር፡
ዘመድ ጎረቤቷን ወዳጂና አክባሪ፡
የሀላል ንጉሷን የእውነት አፍቃሪ፡
ሀቅ ላይ የፀናች ጥንቁቅ እንስት የምር፡
የውበት አለቃ ሲያዋት የምታምር፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሰለፍይ ኮከብ ያች ኒቃቢስቷ፡
መንሀጂና አቂዳ የህነው ርስቷ፡
በመልካምነቷ ሁሉም ሰው የሚያፍራት፡
አሏህ በችሮታው አሟልቶ የሰራት፡
ስትጓዝ በአደብ ሳብ ያለ ቁመቷ፡
ሀያዕ የለበሰች በወጣትነቷ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ብልጥ አርቆ አሳቢ አስተዋይ የሆነች፡
ሚስትነት የገባት መልካም ሴት ይህች ነች፡
የወንድን ልጅ ህይዎት ምትሞላው ሀሴት፡
የዘላለም ንግስት ይህች ነች በላጭ ሴት፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#በኑረዲን_አል_አረቢ
ሙሀረም 15 1441
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🔜✅ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ❗️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️
#ክፍል_ዘጠኝ↩️
〰〰〰〰〰〰〰

↪️
#የተከበርሽው_እህቴ_ሆይ! ኢብን ሂባን የዘገበውን አቡሁረይራ ረድየሏሁ አንሁ ያስተላለፉትን ታላቅ ሐዲስ አስተውይ ፡

📌"إذا صلت المرأة خمسها ، وصامت شهرها ، وحصنت فرجها ، وأطاعت بعلها ،
دخلت من أي أبواب الجنة شاءت"
↪️“ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሶላት ከሰገደች ፤ ወሯን (ረመዷንን) ከጾመች ፤ ብልቷን ከጠበቀች ፤ ባሏን ከታዘዘች ፤ በፈለገችው የጀነት በሮች ትገባለች፡፡” ኢብኑ ሂባን፡ ጦበራኒይ አል ሙዕጀም አል ወሰጥ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አት ተርጊብ፡

📌وروى اإلمام أحمد من حديث عبد الرحمن بن عوف رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "إذا صلت المرأة خمسها وصامت شهرها وحفظت فرجها وأطاعت زوجها قيل لها ادخلي الجنة من أي أبواب الجنة شئت"

↪️“ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሶላት ከሰገደች ፤ ወሯን (ረመዷንን) ከጾመች ፤ ብልቷን ከጠበቀች ፤ ባሏን ከታዘዘች ፤ በፈለገችው የጀነት በሮች ትገባለች፡፡” አህመድ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አት ተርጊብ፡

ከመጥፎ ተጣሪዎች እርቃ በእነዚህ ታላላቅ ነብያዊ ምክሮች ተጠቃሚ በመሆንና ህይዎቷን በመምራት እድለኛ የሆነች ሴት እንኳን ደስ አላት!

#ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! በዚህ ዘመን የኢስላም ጠላቶች ሂጃብሽን አስወልቀው ከተራ ዱርየዎች ተርታ ሊያሰልፉሽ ተዘጋጅተዋል፡፡ ለዚህ ተንኮላቸው ደግሞ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱት ቴሌቪዥኖች፣ ሞባይሎች ፣ ጋዜጦች እና የተለያዩ ሚዲያዎች ናቸው፡፡

🔷በመሆኑም አንዲት ሙስሊም ሴት አላህ ባዘዛት መሰረት ቀጥ ካለችና ሒጃቧን ባግባቡ ከለበሰች በኢማኗ ጥንካሬ የሚከሰቱ ውዝንብሮችን እና የሰይጣን ተንኮሎችን በአላህ ፈቃድ ትከላከላለች፡፡


↪️ከዚህ ቦታ የኡሙ ሰለማን ረድየሏህ አንሃ ጠንካራ ባህሪ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ረሡል صلى الله عليه وسلم ልብሱን በኩራት እየጎተተ ስለሚሄድ ወንድ ስለሚያጋጥመው ቅጣት በተናገሩ ጊዜ ኡሙ ሰለማ ረዲየሏህ አንሃ ሴቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ስትጠይቅ “አንድ ስንዝር ታስረዝም” አሏት “እንደዛ ከሆነማ እግሮቻችን ይገለጣሉ” አለቻቸው፡፡

“በቃ አንድ ክንድ ታስረዝም ከዚህ በላይ እንዳትጨምር” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ አህመድ፡ ቲርሚዚይ፡ ነሳኢይ፡ዘግበውታል

↪️ኢማኗ የደከመባት ሴት በተቃራኒው አንድ ስንዝር ወይም አንድ ክንድ ወይም ከዚያ በላይ እንደ ኢማኗ ድክመት አካሏን ትገልጣለች፡፡


↪️ለቅኑ ጎዳና እንዲመራሽ ፤ ግልጽም ከሆነ ስውር ፈተና እንዲጠብቅሽ ፤ እርሱን
በመታዘዝ ላይ እንዲያግዝሽ ፤ በሐቁ ላይ እንዲያጸናሽ አላህን እማጸናለሁ፡፡ እነሆ አላህ ዱዓን ሰሚና ተቀባይ ነውና ፡፡

【በዚህ ተጠናቀቀ 】

▪️ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ

👉ውድ እህቴ ሆይ እኔም አልኩሺ ሂጃብሺን አደራ! ሂጃብሺ እኮ የመከበሪያሺ ፣የውበትሺ፣የኢማንሺ ፣የሀያዕሺ መለኪያ ነውና ጠብቂው ስረአቱን ጠብቀሺ ልበሺው ሂጃብ ከአላህ ሱበሀኑሁ ወተአላ የተሰጠን ኒዕማ ፀጋ ነው!!

🖊እሙ ፋሩቅ


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w

↪️ከክፍል አንድ ጀምሮ ለማገኘት⤵️⤵️⤵️

https://t.me/Asselefya1/1617
አጠቃላይ ምክር ለሙስሊሟ ሴት. በሸይኽ ሐሰን ገላው ሃፊዞሁሏህ (19-11-2013)
✅ አዲስ ሙሓደራ
↩️ محاضرة جديدة

↪️ #ርዕስ – "አጠቃላይ ምክር ለሙስሊሟ ሴት"
↩️ بعنوان: "نصيحة عامة للمرأة المسلمة"

🎙 በሸይኽ ሐሰን ገላው ብን ሐሰን ሃፊዞሁሏህ
🎙 لفضيلة الشيخ حسن غلاو بن حسن
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ተውሂድን በተግባር
<unknown>
✅ተውሂድን በተግባር

ከክፉ መጠበቂያዎች

🟢 መከራ ሲገጥመን

🟢 ከመኝታ በፊት

🟢 ከፈርድ ሰላት በኋላ

🟢በሉ የተባልነውን ከልባችን እንበል


http://t.me/Abuhemewiya
✅❝በመሸነፍ ውስጥ ያለ ማሸነፍ❞
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️"አላህን ፍራ" ለሚልህ ተሸነፍ። በአላህ ለሚገስፅህ ተሸነፍ። ከጥፋት እንድትመለስ፣ ወደ መልካም እንድትዞር ለሚጎተጉትህ አቀራረቡ ባያምርህም ተሸነፍ። ወንድሜ ሆይ! ለሐቅ እጅ መስጠት ሽንፈት አይደለም። ከመሰለህም ግዴለህም ተሸነፍ። ነፍስያህ እንደዚያ አስመስላ ብታቀርብብህም ነፍስያህን በመርታት አሸንፍ። አስተውል! ከመሙ ጫፍ ላይ ድል ያለበት ሽንፈት ማሸነፍ ነው።

..🖊𝐔𝐬𝐭𝐚𝐳 𝐈𝐛𝐧𝐮 𝐌𝐮𝐧𝐞𝐰𝐨𝐫 «𝐇𝐚𝐟𝐢𝐞𝐳𝐞𝐡𝐮𝐥𝐥𝐚𝐡»


https://t.me/Asselefya1
👉ትንሽ ካነበብኩት ላካፍላችሁ ወደድኩ!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
↪️ምላስን በመጠበቅ የሚገኙ ፋይዳዎች↩️
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹አላህ በተከበረው ቁረአን እንድህ ይላል
وَإِن تَعُدُّوا۟ نِعْمَةَ ٱللَّهِ لَا تُحْصُوهَآ ۗ
የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡{{አንነሕል ፣18}}
وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍۢ فَمِنَ ٱللَّهِ ۖ
""ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ነው፡፡{{አን ነሕል፣ 53}}

↪️አላህ በኛላይ የዋለልንን ጸጋ ቆጥረን አንዘልቀውም።

↪️አላህ ለሰው ልጅ ሁለት ታላላቅ ጸጋዎች እንደሰጠ በተከበረው ቁረአን ግልጽ አደረገ።

أَلَمْ نَجْعَل لَّهُۥ عَيْنَيْنِ : وَلِسَانًۭا وَشَفَتَيْنِ
''"ከእርሱ ሁለት አይኖችንአላደረግንለትምን ?ምላስንም ሁለት ከንፈሮችንም አላደረግንለትምን?){{አል በለድ ፣8-9}}

↪️አዎ❗️ እነዚህ ሁለት ታላላቅ ጸጋዎች አላህ ለሰው ልጅ ለግሷል።

↪️የሁለቱ ዓይኖች ጸጋ ለመመልከት ፣የምላስ ፀጋ ደግም በሁለት ከንፈሮች እገዛ ንግግር ለመናገር፣

↪️ ልክ ለዓይናችን መከላከያ ሽፋፎች እንዳሉት ሁሉ፣ ለአፍ መሸፈኛ ደግሞ ሁለት ከንፈሮችን ንግግርን ለመናገር አድርጓል።

🔻ምን ታላቅ ጸጋና ስጦታ አደረገው!

↪️እርሱን የምናመሰግንበትና እርሱ ለሚወደው ተግባር የምንጠቀምበት እንዲያደርገን አላህን እንማጸናለን።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹ምላስንና ሁለቱን አይኖች አላህን ለመታዘዝ እንጅ ለሌላ አላማ አለመጠቀም።
🔹ምላሳችን አላህን ከሚያስቆጣ ነገር መጠበቅ።የአላህን ጸጋ ከማመስገን ይቆጠራል።
🔹ምላሱንና አይኑን በመጠበቅ አላህ ያከበረው ሰው በታላቅ ጥቅሞች ፣አጠቃላይ በሆኑ መልካሞች ፣ተቆጥሮ በማያልቅ የዱኒያና የአኼራ ፍሬዎች እድለኛ ይሆናል።

💦ምላስን በመጠበቅ የሚገኙ የተወሰኑ ጥቅሞች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
1⃣}}ምላስን መጠበቅ ወንጀል ለማሰረዝና ስራ ለማስተካከል ስበብ ይሆናል ።

↪️አላህ በተከበረው ቁረአን እንድህ
ይላል

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا.
يُصْلِحْ لَكُمْ أَعْمَٰلَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَمَن يُطِعِ
ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدْ فَازَ فَوْزًا عَظِيمًا
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ፡፡ሥራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና፡፡ ኀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል፡፡ አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ፡፡{{አህዛብ፣70-71}}

2⃣}}}ምላስን መጠበቅ ጀነት ለመግባት ዋስናነው።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
፣
፣
🔺በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል!✍
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ሹሩጡ ሶላት #1
ኢብኑ/ሙነወር
ደርስ፦
~~~
* ኪታቡ፦ የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ "ሹሩጡ ሶላት"
* ክፍል፦ አንድ
* በመርከዘ ተውሒድ ለሚማሩ ተማሪዎች እየተሰጠ ያለ
* ሰዓት፦ ዘወትር ቅዳሜ ከመግሪብ በኋላ
* የኪታቡን pdf በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፦
⤵️⤵️⤵️
https://t.me/IbnuMunewor/2098
↪️↪️↪️↪️↪️
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
#እውቀትን_አትደብቅ ‼️‼️

ታላቁ ሊቅ ሼይኽ #ሷሊህ_አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ
قال العلامۃ صالح الفوزان
حفظه الله

الداعيۃ الذي لا يحذرو من دعاۃ الضلالۃ يعتبرُ من الكاتمين العلم

አንድ ዳዒ የሆነ ሰው ከጠማማ ዳዒዎች የማያስጠነቅቅ ከሆነ ይሄኔ እውቀትን ከደበቁት ሰዎች ውስጥ ይቆጠራል ።

https://t.me/abuUseyminabdurehman
ናፍቆኛል
➖➖
አንቺ ውዷ እህቴ ሰው ሀገር ያለሽው፣

የባእድ ሀገራት ነዋሪ የሆንሽው፣

ትዳርሽን ትተሽ ስራ ላይ ያለሽው፣

ባልሽን ልጅሽን የትም የበተንሽው፣

ወላጆችሽ ናፍቀው አንቺ የሌለሽው፣

አይናፍቁሽሞይ ሆነሽ ከወዳኛው።

እኔስ በጣም በጣም በጣምም ናፍቆኛል፣

ሀገር ተመልሰሽ ባይሽ ደስ ይለኛል፣

ወላጆች ቢደሱ ናፍቆታቸው ወጥቶ፣

ትዳር የሌላችሁ ሷሊህ ባል ተገኝቶ፣

ትዳርም ያላችሁ ትዳራችሁ ሰምሮ፣

ባየው ደስ ይለኛል ሁሉ ነገር ሞልቶ።

እህቴ በውጭ ሀገራት ስራ ከመፈለግ
መጥተሽ ከቤትሽ ውስጥ
ልጅ መውለድ ማሳደግ፣

ይልመድብሽ እህት ተውበሽ በተውሂድ፣

ወድህ ይመርብሽ በቤትሽ ማእረግ።

እስከዛው ነይቺ በዱኣሽ ላይ ፅኒ፣

ትዳርሽ ይናፍቅሽ ዱኒያዋን ቀንሺ።

ከሰው ቤት አንቱታ ይሻላል የራስቤት፣

ጎዶሎው ቢበዛም ስላላት ንግስትነት።

በሰው ከመታዘዝ እንቅልፍን ከማጣት፣

በሀሳብ ከመጓዝ ወዲህ ከመሰልቸት፣

የምትወጪበትን ከመቁጠር እለታት፣

ነይና ተደሺ ወላጅም ይደሰት።

ነይና ተደሺ ወላጅም ይደሰት።
💦💦💦💦💦💦💦
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ወደ ጠንቋይ (አውቃለሁ ባይ ጋር መሄድ በኢስላም እንዴት ይታያል ?

ይህ ተግባር በጣም ክልክል ነው !

አንድ ሰው የሩቅ እውቀት እናውቃለን በሚሉት ሰዎቺ ሳያምንባቸው እራሱን ለመጥቀም ብሎ የሄደ ሰው ቢሆን እንኳ ከባድ ወንጀልን ሰርቶል ፡፡

ነብዩ መሀመድ (ﷺ) አቡ ዳውድ በዘገቡት ሐዲስ " ወደ ጠንቋይ ወይም አውቃለሁ ባይ ዘንድ የሄደና የሆነ ነገር የጠየቀ ሰው የአርባ (40) ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም " ብለዋል

ወደነሱ ሂዶ የሚሉትን ያመነና የተቀበለ ሰው ደግሞ በነብዩ (ﷺ) ሃይማኖት የካደ ነው ፡፡

ነብዩ ሙሀመድ (ﷺ) አቡ ዳውድ በዘገቡት ሐዲስ "ወደ ጠንቋይ ወይም አውቃለሁ ባይ ዘንድ የሄደና የሚለውን ያመነ በሙሀመድ ላይ በተወረደው ቁርአን ክዷል " ብለዋል

===========================
🖍 አብዱል ከሪም አል ሀናኒ
===========================
https://t.me/https_Asselfya