💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
Audio
☑️ ዲን ከርስ የሚሞላበት ሳይሆን ጀነት የሚገባበት ነው

ሰሌን ላይ የሚተኙት ዉዱ ነብያችንአለይሂ ሰለቱወሰላም

የሳቸው ተከታይ በመሆንህ ደስ ይበልህ !

ፈጣሪህን አመስግን !

🎤ሙሐመድ ሲራጅ ሙ ኑር
https://t.me/Muhammedsirage
በይቁኒያህ 003
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
አዲስ ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
  〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
     
📚የደርስ አይነት፦ መትበይቁንያ!!

📝مـــتـــن الــبــيــقــوـــنيــة

🎙
አቅራቢ፦ኡስታአቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም ሀፊዘሁላህ

📥 የኪታቡ 𝐏𝐃𝐅 ⇣⇣⇣
« t.me/https_Asselfya/5517
☑️ ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ወደ መስጂዶች መጓዝ ከጂሀድ ፊ ሰቢሊላህ ይመደባል። እርሱም ወንጀልን ያስምራል።

📚መጂመዑ_ረሳዒል 35/4

ፈጅር.........
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☑️ የጧት ዚክር እንዳንረሳ!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡

(ቲርሚዝይ)
==
ሁለት ነገሮችን ውደድ:-
✔️ዝምታንና፣
✔️ፈገግታን።

=
ኹጥባ አህሉሱና ሰለፍዮች ናቸዉ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም
«የጁሙዓ ኹጥባ»

☜أهل السنة هم السلفيون

አህሉ ሱና ሰለፊዮች ናቸዉ!!

🕌 ኮ/ቻ አንሷር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣
t.me/abu_reyyis_arreyyis/7527
✍️ ለሰዉ ይቅርታ ማድረግ ቀላል ነገር ቢሆንም የነበረንን እምነት መልሶ ማግኘት ግን በጣም ከባድ ነዉ።

=
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته. حفظك الله ورعك

قال سبحانه في سورة الصافات عن إبراهيم عليه السلام ( وقال إنّي ذاهب إلى ربّى سيهدين)٩٩"

وقال تعالى أيضاً في سورة يٓس. (أولم يروا أناخلقنا لهم ممّا عملت أيدينآ أنعمًا فهم لها مالكون)٧١"

الشاهيد إلى ربّى و بأيدينآ

የእነዚህን ተፍሲር ምንድን ነው ማንስ ፈሰራቸው ከ3 ክፍለ ዘመናት ነቅል ቢደረግለን?
t.me/ustaz_Kedir_ahmed_fetwa_group/88828
✍️ የተሻልክ ሆነህ መገኘት ያለብህ  ከሌላ ሰዉ ሳይሆን  ከትናንትናዉ ማንነትህ ነዉ

=
ወደ ተውሒድ ጥሪ ማድረግ
Abdusomed MNur
ወደ ተውሒድ (لا إله إلا الله ) ጥሪ ማድረግ አለብን።

🎤በኡስታዝ አብዱሶመድ ሙሐመድ ኑር

https://t.me/https_Asselfya
➪ጀግና ይወለዳል።
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ከመስጅድ በር ላይ ጠላት የሚያሶግድ፡
ፍፁም ለጠላቱ የማያሸነግድ፡
የእምነቱን ህግጋት የሚያስከብር በግድ፡
ጭቆና ሲበዛ ገለባው ይጠራል፡
ከሙስሊሞች መሀል ልባም ይፈጠራል፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
የኢስላም ጠላቶች ቢጫወቱብንም፡
ማስተዋል ከጀመርን ተስፋ አለን አሁንም፡
ባዕድ አምልኮትን ሽርክን ስናስቀረው፡
ሾናት ጭሌ ቆሌን ስንሰባብረው፡
በተውሒድ ላይ ፀንተን ሀቁን ስናከብረው፡
ሱናውን ምድር ላይ ስንተገብረው፡
ያኔ ለሙስሊሞች አንዱ አምላክ ይፈርዳል፡
ከመካከላችን ጀግና ይወለዳል፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
 የዱንያ ውዴታ በልባችን ነግሶ፡
ግፍና መከራ በደል ተደግሶ፡
መሞት እየፈራን ኢማናችን አንሶ፡
የሙስሊሞች መብት ተንቋል ጨርሶ፡
የቁርኣን መቀደድ የመስጂድ ፈረሳው፡
የሚስኪን ቤት መናድ ብሎም የመድረሳው፡
ከአማኞች ልብ ላይ መች ነው የሚረሳው!?
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
አመፅ በርትቶብን ወንጀላችን ከፍቶ፡
አየሩ ታውኮ የሰው ደም ከርፍቶ፡
ሰው በዘር ይሸሻል ከአሏህ ሸፍቶ፡
“ሸሂድ ልሁን” ብሎ የሚነሳ ጠፍቶ፡
ከእስልምናህ ፍቅር ዘር ከቀደመብህ፡
ወላሒ ወቢላህ መመርመር አለብህ፡
እንደ ሙስሊምነት ጤና ይጎልሀል፡
ጎደሎ ፍጡር ነህ ማስተዋል ያንስሀል፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በነጋ በጠባ ለአመፅ እየታጨን፡
የመስጂዱ መፍረስ በምን ልብ ይቁጨን፡
በመጥፎ አስተሳሰብ በዘር ተበክለን፡
ሽርክና ቢዲዐን እንደ ጉድ ታድለን፡
በዘር ሰልፍ መሀል ተሰድረን ቆመን፡
ከአሏህ እርቀን እጂግ በጣም ታመን፡
በክፉ ጠላት ላይ ለስልሰን ከጎመን፡
እባካችሁ እያልን ይዘናል መለመን፡
ይሔው እንስቃለን መስጂዱን አውድመን፡
እኔ እምለው...!?
ግፈኛን ታቅፋ በምትሸልም ሀገር፡
አልላከቅ ካለች ተጣብቃ እንደ መዥገር፡
መስጂድ ፍርስራሽ ላይ ለተሰራች ሸገር፡
ማን ሰሚ አለንና እንደት እንናገር፡
የእናቶች እንባ የህፃናት ሲቃ፡
ከጧት እስከ ማታ ሆኖ በፈረቃ፡
የንፁሀኖች ደም ሲሆን እንደ ጭቃ፡
እንደ ሰበር ዜናው ተላመድነው በቃ⁉️
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በተቻለኝ አቅም እኔ ግን አላምንም፡
ከኢስላሜ አይበልጥም ማንም ሆነ ምንም፡
ነፍሱ በአካሉ  እስካለ በምድር፡
አማኝ በእምነቱ አይቀርብም ድርድር፡
ሙዕሚን ሰው አይደለም ግፍ ለምዶ ሚያድር፡
ተውሒዲን ያወቀ ሱናን የተረዳ፡
ከጨለማው መሀል የበራ ማለዳ፡
የፍትህን አርማ ይዞ እንደ መታገል፡
ሲያሸረግድ ያድራል ለሸይጧኖች ግልገል፡
ፉላን ፉላን ብሎ ቆጥሮ ከአንድ እስከ አስር፡
ሲናከስ የሚውል በዘረኝነት ስር፡
በእደነዚህ አይነት ብንሸማቀቅም፡
እኛ በእስልምና ድርድር አናውቅም፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
መንገድ ጠፋን እንጂ ዝግጁ ነን እኛ፡
ቋንቋ አይከልለንም የኛም ሆነ ኬኛ፡
ሲለመን አይወድም ጥንትም በደለኛ፡
ታሪክ የነገረን አንድ እውነት ግን አለ፡
የሰው ልጅ በደል ላይ ከተደላደለ፡
የሚስኪኖች እንባ ደም ሆኖ ካየለ፡
በዚሁ ከቀጠለ ይህ ግፍ ሄዶ ሄዶ፡
መመለሱ አይቀርም አንድ ጀግና ወልዶ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በዘር ተተብትበን ምንም ባንግባባ፡
በአሏህ የአመነ ዙሮ ወደ ከዕባ፡
መስጂዳችን ሲፈርስ ብናፈስም እንባ፡
በእምነታችን ብቻ ቢበዛም ወከባ፡
ጀግና ይወለዳል ከግፍ በስተ ጀርባ፡
መከራው ሲበዛ አማኝ ያዛመዳል፡
የፖለቲካውን ተጨባጭ ይረዳል፡
ሰው ከዘሩ በላይ እምነቱን ይወዳል፡
ከሽርክም ከጥመት በተውሒድ ይፀዳል፡
ያኔ በአሏህ ፈቃድ ጀግና ይወለዳል፡፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ጀግና ከመከራ መካከል ይፈለቀቃል፡፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
✍️በኑረዲን አል አረቢ➊➍➍➍
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
❝የአቡ ረይስ ኢብኑ ኢማም ዋትሳፕ ደርስ ግሩፕ ይቀላቀሉ⟱⟱⟱⟱

❝ ኮድ ⓵ ⇘⇘
chat.whatsapp.com/Hy8VXIPn2kwDcpSJZ0Y1a1

❝ ኮድ ⓶⇘⇘
chat.whatsapp.com/D1Sh8x6HoJlJArrzMrwOUD

❝ ኮድ ⓷⇘⇘
chat.whatsapp.com/D1SwoMDQ5CE7ypmQ2ulTuR

⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰