💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.66K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
📩 ከቀደምቶቹ የ24 አመቷ ድንቅ መልካም እንስት ..!!

➷ፋጢማ ቢንት አል ኢማሙል በርዛሊ ትባላለች (የሞተቸው በ24 አመቷ) ነው።

➷እች መልካም እንስት በዚህ እድሜዋ ቁርአንን ሀፍዛለች፣ ሀጅም አድርጋለች፣ ከበርካታ የሀዲስ ሊቆችም ሀዲስን ሰምታለች፣ ሀዲስ የሰማችባቸው መሻይኾች ወደ (185) ገደማ ይደርሳሉ።

➷እቺ መልካም እንስት በዚ እድሜዋ "ሶሒሁል ቡኻሪን" ሙሉውን በእጇ ፅፋለች።

➷አባቷ ስለርሷ እንዲህ ይላሉ፦

➷ልጄ የተባረከች ልጅ ነበረች፣ ፈርድና ሱና ዒባዳዎችን በብርታት ትሰራ ነበረ አያመልጣትም ነበር፣

➷የተለያዩ መልካም ስራወች በመስራት ላይ በጣም ትጉህ ነበረች።

➷ባል አግብታ ለአምስት አመት ያክል ከባሏ ጋር ቆይታለች ፡ ታዲያም በዚህ አግብታ በቆየችበት ግዜ በጣም አንገብጋቢ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አንድም ቀን እንኳ ከቤቷ ወጥታ አታውቅም ነበር- ለአንገብጋቢ ጉዳይ ከወጣችም ባሏን አስፈቅዳ ነበር የምትወጣው።

➷ከርሷ የሚያስደስተኝን ነገር እንጂ አይቼ አላውቅም።

➷ሰላት ስትሰግድ በማያት ግዜ በጣም እደሰትና እንዲህ እል ነበር፦ ጌታዬ አላህ ሆይ ! በዚች ልጄ አኸራ ላይ ተጠቃሚ አድርገኝ።

➷ልጄ ከተፈጠረች ጀምሮ ዱንያዊ ጥቅማጥቅም ነገር ጠይቃኝ አታውቅም። የሆነ ነገር ግዛልኝ ብላኝም አታውቅም።


📚 أعيان العصر وأعوان النصر للصفدي (31/30/4)


https://t.me/https_Asselfya
☑️ ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

ሶብር አድርጊ። ምንዳሽንም ከአላህ ፈልጊ። ያለሽበት በሆነው ሸሪአዊ ሂጃብ (ኒቃብ) ላይ ፅኚ። የሰዎች ንግግር፦ አክራሪ ናት፣ አጥባቂ ናት ቢሉሽ ምንም አይጎዳሽም።

📚فتاوى نور على الدرب
‏﴿ يَا أيُّهَا الّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا علَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيما ﴾.

#تلاوة من سورة الأحزاب. الشيخ: محمد السبيّل
☑️ የዱኒያንና የነዋሪዎቿን ባህሪ ጠንቅቆ ያወቀ ሰው----

 ▪️መጥፎ ሰው መሆንን እንጂ መባልን አይፈራም።
 ▪️ጥሩ ሰው ለመሆን እንጂ ለመባል አይጥርም።
 ▪️የበጎ ስራዎቹን ምንዳም ከአላህ እንጂ ከሰዎች አይጠብቅም።

➙የሰው ልጆች አብዛኞቹ ከሃዲና ውለታ በይ ናቸው።
አይደለም ፍጡርን የሰው ልጅ ፈጣሪውንም ከማማረርና በመጥፎ ከመጠርጠር ወደኋላ አይልም።

ኢማም አሽሻፊዒይ እንዳሉት ሁሉን ማስደሰት መቼም የማይሳካ ግብ ነው።

ብልህ ጌታውን የሚያስደስትበትና ለራሱ የሚበጀውን መንገድ ይዞ ይጓዛል።
በእንቅስቃሴዎቹ ሁሉ ትልቅና ዋና አላማውን አላህን ማስደሰትና ኣኺራውን ማስተካከል ያደርጋል።


=
https://t.me/https_Asselfya
🎈እህቴ ሆይ !በሂጃብሽ ንግስት ሁኝ!!
   〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
☑️ ሼኸ ህ ሷሊህ አልፈውዛን "አላህ ይጠብቃቸው" እንዲህ አሉ።

ሴት ልጅ ፊቷን ገልጣ የምትወጣ ቢሆን ኖሮ ሊያጫት ለሚፈልግ ሰው ሂድና ተመልከታት የሚል ፍቃድ ባላስፈለገ ነበር።

📓اتحاف الطلاب | ٣٨٥
=

https://t.me/https_Asselfya
በኢባዳ ላይ መፅናት
abdu shikur abu fewzan
↪️ አዲስ ሙሐደራ
  


☞ በዒባዳ ላይ መፅናት !!

🎙በአቡ ፈዉዛን «አብዱ ሽኩር»

🕌በኢማሙ ማሊክ መስጅድ አሶሳ

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
🛍ጥሩ እናት ለልጇ እንዲህ ብላ መከረች!!


ልጄ ሆይ
【عندما يغضب زوجك أغلقي أذنيك وعندما تغضبين أقفلي فمك..وستكون الحياة جميلة】
ባልሽ በተቆጣ ጊዜ ጆሮሽን ያዢ። አንቺ በተቆጣሽ ጊዜ አፍሽን ዝጊ። ይህ ካደረግሽ የትዳር ህይወትሽ ያማረና የሰመረ ይሆናል።

=
https://t.me/https_Asselfya
▪️ ሁሌም እውነተኛ ሁን !!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
📩አዛኙ ውዱ ነብያችን እንዲህ በማለት ይመክሩናል

▪️አደራ እውነተኛ በመሆን ላይ
▪️እውነት ወደ መልካም ተግባር ይመራል
▪️መልካም ተግባር ደሞ ወደ ጀነት ይመራል

=
https://t.me/https_Asselfya
"  እኔ እወድሻለሁ"
==========

እህቴ ጠንክሪ  በተውሂድሽ ብቻ።

በጨመረ ቁጥር የጥላት ጥላቻ፣

ወዳጆችሽ ይብዙ ጠላትሽ ይኮሽሽ፣

አይዞሽ እህቴ ሁሌም ከጎንሽ ነኝ፣

አብሬ አልጠላሽም ሙስሊም እህት ነኝ፣

ጉዞሽን ቀጥይ ከሰለፎች ጋራ፣

ጆሮሽ እንዳይሰማ ያወራ ቢያወራ፣

እህቴ በርችልኝ ከተውሂድሽ ጋራ፣

ሀያሽን  ጠብቂ ከአቂዳሽ ጋራ፣

እወድሻለሁኝ ኑሪልኝ በደህና፣

መልካምሽን እንጂ ክፉሽን አልስማ፣


🍃🍃🌺🍃🍃

https://t.me/https_Asselfya
☑️ ብልህ ሙዕሚን የዚህችን ዱኒያ ማሸንገያ አታሸነግለውም ሁሌም ለመጨረሻው ቀን(ለአኼራው ) ለፊ ነው!

ሁሌም ለአኼራው ሚሆነውን ስንቅ ለማዘጋጀት አመቺ ሚሆኑ እናም ወደ አላህ ይበልጥ ሚያቃርቡ ጊዜያቶችን እድል አያስመልጥም!

እኛም ከትክክለኛ ሙዕሚኖች ዘንድ እንድንመደብ ይህን ትልቅ እድል ጠፊ በሆነችው ዱኒያ ማስመለጥ የለብንም!


      {بَلْ تُؤْثِرُونَ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا※وَٱلْـَٔاخِرَةُ خَيْرٌۭ وَأَبْقَىٰٓ}

{ይልቁንም የዱኒያን ሕይወት ትመርጣላችሁ※
የመጨረሻይቱ አኺራ (ሕይወት) በላጭ እና ሁል ጊዜ ዘውታሪም ናት}

አላህ ጊዜያቸውን በአግባቡ ከሚጠቀሙት ያድርገን!

=
https://t.me/https_Asselfya
ኢስላምን መገንዘብ
NABAWI TUBE
ኡስታዝ ሳዳት ከማል

ኢስላምን መገንዘብ

በበድረል  ኩብራ  መስጂድ
የቀረበ  ሙሐደራ

t.me/NABAWITUBE
☑️ እናታችን አኢሻ (رضي الله عنها) እንዳስተላለፈችው የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል።

«እናንተ ሰዎች ሆይ! (ከመልካም) ስራ የምትችሉትን ያክል ብቻ ያዙ። እናንተ እስካልተሰላቻችሁ አላህ አይሰለችም። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስራ ትንሽ እንኳ ብትሆን ዘውታሪነት ያለውን ነው።»

[ 📖 صحيح البخاري (٥٨٦١) ]
=

t.me/https_Asselfya