💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
የቀልብ ዶክተር ችግሮች ❶
🎙 በወንድም አቡ ዒምራን ሙሐመድ
የቀልብ ዶክተር ችግሮች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
ራሱን የቀልብ ዶክተር በማለት ሰይሞ በቴሌግራም ቻናልና ግሩፕ በመክፈት ለሚንቀሳቀሱት ማንነታቸው ለማይታወቅ አካላት ይድረስ


ይ ቀ ጥ ላ ል

🎙 አቡ ኢምራን ሙሐመድ መኮንን

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
📌📌 ከሶለዋት ምንዳ ውስጥ📌📌

♻️- وعنْ عبداللَّه بن عمرو بن العاص، رضي اللَّه عنْهُمَا أنَّهُ سمِع رسُول اللَّه ﷺ يقُولُ: مَنْ صلَّى عليَّ صلاَةً، صلَّى اللَّه علَيّهِ بِهَا عشْرًا

📌♻️ የአላህ መልእክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል።

{{በኔ ላይ
#አንድ ሶላት ያወረደ አላህ በሱ ላይ #በአስር እጥፍ አድርጎ ያወርድበታል ። }}
📚 رواهُ مسلم.

♻️ وعن ابن مسْعُودٍ  أنَّ رسُول اللَّهِ ﷺ قَالَ: أَوْلى النَّاسِ بِي يوْمَ الْقِيامةِ أَكْثَرُهُم عَليَّ صَلاَةً

📌♻️የአላህ መልእክተኛ (صلى الله عليه وسلم) ቀጣዩን ተናግረዋል ሲል ኢብኑ መስኡድ (رضي الله عنهما) አስተለሰልፏል።

🔺🔻የውመል ቂያማ ወደኔ ቅርብ የሆነና የኔን ሸፈአ (ምልጃ) ለማግኘት ይበልጥ ተገቢው ሰው ማለት፦
#በኔ #ላይ #ሶለዋትን #የሚያበዛው #ነው


📚 رواه الترمذي وقال: حديثٌ حسنٌ

https://t.me/https_Asselfya
↪️ ብልጥ ሁኝ ↩️
🔹ጨዋ ሴት ፎቶ አትፖስትም
🔹ቆንጆ ሴት ፎቶ አትፖስትም
🔹አስተዋይ ሴት ፎቶ አትፖስትም
🔹አሏህን ፈሪ ሴት ፎቶ አትፖስትም
📌♻️ልቦና በህይወትና በሞት ደረጃ ከሆነ ልቦችን በሶስት ከፍለን መመልከት እንችላለን።

1📌♻️.ሰላማዊ የሆነች ቀልብ፣ በማንኛውም መልኩ ሰላማዊ የሆነችና ሽርክ የሌለባት ቀልብ ነች።ይልቁንም በመውደድ ፣በፍላጎት፣በመመካት፣ተፀፅታ በመመለስ፣በመዋደቅ፣በመፍራትና በተስፋ አሏህን ጥርት አድርጋ ታመልካለች።

👉 ከወደደች ለአሏህ ብላ ትወዳለች፣ከጠላች ደግሞ ለአሏህ ብላ ትጠላለች፣ከሰጠች ለአሏህ ብላ ትሰጣለች ፣ከከለከለች ደግሞ ለአሏህ ብላ ትከለክላለች።ለማንኛውም ነገሯ ዳኛዋ በረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ የወረደው ህግ ነው።በአቂዳም በንግግርም በተግባርም ከአሏህ ህግ ውጭ ሌላን አታስቀድምም።

2.📌♻️የሞተች ቀልብ፣ምንም ህይወት የሌላት ነች፣ጌታዋን አታውቅም፣አትገዛም ትዕዛዙን አታከብርም ፣አላህ የሚወደውን አትሰራም፣ ይልቁንም የአላህ ቁጣ እና ጥላቻ ቢኖርበት እንኳ ከስሜቷ ጋር ነው የምትንቀሳቀሰው፣ ፍርሀቷም፣ ተስፋዋም፣ ውዴታዋም፣ ጥላቻዋም፣ማላቋም፣ ማዋረዷም፣ ከአሏህ ውጭ ነው።ስትወድም ስትጠላም ስትሰጥም ስትከለክልም ለስሜቷ ነው። ስሜቷና የዱንያ ፍላጎቷ ኢማሟ(መሪዋ) ማሀይምነት ሹፏሯ ዝንጋቴ መርከቧ ነው።

3📌♻️.ህይወትና በሽታ የተቀላቀለባት ቀልብ፣ ይህች ቀልብ ሁለት ገፅታዎች ያሏት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ አንድኛው ገፅታ በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላኛው ገፅታ ያሸንፋታል።እርሷ ከሁለቱ ወደ አሸነፈው ትሆናለች።በውሥጧ የአላህ ውዴታ፣ኢማን፣ ኢኽላስ እና ተወኩል አላት።ይህ የህይወት ገፅታዋ ነው።ስሜት ፣ ምቀኝነት ፣ ኩራት ፣በራስ መደነቅ እና የበላይነትን መፈለግ የጥፋትና የክስረት ገፅታዋ ነው።ይቀጥላል
https://t.me/https_Asselfya
Audio
ዛሬ የተደረገ ደስ የሚል የጁሙዐ ኹጥባ

🍃ስለ ተዉባ

🎤በወንድም አብዱ ሽኩር

በኢማሙ ማሊክ መስጂድ
https://t.me/https_Asselfya
አላህን ማሥታወሥ ያለዉ እና ትሩፋት


🔸አላህን ማሥታወሥ ነፍሥያ እና ሸይጧን ላይ ድል የመቀዳጃ ትልቅ በር ነው
🔹 ወደ አላህ ሡብሀነ ወተዓላ መዳረሻ መንገድ ነው
🔸 አላህ ሡብሀነ ወተዓላ የዚክርን በር የከፈተለት ሰው የሁሉንም የኸይር በሮች አግኝቷል
🔹የዚክር በር የተዘጋበት ሰው የኸይር በሮች ተዘግተውበታል
🔸ዚክርን አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ያገራለት ሠው ዒባዳዎች ሁሉ ይገሩለታል
🔹ዚክር የከበደውና ከዚክር የሠነፈ ሰው ከዒባዳዎችም ይሠንፋል
🔸 ዚክር ማብዛት ሸይጧንን ከሰው ልጆች ያርቃል
🔹ዚክር አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ያሥደሥታል፣የአዱንያን ጭንቀት ያሥወግዳል
🔸በልብ ውሥጥ ደሥታን ይፈጥራል፣የደረቁ ቀልቦችን ያረጥባል
🔹ወንጀሎችን ያራግፋል የብቸኝነትን ስሜት ያሥወግዳል ከአላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ ቅጣትም ይጠብቃል
🔸 ዚክር የሚያበዛ ሠው ከሙናፊቅነት ይድናል
🔹የቂያማ ቀን ከመፀፀት እና ከመቆጨትም ያድናል
🔸ጀነት ላይ የሰው ልጆች አትክልት እና ፍራፍሬ የሚያገኙትም በአዱንያ በሚያደርጉት ዚክር ልክ ነው፡፡

🔹የህሊናን እረፍት ይሠጣል
🔸ዚክር የሚል ሰው ላይ የአላህ ራህመት ይወርድበታል፣ መላኢኮች ዙሪያውን ይከቡታል
🔹 በአዱኒያ ዚክር ለሚያበዛ ሰው አላህ ግንባሩ ላይ ኑርን ይሠጠዋል፣
ቀብር ውስጥም አላህ ብርሃንን ይፈጥርለታል፡፡
🔸የቂያማ ቀንም በአዱኒያ ያደርገው የነበረው ዚክር ሲራጥን በሠላም እንዲሻገር ያደርገዋል፣ ፊቱም ያበራል፡፡

↪️ለዚህም ነው አላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ የሠው ልጆች ዚክርን እንዲያበዙ በተለያዩ የቁርኣን አያዎች (አንቀፆች) ያዘዛቸው፣

💦 ረሡልም ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም በብዙ ሀዲሶች ዚክርን ማብዛት እንዳለብን ገልፀዋል፣ ዚክር የሚያበዙ ሰዎች የሚያገኙትን ትሩፋትም ጠቅሠዋል፣
🚩አላህ ሡብሀነ ወተዓላ በቁርኣኑ
يَا أَيُّهَا الَّذَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا
وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
(ሡረቱል አህዛብ፡41-42)
[ "እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ :—አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ብዙ ማሥታወሥን አሥታውሡት ጠዋትና ማታም አጥሩት"] ይላል
https://t.me/https_Asselfya
በአራት ነገራቶች አማካኝነት የልብ ድርቀት ይፈጠራል‼️

🔹 ከልክ በላይ መብላት
🔹ብዙ መተኛት
🔹ብዙ ማውራት እና
🔹 አላስፈላጊ የሆነ መቀላቀል ሲከሰት

↪️እነዚህን ነገሮች ከሚፈለገው በላይ ከተጠቀምናቸው ልባችን መድረቅ እንደሚችል ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁሏህ አልፈዋኢድ በተሰኘው ኪታባቸው ላይ አስፍረዋል።ሁሉንም በመጠኑ ለማድረግ እንሞክር ‼️
https://t.me/https_Asselfya
📍خطبة الجمعة
📍የጁሙዓ ኹጥባ
↓↓↓
🌐 የጀነት ፀጋዎችና የጀነት መግቢያ መንገዶች

🌐 نعيم الجنة وسبل الوصول إليها

🕌 ደሴ አል-አዝሓር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/2849
ወንድሜ

የትም ሆነህ አላህን ፍራው!

በቀን፡በማታ በጫካ፡በገደል በየትም ሁኔታ ላይ ሁን ጌታህ ያይሀል እና አላህን ከመፍራት ወደ ኀላ አትበል፡፡

አላህን በትክክል ከፈራሀው

☞ የእውተኛ መለያ ብርሀን ያደርግልሀል
☞ወንጀልህን ያብስልሀል
☞ ይምርሀል

ሰለዚህ ወዳጄ አላህን በመፍራት ላይ ጠንከር በል አደራ !

አላህ (ﷻ) አንዲህ ይለናል

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن تَتَّقُوا اللَّهَ يَجْعَل لَّكُمْ فُرْقَانًا وَيُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያን ብርሃን ያደርግላችኋል፡፡ ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከእናንተ ላይ ያብስላችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡

https://t.me/https_Asselfya
#እንዲሁ በተለምዶ ሚስት ብቴድ
በሌላ ሚስት ትተካለች ይባላል፦
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#አንዳንዴ ግን ፍፁም በሌላ ሊተኩ የማይችሉ
ፍፁም የማይረሱ የትዳር አጋሮችም አሉ።

#የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በርካታ ሚስቶች ኖሯቸው ሳለ "በርግጥም አላህ ከኸዲጃ የተሻለችን ፍጹም አልተካኝም" ብለው በግልጽ ተናግረዋል።

#ቀኝ እጅ እና የቁርጥ ቀን ወዳጃቸውም ነበረች ሁሉም ሰው ፊቱን ሲያዞርብኝ እሷ ግን በኔ ፍፁም እምነት ነበራት! ረሱል ﷺ ስለ ኸዲጃ رضيﷲ عنها ከተናገሩት.. !!
💦መስለማ ቢን አብዱል መሊክ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

መልካም ሚስት ለአንድ ሙእሚን ከሁለት አይኑ፣ ከሁለት እጁና ከሁለት እግሩ በላይ አስፈላጊና በላጭ ነች።
📚【 أحسن المحاسن للثعالبـﮯ : ٣٦٨ 】
➡️አንዳትሞኝ ንቃ‼️

አይንናስ ቡዳ ቢይዝህ መልከኛ ነኝ‼️ ወይም ሀብታም ነኝ ‼️ብለህ እንዳታስብ የያዘብህ ምክኒያት ከአሏህ ዚክር በመራቅህ ምክኒያት መሆኑን አስታውል።
የጧት ዚክር


سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ: عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ. (3× إذا أصبح)

‘ ‹‹ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ ምስጋናም፡፡ በፍጡራኑ ቁጥር ልክ፤ ነፍሱ በወደደችው ልክ፤ በዙፋኑ ክብደት ልክ፤ በቃላቱ ብዛት ልክ፡፡›› ሦስት ጊዜ

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلاً مُتَقَبَّلاً. (إذا أصبح)

‹‹ኣላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን, መልካም የሆነ ሲሳይን, ተቀባይነት ያለውን ተግባርን እጠይቅሃለው፡፡››-

أَسْتَغْفِرُ اللهَ وَأَتُوْبُ إِلَيْهِ. (100× في اليوم)

‘አላህን ምህረትን እምፀ ናለሁ፡፡ወደርሱ በፀፀት እመለሳለሁ፡፡››- በቀን መቶ ጊዜ

اَللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ. (10×)
አላህ ሆይ! በነብዩ ላይ ሰላምታ አውርድ፡፡ ሰላም አስፍንም፡፡›› አሥር ጊዜ .’

https://t.me/https_Asselfya
☞የዱንያን ጭንቀት አትሸከሚ ዱንያ የአላህ ነች
☞ስለ ርዝቅሽም አትጨናነቂ ርዝቅም ከአላህ ነው
☞ወደፊት የሚያጋጥምሽን ችግር አታስቢ በአላህ እጅነው ያለው ሁሉም ነገር

☞ስለ አንድ ሀሳብ ብቻ ተጨነቂ አላህን እንዴት ማስደሰት እንደምትችይ አላህን ካስደሰትሽ ተደስቶብሽ ያስደስትሻል መብቃቂያሽ ሆኖልሽ የደስታን ሀብት ይሰጥሻል ።ከሃብት ሁሉ ትልቅ ሃብት የልብ ሃብት ነው።አቂደን መገንዘብ ነው።ሀላሉን ከሀራም ለይቶ ማወቀና ጠቃሚና ጎጂን መለየትነው።አብሽሪ ሁሉም ነገር ጊዜው ስደርስ በአሏሀ ምርጫ ይመጣልናል።ሪዝቃችን ማንም አይነጥቀንም።ዬትም አያመልጠንም አሏህ የፃፈልን ነገር እሺ
☞ልብሽ በደማበት የህይወት ችግር ተስፋ አትቁረጪ
☞ወደ አላህ ተጣሪ ወደ ኸይር ቀይርልኝ ብለሽ
☞ሀዘን በስግደት ይጠፋል
☞ደስታ በዱአ ይመጣል
ብቻ ምን ልበልሽ

ለነገሮች በጣም ቦታ ሰጠሽ አትጨናነቂ ሰበቡን አድርሺ ከዚያም በጌታሽ አሏህ ተመኪ "በእርሱ የተመካ ሁሌም ኡፍፍፍፍፍፍፍ እንዳለ ነው

https://t.me/https_Asselfya
Audio
ምክር ለሴቶች‼️


ሴቶችን ትዳር አልባ ያደረጉ ዋና ዋና ጉዳዮች

🇸🇦ከቤተሰብ መራቅ
🇸🇦ገንዘብ ማሯሯጥ
🇸🇦ትዳርን መፍራት
🇸🇦የማይገኙ መስፈርቶች


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
በአላህ ፍቃድና እገዛ ዛሬ ከአሱር ሰላት በኀላ ረውደቱል ባዲኢን የ122 ሀዲስ ቂርአት ደርስ ከቀኑ 10:30 ላይቭ በቴሌ ግራም ይተላለፋል። አድራሻ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
የሱጁደሰህው [የመርሳት ሱጁድ]
ምክንያቶች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
በሶላት ውስጥ የመርሳት ሱጁድ የሚፈጸምባቸው ምክንያቶች ሶስት ሲሆኑ፦
❶ኛ፡- መጨመር
❷ኛ፡- መቀነስ እና
❸ኛ፡- መጠራጠር ናቸው፡፡

❶ኛ፡- #መጨመር
መጨመር፡- ማለት አንድ ሰው በሶላቱ ውስጥ ሩኩኡን ወይም ሱጁዱን ወይም ቂያሙን ወይም ቁኡዱን ( መቀመጡን) ከመደበኛ ቁጥሩ በላይ መጨመር ማለት ነው፡፡

❷ኛ፡- #መቀነስ
መቀነስ፡- ማለት አንድ ሰው ከሶላት ማዕዘናቶች ወይም ዋጅባቶች ከመደበኛ ቁጥሩ መቀነስ ማለት ነው፡፡

❸ኛ፡- #መጠራጠር
መጠራጠር ፡- ማለት ሶስት ወይስ አራት ረከዓ ነው የሰገድኩት? ብሎ መወላወል ማለት ነው፡፡

↪️ #መጨመር ጭማሬን አስመልክቶ አንድ ሰው በሶላቱ ውስጥ ሆን ብሎ ሩኩዕ ወይም ሱጁድ ወይም ቂያም ወይም ቁኡድን ከጨመረ አላህና ረሱል ካዘዙት ውጭ በመተግበሩ ሶላቱ ተቀባይነት አያገኝም፡፡
የአላህ መልክተኛ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ቡኻሪና ሙስሊም በተዘገበ ሐዲስ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"من عمل عملا ليس عليه أمرنا فهو رد"
رواه البخاري ومسلم
“የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ እርሱ ተመላሽ ነው፡፡”
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
ከሶላቱ ላይ ረስቶ ቢጨምር ግን ሶላቱ አይበላሽም፡፡ ነገር ግን ከሰላምታ በኋላ የመርሳት ሱጁድ በመስገድ ሊጠግነው ይገባል፡፡
ለዚህ ማስረጃው ኢብን መስኡድ ያስተላለፉት ቡኻሪ እና ሙስሊም የዘገቡት ሐዲስ ነው
ነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የዙህር ሶላትን አምስት ረከዓ አድርገው ሰገዱ፡፡ ካበቁ በኋላ “ሶላት ተጨመረ እንዴ? በማለት ተጠየቁ፡፡ እርሳቸውም “ምንድን ነው?!” አሉ “አምስት ረከዓ ነው እኮ የሰገድከው!” አሏቸው፡፡ ወደቂብላ በመዞር እግራቸውን አጠፉ፡፡ ከዚያም ሁለት ሱጁዶችን ሰገዱ፡፡

↪️ #መቀነስ (ማጉደል) ከሶላት ማዕዘናቶች (ፈርዶች) አንዱን ቢያጎድል አማራጮች የሚከተሉት ናቸው።
➲ ከሁለተኛው ረከዓ ተመሳሳይ ቦታ ሳይደርስ የረሳውን ቀድሞ ቢያስታውስ የረሳውን ማዕዘን ተመልሶ ይፈጽም፡፡
➲ ከሁለተኛው ረከዓ ተመሳሳይ ቦታ ላይ የረሳውን ቢያስታውስ ሁለተኛውን ረከዓ ላመለጠው ማዕዘን ትክ ያድርግና ሌላ አንድ ሙሉ ረከዓ ይስገድ፡፡
በእነዚህ ሁለት ባህሪያት ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ያድርግ፡፡

ለመጀመሪያው ምሳሌ፡- በሁለቱ ሱጅዶች መካከል ሳይቀመጥ አንድ ሱጁድ አድርጎ ወደቂያም ሄደ ፋቲሃን ሊጀምር ሲል አስታወሰ ወዲያው ይመለስና የረሳውን ሱጁድ ይፈጽም ፡፡ ከዚያም መጨረሻ ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ያድርግ፡፡

ለሁለተኛው ምሳሌ፡- በሁለት ሱጁዶች መካከል ሳይቀመጥ አንድ ሱጁድ ረስቶ ከሁለተኛው ረከዓ ተመሳሳይ ቦታ ላይ አስታወሰ የዚህ ጊዜ የሁለተኛው ረከዓ እንደአንደኛ ረከዓ ተቆጥሮ ሌላ አንድ ረከዓ ይጨምር ከዚያም አሰላምቶ ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡

➡️ ማዕዘን ሳይሆን ዋጅብ ነገር ቢያጎድል ለምሳሌ “ሱብሃን ረቢየል አእላ” የሚለውን ዚክር ረስቶ ቢነሳ ሶላቱን ዝም ብሎ ይቀጥል ፡፡ ከሰላምታ በፊት ሰጀደተ ሰህው ያድርግ፡፡ ምክንያቱም ነብያችን - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የመጀመሪያውን አታህያቱ በረሱበት ወቅት ወደሶላታቸው ቀጠሉ እንጅ አልተመለሱም፡፡

↪️ #መጠራጠር፦ መጠራጠር ማለት ጨመርሁ ወይስ ቀነስሁ? ብሎ መወላወል ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ሶስት ሰገድሁ ወይስ አራት ረከዓ ሰገድሁ ብሎ ቢወላውል ከሚከተሉት ሁኔታዎች አይዘልም፡-
መጨመር ወይስ መቀነስ ከሚለው ከሁለቱ እርግጠኝነቱ ያመዘነውን ይውሰድና ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡
ከሁለቱ አንዱ ሚዛን ካልደፋለት ግን እርግጠኛ የሆነበትን ይውሰድ እርሱም አነስተኛው ቁጥር ነው፡፡ ሶስት ወይስ አራት ሰገድሁ? ካለ ሶስትን ይውሰድና አራተኛውን ረከዓ ሞልቶ ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡

ማጠቃለያ፦
➲ ከዋጅብ ነገሮች አንዱን ዋጅብ ከተወ ወይም ከረከዓዎች ቁጥር አንዱ አመዛኝ አልሆንለት ብሎ ከተጠራጠረና አነስተኛ የሆነውን ቁጥር ወስዶ ከሰገደ ሰጀደተ ሰህው ከሰላምታ በፊት ተፈጻሚ ያደርጋል፡፡
➲ ከሶላቱ ላይ ረከዓ ከጨመረ ወይም ተጠራጥሮ ከሁለቱ አንዱ አመዛኝ ከሆነለት ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ያደርጋል፡፡
مجموع الفتاوى محمد بن صالح العثيمين (1/ص
https://t.me/https_Asselfya
👉በዘመናችን ትልቁ ፈተና

ሁለት የሰለፍያን መንሀጅ የሚከተሉ ጥንዶች አለመገናኘታቸው ነው።

➡️የቢድአ ሰወች ምሳሌ⬅️

↪️የቢድአ ሰወች ሱና ጋ ያላቸው ምሳሌ

ወርቅና አጥንት እንደተጣለለት ውሻ ማለት ናቸው ‼️
💦ሱና ወርቅ ነች ብልሆች እንጂ አያነሷትም
🔻ቢድአ ጥንብ ነች ውሾች እንጂ አያነሷትም ‼️
ፍቅርን በትዳር ውስጥ ፈልጉት.......
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
💢ኢስላም በፍቅር ዙሪያ ከማንም የማይዋሠው ግልፅ እና የማያሻማ አቋም አለው። ለዚህ ነው በታላቁ መለዕኮታዊ መፅሐፍ (በቁርዓን) ውስጥ ስለፍቅር እና ተያያዥ ነጥቦች በተደጋጋሚ የተወሣው።

🔺በመሠረቱ ቁርዓን ፍቅር እና ውደታን
በተለያዬ ቃላቶች በስፋት ገልፆታል ለምሣሌ፦
መወዳ
ሁብ
ሸገፍ
ወልይ እና ሌሎችም..

♻️ፍቅር በትዳር ውስጥ ሲሆን፦ ደስታ፤ ሐሴት፤ እርካታ፤ የልብ መረጋጋት፤ እርስ በርስ መተማመን፤ እንድሁም እዝነት(ራሕማ) ....አለው።
🚫ፍቅር ከትዳር ውጭ ሲሆን ደግሞ፦ የልብ ሕመም (ስቃይ) ፤ከሸይጧን ፈተና ላይ መውደቅ፤ በስሜት መነዳት፤ ወንጀልን መዳፈር፤ አላህን ማመፅ ፤ ከአላህ መራቅን፤ ያስከትላል።

ፍቅርን ከጋብቻ በፊት አትግባበት❗️

ተሳስተህ (አዳልጦህ) ከገባህበት ግን መድሃኒቱ አንድ እና አንድ ብቻ ነው - እሱም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ፦
#የፍቅር መድሃኒቱ ያፈቀርካትን ሴት ማግባት ነው።

👁‍🗨ግን ፍቅር ምንድን ነው

ፍቅር መልካም ተግባር ነው፤ፍቅር የምናደርገው ድርጊት ነው፤ፍቅር ስሜት አይደለም፤ፍቅር የራስን ስሜት እና ፍላጎት ማሟላትን አይወክልም፤ትክክለኛው ፍቅር ላፈቀሩት እና ለወደዱት ሰው በቅን ልቦና የሚያከናውኑት ተግባር ነው።ፍቅር የደግነት ተግባር ነው መልካም ቃላትን መናገር ለአፈቀሩት ሰው መራራት እና ማዘን፤መርዳት እና ማመስገን ፈገግ ማለትን እና ማገዝን የሚወክል ቃል ሲሆን ሌሎችም መልካም ተግባራትን ያካትታል።


https://t.me/https_Asselfya