💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.66K subscribers
1.29K photos
494 videos
125 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
◾️ግራ እንዳትጋባ፦ የዲን ባለቤቷን አግባ‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

✅ ታዋቂው የዲን ሊቅ፣ የታሪክ ምሁርና የኢልም፣ የሲድቅ፣ የፊቅህ ባለቤት የሆነው ኢስሀቅ ቢን ራሀወይህ፦ አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት አገባ። የዚህች ሴት ባል ከመሞቱ በፊት የኢማሙ ሻፍእይና የሌሎች ኡለማዎች የኪታብ ክምች ነበረው። ሰዎች ለኢስሀቅ ሌሎችን ትተህ ይህችን ሴት እንዴት መረጥክ ብለው ጠየቁት። እሱም፦ ለኪታቦቹ ብዬ ነው። ሴት ልጅ ለኪታቧ ሲባል ትገባለች አላቸው።

📚(السير للذهبي ص 70/ج 10)

➲የኢልምና የዲን ጥፍጥና ያወቀ ሰው ከምንም በላይ ዲን ያላትን ይመርጣል። በተለይ በዚህ ዘመን በኢማን በተቅዋ የተገነባች ሴት ከምንም በላይ ወሳኝ ነው። የአብዘሀኛው የትዳር ችግር መንስኤው መሰረቱ ዲን ባማከለ መልኩ ባለመገንባቱ የሚፈጠር ነው።

➲ አንዳንዱ ግን ያሳዝናል። የትዳር አጋር ሳይሆን በግ ይመርጥ ይመስል የሌለ።መስፈርት በማስቀመጥ ወፍራም ቀጭን፣ ጥቁር ነጭ፣ አጭር ረጅም እያለ የዲን ባለቤቷን ትቶ አስተምራታለሁ፣ እቀይራታለሁ በሚል ሂሳብ መልክ፣ ገፅታ፣ ሀብትና ዘር በማየት ዲን የሌላትን ሚመርጥ በዝቷል። እቀይራለሁ ብለው አግብተው ተቀየረው የቀሩ ስንቶች እንዳሉ አላወቀም።

➲እውነተኛ ደስታ፣ የማያልቅ ሀብት፣ ዘላቂ እፎይታና በረካ ያለው ከዲን ባለቤቷ ጋር ሲሆን ብቻ ነው። የፈለገ መልክ ቢትረፈረፈ፣ ሀብት ቢሞላ ዲን ከሌለ ሁሌም ስቃይ፣ ጭቅጭና መከራ ነው። እንዲህ አይነት ትዳር እድሜውም አጭር ነው።

➲ ሀብት አይተህ ካገባህ አላቂና ጠፊ ነውና ሀብቱ ሲያልቅ የትዳርህ ጉዳይ ያበቃል። መልክ አይተህም ካገባህ ሁለት ሶስት ስትወልድ ይረግፋልና የዛኔ የትዳርህ ማገር ይፈርሳል። ተቅዋ፣ ሀያእ፣ ኢማንና ዲኗን አይተህ ካገባህ ግን የማይጠፋና የማይፈርስ፣ ሁሌም ከሷ ጋር የሚቀር ነውና ትዳርህ ያማረና የሰመረ ሆኖ ይቀጥላል።

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ሞት በኡስታዝ ሳሊም
« አዲስ ልብ የሚነካ ሙሀደራ »
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️


➡️ሞት‼️

➲ስለሞት የሰለፎች ወርቃማ ንግግር!!

➲ከሰለፎች የሞት ስካር!!

➲የዑመር አሟሟት በሰፊው የተዳሰሰበት!!

🎙በኡስታዝ አቡ ሙስዓብ ሳሊም

በሀርቡሰለፍዮችመድረሳ-አህሉ-ተውሂድ-
አጠቃላይ የሚለቀቁ ፕሮግራሞችን ለማግኝት
📲 Telegram channel
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/altewhiduawelen
ወይም➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/sefinetunuh
👍1
✍ ስለ ወለጋ ምን ማለት ይቻላል ጎበዝ ..??

▪️ የሰውን ልጅ አላህ ከሌላው ፍጡር ለየት ያደረገው እንዲያስብ ነበር ግን በኛው ዘመን የሰው ጭንቅላት ተሸክመው ግን የሰው አስተሳሰብ ሳይሆን እንደ እንስሳ የሚያስቡ ሰዎች ስላየሁ በግሌ በጣም አዝኛለሁ ሓቂቃ..!!

▪️ይገርማል የወለጋ ነገር ያሳዝናል የወለጋ ነገር ወላሂ ሰው የራሴ ሀገሬ ብሎ ንብረቱን ያፈራበትን ቤተሰብ የመሰረተበትን ሀገር ያለ ምንም #ቅሪት እያባረሯቸውና እያስሰደዷቸው ይገኛሉ ..!!

▪️ በአሁን ግዜ የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታዋን ስናይ ሁሉም ሰው በዘሩ እና በቋንቋው ብቻ አንድ ወደሚሆንበት ሀገር ብቻ መሄድ ያለበት ይመስላል ሓቂቃ..!!

▪️ ተውጅ በአላህ..!! መጠጣችሁ የሰው ደም አይሁን ..!! እረ ይቅር ለልጆቻችሁ የዘርን ጥላቻን አታውርሱ እርስ በእርስ የተዋለደን ሰው አታገዳድሉ እረፉ !! እንስሳ እንኳ እንዲህ ጨካኝ አይሆንም አዑዙቢላህ ..!!

▪️እኔ እንደራሴ የወለጋን ግፉ የምገልፅበት ቃላትም የሉኝም ወላሂ ነው የምላችሁ የነሱን ግፍ ለማወቅ እስኪ ከዛ ተሰደው የመጡትን ጠይቁ ፣ እንዲሁም እየሰማን ያለነውንም እዩ ጉድ የሰው ልጅ ሂወት የረከሰበት ሀገር ማለት #ወለጋ ነው ሓቂቃ ..!!

▪️ግን እኔ የገርመኝ ሰውን በመጨፍጨፍ ዝም ብሎ አራሽ ገበሬዉን መዝረፍና ማሳደድ ማባረር ለነሱ እረፍት ከሰጣቸው ያው አብዝሃኛው #ወጥተውላቸዋል ደስ ይበላቸው ግን ወላሂ ምን አይነት ሰዎች እንደሆኑ አየናቸው ሓቂቃ ..!!

▪️ ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ ዘረፉ ጭፍጨፋ የሰው ሞት ነው የምንሰማው ከዝሁ ሀገረ ወለጋ ግን የሚገርመው ገዳዮቹም እነዛው የጫካው #አውሬዎች ናቸው አላህ የጃቸውን ይስጣቸው ..!!

▪️ እኔ ብቻ እንደው አላህ ይሁናችሁ የምለው ግን እንደ ሀሳብ እነዝህን ሰዎች አምናችሁ እዛ አትቀመጡ ነው የምለው በሰላም ሀገር ቆፍሮ መብላት ይሻላል ካቂቀን እንደው የሰው ደም የጠማቸው ሰዎች ጋር እንዴት ነው የምንቀመጠው በአላህ ..??

▪️ የመንግስትንም ነገር እያችሁት እያየነው ነው እዛ የሚደርሰው ህዝቡ ካለቀ ከተጨፈጨፈ ቡሀላ ነው ለዝህም የቶሌው ጭፍጨፋ አምሳያ ነው የሚሰራው #ሸፍጥ እኮ ጉድ ነው እናንተየ

▪️ እናም ወገኖች አብሽሩ ወደ አኼራህ የሄዱ ሙስሊም አባቶችን እናቶችን ወንድሞችን እህቶችን አላህ ይማራቸው አላህ ሶብሩን ይወፍቃችሁ አብሽሩልኝ

✍ አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን አልጀበርቲ

http://t.me/abuUseyminabdurehman
http://t.me/abuUseyminabdurehman
👍1
ኹዝ_አቂደተክ_በአብዱረህማን_አቡ_ዑሰይሚን.apk
78.3 MB
📚የኹዝ አቂደተከ ሚነል ኪታቢ ወሱና ሶሂሀ ሙሉ ቂርአት!!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖


📲አንዴ ብቻ በማውረድ ባሻዎት ጊዜ ያለ ኔት እንደፈለጉ መጠቀም ይችላሉ!!

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

➡️በአቂዳና በተውሂድ ጉዳይ ወሳኝ ቂርአት ስለሆነ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ይድርጉት!

【الدال على الخير كفاعله】

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
t.me/abuUseyminabdurehman/11389
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/abuUseyminabdurehman
✍️ለሴቶች ብስራት!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️

📚ተንቢሀት ኪታብ በፁሁፍ መልኩ ተከታታይ ቀረበላችሁ!

➧ከታች ባለዉ ሊንክ ገብታችሁ ተከታተሉ ትጠቀማላችሁ!!

✍️በእህታችን ኡሙ አብዲላህ
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/beytbenatasselfyat
https://t.me/beytbenatasselfyat
🔊ታላቅ  የሙሀደራ  እና የኒያ ፕሮግራም
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🏢በአል ኢህሳን የየቲሞች ሴንተር የመርከዝ ግንባታ ልዬ የሆነ  የዳዕዋ  ፕሮግራም ዝግጂት!

⏰እለተ áˆ°áŠž ምሺት 3:00 ጀምሮ ይጠብቁ!

➡️ተጋባዥ የሱና  ኡስታዞቻችን ወንድሞቻችን"
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️


🎙ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀሰን ኢንዲሪስ
       ➧ርዕስ፦የሀገር ሰላም አሳሳቢነት!!

🎙ወንድም አቡ ፈውዛን አብዱ ሽኩር
     âž§áˆ­á‹•áˆľ ፦ሁለየም ሀቅ የበላይ ነዉ!!

🎙ወንድም አቡ ረይስ ኢብኑ ኢማም
     ➧ርዕስ፦የሴቶች አለባበስ ገፀታ!!

የፕሮግራም መሪዎች አቡ ሂበቱላህ እና አቡ ማሒ

ውድ የሱና  እህት  ወንድሞች  የአል-ኢህሳን መርከዝ አላማ  በአሏህ  ፍቃድ  እውን ይሆን ዘንዳ አል-ኢህሳን  ሁሌም  ጥሬዋን  በአላህ  ስም  ታስተላልፋለች ::

ይህንን ልዬ  የሆነ  ፕሮግራም  ጥሪ በመታደም  ሌሎቹንም  በመጋበዝ  አሻራዎትን በመጣል ሃላፊነትዎን  እንድወጡ  ስንል  ጠርተነዎታል ::

አል-ኢህሳን መርከዝና የየቲሞች መረዳጃ ማህበር

መቅረት á‰€áˆ­á‰ś áˆ›áˆ­áˆá‹ľ á‹Ťáˆľá‰†áŒŤáˆ  ይታደሙ!!

📲ፕሮግራሙ  የሚተላለፍበት ሊንክ አድራሻ!
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/AlihsanCharityAssociation
t.me/AlihsanCharityAssociation
Audio
አላህ ሆይ ልባችንን ለቁርአን አግራልን። ቀልባችን በቁርአን አለስልስልን።
ይደውሉ ይዘዙን መርሀበን እንላለን
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
ኑረዲን አል አረቢ
0920479868
ጀውሐር
0939786740

ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
በአሏህ እገዛ
ሀላል የሆነን እና የቻልነውን አብረን እንሰራለን

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
@jewharandnuredinonlinemarket
@jewharandnuredinonlinemarket
السلام وعليكم ورحمة الله وبركاته
አስደሳች ዜና ለከለላ ወረዳ ሙስሊሞች በሙሉ በተለይ ደግሞ ለከለላ እና አካባቢዋ ላላችሁ ሰለፍዮች።
      
ታላቅ የሙሐደራ እና የኮርስ ፕሮግራም የዛሬ ሳምንት ከቀን ጁመአ  ከህዳር 30/2015  ዓ·ል ጀምሮ እስከ ታህሳስ 02/2015 ዓ·ል ድረስ ታላቅ የሙሐደራናየኮርስ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል ።
ከተለያዬ አካባቢ የሚመጡ ኡስታዞች ና መሻይኾች

✅ሸይኽ አብዱሶመድ ከከለላ
✅ሸይኽ ሙሃመድ መኪን ከደሴ
✅ሸይኽ አህመድ አወቀ ከኮምቦልቻ
✅ሸይኽ ሙሃመድ ጘዛል ከደሴ
✅  ኡስታዝ ሰኢድ በያን ከቲርቲራ
✅ኡስታዝ አብዱረህማን (አቡ ሂዛም) ከአፋር
✅ኡስታዝ አቡ አረይስ ሙሐመድ ኢማም ከደሴ
✅ወንዲም  ኡቡ ኡሰይሚን አብዱረህማን ከደቡብ ወላይታ
✅ወንድም ኑረድን አል አረቢ ሀፊዞሁሙሏህ
ሌሎችማ ተሳታፊዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።


  የዳዕዋ ፕሮግራም
   በከለላ፣በቲርቲራ፣በልጓማ፣በሻፊ፣በደገር
የኮርስ ፕሮግራም ፦በከለላ እና ልጓማ


ማሳሰቢያ:— በቀን በታህሳስ 02/2015 ዓ·ል በሁሉም ቦታ ያለን ሱና ወዳድ ወንድምና እህቶች ሆይ በከለላ ሰላም መስጅድ(ትልቁ) ከጧቱ 02:30—06:30 ድረስ ሞቅ፣ደመቅ፣ፏ ያለ የዳዕዋ ፕሮግራም ስላለ መጥተን ተጠቀሚዎች እንድንሆን ስንል በደስታ እንገልፃለን።

ተጨማሪና የሚቀየር ፕሮግራም ፣ማን የት ያደርጋል የሚለውንና የመስጅዶችን ስም በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ ኢንሻ አሏህ።

ሌሎች ፕሮግራሞችን እና ሙሉ የከለላ ሰለፍዮችን እንቅስቃሴ ለማግኘት ቴሌግራም ቻናል⤵️⤵️⤵️

https://t.me/kelelaqiratcenter
https://t.me/kelelaqiratcenter;

የቴሌግራም ግሩፕ⤵️⤵️⤵️
https://t.me/yeselefyadaewakelela
https://t.me/yeselefyadaewakelela
ኡሱሉ_ሰላሳ_በአብዱረህማን_አቡ_ዑሰይሚን.apk
110.8 MB
📲አድስ አፕልኬሺን ተለቀቀ
〰️〰️〰️〰️〰
️〰️〰️〰️

📚የኡሱሉ ሰላሳ ሙሉ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖


ለመቅራት እንዲያመች የኪታቡ ሙሉ የድምፅ ማብራሪያ ከፒድኤፉጋ አብሮ የተዘጋጀ ነው!


በአፕልኬሽን መልኩ ስለተዘጋጀ አንዴ አውርደው እንደፈለጉ መጠቀም ይችላሉ!!

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴ሸር በማድረግ የኸይር ሰበብ ይሁኑ!

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/abuUseyminabdurehman/11470
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
t.me/abuUseyminabdurehman
✔️እውቀት እና የእውቀት ባለቤቶችን መውደድ!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

▪️قال ابن القيم :

ኢማም ኢብኑ-ል-ቀዩም ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

فمن أحب العلم وأهله فقد أحب ما أحب الله .
«እውቀትን እና የእውቀት ባለቤቶችን የወደደ በእርግጥም አላህ የወደደውን ነገር ወዷል።»

[مفتاح دار السعادة (٤٣٥/١)]
[📚 መፋቲሂ ዳሩ ሰአዳ (435/1)]

▪️وقال أيضا :
አሁንም እንዲህ አሉ፦

فمحبة العلم من علامات السعادة
وبغض العلم من علامات الشقاوة .

«እውቀትን መውደድ ከደስታ ምልክት ነው፤ እውቀትን መጥላት ከእድለቢስነት ምልክት ነው።»

[مفتاح دار السعادة (٤٣٥/١)]
📚መፋቲሁ ዳሩ ሰአዳህ (435/1)

▪️وقال أيضا :
እንዲህም አሉ፦

حب العلم وطلبه أصل كل طاعة
وحب الدنيا والمال وطلبه أصل كل سيئة .
«እውቀትን መውደድና እውቀትን መፈለግ አላህን የመታዘዝ ምንጭ (መሰረት) ነው። ዱንያ እና ገንዘብ መውደድ እንዲሁም ዱንያ እና ገንዘብን መፈለግ የወንጀል ምንጩ (መሰረቱ) ነው።»

[مفتاح دار السعادة (٤١٩/١)]
[📚 መፋቲሁ ዳሩ ሰአዳ (419/1)]

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينے

                   
t.me/abdu_rheman_aman
አድርሱልኝ አደራ ሰጠኋችሁ....

ቲርቲራ፣
ሻፊ፣
ከላላ፣
ደገር......

ቦረና ሲባል ጀግንነት የሚሰማኝ እኔን ብቻ ነው?

👉ቲርቲራ፣ ሻፊና ፣ከላላ ፣ደገር.....

👉ቲርቲራ........!!
-------------------------------------------
የቲርትራው ኮከብ ጀግናው ከቦረና፡
የሻፊ ላይ ነብር የደገር ሳተና፡
መጣንልህ ዛሬ ተዘጋጅ ወንድሜ፡
እያስታወስኩህ ነው በሩቁ አስቀድሜ፡
አካልህ አካሌ ደምህ ነው ከደሜ፡
ሽርክና ቢዲዐው ጥመት ይቀርና፡
በተውሒድ በሱና ይዋባል ቦረና፡
ኢንሻ አሏህ.....‼️
አልሀምዱ ሊላሒ ደስ ሲል በረቢ፡
አማኝን በሙሉ በአንድነት ሰብሳቢ፡
ለየዋህ ህዝቦቹ አዛኝና አሳቢ፡
በቁርዐን በሀዲስ ኢስላምን መጋቢ፡
ከልቡ ላይ ለብሶ የተውሒድን ጋቢ፡
የጥመትን ጎራ በሀቅ ለማቅለጥ፡
ደጉን የወሎ ህዝብ ቶሎ ለማስመለጥ፡
ቁልቁለቱን ወርደን ተቃንተን ተራራ፡
ንፋስ እየመታው ብርድና ጠራራ፡
ጀግና ለመዘገር ተጓዝን ቲርቲራ፡
👉ሻፊ........!!
-------------------------------------------
ወሎ በሽርክ ነው የታወቀው ቢሉን፡
ቢሰድቡን ቢተቹን በጥመት ሊያስበሉን፡
ባይተዋርነትን ሁሉን ነገር ችለው፡
በቁርዐን እውነት በአሏህ ቃል ምለው፡
ከቢዲዐ ኮተት ወደ እውነት ኮብልለው፡
መስጂድ አቋቁመው ከሰወች ተ'ገ'ለው፡
ምንም ግፍ ቢበዛ ሐቅ አደናቃፊ፡
ጥሪያችን ነው ብለው ሁሉንም አቃፊ፡
ከጀግኖቹ መንደር ከሱና ደጋፊ፡
አንቀርም መጥተናል ፈቅደን ወደ ሻፊ፡
👉ከላላ.........!!
-------------------------------------------
ፍቅር እንደ ዳቦ ከሚገመጥበት፡
ጀግና የሱና ልጅ ከሚራወጥበት፡
ሀቅን ለመቀበል ፍርሀት ከሌለበት፡
የከላላን ሜዳ እስኪ ልሒድበት፡
የቦረናን ጀግና ለማየት ናፍቄ፡
ደስታ ተሰምቶኝ ፈቅጀና ስቄ፡
ከላላ ነኝ ብዬ ሳያሰጋኝ ስንቄ፡
ጀግኖቼን ልዘይር ከላላ ዘልቄ፡
እኔ ናፍቄያለሁ ያንተን ምን አውቄ፡
ያገሬ ሰው ንቃ አትሁን ተላላ፡
ደዕዋ ተደግሷል ቦረና ከላላ፡
👉ደገር........!!
-------------------------------------------
ከሸህ ሸረፈዲን የአምልኮ ስፍራ፡
ሀቅን ልንናገር ማንንም ሳንፈራ፡
ጀግናው የደገር ልጅ ተዘጋጅ ጠብቀኝ፡
ናፍቄህ ስመጣ አንተም እኔን ናፍቀኝ፡
መረዳት ከፈለክ ናፍቆቴን ከልቤ፡
አንብበህ ተረዳ በፃፍኩት ደብዳቤ፡
ተስፋ ሰንቀናል እውነት ለመናገር፡
የተውሒድ ሰው አለ በጅምላ አትናገር፡
ፅኑ ሰው አለበት የማይደናገር፡
የሱና ሰው አለው አትንኩት ያን ሀገር፡
ሽርኩ ብቻ ሳይሆን ተውሒዱ ሊነገር፡
ያውና ተሳፈርን ልንዘምት ወደ ደገር፡
-------------------------------------------
በኑረዲን አል አረቢ➊❹❹❹
------------------------------------------
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
-------------------------------------------
✔️ከላላ ቲርቲራ ሻፊ ደገር
እኳን ደስ አላቺሁ በጉጉት በተስፋ ለዚህ ቀን በቃቺሁ የተውሂድ አርበኞቺ የሱና ጠበቃ ይሄው መጡላቺሁ እናንተን ዚያራ ሊያስደስታቺሁ እኛ ደስ ብሎናል እኳን ደስ አላቺሁ!!

✔️ከላላ  እካን ደስ አላቺሁ !

➴ቀንና ሳአቱን ስጎድ ስትቆጥሩ
መቸይሆን ቀኑ በጉጉት ስትኖሩ
ይሄ ደረሰና አኑ መገዱን ሰበሩ
በአላህ ታግዘው መገድ ላይ ናቸው
መገዱን እያዩ ጉጉት ጨምሮባቸው
እናንተን ለማየት ጓጉቶ ልባቸው
የመገድ እርዝመት ምንም ሳይመስላቸው
ጎራና ጉራጉር ሳይበግራቸው
እናንተን ለማየት መገድ ላይ ናቸው


✔️ደገር:

➴ያንን የሽርክ ኮተት መትገው ሊጥሉ
ተዉሂድና ሱናን በቦታው ሊተክሉ
በአላህ ታግዘው ቃል ገብተዋል አሉ
ያን የደገር ዶሪህ ተስሩ ሊነቅሉ
ቢዳአን ኹራፋት ድራሹን ሊጥሉ
ከያቅጣጫው ኡለመና ኡስታዝ ዘምተዋል አሉ


✔️ቃላቸው ደስ ሲል!

➴ተውሂድን ሊያስተምሩ ቃል መጋባታቸው
በአላህ ታግዘው ጉዞ መግባታቸው
ወላሂ ደስ ሲሉ አረማመዳቸው
እርስ በርሳቸው መከባበራቸው
ምን ይሆን ሚስጥሩ እዲህ ያማረበት
ሁሉ ሰው አይቷቸው የሚቀኑበት
ሰውቺ ሳዩዋቸው በጣም የተገረሙበት !?
ምድነው ሚስጥሩ እድህ ያማሩበት ?!


➴ልገረህ ወዳጀ እደህ ያማሩበት ?
ያስተሳሰራቸው አድ ቃልነው የተውሂድ ዘለበት
እቅስቃሴያቸው በተውሂድ አድነት
ይሄነው ሚስጥሩ እድህ ያማሩበት
የቢዳአ ኮተት የለም እነሱጋር
ሱናነው ያለው እነሱጋር
አጠማመራቸው እጂጉን ያስቀናል
ሱናውን ሲሰብኩ የማ ይቀዘፋል
ጣፋጪ አደበታቸው እጂጉን ያጓጓል
በሱናላይ መጽናት እደዚህ ያስዉባል


✔️ከላላወቺ እንኳን ደስ አላቺሁ !

✍️ቢንት ሙሃመድ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/yeselefyadaewakelela
https://t.me/yeselefyadaewakelela
➧ኢብኑ ተይሚያ~ የሱንናዉ አንበሳ
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬


◉ክፍል  42

✍️አንበሳዉ  በወህኒ!➀
   ➠➠➠➠➠➠➠➠


✔️ለኢስላም እና ለሙስሊሞች ሲሉ ዱኒያ እርካታዎችን እርግፍ አድርገዉ የተዉት ሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ በሂወታቸዉ የደረሰባቸዉ ፈተና እና እንግልት የተመለከተ ልቡ በቁጭት ይቃጠላል። አይኖቹ እንባ ያረግፍሉ።

✔️ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ረሒመሁላህ እንደሚሉት፦"የደጋጎች ታሪክ አና በነሱ ላይ ስለደረሱ ፈተናዎች የሚያትቱ ለምሳሌ፦ የአቡል ዐረብን "አልማሒን"እና የሌሎችንም_ኪታቦች የተመለከተ ሰዉ እንደ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ በእስርም ሆነ ሌላ እንግልት የደረሰበት ዓሊም አያገኝም።(አልመዳኺል 31)

✔️ድብደባ፣የቁም እስር፣ወህኒ፣ወከባ፣ዛቻ እና ማስፈራሪያ ወዘተ አስተናግደዋል።ባጠቃላይ ሰባት ግዜ ለእስር ተዳርገዋል።አጠቃላይ በወህኒ ያሳለፉት ቆይታ አምስት አመት ነዉ።ይህ ሁሉ የሚሆነዉ ፈር በለቀቁ አንጃዎችና ግለሰቦች ላይ በሚሰጡት መልስ ሳቢያ ነዉ።

✔️አላማቸዉ  አንደበታቸዉ እንድለጎም፣ብእራቸዉ እንድነጥፍ ቢሆንም እስከ ደም ጠብታ ታግለዋል።አዎ ለቢድዕ አንጃዎች የሱንና ሰዎች መልስ ከሰይፍ በላይ ያማቸዋል።

✍️የእስር ቆይታዎቻቸዉ፣ምክንያቶቻቸዉ ተያያዥ መረጃዎች ባጭሩ ይመስላሉ፦

➾የመጀመሪያ እስራት፦ በ692 ሂ.ዐስሳፍ የተባለ ክርስቲያን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንደተሳደበ በርካታ ሰዉ መሠከረበት።ሰዉየዉ በአንድ አሚር ከለላ ስር ነበር።ኢብኑ ተይሚያህ እና አልፍሪቂ ተገናኝተዉ ለአሚር ዒዘዲን አይበክ አልሐመዊ ጉዳዩን አሳወቁ።

        የሱንናዉ ጥይት የተኮሰዉ
         ዘመን ተሻግሮ ዛሬም ጠበሰዉ።
        ቢድዐ ሲሮጥ ዙፍኑ ሊወጣ
         አሸማቀቀዉ እያቀናጣ!!!


➾ከዚህ አካሄዳቸዉ  ትልቅ ቁም ነገር ልንማር ይገባል። አፍራሺ ግብረ ሃይሎች ያለ የሌለ ዉንጀላ ሲለጥፉብህ አትብከንከን፣አትርበትበት፣ በባዶ አትንጨርጨር።ይልቁንም ዉንጀላቸዉን  የሚያደባይ ሾል ለህዝብ አቅርብ።አንድ ሲራመድ አንተ በእጥፍ አይደለም፣ይልቅ በብዙ እርምጃ ተጓዝ።


➾የጥፍት ሃይሎች በአጃቢም ፣በገንዘብም፣በጉልበትም፣በመድረክም፣የፈረጠዉ ስለሆኑ ተስፍ አትቁረጥ።ከሹማምንት ጉያ ተወትፈዉ ስላጠቁህ አትደንግጥ።

➾አታይም ኢብኑ ተይሚያን? ድምፃቸዉ ሊያፍኑ የሚሹ ጠላቶቻቸዉ ከርቸሌ በወረወሯቸዉ ቁጥር እጃቸዉን አጣጥፈዉ አይቀመጡም።ይልቁንም እነሱ አቧራ ያስነሱበትን ርእስ ፍንትዉ የሚያደርግ ኪታብ ዉስጥ ሆነዉ ይተኩሳሉ።

➾ከዒልማቸዉ ከተማሪዎቻቸዉ ብስለት የሚወሰድ ትልቅ ትምህርት አለ።እያንዳንዱ ከሳቸዉ ኋላ መጥቶ ስሙ የገነነ ዓሊም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ  የሳቸዉ ዉለታ አለበት።

➾ እስኪ ማነዉ ከኢብኑ ተይሚያ ፣ከኢብኑል ቀይም፣ከዘሀቢ፣ከሚዝዚ፣ከኢብኑ ዐብዲል ሃድ፣ከኢብኑል ወርድ፣ከኢብኑ ከሢር፣..........እዉቀት ያልተቋደሰዉ።

➾እነ ሱብኪ የነ  ዘሀቢ ተማሪ ናቸዉ።ኢብኑ ረጀብ የኢብኑ ተይሚያ ተማሪዎች ፍሬዎች ናቸዉ።እነ ሰኻዊ  የነ ኢብኑ ሐጀር ተማሪዎች ናቸዉ።ከሰንሰለቱ ጫፍ ላይ ያለዉ ማን እንደሆነ ይታይሀል? አስተዉል!ብቸኛ ናቸዉ እያልኩህ አይደለም። ብቻ የትግልህ ወሳኝ መሳሪያ ነዉና እራስህ ከዒልም አደራጁ።

✍️ኢንሻ አላህ  ይቀጥላል...............

አስተያየት ፣ሃሳብ ፣እርምት ፣ካለ ከታች ባለዉ ቦት ያቀበሉ ይደርሰናል!! @abuUseyminBot
↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/abuUseyminabdurehman
የስኬታችን ቁልፍ!!
በኑረዲን አል-አረብ
☑️አድስ ~ሙሐደራህ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️
〰️

👉ቁርአን እና ሀድስ እንከተል!

🎙በወንዲም ኑረዲን አል-አረቢ

በከላላ መስጂደ ተዉፊቅ የተደረገ!!

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
http://t.me/nuredinal_arebi
t.me/kelelaqiratcenter/792
👍2
👉አንድት የፈተና ሰአት ብዙ ያንተ ያልሆኑ ሰዎችን ታሳውቀሃለች!!✍
👍3