💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.65K subscribers
1.29K photos
494 videos
125 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☑️የጁሙዕ ረፍዱ ስጦታ ይሁንላችሁ!!

➧የሸይኻችን ሸይኽ አወል አሕመድ አልከሚሴ ቻናል ተቀላቀሉ!!

➺ሸር በማድረግ የኸይር ሰበብ ይሁኑ!!
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed
https://t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed
☑️ በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን ቻናል
የሚሰጡ ትምህርቶች!


የቁርዓን ቲላዋዎች!

➺የተጂዊድ ትምህርቶች!

➺የቃኢዳዎች ቂርዓቶች!

➺ተከታታይ የኪታብ ደርሶች!

➺የተለያዩ የሱና ኡስታዞች ወንድሞችመሓደራ ፁሁፎች!

☑️ወቅታዊ ሙሐደራና ፁሁፍ ምክሮች እናም ሌሎች ጠቃሚ እዉቀትን የሚያስጨብጥን የገኙበታል!

➧ይቀላቀሉሸር በማድረግ የኸይር ሰበብ ይሁኑ!

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/abuUseyminabdurehman
ሙሓደራ የነብዩ ሞት "ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም"
🎙 أبو ريس محمد بن إمام آل إمام
#አዲሥ_ሙሓደራ

         →ርዕስ

وفاة الرسول صلى الله عليه وسلم
የነብዩ "ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም" ሞት!

🕌 ደሴ አል-አዝሐር መስጂድ

📅{ليلة السبت 12 من شهر ربيع الأول/ 1444}

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም


t.me/abu_reyyis_arreyyis/6436
t.me/abu_reyyis_arreyyis/6436
ለምታስተውሉ ብቻ!
~
ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መስጂድ ውስጥ ግብይት እንኳ እንዳይፈፀም ከልክለዋል። በስክነት አላህን ለመገዛት የተገነባው የአላህ ቤት በዚህ መልኩ በቆሻሻ ሲሞላ አይሰቀጥጣችሁም? ይህንን ሁሉ ቅጠል በልተው ሰውነታቸው ከሞቀ በኋላ የሚከተለውን ጭፈራ ደግሞ አስቡት። ይህንን ነው ኢስላም ያስተማረን? በነገራችን ላይ ይሄ ተግባር የመካ ሙሽሪኮች ተግባር ነው። አላህ እንዲህ ብሏል:-
وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ
{በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አንፋል፡ 35]
ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር በአራቱም መዝሀብ የተወገዘ እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው። ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው። ፀለማዎች ይህንን ነውረኛ ተግባር እጅግ በጠነከሩ ቃላት ኮን ነውናል። ጥቂት ምሳሌ ልጥቀስ።
.
1. አቡል ወፋእ ኢብኑ ዐቂል (513 ሂ.)፡-
"በዜማና የመሳሪያ ድምፅ እየተከተለ የሚደንስና የሚጨፍር ባለ ፂም ማየት ምንኛ አስቀያሚ ነው? ባለ ሽበት ሲሆን ደግሞ የባሰ ነው! በተለይ ደግሞ በወጣቶችና በሴቶች ድምፅ ሲታጀብ። ከፊቱ ሞት፣ ጥያቄ፣ መቀስቀስና ሲራጥ ያለበት፣ ከዚያም ከሁለቱ አገሮች ወደ አንዱ የሚሆን ሰው እንደ እንስሳት ዝላይ ሊዘል፣ እንደ ሴቶች ማጨብጨብ ሊያጨበጭብ እንዴት ይዋጥለታል?!" [ተፍሲሩል ቁርጡቢ: 10/263]

2. ኢብኑል ጀውዚይ (597 ሂ.)፡-
የሱፍያ ክፍሎችን ተግባር አንስተው ባወገዙበት እንዲህ ብለዋል:– “በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ … ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው ከኢስላም እንደሚወጣ በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡” [ሶይዱል ኻጢር፡ 168]

3. አልቁርጡቢ (671 ሂ.)፡-
“ሱፍዮች የፈጠሩትን (ዜማ) በተመለከተ በክልክልነቱ ላይ ውዝግብ ከማይነሳበት ነገሮች ነው። ነገር ግን ብዙ በመልካም የሚታሰቡ ሰዎችን ስሜት አሸንፏቸዋል። ብዙዎቹ ላይ የእብዶችና የህፃናት ስራዎች እስከሚታዩባቸውና በተጠና መልኩ እስከሚደንሱ ደርሰዋል። ከዚያም ከፊል ሰዎች መቃረቢያና መልካም ስራ እስከማድረግ ደረሱ።…” [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 14/54]

4. ሲዩጢ (911 ሂ.)፡-

"ከነዚህም (ቢድዐዎች) ውስጥ የሆነው በመስጂድ ውስጥ የሚፈፀም ጭፈራ፣ ዘፈን፣ ድቤ መምታት፣ ማሲንቆና ሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች ናቸው። ይህንን ከመስጂድ ውስጥ የፈፀመ ሊባረርና ሊደበደብ የሚገባው ጠማማ ሙብ - ተዲዕ ነው፡፡ ምክንያቱም አላህ እንዲላ፞ቅ ያዘዘውን ነገር እያቃለለ ነውና፡፡ … (ከመስጂድ ውስጥ) የዘፈነ ወይም የጨፈረ ቅጣት የሚገባው የሆነ ጠሞ አጥማሚ ሙብተዲዕ ነው፡፡” [ሐቂቀቱ ሱና፞ ወልቢድዐ፡ 191]

5. አልኢማም አሶ፞ንዓኒ (1182 ሂ.):–

"ጭፈራና ጭብጨባ የአመፅና የብልግና ሰዎች ስራ ነው። አላህን የሚወድና የሚፈራ ሰው ተግባር አይደለም።" [ሱቡሉ ሰ፞ላም: 3/130–131]

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Audio
☑️ አዲስ የቂርአት ፕሮግራም!!


♦️የኪታቡ ርዕስ
➫➫➫➫➫➫

🌐«የነብዩ ልደት (መውሊድ) በተመለከተ።»

↪️ (ክፍል  ➃)


🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

የኪታቡ PDF ለማግኘት⤵️
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/8307
ውድ_እህቴ  !!!

ልብሽ መልካምን ነገር ለመስራት ጉዞ ከጀመረች ምን ጊዜም ከፊትሽ ብርሃን አይጠፋም ወደ መልካም ካመራሽ መልካም ነገር ይገጥምሻል!!

ወደ ወንጀል ከሄድሽ ግን ጨለማ ከፊትሽ አይለይም!!

ወንጀል ማለት ጨለማ ነው::
መልካም ነገር ደግሞ ከአላህ እሚመጣ ልዩ ብርሀን ነው!!

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
አላህን ማወቅ
➻➻➻➻➻➻

አላህ ስለመኖሩ ማስረጃዎች
➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯

🔃وَاللَّهُ أَخْرَجَكُم مِّن بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئًا وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۙ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

አላህም ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም አደረገላችሁ፡፡(አል ነህል 78)

አላህ እኛን የፈጠረን እሱን በብቸኚነት እንድናመልከው ነው። ከእናታችን ሆድ ስንወጣ ምንም የማናውቅ ሆነን ወጣንየተፈጠርንለትን አላማ እናሳካ ዘንድ፣ እሱን እናውቀው ዘንድ መስሚያን፣ መመልከቻን እና ልቦናን አደረገልን። አዛኙ ጌታችንን እናውቀው ዘንድ እነዚህንና ሌሎችን የማናያቸውን ውለታዎች ለገሰን

🔃أَلَمْ يَرَوْا إِلَى الطَّيْرِ مُسَخَّرَاتٍ فِي جَوِّ السَّمَاءِ مَا يُمْسِكُهُنَّ إِلَّا اللَّهُ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

ወደ በራሪዎች በሰማይ አየር ውስጥ (ለመብረር) የተገሩ ሲኾኑ (ከመውደቅ) አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው ኾነው አይመለከቱምን!? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አሉ፡፡ (አል ነህል 79)

➭ሳይንስ የመሬት ስበት (gravity) እያለ ቢያወራም ሁሉን ማድረግ የሚችለው ፈጣሪያችን አላህ አሞራዎችን በሰማይ አየር ላይ እንዳይወድቁ፣ እንዲሳፈፉ አድርጓቸዋል። ይህንንም ማድረግ የሚችለው ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ የሆነው ከሰባት ሰማያት በላይ ከአርሹ በላይ ያለው ሀያሉ አላህ ነው

🔃الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ مَهْدًا وَسَلَكَ لَكُمْ فِيهَا سُبُلًا وَأَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجْنَا بِهِ أَزْوَاجًا مِّن نَّبَاتٍ شَتَّىٰ🔄كُلُوا وَارْعَوْا أَنْعَامَكُمْ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّأُولِي النُّهَىٰ

➧(እርሱ አላህ ) ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ፣ በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መንገድን ያገራላችሁ፣ ውሃንም ከሰማይ ያወረደ ነው (አለ)፡፡ በርሱም ከተለያየ በቃይ ዓይነቶችን አወጣንላችሁ። ብሉ እንስሳዎቻችሁንም አግጡ፤ (ባዮች ኾነን አወጣንላችሁ)፡፡ በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ ተዓምራት አለበት፡፡ (ጦሃ 53__54)

ይህን ሁሉ ያገራልን ከእናት በላይ አዛኝ የሆነው አላህ ሲሆን ሀይልም ጥበብም በአላህ ብቻይብቃ

🔃 مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ

ከእርሷ (ከምድር) ፈጠርናችሁ፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ (ጦሃ 55)

ከምንም በፊት የነበረው ብቸኛው ፈጣሪያችን አላህ ነው። ከዚያም ፍጡራኑን ፈጠረ። በመጨረሻም ፍጡራኖች በተወሰነላቸው ጊዜ ሲሞቱ ሀያሉ ጌታችን ብቻ ይቀራል። አላህ የሰው ልጆችን ከአፈር ፈጠረ። ከዚያ የሰው ልጅ ሞቶም ወደ አፈር ይመለሳል። በመጨረሻም ከመቃብር ህያው ሆኖ ይቀሰቀሳል። ይህን ሁሉ በማድረግ ላይ ቻይ የሆነው አላህ ጥራት ይገባው

🔃يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ وَيُحْيِي الْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا ۚ وَكَذَٰلِكَ تُخْرَجُونَ

ሕያውን ከሙት ያወጣል፡፡ ሙታንም ከሕያው ያወጣል፡፡ ምድርንም ከሞተች በኋላ ህያው ያደርጋታል፡፡ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጣላችሁ፡፡ (አል ሩም 19)

ይህን ሁሉ ማድረግ የሚችለው ብቸኛው አላህ ነው


✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

አላህን ማወቅ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ!

♦️ክፍል አንድን ለማገኘት

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘

https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/10460

➶➶➶➶➶➶➶➶➶➶➶➶➶➶➶➶

ወደ አቡ ሂበቲላህ ቻናል ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
የመልካም ሚስት ስብዕና
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

የባሏን ውለታ የማትክድ
▰▱▰▱▰▱▰▱

➝የአላህ መልዕክተኛصَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم ሆይ"በጎ የዋሉልንን መካድ ምን ማለት ነው? አልኳቸው እርሳቸውም እንድህ አሉ፦

🔃"لعلَّ إحداكنَّ تطول أيْمَتها من أبويها ،ثم يرزقها اللّٰه زوجََا ويرزقها منه ولدًا فتغضبُ الغضبة ،فتكفر فتقول : ما رأيت منك خيرًا قط"
ከእናንተ መካከል አንዳችሁ ትዳር ይዘገይባትና ከዚያም ባልን ይሰጣታል ከእርሱም ልጅን ይቸራታል። አንደ ስትቆጣ ግን ውለታውን ሁሉ ትረሳና ከአንተ ላይ ፈፅሞ አንድም ቀን መልካምን ነገር አይቼ አላውቅም ትላለች

🔃"تطول أيمتها أبويها"
➘የሚለው ትዳር ይዘገይባታል ማለት ነው።

በሌላ ሀድስ ደግሞ ነሳኢይ "አስሱነን አልኩብራ" በተሰኘው ሀድስ ጥንቅራቸው ከአብዱላህ ኢብኑ ኡመር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛصَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم እንድህ ብለዋል

🔃"لا يَنظوُ اللَّهُ إلى امرأةٍ لا تَشكرُ لزوجِها وَهيَ لا تَستَغني عنهُ"

"ከእርሱ የማትብቃቃ(የምያስፈልጋትን ሁሉ የሚያደርግላት) ሆና ሳለ ባሏን የማታመሰግን ሴት አላህ ወደ እርሷ (በእውነት)አይመለከትም

ባሏን የምታከብርና ሐቁን የምትጠብቅ
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ከመልካም ሚስት ስብዕናዎች መካከል አንዱ ባሏን የምታከብር፣ መብቱን የምትጠብቅ ክብርና ልኩን የምታውቅ መሆኗ ነው።

👉በዚህ ርዕስ ላይ ብዙ ሀድሶች የመጡ ሲሆን ከእርሱም መካከል ጠበራኒ " አል ሙዕጀም አል ከቢር"በተሰኘው ድርሳናቸው ላይ ያሰፈሩት ይገኘበታል።

ከአብዲላህ ኢብኑ አባስ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛصَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم እንድህ ብለዋል ፦

🔃عن ابن عباس رَضِيَ اللّٰهُ عَنْهُما أنّ رسول اللّٰه صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال:" لا آمر أحدًا أن يسجد لأحدٍ ، ولو أمرتُ أحدًا أن يسجدَ لأحدٍ لأمرتُ المرأة أن تسجدَ لزوجها"
አንድም ሰው ለሌላ ሰው (ማንም ለማንም) እንዲሰግድ አላዝም ፤ አንድ ሰው ለሌላ ሰው እንድሰግድ ባዝ ኖሮ ሴት ልጅ ለባሏ እንድትሰግድ አዛት ነበር

እንደዚሁም ጠበራኒ በ "አልሙዕጀም አል ከቢር"ከየዚድ ኢብኑ አርቀም እንዳስተላለፉት።

🔃أنّ معاذًا قال يا رَسُول اللّٰه أرأيت أهل الكتاب يسجدون لأساقفتهم وبطارقتهم أفلا نسجد لك؟

ሙዓዝ እንድህ አለ፦ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አህለል ኪታቦች (አይሁድና ነሷራ) ለጳጳሶቻቸውና ለመሪዎቻቸው ሲሰግዱ አላዩምን እኛስ ለምን ለእርሶ አንሰግድም?

ነብዩ صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم እንድህ አሉ፦

🔃قال "لَوْ كُنْتُ آمِرًا أَحَدًا أنْ يَسْجُدَ لِغَيْرِ اللَّه لأَمَرْتُ الْمَرْأَةَ أَنْ تَسجُدَ لِزَوْجِهَا ،وَلاتُؤَدِّي الْمَرْأَةُ حَقَّ زَوْجِهَا حَتَّى لَوْ سَأَلَهَا نَفْسَهَا عَلَى قَتَبٍ لَمْتَمْنَعْهُ"

"አንድ ሰው ለሌላ ሰው እንድሰግድ ባዝ ኖሮ አንድት ሴት ለባሏ እንድትሰግድ አዝ ነበር፤ አንድ ሴት ባሏ ለፍቅር ጨዋታ ፈልጓት የግመል ጀርባ ላይ ሆና እንኳ ሲጠራት እሺ ብላው ብትመጣ የባሏን ሀቅ አታሟላም



✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

የመልካም ሚስት ስብዕና ከሚለው ከአብዱረዛቅ ቢን ዐብዱልሙሕሲን አልበድር ኪታብ የተወሰደች!

የፋሩቅ እናት

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

ከመጀመሪያው ክፍል ጀምሮ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
https://t.me/https_Asselefya1/4982
https://t.me/https_Asselefya1/4982

➧ው ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
የመልካም ሚስት ስብዕና
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

ባሏን የምታከብርና ሐቁን የምትጠብቅ
➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪

በተለይ ደግሞ ባልየው የመልካም ስብዕና ባለቤት፣ አላህን ፈሪ፣ በዲኑ ፅናት ያለው፣ አምልኮውን በአግባቡ የሚያከናውንና የአላህን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ከሆነ ሐቁ የዛኑ ያክል እጥፍ ድርብ ይሆናልኢማሙ ቲርሚዚይ እና ኢብኑ ማጃህ ከሙአዝ ቢን ጀበል እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم እንድህ ብለዋል

🔃قال رَسُوْل صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم :، "لَا تُؤْذِي امْرَأَةٌ زَوْجُهَا فِي الدُّنْيَا إلَّا قَالَتْ زَوْجَتُهُ مِنَ الْحُورِ العِينِ ; لَا تُؤْذِيهِ قَاتَلَكِ اللّٰهُ.، فَإِنَّمَا هُوَعِنْدَكِ دَخِيلٌ يُوشِكُ أَنْ يُفَارِقَكِ إِلَيْنَا"

➪"ዱኒያ ላይ አንድት ሴት ባሏን የምታስቸግር ከሆነ ፤በተቃራኒው ጀነት ያለችው ሚስቱ (አልሑሪል ዒይን) አታስቸግሪው! አላህ ይርገምሺና! እርሱ እኮ ልክ አንቺ ዘንድ እንዳለ እንግዳ ነው፤ አንቺን ተለይቶ ወደኛ መምጣቱ አይቀርም። "ትላለች።

የዕውቀት ባለቤቶች (ዑለማዎች) ይህን ሀድስ አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፦ ይህ ሀድስ ባሎቻቸውን ለሚያስቸግሩ ሴቶች ከባድ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው!

በልጆቿ መሀል ፍትሀዊ የሆነች
➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻

ከመልካም ሚስት መገለጫ ባህሪያት መካከል አላህ የልጅ ፀጋን ከለገሳትና ክብርንም ካጎናፀፋት በመካከላቸው ፍትሃዊ ትሆናለች።

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል

🔃قال عَلَيْهِ الْصَّلَاةُ وَالسَّلَامُ " اعْدِلُوا بَيْنَ أَوْلَادِكُمْ ،اعْدِلُوا بَيْنَ أَوْلَادِكُمْ

በልጆቻችሁ መካከል ፍትሀዊ ሁኑ! በልጆቻችሁ መካከል ፍትሀዊ ሁኑ
!
ይህ ሀድስ በሱነን አቢ ዳውድ የተዘገበ ሲሆን። በዚህ አይነት መልዕክት ያላቸው ብዛት ያላቸው ሐድሶች ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተወርተዋል።

ቤቷ ውስጥ የምትረጋጋ!
➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩

ከመልካም ሚስት መገለጫ ባህሪያት መካከል ቤቷ ውስጥ ረግታ የምትቀመጥና ወጣ ገባ ያማታበዛ መሆኗ ነው! ከቤት ከወጣችም ለጉዳይ ካልሆነ በቀር አትወጣም። እንድሁም ከቤቷ ተገላልጣና ተራቁታ አትወጣም! ዓይኗንም (በሸሪአ የተከለከለ ነገር ከመመልከት) ትጠብቃለች! ሰበር ታደርጋለች ብልቷንም (ከሀራም) ትጠብቃለች

ይህንን በተመለከተ የተወሰኑ የቁረአንና ሀድስ አስረጂዎች ከፊት አሳልፈናል ከእነዚህም መካከል ኢማሙ አጠበራኒ "አል አውሰጥ"በተሰኜ ኪታባቸው ሳሊም ቢን አብዲላህ ቢን ኡመር ከአባታቸው እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ፦

🔃المَرْأَةُ عورةٌ خرجتِ استشرفها الشَّيطان ، وإِنَّها لاتكونُ أقرْبَ إلى اللّٰهِ منها فِي قَعْرِبيتها.

ሴት ልጅ " ዐውራህ" ናት ከቤት ከወጣች ሸይጣን
ያሱባታል (የአላማው መምቻ) ያደርጋታል፤ ወደ አላህ የበለጠ ቅርብ የምትሆነው ቤቷ (ጓዳዋ)ውስጥ ስትሆን ነው



✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

የመልካም ሚስት ስብዕና ከሚለው ከአብዱረዛቅ ቢን ዐብዱልሙሕሲን አልበድር ኪታብ የተወሰደች!

የፋሩቅ እናት

📚አንብብ! ከማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል

ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
👍1