💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ከዚሁ ካገኘሁት ባይጠቅማችሁም አይጎዳችሁ"ለተጠቀመበት ትልቅ ትምህርት ነዉ።
አሏህ የፃፈልሽ ላያመልጥሽ መዝረክረክ
አታብዢ እህቴ በተለይ በዚህ ሚድያ"
:
:
⭕️ ጥንቁቅነቷ አስገረመው‼️
ከዛም ለሚስትነት እንደሚፈልጋት ነገራት

📱#እሷም_በበጎ_ጎኑ_በማየት_እንዲያወራት_በሩን #ከፈተችለት_ፈቀደችለት_ለረጂም_ጊዜ_አወሩ

🔻 ከቀን ቀን የጥንቁቅነቷ ገፆች መርገፍ ጀመሩ

ከዛም ተዋት! ✂️
⭕️ ምክንያቱም ጥንቁቅ ሴት እፈልጋለሁ #ስለሚልና እሷ ደግሞ ጥንቁቅነቷ ስለተወገደ ‼️

መልዕክቱ ላንቺ ነው ውዷ እህቴ
ንቂ! ........ አሁንም አረፈደም

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ማጠቃለያ ምክር
Muhammedsirage M.NUR
አጠር ያለች ምክር‼️
=============
||
#ኢንተርኔት
#ማህበራዊ ድረገጾች እና ሌሎች ነገሮችም ተዳሰውበታል

💦 በማጠቃለያ ምክር

🎙#Ustaz Muhammedsirage M. NUR አሏህ ይጠብቀው

ጆይን በማለት ቤተሰብ ይሁኑ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
የተስቢህ፣ ተህሚድ እና ተክቢር ትሩፋት



قال صلى الله عليه وسلم : « من قال : سبحان الله وبحمده في يوم مائة مرة حطت خطاياه ولو كانت مثل زبد البحر »

↪️የአላህ መልዕክተኛ (ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ

💦‹‹በቀን መቶ ጊዜ (ለአላህ ምስጋናና ጥራት ይገባው፡፡) ያለ ሐጢአት የባህር አረፋ ያክል እንኳ ቢሆን ይታበስለታል፡፡››


وقال صلى الله عليه وسلم : « من قال لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ عشر مرار . كان كمن أعتق أربعة أنفس من ولد إسماعيل »

↪️የአላህ መልዕክተኛ (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ

🔻ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ለረርሱ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው›› የሚለውም አሥር ጊዜ ያለ

🔹 ከኢስማኤል ልጆች አራት ያህሉን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፡፡ .

وقال صلى الله عليه وسلم : « كلمتان خفيفتان على اللسان , ثقيلتان في الميزان , حبيبتان إلى الرحمن : سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ سُبْحَانَ اللهِ الْعَظِيْمِ. »

">የአላህ መልዕክተኛ (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሁለት ንግግሮች አሉ፡፡ ምላስ ላይ ቀላሎች÷ ሚዛን ላይ ደግሞ ከባዶች ናቸው፡፡

↪️ከአላህ ዘንድም ተወዳጅነት አላቸው፡፡ (እነሱም)‹‹

سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ سُبْحَانَ اللهِ الْعَظِيْمِ

🔹‹ ለአላህ ጥራትና ምስጋና ይገባው፡፡ ለታላቁ አላህ ጥራት ይገባው››

وقال صلى الله عليه وسلم : « لأن أقول سُبْحَانَ اللهِ وَالْحَمْدُ لِلَّهِ وَلاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَاللهُ أَكْبَرُ , أحب إلي مما طلعت عليه الشمس »

የአላህ መልዕክተኛ (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡:

سُبْحَانَ اللهِ وَالْحَمْدُ لِلَّهِ وَلاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَاللهُ أَكْبَرُ

🔻‹አላህ ጥራት ይገባው፡፡ ምስጋናም ለአላህ ተገቢው ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አላህ ከሁሉም የላቀ ነው››

በማለት (አላህን ማወደስ) ፀሀይ ከምትወጣበት (ቦታና ሃብት) ሁሉ ይበልጥ ከኔ ዘንድ ተወዳጅ ነው፡፡.’
🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄🪄
وَقَالَ -صلى الله وسلم-: ((أَيَعْجِزُ أَحَدُكُمْ أَنْ يَكْسِبَ كُلَّ يَوْمٍ أَلْفَ حَسَنَةٍ)) فَسَأَلَهُ سَائِلٌ مِنْ جُلَسَائِهِ، كَيْفَ يَكْسِبُ أَحَدُنَا أَلْفَ حَسَنَةٍ؟ قَالَ: ((يُسَبِّحُ مِائَةَ تَسْبِيْحَةٍ، فَيُكْتَبُ لَهُ أَلْفُ حَسَنَةٍ أَوْ يُحَطُّ عَنْهُ أَلْفُ خَطِيْئَةٍ))

መልዕክተኛው (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) ፡- ‹‹ከናንተ አናዳችሁ በየቀኑ አንድ ሺህ የመልካም ሥራ ምንዳ (ሐሰና) ማግኘት ይሳነዋልን?›› በማለት ጠየቁ፡፡

💦ከታዳሚዎች አንዱ ፡- ‹‹እንዴት በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳዎችን ማግኘት ይቻላል?›› በማለት ጠየቀ፡፡

💦‹‹መቶ ተሰቢሕ›› ያድርግ፡፡ አንድ ሺህ ምንዳ ይጻፍለታል፡፡ ወይንም አንድ ሺህ ሐጢአቶች ይታበሱለታል፡፡›› አሉ፡፡ ’

من قال : سبحان الله العظيم وبحمده غرست له نخلة في الجنة

سُبْحَانَ اللهِ العَظِيْم وَبِحَمْدِهِ

"🔹ለታላቁ አላህ ጥራትና ምስጋና ይገባው÷ያለ ጀንነት ውስጥ አንድ የተምር ዛፍ ይተከልለታል፡፡

وقال صلى الله عليه وسلم : « يا عبد الله بن قيس ألا أدلك على كنز من كنوز الجنة ؟ " فقلت : بلى يا رسول الله ، قال : " قل لا حول ولا قوة إلا بالله »

💦መልዕክተኛው (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) ፡፡ ዓብደላህ ኢብን ቀይስ ሆይ ከጀነት ድልቦች አንዱል ልጠቁመህን?>> አሉ። የ አላህ መልክተኛ ሆይ አዎ የጠቁሙኝ አላቸው

لاَ حَوْلَ وَلَا قُوَةَ إِلَا بِاللهِ
🔹ብልሐትም ኃይልም በአላህ ቢሆን እንጅ የለም
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
وقال صلى الله عليه وسلم : « أحب الكلام إلى الله أربع ، لا يضرك بأيهن بدأت : سبحان الله , الحمد لله , ولا إله إلا الله , والله أكبر»

↪️ነቢዩ (ስለሏሁአለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ከአላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። በየትኛውም ብትጀምር ልዩነት የለውም፡፡ .’

سُبْحَانَ الله , وَالحَمْدُ لله , وَلَا إِلَهَ إِلَا الله , وَاللهُ أَكْبَر

إِنَّ أَفْضَلَ الدُّعَاءِ الْحَمْدُ لِلَّهِ، وَأَفْضَلَ الذِّكْرِ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ

ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ

الْحَمْدُ لِلهِ
አልሐምዱ ሊላህ

ከዚክሮች ሁሉ በላጩ ደግሞ:

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
سورۃ الفاتحۃ
<unknown>
በዳሩል ሀዲስ መድረሳ ለኮድ1 ተማሪዎች የሚሰጥ ተከታታይ ቅርአት ከተወሰነ የተጅዊድ ማብራሪያ ጋር

⤴️ #ክፍል_አንድ

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
የጧት ዚክር


سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ: عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ. (3× إذا أصبح)

‘ ‹‹ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ ምስጋናም፡፡ በፍጡራኑ ቁጥር ልክ፤ ነፍሱ በወደደችው ልክ፤ በዙፋኑ ክብደት ልክ፤ በቃላቱ ብዛት ልክ፡፡›› ሦስት ጊዜ

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلاً مُتَقَبَّلاً. (إذا أصبح)

‹‹ኣላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን, መልካም የሆነ ሲሳይን, ተቀባይነት ያለውን ተግባርን እጠይቅሃለው፡፡››-

أَسْتَغْفِرُ اللهَ وَأَتُوْبُ إِلَيْهِ. (100× في اليوم)

‘አላህን ምህረትን እምፀ ናለሁ፡፡ወደርሱ በፀፀት እመለሳለሁ፡፡››- በቀን መቶ ጊዜ

اَللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ. (10×)
አላህ ሆይ! በነብዩ ላይ ሰላምታ አውርድ፡፡ ሰላም አስፍንም፡፡›› አሥር ጊዜ .’


https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
መልካም እህት ጋር መቀማመጥ
ብዙ ያስተምራል ብዙም ያስደስታል
መልካሟ እህት ከህይወታችን መልካም
ዑደት መካከል አንዷ ነች!!


እንድት በረቱ እንድት ጠነክሩ ከሚመክሯቹህ
ስህተት ላይ ካላቹህ ከሚያርሟቹህ እህቶች
ከእውነተኞቹ ብዙ ከማውራት ብዙ ማወቅን
ከሚሹ ብዙ ቦታ መገኘትን ከሚሹ ብዙ
ዲናዊ እውቀት ላይ ትኩርት ከሚያደርጉ
እንስቶችጋር እንወዳጅ።

ማስመሰል የሌለበት ሀያት
በተውሂድ የተሳሰሩ እውነተኛ
ወዳጆች ጋር ነው‼️

30 ቃላቶችን በመደርደር መቆለማመጥ
አይጠቅምም በል በመመላለስ ሰአት
መፍጀት ቢሆንጂ ይልቁንስ እውነተኛ
ሁብ አንቺ ያለሽበትን የኢልም መቅሰሚያ
ቦታ ወይም መድረክ እሷም እንድትገኝ
በማድረግ ብሎም አንቺ ብቻ ለመብለጥ
ማሰብ ሳይሆን እኩል ትሆኑ ዘንድም
ወደ ኸይሩ መአድ መጎተት ስትችይ ነው‼️

ዝብሎ ውዴ.....ከዛ...ወከዛ..ማይንፈዕ!

ይህ የእውነተኞች ተግባር ነው አሏህ
ከእውነተኞች ያድርገን አሚን!
↷⇣🌹⇣↶
https://t.me/https_Asselfya
Audio
አስርቱ ውድ ቀናቶች


🇸🇦በነዚህ ቀናት የሚሰሩ ስራዎች
🇸🇦ቀናቶቹ ሚጀምሩት መች ነው
🇸🇦የነዚህ ቀናቶች ትሩፋት

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
🔻በሁለት ቅንድብ መካከል ያለን ፀጉር ማንሳት በተመለከተ
ስለ ሀገራችን ሐዳዲዮች
Sunnah Light
በድጋሚ የተለቀቀ‼️
-----------------------
1, እንደዚሁም ሀዳዲያ የሚባል አንጃ አለን?
2, የአገራችን ሀዳዲዮች ችግራቸው ምንድነው?
3, ጀምዒያ የሚባል ራሱን የቻለ አንጃ አለን?
ከዚህ ቀደም በአሸዋሜዳ ደርስ ለተጠየቀው ጥያቄ ላይ የተሰጠ ምላሽ

🎙በተወዳጁ #ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አሏህ ይጠብቀው

https://t.me/https_Asselfya
አንድ ወንጀል ሌላ ወንጀል ይበልጠዋል። አንዱ የከፋ ሲሆን ሌላው የቀለለ ይሆናል። ሆኖም ግን ማንኛውም ወንጀል የአላህን ቁጣ የሚያስከትል ከመሆኑ አንፃር መጠንቀቅና መራቅ አለብን። የወንጀሎች ሁሉ ቁንጮና ዋና ሽርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) ነው።

♻️ ሶላት መተው ግን፦
◾️ዝሙት ከመስራት
◾️የሰውን ነፍስ ከማጥፋት
◾️መጠጥ ከመጠጣት
◾️ከስርቆትና ማጭበርበር
🇸🇦የበለጠና የከፋ ወንጀል ይሆናል።


http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
01 ኢና ኩና ሺ ጃሂሊያ ሊሸይኽ ሷሊሕ አል—ፈውዛን
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ዛሬ ሰኞ የቀጥታ ስርጭት የኪታብ ደርስ

📚📚 ኪታብ = ኢና ኩና ፊ ጃሒሊያ

አዘጋጅ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን

⌚️⌚️ በሳምንት ③ ጊዜ ምሽት 3:00 ቡሓላ

🎤🎤 በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)

ትምህርቱን ለመከታተል በቀጥታ 👇
👇
https://t.me/UstazKedirAhmed
የዊትር ቁኑት ዱዓ

« يقوم يصلي إن أراد ذلك »

اَللَّهُمَّ اهْدِنِيْ فِيْمَنْ هَدَيْتَ، وَعَافِنِيْ فِيْمَنْ عَافَيْتَ، وَتَوَلَّنِيْ فِيْمَنْ تَوَلَّيْتَ، وَبَارِكْ لِيْ فِيْمَا أَعْطَيْتَ، وَقِنِيْ شَرَّ مَا قَضَيْتَ، فَإِنَّكَ تَقْضِيْ وَلاَ يُقْضَى عَلَيْكَ، إِنَّهُ لاَ يَذِلُّ مَنْ وَالَيْتَ، [وَلاَ يَعِزُّ مَنْ عَادَيْتَ]، تَبَارَكْتَ رَبَّنَا وَتَعَالَيْتَ.

↪️🔻አላህ ሆይ! ሌሎችን እንዳቀናኸው እኔንም አቅናኝ፡፡ ለሌሎች ጤና እንደሰጠኸው ለእኔም ስጠኝ፡፡ ለሌሎች ዋቢ እንደሆንክ ለኔም ዋኒ ሁነኝ፡፡ በሰጠኸኝ (ፀጋ) ረድኤትህን ጨምርልኝ፡፡ ከወሰንከው ክፉ ነገር ጠብቀኝ፡፡ አንተ ትወስናለህ፡፡ በአንተ ላይ አይወሰንብክም፡፡ አንተ የተወዳጀኸው አይዋረድም፡፡ አንተ ጠላት የሆንከው ክብር አይጎናፀፍም፡፡ የተቀደክና ልዑል ነህ፡፡

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَعُوْذُ بِرِضَاكَ مِنْ سَخَطِكَ، وَبِمُعَافَاتِكَ مِنْ عُقُوْبَتِكَ، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْكَ، لاَ أُحْصِيْ ثَنَاءً عَلَيْكَ أَنْتَ كَمَا أَثْنَيْتَ عَلَى نَفْسِكَ.

.↪️💦አላህ ሆይ! በእርካታህ ከቁጣህ÷ በይቅር ባይነትክ ከቅጣትክ እጠበቃለሁ፡፡ በአንተ ከአንተ እጠበቃለሁ፡፡ አንተ ራስክን ያወደስከውን ያክል ላወድስክ አይቻለኝም፡፡

اَللَّهُمَّ إيـَّاكَ نَعْبُدُ، وَلَكَ نُصَلِّيْ وَنَسْجُدُ، وَإِلَيْكَ نَسْعَى وَنَحْفِدُ، نَرْجُوْ رَحْمَتَكَ، وَنَخْشَى عَذَابَكَ، إِنَّ عَذَابَكَ بِالْكَافِرِيْنَ مُلْحَقٌ. اَللَّهُمَّ إِنَّا نَسْتَعِيْنُكَ وَنَسْتَغْفِرُكَ، وَنُثْنِيْ عَلَيْكَ الْخَيْرَ، وَلاَ نَكْفُرُكَ، وَنُؤْمِنُ بِكَ، وَنَخْضَعُ لَكَ، وَنَخْلَعُ مَنْ يَكْفُرُكَ

🎀↪️አላህ ሆይ! አንተን ብቻ እናመልካለን፡፡ ላንተ እንሰግዳለን፤ እናጎበድዳለን፡፡ ወደአንተ እንሮጣለን፤ እንገሰግሳለን፡፡ እዝነትህን እንቻለን፡፡ ቅጣትህን እንፈራለን፡፡ ቅጣትህ ከሀድያንን ያገኛል፡፡ አላህ ሆይ! እርዳታህን እንጥይቅሀለን፡፡ ምህረትህን እንማፀንሃለን፡፡ እናወድስሃለን፡፡ አንከድሀም፡፡ ባንተ እናምናለን፡፡ ላንተ እንንበረከካለን፡፡ አንተን የካደህን እንተዋለን፡፡
https://t.me/https_Asselfya
سورۃ الناس
<unknown>
#በዳሩል_ሐዲስ_መድረሳ ለኮድ 1 ተማሪዎች የሚሰጥ ተከታታይ ቅርአት ከተወሰነ የተጅዊድ ማብራሪያ ጋር ፨

>>>>>>>>>>>>>><<<<<<<<<<<<


⤴️ ክፍል #ሁለት


🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን
https://t.me/https_Asselfya
የወንጀል ቅጣት ሙእሚን ከሆነ ሰው ላይ እንዴት ልትወገድ ትችላለች?
———
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“ግልፅ የሆኑ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎች የወንጀል ቅጣት ከባሪያው በአስር ምክንያቶች እንደሚወገድ አመላክተዋል።
① መፀፀት (ተውበት) ማድረግ። ይህ በሙስሊሞች መካከል ሙሉ በሙሉ ስምምነት ያለበት ነው።
② ኢስትግፋር ማድረግ።
③ ወንጀል እንዲታበስ ምክንያት የሚሆኑ መልካም ስራዎችን መስራት።
④ የሙእሚን ዱዓ ለሙእሚን ቅጣትን ይመልሳል። ለምሳሌ በጀናዛው ላይ መስገዳቸውን ይመስል።
⑤ ለሟች ከሚሰሩ መልካም ነገሮች መስራት፣ ሶደቃና የመሳሰሉ ነገሮችን ማድረግ ሰበብ ይሆናል።
⑥ በእለተ ትንሳኤ ለወንጀለኞች የነቢዩ ﷺምና የሌሎችም ምልጃ (ሸፈዓ) ማግኘት።
⑦ አላህ ወንጀልን የሚያብስባቸው በዱኒያ ላይ የሚደርሱ የተለያዩ መከራዎች።
⑧ በቀብር ውስጥ የሚደርስበት ፈተና ጭንቀትና ፍርሃት።
⑨ የቂያማ ሁኔታዎች፣ ጭንቀትና መከራዎቿ።
10, የአላህ እዝነት፣ ከባሪያው ያለ ምንም ምክንያት ይቅር ባይነትና ምህረት።”
[ምንጭ:- መጅሙዕ አልፈታዋ]
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ


#join ⤵️
https://t.me/https_Asselfya
{{‍የጥዋት ዚክር}}


أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ الْمُلْكُ لِلَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرُ. رَبِّ أَسْأَلُكَ خَيْرَ مَا فِيْ هَذَا الْيَوْمِ وَخَيْرَ مَا بَعْدَهُ، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِيْ هَذَا الْيَوْمِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهُ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ وَسُوْءِ الْكِبَرِ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ فِي النَّارِ وَعَذَابٍ فِي الْقَبْرِ.

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
↪️ማለዳ ላይ ለመድረስ ነቅተናል፡፡ በዚህ ሰዓት ሉዓላልነት የዓላማት ጌታ የሆነው አላህ ነው፡፡ ምስጋና ከአላህ ነው፡፡

💦 ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋሪ የለውም፡፡ ሉዓላዊነት የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም የርሱ ብቻ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ የዚህን ቅና የቀጠዩን /የሌሊቱን/ መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡

↪️ ከዚህ ቀንና ከቀጣዩ /ከሌሊቱ/ ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ ከእሳት ቅጣት ከቀብር ውስጥ ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ።
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀 pinned «የጧት ዚክር سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ: عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ. (3× إذا أصبح) ‘ ‹‹ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ ምስጋናም፡፡ በፍጡራኑ ቁጥር ልክ፤ ነፍሱ በወደደችው ልክ፤ በዙፋኑ ክብደት ልክ፤ በቃላቱ ብዛት ልክ፡፡›› ሦስት ጊዜ اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ…»
رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِنْ لَدُنْكَ رَحْمَةً ۚ إِنَّكَ أَنْتَ الْوَهَّابُ

«ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፡፡ ከአንተ ዘንድ የኾነን ችሮታም ለኛ ስጠን፡፡ አንተ በጣም ለጋስ ነህና፡፡»🖋
አንዳንድ ሴቶች ሀያዕ ሲባል መንገድ ላይ ሲሄዱ አንገት መድፋት & ሰዎች ስለኔ ጥሩ አመለካከት እንድኖራቼው ዝቅ ማለት ብቻ ይመስላቼዋል።

★ሀያዕ ( አይፋርነት) ማለት አሏህ ማይፈልግበት ቦታ አለመገኜትና ከቆሻሻ ነገሮች ሁሉ መፅዳትንም ያካትታል።
🗞 ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት

💦ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦

عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رَضِيَ الله عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ". صحيح الجامع ، رقم 1133

ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ ቀናት ናቸው። ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናት» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚዕ 1133 ላይ አስፍረውታል

عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر. قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء" أخرجه البخاري

ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:‐
«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች በበለጠ ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል

በነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል:‐

1. ጾም፦ ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም)

2. ዚክሮችን ማብዛት፦ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል።

عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : "ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد" أخرجه احمد 7/224 وصحّح إسناده أحمد شاكر

ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፤
«ከነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል አህመድ ሻኪርም ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል።

ከተክቢር አደራረግ መካከል፤
الله أكبر ، الله أكبر لا إله إلا الله ، والله أكبر ولله الحمد
“አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ” የሚለው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ይዘቶች አሉት።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሊደረግ የሚገባው ይህ ተክቢር ብዙ ሰዎች ስለማይፈጽሙት እየተረሱ ካሉ ሱናዎች መካከል ነው። ሰዎችን ለማስታወስ እና ሱናን ህያው ለማድረግ ድምጽን ከፍ አድርጎ ተክቢር ማድረግ ያስፈልጋል። ዓብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቡሁረይራህ በነዚህ አስር ቀናት ገበያ ወጥተው ተክቢራ ሲያደርጉ ሰዎችም እያስታወሱ ተክቢራ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ይህም፤ ሁሉም ሰው የራሱን ዚክር ያደርጋል ማለት ነው እንጂ ሰዎች እየተሰባሰቡ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ያድርጉ ማለት አይደለም። ይህ መረጃ ያልተገኘለት የተሳሳተ አፈፃፀም ነው።

3. ሐጅና ዑምራ፦ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعته يقول: "الحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة" متفق عليه.
ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡»
ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል

4. ኡድሂያ፦ በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች አጠር ያለ ግንዘቤን ይሰጣሉ፤

- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ሱናዎች መካከል ነው። የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረጉ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ (ተቅዋ) ነው።

- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

- ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል
ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

- የአላህ መልዕክተኛ እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ፣ የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋርትም ይቻላል።

- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ለቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

- ኡድሂያውን ለራሱ፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።

- በዒድ ቀን ኡድሂያን ለማረድ አስቦ የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም። ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህ በሀጅ ላይ ያሉ ሰዎችን የሚመሳሰልበት ነብያዊ ትዕዛዝ ነው። ሆኖም ይህ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው። እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም።

የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸውና የቻልነዉን ሁሉ በመፈጸም ወደ አላህ መቃረብ ይገባል፤ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ሰደቃ ማብዛት፣ ሱና ሰላቶችን ማብዛት፣ ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማብዛት፣ ዱዓን ማብዛት…ወዘተ ያስፈልጋል።

አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ የአላህ ባሮች ያድርገን።

አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
ህዳር 23/ 2004 ዓ.ል

https://t.me/https_Asselfya