💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.65K subscribers
1.29K photos
494 videos
125 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ተነፋፍቀው ላሉ ለትዳር ጥንዶች የተገጠመ👇
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

➧ለትዳር ጥንዶች የሀላል ጨዋታ በግጥም።

➺ባል

አንቺ የኔ ፍቅር የህይወት ጨረቃ
ልቤ ይከፋዋል ሳጣሽ ለደቂቃ
ሴቶች ብዙ ናቸው አንቺ ግን ልዩነሽ
ህይወቴን አድሻት ካጠገቤ ሆነሽ!!

➲ሚስት
አንተ የኔ ፍቅር የህይወቴ ነፀብራቅ
ፍቅርህ ምግቤ ነው ከጎኔ አትራቅ ወንዶች ብዙናቸው አንተግንልዩነህ
ፍቅርህን መግበኝ ካጠገቤ ሆነህ
!!

➺ባል
የትዳሬ አጋር የልጆቼ እናት
ደስታዬ አለሜ የሀላል ሚስቴ ናት
ጌታዬ ይመስገን እሷን አድሎኛል
ውዴን የመሰለ ከቶ ኬት ይገኛል
!!

➲ሚስት
የልጆቼ አባት የትዳሬ አጋር
ተስፋዬ ብሩህ እስካለው ካንተጋር
መኖርህ መኖሬ
መጥፋትህ መጥፋቴ
ሳጣህ ቅር ይለኛል አትጥፋ ከፊቴ!!

➺ባል
የሽቶ መኣዛ የቴምር ጭማቂ
ሁቢ ማር ወለላ ሁሌም ተናፋቂ
ጣፋጭ ነገር ሁሉ
አንቺን ይመስሉኛል
ብቻምን ልበልሽ ቃላቶች ያጥሩኛል!!

➲ሚስት
የአይኔ ማረፊያ የህይወቴ ፀደይ
የፊትህ ብርሀን ይበልጣል ከፀሀይ
የረህማን ስጦታ የጀሊሉ ኒእማ
አንጀቴ ይርሳል ድምፅህን ስሰማ
!!

➺ባል
ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን
የፍቅር አደለም ሳስበው ነገሩን
ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር
አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር
!!

➲ሚስት
እኔ እንክት ልበል እኔ ልሰባበር
እሾህ አይንካብኝ እንኳንስ መሰበር
የፍቅር አርበኛ ፊት አውራሪ ጀግና
አንተ መውደድ እንጂዱላ መች ታውቅና!!


➺ባል
እኔ እዚህ ጎራ አንቺ እዛ ማዶ
ልቤ አረረልሽ በፍቅርሽ ማገዶ
የልቤ በረዶ መዳኒቴ ነሽ
ውዷ ባለቤቴ ሁቢ እንዴት ነሽ?

➲ሚስት
ፈረስ አይጋልበው በበቅሎ አይደረስ
በርሬ እንዳልመጣያለህበት ድረስ
ውዱ ባለቤቴ ፍቅርህ ለበለበኝ
አሁንስ ከብዶኛል በዱኣህ አስበኝ።


✍️ተነካክቶ የተወሰዴ !!

©በተለያዬ ቦታ ተራርቃችሁ ያላችሁ ጥንዶች
አላህ በሰላም ያገናኛችሁ!

➜ላጤዎችም አላህ ይዘዉጃችሁ!!

{ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ!}

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
↪️ አዲስ ሙሀደራ


♦️የሙሀደራው ርዕስ
➫➫➫➫➫➫➫➫

🌐«የኢኽላስ አሳሳቢነትና አንገብጋቢነት በሰፊው ተዳሶበታል።»

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
ኹዝ ዓቂደተክ خذ عقيدتك (ትግርኛ).apk
66.5 MB
📲አድስ አፕልኬሺን ተለቀቀ!!

➧ኪታብ ኹዝ አቂደተክ ሚነል ኪታቢ ወሱነቲ አስ_ሰሒሓ { በትግርኛ }ቋንቋ!!

🎤በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

©ቴሌግራም አድራሻ!
↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/abuUseyminTigrgna
🔹ጥበብ የአላህ ጸጋ ነዉ
〰️〰️ 〰️〰️ 〰️〰️
يُؤْتِى ٱلْحِكْمَةَ مَن يَشَآءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ ٱلْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِىَ خَيْرًۭا كَثِيرًۭا ۗ
ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል።ጥበብንም የተሠጠዉ ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠ፡፡
✍️ ያረብ ሀገር ሴቶች

የሱና ፈር ቀዳጅ የተውሂድ አርበኞች
የማይበገሩ ጠንካራ አምበሶች
ውበት ድምቀት ናቸው እሩቅ አሳቢዎች
አላህ ያግዛቸው ያረብ ሀገር ሴቶች


እቃ እያጠቡ ተውሂድ የሚማሩ
ምግብ እየሰሩ ኢልምን የሚቀስሙ
ሰለቸኝ ደከመኝ መች ብለው ያውቃሉ
እረፍታቸው ሁሉ ለዲን ይሰጣሉ
በኸይር መንገድ ላይ መቼ ይታጣሉ
እርዳቸው ረበና ሀያል ነህ ጀሊሉ

♻️ ክብር ላረብ_ሀገር_ሴቶች

🖋 ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/abuUseyminabdurehman
👍6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
【إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا】
 [الأحزاب:56] .
ኹጥባ የመጠቁ ስነምግባሮች
abu reyyis mohamed ibnu imama
خُطْبَةُ الْجُمُعَةِ
የጁሙዓ ኹጥባ

الأخلاق العالية
የመጠቁ ስነምግባሮች

🕌 ደሴ አል-አዝሐር መስጂድ

📅محرم/21/ 1444

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
↓↓↓
t.me/abu_reyyis_arreyyis/6250
t.me/abu_reyyis_arreyyis/6250
⤵️ጀግና ይሁን ልብህ


➧ከስህተትህ ታረም ከወንጀልህ ፍራ፡
ከጥመት ተጠበቅ መልካም ነገር ስራ፡
ቀጥ በል ተስተካክለህ ተግባርህ ይቀደም፡
ሽርክና ቢዲዐ ፊት ለፊትህ ይውደም፡

;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;://;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
➧ፍፁም አይምረርህ ጭቆናና ግፉ፡
ከሀቅ አታሸግሽግ ፀፀትህ ነው ትርፉ፡
በመረጃ በርታ በርጋታ ተቀመጥ፡
በደል ቢፈጂህም እንደ ሣት ረመጥ፡
ይሻልሀልና ኋላ ከመርመጥመጥ፡

========\\\==========
➧ሀቅ ላይ ስትሆን አይቀርም ፈተና፡
ገለባና ምርቱን ሊለይ ነውና፡
በቂርዐት በርታ በእውቀት ተዘጋጂ፡
ለጠላትም ቢሆን ሁን እውነትን ፈራጂ፡

≈≈≈≈≈≈≈≈≈\\≈≈≈≈≈≈≈≈
➧ባንድራውን ይዘህ ወደፊት ተራመድ፡
ገደል አታስተውል ፈፅሞ አትሽመድመድ፡
በዕምነትህ ኩራ በል ወደፊት ገስግስ፡
የሽርክ የቢዲዐ የጥመት ግሣንግስ፡
ተጠንቀቅ አደራ ለሰው አታግበስብስ፡
በንፁህ ልብህ ላይ ንፁህ ተውሒድ አንግስ፡


➧ሰለፍያ ይ
ን ውብ ትምህርት ቤትህ፡
ቁርዐት ሀዲስ ይሁን ምንጊዜም ትርክትህ፡
የነብያት ታሪክ ፤

➧የሰሀቦች
ድል ይህ ይሁን ቀለብህ፡
ፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ጀግና ይሁን ልብህ፡

➴➴➴➴➴➴➴
➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/IbnuTeymyaYesunawAmbesa
https://t.me/IbnuTeymyaYesunawAmbesa
👍3
Audio
👍1
Audio
▪️ تلاوة من سورة النحل
▪️ القارئ: #ياسر_الدوسري
•••━══❁✿❁══━•••
▪️إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُوا۟ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسْتَقَٰمُوا۟ تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا۟ وَلَا تَحْزَنُوا۟ وَأَبْشِرُوا۟ بِٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ
☑️እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡

📚ሱረቱል ፉሲለት 30}
➡️እስቲግፋር እና ተውባህ
     ➯➯➯➯➯➯➯➯➯

➡️የአላህ መልእክተኛ  ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም እንዲህ ብለዋል። እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ በፀፀት ተመለሱ፡፡ እኔ በየቀኑ ከመቶ ጊዜ ያላነሰ ተውበት አደርጋለሁ፡፡

📚{ሙስሊም ዘግቦታል።}

➡️የአላህ መልእክተኛ  ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም እንዲህ ብለዋል። ‹‹አላህ ለባሪያው ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ከመጨረሻው የሌሊቱ ክፍል ላይ ነው፡፡ በዚያ ወቅት አላህን ከሚያወሱት ለመሆን ከቻልክ ሁን።
📚{ሙስሊም ዘግቦታል ።}

➡️የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም  እንዲህ ብለዋል። በቀን መቶ ጊዜ አላህን ምህረት የመለመን ፍላጎት ልቦናዬ ውስጥ ያድራል፡፡
📚{ሙስሊም ዘግቦታል።}

➡️የአላህ መልዕክተኛ  ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም እንዲህ ብለዋል።
አንድ ባሪያ አላህ ዘንድ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ነው፡፡ ሱጁድ ላይ ዱዓ አብዙ፡፡

📚{ሙስሊምዘግቦታል።}

➡️የአላህ መልእክተኛ ሰላሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል።
አላህ ጥራት ይገባው እንዲሁም ምሰጋና ለርሱ ነው። ሱብሃነ አላሂ ወቢሀምዲሂ (سبحان الله وبحمده) የሚለውን ዚክር በቀን መቶ ግዜ ያለ ሰው ወንጀሉ እንደ ባህር አረፋ የበዛ እንኳ ቢሆን ይራገፍለታል።

📚{ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበውታል።}

በሶስት ነገራቶች ላይ የኢማንን ጥፍጥናን ካገኛችሁ ፈልጉት።አልበለዚያ በሩ ዝግ ነው።
➘በሶላት ፣በዚክር፣ በቁረአን።

📚ሃሰኑል በስሪ رحمه الله።}

♦️አላህ  ሆይ!  አንተን በማውሳት፣ በማመሰገን እና በሚገባ አንተን በማምለክ ላይ እርዳን።