💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.6K subscribers
1.29K photos
494 videos
125 files
5.17K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
✅💢የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው❗️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹📌የመጀመሪያው እውቀትና ተግባር ሰዎች የተፈጠሩለት አላማ ነው።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

📌ሁለት ፍጡራንየተፈጠሩበት አላማ ሲሆን የእውቀት አስፈላጊነት ለተግባር ነው።

🔺 አላህ ፍጡራንን ሊያውቁት እና ሊገዙት ፈጠረ።

🔹ለመጀመሪያው መረጃ የሚከተለው የቁረአን አንቀጽ ነው ።
ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ وَمِنَ ٱلْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ ٱلْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌۭ وَأَنَّ ٱللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَىْءٍ عِلْمًۢا
አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መኾኑን በዕውቀት ያካበበ መኾኑን ታወቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ።

🔺እውቀት ፍጡራን የተፈጠሩበት አላማ ነው ለሚለው ደግሞ መረጃው የሚከተለው የቁረአን አንቀጽ ነው

وَمَا خَلَقْتُ ٱلْجِنَّ وَٱلْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

📌እውቀትና አምልኮ ሁሉም ሰዎች የተፈጠሩበት አላማ ነው። ወደ አላህ የሚያቃርብ በሆነ ጠቃሚ እውቀት ካልሆነ በቀርአምልኮት አምልኮ ሊሆን አይችልም። አውቆ የሰራ የተፈጠረበትን አላማ በትክክል አሳክቷል። በዚህ ምክንያት የእውቀት ባለቤቶች የሚከተለውን ይናገራሉ።

🔹ለእርሱ ሲባል የተፈጠርንበት እርሱን ለማረጋገጥ የተገኘንበት ተውሂድ ሁለት ጎኖች አሉት።

👉የእውቀት ጎንና የተግባር ጎን ናቸው።

📌በእውቀት የምናጸድቀው የተውሂድ ክፍል እና በተግባር ተፈጻሚና ተፈላጊ የሆነው የተውሂድ ክፍል ናቸው። አምልኮ በተገቢው ሁኔታ ሊረጋገጥ ባሪያው ትክክለኛ ለአላህ ታዛዥ ይሆን ዘንድ የግድ ሁለቱ መኖር አለባቸው።

✅ያለ ተግባር የእውቀት ባለቤት ቢሆን በአላህ ቁጣ ይመለሳል።ምክንያቱም የእውቀትን አላማ በትክክል አላረጋገጠም።ያለ እውቀት የተግባር ባለቤት ከሆነ ደግሞ ቀጥተኛ ከሆነው የአላህ መንገድ ይሻፈፋል።

🔹ለዚህ ነው ታላላቅ ዱዓዎችን በውስጧ የሚገኝባትን ፋቲሃ ዘወትር በየሶላታችን እንድንቀራት በሸሪዓ የተደነገገው።
ٱهْدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلْمُسْتَقِيمَ صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ ٱلْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ
📌ቀጥተኛውን መንገድ ምራን ።የእነዚያን በነሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ {ምራን በሉ።

🔹በእነርሱ ላይ ጸጋውን የዋለላቸው ሰዎች የእውቀትና የተግባር ባለቤቶች ናቸው።

🔹የተሳሳቱ የተባሉት ደግሞ ያለ እውቀት የሚሰሩ ሰዎች ናቸው።

📌ሱፍያን ብን ዑየይናህ :- ረሂመሁሏህ የሚከተለውን ተናግረዋል ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔹ከዑለማዎቻችን የተበላሹት ከአይሁድ ጋር መመሳሰል አለባቸው። ከዓቢዶቻችን (ያለጥልቅ እውቀት አላህን የሚገዙት )የተበላሹት ደግሞ ክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል አለባቸው።

📌ምክንያቱም አይሁዶች እውቀት አላቸው ግን አይሰሩበትም።

🔹አላህ በተከበረው ቁረአናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል።
مَثَلُ ٱلَّذِينَ حُمِّلُوا۟ ٱلتَّوْرَىٰةَ ثُمَّ لَمْ يَحْمِلُوهَا كَمَثَلِ ٱلْحِمَارِ يَحْمِلُ أَسْفَارًۢا ۚ
የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት (ያልሠሩባት) ሰዎች ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ቢጤነው።

💢ሁለተኛ አንድ ባሪያ በእውቀት ምን እንደስራበት ይጠየቃል

🖊ኢንሻአላህ ቀጥላል🖊
አንብብብብ❗️ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል።

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
〰〰〰🔻🔻🔻〰〰〰〰
🔻[ የአደም ልጅ ሲሞት ከሶስት ነገር በስተቀር ስራው ይቋረጣል:-
〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹ቀጣይነት ያላት ሶደቃ(ምጽዋት)፣
🔹የሚጠቀሙበት እውቀት፣
🔹ዱዓ እሚያደርግለት ጡሩ ልጅ::]

📚ሙስሊም ዘግበውታል።
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ◾️ተከታታይ ፅሁፍ 〰〰〰〰〰〰 ➧ክፍል አንድ ✅ከንግግር ሁሉ በላጭ የአላህ ንግግር ነው። ምርጥ የሚባለው መመሪያ የሙሐመድ صلى الله عليه وسلم መመርያ ነው። ከነገሮች ሁሉ የከፋው በዲን ላይ ፈጠራ ነው። ፈጠራ የተባለ ሁሉ ቢድዐ ነው። ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ነው። ➠ይህች አጠር ያለች መፅሐፍ በአላህ ፍቃድ አብዛኛው ሰው ዘንድ…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሁለት
〰〰〰〰〰

➭በአላህ ፈቃድ ይህችን አጭር ማስታወሻ በውስጣቸው አርእስቶች የያዙ ሁለትዋና ክፍሎች አድርጌ አዘጋጅቻታለሁ። በክፍል አንድ መግቢያ እና መንደርደሪያ፣የተፈጠርንለትን አላማ (ተውሒድን)፣ እዚህ ምድር ላይ የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት እንደጀመሩ፣ በፍጡራን እና በፈጣሪ አላህ መሃል ያለው ታላቅ ልዩነት፣አምልኮ ለማን እንደሚገባው እና ከማንስ ላይ መግፈፍ መንፈግ እንዳለብን፣ ነብያት በምን መልእክት እንደተላኩ፣ ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ለምን አይነት ሰዎች እንደተላኩ፣የሺርክን አስከፊነት በአጭሩ የተቃኘበት ክፍል ነው።

➢ክፍል አንድ ላይ የተዘረዘሩት አንኳር ነጥቦች ክፍል ሁለት ላይ ያሉት የሺርክ፣
የክህደት ስንኞች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ለሙስሊሙ ኡማ ማስገንዘቢያ የሚሰጡ መንደርደሪያ ናቸው። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ሀቅን በሃቅነቱ እንዲያሳየን የምንቀበለውም እንዲያደርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ እንዲያሳየን የምንርቀውም እንዲያደርገን ጌታችንን አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እለምነዋለሁ።


➧የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት ጀመሩ?
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

➲ወንጀልን ወንጀል ይበልጠዋል። ለምሳሌ ዝሙት ከታላላቅ ወንጀሎች ውስጥ ነው። አንድ ሰው ከሌላ ሴት ጋር ዝሙት መስራቱ እና ከእናቱ ጋር ዝሙት መስራቱ በጣም ልዩነት አለው። እናቱን መገናኘቱ ይከፋል። ልክ እንደዚሁ የሰው ልጅም ይሁን አጋንንት የተፈጠሩበት ዋና አላማ አላህን በብቸኝነት ለመገዛት ነው።

➻
ይህንን የተፈጠሩለትን ታላቅ አላማ ተቃርነው በእርሱ በአላህ ላይ ቢያጋሩ ታላቁን በደል ሰርተዋል። የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم ከወንጀሎች ሁሉ ታላቁ እና የከፋው የትኛውእንደሆነ ሲጠየቁ “እሱ አላህ ፈጥሮህ ሲያበቃ በእርሱ አላህ ላይ ብጤን ሸሪካን ልታደርግለት ነው” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 4477፣ ሙስሊም፡ 86]

➠አላህ ዘንድ ታላቁ ወንጀል ምን እንደሆነ በሰፊው ሊዳሰስ ይገባል። አላህ በእያንዳንዱ ህዝብ መሃል መልክትኞቹን መጽሀፍ አስይዞ የሚልክበት ዋና መልእክት በምን እንደሚደፈርስ ሊታወቅ ይገባዋል።

በምን ምክንያት የሰው ልጆች የተፈጠሩለትን አላማ ተቃርነው፣ የአባታችንን አደም ንጹህ የተውሒድ መንገድ ተቃርነው፣ በብቸኛው
ፈጣሪያችን እና አምላካችን አላህ ላይ ፍጡራንን አማልክት አድርገው ያዙ?

📚➤መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ሀሳቡ ይቀጥላል
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
✅💢የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው❗️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🔹📌የመጀመሪያው እውቀትና ተግባር ሰዎች የተፈጠሩለት አላማ ነው። 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 📌ሁለት ፍጡራንየተፈጠሩበት አላማ ሲሆን የእውቀት አስፈላጊነት ለተግባር ነው። 🔺 አላህ ፍጡራንን ሊያውቁት እና ሊገዙት ፈጠረ። 🔹ለመጀመሪያው መረጃ የሚከተለው የቁረአን አንቀጽ ነው ። ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ وَمِنَ…
💢የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው❗️
〰〰〰〰〰➰➰➰〰〰〰
✅ሁለተኛው አንድ ባሪያ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት ይጠየቃል

🔹📌ረሱል ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባገኙት እውቀት ምን እንደሰሩበት ይጠየቃሉ ብለዋል።

🔺አቡ በርዘት ረድየሏሁ አንሁ ከረሱል ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ሰምቶ የሚከተለውን ሀድስ አስተላልፏል

🔹📌የትንሳኤ ቀን ከአራት ነገሮች ሳይጠየቅ የባሪያው እግር ካለበት ቦታ አይነቃነቅም።ከእነርሱ መካከል የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም አወሱ- ከእውቀት ምን እንደሰራበት {ቲርሚዚ፣2417 አድ ዳሪሚይ: 554ሀድሱን አልባኒ ሳሂህ ብለውታል ሶሂህ አት ቲርሚዚይ :2417}

🔺አቡደርዳዕ ረድያሏሁአንሁ የሚከተለውን ተናግሯል
➖➖➖➖➖➖➖
🔹📌እኔ የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጥረታቱ መካከል ጠርቶ አንተ አወይሚር ሆይ ! በአወከው ምን ሰራህበት ? ብሎእንዳይጠይቀኝ ነው የምፈራው ። {ኢስቲሐፉል ኸይረቲ አል ሚህረቲ :8/16}

👉ይህ አስደንጋጭ አደገኛ የሆነ ቦታ ነው ማንኛውም ባሪያ ከታነጸው እውቀት በአወቅከው ነገር ምን ሰራህበት ?"ተብሎ የትንሳኤ ቀን መጠየቁ አይቀርም
🔺ምክንያቱም የማወቃችን ትልቁ አላማ ተግባር ነው። ለዚህ ነው ማንኛውም ሰው ከተማረው ትምርት የሚጠይቀው ።

🔹📌በርካታ ሰለፎች የሚከተለውን ይናገሩ ነበር:-
〰➰〰➰➰〰
🔹📌ለእኔም ሳይኖረኝ በእኔም ላይ ሳይኖር በእውቀቴ (ሳልጠየቅ) ነጻ ብሆን እመኛለሁ።"

↪️በዚህም ሰልፎች የተስተካከለ እውቀትና ተግባር እያላቸው ምን ያክል አላህን እንደሚጠነቀቁና እንደሚፈሩ ያመለክታል።

🔺ሀሰን አል በስሪ ረሂመሁሏህ ደግሞ የሚከተለውን ተናግሯል
➖➖➖➖

🔹ሙእሚን መልካምንና ፍርሀትን አጣምሮ ይዟል።
🔹ሙናፊቅ ደግሞ ክፉ ስራንና መልካም ተስፋን አጣምሮ ይዟል። {አዙህድ ሊብኒ አል ሙባረክ : 985}

↔️ዓብደሏ ብን አቢ ሙለይካ -ረሂመሁሏህ ደግሞ የሚከተለውን ተናግረዋል
〰➰〰〰➰
🔺ሁሉም ኒፋቅን በነፍሳቸው ላይ የሚፈሩ ከሰላሳ የሚበልጡ ሶሀቦችን አግኝቻለሁ።( ቡሀሪ በሶሂህ ታባቸው ኪታቡ አል ኢማን ባቡ ኸውፉል ሙእሚን ላይ በተዕሊቅ አውርቶታል)

◾️ለአማኞች በአንድ ላይ ሀለት ታላላቅ ደረጃዎችን አጣምሮላቸዋል።
◾️በመልካም መታዘዝና ያማረ ተግባርን እየሰሩ ስራችን ከእኛ አይቀበበልም ብለው አላህን እንድፈሩ አድርጓቸዋል።

🖊አላህም በተከበረው ቀረአናዊ አንቀፅ የሚከተለውን ተናግሯል

وَٱلَّذِينَ يُؤْتُونَ مَآ ءَاتَوا۟ وَّقُلُوبُهُمْ وَجِلَةٌ أَنَّهُمْ إِلَىٰ رَبِّهِمْ رَٰجِعُونَ
እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡{አልሙእሚን :60}

[[እነዚያ አስካሪ መጠጥ የሚጠጡ ፣ዝሙት የሚፈጽሙ ፣የሚሰርቁ ናቸው ።?በማለት ስለዚህ ቁረአናዊ አንቀጽ ትርጓሜ ለረሱል ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ጥያቄ አቀርቡላቸው። ትላላች እናታችን አኢሻ ረሱል ስለሏሁአለይሂ ወሰለም አይደለም የ{ አቡበከር }ልጅ ሆይ !ነገር ግን እየጾሙ እየስገዱ ፣እየሶደቁ ከእነርሱ ይህን መልካም ስራችንን አላህ ላይቀበለው ይችላል ብለው ስጋት ያደርባቸው ናቸው። እነዚህ ሰዎች በመልካም የሚሽቀዳደሙ ናቸው ። በማለት ምላሽ ሰጡ።{{አህመድ ፣25 263 ቲርሚዚይ 3175ኢብኑ ማጃህ 4198}}

🖊አላህም በተከበረው ቁረአናዊ አንቀጽ
وَإِسْمَٰعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّآ ۖ إ
(ኢብራሂምና) ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡
ወሀይብ ብን አልወርድ ረሂመሁሏህ ይህን ቀረአን አንቀጽ አነበበና አለቀሰ።ከዚያም የሚከተለውን ተናገረ

"" 🔹📌የአላህ ወዳጅ{ኢብራሁም}ሆይ!የአላህን ቤት መሰረቶች ከፍ ታደርጋለህ {ተፍሲር ኢብኑ ከሲር 1/206}

✅ሶስተኛው በእውቀት ለማይሰራ ሰው የተላለፈ ዛቻና ማስጠንቀቂያ

🖊ኢንሻአላህ ይቀጥላል🖊

↪️መጻፍ ካልቻልክ አንባቢ ሁን❗️

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Forwarded from Ibrahim hayerdin
የቁርኣን ሀለቃው በአዲስ መልክ ከሱረቱ ተህሪም የሚጀምር ይሆናል።
#ሶስተኛ ጁዝ
ኑ!!ቁርኣንን በአጭር ጊዜና ቀለል ባለ መልኩ
አብረን እናኽትም!!
@ibrahim_furii
@ibrahim_furii
👍ሼር ሼር
♻️የ32ቱ ጥርሶች ስያሜ በአረብኛ

🟢አስ‘ሰናያ ………… (4)
🔴አር_ረባኢያት………(4)
🔵አል_አንያብ……… ( 4)
▶️አድ‘ደዋሒክ………(4 )
🟡አጥ‘ጠዋሂን…… (12)
🟠አን‘ነዋጅዝ……… (4
)

🌐https://t.me/ibrahim_furii
🌐https://t.me/ibrahim_furii
سورة الكهف - فارس عباد
فاعس ؚباد
#سورة_الكهف_بصوت
#فاعس_ؚباد

@sura_alkahf


▪️የአሏህ መልእክተኛ ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም ቀጣዩን ብለዋል፦
☞︎︎︎በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።»
حسنه الألباني في
تخريج مشكاة المصابيح - رقم:(2116)

▶️ለይለቱል ጁምዓ ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ (በካዕባ) መካከል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
صححه الألباني في
صحيح الترغيب -رقم: (736)
🔻እውቀትን መፈለግ ያለው ቱርፋት⤵️⤵️⤵️

✅💢የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል

👉እዉቀትን በመፈለግ ላይ የተጓዘ ሰዉ አላህ ለሱ የጀነትን መንገድ ያገራለታል ።

⤵️የአላህ መልክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል፣

አላህ መልካም የሻለት የሆነ ሰው ድኑን ያስገነዝበዋል።

↪️የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል:-
🔹አንድ ሰው ሲሞት ስራው ሁሉ ይቋረጣል። ሶስት ነገራቶች ሲቀሩ፣
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
▪️ ሰደቀቱል ጃርያ የማይቋረጥ ሰደቃን የሰጠ የውሀን ጉድጓድ መቆፈር ይመስል፣ የአላህን ሱብሀናሁተአላ መስጅድ መገንባት ይመስል

▪️ ሳሊህ ልጅ የወለደ ሰው ከዚያም ልጁን በሸርዓዊ እውቀት ኮትኩቱ{በተርቢያ} ያሳደገ
▪️ ሸርዓዊ እውቀት ኖሮት ለሌሎች አስተምሮ ያለፈ ሰው ሲቀር ሁሉም ስራው ይቋረጣል።

https://t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሁለት 〰〰〰〰〰 ➭በአላህ ፈቃድ ይህችን አጭር ማስታወሻ በውስጣቸው አርእስቶች የያዙ ሁለትዋና ክፍሎች አድርጌ አዘጋጅቻታለሁ። በክፍል አንድ መግቢያ እና መንደርደሪያ፣የተፈጠርንለትን አላማ (ተውሒድን)፣ እዚህ ምድር ላይ የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት እንደጀመሩ፣ በፍጡራን እና በፈጣሪ አላህ መሃል ያለው ታላቅ ልዩነት፣አምልኮ ለማን እንደሚገባው…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሶስት
〰〰➰➰➰

➲ከሰው ልጆች ሁሉ አባት ነብዩላህ አደም (አለይሂ ሰላም)እስከ መጀመሪያው መልእክተኛ ኑሕ(አለይሂ ሰላም)ድረስ አስር ክፍለ ዘመን ነበር።በዚህ ወቅት የሰው ልጆች ሁሉ በአንድ ሃይማኖት በእስልምና ውስጥ ነበሩ። ችግሩ የተፈጠረው አንድነቱ የፈረሰው ኑሕ(አለይሂ ሰላም) የተላኩባቸው ሰዎች በደጋጎች ላይ ድንበር አልፈው የባእድ አምልኮት ላይ ሲወድቁ ግዜ ነው።

🔁በዚህም የተነሳ አዛኙ አላህ እነዚያ ህዝቦች የተፈጠሩለትን አላማ ያውቁ ዘንድ የመጀመሪያውን መልእክተኛ ኑሕ (አለይሂ ሰላም)ወደ ተውሂድ እንዲጠሯቸው ላካቸው። ኑሕም(አለይሂ ሰላም) ዘጠኝ መቶ ሀምሳ አመት የተውሂድ ጥሪ እንዲቀበሉ ይህን የተቀበለም ብስራት እንዳለው ፣ከአላህ ውጭ ሌላ አካል እሚፈጽሙትን አምልኮ እንዲርቁ ይህን ካላደረጉ ከባድ አደጋ እንደሚያጋጥማቸው በማስጠንቀቅ ተጣሩ።

➠ልብ እንበል የሰይጣ ወጥመዱ ከባድ ነው። በአንድ ሀይማኖት ላይ የነበሩትን ህዝቦች በታተናቸው። አብዛሀኛዎቹ የመጀመሪያውን መልእክተኛ ኑሕ ጥሪ አንቀበልም ብለው ለጥፋት ተዳረጉ።

➧አላሁ(ሱብሀነሁተዓላ )የነዚህን አጋሪያን (መጥፎ ፉጡሮች) መጨረሻ ከባድ የሆነ ቅጣት ቀጥቷቸው ከባድ አደጋንም ተከናነቡ። ጥፋታቸው ከባድ ስለነበረ በአላህ ትእዛዝ ሰማይ የያዘችውን ውሃ ለቀቀች ።ምድር የያዘችውን ውሃ ተፋች፣ተራራ የሚያካክሉ ፣ማእበሎች ተነስተው እነዚህ ሁሉ አመጸኞች ውርደትን ቀመሱ። በሁለት አገርም ተዋረዱ።

📘ዝግጅት መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ።

°
°
°
✍ኢንሻአሏህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

✏️መጻፍ ካልቻልክ አንብብብ‼️ማንበብ የተሻለ ሰው ያድርጋል።

⤵️ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ቀጣይ ክፍሎችን ይከታተሉ።

ጆይን በማለት ተጠቃሚይ ሁኑ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
◾️እውቀት የጀነት መንገድ ነው
◾️እውቀት መፈለግ ነፍስ በምትጠላው ነገር የተከበበች ነች
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
لقد فنوا و ما بقي منهم أحد
هشام عزب
◾️ገሳጭና እጅግ መካሪ ግጥም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ በኦድዮ መልኩ (በአናሳ mb)

☑️ ይህች ናት ዱንያ ግን ማን ይገሰፅ?

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
ማን ነው ሰለፊ??? እንነማን ናችው ሰለፊዮች??? በታላቁ ሸይክ ሱለይማን አሩሃይሊ

አዲስ ነው አድምጡት‼
@abutoiba
Audio
◾️አስደናቂው የመልእክተኛው ፅናት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

☑️ በነብያችን ላይ የደረሱ ሙሲባዎች
🔘በእሁ ዘመቻ ላይ የተከሰተው
🔘የእናት አባታቸው ማጣት
🔘የአብዱል ሙጠሊብን ማጣት
🔘የአቡ ጣሊብና የኸድኛ ሞት
🔘የልጆቻቸው ተከታታይ ሞት
🔘በጧኢፍ ሰዎች የደረሰባቸው ግፍ
🔘የመካ ሚሽሪኮች ተንኮልና ሴራ
➡️ ይህ ሁሉ ሙሲባ በምን ተሻገሩት⁉️
▪️የሙእሚን ትልቁ ሙሲባ…
▪️የመልእክተኛው መሞት…

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
[ከእንቅልፍ ሲነቁ የሚደረግ ዱአ ]
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

((اَلْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِيْ عَافَانِيْ فِيْ جَسَدِيْ، وَرَدَّ عَلَيَّ رُوْحِيْ، وَأَذِنَ لِيْ بِذِكْرِهِ))

አልሐምዱ ሊልላሂልለዚ ዓፋኒ ፊ ጀሰዲ፣ ወረድደ አለይየ ሩሒ ፣ ወአዚነ ሊ ቢዚክሪህ

ለአካሌ ጤንነት ለለገሰኝ፣ ነፍሴንም ለመለሰልኝ እንዳወሳውም ለፈቀድልኝ አሏህ ምስጋናው ይግባው !!
➱አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልእክተኛ
እንዲህ አሉ፡-
〰〰〰〰〰〰〰

"▪️አምስት ወቅት ሶላቶችን መስገድ፣ ጁሙዓ ተሰግዶ ቀጣዩ ሳምንት ጁሙዓህ
እስኪመጣ፣ ረመዷን ተጹሞ ቀጣዩ ረመዷን እስኪመጣ ድረስ ሰውየው ትላልቅ ኃጢአትን እስከተጠነቀቀ ድረስ
በመሀከላቸው ያለውን ትናንሽ ኃጢአት
ያስሰርዛሉ" (ሙስሊም)፡፡
🖊 እህቴ ሆይ..
የአንቺ ውበት
በኒካህ ለተሳሰርሽው ባልሽ
ብቻ እንጂ ለተለያዩ የሶሻል
ሚድያ ተኩላዎች አይደለም
#እኛ ማለት "ሪዝቃችንን" እየበላን "አጀላችንን" የምንጠብቅ ሚስኪን ህዝቦች ነን

_(ኢማሙ አህመድ)_
ረሱል ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም ድን መመካከር ነው አሉ፤
ለማን አልናቸው? እሳቸውም አሉ፦
🔹 ለአሏህ
🔹ለኪታቡ
🔹ለመልዕክተኛው
🔹ለሙስሊም መሪዎች
🔹ለአጠቃላይ ለህዝቡ

https://t.me/https_Asselfya
ለመውደድ ብዙ ምክንያት
ለመጥላት ግን አንዲት ተራ ስህተት
በቂ በሆነበት በዚ ገራሚ ዘመን
የሚወድክን ሰው አጥብቆ መያዘን ልመድ‼️