💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.6K subscribers
1.29K photos
494 videos
125 files
5.17K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
Audio
🎧 የ ሩቃ ቁርዓን በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)።

🎼 ማራኪ የሆነ ድምፅ ከ ኢብኑ አባስ መርከዝ

🎙 الخضر بن أحمد الخميسي الولوي الحبشي
https://t.me/https_Asselfya
💎ታላቁ ሰሀብይ አቡ ደርዳእ አላህ መልካም ስራው ይውደድለትና እንዲህ ብሏል።

የዲን እውቀት ፈልጉ። ካልቻላችሁ የእውቀት ባለቤቶችን ውደዱ። እነሱን መውደድ ካልቻላችሁ ሌላው ቢቀር አትጥሉዋቸው።

📚(صفة الصفوة 240/1)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምላስ አደገኘነት

በሚል ረዕስ የተሰጠ ምክር ነው እናድምጠው

@abutoiba
ኢትዮቢያ ሀገሬ አይዞሽ አትከፊ

ዛሬ ቢከብድሽም ባያስፈካ ፊት
አድስ ሂወት አለ ገና ወደፊት
ነበር ሊባልለት ብዙ አትጨነቂ
አሳዝዝኙ ግዜ እንደሚያልፍ እወቂ
ሁልግዜም አይኖርም ታሪክ ይቀየራል
ኢንሻአላህ ነገ መልካም ቀን ይመጣል
ደስተኛ ሁኝና ሁሉን አሸንፊ
ይሳካል ያሰብሽው አብሽሪ አትከፊ


የአላህ ቤተሰቦቻችንን ድምጽ አሰማን
https://t.me/https_Asselfya
የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ እንዲህ አለ

▪️የሆነ ቀን ከአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀምጠን እያለ፡

▪️በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው፥ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ፥ የመንገደኛ ምልክት የማይታይበት፥ ከኛ ውስጥም ማንም የማያውቀው ሰውዬ ብቅ አለና እነብዩ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀመጠ።

💦 ጉልበቱን ከጉልበታቸው ጋር አገጣጠመ፥ መዳፉንም ታፋው ላይ አስቀመጠ። ከዛም አንተ ሙሓመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ አላቸው።

🔻 የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “

▪️ኢስላም ማለት ፦ በእውነት የሚመለክ ጌታ አንድ አላህ ብቻ ነው ብሎ እና ሙሓመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣

▪️ሶላትን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስገድ፣ ዘካን ማውጣት፣ ረመዳንን መጾም፣ የአላህ ቤትን ከቻልን መጎብኘት።”

💦 ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ዑመርም እንዲህ አለ “በሱ ተገረምን! እሳቸውን ይጠይቃል መልሶ እውነት ተናገርክ ይላቸዋል!

💦” ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢማን ንገረኝ አላቸው።

የአላህ መልእክተኛ[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ

▪️ “ኢማን ማለት ፦ በአላህ ማመን፣ በመላኢኮች ማመን፣ በመጻህፍት ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፣ በአላህ ውሳኔ ከፋም በጀም ማመን” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ።

▪️ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢሕሳን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ

▪️ “ኢሕሳን ማለት አላህን እንደምታየው አድርገህ ልታመልከው ነው፥ አንተ ባታየውም እሱ ያየሃል እና።” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ሰአቷን ንገረኝ አላቸው።

▪️የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ የሚያውቅ አይደለም” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ምልክቶቿን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ባርያ ጌታዋን ልትወልድ ነው፣ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ፥ እርቃናቸውን የነበሩ፥ ድሆች የነበሩ የፍየል ጠባቂዎች ህንጻ ለመስራት ሲሽቀዳደሙ ልታይ ነው።” ከዛ ቡሃላ ሰውየው ሄደና ብዙ ቆየን። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “አንተ ዑመር ሆይ!

🔻ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?” ዑመርም “አላህና መልእክተኛው ያወቁ ናቸው።” በማለት መለሰ።

🔻የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ የመጣው እኮ ጂብሪል ነው፥ ሃይማኖታቹህን ሊያስተምራቹህ መጣቹህ።”

📚ሙስሊም ዘግቦታል

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
የዑለማኦች አቋም በተውሂድ ዙሪያ
Abu Useymin
🔷 አዲስ ሙሐደራ 👇👇👇👇👇

➡️የዑለማኦች አቋም በተውሂድ ዙሪያ ‼️

ትክክለኞቹ ዓሊሞች እነማናቸው ⁉️

↗️እና ሌሎችም ወሳኝ ነጥቦች ተዳሰዋል

🎧ይደመጥ ባረከሏሁ 👆👆👆

🎙By Abdurehman Abu Useymin

https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
ዛሬ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ!
لا يحل نشر أسرار العلاقة الزوجية
<unknown>
لا يحل نشر أسرار العلاقة الزوجية ..

الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله
https://t.me/https_Asselfya
◾️ተቀርተው ያለቁ ደርሶች ስብስብ


🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
➡️ ተቀርተው የተጠናቀቁ ደርሶች


↪️ የቁርአን በተጅዊድ ቂርአት
🔻{ከሱረቱል ፋቲሀ―ሱረቱል ሐሽር}
t.me/Ibnuheyru123/419
t.me/Ibnuheyru123/419

↪️ የኡሱሉ ሰላሳ ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/1688
t.me/Ibnuheyru123/1688

↪️ የኪታቡ ተውሂድ ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/1746
t.me/Ibnuheyru123/1746

↪️ የቃኢደቱ ኑራንያ ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/1851
t.me/Ibnuheyru123/1851

↪️ የቱህፈቱል አጥፋል ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/1905
t.me/Ibnuheyru123/1905

↪️ የሹሩጡ ሶላት ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/1937
t.me/Ibnuheyru123/1937

↪️ የሑዝ አቂደቱከ ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/1962
t.me/Ibnuheyru123/1962

↪️ የዱሩሱል ሙሂማ ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/1997
t.me/Ibnuheyru123/1997

↪️ የተንቢሀት ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/2143
t.me/Ibnuheyru123/2143

↪️ የነዋቂዱል ኢስላም ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/2230
t.me/Ibnuheyru123/2230

↪️ የሸርህ አልዋጂባት ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/2246
t.me/Ibnuheyru123/2246

↪️ የአዝካር ወል ኣዳብ ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/2371
t.me/Ibnuheyru123/2371

↪️ የቀዋኢዱል አርበአ ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/2541
t.me/Ibnuheyru123/2541

↪️ የፈኑ ተጅዊድ ሙሉ ቂርአት
t.me/Ibnuheyru123/2553
t.me/Ibnuheyru123/2553

ሼር በማድረግ የኸይር ሰበብ ይሁኑ
ዓብደላህ ኢብን መስዑድ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ። “

እያንዳንዳቹህ በእናቱ ሆድ ውስጥ ፍጥረቱ ይሰበሰባል። አርባ ቀን ንፍጥ የሚመስል ፈሳሽ ይሆናል። ከዛም የረጋ ደምን ይመስላል ለተመሳሳይ ግዜ (40 ቀን)። ከዛም የታኘከን ስጋ ይመስላል ለተመሳሳይ ግዜ (40 ቀን)።

▪️ ከዛም መልእክተኛ ይላክና ሩሕ ይተነፍስበታል። መልእክተኛውም በአራት ነገሮች ላይ ይታዘዛል። ሲሳዩን፣ ፍጻሜውን፣ ስራውን፣ የተከፋ ወይንም ደስተኛ መሆኑን እንዲጽፍ ይታዘዛል።

🔻 ከሱውጭ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ በሌለው ጌታ እምላሎህ ! አንዳቹህ በሱና በጀነት የስንዝር ያክል ርቀት እስከምትቀረው ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራና ከዚያም መጨረሻ ላይ መጽሃፉ ይቀድመውና የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል።

🔻ደግሞ አንዳቹህ በሱና በእሳት የስንዝር ያክል ርቀት እስከምትቀረው ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና ከዚያም መጨረሻ ላይ መጽሃፉ ይቀድመውና የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።

📚 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።


https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ወቅታዊ ፈተናወችና በፈመከራዎቹ ስለመታገስ
🎙 በአቡ ዒምራን ሙሐመድ
ወቅታዊ ፈተናወችና በፈመከራዎቹ ስለመታገስ [ከሙሐደራ 23 የተቀነጨበ (ሙሉውን በቅርቡ) ይጠብቁ]

የሰው ልጆች በተለያዩ ፈተናዎች ለአብነትም በድርቅ፣ በጦርነት፣ በወረርሽኝ እና በመሳሰሉት መፈተናቸው አይቀሬ ነው። ከኛ በፊት ያሉት ህዝቦች እንደተፈተኑት ሁሉ እኛም እንፈተናለን ልክ እንደኛ ወደፊት የሚመጡትም ትውልዶች ይፈተናሉ። ፈተናውም በተለያዩ ገፅታዎች ሊቀርብ ይችላል። ሀያሉ ጌታችን በተከበረው ቁርአኑ በሚከተለው መልኩ እንዲህ ብሏል
وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ

ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በጀነት) አብስር፡፡
[አል-በቀራህ 155]

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማንበብ ይጫኑ
➷➴➴➷➴➷➴➷➴
https://t.me/AbuImranAselefy/4118
https://t.me/https_Asselfya
ስለ ሱጁደ ቲላዋ አጭር ገለፃ !!
_____________________

ቁርአን ላይ የሚገኙት የሱጁደ ቲላዋ ምልክቶች ብዛት አጠቃላይ ሁሉም (15) ናቸው ።

ቁርአን እየቀራን ሳለን እነዚህን የሱጁድ ምልክቶች ስናገኛቸው ጊዜ ሱጁ እንወርዳለን ።

ሱጁደ ቲላዋ ሁክሙ (ሱና) ነው።

ሱጁደ ቲላዋ ተሸሁድ የለውም ። ማሰላመትም አያስፈልገውም ።

👉 አካሄዱ ባጭሩ በዚህ መሰረት ነው፦ ቁርአን እየቀራህ ሳለህ የሱጁድ ምልክት ካጋጠመህ አሏሁ አክበር ብለህ ልክ ሶላት ስትሰግድ እንደምትወርደውሱጁድ - ሱጁድ ትወርዳለህ - ከዛ ይሄን ዱዓ ትላለህ

ﺳﺒﺤﺎﻥ ﺭﺑﻲ ﺍﻷﻋﻠﻰ " ، " ﺳﺒﺤﺎﻧﻚ ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺭﺑﻨﺎ ﻭﺑﺤﻤﺪﻙ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻲ " ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻟﻚ ﺳﺠﺪﺕ، ﻭﺑﻚ ﺁﻣﻨﺖ، ﻭﻟﻚ ﺃﺳﻠﻤﺖ، ﺳﺠﺪ ﻭﺟﻬﻲ ﻟﻠﻪ ﺍﻟﺬﻱ ﺧﻠﻘﻪ، ﻭﺻﻮﺭﻩ، ﻭﺷﻖ ﺳﻤﻌﻪ ﻭﺑﺼﺮﻩ، ﺑﺤﻮﻟﻪ ﻭﻗﻮﺗﻪ " ، " ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻛﺘﺐ ﻟﻲ ﺑﻬﺎ ﺃﺟﺮﺍً، ﻭﺿﻊ ﻋﻨﻲ ﺑﻬﺎ ﻭﺯﺭﺍً، ﻭﺍﺟﻌﻠﻬﺎ ﻟﻲ ﻋﻨﺪﻙ ﺫﺧﺮﺍً ﻭﺗﻘﺒﻠﻬﺎ ﻣﻨﻲ ﻛﻤﺎ ﺗﻘﺒﻠﺘﻬﺎ ﻣﻦ ﻋﺒﺪﻙ ﺩﺍﻭﺩ " ،

ከፈለግክ ከዚህም ሌላ መጨመር ትችላለህ

ከዚያ ከሱጁድ መነሳት ብቻ። ማሰላመት ምናምን አያስፈልገውም ።

ሱጁድ ላይ የሚባለውን ዱዓ በተመለከተ ይሄን ሁሉ ይረዝምብኛል አልሀፍዘውም ካልክ ይሄን ብቻ ማለት ትችላለህ 👇👇

" سبحان ربي الأعلى "
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk