💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.59K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.17K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
በውሃ ቀጠነ የሚፈርሰው የዘመኑ ትዳር
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር "ሃፊዘሁላህ"
➡️ ያለ ወልይ ኒካህ ማሰር
➡️ በውሃ ቀጠነ የሚፈርስ ትዳር
➡️ መቼ ነው ቃዲ ኒካህ የሚያስረው

🌐ሴቶች በትኩረት አዳምጡት

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
በጣም አሳሳቢ... ማሳሰቢያ በሱጁደ ቲላዋህ
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር "ሃፊዘሁላህ"
➡️ ስጁዱ ቲላዋ በተመለከተ ወሳኝ ነጥቦች

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
✅ዓብደላህ ኢብን ዓባስ በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ

▪️ “አላህ ለኔ ከህዝቦቼ መሳሳትን፣ መርሳትን እና ተገድደው የሰሩትን ይቅር ብሏል።”

ሓዲሱን ኢብን ማጃህ፣ አል-በይሃቅይ እና ሌሎችም ዘግበውታል።
አህባሾች ከ73ቱ ፊርቃዎች ናቸውን.?
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር "ሃፊዘሁላህ"
♦️አህባሾች ከ73ቱ ፊርቃዎች ናቸውን?

♦️ከኢስላምስ ይወጣሉን?

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ

https://t.me/https_Asselfya
Audio
✅ ቁርአንን አስተካክሎ ማንበብ ትልቅ የአላህ ኒእማ ነው። ጥረት ከተደረገ እንደ ቁርአን ቀላል ነገር የለም።
🎙️ تلاوة من سورة ق
للقارئ: #أيوب_أمزيل
•••━══❁✿❁══━•••
https://t.me/https_Asselfya
የነብዩ صلى الله عليه وسلم የልጅ ልጅ እና ለሳቸው ቅርብ የነበረው ሓሰን ኢብን ዓልዪ ኢብን አቢ ጣሊብ ከ አላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمየሚከተሉትን ሓፈዝኩ(ሸመደድኩ) አለ።

“የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደማያጠራጥርህ ሂድ።”

📚 ቲርሚዝዪና ነሳኢ ዘግበውታል
↪️ውዷ እህቴ
〰〰〰〰〰
☞የዱንያን ጭንቀት አትሸከሚ ዱንያ የአላህ ነች
☞ስለ ርዝቅሽም አትጨናነቂ ርዝቅም ከአላህ ነው
☞ወደፊት የሚያጋጥምሽን ችግር አታስቢ በአላህ እጅነው ያለው ሁሉም
ነገር

🔻ስለ አንድ ሀሳብ ብቻ ተጨነቂ አላህን እንዴት ማስደሰት እንደምትችይ አላህን ካስደሰትሽ ተደስቶብሽ ያስደስትሻል መብቃቂያሽ ሆኖልሽ የደስታን ሀብት ይሰጥሻል ።ከሃብት ሁሉ ትልቅ ሃብት የልብ ሃብት ነው።

↪️አቂደን መገንዘብ ነው።ሀላሉን ከሀራም ለይቶ ማወቀና ጠቃሚና ጎጂን መለየትነው።አብሽሪ ሁሉም ነገር ጊዜው ስደርስ በአሏሀ ምርጫ ይመጣልናል።ሪዝቃችን ማንም አይነጥቀንም።ዬትም አያመልጠንም አሏህ የፃፈልን ነገር እሺ
☞ልብሽ በደማበት የህይወት ችግር ተስፋ አትቁረጪ
☞ወደ አላህ ተጣሪ ወደ ኸይር ቀይርልኝ ብለሽ
☞ሀዘን በስግደት ይጠፋል
☞ደስታ በዱአ ይመጣል
ብቻ ምን ልበልሽ

▪️ለነገሮች በጣም ቦታ ሰጠሽ አትጨናነቂ ሰበቡን አድርሺ ከዚያም በጌታሽ አሏህ ተመኪ "በእርሱ የተመካ ሁሌም ኡፍፍፍፍፍፍፍ እንዳለ ነው‼️

https://t.me/https_Asselfya
👍1
Forwarded from =>የሰለፍያ ጎዳና ትክክለኛዋ ጎዳና ናት። (بنت سعيد النساء السلفيه ربي احفظ لي أمي من البدع وضلال)
🌹እማ🌹

የመኖሬ ሚስጥር የህይወቴ አለኝታ፡
የስኬቴ ሰበብ የራህማን ስጦታ፡
ስከፋ ምታዝናኚኝ ሆነሽኝ ጓደኛ፡
ሁሌ ምትፈልጊኝ እንድሆን ደስተኛ ፡
እንቅልፍ ማይዞርብሽ እኔ ሳልተኛ፡፡

እማዬ...
አንቺ እየተራብሽ እኔን ምታበዪኝ፡
አንቺ እየደማሽ እኔን ምታክሚኝ፡
ህመምሽን ደብቅሽ ፈገግ ምትዪልኝ፡
ስትወጪ ስትወርጂ ድካምሽን ሳትነግሪኝ፡
እንዳላስብ ብለሽ የምትጨነቂልኝ፡
ጭንቀትና ሀዘኔን ሁሉ ምታስረሺኝ፡
በለስላሳ እጆችሽ እየደባበሽኝ፡፡
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ማን አለ እንዳንቺ እማ የኔ ፍቅር፡
ህይወቴ እንዲደምቅ የሆንሽልኝ ሚስጥር፡
እኔማ ያላንቺ አላስብም መኖር፡
ፈገግታሽን ሳላይ አልችልም ማደር፡፡
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
አንቺ እየበረደሽ ለኔ ምታለብሽኝ፡
ለራስሽ ተጨንቀሽ እኔን ምታፅናኚኝ፡
ፈተና ሲገጥመኝ ምትሆኚው ከጎኔ፡
ሁሉም ችላ ቢለኝ ቢረሳኝም ያኔ፡
አንቺ መች ረስተሽኝ ታውቂያለሽና፡
አብረሽኝ ያለሽው ድሮም በርግዝና፡፡
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ጡትሽን አጥብተሽ ፀባዬንም ችለሽ፡
መሄድ ያስለመድሽኝ አንድ ሁለት ብለሽ፡
ስወድቅ ደንግጠሽ እየወጣ ልብሽ፡
የምታባብዪኝ እምባዬን እየጠረግሽ፡፡
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
እማ ኡሚ ፍቅር የዱንያ ጀነቴ፡
ከምንም ትበልጫለሽ አንቺ ውዷ እናቴ፡
ማንም አይንካሽ ነሽና ስስቴ፡
ያልሽኝ አረጋለው ነሽና ንግስቴ፡
አንቺን ብቻ ስካድም ቢያልቅም ጉልበቴ፡
ብቻ ላስደስትሽ አንቺ ነሽ ሀብቴ፡
የኔ ውድ እንቁ አንቺ ነሽ ንብረቴ፡
መቼም ማልቀይርሽ በርካሽ ምናምንቴ፡
በዱንያ ሸቀጦች ባሉባት ኮተቴ፡፡
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ካንቺ በታች ያለው እመኚኝ ከንቱ ነው፡
ከእናት በታች ያለው ከድሮም ርካሽ ነው፡
ልግለፅሽ ብል ብዕር የማይበቃኝ፡
ቃላቶችም ጠፍተው ጣቴ የሚከዳኝ፡
እንደውስቲ ንገሩኝ እንደናት ማናለ፡
የፍቅርን ጥግ ማስተማር የቻለ፡፡

ብወድሽ. ብወድሽ አብዝቸ ብወድሽ።
እማ ለዉለታሽ ወደር አጣሁልሽ።
ጊዜ የማይሽረዉ የሚኖር ዘላለም።
ፍቅርሽን የሚተካ የለም በዚች አለም።
ያላንቺ አልኖርም እኔማ ባዶ ነኝ።
እኔም እኔ አይደልሁ እማ. ያቺኮነኝ።
እማ ናፍቆትሽ ቢበዛ ትዝታሽ ቢያከሳኝ።
እማ ባንቺ ፍቅር ፈጣሪ ፈተነኝ ።
እማ ናፍቆትሽም በዛ ትዝታሽ ገደልኝ።
ድምፅሽን ሳልሰማ ሳምንታት አልፈኝ
ኡሚ ምን ሆንሽብኝ እያልኩ አሳቡም ገደለኝ
الله المستعان
اللّهُـمَّ إِنّـي أَعـوذُ بِكَ مِنَ الْكُـفر ، وَالفَـقْر ، وَأَعـوذُ بِكَ مِنْ عَذابِ القَـبْر ، لا إلهَ إلاّ أَنْـتَ. 
Audio
መሳጭ ቲላዋ
ዉስጥን ሰርስሮ የሚገባ

https://t.me/https_Asselfya
◾️وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ

➡️«ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በጀነት) አብስር፡፡»

◾️الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ
➡️«እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡»

◾️أُولَـٰئِكَ عَلَيْهِمْ صَلَوَاتٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَرَحْمَةٌ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُهْتَدُونَ
➡️«እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የኾነ ውዳሴዎች ችሮታም አለላቸው፡፡ እነርሱም (ወደ እውነት) ተመሪዎቹ ናቸው፡፡»


📚(ሱረቱል በቀራ 155–157)
◉የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል◉

➩◉ጥርጣሬን ➷ተጠንቀቁ ➷ምክንያቱም ➷ጥርጣሬ ከውሸት ➷ከቅጥፈቶች ሁሉ ➷የላቀው ነውና‼️
https://t.me/https_Asselfya
የመከራ ሰበቦችና መወገጃዎቹ
.mp3
Abu Useymin
🔷 አዲስ ሙሐደራ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

#የመከራ_መገኘት_ሰበቦች_እና__መወገጃዎቹ

=========================

▶️ ይደመጥ ባረከሏሁ ፊኩም ።

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
ምን ይሻላል?
~~~~ ~~
ሰው እንዴት አንድ ጥፋት ባላጠፋበት ሁኔታ ቋንቋው ወይም ዘሩ ስለተለየ ብቻ ይገደላል? ለምንስ ንብረቱ ይዘረፋል ይቃጠላል? እንዲያው ምን አይነት ጊዜ ላይ ደረስን? ስለ አሃዳዊነትና ፌደራሊዝም ሰርክ የምትተነትኑ ፖለቲከኞች ሆይ! የሰው ህይወት የማይገደው፣ ሰው ሰው የማይሸት ፖለቲካችሁን ቀቅላችሁ ብሉት!! ለህዝቡ ከመከራ በቀር ቁምነገር የሌላችሁ እርኩሶች ናችሁ!!

እናንተ ናችሁ ስለ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የምትደሰኩሩት? ከየትም ብሄር ሁኑ! የተቀናቃኝ ፖለቲከኞችን ቃላት እየሰነጠቃችሁ እርኩስ ትንታኔ የምትሰጡትን ያክል ምናለ በብሄራችሁ አባላት የሚፈፀሙ አውሬያዊ ተግባራትን በስሱ እንኳ ብትነቅፉ! ይሄ ነው የመማራችሁ ጥግ? ይሄ ነው የንቃታችሁ መጠን? ይሄ ነው ለወገን መቆርቆር? እንቆረቆርለታለን የምትሉትን ትውልድ የእውነት ብታስቡለት ኖሮ ስነ ምግባሩን ለመግራት በሰራችሁ ነበር!! ግማሹ ህይወት እየረገፈ ከትላንት ጋር ተጣብቆ የአፄዎችን ብፁእነት ሊግተን ይውተረተራል። ሌላው ትላንት በአፄዎቹ የደረሰበትን ግፍ ምንም በማያውቁ ምስኪኖች ላይ ያወራርዳል። ሶስተኛው ረድፈኛ አጉል ሚዛናዊ ነኝ ባይ በየለቱ ከሚረግፈው ነፍስ ይልቅ በሚነቅፋቸው አካላት ቃላት ስንጠቃ ላይ የተጠመደ ነው።

ሁሉም ነቅቻለሁ ባይ እንቅልፋም! ሁሉም ሚዛናዊ ነኝ ባይ ወልጋዳ! ሁሉም ሰው ነኝ ባይ አውሬ! የወገናችን እጣፈንታ በነዚህ የዝንጀሮ ሸንጎዎች ላይ ወድቆ አበሳው በዛ!! ምንድነው የሚሻለን? ወላሂ ስንት ወገኖች ናቸው በሰላም የሚኖሩበት ብቻ ሳይሆን ሸሽተው ለመውጣት እንኳ መንገድ የተዘጋባቸው!! ምንድነው
የሚሻለን?

ወላጆች ሆይ! ያገር ሽማግሌዎች ሆይ! አቅመ ደካማ ምስኪኖችን ዘር እየለዩ፣ ቋንቋ እየመረጡ እያጠቁ ያሉት የናንተው ልጆች እንጂ ከሌላ ፕላኔት የመጡ አይደሉም። ምናለ ልጆቻችሁን ብትቆጣጠሩ? ምናለ “ኧረ አይበጅም! ግፉ ለትውልድ ይተርፋል። መቋጫውስ ምንድነው?” ብላችሁ ብትመካከሩ? እንዴት ባገር በቀየው አስተዋይ ይጠፋል? ምን አይነት የእንጨት ሽበት የበዛበት ዘመን ላይ ደረስን!!

በያቅጣጫው እየደረሰ ያለውን ችግር ሰምታችሁ እንዳልሰማችሁ፣ አይታችሁ እንዳላያችሁ የዝሆን ጆሮ ይስጠን ያላችሁ ዱዓቶች፣ ኡስታዞች፣ መሻይኾች ሆይ! ለመሆኑ ችግሩ ምን ሲደርስ ነው የምትናገሩት? ምንም በማያውቁት ምክንያት በየጥሻው እየታረዱ እየወደቁ ያሉ ደካሞች የናንተ ቤተሰቦች ቢሆኑ እውነት ዝም ትሉ ነበር? እውነት እየጠፋ ያለው የወገናችን ነፍስ ከናንተ የመጅሊስ ሽኩቻ ያነሰ ጉዳይ ነው? እንዴት ባደባባይ ወጥቶ ለሁሉ በሚደርስ መልእክት አላህን ፍሩ የሚል ይጠፋል? ነው ወይስ እየደረሰ ያለው ጉድ አይሰማችሁም አይታያችሁም? ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ
ራጂዑን!!


በአውሮፓ ኳስ ጧት ማታ የምትነዛነዙ ገልቱዎች፣ በአርቲ ቡርቲ ነጋ ጠባ ጆሯችንን የምታደነቁሩ ኮተታም ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች! ምናለ ትውልዱን በመቅረፅ፣ ለችግሩ እልባት በመፈለግ ላይ ብትተጉ! በይሉኝታ ተሸብባችሁ፣ በከርሳችሁ እያሰባችሁ የምታልፉት እያንዳንዱ ግፍ ነገ በራችሁን ማንኳኳቱ አይቀርም።
በመጨረሻም ችግሩን ለመፍታት ወይም ለመቀነስ ከሁሉም የተሻለ ሰበብ እያላችሁ ቆማችሁ የምትመለከቱ አልፎም የምታባብሱ ሹማምንቶች፣ ነፍጥ አንጋቾች፣... ከአኺራ በፊት አላህ ዱንያ ላይ ያዋርዳችሁ! አላህ የጃችሁን ይስጣችሁ! ከቤታችሁ ሃዘን ይግባ! መከራ ይመላለስባችሁ!
‌أَلَا ‌لَعۡنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلظَّٰلِمِينَ
https://t.me/IbnuMunewor