💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.59K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
↪️እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው፡፡
ሶላቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡”

【ሱረቱ አል- ጁሙዓህ፡ 9 - 10】
🔷 ወንድማዊ ምክር
የሰውን ሐሳብ የኔ ነው ብላችሁ ርእስ ቀይራችሁ ስሙን አጥፍታችሁ የራሳችሁን ስም ፅፋችሁ በቻናላችሁ ላይ የምትለቁ ይህ ተግባር በየትኛውም መመዘኛ ስህተት ነው ። ወንድሜ ሆይ እራስህን ለመሆን ሞክር , ምክንያቱም በሌላ የተሸፈነ ማንነት ሽፋኑ ተነስቶ መታየቱ አይቀርምና ። አንድ ሙስሊም ነኝ ከሚል ሰው እንዲህ አይነት ተግባር አይጠበቅም እንኳን ወደ ሱና ከፍ ብያለሁ ከሚል ይቅርና ። አላህ ሰዎች እንኳን ባልሰሩት ስራ መመስገን ሊፈልጉ ይቅርና በራሳቸውም ስራ ሊመፃደቁ እንደማይገባ ካልሆነ ግን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እንዲህ በማለት ይነግረናል : –
" لَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَفْرَحُونَ بِمَا أَتَوا وَّيُحِبُّونَ أَن يُحْمَدُوا بِمَا لَمْ يَفْعَلُوا فَلَا تَحْسَبَنَّهُم بِمَفَازَةٍ مِّنَ الْعَذَابِ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيم ٌ"
آل عمران ( 188 )
" እነዚያን በሠሩት ነገር የሚደሰቱትንና ባልሠሩትም መመስገንን የሚወዱትን አታስብ ፤ ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸው ብለህ አታሰባቸው ፡፡ ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው ፡፡"
ይህ አንቀፅ የዚህ አይነቱ ተግባር የሙስሊሞች አለመሆኑን ነው የሚያሳየን ። በዲን ጉዳይ አንድን ንግግር ስንወስድ ንግግሩን ወደ ባለቤቱ ማስጠጋት አማና ዒልሚያ በመባል ይታወቃል ። የእውቀት አደራ ነው ። ይህ ከሌለ አደራ እንደመብላት ይቆጠራል ።
ትላንት ( ወደ አላህ ሽሹ ) በሚል ርእስ የፃፍኩትን ፁሁፍ አንዱ ተነስቶ ( ወደ አለህ እንሽሽ ) በሚል ርእስ ቀይሮ ስሙን አጥፍቶ በራሱ ስም በቻናል ላይ የለቀቀው መሆኑን ሲያሳዩኝ በጣም ነው ያዘንኩት ። ምን አይነት ትወልድ እያፈራን እንደሆነ ያውም በዲን ጉዳይ !!!!!
መልእክቱ ራሱ ከእንደዚህ አይነት ተግባር እንራቅ የሚል ነው ። ከወንጀል ርቀን ተውበት አድርገን ወደ አላህ መጠጋት እንዳለብን ነው የሚመክረው ።
ታዲያ ያልሆኑትን ነኝ እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለ እንዴ ?
የሰውን ሐሳብ የኔ ነው እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለ?
ያልሰጡትን ሰጥቻለሁ እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለን ?
ሰው የፃፈውን ሽፋኑን ቀዶ ጥሎ በራስ ስም ሌላ ሽፋን አበጅቶ ለአንባቢ እያቀረቡ ወደ አላህ መሸሽ አለ እንዴ ?
ይህ ተግባር እኔንም ሆነ ሌሎች ሀሳባቸው የሚሰረቅባቸውን ወንድሞች አይጎዳም የሚጎዳው ባለቤቱን ነው ። ሌሎችም ለካ እንዲህ ማድረግም ይቻላል እንዴ ብለው የዚህ አይነት የሐሳብ ሌብነት ውስጥ እንዳይገቡ ነው ለማስታወስ የተፈለገው ። እንጂ ተግባሩ የግለሰቡን ማንነት ከማሳየቱ ሌላ ፋይዳ የለውም እና ከእንደዚህ አይነት ተግባር እንጠንቀቅ ።
https://t.me/bahruteka
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
📌ግጥም "መኖር እንደ ዘበት "

በጣም መሳጭና ገሳጭ የሆነ ግጥም


🎙ኡስታዜ ኢብኑ ሙነወር አላህ ይጠብቀው


ወደ ቴሌግራም ቻናል ጆይን ለማለት
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
https://telegram.me/abutoiba

ወንድማዊ መክራችሁን በዚህ ለግሱኝ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
@AbuAyub_bot
ሂድ ወደ ገጠሩ ተውሂድ መግባቸው ‼️
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️

ወጣቱ ተነሳ ሁልህም በአንድነት
ተውሂድን አስተምር ሽርኩ ይንኮታኮት
ቢድዓ ይወገድ የሱናችን ጠላት

በገጠር ላይ ያሉ ተውሂድ የጠማቼው
ብዙ ሰወች አሉ አኔ የማውቃቸው
እውቀት አልባ ሁነው አስተማሪ አጥተው
ጀግናየ ሂድና ተውሂድ መግባቸው
የረሱሉን ሱና በደንብ አሳያቸው
በሱና ይዋቡ ከሽርካሽርክ ወጥተው
ሽርክ እና ቢድዓን ከስሩ እጨደው
ደግሞ እንዳይነሳ ድቅቅ አድርገህ ጣለው
በሱ ቦታ ወስደህ ተውሂድን ትከለው

የሀገሬ ህዝብ በጣም የምወደው
የሰው ልጅን ክብር በደንብ የተረዳው
እንግዳ ተቀባይ ሰውን አክባሪ ነው
ነገር ግን አቂዳው በጣም ደካማ ነው
ተውሂድን አያውቅም አስተማሪም የለው
በሽርክ በቢድዓ የተዘፈቀ ነው
ለቀብር ለጅኑ ቁርባ የሚያቀርብ ነው
ብቻ በአጠቃላይ በሽርክ በሽታ የተበከለ ነው

ትንሽም ቢኖሩ የሱፍይ ሸኽ ናቸው
አኼራን የረሱ ዱንያቸውን ወደው
ከሽርክ ከቢድዓ ማስጠንቀቅን ትተው
አስረው ይዘውታል ምርኮኛቸው አድርገው

አላዋቂው ህዝብ እሱን እንዲያከብረው
ብሎ ይሰብካል እኔ ላስጣችሁ ሀጃችሁ ምንድነው
ጫቴን እየቃምኩኝ ያረቢ እርዳኝ ብለው
እኔን ይሰማኛል ጌታየ ቅርብ ነው
ብሎ ይፎክራል ልክ አቅም እንዳለው
እነሱም ጃሂሎች እውቀት የሌላቸው
ሸኹ መጀን አሉ ይሰጣል መስሏቸው

አንተ ውድ ወንድሜ አድምጠኝ ልንገርህ
ሀቅን ከመናገር ወደ ሗላ ብለህ
አለባብሶ መሄድ መቼም ላያዋጣህ
ሀቅን ከማስተማር በጣም ተዘናግተህ
አኼራን ዘንግተህ ዱንያን አስቀድመህ
መቼም የማይቀር ነው አንድ ቀን መሞትህ
ገጠር የሚገኙ ምስኪን ዘመዶችህ
ተውሂድ መግባቼው ከሽርክ አስወጥተህ

ወንድሞች እንንቃ ተውሂድን እንዝራው
ከተማ ገጠሩ አጭዶ እንዲበላው
ሽርክ እና ቢድዓን አራግፎ ይጣለው
ሸኹ ድረሱልኝ ማለቱን ይተወው
በጠዋትም በማታም ተውሂድ እንመግበው
በሰለፎች መንገድ ጉዞውን ያድርገው

🖊 ቢንት አህመድ
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
◼️የተጅዊድ ኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖

↪️ሂዳየቱል ሙስተፊድ
👇👇👇👇👇
【ክፍል 2⃣0⃣】
〰〰〰〰〰

✅ መዱል ላዚም ኪልምይ ሙኸፈፍ
✅ መዱል ላዚም ኪልምይ ሙሰቀል
✅ መዱል ላዚም ሀርፍይ ሙኸፈፍ
✅ መዱል ላዚም ሀርፍይ ሙሰቀል

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

🔺ደርሱን ለመከታተል⤵️⤵️⤵️⤵️

https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
✅ ➷ሙራቀበቱሏህ!

➷የአሏህ ፍራቻ "ተቅዋ" ን በመላበስ ኢማንን ለማበልፀግ ከሚያግዙ ብዙ ነገሮች መካከል የአሏህን ተቆጣጣሪነት ማሰብ እና ለምንሰራው ስራ ሁሉ አላህ እንደሚያየን ማሰብ *"ሙራቀበቱላህ"* በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል።

➷አሏህ ተመልካች መሆኑን በማስታወስ አላህን በራሳችን ላይ ተቆጣጣሪ ማድረግ ስንል፤ ስራን መገምገም፣ በግልፅም ይሁን በድብቅ የምንሰራዉን ሁሉ አላህ እንደሚያውቅ ማስተዋል ማለት ነው። በተለይ ከሰዎች እይታ በራቅንበት ወቅት አሏህን በኛ ላይ ተቆጣጣሪ ማድረግ ተቅዋን በእጅጉ ከሚያበለፅጉ ነገሮች ዋነኛው ነው።

➷ አሏህን ባናየው እንኳ እርሱ ያየናልና ስናመልከው እንደምናየው አድርገን መሆን አለበት። ኢህሳን የምንለው የመልካም ስራ እርከን ይህ ነው። ከአላህ እይታና ቁጥጥር መራቅ አንችልም።

➷አል አንደሉሲይ ልጃቸውን ለመምከር የቋጠሯቸው ስንኞች ተከታዩን መልእክት ያዘሉ ነበሩ፤
وإذا خلوت بريبة في ظلمة
والنفس داعية إلى الطغيان

فاستحيي من نظر الإله وقل لها
إن الذي خلق الظلام يراني

➷በጨለማ አሻሚ ቦታ ላይ ሆነህ
ነብስህ ድንበር እንድትጥስ ስትገፋፋህ፤

➷ጌታህ ያይሀልና ሀፍረት ይሰማህ...
ለነብስህም በላት፤ ጨለማን የፈጠረው አምላክ ይመለከተኛል!!

➷ስለዚህም፤ ለምንናገረውና ለምንሰራው ሁሉ አላህን እንፍራ! መልካም ስራን ስንፈፅምም ፍፁም ለአላህ ብቻ ይሁን።

➷አሏህ ተቅዋን እና መልካም ስራን ያግራልን!

وصلَّى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلَّم
https://t.me/IbnuMohammedSunah01

💦💦💦💦💦
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
🔻ቆየት ካሉ ምርጥ ሙሐደራ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📌በሱና ላይ መፀናት

🎙በወንዲም አቡ ሒበቱላህ አሏህ ይጠብቀዉ!!

https://t.me/https_Asselfya
ሸዳድ ኢብን አውስ በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمእንዲህ አሉ።

✅ “አላህ በሁሉም ነገር ላይ መልካምን ማረግ አዟል። በምትገሉ ጊዜ አገዳደላቹህን አሳምሩ። እንስሳትን ስታርዱም አስተራረዳቹህን አሳምሩ። አንዳቹህ ቢላውን ይሳል፥ የሚያርደውንም እንስሳ ይገላግለው።”
📚 ሓዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል።

https://t.me/https_Asselfya
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ

➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹ጣሁት ማለት ምን ማለት ነው
🔹ዋና ዋና የጣጉት አይነቶች

🔻【ክፍል 4⃣8⃣】
〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
✅ የነብዩ صلى الله عليه وسلمአስተናጋጅ የነበረው አነስ ኢብን ማሊክ በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمእንዲህ አሉ።

↪️ “አንድ ሰው ለራሱ የሚወደውን ነገር ለሙስሊም ወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።”
📚ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
من ترك ابنته أو زوجته تخرج متبرّجة ؛ فهو إمّا فخورٌ بالعارِ، أو مغلوبٌ بالدّارِ، أو ديّوثٌ لا يَغار !!!

وسلّم لي على الحريّة الشّخصيّة !!

#الحياء
✍ ‏قال الإمام شيخ الإسلام ابن تيمية

- رحمه الله تعالى - :

" وكشف النساء وجوههن بحيث يراهن الأجانب غير جائز " .

📗 الآداب الشرعية ( ١ / ٢٨٠ ) .
↪️አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ - እንድህ ብላለች “የአላህ መልክተኛ የሰኞን እና የሐሙስን ጾም (ለመጾም በጉጉት) ይጠባበቁ ነበር፡፡”
📚 (ቲርሚዚይ: 745)

✅ሙእሚኖች ለመልካም ነገሮች ጉጉቱ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሰኞ እና ሐሙስን መጾም፤ በየወሩ አስራ ሶስት፣ አስራ አራት እና አስራአምስተኛው ቀን መጾም፤ ዚክር (ተስቢህ ተህሊል ተህሚድ ማብዛት) ፤ ቁርአን መቅራት ፤ በሽተኛን መጠየቅ ፤ ወደተውሂድ ጥሪ ማድረግ ፤ ሰዎችን መልካም ነገር ማስተማር፤ በመልካም ማዘዝ፤ ከመጥፎ መከልከል የዘወትር ተግባራችን ሊሆን ይገባል፡፡

🔻ሙእሚን አጋጣሚዎችን ይጠቀማል ፤ ጊዜውን ሳያባክን አላህ ለሚወደውና ወደርሱ ለሚያቃርበው ተግባር ይጠቀማል ፤ በቤቱም፤ በመንገዱም፤ በመስጅዱም ፤ በሁሉም ቦታ በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ የአላህን ሰዋብ (ምንዳ) ተስፋ ያደርጋል ፤ የአላህን ቅጣት ይፈራል፡፡
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk