💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
8.85K subscribers
1.53K photos
540 videos
136 files
5.76K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🌸مَّثَلُ ٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى وُعِدَ ٱلْمُتَّقُونَ ۖ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ ۖ أُكُلُهَا دَآئِمٌۭ وَظِلُّهَا ۚ تِلْكَ عُقْبَى ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوا۟ ۖ وَّعُقْبَى ٱلْكَٰفِرِينَ ٱلنَّارُ

~"አላህን ለሚፈሩ ባሮች ቃል የተገባችው ጀነት ምሳሌዋ ፣ከስርዋ ወንዞች ይፈሳሉ።ምግቧ ሁልጊዜ የማይቋረጥ ነው።ጥላዋም የማይቋረጥ፣ ይህቺ የእነዚያ የተጠነቀቁ ሰዎች መጨረሻ ናት።የካሃዲዎችም መጨረሻ እሳት ናት።"
{ሱረቱ አር‘ራዕድ}

አላህ ከጀነት ሰዎች ያድርገን።

t.me/https_Asselfya
03 ሀዚሂ ደዕወቱና ወዓቂደቱና
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
🔖ሀዚሂ ደዕወቱና ወዓቂደቱና

👉ክፍል ሁለት (➂ )

🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ

~የኪታቡ pdf👇
     t.me/https_Asselfya/12607
ሁሉም ኒዕማ ተወጋጅ ነው 🌺

👉 የጀነት ሰዎች ኒዕማ ሲቀር🫀

ሁሉም ጭንቀት(ስቃይ) ተወጋጅ ነው

👉 የጀሀነም ሰዎች ጭንቀት ስቃይ መከራ ሲቀር💦

📗 المجالسة وجواهر العلم ١٥٩١
👍2
ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፡-

“በፍርዱ ቀን መጋረጃው በተገፈፈ ጊዜ ሰዎችም የሠሩትን ምንዳ ባዩ ጊዜ ከዚክር (አላህን ከማውሳት) የበለጠ ምንዳ ያለው ሥራ አያገኙም።

በዚህ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች በመጸጸት እንዲህ ይላሉ፦

‹ከዚክር በላይኮ በእርግጥ ለእኛ ቀላል ነገር አልነበረም›።

(አል-ወቢል አል-ሰይብ 1/78)

▣ በቀን ውስጥ ለዚክር የሚሆን የተመደበ ጊዜ ይኑረን፣ ዚክር የአኼራን ብቻ ሳይሆን የዱንያን ህይወት ሁሉ የሚያገራ የአላህ ስጦታ ነው።
قال الشيخ *ابن عثيمين* رحمه الله :

" *إن النعم إذا لم تشكر زالت وأكبر نعمة أنعم الله بها على عباده هي نعمة الدين فإذا لم تشكر فإنها تزول كغيرها من النعم".*

📝[تفسير سورة النور (٣٦٦)].
☀️ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን ((ሀፊዘሁሏህ)) እንዲህ ይላሉ፦

      ሴት ልጅ ትልቅ የሆነ ግዴታ አለባት ወደ አሏህ  ዳእዋ በማድረግ ስለዚህ... በእውቀት የታጠቀች ልትሆን ይገባታል!

ምንጭ
📚{{المحاضرات ٥٥٨/٥ }}
👍5
🔖ከጋብቻ በፊት ወላጆች ለሴት ልጆቻቸዉ የሚሰጡት ምክር...!

ጋብቻ ከመፈፀሙ በፊት ወላጆች ለልጆቻቸዉ ምክር መስጠታቸዉ ይወደዳል።(እንዳደርጉትም ይመከራል)አነስ (ረ.ዐ)እንደተናገሩት የነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም ባለደረቦች ሴት ልጃቸዉን ለባል ሲሰጡ ባሏን እንድትንከባከበዉ ምክር ይለግሷት ነበር ብለዋል።

~አብደላህ ኢብን ጃዕፈር ኢብን አቡ ጣሊብ (ረ.ዐ)#ለምሳሌ ለሴት ልጁ የሚከተለዉን አራት ነገሮች እንዲትተገብር መክሯታል።
➀.ቅናትን አደራሽን ለፍች ምክንያት ነዉና።
➁.ወቀሳን አታብዠ ለጥላቻ(ለቂም)ምክንያት ነዉና።
➂.ኩልን ተጠቀሚ እርሱ ከማጊያጋጫዎች ሁሉ በላጭ ነዉና
➃.ዉሃ ከሽቶ ሁሉ በላጭ ነዉ ።

=
t.me/https_Asselfya
👍9
🔖በዚች አለም ላይ የሚገኝ ነገር ሁሉ አላህን ለማስታወስ ካልዋለ ከጨዋታ(ከዛዛታ)ይቆጠራል። አራት ነገሮች ሲቀሩ፦
➀.ሚስትን መንከባከብ
➁.ፈረስን ማልመድ(መንከባከብ)
➂ .ቀስት መወርወር
➃.ዉሃ ዋናን መለማመድ።

     t.me/SleSlkachin
حُسن الظن بالله سبحانه وتعالى
خطبة الشيخ غسان الحميدي
🔸حُسن الظن بالله سبحانه وتعالى

#خطبة الجمعة
جامع الرحمن بقرية الحبيل لحج
🎙للشيخ الفاضل|
غسان الحميدي حفظه الله

🗓 بتاريخ ١٠ صفر ١٤٤٨ه‍
┈┉┅━━•❁•━━┅┉┈
◢للمزيد| قناة الخطباء
➢https://t.me/ooooh5
ሴቶች ከተማሩ በኋላ ብዙ አይነት ሁኔታ ይኖራቸዋል፦

1. ከተማሩ በኋላ አግብተው መቅራትን እርግፍ አርገው የተው አሉ። የቀሩትን ኪታብ እንኳ ከቤታቸው ሁነው የማያነቡ። ምክንያቱ ደግሞ በቤትና በልጅ እንክብካቤ ላይ መጠመዷ ነው። ጨዋታ፣ ስበሰባ ሲሆን ግን ...። ለብዙ ሰአቶች ቴሌቪዥን ላይ እያፈጠጡ የሚቀመጡ ለቂርአት ግን ጊዜ የሌላቸው።

2. ተምረው አግብተው ስራ የያዙ አሉ። ነገር ግን አላማዋ ስራዋ ላይ ብቻ ነው። ቂርአት፣ ሙራጀዓ፣ ኸይር ማሰራጨት ተትቷል። በስራዋ ቢዚ ናታ። እነዚህ አይነቶች ድሮም የዒልም ድርሻ የላቸውም። ስራ ነበር አላማቸው አግንተዋል። ማንበብ የለም፣ ማዳመጥም የለም።

3. ተምረው አግብተው ከነሱ በላይ ተጨባጭን የሚገነዘብ እንደሌለ የሚያስቡ ናቸው። ጋዜጣ ሰብሳቢ፣ ውዳቂ ታሪኮችን ለቃቃሚ፣ አድስ ነገር አባራሪ። እነዚህ እስልምና ላይ ከባድ ጉዳት አላቸው። ሀፍረትን እርግፍ አርገው ጥለው ከሌሎች ላይም የሚገፉ፞። እነዚህ ለመጥፎ ስራ፣ ለመገላለጥ፣ ለወንድና ሴት መቀላቀል ሰበቦች ናቸው።

ለእንደዚህ አይነት ሴቶች ምክሬ፦

• ቁርአንን በመቅራትና በማስተንተን ላይ እንዲዘወትሩ
• የቻሉትን ያህል የነብዩን ﷺ ሱና እንዲሐፍዙ
• ዐቂዳ እና ተውሒድ ደርስ ላይ እንዲያተኩሩ
• ወደ ተፍሲር እውቀት በመዞር የአላህን ኪታብ እንዲረዱ - በተለይ ተፍሲረ ሰዕዲይ።
• የፊቅህ እውቀት ላይ በማተኮር እሷን የሚመለከቷትን ነገሮች፡
- ስለ ሐይድ
- ስለ ጦሃራ
- ስለ ሶላት
- ስለ ፆም
- ስለ ሐጅ
- ከባሏ ጋር ሊኖራት የሚገባውን ነገሮች በመማር ላይ እንድታተኩር ነው ምክሬ።
~
ከ“አሃሚየቱል ዒልም ሊልመርኣቲል ሙስሊማ”
የሸይኽ ዐብዱላህ ጦያር ተነካክቶ የተወሰደ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/MOhamedAljawi
https://t.me/MOhamedAljawi
👍3
ከሁሉም በላጭ ስራ! 

   ~~
﴿سُئِلَ رسولُ اللهِ ﷺ أيُّ الأعمالِ أفضلُ؟ قال: الصلاةُ في أولِ وقتِها.﴾

የአላህ መልእክተኛ ተጠየቁ፦ በላጩ ስራ የቱ ነው? አሉ፦ “ሶላትን በወቅቱ (በመጀመሪያው ግዜ) መስገድ።”
ሶሂህ አልጃሚዕ: 1093

=
    t.me/https_Asselfya
ከትዳር ሕይወት አስቂኝ ገጠመኞች
​አንዲት ሚስት ባሏን በቁጣ/በመገረም ጠየቀችው፡
– ከማገባታችን በፊት ድሃ እና ኪሱ ባዶ የሆነ ሰው መሆንህን ለምን አልነገርከኝም?
​እሱም ፈገግ ብሎ መለሰላት፡
– «በዚህ ዓለም ላይ ከአንቺ ውጭ ምንም የለኝም» ብዬ ከአንድ ሚሊዮን ጊዜ በላይ አልነገርኩሽም እንዴ?
አንቺ ደግሞ እንደ የዋህ/ሞኝ እየሳቅሽ ደስ ይልሽ ነበር!
​(አንዳንድ ጊዜ ፍቅር አዘል ንግግሮች እውነተኛ ትርጉም ያስፈልጋቸዋል!©
👍4
አሏህን በትዕግስት ጠብቂው!

ስጦታው ከምታስቢው በላይ
ውብ መሆኑን እመኝ።


ትያለሽም፦ً የደስታን እንባ እያነባሽ
አንደበትም አጥሮሽ እየተንተባተብሽ.

ጌታዬ_ሆይ!
ለካስ ከዱዓ'ዬ በላይ ስመኘው ሳስበው
ከነበረው የበለጠና ያማረን ስጦታህን
ሰጥተህ.. እንድህ ልታስደስተኝና
ልታረጋጋኝ.. ሙሉ ፈገግታና ሰላምን
ልትቸረኝ.. ፈልገህ ነበርጂ አላዘገየኸውም
!!

ያ አል-ረሕማኑ  አመስግናለሁ.. ብለሽ
ደጋግመሽ በስጁድሽ ታመስግኚዋለሽ
قريباً إن شاءالله...!!
👍17
04 ሀዚሂ ደዕወቱና ወዓቂደቱና
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
🔖ሀዚሂ ደዕወቱና ወዓቂደቱና

👉ክፍል (➃  )

🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ

~የኪታቡ pdf👇
     t.me/https_Asselfya/12607
ሞኝ ነሺ.....!!
ቢወድሺ ኖሮ  ማንም እዳያይበት በደበቀሺ ነበር  በሚድያ ለጥፎ የማንም አይን እዳርፍብሺ ባላደረገ ነበር  ፡አንች ግን ስለሚወደኝ ነው በየሚድያው የሚፖስተኝ ብለሺ በተሳሳተ አስተሳሰብ ትሞኛለሺ
ከፈለገ ሴቶች ማናት ሲሉት   ሚስቴ እሚለው ትቶ እህቴ ናት ሊል ይችላል እቴይ!!


نقل
👍7
✅️ልጅ የሚያድገው ወላጆቹን መስሎ ነው።

✅️ልጆቿን በሱና ላይ አታሳድግም፤መጀመሪያ ራሷን በሱና በእዉቀት ያነፀች ብትሆን እንጂ👍

👉ስለዚህ፦ልጅ ከመውለድሽ በፊት: ቅሪ...ተማሪ...እወቂ📚
👍12