💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.03K subscribers
1.41K photos
525 videos
128 files
5.49K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
Forwarded from ስለ ስልካችን
🪷ከወንጀሉ ተውበት አድርጎ የተመለሰ
አባቱን ኣደምን ሲመሳሰል………በወንጀሉ ላይ ፀንቶ የቀጠለ ደግሞ ጠላቱን ዒብሊስን ይመስላል

🪷
👍9
Audio
የኢባዳ ጥፍጥና ማግኘት ከፈለግክ ከወንጀል ራቅየኢባዳ ጥፍጥና የአላህ ስጦታ ነው። ይህ ደግሞ ለወንጀለኛ አይሰጥም

🎙الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله

t.me/https_Asselfya
👍4
"ዐብዱረዛቅ አልሐበሺይ:
አንድ ሰው ለሐሰነል በስሪ እንዲህ ይለዋል "ልጄን  ለማን ልዳር?" 
ሐሰንም "አሏህን ለሚፈራ! ከወደዳት ያልቃታል ያከብራታል፤ ከጠላትም አይበድላትም!"
👍8
➪እርግጥ ➷ሱንይ ሴት የትውልድ መለያ ብሎም መከበሪያ ነች ሱናን ስትይዝ‼️

➷እንደ እንቁ ትከበራለች ➷ከሱና የሸሸች ቀን ግን እንደ አሸዋ ትረክሳለች።
👍9
Forwarded from ስለ ስልካችን
«📲ስልክህን ልተኛ ስትል ፈትሻት ምን አልባት
ጠዋት ሰትነሳ አንተ ላትከፍተው ትችላለህ አሏህ የሚያቀውና የሚያየው ከሰው የተደበቀ ብዙ ወንጀል ሊኖርበት ይችላልና ቀን ሙሉ ለሰራኸው ወንጀል ምህርትን ጠይቀህ ተኛ።»

መልካም
አዳር
👍12
መልካም ሴት ዋጋዋ አይተመንም
በምንም ነገር አትቀየርም መልካምነቷ ጊዜያዊና የማስመሰል ሳይሆን ዘለቄታዊ እና እውነተኛ ነው
!!!
👍12
ذَمُّ قَســـــــــــــوةِ القَـــلب
وذِكرُ أسبابِها، وما تَزُولُ بِه

تَأليفُ الحافظ أبِــــــي الفَرَج:
عبدالرحمن ابن رَجَب الحَنبلي

المُتوفَّى سنة (٧٩٥ هـ) رحمه الله

#ዘሙ_ቀስወቲል_ቀልብ
የኢማም ኢብኑ ረጀብ አልሐንበሊ
በኡስታዝ ዐብዱ ረዛቅ አልባጂ
🪷ሀላል ሪዝቅ መፈለግ በእርግጥ ወገብን ይሰብራል። ነገርግን #በዱንያም በአኼራም  ቀና ብለህ እንድትጓዝ ያደርግሀል

🪷
     t.me/https_Asselfya
👍1
🌻ፀሀይ በጠዋት ብቻ ሳይሆን ከሰአትም ታበራለች።ጨለመብኝ ብለሸ በፍፁም እንዳሰጊ!አንች እስካለሸ ድረስ ሁሌም ብርሃን አለ።በርችልኝ የኔ ጀግና!
👍6
أمؤمن أنت؟!..

سُئِل الحسن البصري:
يا أبا سعيد، أمؤمن أنت؟

فقال:
الإيمان إيمانان...

فإن كنت تسألني عن الإيمان بالله وملائكته وكتبه ورسله والجنة والنار والبعث والحساب فأنا به مؤمن...

وإن كنت تسألني عن قوله تبارك وتعالى:
(إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ) إلى قوله: (أُولَٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا) [الأنفال:2-4]
فوالله ما أدري أنا منهم أم لا....

قال ابن القيم: اطلب قلبك في ثلاث مواطن، عند سماع القرآن، وفي مجالس الذكر، وفي أوقات الخلوة، فإن لم تجده في هذه المواطن؛ فسل الله أن يمن عليك بقلب فإنه لا قلب لك...

📖 الفوائد: 148 .
👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉የወንድ ልጅ መጥፊያዎች 3ናቸው
1.ለብቻ በሚሆንበት ጊዜ አሏህን ይፈራል ወይስ አይፈራም
2.ንብረት (ገንዘብ)
3.ሴት
🔖ጥሩ ባልና ሚስት ለሁለቱም፦ የጋራ መርሆዎች!

1) መተማመን፦ ጥርጣሬ የትዳር ትልቁ ጠላት ነው። ግልጽነት ባለበት ቦታ ሰላም ይሰፍናል፡፡

2) ይቅር ባይነት፦ ፍጹም ሰው የለም:: ጥፋትን ቆጥሮ ከመያዝ ይልቅ በይቅርታ ማለፍና ካለፈ ስሕተት መማር ለትዳር ዕድሜ ይሰጣል፡፡

3) የጋራ ዓላማ፦ ገንዘብን፣ ጊዜንና የወደፊት እቅድን በጋራ መምራት "እኔ" ከሚል መንፈስ ወጥቶ "እኛ" ወደሚል አንድነት ያመራል፡፡

👉ጥሩ ባልና ሚስት ማለት የማይጋጩ ሳይሆኑ፣ ግጭታቸውን በፍቅርና በትዕግሥት መፍታት የሚችሉ ናቸው። ትዳር የሚገነባው በሚያምር ሰርግ ሳይሆን በየቀኑ በሚታዩ ትናንሽ የመከባበር ተግባራት ነው።

    t.me/https_Asselfya
👍5
{ لا إله إلا أنت سبحانك إني كنت من الظالمين }
በእስልምና (በሸሪዓ) እይታ፣ በስራ ቦታም ሆነ በማንኛውም የህይወት ዘርፍ ሰውን መመቀኘት (ሀሰድ) በጥብቅ የተከለከለ (ሀራም) እና በጣም አደገኛ የስነ-ልቦና በሽታ ነው።
ሸሪዓው በስራ ቦታ ለሚፈጠር ምቀኝነት ልዩ ትኩረት ይሰጣል፤ ምክንያቱም ስራ የሰው ልጅ ሲሳይ (ርዝቅ) የሚፈልግበት እና ከሰዎች ጋር በቅርበት የሚገነባበት መድረክ በመሆኑ፣ እዚህ ቦታ ላይ የሚፈጠር ምቀኝነት የስራ አካባቢን መርዛማ ከማድረጉም በላይ የአንድን ሙስሊም እምነት (ኢማን) ያበላሻል።
በስራ ጉዳይ ላይ የሚንጸባረቅን ምቀኝነት የሸሪዓ መነጽር በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ያስረዳናል፦
### 1. የ"ሀሰድ" (የምቀኝነት) ትርጉም በሸሪዓ
በእስልምና ምቀኝነት ማለት፡ "አላህ ለአንድ ሰው የሰጠው ጸጋ (ደሞዝ፣ ማዕረግ፣ እውቀት፣ የስራ ስኬት) ከእሱ ላይ ተነስቶ ለእኔ ቢሰጠኝ ወይም ዝም ብሎ ቢጠፋለት" ብሎ መመኘት ነው።
* አንድ ባልደረባዎ በስራው ጎበዝ ሆኖ ሲመሰገን ወይም ሲያድግ በውስጥዎ መጨነቅ እና ውድቀቱን መመኘት የሀሰድ መገለጫ ነው።

### 2. ምቀኝነት በሸሪዓ የተከለከለበት ዋና ዋና ምክንያቶች
* ከአላህ ውሳኔ (ቀድር) ጋር መጣላት፦ አላህ በቁርኣኑ ላይ እንዲህ ይላል፡-
   > *"በቁርጠኝነት እኛ በመካከላቸው የዚህችን ዓለም ኑሮአቸውን አካፈልን፤ ከፊላቸውም ከፊሉን ታዛዥ አድርጎ እንዲይዝ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች ከፍ አደረግን።"* (አል-ዙኽሩፍ: 32)
   > ስለዚህ የአንድን ሰው የስራ ስኬት መጥላት፣ አላህ ለዛ ሰው የወሰነውን ሲሳይ እና እውቀት እንደመቃወም ይቆጠራል።
   >
* መልካም ስራን ማጥፋቱ፦ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦
   > *"ምቀኝነትን ተጠንቀቁ፤ እሳት እንጨትን እንደምትበላ ሁሉ ምቀኝነትም መልካም ስራዎችን ትበላለችና።"* (አቡ ዳውድ)
   > አንድ ሰው ስራውን በአግባቡ ቢሰራም፣ ቢሰግድም፣ ቢጾምም በውስጡ ምቀኝነት ካለ መልካም ምንዳው (አጅሩ) ይበላሻል።
   >
* ሙስሊሞችን መጉዳት መከልከሉ፦ በሀዲስ ላይ *"አትመቃቀኑ፣ አትጣሉ፣ የላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ"* ተብሏል። በስራ ቦታ ሰውን ለመጣል ወሬ ማማት፣ ስሙን ማጥፋት ወይም ስራው እንዳይሳካ ማሰናከል ትልቅ ወንጀል ነው።
### 3. በሸሪዓ የተፈቀደው "ምቀኝነት" (ግبطة - ฆิบጠህ)
እስልምና በበጎ ነገር መቅናትን እና መወዳደርን ይፈቅዳል። "ጚብጠህ" ማለት፦ "ያ ሰው ባለው የስራ ብቃት፣ ታማኝነት ወይም ማዕረግ ደስተኛ መሆን፣ ነገር ግን 'እሱ እንዳለ ሆኖ አላህ ለእኔም እንደሱ አይነት ስኬት ቢሰጠኝ' ብሎ መመኘት እና ለዛ መጣር" ነው።
ይህ ጤናማ የስራ ውድድር (ሙናፈሰህ) ስለሚፈጥር በሸሪዓ የተወደደ ነው።
### 4. በስራ ቦታ ከምቀኝነት ለመንጻት ምን መደረግ አለበት?

1. ርዝቅ ከአላህ መሆኑን ማመን፦ ያ ሰው ስላገኘ የእርስዎ ሲሳይ አይቀንስም። አላህ ለእርስዎ የጻፈው ነገር በማንም ተጽእኖ እንደማይቀር ማወቅ።

2. ዱዓ ማድረግ፦ ለዚያ ለተቀናቃኝዎ ወይም ለበላይዎ ስኬት በውስጥዎ ዱዓ ማድረግ። ይህ በውስጥ ያለን የበታችነት ስሜት እና ምቀኝነትን ያጠፋል።

3. በራስ ስራ ላይ ማተኮር፦ የሰውን ስህተት ከመፈለግ ይልቅ የራስን ብቃት ማሳደግ እና በሃላል መንገድ ለመግፋት መጣር።
ባጭሩ በስራ ቦታ ሰውን መመቀኘት በዱንያም የስራ ሰላምን ያውካል፣ በአኺራም ከአላህ ዘንድ ቅጣትን ያስከትላል። የስራ ባልደረባ ሲያድግ "ማሻአላህ" ብሎ መመረቅ እና ለራስም ስኬትን ከአላህ መለመን የሙስሊም ባህሪ ነው።

🖊 በአቡ አኢሻ 1447/ذوالحجة/22።

t.me/Abuebrahim22322
t.me/Abuebrahim22322
👍1
Forwarded from ስለ ስልካችን
🔖ቀላል ጥያቄ

የማይሸጥ የማይገዛ ነገርግን ሰዎች አብዝተዉ የሚመገቡት ሃራም የሆነ ስጋ ምንድነዉ !?

=
🔖 የተዉሒድ ጥቅም !

⓵ )በቀጣይ አለም ከቅጣት ሰላም መሆን ደህንነት ማግኘት

⓶)በዱኒያ በቀጥተኛዉ መንገድ የተመሩ መሆን

⓷)ወንጀሎችን መሰረዙ

الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ أُولَئِكَ لَهُمُ الْأَمْنُ وَهُمْ مُهْتَدُونَ} [الأنعام

الظلم في الآية: فسر النبي ﷺ وأصحابه "الظلم" في هذه الآية بأنه الشرك بالله، مستدلاً بقول الله تعالى على لسان لقمان الحكيم: {إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ} [لقمان: 1

~
t.me/https_Asselfya
📣 ታላቅ ብስራት የደውራ ፕሮግራም ጥሪ!

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የአንሷር መስጂድ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እጅግ ደማቅ እና ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች ጥሪውን ያቀርባል።

📚 የፕሮግራሙ ልዩ እንግዳ፦
ታላቁ የ-የመን ሙሓዲስ ፈደይለቱ ሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ (ሀፊዘሁላህ) —(በየመን የሚገኘውና በርካታ ተማሪዎችን ያፈራው የታዋቂው የመዕበር መርከዝ አስተማሪ)

◈እንድሁም ትልቁ አባታችን ፈደይለቱ ሸይኽ ሙሳ አል-ቀጧን (ሀፊዘሁላህ) ይገኛሉ።

🎙️ በፕሮግራሙ ላይ የሚታደሙ መሻይኾች እና ኡስታዞች፦
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን   ከደሴ
▪️ ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ         ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ    ከደሴ
▪️ ሸይኽ ይማም ሰዒድ        ከደሴ
▪️ ሸይኽ አሕመድ አወቀ       ከደሴ
▪️ ሸይኽ በድሩ ዩሱፍ           ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን     ከቢስቲማ
▪️ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ        ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን       ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሐሰን አሊ ቃዲ          ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሁሰይን አቡ ሶላሑዲን ከደሴ
▪️ ሸይኽ አወል አሕመድ መነዮ  ከመረሳ
▪️ ሸይኽ አወል አህመድ          ከከሚሴ
▪️ሸይኽ ዒሳ አደም                 ከደሴ

🔸 ዶክተር /ኡ ሁሴን አሊ         ከከላላ
🔸 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር       ከአ.አበባ
🔸 ዶክተር/ኡ ሰዒድ ሙሳ         ከአ.አበባ
🔸 ኡስታዝ ኸድር አሕመድ     ከከሚሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሒዛም          ከአዳማ
🔸 ኡስታዝ  ዐብደሽኩር          ከአሶሳ
🔸ኡስታዝ ዐብዱሰላም ሐሰን   ከአዳማ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዒምራን   ከሀርቡ
🔸 ኡስታዝ አቡ አዩብ      ከኮቦልቻ
🔸 ኡስታዝ ሙርሰል        ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሻኪር      ከኮንቦልቻ
🔸 ኡስታዝ አቡ ረያን        ከመርሳ
🔸ኡስታዝ መሀመድ አያሌው ከወልዲያ
🔸ኡስታዝ አቡ ዓብዱ ረዛቅ ጅረሳ ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ    ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ ዐብዱልመሊክ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሐሳን        ከኮቦልቻ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሃኒፋ         ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ መ/ሲራጁ       ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ ዐሊይ ሰይድ     ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አንሷር መሀመድ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሐፍሷ         ከደሴ
🔸ኡስታዝ ጀውሀር  ክፍሌ    ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዐብዲረሕማን ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡል መዓሊ      ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሹራ            ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ማሂ            ከኮንቦልቻ
🔸 ወንድም አቡ ሂበቲላህ       ከደሴ
👥 የአንሷር መስጅድ ኢማምና ጀመዓዎቹ ባጠቃላይ...

👤እንዲሁም ሌሎች ከተለያየ ሀገር  በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው መሻይኾችና ኡስታዞችም በቦታው ይገኛሉ!

📆 የፕሮግራሙ ቀናት፦
የመጀመሪያ ቀን፦ ሰኔ 6/2018 (ከፊታችን ቅዳሜ ጧት 3:00) ጀምሮ ለ 4 ተከታታይ ቀናት ይቆያል።

🏘 ማሳሰቢያ፦
ለታዳሚዎች በቂ የምግብ እና የመኝታ ቦታ ተዘጋጅቷል።—የሌሊት ብርድ ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ መልካም ነው።—

🤩በእነዚህ የቴሌ ግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ ይመዝገቡ፦

📝ኡስታዝ አቡ ሻኪራ አህመድኑር
@Abuhureirehonline
   0923467646

📝 ኡስታዝ አቡ ዐዩብ
  092 588 7118
@Attewhid11

📝 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን
@Abu_Hibetillah_Al_aseriy
0942819970

💙የቦታው አቅጣጫ ካስቸገራችሁ በነዚህ የእንግዳ ተቀባይ ወንድሞች ስልክ ቁጥሮች ላይ ይደውሉ፡
📞 ወንድም አንዋር
0916582567
📞 ወንድም አቡ አማር
0913803997
📞 ወንድም ሰኢድ
0935568513
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM