💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.03K subscribers
1.41K photos
525 videos
128 files
5.49K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ነፍስ በ3 መንገዶች ስኬታማና፤ የጠራች ትኾናለች።

قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ۝١٤ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ۝١٥

የተጥራራ ሰው በእርግጥም ዳነ፤ የጌታውንም ስም ያወሳ፤ የሰገደም። [አል‒አዕላ (14—15)]
-

➀. እንዳትቆሺሽ ተገቢውን ክትትል በማድረግ፤

➁. የአላህን ስም ያለማቋረጥ በማውሳት እና፤
➂. ነፍስን በሶላት ጊዜ ከአላህ ጋር በማስተሳሰር።

t.me/https_Asselfya
🔖 አንድ ሰው ወደ ሀሰነል በስርይ መጣና፦ የሰኢድ አባት ሆይ ቀልቤ ደርቋል ምን ላድርግ ብሎ ስሞታ አቀረበ። እሳቸውም በዚክር ስርአት አሲዛት አሉት።

[ ذم الهوى: 69 ]
t.me/https_Asselfya
👍6
🌷 ሰው በውበቱ አይከበርምበኢማኑና በአክላቁ ነው የሚያምር።
ልብሽን በሀያእ፣ አንደበትሽን በዚክር፣ ሕይወትሽንም በሶላት አሳምሪ። 🌸

~ያኔ ሁሉም ቦታ ቦታውን ይይዛል!!

t.me/https_Asselfya
Forwarded from ስለ ስልካችን
👈 وَكُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ وَلَا تُسْرِفُوٓا۟ ۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلْمُسْرِفِينَ
ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ (አላህ ሱብሀነሁ ተአላ) አባካኞችን አይወድምና፡፡
~
🔖የጁሙዓ ቀን ሱናዎች!

①) ገላን መታጠብ
②) ሲዋክ መጠቀም
③) ጥሩ ልብስ መልበስ
④) ሱረቱል ከህፍን መቅራት
⑤) ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)
➅) በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
➆) በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት
⓼) ዱአ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት መጠባበቅ

t.me/https_Asselfya
الخطب المنبرية 5 التحذير من ذنوب الخلوات!! الأستاذ أبو مسلم عمر…
በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁሏህ)
🫵 የጁሙዓ_ኹጥባ (ምክር) - 5

•التحذير_من_ذنوب_الخلوات!!

•  
ከድብቅ_ወንጀሎች_ማስጠንቀቅ!!
   

🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Mp3
t.me/AbumuslimAlarsi/14106
       
          •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)
እህቴ ሞደልሽ ይህች ነች!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

እናታችን አዒሻ እንዲህ ነበረች፦

➩«በቤታችሁ ውስጥ ተሰተሩ(እርጉ)»የሚለውን አንቀፅ ስታነብ«መሸፋፈኛዋ» እስኪረጥብ ድረስ ታለቅስ ነበር።

رواه البخاري(4467)

فما بال نساء المسلمين
في الأسواق يزاحمن
الرجال .....
በየገበያው ውስጥ ከብዙ
ወንዶች.....ጋር #የሚጋፉት የኛዎቹ ሙስሊም ሴቶችስ..!?
👍2
ያ አሏህ!
ከቅናቻ በኋላ አታንሸራተን፡፡
ከታጠብን በኋላ አታጨቅየን፡፡
ከተነሳን በኋላ አትጣለን፡፡
ከቶበትን በኋላ አትመልሰን፡፡
ካንተ ጋር የሕይወትን ጥፍጥና
ከቀመስንና ካጣጣምን በኋላ አትጣላን፡፡
👍13
👉እናቷን እንዲህ አለቻት  እናቴ ለምን
ከቤት ስንወጣ ሽቶ ከለከልሽኝ?

🌸እናቷም፦

አበቦች ሽቶ አያስፈልጋቸውም።
🌹 በባልሽ ዘንድ ተወዳጅና የተከበርሽ ለመሆን ከፈለግሽ ⁉️

በባልሽ ዘንድ ሁልጊዜም ተወዳጅ፣ የተከበርሽና የልቡ ንግሥት ሆነሽ መኖር ትፈልጊያለሽ? እንግዲያውስ ይህንን ትልቅ የትዳር ሚስጥር በተግባር አሳይው።

🌹 ባልሽን መከባከብና እሱን ማስደሰት እንዲሁ ተራ ተግባር ሳይሆን፣ አላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝ "ዒባዳ" መሆኑን እወቂ።

🌹 ባልሽን እንደ ባል አክብሪው  አላህ ለወንዶች የሰጠውን የኃላፊነት ቦታ (ቀዋሚነት) እወቂለት። እሱን ማክበርሽ አንቺን ዝቅ አያደርግሽም፤ ይልቁንም በዓይኑ ላይ ትልቅ ያደርግሻል። አላህን በማመፅ እስካላዘዘሽ ድረስ የታዛዥነትሽን  ልብ ስጪው።

🌹 የቤትሽ "ሰከን" (መረጋገጫ) ሁኚለት ከውጭ በስራና በኑሮ ደክሞት ሲመጣ፣ ቤትሽ የሰላም ወደብ ይሁንለት። ንጭንጭንና ጭቅጭቅን አስወግጂ። በለሰለሰ ንግግርና በፈገግታ ተቀበዪው። ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት፦ "ምርጥ ሴት ማለት ስትመለከታት ደስ የምታሰኝህ ናት ብለዋልና።"

🌹 እልክና ፉክክርን ተዪ  ትዳር የሁለት ተፋቃሪዎች መርከብ እንጂ የፉክክር ሜዳ አይደለም።ከባልሽ ጋር እልህ ውስጥ አትግቢ፣ ለባልሽ ንቀት አታሳይ። ስህተቱ የሱ ቢሆንም እንኳ  በትህትናና በጥበብ ለማሳመን ሞክሪ እንጂ በባልሽ ላይ ድምፅሽን ከፍ አታድርጊ።

🌹 የትዳር ሀቁን ጠብቂለት የባልሽን ስሜት መጠበቅና በሐላል ደስተኛ እንዲሆን ማድረግ የአንቺ ትልቁ ኃላፊነት ነው። በዚህ ረገድ አትዘንጊ፣ አትለግሚ። እሱ ካንቺ ዘንድ እርካታን ካገኘ፣ ልቡ ሙሉ በሙሉ የአንቺ ይሆናል።

🌹 ቤትሽንና ራስሽን ጠብቂ፦ ቤቱን በንጽህና ያዢ፣ ለአንቺም እንዲመቸው አድርጊው። ለባልሽ በሚያምር ሁኔታ ተዘጋጂ። ይህ ማድረግሽ ለሱ ያለሽን ፍቅርና ክብር መግለጫ ነው።

🌹 ይህንን ሁሉ ስታደርጊ ለዱንያ ጥቅም ብቻ ሳይሆን የአላህን ውዴታ ፍለጋ ይሁን። "ባሌን ካስደሰትኩ አላህ ይወደኛል" ብለሽ ነይቺ። ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዲት ሴት አምስት ወቅት ሶላቷን ሰግዳ፣ የረመዳንን ወር ጾማ፣ ብልቷን ጠብቃና ባሏን ታዛ ከሞተች፤ ከፈለግሽበት የጀነት በር ግቢ ትባላለች።" (ኢማም አሕመድ ዘግበውታል)

እህቴ ሆይ! ባልሽን ለአላህ ብለሽ ካከበርሽው፣ አላህ በእሱ ልብ ውስጥ ያንቺን ፍቅርና ክብር ይዘራዋል። ትዳርሽን በኢማንና በጥሩ ስነ-ምግባር አድምቂው።

ያንችው ወንድም አቡ ሒበቲላህ
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
👍3
ukhayati-ash-shobiroh.pdf
705 KB
ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር በጠና ታማ ወደ አኺራህ ስለሔደችዉ እህታቸው የፃፏት ሪሳላህ ናት

ወደ አኺራህ የቀደሙን እህቶቻችንን አላህ በሰፊው እዝነቱ ይማራቸው

آه ما أجمل آثر الأخت على أهلها

وفقدها غصة تترك فراغاً لا يملؤه غيرها، لكن عزاء المؤمن أن الأثر الطيب لا يموت، وما زرعته من حنان وصبر ودعوات صالحات يبقى يظلها ويظل أهلها حتى يجمع الله الشمل في مستقر رحمته.
👍1
دروس وفوائد أبي حزام عبدالرحمن بن سعيد
ukhayati-ash-shobiroh.pdf
አላህ ይዘንላት፤ መልካም ስራዋን ይቀበላት፤ ማረፊያዋን ጀነተል ፊርደውስ ያድርግላት.!!
👍1
እሷም በሰራችው ትጠየቃለች አንቺም በሰራሺው ትጠየቂያለሽ 
የኒቃቢስቷ ወንጀል መስራት ያንቺን መገላለጥ ሀላል አያደርገውም!🙌

©
👍9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#الأطفال_والبراءة 🌱

قال
#السيوطي رحمه الله:

«خمس خصال في الأطفال لو كانت في الكبار مع ربِّهم لكانوا أولياء:

1⃣ لا يهتمون بالرزق
2⃣ ولا يشكون من خالقهم إذا مرضوا
3⃣ ويأكلون الطعام مجتمعين
4⃣ وإذا خافوا جرت عيونهم بالدموع
5⃣ وإذا تخاصموا تسارعوا إلى الصلح».

📚 حسن المحاضرة: 521/1.


🔖እነዚህ አምስት በህፃናት ላይ ያሉ ባህርያቶች አዋቂ  ሰዎች ከጌታቸው አላህ ጋር ቢተገብሩት ምርጥ የአላህ ወልይ (ወዳጅ) ይሆኑ ነበር።

⓵) በሪዝቅ ጉዳይ ምን እበላለሁ ምን እጠጣለሁ በሚል አይጨነቁም
(ለዱንያ ብዙም አያስቡም)

በታመሙ ጊዜም ፈጣሪያቸውን አያማርሩም
👉(አመስጋኞች ናቸው)

➂ ምግብ ሲያገኙም በጋራ ተሰብስበው ይበላሉ።
👉(ራስ ወዳድነትና ስግብግብነት የለባቸውም)

➃ በፈሩ ጊዜ አይኖቻቸው በእምባ ይሞላሉ 
👉(ልባቸው ገር እንጂ ደረቅ አይደለም)

በተጨቃጨቁ ጊዜ ወደ እርቅ ይሮጣሉ
👉(ቂም በቀል አያውቁም)

t.me/https_Asselfya
ለአንድ ጠቢብ ሰው እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ፡- "ሰው የማይቀናበት ጸጋ ታውቃለህን?"
እርሱም መለሰ፡- "ትህትና(መተናነስ)" تواضع
​እንደገናም ተጠየቀ፡- "ባለቤቱ (ተጠቂው) የማይታዘንለት መከራ ታውቃለህን?"
እርሱም መለሰ፡- "ትዕቢት (ኩራት)"
​— ፈይድ አል-ቀዲር 3 / 132


عجيب والله

نقل
👍1
« በአብዛኛው የሰው ልጅ የሚቀናው እንደ ሀብት፣ ስልጣን፣ ውበት ......ባሉ ጎልተው በሚታዩ ምድራዊ ጸጋዎች ላይ ነው። ትህትና ግን ራስን ዝቅ ማድረግን፣ ራስ ወዳድ አለመሆንን እና ሌሎችን ማክበርን የሚጠይቅ በመሆኑ፤ ለተመልካች እንደ ተፈላጊ የክብር ምልክት ሆኖ አይታይም።»

منقول
=
☀️ ኢማሙ ኢብኑል ቀዪም (ረሂመሁሏህ)
እንዲህ ብለዋል፦ “አንድ የአሏህ ባሪያ
አሏህ ዘንድ ሁለት መቆሚያ ስፍራ አለው
የመጀመሪያው፦ ለሰላት እርሱ ዘንድ 
መቆም ሲሆን...
ሁለተኛው ደግሞ፦ የቂያማ ዕለት አሏህ
 ዘንድ የሚቆመው ነው...
የመጀመሪያው ላይ በአግባቡ በመቆም 
የተወጣ ከሆነ ሁለተኛው እና ሌላኛው
የመቆሚያ ስፍራ ላይ ነገሩ ሁሉ ገር ገር
 ይሆንለታል።”

[አል ፈዋኢድ :274]
👍1
መከራ እንግዳ ነው። ከታገሱት ጥሎ ይሄዳል። ጸጋም ቢሆን እንግዳ ነው። በማመስገን ተላምዶ ይኖራል።

ኢብኑል ጀውዚይ
👍10