💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.58K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
➾ ሸይኹል ኢስላም #ኢብኑ_ተይሚይያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦
➺➾➾➾➺➾➺➾➺➾➺
(وأما اتخاذ موسم غير المواسم الشرعية، كبعض ليالي شهر ربيع الأول التي يقال: إنها ليلة المولد، أو بعض ليالي رجب، أو ثامن عشر من ذي الحجة، وأول جمعة من رجب، أو ثامن شوال الذي يسميه الجهال عيد الأبرار، فإنها من البدع التي لم يستحبها السلف، ولم يفعلها، والله سبحانه وتعالى أعلم)
«ሸሪዐዊ ያልሆኑ ክብረ በዓላትን ክብረ-በዓል አድርጎ
#መያዝ ግን ‘የመውሊድ ሌሊት’ የሚባሉትን የተወሰኑ የረቢዐል አወል #ሌሊቶችን ወይም የረጀብ ሌሊቶችን ወይም ደግሞ ዙልሒጃ አስራ ስምንትን ወይም ደግሞ የረጀብ #የመጀመሪያ ጁሙዐን ወይም ደግሞ መሃይማን ‘የደጋጎች ዒድ’ እያሉ የሚጠሩትን #ሸዋል ስምንትን የመሰሉ እነዚህ ሰለፎች እንደሚወደዱ ያልገለጿቸውና ያልተገበሯቸው #ቢድዐዎች ውስጥ ናቸው። ጥራት የተገባው #አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።»
[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 25/298]
አስተውይ እህቴ‼️
➖➖➖➖➖➖

✅ ለምን ይመስልሻል⁉️
〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ በሸሪአችን ሴት ልጅ፦
➲ነብይ ወይም ረሱል ተደርጋ ያልተላከችው
➲ቃዲ ሆና ፍርድ ሰጪ ያልተደረገችው
➲ኢማም ሆና ሰዎችን የማታሰግደው
➲ለሶላት እንድትጠራ ሙአዚን ያልተደረገችው
➲የሶላት ማእዘን የሆነውን ፋቲሀ ወንዶች ባሉበት ድምፇ ከፍ አድርጋ መቅራትን የተከለከለችው
➲ኢማሙ ቢሳሳት እንድታጨበጭብ እንጂ በድምፅ መመለስ ያልተፈቀደላት
➲በሀጅ ተልቢያ (ለበይከላሁመ ለበይክ) ስትል ድምፃ ከፍ እንዳታደርግ የታዘዘችው
➲በተከበረው ቁርአን ድምፃችሁ አታለስልሱ የተባለው
➡️ለምን ይመስልሻል⁉️

◾️መልሱ፦ የሴቶች ድምፅ ወንዶችን ስለሚፈትንና ስለሚያሳስት ነው። በዚህ ሰበብ ጥፋት ላይ ላለመውደቅ በሩን ለመዝጋት ሲባል ነው።

💢 ታዳ አላፊ አግዳሚው ባለበት፣ የሴት ልጅ አዳኝ ጠላቶች በበዙበት፣ ካፊር ፋሲቅ ሙናፊቁና የሁዳ በግልፅ በሚታይበት በየ ሚዲያው ድምፅሽን የምትለቂው፣ በቪድዮ የምትቀርቢው፣ ከወንዶች ጋር ያለሀጃ እንደፈለግሽ የምታወሪው እህቴ ሆይ ተይ ተመከሪ። ነገ አላህ ፊት ቆመሽ ከመጠየቅሽ በፊት ዛሬውን ተመለሺ። ዝናው፣ ጥቅሙ፣ ዳእዋውም፣ ለሴቶች ያለሽ ተቆርቋሪነቱም ቀርቶብሽ ባንቺ ድምፅም ሆነ በሌላ ነገር ወንዶች እንዳይፈተኑብሽ ማድረግሽ ይህ ትልቅ ጅሀድ ነው። አላህም ያዘዘሽ በዚሁ ነው። ማስተማርና መምከርም ከፈለግሽ ሴቶች ብቻ ባሉበት ወንዶች በማይገኙበት ቦታ ይሁን።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
◼️የተጅዊድ ኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖

↪️ሂዳየቱል ሙስተፊድ
👇👇👇👇👇
【ክፍል 1⃣7⃣】
〰〰〰〰〰

✅ የመድል አስልይ ማብራሪያ
✅ የመዱል ፈርእይ ክፍሎች
✅ መዱል ዋጂብ ሙተሲል


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

🔺ደርሱን ለመከታተል⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/https_Asselfya
↪️አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ - እንድህ ብላለች “የአላህ መልክተኛ የሰኞን እና የሐሙስን ጾም (ለመጾም በጉጉት) ይጠባበቁ ነበር፡፡”
📚 (ቲርሚዚይ: 745)

✅ሙእሚኖች ለመልካም ነገሮች ጉጉቱ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሰኞ እና ሐሙስን መጾም፤ በየወሩ አስራ ሶስት፣ አስራ አራት እና አስራአምስተኛው ቀን መጾም፤ ዚክር (ተስቢህ ተህሊል ተህሚድ ማብዛት) ፤ ቁርአን መቅራት ፤ በሽተኛን መጠየቅ ፤ ወደተውሂድ ጥሪ ማድረግ ፤ ሰዎችን መልካም ነገር ማስተማር፤ በመልካም ማዘዝ፤ ከመጥፎ መከልከል የዘወትር ተግባራችን ሊሆን ይገባል፡፡

🔻ሙእሚን አጋጣሚዎችን ይጠቀማል ፤ ጊዜውን ሳያባክን አላህ ለሚወደውና ወደርሱ ለሚያቃርበው ተግባር ይጠቀማል ፤ በቤቱም፤ በመንገዱም፤ በመስጅዱም ፤ በሁሉም ቦታ በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ የአላህን ሰዋብ (ምንዳ) ተስፋ ያደርጋል ፤ የአላህን ቅጣት ይፈራል፡፡

https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
◾️እውነተኛ የነብዩ ወዳጅ ቢሆኑ ኖሮ…
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ መውሊድ አክባሪዎች እውነተኛ የነብይ ወዳጆች ቢሆኑ የነገውን ቀን የአላህ መልእክተኛ ሲያደርጉት እንደነበረው ይፃሙ ነበር እንጂ በነሺዳ፣ በድቤ፣ በውዝዋዜ፣ በእርጥብ እሳት (በጫት) አያሳልፋትም ነበር። ምክንያቱም (المحب لمن يحب مطيع) (ወዳጅ ለወደደው ይታዘዛል) እንጂ አያምፅም። እነሱ ግን ነገሩ በተገላቢጦሽ አደረጉት።

ሀሳን ቢን አጥያ እንዲህ ይላል፦
(ما ابتدع قوم بدعة في دينهم إلا نزع من سنتهم مثلها)
(ሰዎች በዲናቸው ላይ ቢድአን አይፈጥሩም
የቢድአው አምሳያ የሆነ ሱና ከነሱ የተወገደ ቢሆን እንጂ።)
🔺ተመልከት የነገው ቀን ሱናው መፃም ነበር። ይህ ትተው የመውሊድ ቢድአ ሲፈጥሩ ሱና የሆነው ፃም ከነሱ ተወገደ።

አላህም በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»
(ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 31)


➡️ በዚህ የቁርአን አንቀፅ መሰረት የአላህን ውዴታና መሀርታ ለማግኘት እሳቸውን መከተል እንዳለብን ይነግረናል። ይህንን ትሩፋት ለማግኘት የተወለዱበትን ቀን አስመልክቶ የሳቸው ሱና መፃም እንጂ መውሊድ ማክበር አይደለም።

ወንድሜ መውሊድ በማክበርህ ወንጀል እንጂ ምታገኘው አንድም ትርፍ የለምና ከዚህ ቢድአ እራስህን አርቅ።

ለዚህም ነው አዩብ አሰህትያንይ እንዲህ አለ። (ما ازداد صاحب البدعة اجتهادا إلا ازداد من الله بعدا) (የቢድ ባለቤት በቢድአው ላይ ጥረት አይጨምርም ከአላህ መራቁ የጨመረ ቢሆን እንጂ)

➡️ በዚህ መሰረት አህመድ የመዲናው ወይም ሀቢቢ ሀቢቢ ወይም ነብይ ነብይ እያልክ እግርህ እስኪያብጥ ብትደንስ፣ እጅህ እስኪላጥ ብታጨበጭብና ላብ እስኪንጠባጠብህ ድረስ ብትወዛወዝ ወንጀልን እንጂ ምታገኘው አንዳች ጥቅም የለም።

ደሞ አስታውስ መውሊድ ባለማክበርህ ነገ አላህ ፊት ራሱ ብትጠየቅ በቁርአን ስላልተወሳ፣ በሀዲስ ስላልተጠቀሰ፣ ነብዩ ስላላከበሩትና ስላላዘዙት እንዲሁም ሶሀባዎች ስለማያውቁት አላከበርኩም ብለህ መመለስ ትችላለህ። ይህ ሁሉ ነገር እያወቅክና ብዙ ምክር እየሰማህ ባላየ ሆነህ በእልህ በማክበርህ ነገ አላህ ፊት ስትጠየቅ ምን ይሆን መልስህ?

አላህ ከቢድአ፣ ከሁራፋትና ከፊትናው ይጠብቅ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
القارئ إدريس أبكر | إنا أرسلنا نوحا إلى قومه
💭🌸خدمة تلاوات🎧​
▪️ቁርአን የልብ ብርሀን !
✅የዱኒያ የአሄራን ሂወት የሚያቀና ውብ የማይጠገብ የአላህ ቃል ነው።
↪️እናታችን አኢሻ በዘገበቺዉ ሓዲስ የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል ትለናለች!

- عن عائشة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم - قال : ( ركعتا الفجر خير من الدنيا وما فيها ) . رواه مسلم -
✅የፈጂር ሁለት ረካዎች ከዱኒያ እና በዉስጧ ካሉ ነገሮች ሁሉ ይበልጣሉ።

📚[[ሙስሊም ዘግቦታል]]

💦እኒህ ሁለት ረካአ የተባሉት ከፈጂር ሶላት በፊት የሚሰገዱት ሱናወች ናቸዉ።


▪️ ነብያችን ﷺ አገርም ዉስጥ ሁነዉ መንገደኛም ሁነዉ አይተዋቸዉም ነበር።
ያረቢ አገራችንን ሰላም አድርግልን
የዛሬ ቀን ረቢአል አወል 12 ነብዩ ﷺ የሞቱበት ነው። ይህን ቀን አመታዊ የደስታ ቀን አድርጎ መያዝ ሰይጣናዊ መንገድ ነው። በኢስላም የሙት አመት የሚባልም ነገርም የለም። በኢስላም የታዘዝነውን ብቻ እንስራ። ከክስረት እንጠበቃለንና። ነብዩ ﷺ "ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው" ብለዋል።
#ለጊዜ_ወሎ_እየተጠናቀቀች_ነው
~~~~~~~~~~~~~~
ኸረ ሠዎች በጣም ጠንክረን ዱዓ እናድርግ አሏህን እንለምነው
ምንም ባለወቅነው ፖለቲካ
ይሄ መፈናቀል ሀገራችንን እያዳረሳት ነው
ይሄው ወሎ ራያ ቆቦ ወልዲያ መርሳና በአካባቢያቸው የሚኖር ህዝብ ብቻ ነበር እስከ ዛሬ እየተፈናቀለ ያለው አሁን ግን በከባድ ፍጥነት ወራሪው ሀይል ውጫሌን አልፎ ወደ ሀይቅና ደሴ እየተጠጋ ነው

#በጣም_ያስፈራል!
ከዛ ኮንቦልቻ፣ኬሚሴ፣ሸዋ ሮቢት፣ደብረ ብርሀን፣አድስ አበባ
#ላኢላ_ሀ_ኢለሏህ
በተለይ ኬሚሴና መሰል ሙስሊም ሚበዛባቸው አካባቢዎች ላይ የሁለቱም ተዋጊዎች ጫና እንጃ!

✍አብዱረህማን ዑመር

https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
ሙሓደራ 119 በ ቁርዓን በ ሀዲስ አንድ መሆን ያለው ደረጃ
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ወንድማዊ ምክር ለሁሉም ሰለፍዮች
منزلة الوحدة من الكتاب والسنة
በ ቁርዓን በ ሓዲስ አንድ መሆን ያለው ደረጃ

🎙 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/UstazKedirAhmed/6315
Audio
የመውሊድ ቢድአነት በቲቪ ተጋለጠባቸው

ጋዜጠኞቹን አሳፈራቸው

ጋዜጠኛው:-በዛሬው ቀን የነብዩን የልደት በአል እያከበርን እንገኛለን

ኑር ሁሴን፦እ

ጋዜጠኛው፦ በአሉ በናንተ አካባቢ እንዴት እየተከበረ ነው እስኪ ድምፃዊ/ሙነሺድ ኑር ሁሴን ስለ መውሊድና ስለ ስራዎችህ ንገረን?

ኑር ሁሴን፦ ምን እንዳላቸው ከአንደበቱ እንስማ

በድምፅ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑት

⤾⤾⤾⤾⤾⤾⤾⤾

https://t.me/AbuSarahh/835

https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk

ሼር እናድርገው
◾️የዛሬው ቀን አመፅ
〰〰〰〰〰〰〰

✅ የመውሊድ በአል በዲን የተጨመረ መሰረት የሌለው ቢድአ መሆኑ ይታወቃል። መውሊድ ከሌሎች ስህተቶች ቢጠራ ራሱ ቢድአ ስለሆነ ወንጀል ለመሆኑ ይህ ብቻ በቂ ነው። ነገር ግን ከዚህም አልፎ ሌሎች ሙንከራቶች ሲጨመሩበት ነገሩ የበለጠ የከፋ ያደርገዋል።

በዛሬው ቀን በመውሊድ ሽፋን የሚሰሩ ወንጀሎች በጥቂቱ፦
①) የሽርክና የኩፍር ቃላቶች ማነብነብ
②) ወንድና ሴት ቅልቅል (እህቲላጥ)
③) የገንዘብ፣ የጊዜና የምግብ ብክነት
④) እንጉርጉሮ ነሺዳ፣ መንዙማና የሙዚቃ መሳሪያ
⑤) በአላህ ቤት ውስጥ ጫት መቃም
⑥) ውዝዋዜ፣ ጭፈራ፣ ጭብጨባና መውረግረግ
⑦) ነብዩ ይመጣሉ በማለት አርሂቡ እያሉ መቃዠት
⑧) ዝሙት የሚሰራበት አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው
⑨) ፎቶ ቀረፃና ሌሎችም ጥፋቶች ይገኙበታል።

➡️ በጣም የሚገርመው በመልእክተኛው፣ በሶሀባዎችና ከዛም በኋላ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የማይታወቅ አዲስ ፈጠራ መውሊድን አምጥተው ኡማውን ለሁለት ከከፈሉት በኋላ አዛኝ መስለው ተገልብጠው ይህንን መውሊድ ለሚያግዙ ሰዎች ኡማውን አትለያዩ አትከፋፍሉ ማለታቸው ነው።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
➡️ ጃቢር ኢብኑ ዓብዱላሂ ረዲየላሁ ዓንሁ ባወሩት ሀዲስ ነብዩ - ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ ብለዋል ይላል :-
" በለሊት ውስጥ ሰዓት አለች አንድ ሙስሊም የአላህ ባሪያ አግኝቷት አላህን አይጠይቅም የጠየቀውን ቢሰጠው እንጂ "
ሶሂህ ሙስሊም (757)
➳ጥሩ ሰው ከሆንሽ የምታጭው ሰው አይኖርም ነገር ግን የሚያጣሽሰው ይኖራል ሁሌም በአቋምሽ ፅኚ አትቀያየሪ

በእርጋታ በስፋት አገናዝብሽ ተረጂ እኩል አትሁኝ አይቶ ማለፊና ሰምቶ መቻል ባህሪሽ ይሆን ዝምታ አቢዢ ታማኝ ሆኚ ታማኝነት የሙዕሚን መገለጫ ነው