💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.68K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
Audio
ያረብ ..!
ሲትርህን አታንሳብኝ፣
ከዚክርህ አታዘናጋኝ፣
ከዝንጉዎችም አታድርገኝ ።

~
👍3
ይህ ተፈጥሮዬ ነውና ምንም ላደርግ አልችልም።ይህን መጥፎ ባህሪዬን ልቀየረው አልችልም ቻሉት አትበል።

ለማንም የማይበገረው አንበሳ እንኳን ቀስ
እያደረጉት አስለምደዉት ከሰው ጋ አብሮ እንዲኖር ያደርጉታል። ቁጣህን፣ ትእግስት አልባነትህን ሁሉ ካመንክበት ማስቆም ትችላለህ።
👍14
👉ቁመን እየሄድን እየበላን እየጠጣን ለዱኒያ እየተሯሯጥን ዚክርን በመርሳት አላህ ዘንድ የሞተ (የቁም እሬሳ) ልንባል በጭራሸ  አይገባም።

የአላህ መልእክተኛ እንድህ ብለዋል።

➡️ጌታውን የሚያወሳና የማያወሳ ሰው ምሳሌው በህይወት እንዳለና እንደሞተ ሰው ነው።
~
t.me/https_Asselfya
ባልን ወደ ሌላ ሴት አንድከጅል የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉ  ከነሱ መካከል:-

ለባል አለመዋዋብ፣ ባልን አለማክበር፣ ሁሌ በሆነ ባልሆነው  ሲገባ ሲወጣ መጨቃጨቅ፣ ስራ ውሎ ሲመጣ ፊትን አኮሳትሮ መጠበቅ፣ ሳይዋዋቡ መጠበቅ፣ የሚበላቸውን ምግቦች በፅዳት እና አጣፍጦ አለመስራት፣ ሁሌ አሮጌ ልብስ ለብሶ ዝርፍጥፍጥ እዳሉ ተንጨብርሮ መጠበቅ፣ የራስ ንፅህናና የቤት ንፅህን  አለመጠበቅ።

እነዚህ ነገሮች ካሉብሽ ራስሺን ፈትሺ ባልሺ ጥሎሽ ወደሌላ ሳይሄድ!?

منقول
t.me/https_Asselfya
👍11👎2
Audio
እኛ ግን ምን ጎድሎን ነው!?
🪶የ አቡ ቂላባ ድንቅ ታሪክ

«ደስተኛ ሕይዎት ለመኖር የሚያግዙ ነጥቦች»
📖الوسائل المفيدة للحياة السعيدة
ከሚለው የኪታብ ደርስ ላይ የተወሰደ ወንድም አቡ ሱፍያን―
=t.me/Sle_qelbachn1
'محمد باخطيب'
📖🕯️
▫️وَمِنَ اللَّيلِ فَتَهَجَّد بِهِ نافِلَةً لَكَ عَسى
أَن يَبعَثَكَ رَبُّكَ مَقامًا مَحمودًا
▫️
[الإسراء: ٧٩]

وقوله: ﴿ومن الليل فتهجَّدْ به﴾؛ أي:
صلِّ به في سائر أوقاته، ﴿ نافلةً
لك ﴾؛ أي :
لتكون صلاة الليل زيادةً لك في علوِّ القدر
ورفع الدرجات؛ بخلاف غيرك؛
فإنَّها تكون كفَّــــارة لسيِّئاته.
📓 تفسير السعدي


http://t.me/https_Asselfya
~ቅሯት

تعدل ثُلث القرآن
👍18
በመንገድህ ላይ ለጮኸ ውሻ ሁሉ ድንጋይ የምትወረውር ከሆነ ካሰብክበት አትደርስም። so ጉዳት የማያደርሱ ውሻዎችን ባላየ ማለፍ ይልመድብህ።

t.me/Abu_lmran_Alaseriy
👍9
ነጠላ ሰረዝ ታውቃለህ አይደል? ፅሁፍ ላይ አስፈላጊ ነው። ቃላትን ትለይበታለህ፣ ዝርዝር ሃሳብን ትጠቅስበታለህ። ነገር ግን በድምፅ አታነበውም። ትፅፈዋለህ። እናልህ፤ ህይወትህ ላይ አንዳንድ ሰዎች አሉ፤ ክፉ ደጉን ትለይባቸዋለህ። ትምህርትህ ናቸው። ግን “ምን አሉ?” ብለህ አትጮህም። “በምን አሙኝ?” ብለህ ዋይታህን አታሰማም። ይፃፋሉ፤ ግን አይነበቡም።

t.me/abdu_rheman_aman
👍15
﴿إِنَّ اللَّهَ لا يَظلِمُ النّاسَ شَيئًا وَلكِنَّ النّاسَ أَنفُسَهُم يَظلِمونَ﴾


تلاوة من سورة يونس للشيخ د. عبدالعزيز التركي | عشائيّات ربيع الأول 1447هـ
👍7
"ስትታይ በአድማሱ ላይ ያለች ኮከብ ትመስላለች… ውስጧ ግን ባዶ ነበር… ምግባር አጣሁባት… አብሮ የሚያቆየን ምንም አልነበረም።"
አለ…  መልኳን ብቻ አይቶ ካገባት በኋላ…

t.me/abdu_rheman_aman
👍6
🔖 ዝምታ  ከጥበብ ነው !!
     〰️〰️〰️〰️〰️〰️
قال لقمان: يا بني إذا افتخر الناس بحسن كلامهم فافتخر أنت بحسن صمتك.،،،،،،،،

ሉቅማነል ሀኪም ለልጁ እንዲህ ሲል መከረው።

ልጄ ሆይ❗️ሰዎች በመልካም ንግግራቸው ሲኮሩና ሲጎርሩ ፦ አንተ በመልካም ዝምታህ ኩራባቸው (ብለጣቸው)
                [كتاب روائع الحكمة/٣٤]

t.me/https_Asselfya
👍9
🔖እዚህም እዚያም እውር እንዳትሆን !

ቁርኣን ውስጥ ካሉ በጣም አስፈሪ እና አስተማር ከሆኑ አንቀጾች አንዱ የሚከተለው የሱረቱል-ኢስራእ ቁጥር 72 አንቀፅ ነው፤
{ وَمَن كَانَ فِے هَـٰذِهِۦۤ أَعۡمَىٰ فَهُوَ فِے ٱلۡـَٔاخِرَةِ أَعۡمَىٰ وَأَضَلُّ سَبِیلࣰا }
[سُورَةُ الإِسۡرَاءِ: ٧٢]
"በዚህች ዓለም ላይ ሲኖር እውነቱን ከማወቅና ከመከተል ልቡ የታወረ ሰው በመጨረሻው ዓለም (ኣኺራህ) ላይም እውር ይሆናል።
ምድር ላይ ሲኖር የሐቅን መንገድ ከሳተው ይልቅም ኣኺራህ ላይ የጀነትን መንገድ ይስታል!"
ይህ ችግር እንዳይገጥመን ዲናችንን በሚገባ መማር፣ አላህ እና መልእክተኛው የሚወዱትን አውቀን መተግበር፣ የሚጠሉትንም አውቀን መራቅ ይጠበቅብናል።
ግምባር ላይ ያለውን የዓይን ብርሃን ከማጣት ይልቅ የልብን (የዕውቀትና የኢማንን) ብርሃን የማጣት አደጋ ሊያሳስበን ይገባል።

منقول
ዘውታሪ የሆነ ሰላምና መረጋጋት ይኖራችሁ ዘንድ  ሁልጊዜም ፤ በሁሉም ሁኔታ ዉስጥ አላህን አውሱ። ሥሙን በምላሳችሁ አድርጋችሁ ዋሉ።

ደስታም ሆነ መልካም ነገር ሁሉ አላህን በማውሳት ዉስጥ ነው የሚገኘው።
👍12
እንዲህም ቤት ደስ ይለኛል! ሁለት የሚፋቀሩ ባልና ሚስት ያሉበት...ከረሂሙ ጋር ባላቸው ውብ ግንኙነት የተፋቀሩ...በዛች አራት ማዕዘን ቤታቸው ውስጥ ሌላ ትንሽ አለም የፈጠሩ...
ጥ..ል..ቅ ያለ ረጅም ወሬ...ተጨቃጭቀው እዛው ሚስማሙ...እዛው ተጣልተው እዛው የሚታረቁ...ስለነሱ ጉዳይ ማንም ሳያውቅ የሚኖሩ...ውብ የሁለት ጥንዶች ቤት...ትንሽዬ አለም! ሰሜኑን እሱ...ደቡቡን እሷ...ምስራቁን እና ምዕራቡን ፍቅርና መተሳሰባቸው የሞላው...ጥንጥዬ አለም!
t.me/abdu_rheman_aman
👍2
ልደትን ማክበር
Daru tewhid
ሰዎች ማልቀስና መጨነቅ በነበረባቸው ቀን ልደታቸው እያከበሩ እንኳን ደስ አለህ ፣እንኳን ደስ አለሽ ይባባላሉ።

🎙በኡስታዝ አቡል ዐባስ ሀፊዘሁላህ

t.me/Darutewhide
👍3
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው!
~
መውሊድ ቀደምት የኢስላም ትውልዶች ዘንድ የማይታወቅ መጤ ፈጠራ መሆኑን ራሳቸው የመውሊድ አክባሪ የሆኑ አካላት የመሰከሩትን አሳልፌያለሁ። እነዚሁ አካላት መውሊድ ከክርስቲያኖቹ ገና ተኮርጆ በፉክክር እንደሚከበር የተናገሩቱን ደግሞ እናያለን። ዘግይተው የመጡ አንዳንድ የነጋባቸው ሱፍዮች ግን “መውሊድ በሀይማኖታችን መረጃዎች መሰረት የተፈቀደ በመሆኑ ላይ ከተግባባን ከክርስቲያን ወይም ከሂንዱ እምነት ጋር ባጋጣሚ ተመሳስሎ ቢገኝ ችግር የለውም” ይላሉ። በሀይማኖታችን መሰረት ቢኖረውማ እነ ኢብኑ ሐጀር “የመውሊድ ተግባር መሰረቱ ቢድዐ ነው። በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች ከአንድም አልተላለፈም” አይሉም ነበር።

እያከበሩ ያሉት ሌላ መልክ ያለው ገና ነው፣ chrismas ማለት ልደት ማለት ነው። ልደት ማለት ደግሞ በዐረብኛው መውሊድ ማለት ነው። ስለዚህ የሚከበረው ማንነት እንጂ የተለየው የሚያከብሩት ገናን ነው። የክርስቲያኖች ገና = የሱፍዮች መውሊድ! የክርስቲያኖች መውሊድ = የሱፍዮች ገና!
እንዲያውም መውሊድን የሚያከብሩት ከክርስቲያኖች ጋር ለመፎካከር ብለው ነው። የፉክክር ዒባዳ ማለት ነው! ይህንን ሐቅ በኪታብ ሳይቀር ያሰፈሩት አሉ። መረጃ እጠቅሳለሁ፡-

1. ሰኻዊ ምን እንደሚል ተመልከቱ፡- “ባለ መስቀሎቹ (ክርስቲያኖች) የነብያቸውን ልደት ትልቁ ዒዳቸው አድርገው የሚይዙ ከሆነ ሙስሊሞችም (ነብያቸውን) በማክበርና በማላቅ ይበልጥ የተገቡ ናቸው።” [አቲብሩል መስቡክ፡ 14]

2. ከጀዘሪም ቃል በቃል ተላልፏል።

3. አቡል ዐባስ አልአዘፊ (መውሊድን ለምዕራቡ ዐረቢያ ያስተዋወቀ ነው)፡- በክርስቲያን በዓላት ላይ የሚሳተፉ ወጣቶችን ለመመለስ ሲል እንደጀመረው በግልፅ ተናግሯል።

4. ዐብዱላህ አልሀረሪ (የአሕባሾቹ መሪ):- ንጉስ ሙዞፈር መውሊድን የጀመረው ክርስቲያኖች የመሲሕ ልደትን በዓል ሲያከብሩ ተመልክቶ ነው። በዚህም ሳቢያ ሰይዳችንን ሙሐመድን ﷺ ስላወጣልን አላህን ለማመስገን ሲል መውሊድን ጀመረ ይላል። [ኢዝሃሩል ዐቂደቲ ሱኒያህ፡ 240]

ተመልከቱ እንግዲህ ! እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ አመክንዮ እየጠቀሱ የመውሊድ ቢድዐን የፈቀዱ አካላትን እየዘረዘሩ ነው በብዛት ሊያሳምኑ፣ ራሳቸውን ሸውደው ሌሎችን ሊሸውዱ የሚነሱት። ለማንኛውም የመውሊድ ቢድዐን በፉክክር የተለከፉ ሰዎች የፈጠሩት መጤ ፈሊጥ ነው። በዚህ መልኩ በሌሎች መመሳሰል የተወገዘ እንደሆነ ነብያችን ﷺ አጥብቀው አሳስበው ነበር።

* ማስረጃ አንድ፦

مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
"አንድን ሕዝብ የተመሳሰለ (የተከተለ) ከእነርሱ ነው (እንደነርሱ ይቆጠራል)።" [አቡ ዳውድ ፡ 4031]

* ማስረጃ ሁለት፦

በሌላም ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

لتتَّبعنَّ سَننَ من كانَ قبلَكم حذو القُذَّةِ بالقُذَّةِ حتَّى لو دخلوا جحرَ ضبٍّ لدخلتُموه. قالوا: اليَهودُ والنَّصارى؟ قالَ: فمَن

“በርግጥ ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የወከሎ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቢጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!” አሉ። [ቡኻሪ፡ 7320]

የተናገሩት በትክክል ተፈፀመ። ለብዙ ጥፋቶች የሚያጋልጠው በዓል ከክርስቲያኖች ተኮርጆ በ"ፋጢሚያ" ሺዐዎች ተጠንስሶ፣ በሱፍዮች ተዛምቶ ብዙ ሙስሊም ሊዘፈቅበት በቅቷል።

የሚያሳፍረው “ክርስቲያኖቹ የነብያቸውን ልደት እያከበሩ የኛ ነብይ ከማን ያንሳሉ?” የሚሉት ነገር ነው። ሱብሓነላህ! ለመሆኑ ዒሳ የኢስላም ነብይ አይደሉም እንዴ?! ታዲያ ይሄ ምን የሚሉት አፀያፊ ሎጂክ ነው? ደግሞ ምንም ሳያፍሩ መውሊድን የሚቃወሙ ሙስሊሞችን “የነቢ ጠላቶች ናቸው!” እያሉ ከባድ ክስ ይከሳሉ። የነብዩን ﷺ መውሊድ አለማክበር እሳቸውን መጥላት ከሆነ እናንተም የክርስቲያኖቹን ገና (chrismasን) ባለማክበራችሁ የዒሳ ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። መውሊድን ማክበር ነብዩን ﷺ ማክበር ከሆነ የሌሎቹን ነብያት ልደቶች ስለማታከብሩ ለሌሎች ነብያት በሙሉ ክብር የሌላችሁ የነብያት ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። ከአንደበታችሁ በቀጥታ ባይወጣም አመክኗችሁ የሚሰጠው ይህንን ነው።

ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
👍5