💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.58K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
◼️በሁሉ ነገርህ ላይ ታጋሽ ሁን‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

💦ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ አብዘሀኛው በሰውነታችንም ሆነ በቀልባችን ላይ ለሚገኙ አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ በሽታዎች የመፈጠር ሰበብ ትእግስት (ሶብር) ማጣት ነው።

📜زاد الـمعاد ٣٠٦/٤
https://t.me/https_Asselfya
حلقة القرءان في مدرسة مركز ابن عباس
Super Effect Edited
ይደመጥ እንዳይታለፍ

በመርከዝ ኢብኑ ዐባስ ውስጥ ለቁርአን ማስተካከያ ከሚሰጠው የሀለቃ ቂርአት የተወሰደ
https://t.me/https_Asselfya
27 ኢና ኩና ፊ ጃሂሊያ ሊሸይኽ ሷሊሕ አል—ፈውዛን
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖

↪️ኢና ኩና ፊ ጃሒሊያ

↪️ አዘጋጅ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን

◾️ክፍል 2⃣6⃣
〰〰〰〰〰

🎙 በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)

ደርሱን ለማግኘት⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
መውሊድ፣ ሙስሊሞች የዘነጉት ግና ጠላት የተረዳው አደጋ!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መውሊድ ውስጥ ከኢስላማዊው አስተምህሮት ያፈነገጡ የባእድ አምልኮቶች፣ ጭፈራዎችና አይነታቸው የበዛ ጥፋቶች አሉ፡፡ እነዚህ አፈንጋጭ ምግባሮችና ገፅታዎች በኢስላም ስም እየታሰቡ ይቀጥሉ ዘንድ ከፍ ያለ ፍላጎት ያላቸው ከሃዲዎች በተለያዩ ጊዜያት ለዚህ መጤ በዓል ድጋፋቸውን ሲሰጡ፣ የጥፋት ቦታዎችን ሲያንፁና መሰረተ - ልማት ሲዘረጉ ያጋጥማሉ፡፡ በሃገራችን እንደ አናጂና ያሉ የሺርክ ቦታዎችን የአሜሪካ ኤምባሲና ሌሎችም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ እንደነበር የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ በርግጠኝነት እነዚህ አካላት ለኢስላም ተቆርቁረው እንዳልሆነ ወዳጅ ቀርቶ ጠላትም አይዘነጋውም፡፡ እስራኤላዊው የቴልአቪቭ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሃጋይ ኢርሊች ለኢትዮጵያ የሚበጀው እስልምና አሕባሽ ነው እንዳለ የምናስታውስ ይመስለኛል፡፡ አላማቸው ከኢስላም ስሙን ብቻ የተሸከመ፣ ከቁርኣንና ከሐዲሥ በብዙ ርእሰ ጉዳዮች የተኳረፈ፣ በሃገር በቀል እንቶ ፈንቶዎች የተተበተበ፣ በህዝበ ሙስሊሙ መሀል የሚገኙ የባእድ አምልኮቶችን ለመጋፈጥ ወኔ የሌለው የላሸቀ “እስልምና”ን መጠበቅ ነው፡፡

ግብፃዊው የታሪክ ፀሐፊ አልጀበርቲ የፈረንሳዩ መሪ ናፖሊዎን ቦናፓርቴ ግብፅን በተቆጣጠረ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሲተርኩ የ 1213 ሂ. ክስተትን እንዲህ ይገልፁታል፡- የጦሩ አዛዥ የነብዩን ﷺ መውሊድ እንደልማዳቸው ለምን እንዳላከናወኑ ጠየቀ፡፡ ሁኔታዎች እንደቆሙ፣ ነገሮች እንደተራቆቱ፣ ለተለያዩ ወጪዎች የሚውል ገንዘብ እንደሌለም ሸይኽ በክሪ ተናገሩ፡፡ ናፖሊዎን “የግድ መዘጋጀት አለበት” በማለት ለዚሁ ተግባር ይታገዙበት ዘንድ ለሸይኽ በክሪ 300 የፈረንሳይ ገንዘብ ሰጠ፡፡ ከዚህ በኋላ ሻማዎችና ችቦዎች ተለኮሱ፡፡ ፈረንሳውያኑም ለመውሊድ ተሰባሰቡ፡፡ ከበሮዎቻቸውን እየመቱ ጨፈሩ፡፡ ትልልቅ ከበሮዎችና የተለያዩ ድምፆችን የሚሰጡ የሙዚቃ መሳሪያዎች ወደ ሸይኽ በክሪ ቤትም ተልከው ሌት ከ ተቀን ተደለቀ፡፡ ሌሊቱን ጧፍ ሲቀጣጠልና ርችቶች ወደ ሰማይ ሲተኮሱ አደረ፡፡ [መዝሀሩ ተቅዲስ፡ 47]

ጄ ክርስቶፎር ሄሮልድም እንዲህ በማለት ተመሳሳይ ታሪክ ያወሳል፡-

“የካይሮ ታዋቂ ሰዎች በዓሉን የሚያከብሩ አይመስሉም፡፡ ስለሆነም ናፖሊዎን ቦታውንም በጀቱንም በመፍቀድ አበረታታቸው፡፡ ካይሮ በዓሉን ለሶስት ቀናት አከበረች፡፡ ሱፊዮች በድካም እስከሚወድቁ ድረስ በጎዳናዎች ወጥተው ደነሱ፡፡ የፈረንሳይ ወታደሮችም የሙዚቃ ትርኢት አሳዩ፡፡ እሳት አቀጣጠሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦናፓርቴ የሸይኽ በክሪ እንግዳ ነበር፡፡ እስከ አንገቱ በተቆለፈው ጥቁር የደንብ ልብሱ የበዓል ገመዶችንና ጥምጣሞችን አድርገው የቁርኣን አንቀፆችን ከሚያነበንቡና ዶቃቸውን ከሚስቡ ሸይኾች ጋር ልዩ ገፅታ ነበረው፡፡” [Herold, J. C. Bonaparete in Egypt, published in 1962]

ምናልባት “እንዲህ አይነቱን የቢድዐ ድግስ በመደገፍ ፈረንሳውያኑ ምን ያተርፋሉ?” የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ የመውሊድ ደጋፊዎች “ጠላት ከህዝብ ልብ ውስጥ ለመግባት ያደረገው ነው፡፡ ልክ ሌሎች ዲናዊ ጉዳዮችን ለመፈፀም ጠላት ቢያግዘን እነዚያን ጉዳዮች በክፉ ልንመለከት ነው ወይ?” እንደሚሉ ይጠበቃል፡፡ እውነት መውሊድ በዚህ መልኩ የሚታይ ነው? መልሱን በወቅቱ ለነበሩት የታሪክ ፀሐፊው አልጀበርቲ እንለቀቅ፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፡-

“ፈረንሳውያኑ ይህን ለሰዎች የፈቀዱበት ምክንያት በውስጡ ከሸሪዐዊ አስተምህሮቶች ማፈንገጥ፣ የሴቶች መሰባሰብ፣ ስሜቶችን መከተል፣ አጉል ዛዛታና ሐራም የሆኑ ድርጊቶች ስላሉበት ነው፡፡” [ዐጃኢቡል ኣሣር፡ 2/306]

ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
Audio
✅ የመውሊድ ደጋፊዎች ሹቡሀ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ማምታቻ 8⃣
〰〰〰〰〰

➲የቁርአን አንድ ላይ መሰብሰብ
➲የሀዲስ መዘገብና ሌሎችም

🔻የቁርአን መሰብሰብ ለመውሊድ በጭራሽ መረጃ አይሆንም!!

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
حلقة القرءان في مدرسة مركز ابن عباس (②) Trim
Super Effect Edited
②
ይደመጥ እንዳይታለፍ

በመርከዝ ኢብኑ ዐባስ ውስጥ ከሚሰጠው የሀለቃ ቂርአት የተወሰደ

ከትላንቱ የቀጠለ

👉 ረጋ ያለ ቂርአት
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
[] የመልካም ሴት ባህሪያት [] ክፍል አንድ
[] مركز أبي موسى الأشعري []
🌾ክፍል አንድ🌾

✴️[] አዲስ እና ተከታታይ ትምህርት ለሴቶች []

🌟 የመልካም ሴትን ባህሪያት የምትገልፅ ልዩ ግጥም!🌟

⭐️ የግጠሟ ስም: " الجوهرة المكنونة للدرة المصونة "

✒️✒️ አዘጋጅ: ሸይኽ ዐሊይ ኢብኑ የሕያ አል-ሐዳዲ

🕰 የትምህርቱ ቀን እና ሰአት:
ዘውትር ረቡዕ እና ቅዳሚ ከመግሪብ ሰላት በሇላ

🖱የትምህርቱ አድራሻ: በ Voice Chat
🌾መርከዝ አቡ ሙሳ አልአ-ሽዐሪ Online የቁርአን ሒፍዝ ማእከል🌾 ።
https://t.me/kurantejwid

🎙የትምህርቱ አቅራቢ:
አቡል ዐባስ ናስር ሙሐመድ
PDF ለማግኘት
https://t.me/https_Asselfya/1094
ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን አሏህ ይጠብቃቸው እንዲህ አሉ፡–
መልካም የሆነች ሴት ልጅ ከአንድ ሽ ወንድ ልጅ ትበልጣለች።
28 ኢና ኩና ፊ ጃሂሊያ ሊሸይኽ ሷሊሕ አል—ፈውዛን
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖

↪️ኢና ኩና ፊ ጃሒሊያ

↪️ አዘጋጅ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን

◾️ክፍል 2⃣8⃣
〰〰〰〰〰

🎙 በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
🍃 ወንድን ልጅ የምትገጥመውን መልካም ሴት ከማግኘት በላይ #የሚያረጋጋው(የሚያረካው) ምንም ነገር የለም…
………………
🍃 ቀጣዩ የአሏህ ቃል ማስረጃ ይሆነናል
……………………………………………
{وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ}

{ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡}
🍃🍃🍃 ሩም 21🍃🍃🍃

👇 ሊንኩን ሼር ያርጉ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
✅☆ ትክክለኛው የህሊና እርፍት የሚኖረው
በሁሉም ነገር ላይ አልሀምዱ ሊላህ
ማለትን ስታበዛ ነው❗️

💦⇨እራስህን በዱንያ አታጨናንቅ
ሁሉም ነገር የተፃፈ ነው ታገኘዋለህ ።

🎓 በክር ኢብኑ ዓብዲላሂ የተባለ ሊቅ እንዲህ ይላል :-
〰〰〰〰〰〰〰〰
" አንድ የአላህ ባሪያ አንድ ጊዜአልሀምዱ ሊላህ አይልም ለሱ የአላህ ኒዕማ ዋጂብ ብትሆን እንጂ

▪️የዚህ ኒዕማ ዋጋ ምንድነው ?
👉ዋጋው አሁንም አልሀምዱ ሊላህ ማለት ነው ።
👉ሌላ ኒዕማ መጣ
እንደዚሁ የአላህ ኒዕማ አያልቅም
"
አሽሹክር ሊብኒ አቢዱንያ ( 14 )
"ዒልም ካለ……… መግባባት አለ።
"ዒማን ካለ……… አማና አለ።
"ዒኽላስ ካለ……… መተናነስ አለ።
"ዒሕሳን ካለ……… ትህትና አለ።
"ተወኩል ካለ……… ስኬት አለ።
"ተቅዋ ካለ………… ታማኝነት አለ።

"አላህ ይወፍቀን ያረብ
29 ኢና ኩና ፊ ጃሂሊያ ሊሸይኽ ሷሊሕ አል—ፈውዛን
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖

↪️ኢና ኩና ፊ ጃሒሊያ

↪️ አዘጋጅ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን

◾️ክፍል 2⃣9⃣
〰〰〰〰〰

🎙 በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
👍1