💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.73K subscribers
1.27K photos
494 videos
123 files
5.14K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
إنَّ أَساسَ الصَّلاحِ فِي المَرأةِ َلاحُها_مَعَ_ربِّها، بِحُسنِ طَاعتِه، وحُسنِ التَّقرُّب إليهِ، وَالمُواظبَة علَى عِبادَتِه، فإنَّ هَذا الصَّلاح وتِلكَ الاستِقامَة هيَ سِرُّ سَعادتِها، وَسِرُّ فَلاحِها، وسِر تَوفِيقِها فِي حَياتِها ڪلِّها بِما فِي ذلِك حيَاتها الزَّوجِيَّة، وصَلاح أوْلادِها، وذُرِّيَّتِها، وَعيشِها العَيشَ المُبارك الهَنيءَ".

ِفَاتُ_الزَّوجَة_الصَّالِحَة
ِلشَّيْخِ_عَـبْدِ_الـرَّزَّاقِ_البَـدْرِ حفظه الله (ص ١١)
ለፊታችሁ ውበት …!
~
የሰው ልጅ ፊት የልቡ መስታወት፣ የውስጡ ማንነት ነፀብራቅ ነው፡፡ ውበቱ በቅንድብና በአይን ጥራት፣ በአፍንጫ ቅጥነትና በከንፈር ቅርፅ ብቻ የሚለካ አይደለም፡፡ እውነተኛው ውበት ከነፍስ ጥልቀት የሚመነጭና በገፅ ላይ የሚፈነጥቅ ሰማያዊ ብርሃን ነው፡፡ ይህ ብርሃን የኢማን ነፀብራቅ ሲሆን ጥቁረቱ ደግሞ የወንጀል ጥላ ነው።

ሰው ከሰው ከአይኖች ተሰውሮ፣ በድብቅና በስውር አላህን ሲያምፅ፣ የወንጀሉ አስከፊነት በቅድሚያ የሚታተመው በፊቱ ላይ ነው፡፡ ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዳሉት፣ ኃጢአት በተለይም በድብቅ የሚፈጸም ሲሆን፣ ፊት ላይ ጨለማን ያሰፍናል። ይህ ጨለማ በአይን የሚታይ አካላዊ ጥቁረት ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን የፊትን ገፅታ ያበላሻል፣ ውበትንና ሞገስን ይገፋል፡፡ ወንጀለኛ ሰው ምንም ያህል አካላዊ ውበት ቢኖረው፣ በፊቱ ላይ የሚነበብ አንድ ዓይነት ጭጋግና አስፈሪነት አለ፡፡ ይህንን የውስጣዊ ማንነት ጥቁረት አማኝ የሆነ ሰው ልቡ ሊረዳውና ሊገነዘበው ይችላል።
ኃጢአት የልብን ብርሃን እንደሚያጠፋ እሳት ነው፡፡ ልብ በጨለመ ቁጥር፣ የፊት ገፅታም ያንን ተከትሎ ይጠቁራል፣ ይከብዳል፣ ማራኪነቱን ያጣል፡፡ የአላህን ትእዛዝ በድብቅ መጣስ፣ ልክ ንፁህ ልብ ላይ ጥቁር ነጥብ እንደመጣል ነው፡፡ ወንጀሎች ሲደጋገሙ፣ ነጥቦቹ እየበዙ ልብን ሙሉ በሙሉ ይሸፍኑታል፤ ያኔ የፊትም ብርሃን ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል፡፡

በአንፃሩ ለአላህ የሚደረግ አምልኮ በተለይም በለሊት ተነስቶ መስገድ፣ ዚክር ማብዛትና ቁርአን መቅራት የፊት ብርሃንና ውበት ምንጭ ነው፡፡ መልካም ስራና የአላህ ፍራቻ በሰው ልጅ ፊት ላይ ብርሃንን፣ በልብ ውስጥ ኑርን፣ ሪዝቅ ውስጥ ስፋትንና በሰዎች ልብ ውስጥ ውዴታን ይፈጥራል፡፡ኢባዳ የነፍስ ምግብና የልብ ማፅጃ ነው፡፡ ልብ በኢባዳ በጠራና በደመቀ ቁጥር፣ ፊታችን ላይ የሚፈነጥቀው ብርሃን ይጨምራል፡፡ ይህ ብርሃን ሰዎችን የሚስብ፣ መተማመንን የሚፈጥርና ለመልካም ነገር የሚገፋፋ ሰማያዊ ሀይል አለው፡፡ የአላህ ባሪያ በሱጁድ፣ በዱዓና እርሱን በማስታወስ በሚያሳልፋቸው ጊዜያት፣ የአላህ ኑር  ፊቱን ይሸፍነዋል፡፡ ይህ ውበት ጊዜ የማይሽረው፣ በእርጅና የማይደበዝዝ፣ ከሞት በኋላም በቀብርና በቂያማ ቀን የሚከተል ዘላለማዊ ድምቀት ነው።

•ስለዚህ እውነተኛውንና ዘላቂውን ውበት የምንሻ ከሆነ፣ የፊታችንን ሳይሆን የልባችንን ንፅህና እንጠብቅ፡፡ የድብቅ ወንጀልን ጨለማ በማስወገድና በኢባዳ ብርሃን በመተካት፣ ፊታችን በዱንያም በአኼራም እንዲያበራ እናድርግ፡፡ የሰው ልጅ ፊት የውስጡ መስታወት መሆኑን አንዘንጋ፤ ውስጣችንን በአላህ ፍቅርና ፍራቻ እናሳምር፣ ያኔ ውጫዊ ገፅታችን በሰማያዊ ብርሃን ያጌጣል።

🔖ስለ ቀልባችን-
|•|
t.me/Sle_qelbachn1
👍1
ሱረቱል ቂያማህ
<unknown>
ሶደቀቱን ጃሪየህ

ቅዝቃዜውን በቲላዋ ...
👍2
"ወንድሜ"

«ላታገባት ባዶ ተስፋ አትስጣት
«ላታገባት አለሁሽ አትበላት
«ላታገባት አትዋሻት
«ላታገባት እንደ ምርጫ አትጠቀማት

እህት አለህ አይደል በእህትህ ላይ እንደርስ የማትፈልገውን አንተ በሰው እህት ላይ አታድርስ

«ላታገባት አትዋሻት  የቃላት ድርደራ በመሀላ ብዛት አታሳምናት አላህን ፍራ ውሸት አኗኗርን ቀርቶ አሟሟትን ያበላሻል እባክህ ወንድሜ በሴት ልጅ እድሜ አትጫዎት ነገ ሴት ልጅ ትወልዳለህ በቃ እውነቱን ንገራት አማራጭ አታድርጋት እባክህ አላህን አፍራ !! ነገ አላህ ፊት እራቁት መቅረብ አለና አስተውል በቃ አትዋሽ !

منقول
=
t.me/https_Asselefya1
👍13
እየተስተዋለ!
~
ላይክ አጅርም ወንጀልም ይኖርበታል። የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችንን እያስተዋልን። ወንጀልን፣ ጥፋትን ፣ ክፋትን በላይክ፣ በኮመንት መደገፍና ማሰራጨት በስራ መዝገባችን ላይ ወንጀል ማስመዝገብ ነው። ጥፋት በማስራጨት፣ ዲንን በመጉዳት፣ ሹቡሃ በመንዛት፣ አጥፊዎችን በማስተዋወቅ ላይ የተሰማሩ አካላትን ፎሎው፣ ላይክ፣ ሰብስክራይብ፣ ጆይን፣ ... ማድረግ ለጥፋታቸው እገዛ መስጠት ነው። ስለዚህ ከንዲህ አይነት ገፆች ወይም አካላት ዛሬ ነገ ሳንል በጊዜ እንራቅ።

በሌላ በኩል የዲንም ይሁን የዱንያ ጠቃሚ ትምህርቶችን ስናገኝ በላይክ፣ በኮመንት፣ በማሰራጨት እናግዝ። ይህንን ማድረግ አጅር እንዳለው አይረሳ። ሶደቃ መልኩ ብዙ ነው። ላይክና ሼር ምን ያህል ነው ወጪው? አምስት ሳንቲም ላናወጣበት አጉል እንሰስታለንዴ? ብንሰስት እኛው ነን የሚቀርብን። ኸይር በማሰራጨትና በመደገፍ የሚገኘው አጅር ነው የሚያልፈን። ስለዚህ በምንገኝባቸው ፕላትፎርሞች ሁሉ ወገናቸውን ለመጥቀም ደፋ ቀና እያሉ ያሉ አካላትን ስራቸውን እንደግፍ። እዚህ ግባ የሚባል ቁም ነገር የሌላቸው እንቶ ፈንቶዎች በሺ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ላይክና ቪው እያገኙ የቁም ነገር ስራዎች የተመልካች ድርቅ ሲመታቸው ማየት አሳፋሪ ነው።

ብቻ ለራሳችን ለነጋችን ስንል እንወቅበት። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል :-

{ فَمَن یَعۡمَلۡ مِثۡقَالَ ذَرَّةٍ خَیۡرࣰا یَرَهُۥ (7) وَمَن یَعۡمَلۡ مِثۡقَالَ ذَرَّةࣲ شَرࣰّا یَرَهُۥ (8) }
"የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል። የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል።" [አዘልዘለህ: 7-8]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
👍4
🔖ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብን።
             ➀) ሆስፒታል
             ⓶) እስር ቤት
             ⓷) መቃበር

➡️በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ የሚበልጥ የተሻለ ምንም ነገር እንደሌለ እንረዳለን።

➡️በእስር ቤት ለሰው ልጅ ነፃነት በጣም ውድ እና አስፈላጊ ነገር እንደሆነ እናውቃለን።

➡️ በመቃብር ውስጥ ምድራዊ ህይወት የምንኮራበት ስጋ፣አቋም፣መልክ፣ደም ግባትና ሀብት ንብረት ምንም ዋጋ እንደሌለው እንለያለን።

ዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው።የዛሬ ድርጊታችን የነገ ውጤት ነው። ስለዚህ በተሰጠንና ባለን የምንደሰት፣ቅን፣ሩህሩህ፣ትሁት እና አመስጋኝ እንሁን።ጌታችን አስተዋይ ልቦና ያድለን።

t.me/https_Asselfya
👍13
Audio
تلاوة جدًا رائعة ، اللهمَّ بارك..
👍3
سُبحانك اللهمّ وبحمدك، أشهدُ أن لاَ إله إلاّ أنتَ، أستغفرك وأتوبُ إليكَ.
الوصية بالنساء خيرا / قصة شاب مع الشيخ ابن باز رحمه الله / يحكيها…
دعوة التوحيد والسنة
- يا إبني الدنيا ما فيها حور عين.

- قصة أحب أن احكيها عن الشيخ ابن باز رحمه الله.

-🎙 الشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله.
ተቅዋ
«አቡ ሑረይራ Online የቂራአት መድረሳ»
🔖አድስ ሙሐደራ   

ቁጥር ⓵〗

📋ርዕስ አሏህን መፍራት ❴ተቅዋ
ሌሎች ነጥቦችም ተዳሰውበታል ...¡¡


🎙በወንዲም አቡ ሱፍያን

http://t.me/abuhureyrahmedresa
👍2
የማታ ዚክር አትርሱ

~ዚክር የልብ ሀይል የአካል ብርታትና የትኛውንም ጣዕም የማይስተካከለው የቀልብ ምግብ ነው።

=
t.me/https_Asselfya
🔖ሸቂቅ አልቡልሂ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

~ የሚደርስበትን ሙሲባ ከአላህ ዉጪ ላለ አካል አቤት የሚልና ስሞታ የሚያቀርብ ሰው የመልካም ስራ ጥፍጥና አያገኝም።
📚 سير أعلام النبلاء315/9

t.me/https_Asselfya
👍3
በአካልም ይሁን በማህበራዊ መገናኛዎች ጓደኞቻችንን መምረጥና መለየት ይገባል። በጓደኛ ሰበብ የተጠቀመ፣ የተለወጠ እንዳለ ሁሉ፤ በጓደኛ ሰበብ መንገድ የሳተ፣ በጓደኛ የልብ ድርቀት የተጋባበት ፣ በጓደኛ ከኸይር የራቀ፣ ጥፋት የተላመደ፣ ሐያኡን ያጣ ፣ ... ብዙ አለ።
ስለዚህ ራሳችንንም ልጆቻችንንም ከመጥፎ ጓደኝነት እንጠብቅ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
كَيْفَ يَكُونُ اَلْمَالُ وَالْكَسْبُ اَلْحَرَامُ سَبَبًا فِي عَدَمِ اِسْتِجَابَةِ دُعَاءِ اَلْمُضْطَرِّ وَهُوَ فِي أَمَسِ اَلْحَاجَةِ إِلَيْهِ...؟

~
t.me/https_Asselfya
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፈገግታ ሱና ነው ፈገግ እያላቹህ። በዚያውም ወንዶችየ  ትምህርት ውሰዱ።

~
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልባችሁ ንፁህ ሆና በነበር የጌታችሁን ንግግር «ቁርአንን» ቀርታችሁ ባልጠገባችሁት ነበር።

ዑስማን ኢብኑ ዓፋን

وكيف يشبع المحب من كلام محبوبه، وهو غاية مطلوبه!

t.me/https_Asselfya
👍8