💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.58K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ㅤ🍃💐🍃_ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ 👒

🍃🌹 تَدبَّر سُورَة الكَهف 🌹🍃

{ وَلْيَتَلَطَّفْ وَلَا يُشْعِرَنَّ بِكُمْ أَحَدًا }.

በህይወት ውስጥ ያለው ችግር ምንም ያህል እየከበደ ቢሄድም በርጋት በመልካም ተስፋ ለማሸነፍ ሞክሩ!

አስሀቡል ካህፍ በችግሮቻቸው መረጋጋታቸው ለችግሮቻቸው መፍትሄ አልተቸገሩም!

አላህ ለእነሱም ሁሉን አገራላቸው! 🍃

#አላህ ሆይ ቁርዐንን በመረዳት
ላይ አበርታን💎

👒_ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ 👒👒
خُلِقَ الْإِنسَانُ مِنْ عَجَلٍ ۚ سَأُرِيكُمْ آيَاتِي فَلَا تَسْتَعْجِلُونِ

(ሱረቱ አል-አንቢያ - 37)
ሰው ቸኳይ ሆኖ ተፈጠረ፡፡ ተዓምራቶቼን በእርግጥ አሳያችኋለሁና አታቻኩሉኝ፡፡
#የሰለፎች ኢኽላስ

አዩብ አስሰኽቲያኒ ረሒመሁሏህ
ለሊቱን ሙሉ በኢባዳ ቆመው ሲያበቁ ይህንንም ተግባራቸው ከሰዎች ይደብቁ ነበር።
የሱብሂ ጎህ ሲቀድ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ
ገና በዛች ሰአት ከእንቅልፋቸው እንደተነሱ
ያስመስሉ ነበር!።
ሴት አሰጋጅ ስትሆን የት ነው የምትቆመው?
-----------------------------------------------
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላል፡-
“ሴቶች በህብረት ከሰገዱ አሰጋጃቸው መሀላቸው ትቆማለች፡፡ ይሄ ይበልጥ ሰታሪ ነውና፡፡ ለሴት ልጅ በተቻለ መጠን መስሰተር ነው የሚፈለገው፡፡ እንደሚታወቀው አንዲት ሴትከፊታቸው ከሴቶች ፊት ከምትቆም ይልቅ ከመሃላቸው መቆሟ ይበልጥ ሰተር ያደርጋታል፡፡ ለዚህ ማስረጃው ከዓኢሻና ከኡሙ ሰለማ ረዲየላሁ ዐንሁማ ሴቶችን ሲያሰግዱ በሶፋቸው ውስጥ ሆነው ያሰግዱ እንደነበር የተወራው ነው፡፡ ይሄ የሶሐብያ ድርጊት ነው፡፡ እዚህ ላይ ትክክለኛው እይታ (የሶሐባ ንግግር/ ድርጊት) ቁርኣን ወይም ሐዲሥ እስካልተፃረረ ድረስ ማስረጃ ይሆናል የሚለው ነው፡፡
አንዲት ሴት ከአንዲት ሴት ጋር ከሆነች ልክ አንድ ወንድ ከአንድ ወንድ ጋር እንደሚቆመው ትቆማለች፡፡” [አሽሸርሑል ሙምቲዕ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፡ 4/387]

https://t.me/https_Asselfya
ምድር ክብ ናት? ወይስ
AudioTrim
ምድር ክብ ናት ወይስ ጠፍጣፋ?
〰〰〰〰〰〰〰

ከሱረቱ ናዚዐት والأرض بعد ذالك دحها ከሚለው አያ ተፍሲር የተብራራ

🎙በኡስታዝ ሲራጅ ንጋቱ
https://t.me/https_Asselfya
👉ሸይጧን ሁለቴ እንዲያሸንፍህ

አትፍቀድለት

① ወንጀል አሰርቶህ እንደገና

② ከአላህ እዝነትና ምህረት
ተስፋ እንዳያስቆርጥህ ።

https://t.me/menhajselefiya123
Audio
🔻በሁለት ቅንድብ መካከል ያለን ፀጉር ማንሳት በተመለከተ
ሳሊህ የሆነ የዲን ወንድም ከነፍስህ ይበልጣል ምክኒያቱም ነፍስህ በመጥፎ አዛዥ ናት ሳሊህ ወንድም ግን በመልካም እንጂ በሌላ አያዝህም

(ኢብኑ አልቀይም ረሂመሁሏህ)
💦ሸኽ አልባንይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

✅ ባልና ሚስት በፊቅህ ጉዳይ ላይ ከተለያዩና ካልተግባቡ (የተለያየ አቋም ከያዙ) ወንዶች በሴቶች ላይ የበላይ ናቸውና የሷን አቋም ትታ ልትታዘዘው ይገባል።
🎙فتاوى جدة 25
◾️ነገር ግን
👉አብዘሀኛው የዘመናችን የባልና ሚስት ጭቅጭቅና ንትርክ በዲን (በፊቅህ) ጉዳይ ሳይሆን ተራ በሆነ በዱንያ ጉዳይ ነው።
ቁርኣን ተፍሲር
―――――
ሡረቱ ጦሀ
#ክፍል 6_8

🎤በሸይኽ አወል ቢን አሕመድ አል_ኬሚሴ
https://t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed
◼️በሁሉ ነገርህ ላይ ታጋሽ ሁን‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

💦ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ አብዘሀኛው በሰውነታችንም ሆነ በቀልባችን ላይ ለሚገኙ አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ በሽታዎች የመፈጠር ሰበብ ትእግስት (ሶብር) ማጣት ነው።

📜زاد الـمعاد ٣٠٦/٤
https://t.me/https_Asselfya
حلقة القرءان في مدرسة مركز ابن عباس
Super Effect Edited
ይደመጥ እንዳይታለፍ

በመርከዝ ኢብኑ ዐባስ ውስጥ ለቁርአን ማስተካከያ ከሚሰጠው የሀለቃ ቂርአት የተወሰደ
https://t.me/https_Asselfya
27 ኢና ኩና ፊ ጃሂሊያ ሊሸይኽ ሷሊሕ አል—ፈውዛን
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖

↪️ኢና ኩና ፊ ጃሒሊያ

↪️ አዘጋጅ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን

◾️ክፍል 2⃣6⃣
〰〰〰〰〰

🎙 በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)

ደርሱን ለማግኘት⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
መውሊድ፣ ሙስሊሞች የዘነጉት ግና ጠላት የተረዳው አደጋ!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መውሊድ ውስጥ ከኢስላማዊው አስተምህሮት ያፈነገጡ የባእድ አምልኮቶች፣ ጭፈራዎችና አይነታቸው የበዛ ጥፋቶች አሉ፡፡ እነዚህ አፈንጋጭ ምግባሮችና ገፅታዎች በኢስላም ስም እየታሰቡ ይቀጥሉ ዘንድ ከፍ ያለ ፍላጎት ያላቸው ከሃዲዎች በተለያዩ ጊዜያት ለዚህ መጤ በዓል ድጋፋቸውን ሲሰጡ፣ የጥፋት ቦታዎችን ሲያንፁና መሰረተ - ልማት ሲዘረጉ ያጋጥማሉ፡፡ በሃገራችን እንደ አናጂና ያሉ የሺርክ ቦታዎችን የአሜሪካ ኤምባሲና ሌሎችም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ እንደነበር የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ በርግጠኝነት እነዚህ አካላት ለኢስላም ተቆርቁረው እንዳልሆነ ወዳጅ ቀርቶ ጠላትም አይዘነጋውም፡፡ እስራኤላዊው የቴልአቪቭ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሃጋይ ኢርሊች ለኢትዮጵያ የሚበጀው እስልምና አሕባሽ ነው እንዳለ የምናስታውስ ይመስለኛል፡፡ አላማቸው ከኢስላም ስሙን ብቻ የተሸከመ፣ ከቁርኣንና ከሐዲሥ በብዙ ርእሰ ጉዳዮች የተኳረፈ፣ በሃገር በቀል እንቶ ፈንቶዎች የተተበተበ፣ በህዝበ ሙስሊሙ መሀል የሚገኙ የባእድ አምልኮቶችን ለመጋፈጥ ወኔ የሌለው የላሸቀ “እስልምና”ን መጠበቅ ነው፡፡

ግብፃዊው የታሪክ ፀሐፊ አልጀበርቲ የፈረንሳዩ መሪ ናፖሊዎን ቦናፓርቴ ግብፅን በተቆጣጠረ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሲተርኩ የ 1213 ሂ. ክስተትን እንዲህ ይገልፁታል፡- የጦሩ አዛዥ የነብዩን ﷺ መውሊድ እንደልማዳቸው ለምን እንዳላከናወኑ ጠየቀ፡፡ ሁኔታዎች እንደቆሙ፣ ነገሮች እንደተራቆቱ፣ ለተለያዩ ወጪዎች የሚውል ገንዘብ እንደሌለም ሸይኽ በክሪ ተናገሩ፡፡ ናፖሊዎን “የግድ መዘጋጀት አለበት” በማለት ለዚሁ ተግባር ይታገዙበት ዘንድ ለሸይኽ በክሪ 300 የፈረንሳይ ገንዘብ ሰጠ፡፡ ከዚህ በኋላ ሻማዎችና ችቦዎች ተለኮሱ፡፡ ፈረንሳውያኑም ለመውሊድ ተሰባሰቡ፡፡ ከበሮዎቻቸውን እየመቱ ጨፈሩ፡፡ ትልልቅ ከበሮዎችና የተለያዩ ድምፆችን የሚሰጡ የሙዚቃ መሳሪያዎች ወደ ሸይኽ በክሪ ቤትም ተልከው ሌት ከ ተቀን ተደለቀ፡፡ ሌሊቱን ጧፍ ሲቀጣጠልና ርችቶች ወደ ሰማይ ሲተኮሱ አደረ፡፡ [መዝሀሩ ተቅዲስ፡ 47]

ጄ ክርስቶፎር ሄሮልድም እንዲህ በማለት ተመሳሳይ ታሪክ ያወሳል፡-

“የካይሮ ታዋቂ ሰዎች በዓሉን የሚያከብሩ አይመስሉም፡፡ ስለሆነም ናፖሊዎን ቦታውንም በጀቱንም በመፍቀድ አበረታታቸው፡፡ ካይሮ በዓሉን ለሶስት ቀናት አከበረች፡፡ ሱፊዮች በድካም እስከሚወድቁ ድረስ በጎዳናዎች ወጥተው ደነሱ፡፡ የፈረንሳይ ወታደሮችም የሙዚቃ ትርኢት አሳዩ፡፡ እሳት አቀጣጠሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦናፓርቴ የሸይኽ በክሪ እንግዳ ነበር፡፡ እስከ አንገቱ በተቆለፈው ጥቁር የደንብ ልብሱ የበዓል ገመዶችንና ጥምጣሞችን አድርገው የቁርኣን አንቀፆችን ከሚያነበንቡና ዶቃቸውን ከሚስቡ ሸይኾች ጋር ልዩ ገፅታ ነበረው፡፡” [Herold, J. C. Bonaparete in Egypt, published in 1962]

ምናልባት “እንዲህ አይነቱን የቢድዐ ድግስ በመደገፍ ፈረንሳውያኑ ምን ያተርፋሉ?” የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ የመውሊድ ደጋፊዎች “ጠላት ከህዝብ ልብ ውስጥ ለመግባት ያደረገው ነው፡፡ ልክ ሌሎች ዲናዊ ጉዳዮችን ለመፈፀም ጠላት ቢያግዘን እነዚያን ጉዳዮች በክፉ ልንመለከት ነው ወይ?” እንደሚሉ ይጠበቃል፡፡ እውነት መውሊድ በዚህ መልኩ የሚታይ ነው? መልሱን በወቅቱ ለነበሩት የታሪክ ፀሐፊው አልጀበርቲ እንለቀቅ፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፡-

“ፈረንሳውያኑ ይህን ለሰዎች የፈቀዱበት ምክንያት በውስጡ ከሸሪዐዊ አስተምህሮቶች ማፈንገጥ፣ የሴቶች መሰባሰብ፣ ስሜቶችን መከተል፣ አጉል ዛዛታና ሐራም የሆኑ ድርጊቶች ስላሉበት ነው፡፡” [ዐጃኢቡል ኣሣር፡ 2/306]

ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor