💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.69K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
~ኢላሂ
~ዱዓችንን ማሳመር ባንችል እንኳ
ሓጃችንን አንተ ታውቃለህ ።

ምላሣችንን ቢንተባተብም
ሀሳባችንን ትረዳለህ።
~ደክሞኛል ደግፈኝ ያ ረቢ...

~
👍11
ሴቶች እህቶቻችን ሆይ ፡-
በየ ሶሻል ሚዲያው አግቡን አጋቡን በማለት ራሳችሁን አታርክሱ ! አሏህ ባዘዘው መንገድ ቀጥ በሉና በቀጥተኛ በር ለመግባት ሞክሩ ።  አሁን ያለችሁበት መንገድ በሰዎች ላይ ፈተና ከመፍጠርና እናንተን ከማርክስ ውጭ ሌላ ጥቅም የለውም ደሞም የ ዘራፊዎችና የ" ሞካሪዎች " ሲሳይ መሆናችሁን ብትጠነቀቁ ጥሩ ነው ! የተቆርቋሪ ወንድም ምክር አድርጋችሁ ብታስቡት መልካም ነው !

https://t.me/Muhammedsirage
👍15
አስመሳይ አግብቼ ግራ ከምጋባ፣
ተደብቄ ልኑር ልቅር ሳላገባ።
ተመሳሳይ ኮፒ በመቅረቷ አልባባም፣
እምነት አሰዳቢ ፍፁም አላገባም።
የአላህን ትዕዛዝ ሂጃቧን አድርጋ፣
ከተጨማለቀች ከአጂነብይ ሰው ጋ፣
እሷን አላገባም ከቶ ቁሜ ልቅር፣
በብቻየ አለም ውስጥ ተደብቄ ልኑር።

አቂዳየ እያለ ምን አለው ካለችኝ፣
እስልምናየን ይዤ ድሃ ካረገችኝ፣
መስፈርቷ ከሆነ ቤት ና መኪና፣
ኒቃቢስትም ብትሆን ብትሄድ ተሸፍና፣
ትቅርብኝ ይች ልጂ እኔ አላገባትም፣
ኪታቤን አዝየ ሄዳለሁ የትም።

እውቀት ፍለጋየን አቀጣጥላለሁ፣
እምነት አሰዳቢ ለምን አገባለሁ።
ጀግና የጀግና ልጂ በመንሀጂ ያደገች፣
በሰለፎች አሰር አምራ የደመቀች፣
አላህ ከገጠመኝ ውብ ትዳር ፈላጊ፣
አስተዋይ መካሪ ንደት አረጋጊ፣
የሙብተዲ ጥላት ጦረኛ ተዋጊ፣

ሽርክን አፈራራሽ የተውሂድ ምርኮኛ፣
የቢድአ ካንሰር የሱና ሱሰኛ፣
እምነቷ ሲደፈር የሚያንዘረዝራት፣
ከእግር እስከ ራሷ ንደት የሚወራት፣
በአቂዳዋ ታጋይ ጀግና አርቆ አሳቢ፣
የእህቶቿ ሞደል በሂጃብ ተዋቢ፣

ከመጥፎ ከልክላ በመልካም ላይ አዛዢ፣
ውድ ባልተቤቷን በፍቅር አደንዛዢ።
ለረጂሙ ጉዞ ስንቋን የሰነቀች፣
በተውሂድ በሱና በሀቅ የደመቀች።
ከመንሀጀ ሰለፍ ሁሌ የማትለወጥ፣
ያወራ ቢያወራ ልቧን የማትሰጥ።

ይህችን መሳይ ሞደል ታስፈልገኛለች፣
እህትም ፣ባልተቤት እናት ትሆናለች።
ችግሩ እሷ ግን የት አለች የት አለች፣
ልፈልግ በዱኣ ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም፣
እምነት አሰዳቢ አልለማመጥም፣
ተውሂድ ያልገባት ልጂ አርፋ አትቀመጥም።

ያ አላህ
እኔንም አድርገኝ ከነጓደኞቼ፣
ቀጥ ብየ የምሄድ አንተኑ ፈርቼ።
ሀቅ የምገልፅበት ስጠኝ እምቅ ወኔ፣
ተውሂድ ላስተምረው ይጠቀም ወገኔ።
ጀግናይቱ የት አለች ለባሽ ጥቁር ካባ፣
ብቸኝነት ይብቃኝ አትፈትነኝ ላግባ


 
ከወንዶቹ  መንደር
👍10
ኡስታዝ ሳዳት ከማል ሙአዝ ሀቢብን አስጠነቀቀ
SadatKemal Abu Meryem
🛑👉ኡስታዝ ሳዳት ከማል ሙአዝ ሀቢብን አስጠነቀቀ!

አላህን ፍራ ነብዩን የሚወድ ከአስቴር አይኮርጅም ! የምንቃወመዉ በማስረጃ ነዉ!


=
👍6
የሰው ልጅ በህይወቱ ያሳለፋቸውን ከባባድ የጭንቀት እና የችግር ቀናት ሊረሳ ይችላል። በችግሩ ጊዜ ፊቱን ያዞረበትን ሰው እና በችግሩ ጊዜ አይዞህ ያለውን ባለውለታውን ግን አይረሳም።
👍12
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«ከኒካህ በፊት ያለ የፍቅር ቅዠት ማእከላዊ
እስር ቤት ሲሆን ከኒካህ በኋላ ያለው ንፁህ ፍቅር ግን ምድራዊ ጀነት ነው።!!
በተለይ ዲን እና አኽላቅን መስፈርት በማድረግ ላይ የተመሰረተ ትዳር ከሆነ ኒዕመል መታዕ...
👍32
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍂  إِنَّ ٱلَّذِینَ یَتۡلُونَ كِتَـٰبَ ٱللَّهِ 🍂
🎙  القارئ #عبدالرحمن_الحسينان
~
👍2
الحمدُ للهِ الَّذي بِنعمَتِه تَتمُّ الصَّالحاتُ .

አልሐምዱሊላህ! በፀጋው መልካም ነገሮች ሁሉ ይሳካሉ፡፡

~
👍13
~አንዲት ሴት አለች… እራሷን እየጠበቀች ለማይገባት ሰው ልትዳር የምትታጭ። አንዲት ሴት አለች ከማግባት የበለጠ ሊያገቧት የፈለጓት የሚያስፈራት። አንዲት ሴት አለች ብን ብላ ከቤተሰቦቿ መለየት ፈልጋ ሀያዕ ይዟት የተቀመጠች። አንዲት ሴት አለች በልጅነቷ ጥቃት ደርሶባት ለማንም ትንፍሽ ሳትል ኖራ በቤተሰብ በኩል ትዳር ሲመጣላት የምትበረግግ። አንዲት ሴት አለች ከገላዋ በቀር ምንም መስጠት የማትችልበት ሁኔታ ላይ ያለች። አንዲት ሴት አለች ልጅ አምሯታል፣ እናት መሆንን አጥብቃ ትፈልጋለች ግና ለልጇ አባት ለሷ ባል የሚሆናትን ትክክለኛው ሰው እስከሚመጣ ድረስ ስለምትጠብቅ የሆነ የደበቀችው ነውር አለባት ተብላ የምትታማ።

~ አንድ ወንድ አለ ከስሜቱ ጋር እየታገለ የሚኖር፣ ትዳር ፈልጎ ትዳር የተወደደበት። አንድ ወንድ አለ የሚረዳው ያላገኘ፣ ልፋ ብቻ የሚል ፍርድ የተፈረደበት። አንድ ወንድ አለ ልቡ ተሰብሮ ምንም እንዳልሆነ ጠንክሮ የሚንቀሳቀስ። አንድ ወንድ አለ ከዘመድ መጠጋት፣ ከሰው መቀላቀል የሚያስፈራው፣ እራሱን ለሁሉም ኃላፊነት በታትኖ ለራሱ መሆን ያቃተው። አንድ ወንድ አለ እናት እና ሚስት መሆን የምትችል ሴት የሚፈልግ፣ የልጆቹን እናት በጥንቃቄ የሚመርጥ። አንድ ወንድ አለ የሚወደውን ሰው ክብር ስለሚጠብቅ ሞኝ የተሰኘ፣ ድንበር አልፎ ስለማይባልግ ፈሪ የተባለ። አንድ ወንድ አለ ጉዳዮቹን ለራሱ መስጥሮ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈፀም ደፋ ቀና የሚል። አንድ ወንድ አለ ኃላፊነቶቹ ያጎበጡት፣ የሚንከባከባቸው ነፍሶች በዝተው የራሱን ነፍስ የረሳ አንድ ወንድ አለ።

ስለ ሰዎች የልብ ጉዳይ በእርግጠኝነት በፍፁም አታውቁም። ሁሉም የራሱ ቁስልና ህመም አለው። ቆሞ የሄደ ሁሉ ደስተኛ አይደለም። በበሽታ የሚማቅቅ ሁሉም አልከፋውም። የተቆነጀ ሁሉም ያማረ ታሪክ የለውም። አስጠሊታ የተባለ ሁሉም ቆንጆ ታሪክ የለውም ማለት አይደለም። ስለ ሰዎች የውስጥ ትግል አታውቁምና አጓጉል አትፍረዱ።…
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
👍9
🔖 አየሀው የእገሌ መኪና... እንዴት ያምራል !!አይባልም

~የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም
እንዲህ ብለዋል።

«ከእናንተ አንዳችው ከራሱም ሆነ ከገንዘቡ ወይም ከወንድሙ የሚያስደስተውን ነገር ያየ ሰው ባረከላሁ ይበል ምክንያቱም አይነናስ ሐቅ ነው።»
~
t.me/https_Asselfya
👍12
ኢላሂ!!

   ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር መታመሙን ስሰማ በጣም አዘንኩ ተጨነቅኩም። ትላንት ስልክ ደውየ ድምፁን ስሰማው ብረጋጋም ጉዳቱ የደሰበት የሰውነት ክፍል spinal cord ጋ መሆኑን ሲነግረኝ ግን በሃሳብ ተዋጥኩ። የጀርባ አጥንት ጉዳት አላህ ያቅልለት እንጅ ክፉ ቦታ ነው። የጉዳቱ ደረጃ ከፍ ካለ ሰውነት paralyzed ሁሉ ሊያደርግ ይችላል። ኢላሂ በሰፊው እዝነትህ ይሁንብህ ኡስታዛችንን አንተው አሽርልን።

ሀኪም ቤት ሂዶ እንደነበርና ወደፊትም ቀጠሮ እንዳለው አሳውቆኛል። እናማ የሱና ቤተሰቦች ከልባቹህ ዱዓ አድርጉለት። ኢብኑ ሙነወር ማለት አንድ ግለሰብ ሳይሆን እስካፍንጫው የታጠቀ ሙሉ ክፍለ-ጦር ነው። በአቅሙ ልክ በሙሉ ፅናት ለሱና ዘብ ቁሞ ቢድዓና የቢድዓ ሰዎችን አንገት ሲያስደፋ የኖረ ጀግናችን ነው።

እኛ ሰዎች ስንባል የተሰጠንን ፀጋ ታላቅነት የምንረዳው ስናጣው ስለሆነ እንጅ በአለንበት የፊትና ዘመን እንደ ኢብኑ ሙነወር አይነት የተሰላ ሰይፍ ከመታደል በላይ ትልቅ ፀጋ የለም። ካስተዋላቹህ የእርሱ እና መሰሎቹ ከሚዲያ መራቅ ለቀናትም ቢሆን እንኳ ትልቅ ተፅዕኖ አለው። t.me/Abu_lmran_Alaseriy
👍23
‏video-output-1C3FC84B-D6CE-4AF1-AFEA-1AA661C45363
🔹 تجد كثير من النّاس يعرف أشياء كثيره الا دينه !.

🎙الشيخ عبدالرزاق البدر وفقه الله تعالى
~የኢማንህን ልክ ለማወቅ ብቻህን ስትሆን ራስህን ተከታተለው። ለብቻህ ስትሆን አላህ የደነገገብህን ዒባዳ በተገቢው ትወጣለህ? ለብቻህ ስትገለል አላህን ትፈራለህ? ለብቻህ ስትገለል አላህን ለማመፅ ሀያእ ይዝሃል? ለብቻህ ስትገለል የአላህን ቅጣት ፈርተህ እንባ ታነባለህ?
👍15
እውነት ወይም ሀሰት

1, አላህ እኛን የፈጠረን እሱን ብቻ እንድናመልከው ነው ።

(ከመልሱ ጀርባ ጠቃሚ ነገር አለ)
🔖 የማታ ዚክር አትርሱ ...!
~    ~    ~    ~     ~   ~   ~
🌻اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَاْلآخِرَةِ، اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِيْنِيْ وَدُنْيَايَ وَأَهْلِيْ وَمَالِيْ. اَللَّهُمَّ احْفَظْنِيْ مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ، وَمِنْ خَلْفِيْ، وَعَنْ يَمِيْنِيْ وَعَنْ شِمَالِيْ، وَمِنْ فَوْقِيْ، وَأَعُوْذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِيْ.
#አላህ ሆይ! በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ይቅርታንና ጤንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡

አላህ ሆይ! በሀይማኖቴ፥ በዚህች አለም ህይወቴም፥ በቤተሰቦቼም፥ በንብረቴም ደህንነትን እጠይቅሃለሁአላህ ሆይ! ነውሬን ሸፍንልኝ፡፡

አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴ  ከኃላዬም፥ ከቀኜም፥ ከግራዬም፥ ከበላዬም ጠብቀኝ፡፡ ከበታቼም እንዳልጠቃ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡
   ~
   
t.me/https_Asselfya
👍2