💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.73K subscribers
1.27K photos
494 videos
123 files
5.14K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🔖رِجَالٌ لَّا تُلْهِيهِمْ تِجَارَةٌ وَلَا بَيْعٌ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَإِقَامِ الصَّلَاةِ وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ ۙ يَخَافُونَ يَوْمًا تَتَقَلَّبُ فِيهِ الْقُلُوبُ وَالْأَبْصَارُ 

[النور : 37]
~
👍7
ሰው እንዴት ሙታን ይማፀናል?
~
ሙታን የሚጣሩ ብዙ ወገኖች አሉ። ሙታኖች አይጠቅሙም፣ አይጎዱም። ሙታን ምን አቅም አላቸው? እንኳን እነ ሸይኽ ጫሊ፣ አና፣ ዳና፣ ቃጥባሬ፣ አብሬ፣ አናጂና፣ ገታ፣ መጂት፣ ሸህ ዐሊ ጎንደር፣ ደገር፣ ... ታላቁ የአላህ ነቢይ ዒሳም እናታቸው መርየምም አይጠቅሙም አይጎዱም። ይሄው ጌታችን አላህ ዒሳንና መርየምን የሚያመልኩ ሰዎችን ሁኔታ ከተነተነ በኋላ እንዲህ ይላል፦
{قُلۡ أَتَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا یَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرࣰّا وَلَا نَفۡعࣰاۚ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡعَلِیمُ}
{“ሰሚውና አዋቂው አላህ ሆኖ ሳለ ከአላህ ሌላ ለናንተ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችልን ትገዛላችሁን?” በላቸው፡፡} [ማኢዳህ፡ 76]

ወገኔ ሆይ! ለሁሉ የሚበቃ ህያው ጌታ እያለህ ሙታን ሰፈር ምን አልከሰከሰህ? ወላሂ አብሬት አልከው ጫሊ፣ ደገር አልከው ዳኒይ፣... እድሜ ልክህን ብትጮህ ማናቸውም አይሰሙህም። ቢሰሙህ እንኳ ምላሽ የሚሰጡበት አቅሙ የላቸውም። ይሄ የኔ ቃል አይደለም። ሃያሉ ጌታ ምን እንደሚል ተመልከት፦
{وَٱلَّذِینَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا یَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِیرٍ (13) إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا یَسۡمَعُوا۟ دُعَاۤءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُوا۟ مَا ٱسۡتَجَابُوا۟ لَكُمۡۖ وَیَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ یَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا یُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِیرࣲ (14)}
{እነዚያም ከርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ (ስሷ) ሽፋን እንኳን የላቸውም። ብትጠሯቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም። ቢሰሙም አይመልሱላችሁም። በትንሳኤ ቀንም እነሱን ከአላህ ጋር ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ-አዋቂው ማንም አይነግርህም።} [ፋጢር፡ 13-14]

እንዲያውም እወቅ! እነዚህ ዛሬ ለጭንቅ ለችግር ይደርሱልኛል ብለህ የምትማፀናቸው አካላት ነገ በቂያማ ቀን ጠላቶችህ ነው የሚሆኑህ። ከራሴ አይደለም የማወራው። ምስክሬ ቁርኣን ነው፦
{وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن یَدۡعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا یَسۡتَجِیبُ لَهُۥۤ إِلَىٰ یَوۡمِ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَاۤىِٕهِمۡ غَـٰفِلُونَ (5) وَإِذَا حُشِرَ ٱلنَّاسُ كَانُوا۟ لَهُمۡ أَعۡدَاۤءࣰ وَكَانُوا۟ بِعِبَادَتِهِمۡ كَـٰفِرِینَ (6) وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَیۡهِمۡ ءَایَـٰتُنَا بَیِّنَـٰتࣲ قَالَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَاۤءَهُمۡ هَـٰذَا سِحۡرࣱ مُّبِینٌ (7)}
{እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ለሱ የማይመልስለትን ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ይበልጥ የጠመመው ማነው? እነሱም (ተጠሪዎቹ) ከጥሪያቸው የዘነጉ ሆነው ሳለ?! ሰዎች (ቂያማ) በተሰበሰቡ ጊዜም ለነሱ ጠላቶች ይሆናሉ። መመለካቸውንም የሚክዱ ይሆናሉ።} [አሕቃፍ፡ 5-6]

ግዴለህም ከፍጡር አትነካካ። {ህያው በሆነው በዚያ በማይሞተው ላይ ተመካ።} [ፉርቃን፡ 58]
ደግሞ እወቅ። ለጭንቅ ለችግር መጣራት፣ ሪዝቅ ፈልጎ፣ አደጋን ፈርቶ መማፀን፣ ዱዓእ ማድረግ ዒባዳ ነው፣ አምልኮት። ዒባዳ ደግሞ የፈጣሪ ሐቅ ስለሆነ ለፍጡር አይስሰጥም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-
الدُّعاءُ هو العبادةُ
{ዱዓእ በእርግጥ አምልኮት ነው።} [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1329]

ታዲያ ዱዓእ አምልኮት ከሆነ ለፍጡር መሄድ አለበትን? በጭራሽ! ልክ እንደ ሶላቱ፣ እንደ ፆሙ ለአላህ እንጂ ለማንም ሊስሰጥ አይገባም። ኃያሉ ጌታ እንዲህ ይላል
{فَلَا تَدۡعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدࣰا}
{ከአላህ ጋር አንድንም አትጣሩ!} [ጂን፡ 18]

ነብዩም ﷺ {ስትለምን አላህን ለምን} ይላሉ። [ሚሽካቱል መሷቢሕ፡ 5302]

ቀድሞ ነገር ፍጡር ማንስ ቢሆን ምን ሊፈይድ ይጠራል? አዛኙ ጌታ:-

* {ለምኑኝ እመልስላችኋለሁ} አላለምን? ይህንን አታምንም?
* {ባሪያዬ ስለኔ ከጠየቀህ እኔ ቅርብ ነኝ} አላለምን? ትጠራጠራለህ?
* {አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን?} እያለ ነው። "አዎ በቂ አይደለም" ነው መልስህ? ከበቃህ ታዲያ ፍጡር ዘንድ ያውም ሙታን ሰፈር ምን ትሰራለህ? ለራስህ ስትል እወቅበት። ቁርኣንን ጥለህ ከአባት፣ ከአያት በመጣ ውርስ አትሸነፍ። በህሊናህ ላይ አትሸፍት። ሰው እንዴት በዚህ ዘመን ሙታን ይደርስልኛል ብሎ ያምናል? ልክፍት ነው!
=
(ኢብኑ ሙነወር ፣ ሸዋል 18/1444 (ሚያዚያ 30/ 2015 ))
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
👍4
Forwarded from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ] (Muhammed Ibnu Fedlu [Abu Nuh])
Hp Laptop
slightly used
Storage  512/8
Model 840 g6 8th generation
Core l5
Price 39,000 ብዛት ለሚፈልግ ልዩ ቅናሽ አለው

ለመግዛትም ሆነ ለማዘዘ 👉 @AbuNuhibnufedlu ማናገር ትችላላችሁ

ወይም 📞 0947778381 ላይ መደወል ትችላላችሁ።
🔖ዛፍ ሲወድቅ እንጂ
ሲያድግ ድምፅ የለውም
ለውጥህን በዝምታ አድርገው!

~
t.me/https_Asselfya
👍26
🔖ኢማሙ አህመድ "አላህ ይዘንላቸውናለአላህ ብሎ መውደድ ማለት ምን ማለት ነው? ተብለው ተጠይቀው፦
«ለየትኛው ዱንያው ጥቅም ብለህ አለመውደድህ ነው» ብለው መልሰዋል።

📚طبقات الحنابلة 1/57.
~
t.me/https_Asselfya
👍8
🔖የሴት ምርጥ ማለት!
~በአላህ ላይ ተወኩል ያላት!
~በአላህ ቀድር ያመነች!
~ባዕድ ወንድ የማያያት!
~ራሷን ፈታኝ + ተፈታኝ ከመሆን የምትጠነቀቅ!
~ብzuከመናገር ብዙ ማዳመጥን የምትመርጥ!
~ጅህልናን ለማስወገድ በዒልም መቀሰም ላይ የበረታች! 
~ በሸሪዓዊአለባበስ ራስዋን የሰተረች !አይነ አፋር የሆነች!

~የሀያዕ ካባ የተላበሰች ከማንኛውም ነገር ቁጥብ የሆነች!
~በዒባዳዋ ጠንካራ የሆነች!
~ራስዋን ከዕዩልኝ ( ሪያዕ)ስራ ያፀዳች!

~በውበቷ ብቻ ሳይሆን በሰነ - ምግባሯ የተዋበች! ኡመሀተል ሙእሚንን አርዓያ ያደረገች!

~ከማንኛውን የጠመመ አንጃ  ፀድታ_ድኗን_ በሱሀባዎች አረዳድ የተረዳች!

~ያለ ዕውቀት ከመናገር የተቆጠበች
የሰማችውን + ያየችውን ሁሉ የማታወራ!

~ለጓደኞቿ ጥሩ ተምሳሌት የሆነች!
የባሏን ሀቅ የምትጠብቅ!

~ከሶሻል ሚዲያ ፊትናዎች እራሷን የጠበቀች! #ዕይታዋንየምትቆጣጠር + ሰበር የደረገች!

👉ውዷ እህቴ ራሳችንን እንፈትሽ !!

t.me/https_Asselfya
👍6
Audio
Sheikh Mohamed Welle
🔖ሴቶች በኢስላም

~ክፍል አንድ

🎙 በሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁላ፞ህ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በየትኛውም ሁኔታ ክብሯን የምትጠብቅ ሴተን አላሀ ያግናኛችሁ ወንዶች!
👍21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔹 نفسك إن لم تشغلها بالحق شغلتك بالباطل

🎙الشيخ
محمد بن رمزان الهاجري
حفظه الله تعالى و رعاه
صلاح القلب
الشيخ أحمد الحكمي
🔖የቀልብን መስተካከል ዘጠኝ ነገሮች ዉስጥ ፈልጉት!!
صلاح القلوب في تسعة أشياء:


🎙 لشيخنا الفاضل
أحمد بن عبدالله الحكمي
حفظه الله تعالى

١. قراءة القرآن بتدبر
٢. خلاء البطن بتقليل الأكل
٣. قيام الليل بالعبادة
٤. التضرع عند السحر
٥. مجالسة الصالحين
٦. الصمت عما لا يعني
٧. العزلة عن أهل الباطل والجهل
٨. ترك الخوض في الناس
٩. أكل الحلال
t.me/https_Asselfya
👍2
يَقُولُونَ يَا لَيْتَنَا أَطَعْنَا اللَّهَ || الشيخ محمد عبادة
<unknown>
👉ጣፋጭ ቲላዋ

~ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፦

➡️ ቁርአን የሚያዳምጥ የሆነ አካል በእያንዳንዱ ፊደል ቃሪውን በአጅር የሚጋራው ይሆናል። ለሁሉም ሙስሊም ወንድሞቻችን ቁርአን በማድመጥ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እንመክራለን።

~
t.me/https_Asselfya
🔖ሴቶች ከፋጢማ ተማሩ !!


ፋጢማ አላህ መልካም ስራዋ ይውደድላትና የጅሙአ ቀን ከአሱር በኋላ አንድ ሰው ታስቀምጥና ፀሀይ እንዲመለከትላት ታዘዋለች። ይህ ሰው ፀሀይ ልትገባ እየተቃረበች መሆኑን ሲነግራት፦ ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጋ በመተው ፀሀይዋ እስክትጠልቅ ድረስ ወደ ዱአ ትዞር ነበር

📚فتح الباري./ كتاب الجمعة(١٦٢٢)

👉የጅሙአ ቀን ወቅተል ኢጃብ የተባለው ሰአት እቤታችሁም ሆናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። በተለይ የጅሙአ የቀኑ መጨረሻ ፀሀይ ልትገባ በምትቃረብበት ሰአት ጌታችሁን በመለመን ላይ በርቱ። ምናልባትም የተለመነ ነገር ሁሉ እሺ ሚባልበት ወቅት ሊሆን ይችላልና።

t.me/https_Asselfya
👍2
‏﴿وقرن في بيوتكن ولا تبرجن تبرج الجاهلية الأولى﴾

كلمة {في بيوتكن} أبلغ من كلمة (وقرن في البيوت)، كأنه يقول: هذا البيت ‌ما ‌بُني ‌إلا ‌لكِ، سترًا لكِ وصونًا، فالزمي هذا البيت الذي من أجلكِ بُني.

📚ابن عثيمين تفسير سورة الأحزاب (ص: ٢٤٠).
👍1
«ይገባዋል አባ»

እንዳንዴ እንደ ልጅ ሆድ ብሶን ሲከፋን፡
እንደ ወጀብ ሆኖ ሰው ሁሉ ሲገፋን፡
ማድመጫም ማሽተቻም ሲዘጋ በጉንፋን፡

ከአበቦች መሐል ፅጌረዳ ቀጥፎ፡
እንቅፋታችንን በብርሀን አጥፎ፡
ያሰናከለንን በትግል ቀርጥፎ፡
በልጁ መስመር ላይ ራሱን አንጥፎ፡

ይህን ሁሉ እሚያደርግ ውብ አንድ ሰው አለ፡
ያልተማረ ጠቢብ ተራራ ያከለ፡
ናፍቆኛል ያ ጀግና ልየው የት እንዳለ!!



.....አባባዬ....
.....አበባዬ....
.....ውብ ካባዬ....
......ልዩ አርማዬ.....

በጨለማ አልቅሶ እንባውን የሚያብስ፡
ለራሱ እያከከ እኔን የሚዳብስ፡
እሱ እየታረዘ ለልጁ እሚያለብስ፡
የኔ አንጀት እንድሽር ውስጡን የሚጠብስ፡
በልጁ ደስታ ልክ ፕላን ሚቀለብስ፡
ውብ አንድ ሰው አለ ከሁሉም የሚብስ፡

ንግስና ቢቸረው ቢሸለም ጡሩራ፡
በጡብ የተካነ ምን ህንፃ ቢሰራ፡
ቢጎዘጎዝ ምንጣፍ ፅጌረዳ አበባ፡
ውብ ጫማ ቢጫመት ቢለብስ ውድ ካባ፡
ምንም ቢያደርጉለት ይገባዋል አባ!!

....በኑረዲን አል_ዓረብ

t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
👍12👎1
2_5399973514092504784.ogg
185.1 KB
متى يرتاح المؤمن ؟

د. محمد بن غيث وفقه الله تعالى 🎙
"በቀልድም እንኳ ቢሆን ጓደኝነትን የሚሸረሽሩ ነገሮችን ከመናገር ተቆጠብ --- ወዳጅነት ውድ ነው!

~
t.me/https_Asselfya
👍10
አይ አሕባሾች! ግን ምን አይነት ፍጡሮች ናችሁ?

እንደሚታወቀው በተለያዩ ጊዜ በንፅፅር ዳዕዋ ላይ በተሰማሩ ኡስታዞችና ዳዒዎች አማካይነት ብዙዎች ወደ ኢስላም እየሰለሙ እንደሆነ ይታወቃል። ካፊሮች ወደ ትክክለኛው መንገድ ወደ ኢስላም እንድመሩ ለሂዳያ ሰበብ የሆኑና እየሆኑ ያሉ ኡስታዞቻችንን ዳዒዎቻችንን ልናግዛቸውና በምንችለው ሁሉ ከጎናቸው ልንቆም ይገባናል።አሏህ ለሁሉም ሰው የሂዳያ ሰበብ እንዲያደርጋቸውና አምሳያዎቻቸውን እንዲያበዛ ዱዓ እናድርግ።!

ይሁን እንጂ ለእንዲህና መሰል ለኸይር ስራ ያልታደሉት አሕባሾች ደግሞ ይህን ኸይር ስራ ለማደናቀፍና እንቅፋት ለመሆን ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል።ድሮም የአሕባሽ ስራ መበጥበጥና ሁከት መፍጠር ነው።ይህ አዲስ ነገር አይደለም። በተለይ ደግሞ የመጅሊስን ስልጣን ከተነጠቁ ወዲህ ጤናቸውም ትክክል አይመስለኝም።

ዶክተር ተብዬው ስለ የሚሰልሙ ሰዎች ተጠይቆ መጀመሪያ ከነበሩበት እምነት የስም ለውጥ አደረጉ እንጂ ምንም ያው እዛው ኩፍር ውስጥ ናቸው።ምንም ልዩነት የለውም። ነሷራ እያለ አባታችን ሆይ! በሰመያት የምትኖር ይል ነበር! ሰለመ ካሉ በኋላ አባታችን አትበል ይሉታል። ያው ተጅሲም ነው የሚያመልከው አለ ፈትዋ መሆኑ ነው! ድንቄም ፈትዋ!

ለነገሩ አሕባሾቹ እነ
ሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ ዶክተር ተብዬው አቡበክር፣ ሐሰን ታጁ፣ዑመር ኮምቦልቻና ሌሎችም የአሕባሽ ግልገሎች አይደለም ከኢስላም ውጪ ያለን ሰው በንፅፅር ዳዕዋ አድርገው ወደ ኢስላም ልያመጡ ቀርቶ ኢስልምና ውስጥ ያለውንም ሰው ሺርክያት ወደ ቀብር አምልኮ፣የቀብር አፈር ወደ መብላት፣ወደ ጫት መቃምና በመንዙማ ነብዩን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን እናወድሳቸዋለን በሚል ሴትና ወንድ አደባልቆ ወደ መጨፈርና መዝለል ነው ጥሪ የሚያደርጉት።ስራቸው ይሀው ነው። ከዛም ይህ ነው ነባሩ እስልምና ይሉሃል።! ነባሩ ማለት የጥንት የጧቱ የሷሓቦቹ?! ድንቄም ነባሩ እስልምና!!

ኢንሻ አሏህ ዳግም ወደ መጅሊስማ አትመለሱም!! ህዝበ ሙስሊሙን ልታሳስሩ፣ልታስደበድቡ፣ልታስገድሉ፣መስጂዶችን ከቂርኣት፣ከዳዕዋና ከዒባዳ ባዶ አድርጋችሁ ጫት መቃሚያ መጨፈሪያ ድቤ መደብደብያ ልታደርጉት አሏህም አያሳካላችሁም ኢንሻ አሏህ!!

     ወንድማችሁ:- አቡ መርየም

       የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ ሼርም ያድርጉ።
👉http://t.me/AbuMeryemNeja 👈
👍4