💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.72K subscribers
1.27K photos
494 videos
123 files
5.14K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🔖የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ አሉ:-

«የጀነት በሮች ዘወትር ሰኞና ሀሙስ ይከፈታሉ፣ በነዚህ ቀን በአላህ ላይ ለማያጋሩ ባሮች ሁሉ ሃጢያታቸው ይማርላቸዋል ፀብ ያላቸው ሰወች ሲቀሩ እነሱን እስኪታረቁ ጠብቋቸው ይባላል»።

📚ሶሒሁ ሙስሊም
=
t.me/https_Asselfya
🔖ከፈጅር ሶላት በፊት  ሁለት ረከአ መስገድ !!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
እናታችን አኢሻ  በዘገበቺዉ ሓዲስ የአላህ መልክተኛ  እንዲህ ብለዋል ትለናለች፦

- عن عائشة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم - قال : ( ركعتا الفجر خير من الدنيا وما فيها ) .

رواه مسلم  -

~የፈጂር ሁለት ረካዎች  ከዱኒያ እና በዉስጧ ካሉ ነገሮች ሁሉ ይበልጣሉ።

  📚[[ሙስሊም ዘግቦታል]]


t.me/https_Asselfya
ሙሉ ፀሁፍ ከታች ባለዉ ሊንክ ገብተዉ ያንብቡ
አንብበዉ ሲጨርሱ ለሌሎች ማሰራጨት አይርሱ!

↷↓↓↶
t.me/IbnuMunewor/4692
t.me/IbnuMunewor/4693
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
أركان طلب العلم ...
الشيخ محمد آدم الإثيوبي .. رحمه الله تعالى.
11-القواعد الحسان
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም
🔖 አዲስ ተከታታይ ደርስ

📚የአል_ቀዋዒዱል_ሒሳን ኪታብ

~ ክፍል - 11

🎙️ሸይኽ ሙሐመድዘይን ሸይኽ ኣደም

የኪታቡን  Pdf   ለማግኘት* ↓↓↓
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/8593
«ስኬታማ መሆን ከፈለክ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀምበት፣ እያንዳንዷ ችላ ብለህ የምታሳልፋት ጊዜ ዎጋ ታስከፍልሃለችና፣ በአግባቡ ተጠቀምባት»።

=
🔖 ለማየት ስንሄድ መታየትም አለ .. ህእ¡
🔖የምትናፍቅ ብቸኛዋ ሀገር ጀነት
ሁሉ ነገር በዉስጧ ያለባት ሀገር ጀነት

~ጀነት ዉስጥ ሞት የለም
~ጀነት ዉስጥ ላጤ የለም
~ጀነት ዉስጥ ሀሳብ የለም
~ጀነት ዉስጥ ጭንቀት የለም
~ጀነት ዉስጥ እርጅና የለም
~ጀነት ዉስጥ ከወርቅ የተሠሩ ህንጻዎች አሉ።

ጀነት .....
اللَّهُمَّ إِنِّيْ أسْألُكَ الْجَنَّةَ وَأعُوْذُ بِكَ مِنَ النَّارِ

        ~
        t.me/https_Asselfya
[ فضل الصيام في شهر الله محرم.. ]

عن أبي هريرة رضي الله عنه يرفعه، قال :
سئل : أي الصلاة أفضل بعد المكتوبة ؟
وأي الصيام أفضل بعد شهر رمضان ؟ فقال :
" أفضل الصلاة بعد الصلاة المكتوبة، الصلاة في جوف الليل، وأفضل الصيام بعد شهر رمضان، صيام شهر الله المحرم "

[رواه مسلم ١١٦٣ ]
🔖ትዳርና አላማ...!

ዲኑንና አኽላቁን  የምተወጅለት ባል መጥቶልሽ አላማ አለኝ እያልሽ. የምትመልሽ እህት.  ምን ታይቶሽ ነው?  ከትዳር የሚያግድ አላማ ምን አይነት አላማ ሆኖ  ነው? አላማሽ ተሳክቶ  ትዳሩስ ቢጠፋ? ትዳር የአላህ እርዚቅ ነው ልትይኝ ትችያለሽ. ትክክል ነሽ  እርዚቅን መልሶ  . ሌላ እርዚቅ መፈለግ ግን . ብልህነት አይደለም።“የተገኘን ትቶ ያልተገኘን መፈለግ ጥበብ አይደለም" ከትዳር የበለጠ ምን አላማ አለ?    ትዳር እና አላማ በምንም አይጋጭም በተለይ ሴት ልጅ አግብታም ላለመችለት ህልም መኖር ትችላለች።እንዳምው ብርታትን ታገኛለች።

منقول
.. t.me/https_Asselfya
👍1
~ሰዎች ላይ የምታየውን  ለውጥ  አንተም ጋር እንዲኖር ከፈለክ አንተም እንደነሱ መታገል ብቻ ነው።አለቀ!!

~
🔖ሶላት ከማሰላመትህ በፊት ከአራት ነገሮች ተጠበቅ....!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

إِذا فَرَغَ أَحَدُكُمْ مِنَ التَّشَهُّدِ الآخِرِ، فَلْيَتَعَوَّذْ باللَّهِ مِن أَرْبَعٍ: مِن عَذابِ جَهَنَّمَ، وَمِنْ عَذابِ القَبْرِ، وَمِنْ فِتْنَةِ المَحْيا والْمَماتِ، وَمِنْ شَرِّ المَسِيحِ الدَّجّالِ.

~“አንዳችሁ በመጨረሻው ተሸሁድ ላይ በሆነ ግዜ ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቅ፦

~ከጀሀነም ቅጣት
~ከቀብር ቅጣት

~ከህይወትና ከሞት ፈተና እንዲሁም ከመሲሁ ደጃል ፈተና።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል

~
t.me/https_Asselfya
👍2
•°

" ቁርኣንን ማዳመጥ ከመልካም ስራዎች አንዱ ነው"
🔖ትንሽ ስለትዳር
---------
ትዳር ላወቀበት ምርጥ ህይ ወትህ ነው። እንዳውም በምርጥ ትዳር ላይ ያሉ ሰዎች ዘግይቼ ነው ያገባሁት በማለት ይቆጫሉ። የነብዩን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን) ትዕዛዝ አክብረው በሸሪዓው መስፈርት የመረጡና አላህን የሚፈሩ ምርጥ ህይወት ውስጥ ናቸው። ይሁን እንጅ ቻሌንጅ የለም ማለት አይደለም። ቻሌንጆቹ እንደ ብልጠታችን ሊቀሉና ሊከብዱ ይችላሉ። ትዳር ትልቅ ት/ ት ቤት ነው። እንደፈለጉ መውጣት መግባት የለም። ሁሉም በሰአት ነው። ከትዳር በፊት እንደፈለጉ ማምሸት የሚቀናቸው ሰዎች ትዳር ውስጥም ይፈታተናቸዋል። አንዳንዶች እስር ቤት ነው ሲሉም ይሰማሉ። መንዘላዘል ለለመደ በርግጥም እስር  ቤት ነው። ምርጥ እስር ቤት ።# ዝርክርኮችን አንቆ የሚይዝ። እንጅማ:- ትዳር እስር ቤት ነው ማለት

~አንደኛ:- ከአማኝ ይህ ቆሻሻ ንግግር አይጠበቅም።

~ሁለተኛ:- ነብያቶች እስር ቤት ውስጥ ነበር የኖሩት ማለት ነው።

~ሶስተኛ:- መልካም ቀደምቶችም እንዲሁ እስር ቤት ውስጥ ነበሩ የኖሩት ማለት ነው።

~አራተኛ:- ይህ ሁሉ ባለትዳር እስር ቤት ውስጥ ነው ያለው ማለት ነው? 

👉ለዚህ መጥፎ አስተሳሰብ ያነሳሳቸው አንድም ከመጥፎ ስነ ምግባራቸው የተነሳ አለያም በሚያጋጥማቸው መጥፎ አጋር ሊሆን ይችላል። እንጅ ያለ ትዳር መኖር በጣም ከባድ! ነው።
ይህን አማኝ ሁሉ ያውቀዋል። ይህን  አስተሳሰብ የሚያስቡ ሰዎች ለሀራም የማይጨነቁ ዋልጌዎች አስተሳሰብ ሾር የወደቁ ናቸው።

በትዳር ውስጥ ትልቅ ደስታ አለ። አሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል።  

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًا لِّتَسْكُنُوٓا۟ إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَءَايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

«ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡»  áŠ áˆáˆŠáˆ 21

👉ስለዚህ ትዳር ነፍሶቻችን የምትረካበት ፍቅርና እዝነት ያለበት ህይወት ነው። ስለዚህ ያላገባን  እናግባ ። ልጅ ያለንም "ዲኑንና ስነ ምግባሩን የምትወዱት ከመጣ ዳሩት " ብለዋልና ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እና ልጆቻችን እንዳራቸው ። በጊዜ መዳር ለልጆቻችን እዝነት ነው። በተለይ ሀብታሞች ለልጃችሁ የመጣውን ባል ደሀ ነው ብላችሁ አትመልሱ። ከቻላችሁ አቋቁሙት። መቼም ብር ከልጃችን በላይ አይደለም።

ሴቶችም አደራ አቅም የቻለውን ጠይቁ ከአቅም በላይ አትጠይቁ አላህን ፍሩ። አላህን ከፈራን ከማናስብበት አላህ ይሰጠናል። ትዳር ዛሬ ገብተንበት  ነገ የምንተወው እቃ እቃ ጨዋታ አይደለም!። ስለዚህ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። መልካም ከሆንን አሏህ መልካሟን ይሰጠናል። አትጠራጠሩ "መልካም ሴቶች ለመልካም ወንዶች ናቸው" ብሏል አሏህ። መምረጥ ያለብን ማንን እንደሆነ ማወቅ አለብን። አንዳንዶች ሚስት ፈልግልኝ የሚሉህ አይተህና ሰምተህ የማታውቃት አይነት ሴት ነው። ወንዶች ቁንጂና ላይ ያላችሁን መስፈርት አስተካክሉ። ቁንጅና ከዲንና ከጥሩ ስነ ምግባር ጋር ከተገኘ …… ነገር ግን ስታያት ደስ የምትልህ በቂ ናት።

አንዳንዱ ደግሞ ምን አይነት ነው የምትፈልገው ስትለው ዲን ያላት ይልሀል። ዲን ሲልህ  በጣም ቆንጆ ማለቱ  ነው። ይህንን የምታውቀው ሲያገባ ነው። ጠንካራ ያልከው ወጣት ጅልባብ እንኳን መልበስ ያቃታትን ያገባና አስተካክላታለሁ ይልሀል። ኋላ ግን እሱ ሳይሆን እሷ ታስተካክለዋለች። ሾል እንደ ኒያ አይደል የሚገኘው ። ስለዚህ ኒያህን እስተካክል። ትዳር ውስጥ ከገባን በኋላ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት ይጠበቅብሀል።

ለዚህም የመጀመሪያው:- አላህን መፍራት ነው።
ሁለተኛ:- ባህሪዋን ጠንቅቆ ማወቅ  በተለይ  በጣም የምትጠላውን ነገር በተቻለ መጠን መራቅ። ይህ ማለት አንዳንዴ ሴቶች ሸሪዓ የማይከለክለው ነገር ቢሆን እንኳን ሊጠሉ ይችላሉ ። የዚህን ጊዜ አንተ ሀራም አይደለ እያልክ አንጀቷን እንዳታሳርረው ተጠንቀቅ።

ሶስተኛ:- ሁሌም ስህተትህን ማመን የበላይ መሆንን ብቻ አታስብ።
በነገራችን ላይ ትዳር የመጀመሪያ አካባቢ ስንደዋወል እንደነበረን ስሜት አይደለም። ይሞቃል ይበርዳል። በበረደ ጊዜ ይህ መሆኑን ባውቅ ኖሮ እያልክ አታማር።

አራተኛ:- ስሜቷን የሚጎዱ ነገሮችን መጠንቀቅ። ለምሳሌ ሾለ ሁለተኛ ሚስት ማውራት። አንዳንዱማ ይገርማል እንዲትለማመደው እኮ ነው ይላል። ይህ ሞኝነት ነው። ምክንያቱም የሚለመድ ነገር ስላልሆነ። እንኳን ያንተ ሚስት የነብዪም ባለቤቶች አልለመዱትም። አልሰማህም እንዴ አንዷ ባለቤታቸው ምግብ ሰርታ ወደ ነብዩ ልካ ያችኛዋ ባለቤታቸው ምግብ የመጣበትን እቃ ስትሰብረው። ግዴለህም ልምከርህ መለፍለፍ ይቅርብህ። ጀግንነት አይደለም። ጀግንነት ማለት የያዝካትን በዲንም በዱንያም በመንከባከብ ማስደሰትና (አቅምህ ከፈቀደም ስሜቷን  ሳትጎዳት ሸሪዐው በፈቀደው መልክ የሷንም ሀቅ ጠብቀህ ሌላ ደርበህ ማግባት) ነው። ግን ስንቶቻችን ነን ለሁለተኛ ሚስት ተቅዋችን ስነ ምግባራችንና አቅማችን የሚፈቅደው። ብዙ ወንዶችኮ ገና ሁለተኛ እንዳገቡ የመጀመሪያዋን እንደ ሙዝ ልጣጭ አሽቀንጥረው ነው የሚጥሏት። ምክንያቱም ተቅዋ የለማ ይህ የሚያደርግ የቂያማ ቀን ጎኑ ተንሻፎ ይቀሰቀሳል።  ስለዚህ ስናገባም አሏህ እንፍራ በትዳርም ውስጥ ሆነን አሏህን እንፍራ ። አላህን የሚፈራ መውጫ ያደርግለታልና።

  منقول
t.me/https_Asselfya
👍1
Forwarded from Abu_selman ((Abdulalim))
የአሰሪዋ ስልክ ቁጥር
👇👇👇
mama jo
Mobile 07 8506 9345
❝የሴትነት ሞራል ...!

በነገ ተስፋ ላይ  እቅዷን ሰንቃ፤
ሁሉን እየቻለች ችግሮቿን ንቃ፤
ሰለፍያዋ እንስት ትታያለች ደምቃ፤

በስደት  አለም ላይ ህይወቷን ገብራ፤
ዉስጧ  እየታመመ ዉጯ  የሚያበራ፤
ዉድ የአላህ ባሪያ ያች ሰለፍያ ትታያለች አምራ ..!

  አንድ ጊዜ ስትቆርጥ  ሺ ጊዜ ስትለካ ፤
እንደነ ኸድጃ ደግሞ እንደበረካ፤
በዱኒያዊ ወረት በጌጥ ሳትረካ፤
ሴትነት እንዲህ ነዉ  ታዕምር ነዉ ለካ፤
   ~
       http://t.me/asselfya