💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.66K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
📍የሒጃብ ጥፍጥና⁾                 { እና } ⁽❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾ 👉🔖ክፍል ሁለት ▪️ስለሒጃብ በሁለተኛ ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ ➥ሌለኛዋ እህት ደግሞ ፦ "ለምን ነገሮችን  እናከባብዳቸዋለን ኢስላም ገር የሆነ ሀይማኖት ነው {ነአም ገር ነው } ። ታዲያ ሰወች ለምን አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርጉታል ? ሂጃብ ሴትን ልጅ ከሚያስጨንቋት ነገሮች አንዱ በመሆኑ  ለምን እንድትቸገር…
📍⁽የሒጃብ ጥፍጥና⁾
                { እና }
⁽❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾

➟
ክፍል ሶስት

▪ስ
ለሒጃብ በሶስተኛነት ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ

👉ሌላኛዋ እህታችን ደግሞ ! "በኢስላም ስራ (ከስብ) ከአምልኮ ተግባር ይቆጠራል ተብሏል ፤ ስራን መፈለግ ደግሞ ኢስላማዊ ግደታ ነው ፤ሂጃብ ለብሶ የስራን ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ጉዳይ ነው በዚህ የተነሳም ሂጃብ ላለማድረግ ተገድጃለሁ፤ ምክንያቱም ለኑሮ የሚያስፈልጉኝን ወጪወች ለማግኘት መስራት ይኖርብኛል ። በማለት ሀሳቧን ትገልፃለች !

●ውድና የተከበርሽው እህቴ ! የሚከተሉትን የቁርአን አንቀፆች እንመልከት ጌታችን አላህﷻ እንድህ ይላል፦

وَفِى ٱلسَّمَآءِ رِزْقُكُمْ وَمَا تُوعَدُونَ
«ሲሳያችሁም የምትቀጠሩትም (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ውስጥ ነው»፡፡
.
إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلرَّزَّاقُ ذُو ٱلْقُوَّةِ ٱلْمَتِينُ
«አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው»፡፡

↬እንግድህ ሙስሊም ነን እስካልንና የሁሉንም ፍጡራን ሲሳይ የሚሰጠው አላህ ነው ብለን ካመንን ዘንዳ ሲሳያችን ከየት ይመጣልናል ብለን  ለምን ይሆን የምንጨነቀው !

ሁሌም ቢሆን የሰጭውን ( የአላህን) በር ማንኳኳትና ሲሳያችንን እንድለግሰን መጠየቅ ይኖርብናል ፤ አላህ ሁሉን  ሲሳያችንን እንድለግሰን በማሰብ ከማንም ፍጡር ምንም ነገር መከጀል የለብንም፤ የአላህን  በር ለማንኳኳት ደግሞ ራሳችንን ለእርሱ ማስገዛትና ትእዛዙን ማክበር የግድ ይለናል ፤ ከዚጋ ሌላው ማወቅ ያለብን ነገር አላህ ወደዚች ምድር ሲያመጣን ለኑሮ የሚያስፈልጉንን ነገሮች አሟልቶ በመስጠት መሆኑን ነው።

↳ተወዳጁ ነብይ (ﷺ) እንድህ ይላሉ፦
" ማንኛዋም ነፍስ በዚህ አለም የምትቆይበትን ጊዜ ሳትጨርስና የተወሰነላትን ሲሳይ (ሪዝቅ) ሳታጠናቅቅሞት አያገናትም" ።

↬የሲሳያችንን(ሪዝቅ) በር ይከፍታሉ የሚባሉ ሌሎች ሰበቦች ካሉ ተቅዋ ( አላህን መፍራት) እና ትእዛዛቱን በሚገባ መከተል ናቸው ፤ ከዚህ ውጭ ግን ከፍጡራን አንዱን በማስደሰትና የፈጣሪን ትዕዛዝ ወደ ኋላ በማድርግ የሚገኝ አንዳች ሲሳይ የለም።

አላህ (ﷻ) እንድህ ይላል ፦

وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ ٱلْقُرَىٰٓ ءَامَنُوا۟ وَٱتَّقَوْا۟ لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَٰتٍۢ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ وَلَٰكِن كَذَّبُوا۟ فَأَخَذْنَٰهُم بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ۞
የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው፡፡

●በሀድሰል ቁዱስ አላህ (ﷻ) እንድህ ይላል፦

"አንተ የአደም ልጂ ሆይ! በስልጣን ላይ ስላሉ ሰወች አትፍራ ፤ የእኔ ንግስና እስካሁንም አለና ።የሲሳይህን መዘግየት እያየህ ስጋት አይደርብህ ፤ የእኔ ሃብት ተዝቆ አያልቅምና፤ የአደም ልጂ ሆይ! ሁሉንም ነገሮች የፈጠርኩት ላንተ ነው፤ አንተን ደግሞ የፈጠርኩህ ለእኔ ብቻ ነው። የኔን መንገድ ብትጠብቅና ታዛዥ ብትሆን ሁሉም ነገር አንተን ይከተላል።"

➫እንግድህ ውድ እህቴን የምመክረው የአላህን
ትእዛዝ በማክብርና  እርሱን በማስደሰት መንገድ ላይ አዘውትሪ በማለት ነው። እንድህ የምታደርጊ ከሆነ ሁሉም ነገር ይታዘዝሻል፤ እንድሁም ምርጥ የሆነውን ሲሳይ (ሪዝቅ) ከማታስቢው አቅጣጫ አላህ ይሰጥሻል። የአለማት ጌታ እና አስተናባሪ የሆነው አላህ እንድህ ይላል

وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجْعَل لَّهُۥ مَخْرَجًۭا
አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡

📝ይ.ቀ.ጥ.ላ.ል.......
𝐓𝐞»t.me/https_Asselfya
ከሽርክ መዳኛ ሰበቦች
Daru tewhid
አዲስ ሙሀደራ

ከሽርክ መዳኛ ሰበቦች....!?

ዛሬ ሻዕባን 1/1445 በፉሪ ሰልሰቢል መስጂድ የቀረበ ምክር

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

~ t.me/Darutewhide
~ዋጋህን የምታውቅ ከሆነ
ማንም እንዲያረጋግጥልህ
አትጠብቅ!

~
👍1
👉~ጠንካራ ሴት የሚያደርጉሸ ነገሮች....!

~ጠንካራ ሴት ሁለየም በስሜቷ በጊዜዋ በማንነቷ ላይ አንድ ሠዉ እንድጫወት አትፈቅድም። እንድሁ መርዛማ ሰዎችን በቀላሉ መለየት ትችላለች ሁለየም ትኩረቷ እራሷን ማሻሻል የተሻለን ነገን መገንባት ላይ ነዉ። #እሚጠቅሟትን ነገሮችን ታነባለች አዳድስ እዉቀቶችን ትገበያለች። ብቻ ከትላንቱ ዛሬ ከዛሬ ነገ ከፍ ያለ ሰብእና እሚያላብሷትን ነገሮች አላማቋረጥ ታደርጋለች።

~ጠንካራ ሴት የለዉጥ ስሜት አላት.
ዉጤታማ አወንታዊ ናት ለለዉጥ ያጎፈረችና ዉጤታማነትን ለመጨመር ጊዜዊ እንቶ ፈንቶ እንድባክን አታደርግም። #አስቸጋሪና መጥፎ ጊዜያቶች ሲገጥሟት ነገሮችን አወንታዊ ጎኖችን ተመልክታ እንደት ማለፍ እንዳለባት ጠቅቃ ታዉቃለች።

t.me/https_Asselfya
Audio
✅ ጣፋጭ ቂርአት !

t.me/https_Asselfya

~ከቁርአን በላይ ጣፋጭ የለም!
~አላህ ሆይ
  ብትቀጣኝ እኔ ለዚህ የተገባሁ ነኝ፤
ይቅር ብትለኝ  አንተ ለዚህ የተገባህ ነህ”!!
 

ኢላሂ .....
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
📍⁽የሒጃብ ጥፍጥና⁾                 { እና } ⁽❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾ ➟ክፍል ሶስት ▪ስለሒጃብ በሶስተኛነት ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ 👉ሌላኛዋ እህታችን ደግሞ ! "በኢስላም ሾል (ከስብ) ከአምልኮ ተግባር ይቆጠራል ተብሏል ፤ ስራን መፈለግ ደግሞ ኢስላማዊ ግደታ ነው ፤ሂጃብ ለብሶ የስራን ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ጉዳይ ነው በዚህ የተነሳም ሂጃብ ላለማድረግ ተገድጃለሁ፤ ምክንያቱም…
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Photo
📍የሒጃብ ጥፍጥና⁾
   {
እና }
⁽
❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾

➟
ክፍል አራት

▪
ስለሒጃብ በአራተኛነት ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ

~
ሌላዋ እህታችን ደግሞ "ባለቤቴና ወላጆቸ ሂጃብ እንድለብስ ፈፅሞ አይፈቅዱልኝም "፤ሙስሊም እስከሆንኩ ድረስ የእነርሱን ትእዛዝ ደግሞ ማክበር ግደታ አልፕብኝ በሚል ሀሳብ ትሞግታለች ።

↘️ቤተሰቦችንና ባለቤትሽን መታዘዝን በተመለከተ አንቺ በትክክለኛው ሁኔታ ላይ ያለሽ መሆኑ ይታወቃል። ምክንያቱም ባልንና ወላጆችን መታዘዝና ማክበርሽ የሚያሳየው ለአላህና_ለመልእክተኛውለያለሽን ጥልቅ ፍቅርና ይህን ግደታ የሆነ የእምነት አካል ለመፈፀም ቁርጠኛ መሆንሽን በተግባር ማሳየት መቻልሽን ነው ፤
እዚ  ላይ የሚነሳው ዋነኛ ጥያቄ"አንድት ሴት እነኝህን አካላት (ባልንና ወላጆችን) እስከምን ድረስ ነው ልትታዘዛቸውና የነርሱን ፍቃድ ልትሞላ የምትችለው ?" የሚል ይሆናል ። በማንኛውም  የህይወት እንቅስቃሴያችን እነዚህን  ክፍሎች በጭፍን መታዘዝ ይኖርብናልን ❓
የእነርሱን ትእዛዝ  ስናከብር የምንኖረው እስከ ምን ድረስ ነው ? ለዚህ አብይና ወሳኝ የሆነ  ጥያቄ ነብዩ () መልስ አላቸው ።እንደሚከተለው ተናግረዋን ፦ "የፈጣሪን ትእዛዝ በመጣስ ለፍጡር መታዘዝ የለም " {እህመድ እና ሀኪም}
➽ከዚ በተጨማሪ ማወቅ  ያለብሽ  ጉዳይ የነዚህን ቤተሰቦችሽን ትእዛዝ የፈጣሪሽን ትእዛዝ ለማክበር በማሰብ መጣስሽ ከፈጣሪሽ ጋ ያለሽን ቀረቤታ  በጣም የሚያሻሽለው  ከመሆኑም በላይ እነርሱንም የአላህን ትእዛዝ እንድጠብቁ ሊያነቃቃቸውና ሊያስገነዝባቸው ስለሚችል ጉዳዩ በሁሉም አቅጣጫ በጎ የሆኑ ገፅታወች ሊኖሩት ይችላል ።

👉
እዚ ላይ ለወላጆችና ለባሎች ልባዌ ከሆነ ምክራችን ጎን  ለጎን የምንጠይቃችሁ ነገር ሴት ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን በተመለከተ ሀያል የሆነውን የዓለማት ጌታ አላህን ፍሩ ፤ እናተ እነዚህን በስራችሁ  የሚገኙ ሴቶች ከተጋጋመው መቀጣጠያዎቹ ሰውና ድንጋይ ከሆነው አስፈሪ የጀሀነም እሳት ልትጠብቋቸው ግደታ አለባችሁ

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًۭا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٌۭ شِدَادٌۭ لَّا يَعْصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡

(
አል ተህሪም ፡ 6)

➡️
በተጨማሪም ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም አባቶችንና  ባሎችን (በአጠቃላይ በስራችው ሰወችን የሚያስተዳድሩ  ጠባቂወችን) በሚመለከት የተናገሩትን ማጤን ይኖርባችሁል።እንድህ ብለዋል ፦ " ...አባወራ ለቤተሰቡና በስሩ ለሚገኙ ጠባቂ ነው፤ ነገ በፍርዱ ቀን ስለነርሱ ይጠየቃል" ።{ቡኻሪ}

➫
እህቴ ሆይ ! አላህ ()  ልብሽን ለእምነትና ሀቅን ለመቀበል ይክፈትልሽ ፤ ወደ ቀናው መንገድም ምትመሪ ያድርግሽ ።

ይ.ቀ.ጥ.ላ.ል.......
𝐓𝐞»t.me/https_Asselfya
ልብህን ንፁህ አድርግ
~
አንድ ሰው ወደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድረዲየሏሁ ዓንሁ ዘንድ መጣና  እገሌ ሚባል ሰው ሰድቦሀል አለው።ኻሊድም:-ያ "ስራው ሚሰፍርበት መዝገቡ ነው ።በሚፈልገው ነገር ይሙላው "ብሎ መለሰለት።

አንድ ሰውዬ ለወህብ ኢብኑ ሙነቢህ "እንትና ሚባል ሰው ሰደበህ "ብሎ ነገራቸው።እሳቸውም:-"ሸይጧን ካንተ ውጪ ሌላ መልእክተኛ አላገኘም እንዴ?" ብለው መለሱለት።

አንዱ ለሌላ ሰውዬ "እገሌ ሚባል ሰው ሰደበህ"አለው።ሰውየውም:-ተሳዳቢው የወረወረው ቀስት አላገኘኝም።አንተ ለምን ልቤ  ላይ ትተክለዋለህ" አሉት።

አንድ ሰውዬ ለኢማ ሻፊዕይ :-እገሌ ሚባል ሰው በክፉ ያነሳሀል "አላቸው።እሳቸውም "እውነትህ ከሆነ አንተ(ነማም)ወሬ አዋሳጅ ነህ።እየዋሸህ ከሆነ ደግሞ(ፋሲቅ)አመፀኛ ሰው ነህ "ብለው መለሱለት።