💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
#ተበድሎና ተገፍቶም ፈገግታው ከፊቱ
የማይጠፋ ሰው በጣም ጠንካራ ነው!
~
✅ የእናትሸ ልጅ የማያዉቀዉን ሚስጥር ለባእድ ወንድ ስነግሪ የዛኔ ነዉ የረከሸዉ !!
⭕️👉ይድረስ እንደ <መርየም መመረጥን> ለምትሹ ለውድ ሙእሚን እህቶቸ ሁሉ....!

~እኔ እንዴት እንደመርየም እመረጣለሁ ብለሽ እያሰብሽ ነው አይደል??? አንቺ ያለአባት ልጅ ትወልጃለሽ ማለት አይደለም። ወይም ኢሳ ዐለይሂ ሰላም ባንቺ ማህፀን ድጋሚ ይወላዳል ማለት አይደለም ነገር ግን እንደ መርየም የአላህ ሱብሀነሁ ተአላ ምርጥ ባሪያ ሆነሽ መመረጥ ትችያለሽ!!

~#ውዷ እህቴ አትጠራጠሪ ጌታሽ ዘንድ ምርጥ ባሪያው ሆነሽ መመረጥ ትችያለሽ። ነገር ግን ምርጫው በዘፈቀደ ሳይሆን በመስፈርት ነው።መስፈርቱ ምን ይሆን???
ቀድመን የጌታችንን ቃል እንመልከት፦

▪️ﻭَﺇِﺫْ ﻗَﺎﻟَﺖِ ﭐﻟْﻤَﻠَٰٓﺌِﻜَﺔُ ﻳَٰﻤَﺮْﻳَﻢُ ﺇِﻥَّ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﭐﺻْﻄَﻔَﻯٰﻚِ ﻭَﻃَﻬَّﺮَﻙِ ﻭَﭐﺻْﻄَﻔَﻯٰﻚِ ﻋَﻠَﻰٰ ﻧِﺴَﺂﺀِ ﭐﻟْﻌَٰﻠَﻤِﻴﻦَ @ ﻳَٰﻤَﺮْﻳَﻢُ ﭐﻗْﻨُﺘِﻰ ﻟِﺮَﺑِّﻚِ ﻭَﭐﺳْﺠُﺪِﻯ ﻭَﭐﺭْﻛَﻌِﻰ ﻣَﻊَ ﭐﻟﺮَّٰﻛِﻌِﻴﻦَ

# <መላእክትም ያሉትን (አስታዉስ)
መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጸሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡# መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፡፡ ስገጂም፡፡ ከአጎንባሾቹም ጋር አጎንብሺ፡፡»

{ኢምራን ፡42-43}


በአለም ላይ መርየምን የሚያክል እንስት የለም።የእንስቶች ሁሉ አውራ ናት። እዚህ ደረጃ ላይ እንዴት ልትደርስ ቻለች? ምክንያቶቹ ሁለት አንደሆኑ ዑለሞች ተናግረዋል፦

➊ አላህን በፅናት የምታመልክ መሆኗ
➋ ራሷን ከብልግና ተግባራት የጠበቀች መሆኗ ነው።


~#እህቴ ሆይ! እንደመርየም የተመረጥሽ እንስት ለመሆን በነዚህ ሁለት ባህሪያት አርአያነቷን ተከተይ። በዒባዳሽ ላይ በርቺ ብልትሽንም ከሀራም ጠብቂ።
አላህ ኢንዲመርጥሽ ከፈለግሽ በፅናት አምልኪው።ከሰጋጆች ጋር አብረሽ ስገጂ። ዒባዳ ላይ በርቺ። በጎ ስራን አብዢ። ጊዜሽን ፤ጉልበትሽን ፤እውቀትሽንና ገንዘብሽን አላህ ለሚወደው ተግባር አውዪ።
#መርየም የተመረጠችበት ሁለተኛው መስፈርት በቀጣዩ የቁርአን አንቀፅ ውስጥ ሰፍሯል፦

▪️ﻭَﻣَﺮْﻳَﻢَ ﭐﺑْﻨَﺖَ ﻋِﻤْﺮَٰﻥَ ﭐﻟَّﺘِﻰٓ ﺃَﺣْﺼَﻨَﺖْ ﻓَﺮْﺟَﻬَﺎ ﻓَﻨَﻔَﺨْﻨَﺎ ﻓِﻴﻪِ ﻣِﻦ ﺭُّﻭﺣِﻨَﺎ ﻭَﺻَﺪَّﻗَﺖْ ﺑِﻜَﻠِﻤَٰﺖِ ﺭَﺑِّﻬَﺎ ﻭَﻛُﺘُﺒِﻪِۦ ﻭَﻛَﺎﻧَﺖْ ﻣِﻦَ ﭐﻟْﻘَٰﻨِﺘِﻴﻦَ

~#የዒምራንን ልጅ መርየምን ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች(አመነች)፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡

{ተህሪም ፡12}


~ስለዚህ በአላህ ለመመረጥ ብልትሽን ከዝሙት መጠበቅ ይገባሻል ። ምክንያቱም ንፅህና ወሳኝና የማንነት መገለጫ ነውና!!!

t.me/https_Asselfya
ስኬት ማለት፦ ከችግር ቡሃላ ድሎት መኖሩን ማረጋገጥ ነዉ።

~
ዐይንህ ሲደርቅ በቁርአን አርሰው፣
ወገብህ ሲገር በሱጁድ አለስልሰው፣
ቀልብህ ሲደርቅ በሞት አስታውሰው።

.
ከቁርአን ጋር ያረጀች ዐይን አቤት ማማሯ!
ከቁርአን ጋር የኖረች ዐይን አቤት ብርሃኗ!
በቁርአን የተኳለች ቅንድብ አቤት ዉበቷ!
.
t.me/https_Asselfya
Audio
AudioLab
🍃▫️ آيات السكينة ▫️🍃
👉ከቁርአን በላይ ጣፋጭ የለም

~
Forwarded from Abul Abas Nasir || معلم القرآن
📣 የሙሀደራ ዝግጅት
     〰〰〰〰〰〰

የእለቱ ተጋባዥ እንግዶች

1⃣ Abu Imran  ( ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር)
↘️https://t.me/Muhammedsirage

2⃣ Ibnu Munewor ( ሙሐመድ አህመድ ሙነወር)
↘️https://t.me/IbnuMunewor

3⃣ Abul Abas ( ናስር ሙሐመድ) 
↘️https://t.me/kurantejwid


የሙሀደራው ቀን እና ሰአት
↪️ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 3 ከ ጠዋቱ 3:30 ጀምሮ

አድራሻ:  ፉሪ 20 M መግቢያ ፊትለፊት ሰልሰቢል መስጂድ

Live የሚለቀቅበት ቻናል
https://t.me/furiselsebla
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Photo
📍የሒጃብ ጥፍጥና⁾
                { እና }
⁽❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾

👉🔖ክፍል አንድ

▪ስለሒጃብ የመጀመሪያው ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ

⓵.
የእኔ ንፅሕና እና መልካም ስራዬ የሚገለፀው ሒጃብ በማድረጌ ሣይሆን በአለኝ ጥሩ ፀባይ ነው። ለምሣሌ፦ ብዙ ሂጃብ . ኒቃብ .ጅልባብ የሚያደርጉ ታላላቅ የሚባሉ ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሴቶች ያሉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሒጃብ ሣያደርጉ/ሣይለብሱ ጥሩ ፀባይ እና ከፍተኛ ስነምግባር ያላቸው ሴቶች አሉ! የሚል አስተሣሰብ አራማጅ መሆን ነው።

↘️ይህ አይነት እስተሳብ ላለን እህቶች መልስ፦
▪
ሂጃብ መልበስ ንፅህናና ጨዋነት ተጠቃለው የሚሟሉበት ደንብ ወይም ህግ አይደለም ። ንፅህናና ጥሩ ስነ-ምግባር በኢስላማዊ ሸሪዓ ግደታወች ሲሆኑ በዚህም ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ሊያሟሉዋቸውና ሊተገብራቸው ግድ ነው።ሆኖም እነዚህን የማሟላቱ ሂደት ሂጃብ በመልበስ እና ባለመልበስ ላይ የተመካ አይደለም።ስለሆነም ሂጃብ የለበሰች እንስት መጥፎ ነገር ⁽⁽ወንጀል⁾⁾ ብትሰራና ያለበሰችዋ ቁጥብ ልትሆን ብትችል አያስገርምም።በእርግጥ ሂጃብ የለበሰች እንስት ከማትለብሰው ለተሻሉ የስነ- ምግባር እሴቶች የቀረበች መሆኑን ሊጤን የሚገባው መሆኑ እንዳለ ነው።

●በሌላ በኩል ደግሞ ሂጃብን መልበስ ውጫዊ የሆነና ሴቶች ብቻ ሊያሟሉት የሚገባ #መለኮታዊ ትእዛዝ ነው ። ንፅህና እና ጨዋነት ሂጃብ ለመልበስ እንደ ብቸኛ ቅድመ ሁኔታ መታየት እንደሌለባቸው ሁሉ ሂጃብ መልበስም ለንፅህናና ጨዋነት ቅድመ ሁኔታ ሆኖ ሊቀርብ አይገባም።ነገር ግን #ሂጃብ_መልበስ_በንፅህና_ለመቆየትና_ለጨዋነት_ለመልካም ስነ -ምግባር የመጀመሪያው  ደረጃ ነው ማለት እንችላለን።

●ከዚህም በተጨማሪ ሂጃብ ወንዶች# የሴቶችን ውበት እንዳይመለከቱና በተለይ ደግሞ የተለያዩ ሴት ልጅ ምትጠቀምባቸውን መዋቢያወች (cosmetics) ጌጣጌጦች እንድሁም አላስፈላጊ አለባበሶች በማየት ወደ መጥፎ ሁኔታ እንዳይገቡ የሚከላከል መሆኑን መገንዘብ አለብን።

زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ ٱلشَّهَوَٰتِ مِنَ ٱلنِّسَآءِ وَٱلْبَنِينَ وَٱلْقَنَٰطِيرِ ٱلْمُقَنطَرَةِ مِنَ ٱلذَّهَبِ وَٱلْفِضَّةِ وَٱلْخَيْلِ ٱلْمُسَوَّمَةِ وَٱلْأَنْعَٰمِ وَٱلْحَرْثِ )آل عمران14
«ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆችም፣ ከወርቅና ከብር፣ ከተካመቹ ገንዘቦችም፣ ከተሰማሩ ፈረሶችም፣ ከግመል ከከብትና ከፍየልም፣ ከአዝመራም የኾኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመ፡፡»

●ሴቶችን መውደድ በመጀመሪያ የተጠቀሰበት ምክኒያት የሴቶች ውበት አላህﷻ በወንድ ልጅ መንገድ ላይ ያስቀመጠው የመጀመሪያው የፈተና መሰናክል በመሆኑ እንጂ በሌላ አይደለም ። ለዚ ታላቅ የሆነ ፈተና ያለው ብቸኛ መፍትሄ ሴቶች ሂጃብ እንዲለብሱ ማድረግ ሲሆን ይህም ወንዶችንና ሴቶችን እኩል በሆነ ሁኔታ የሚጠበቅባቸው መለኮታዌ እንክብካቤ ነው።ሴት ልጅ ደንቡን ጠብቃ ሂጃቧን ምትለብስ ከሆነ በማህበረሰቡ ውስጥ ለፆታዌ ፍንገጣ የሚደረጉ ወንዶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ የሥነ -ምግባር ዝቅጠትን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና መጫወት ትችላለች ።
منقول
📝ይ.ቀ.ጥ.ላ.ል.......
𝐓𝐞»t.me/https_Asselfya
Forwarded from 20 ሞክሮች ለእህቴ ከማግባትዋ በፊት
ባል እሺ የምትልና ከሱ ሀሳብ  ቀደም ቀደም የማትልን ሚስት ይበልጥ  ይወዳል

ስለዚህ ሚስት ሆይ እሺ ማለትን ሊመጂ ትዳርሽ ሰላም ይሆናል
ሙሐደራ 189 ረድ በወሰን ተላላፊዎች ላይ ክፍል 1
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ሙሓደራ ክፍል 189

አዲስ ሙሓደራ ክፍል 01

ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ

የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇

““የ አብዱል ሀሚድ አልለተሚይ እና  ሁሰይን ሙሀመድ ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““

🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed
✅ እንዴት ነው ውጤታማ የምትሆኑት?

~.በጥቂቱ አውሪ
~.በደንብ አስተውሉ
~.ተረጋጉ
~.ቁጥብ ሁኑ
~.ከመናገራችሁ
በፊት አስተውሉ
~.ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙ
~.ሌሎችን አክብሩ
~.ለመታየት አትቸኩሉ

~
t.me/https_Asselfya
~አንድ ቀን በእድሜው እጅግ የገፋ፣ሽፋሽፍቱ የወረደ፣ወገቡ የጎበጠ፣ሽማግሌ ዱላውን ተደግፎ እየተጎተተ የአላህ መልእክተኛ(ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጣና «የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ትንሽ ትልቅ ሳይል ወንጀልን የተባለን በሙሉ አንድም ሳያስቀር የሠራ ሰው እጣ ፈንታው ምንድነው?» አላቸው፡፡ ቀጠል አደረገና «ወንጀሉ በምድር ላይ ላሉ ሰዎች በሙሉ ቢከፋፈል ሰዎችን የሚያጠፋ ዓይነት የዚህ ዓይነቱ ሰው ተውባ ይኖረዋልን? የአላህንስ ምህረት ያገኛልን?» አላቸው፡፡ ነቢዩም (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ) «ሰልመሃልን?» አሉት፡፡ ሰውየውም «እኔማ ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ አምላክ የሌለ ስለመሆኑና አንቱም የአላህ መልእክተኛ መሆንዎትን እመሰክራለሁ፡፡» አላቸው፡፡

እርሳቸውም «መልካምን ነገር ትሰራለህ፤ ከመጥፎ ነገር ትርቃለህ፤ በዚህም አላህ ሁሉንም ነገር በመልካም መዝገብ ላይ ይፅፍልሃል፡፡» አሉት፡፡ ሰውየውም «ክህደቴንና ጥመቴን ሁሉ!» አላቸው፡፡ እርሳቸውም «አዎን ክህደትህንና ጥመትህን ሁሉ!» አሉት፡፡ ሰውየው ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስተኛ ሆኖ «አሏሁ አክበር! አሏሁ አክበር!» እያለ ሄደ፡፡ ከርሣቸው ዐይን እስኪሰወር ድረስ ይህንኑ ቃል ይደጋግም ነበር፡፡

•አሁን ጭንቀታችሁ ሲረግብ ይታየኛል፡፡ ኢንሻአላህ ይረግባል፡፡ አላህ ሆይ ጭንቀትን አርቅልን፡፡የደስታ ኑሮም አኑረን!
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan
አንዳንድ የ አረቦች ቂቢላ ዘንድ ተለምዶ የሆነ ሰው ሲጠራቸው አቤት ሲሉ " ለቤህ " እሚባል አቤት አባባል አለ

እዚህ ላይ ተጠንቀቁ እህቶች ይህ ለ ሙህሪም እና ሴት ለሴት ብቻ ነው መባባል እሚቻለው

ምክንያቱም የ ውዴታ መግለጫ አቤት አባባል ስለሆነ

ይህን አረቦቹ ያውቁታል ስለዚህ የውጭ ሴቴች ለውጭ ወንዶች አይጠቀሙትም " ሰም ወይም ስሚ " ነው እሚሉት

የኛወቹ እንታረም
قال العلامة مقبل الوادعي ࢪحمه الله :

لو ڪان الطلاق بأيدي بعض النِّساء لطلقت زوجها في اليو۾ عشࢪين مـࢪة.

[ ڪتاب غاࢪة الأشࢪطة ٢/ ٢١٨].🌱