💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
✅ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ወርቃማ ንግግሮች ውስጥ፣

~ወጣት ሆይ ወጣትነትህን ተጠቀም። እራስህን አድን። ሀላፊነትህን ተወጣ። አርአያዎችህን ለይ።

~ቀና_በል_በተውሂድ። ከሺርክ ሰፈር አትልከስከስ!!

~ወጣት ሆኖ ለሺርክ ጠበቃ ለተውሂድ ግን ጠላት ሲሆን ማየት ምነኛ ልብ የሚያደማ ነው ?!ምነኛ የሚያሳፍር ነው ⁉️

📚 ተውሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ" ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ!!


t.me/https_Asselfya
~ፈገግ በሉ

ፈገግታ ሱና ነዉ።

ሌባና ሴቶች ዘዴ አያጡም ይላል ያገሬ ሰዉ...የሌባዉ ግን አትሻብኝ
~ውዷ  እህቴ  ሆይ!  ባለሽ ተብቃቂ።
#አመስጋኝ ሁኝ  ከበላይሽ ያሉትን ሳይሆን በታችሽ  ያሉትን  ተመልከቺ ! 

~አንቺ  ያገኝሺውን  ያላገኙ አሉና።
ባለቤትሽ ምን ላደረገልሽ  ሁሉ  አመስግኝው


ምን አድርገህልኛልና  አትበይው ልብ በይ..

✅ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ።

ባሏን የማታመሰግንና በሱ የማትብቃቃ ሴት የውመልቂያማ አላህ ወደሷ አይመለከትም።

📚صحيح الترغيب - رقم: (1944)
~
t.me/https_Asselfya
የለተሞ መንጋ
~
እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ! ምናልባትም እንዲህ ዓይነቱ ቡድንተኝነት የወለደው ከንቱ ሙገሳ ይሆናል ልባቸውን አሳብጦ ገደል እየከተታቸው ያለው። አንደኛውንም "ሸይኹል ኢስላም" እያሉት እንደሆነ ሰምቼ ነበር። እውነት ይሆን?
ከቅጥፈቱ በላይ የገረመኝ ጠሀ ኸዲር ይህንን አሳፋሪ ወሬ ቁም ነገር አድርጎ መለጠፉ ነው። ሰዎቹ ግን እኛ ከምንገምታቸውም በጣም የራቁ ናቸው።
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
‏ﻗﺎﻝ ﺍﻟﺤﺎﻓﻆ ﺍﻟﻤﺰﻱ ﺭﺣ ﺍﻟﻠﻪ :

"ﻭﻟﻮ ﺳﻜﺖ ﻣﻦ ﻻ ﻳﺪﺭﻱ ﻻﺳﺘﺮﺍﺡ ﻭﺃﺭﺍﺡ ﻭﻗﻞ ﺍﻟﺨﻄﺄ ﻭﻛﺜﺮ ﺍﻟﺼﻮﺍﺏ"
تهذيب ﺍﻟﻜﻤﺎﻝ (362/4)


~አላዋቂ ዝም ቢል ኖሮ ለራሱም አርፎ ሰዎችንም ያሳርፍ ነበር እንዲሁም ትክክለኛው በዝቶ ስህተቱ ያንስ ነበር።

~
~አላህ ሆይ!!
~መልካም ነገር ሲያገኙ ከሚያመሠግኑ
~ችግር ሲገጥማቸዉ ከሚታገሱ

~ወንጀል ላይ ሲወድቁ ፈጥነዉ ምህረት ከሚጠይቁ ባሮችህ አድርገኝ።

~
#ተበድሎና ተገፍቶም ፈገግታው ከፊቱ
የማይጠፋ ሰው በጣም ጠንካራ ነው!
~
✅ የእናትሸ ልጅ የማያዉቀዉን ሚስጥር ለባእድ ወንድ ስነግሪ የዛኔ ነዉ የረከሸዉ !!
⭕️👉ይድረስ እንደ <መርየም መመረጥን> ለምትሹ ለውድ ሙእሚን እህቶቸ ሁሉ....!

~እኔ እንዴት እንደመርየም እመረጣለሁ ብለሽ እያሰብሽ ነው አይደል??? አንቺ ያለአባት ልጅ ትወልጃለሽ ማለት አይደለም። ወይም ኢሳ ዐለይሂ ሰላም ባንቺ ማህፀን ድጋሚ ይወላዳል ማለት አይደለም ነገር ግን እንደ መርየም የአላህ ሱብሀነሁ ተአላ ምርጥ ባሪያ ሆነሽ መመረጥ ትችያለሽ!!

~#ውዷ እህቴ አትጠራጠሪ ጌታሽ ዘንድ ምርጥ ባሪያው ሆነሽ መመረጥ ትችያለሽ። ነገር ግን ምርጫው በዘፈቀደ ሳይሆን በመስፈርት ነው።መስፈርቱ ምን ይሆን???
ቀድመን የጌታችንን ቃል እንመልከት፦

▪️ﻭَﺇِﺫْ ﻗَﺎﻟَﺖِ ﭐﻟْﻤَﻠَٰٓﺌِﻜَﺔُ ﻳَٰﻤَﺮْﻳَﻢُ ﺇِﻥَّ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﭐﺻْﻄَﻔَﻯٰﻚِ ﻭَﻃَﻬَّﺮَﻙِ ﻭَﭐﺻْﻄَﻔَﻯٰﻚِ ﻋَﻠَﻰٰ ﻧِﺴَﺂﺀِ ﭐﻟْﻌَٰﻠَﻤِﻴﻦَ @ ﻳَٰﻤَﺮْﻳَﻢُ ﭐﻗْﻨُﺘِﻰ ﻟِﺮَﺑِّﻚِ ﻭَﭐﺳْﺠُﺪِﻯ ﻭَﭐﺭْﻛَﻌِﻰ ﻣَﻊَ ﭐﻟﺮَّٰﻛِﻌِﻴﻦَ

# <መላእክትም ያሉትን (አስታዉስ)
መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጸሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡# መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፡፡ ስገጂም፡፡ ከአጎንባሾቹም ጋር አጎንብሺ፡፡»

{ኢምራን ፡42-43}


በአለም ላይ መርየምን የሚያክል እንስት የለም።የእንስቶች ሁሉ አውራ ናት። እዚህ ደረጃ ላይ እንዴት ልትደርስ ቻለች? ምክንያቶቹ ሁለት አንደሆኑ ዑለሞች ተናግረዋል፦

➊ አላህን በፅናት የምታመልክ መሆኗ
➋ ራሷን ከብልግና ተግባራት የጠበቀች መሆኗ ነው።


~#እህቴ ሆይ! እንደመርየም የተመረጥሽ እንስት ለመሆን በነዚህ ሁለት ባህሪያት አርአያነቷን ተከተይ። በዒባዳሽ ላይ በርቺ ብልትሽንም ከሀራም ጠብቂ።
አላህ ኢንዲመርጥሽ ከፈለግሽ በፅናት አምልኪው።ከሰጋጆች ጋር አብረሽ ስገጂ። ዒባዳ ላይ በርቺ። በጎ ስራን አብዢ። ጊዜሽን ፤ጉልበትሽን ፤እውቀትሽንና ገንዘብሽን አላህ ለሚወደው ተግባር አውዪ።
#መርየም የተመረጠችበት ሁለተኛው መስፈርት በቀጣዩ የቁርአን አንቀፅ ውስጥ ሰፍሯል፦

▪️ﻭَﻣَﺮْﻳَﻢَ ﭐﺑْﻨَﺖَ ﻋِﻤْﺮَٰﻥَ ﭐﻟَّﺘِﻰٓ ﺃَﺣْﺼَﻨَﺖْ ﻓَﺮْﺟَﻬَﺎ ﻓَﻨَﻔَﺨْﻨَﺎ ﻓِﻴﻪِ ﻣِﻦ ﺭُّﻭﺣِﻨَﺎ ﻭَﺻَﺪَّﻗَﺖْ ﺑِﻜَﻠِﻤَٰﺖِ ﺭَﺑِّﻬَﺎ ﻭَﻛُﺘُﺒِﻪِۦ ﻭَﻛَﺎﻧَﺖْ ﻣِﻦَ ﭐﻟْﻘَٰﻨِﺘِﻴﻦَ

~#የዒምራንን ልጅ መርየምን ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች(አመነች)፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡

{ተህሪም ፡12}


~ስለዚህ በአላህ ለመመረጥ ብልትሽን ከዝሙት መጠበቅ ይገባሻል ። ምክንያቱም ንፅህና ወሳኝና የማንነት መገለጫ ነውና!!!

t.me/https_Asselfya
ስኬት ማለት፦ ከችግር ቡሃላ ድሎት መኖሩን ማረጋገጥ ነዉ።

~
ዐይንህ ሲደርቅ በቁርአን አርሰው፣
ወገብህ ሲገር በሱጁድ አለስልሰው፣
ቀልብህ ሲደርቅ በሞት አስታውሰው።

.
ከቁርአን ጋር ያረጀች ዐይን አቤት ማማሯ!
ከቁርአን ጋር የኖረች ዐይን አቤት ብርሃኗ!
በቁርአን የተኳለች ቅንድብ አቤት ዉበቷ!
.
t.me/https_Asselfya
Audio
AudioLab
🍃▫️ آيات السكينة ▫️🍃
👉ከቁርአን በላይ ጣፋጭ የለም

~
Forwarded from Abul Abas Nasir || معلم القرآن
📣 የሙሀደራ ዝግጅት
     〰〰〰〰〰〰

የእለቱ ተጋባዥ እንግዶች

1⃣ Abu Imran  ( ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር)
↘️https://t.me/Muhammedsirage

2⃣ Ibnu Munewor ( ሙሐመድ አህመድ ሙነወር)
↘️https://t.me/IbnuMunewor

3⃣ Abul Abas ( ናስር ሙሐመድ) 
↘️https://t.me/kurantejwid


የሙሀደራው ቀን እና ሰአት
↪️ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 3 ከ ጠዋቱ 3:30 ጀምሮ

አድራሻ:  ፉሪ 20 M መግቢያ ፊትለፊት ሰልሰቢል መስጂድ

Live የሚለቀቅበት ቻናል
https://t.me/furiselsebla
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Photo
📍የሒጃብ ጥፍጥና⁾
                { እና }
⁽❌ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤወች❌⁾

👉🔖ክፍል አንድ

▪ስለሒጃብ የመጀመሪያው ሚሰነዘር የተሣሣተ ግንዛቤ

⓵.
የእኔ ንፅሕና እና መልካም ስራዬ የሚገለፀው ሒጃብ በማድረጌ ሣይሆን በአለኝ ጥሩ ፀባይ ነው። ለምሣሌ፦ ብዙ ሂጃብ . ኒቃብ .ጅልባብ የሚያደርጉ ታላላቅ የሚባሉ ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሴቶች ያሉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሒጃብ ሣያደርጉ/ሣይለብሱ ጥሩ ፀባይ እና ከፍተኛ ስነምግባር ያላቸው ሴቶች አሉ! የሚል አስተሣሰብ አራማጅ መሆን ነው።

↘️ይህ አይነት እስተሳብ ላለን እህቶች መልስ፦
▪
ሂጃብ መልበስ ንፅህናና ጨዋነት ተጠቃለው የሚሟሉበት ደንብ ወይም ህግ አይደለም ። ንፅህናና ጥሩ ስነ-ምግባር በኢስላማዊ ሸሪዓ ግደታወች ሲሆኑ በዚህም ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ሊያሟሉዋቸውና ሊተገብራቸው ግድ ነው።ሆኖም እነዚህን የማሟላቱ ሂደት ሂጃብ በመልበስ እና ባለመልበስ ላይ የተመካ አይደለም።ስለሆነም ሂጃብ የለበሰች እንስት መጥፎ ነገር ⁽⁽ወንጀል⁾⁾ ብትሰራና ያለበሰችዋ ቁጥብ ልትሆን ብትችል አያስገርምም።በእርግጥ ሂጃብ የለበሰች እንስት ከማትለብሰው ለተሻሉ የስነ- ምግባር እሴቶች የቀረበች መሆኑን ሊጤን የሚገባው መሆኑ እንዳለ ነው።

●በሌላ በኩል ደግሞ ሂጃብን መልበስ ውጫዊ የሆነና ሴቶች ብቻ ሊያሟሉት የሚገባ #መለኮታዊ ትእዛዝ ነው ። ንፅህና እና ጨዋነት ሂጃብ ለመልበስ እንደ ብቸኛ ቅድመ ሁኔታ መታየት እንደሌለባቸው ሁሉ ሂጃብ መልበስም ለንፅህናና ጨዋነት ቅድመ ሁኔታ ሆኖ ሊቀርብ አይገባም።ነገር ግን #ሂጃብ_መልበስ_በንፅህና_ለመቆየትና_ለጨዋነት_ለመልካም ስነ -ምግባር የመጀመሪያው  ደረጃ ነው ማለት እንችላለን።

●ከዚህም በተጨማሪ ሂጃብ ወንዶች# የሴቶችን ውበት እንዳይመለከቱና በተለይ ደግሞ የተለያዩ ሴት ልጅ ምትጠቀምባቸውን መዋቢያወች (cosmetics) ጌጣጌጦች እንድሁም አላስፈላጊ አለባበሶች በማየት ወደ መጥፎ ሁኔታ እንዳይገቡ የሚከላከል መሆኑን መገንዘብ አለብን።

زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ ٱلشَّهَوَٰتِ مِنَ ٱلنِّسَآءِ وَٱلْبَنِينَ وَٱلْقَنَٰطِيرِ ٱلْمُقَنطَرَةِ مِنَ ٱلذَّهَبِ وَٱلْفِضَّةِ وَٱلْخَيْلِ ٱلْمُسَوَّمَةِ وَٱلْأَنْعَٰمِ وَٱلْحَرْثِ )آل عمران14
«ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆችም፣ ከወርቅና ከብር፣ ከተካመቹ ገንዘቦችም፣ ከተሰማሩ ፈረሶችም፣ ከግመል ከከብትና ከፍየልም፣ ከአዝመራም የኾኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመ፡፡»

●ሴቶችን መውደድ በመጀመሪያ የተጠቀሰበት ምክኒያት የሴቶች ውበት አላህﷻ በወንድ ልጅ መንገድ ላይ ያስቀመጠው የመጀመሪያው የፈተና መሰናክል በመሆኑ እንጂ በሌላ አይደለም ። ለዚ ታላቅ የሆነ ፈተና ያለው ብቸኛ መፍትሄ ሴቶች ሂጃብ እንዲለብሱ ማድረግ ሲሆን ይህም ወንዶችንና ሴቶችን እኩል በሆነ ሁኔታ የሚጠበቅባቸው መለኮታዌ እንክብካቤ ነው።ሴት ልጅ ደንቡን ጠብቃ ሂጃቧን ምትለብስ ከሆነ በማህበረሰቡ ውስጥ ለፆታዌ ፍንገጣ የሚደረጉ ወንዶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ የሥነ -ምግባር ዝቅጠትን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና መጫወት ትችላለች ።
منقول
📝ይ.ቀ.ጥ.ላ.ል.......
𝐓𝐞»t.me/https_Asselfya