💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
قال ابن مسعود: عليكم بالعلم قبل أن يُقبَض، وقبضهُ ذهابُ أهله، عليكم بالعلم فإنَّ أحدكم لا يدري متى يَفتَقر أو يُفتَقر إلى ما عنده.

• الجامع لابن وهب (١٣٧١)
✅"የአሏህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ አሉ፦

   እያንዳንዱ ወደ ሰላት የምትራመዳት áŠĽáˆ­áˆáŒƒ "ሶደቃ ምጽዋት" ናት❗️
         
~
~የአቡ ረይስ ተቀርተዉ ያለቁና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን ለማገኘት ጆይን በሉ !!

   ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/durus_abu_reyyis
https://t.me/durus_abu_reyyis

  
እናታችን ዓኢሻ (ረድየሏሃ ዓንሃ) እንዳስተላለፉት "የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ድዳቻው እስኪታይ ድረስ በጣም ሲስቁ አይቻቸው አላውቅም፡፡ ፈገግ ብቻ ነበር የሚሉት"፡፡

📒(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ጭብጥ‼️
~~~~
✍ሳቅ ልብን ያደርቃል፣ ሳቅ አለማብዛት ይወደዳል ምክንያቱም ሳቅ ማብዛት ከአላህ የመዘናጋት ምልክት ነውና፡፡

t.me/https_Asselfya
سريع القرارات اكثرهم ندماً
ብዙ የችኳላ ውሳኔዎች መጨረሻቸው ፀፀት ነው

~
Audio
✅ ቆንጆ ቲላዋ

«وَإِذَا قُرِئَ ٱلْقُرْءَانُ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥ وَأَنصِتُوا۟ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُون
Âť
«ቁርኣንን በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡»

=
👉📚የቁርአን ፊደሎች አጠቃላይ ሶስት መቶ ሀያ ሶስት ሺ ስድስት መቶ ሰባ አንድ (323٫671) ናቸው

👉📚ከቁርአን አንድ ፊደል የቀራ አስር ሀሰናት ወይም ምንዳ አለው

👉 📚ይህ ማለት አንድ ሰው ቁርአን ሲያከትም ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺ ሰባት መቶ አስር (3٫236٫710) ምንዳ ያገኛል ማለት ነው በአላህ ፍቃድ

📚የሙእሚን ጓደኛዉ ቁርአን ነዉና።ቆርጠን እንነሳ እንደት ይሄን ያክል ምንዳ እናሳልፋለን በዋዛ ፈዛዛ ....ሚዲያዎችን እንቀንስ ትኩረት ካደረግን ሁሉም ቀላል ነዉ። ላኪን ትኩረት ሳቢዉ በዝቷልና ትኩረታችን ለአላማችን እናድርግ።

t.me/https_Asselfya
✅ ከአሏህ ውጭ ጭንቀትህን የሚያስወግድ አንድም ሰው የለም።

وَإِن يَمْسَسْكَ ٱللَّهُ بِضُرٍّۢ فَلَا كَاشِفَ لَهُۥٓ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍۢ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌۭ

~አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፡፡ በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

=

    
t.me/https_Asselfya
🛑☞ተቀርተዉ ያለቁ እና በጅምር ላይ ያሉ ኪታብ ደርስ ሰሰብስብ !

~~

☞ሹሩጡ ላኢላሀኢለሏህ ወነዋቂዱል ኢስላም⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/214
https://t.me/durus_abu_reyyis/214

☞ቀዋኢዱል አርበዕ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/224
https://t.me/durus_abu_reyyis/224

☞20ምክሮች ለእህቴ ከማግባቷ በፊት⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/232
https://t.me/durus_abu_reyyis/232

☞ላኢላ ሀኢለሏህ ወማእናሀ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/272
https://t.me/durus_abu_reyyis/272

☞ኩን ሰለፍያ አለል ጃዳህ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/314
https://t.me/durus_abu_reyyis/314

☞ሙዛከራት አህካም ፂያም⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/361
https://t.me/durus_abu_reyyis/361

☞ኡሱሉ ሰላሳ ወአዲለቱሀ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/512
https://t.me/durus_abu_reyyis/512

☞ቱህፈቱል አጥፋል ኪታብ ደርስ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/543
https://t.me/durus_abu_reyyis/543

☞በይቁኒያ ኪታብ ደርስ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1015
https://t.me/durus_abu_reyyis/1015

☞ከሽፉ ሹቡሃት ኪታብ ደርስ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1051
https://t.me/durus_abu_reyyis/1051

☞ወረቃት ኪታብ ደርስ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1066
https://t.me/durus_abu_reyyis/1066

☞ኪታቡ ተዉሂድ ደርስ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1096
https://t.me/durus_abu_reyyis/1096

☞ኡርጅዘቱል ሚእያ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1148
https://t.me/durus_abu_reyyis/1148

☞ሚንሀጅ ፊርቀቱ ናጂያ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1173
https://t.me/durus_abu_reyyis/1173

☞አልቀዋዒዱል ፊቅሂያ በጅምር ያለ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1221
https://t.me/durus_abu_reyyis/1221

☞ቡሉغ አል መራም በጅምር ያለ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1240
https://t.me/durus_abu_reyyis/1240

☞ሙንከራት ኪታብ ደርስ ⇓⇓
https://t.me/durus_abu_reyyis/1294
https://t.me/durus_abu_reyyis/1294

=

🎙በአቡ ረይስ ሙሐመድ ኢብኑ ኢማም ሀፊዘሁሏህ
✅ ምንኛ የታደለች እንስት ነበረች‼️

የኛ አርኣያዎች እነዚ እንቁዎች ናቸው! ሞተውም በባለቤታቸው አንደበት በመልካም ይወሳሉ! ባለ ትዳሯ እህቴ እስኪ በመልእክቱ እራስሽን ፈልጊበት የት እንዳለሽ ከባለቤትሽ ጋ በምን አይነት ሁኔታ እንደ ምትኗኗሪ ና ለሱ ያለሽስ ቦታ ከበሬታ………!!

~አሏህ ሆይ እኛም በመልካም ከሚወሱት ደጋግ ባሮችህ መድበን ሷሊሆች አድርገክ ከሷሊህ ባርያህ ጋ መልካም ሕይወትን ግጠመን!!

~
t.me/https_Asselfya
~በትክክለኛው መንገድ ወደ ትክክለኛው
ቦታ እየተጓዝክ ከሆነ ስለመርዘሙ አትጨነቅ!

=
t.me/https_Asselfya
~ትዳርን ውብ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ መከባበር ነው።  መደማመጥ  ጥፋትን መተራረም  ሶስተኛ ሰው በመሃከላቸው አለማስገባት።

~ባል በሚስቱ ላይ የራሱን ሀሳብ ብቻ አልማንፀባረቅም ይካተታል።

~
t.me/https_Asselfya
✅ በሚተኛ ሰዓት ኩል መኳል....!

ጃቢር ኢብኑ አብዲላህ አል አንሷሪባስተላለፉት ሓዲስ የአሏህ መልዕክተኛን ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦

~"በምትተኙ ግዜ ኩል በመኳል ላይ አደራቹህን! ምክኒያቱም እርሱ አይንን ያጠራል ፅጉርንም ያበቅላልና።"

[صحيح ابن ماجه (2834
)]
t.me/https_Asselfya
~ሰባሓል ኸይር...
➰يَا حَيُّ يَا قَيُّومُ بِرَحْمَتِكَ أَسْتَغِيْثُ، أَصْلِحْ لي شَأْني كُلَّهُ، وَلَا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ

📍አንተ ህያዉ የሆንክ አምላክ ሆይ! አንተ ራስክን የቻልክ አምላክ ሆይ!

▪️በእዝነትህ እታገዛለሁ ።
▪️ጉዳዮን ሁሉ የተስተካከለና መልካም አድርግልኝ።
▪️ለቅጽበት እንኳ እኔን ለራሴዉ ብቻ አትተወኝ።


📚ዚክርና ዱአ የመንፈስ ቀለብ !
=
https://t.me/https_Asselfya
✅ እህቴ ሆይ! በባልሽ ልብ ላቅ ያለ ክብርና ቦታ እንዲኖርሽ  ዘንድ!

~መጀመሪያዉ ላባትሽ ወይምለሙሕሪሚሽ ላቅ ያለ ቦታ  ልብሽ ዉስጥ ይኑር ማንኛዉም የትዳር ጥያቄ ለሚያቀርብልሽ  በዋናዉ በር ካልመጣህ አላቅህም በይዉ።

~አባትሽ ቸልተኛ እንኳን ሆኖ አንቺዉ ጨርሸ ቢልሽ አይ የኔ አባት ዲኔ ያስተማረኝ ማንኛዉም የትዳር ዉሳኔ  መጀመሪያዉ ባንተ በኩል  መምጣት እንዳለበት ነዉ በዚህ መንገድ ቤተሰብሽ የሱና ምንነት እንዲረዱ  እንዲሁም  አንችን  ለትዳር ፈልጎ በቀረበሽ  ሰዉም ያንቺ ምንነት ከፍ እንዲልና ባንቺ ያለዉ ፍላጎት እንዲጨምር ያደርገዋል በዚህ መንገድም እዉነተኛዉ የትዳር ፈላጊና ዉሸታሙ ለመለየት ያስችልሻል።

         t.me/https_Asselfya
⭕️👉 መህሯ_በዛ !በደንብ ይነበብ !!

🔎"ያፈዘዘኝ መልዕክት ነው ተማሩበት"

~ሀቂቃ በጣም ደጋግሜ አንብቤው ግን ያልጠገብኩት ታሪክ #ያሱብሀነክ ምንኛ መታደል ነው

♻️ከአንድ ወዳጄ ጋር ነኝ፡፡ በሀሳብ ይሄዳል ይመጣል፡፡ የሆነ ሊነግረኝ ያሰበው ነገር እንዳለ ያስታውቃል፡፡ ግፋ ቢል የትዳርና የፍቅር ጉዳይ ነው፡፡

“ እ ምንድነው እሱ ተንፍስ እንጂ!” አልኩት፡፡

“ ባክህ የሆነች ልጅ አስቤ …እ”
“ አስቤ ነው ወይስ ወድጄ ”“ ያው በለው”

“እ .. እናናግራታ፤ ወይም እናስናግራት፣ ምን ችግር አለው” አልኩት በፍጥጫ፡፡ ነገሮችን ማቅለል እወዳለሁ፡፡

“የዚያ ዓይነት ሰው አይደለችም፡፡” አለኝ፡፡“እህሳ” አልኩት፡፡

“➷በወላጆቿ በኩል ካልሆነ እንዲያናግሯት ፈቃደኛ አይደለችም፡፡” “ለምን?”

💎“እኔ የወላጆቼ ንብረት ነኝ፤ የነርሱ ክብር የኔ ክብር ነው፡፡ በጓሮ በር የሚሆን ነገር የለም፡፡ የሚፈልገኝ በፊትለፊት በነርሱ በኩል ይምጣ፡፡” ትላለች አሉ፡፡
👉አቤት ዛሬ ላይ በጓሮ በኩል የሚመጣ መብዛቱ!!

➷ â€œáŠĽáŠ“ ምነው ፈራህ ታዲያ?” አልኩት፡፡

➴“ ቤተሰቦቿን አጥንቼ ነበረ፡፡ ወላጆቿ የዋዛ አልመሰሉኝም፤ መህሯ ደግሞ አስፈራኝ”

➴“ምን ያህል ይጠይቁኛል ብለህ ትገምታለህ?”

➴“ምናልባት ሀምሳ ሺህ ወይም መቶ ሺህ”“ወደሃታል?” አልኩት፡፡
“አዎን እንክት ነዋ!” አለኝ፡፡

“➷ምኗን” አልኩት፡፡

💎 â€œáŠ˘áˆ›áŠ• አላት፣ ሐያእ አላት፣ አደብ አላት፣ እርጋታ አላት፣ ትህትና አላት፣ ዒልም አላት፡፡”

➴“ታዲያ ይህን ሁሉ ካላት ምን ቀራት?” አልኩት፡፡“ምንም” አለኝ ተገርሞ፡፡

“➴ታዲያ ምን ይሻልሃል?”“ እንጃልኝ፤ ተረብሼያለሁ፣ ወድጃታለሁ፤ ያለሷ መኖር የምችልም አይመስለኝም፡፡” አለኝ ረገጥ አድርጎ፡፡

 âž´â€œáŠĽáˆˇáŠ• ከወላጇ ጉያ ወስዶ የራስ ለማድረግ መቶ ሺህ ይበዛበታል?”

➴“ እ እ …ተጋነነ” አለኝእያማጠ፡፡“ደግሞም አቅሜን ታውቃለህ፣ ነገ ደግሞ ስንት ነገር አለ?”

➴ â€œ እሷን ወደህ፣ መህሯን ፈርተህ እንዴት ሊሆን ይችላል?”

➴“እናስ ምን ትላለህ አንተ?” አለኝ፡፡

➴“እናማ የፍቅር መድሃኒቱ ጋብቻ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ” አልኩት፡፡

🔖“እንዴት ላግባት ታዲያ?”

👉“ለሷ ስትል ሥራ፣ ሌት ተቀን ጠንክረህ ሥራ፣ ብር ያዝ፣ የፈለገዉን ያህል ታስወጣህ አውጣ ”

“➴ይህን ያህል መጎዳት ያስፈልጋል?”

➴“አዎን ዋጋዋ ነው፣ ዉድ እኮ ናት፡፡ ኢማኗ፣ ሐያኡዋ፣ ዒልሟ፣ አስተዳደጓ፣ ዉበቷ፣ ክብሯ፣ አደቧ፣ ትህትናዋ …. á‹­áˆ… ሁሉ ቢደመር በሚሊዮን ይገመታል ወይ? ቤትህ ብትገባ ስንት ነገር እንደሚቀልልህ አታውቅም፣ ስንቱ ነገር የሚስተካከልልህ! ” አልኩት፡፡

➴በርግጥ ላስተዋለ” አለኝ፡፡

➴“ ለአንዲት ሴት ብለው አስር ዓመት በእረኝነት ያገለገሉ ነቢይ እንዳሉ ታውቃለህ?” አለው፡፡

➴“እረ በፍፁም! እንዴት? ምኗን አይተው”

💎 ሐያኡዋን አይተው፡፡ ቁርኣን ላይ ጎልቶ የተጠቀሰው ጉዳይ ሐያኡዋ ነው፡፡ ዐይናፋር ናት፡፡ ትሁት ናት፡፡ መልኳ፣ ቁመናዋ፣ ትምህርቷ፣ ንግግሯ ሳይሆን ሐያኡዋ ነው የተጠቀሰው፡፡”

⭕️👉ታሪኩ እንዲህ ነው …

🔖ነቢዩ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ሁለት የተጣሉ ሰዎችን ለመገላገል ገብተው ከወገናቸው ያልሆነ ሰውዬ ሳያስቡት ድንገት በእጃቸው ላይ ሞተ፡፡ በዚህም የተነሳ ከግብፅ መሰደዳቸው ግድ ሆነ፡፡ በፍርሃት ከተማይቱን ለቀቁ፡፡ አላህ ቀናዉን መንገድ እንዲመራቸዉ እየለመኑ መድየን ምድር ደረሱ፡፡

🔖ከአንድ መንደር ሲደርሱ የአገሬው ሰዎች ከብቶቻቸዉን ዉሃ እያጠጡ ነበር፡፡ እዚያም ሁለት ሴቶችን አገኙና ምን ሊረዷቸው እንደሚችሉ ጠየቋቸው፡፡ ሰዎች አጠጥተው እስኪመለሱ ፈንጠር ብለው ቆመው ነበር፡፡ የነቢያት ልጆች ናቸውና ሥርዓት ማጣት አይመጥናቸዉም፡፡
ነቢዩ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ከብቶቻቸዉን ዉሃ አጠጡላቸው፡፡

🔖#ካጠጡላቸው በኋላ ከአንድ ዛፍ ጥላ ሥር ተጠጉ፡፡ በሰው አገር ተንከራተው፣ ሆድ ብሷቸው፣ ግራ ገብቷቸው ነበርና ወደ አምላካቸው እጃቸዉን ዘረጉ፡፡ “በጎነትህ የሚያስፈልገኝ ፈላጊ ድሃ ነኝ!” ብለው ድክመታቸዉን ለአምላካቸው ተነፈሱ፡፡ ሁሉ የተረፈህ አምላክ ነህና በእዝነትህ እየኝ አሉ፡፡ ዉሃ ካጠጡላቸው ሴቶች መካከል አንዷ በሐያእ አረማመድ ወደርሣቸው መጣችና አባቷ ስላደረጋላቸው መልካም ነገር ዉለታ ሊከፍሉት እንደሚፈልጉ ነገረቻቸው፡፡ ነቢዩ ሙሳ ወደፈለጋቸው ሰው ሄዱ፡፡ ነቢይ ሹዐይብ ናቸው፡፡ ባጋጠማቸው ጉዳይ አፅናኑት፡፡

🔖ታማኝነቱንና# ወንዳወንድነቱ ያየችው ልጅት ወዳዋለች መሰል “አባዬ ቅጠረው” አለችው፡፡ ስምንት ዓመት አገልግለኝና አንዷን ልጄን ልዳርህ አሉት፡፡ ፈቃደኛ ሆኖ አሥር ዓመት አገለገላቸው፡፡ ልጅቷንም አገቡ፡፡

👑#ከወደድካት አግባት👑

🔖የጠየቀችዉን ሁንላት፣ ለምን በቤተሰቧ ዉስጥ ሠራተኛቸው ሆነህ አሥር አታገለግልም? አንተ ከነብይ አትበልጥም። የሚወዱትን ማግኘት ያስከፍላል፡፡

~#ሀቂቃ እስኪ እራሳችንን እንፈትሽ ሴቶችም ወንዶችም.....

~አንቺ ውዱዋ እህቴ እራሴንም ጨምሮ እውን እንዲህች አይነት ሴት ልጅ ነን ፣#እውን እንዲህ ዋጋ የሚያስከፍል ማንነት ነው ያለን ፣#እውን በዲናችን   በአኽላቃችን#እውን ክብራችንን በኒቃብ በጅልባብ በሀያእ የተጠበቅን ነን  የተስተካከልን ነን  #ሁላችን ከራሳችን ጋር እንተሳሰብ...

~#አንተስ ውዱ ወንዲሜ እንዲህ አይነት ወንድ ነህ ?#እንደሌባ በጓሮ ሳትሄድ በፊለፊት በር ሂደህ ለምትወዳት ሴት ዋጋ ከፍለህ ለሷሊሁዋ #ለተቅይዋ ፣ለሙሀደብዋ ይሄን ሁሉ ለያዘችው ሷሊህ ሴት ዋጋ ከፍለህ እውን የራስህ ታደርጋታለህ ወይስ ?#መልሱን ላንተ ትቼዋለሁኝ..

🔍ውድ ነገር# ምንጊዜም ዋጋ ያስከፍላል።

#منقول
t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
⭕️👉 መህሯ_በዛ !በደንብ ይነበብ !! 🔎"ያፈዘዘኝ መልዕክት ነው ተማሩበት" ~ሀቂቃ በጣም ደጋግሜ አንብቤው ግን ያልጠገብኩት ታሪክ #ያሱብሀነክ ምንኛ መታደል ነው ♻️ከአንድ ወዳጄ ጋር ነኝ፡፡ በሀሳብ ይሄዳል ይመጣል፡፡ የሆነ ሊነግረኝ ያሰበው ነገር እንዳለ ያስታውቃል፡፡ ግፋ ቢል የትዳርና የፍቅር ጉዳይ ነው፡፡ “ እ ምንድነው እሱ ተንፍስ እንጂ!” አልኩት፡፡ “ ባክህ የሆነች ልጅ አስቤ …እ”…
ረዠም ፅሀፍ አልወድም ብላችሁ እንዳያልፋችሁ ...የስንፍና አዋጅ ..