💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
ያለ ተውሂድ ጀነትን መመኘት የቂልነት መጨረሻ ነው ።

=
ለዒልም ተማሪዎች ጉርሻ
~
ኪታብ ከሚቀሩ ተማሪዎች ውስጥ ብዙዎቹ ለልፋታቸው የሚመጥን በቂ ግንዛቤ አይጨብጡም። ከነዚህ በተቃራኒ ደግሞ በቂራአት ማእድ ላይ ያላቸው ቆይታ አነስተኛ ሆኖ የተሻለ የሚጠቀሙ አሉ። ልዩነቱ ከምን የመነጨ ነው? ለዚህ ልዩነት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ አድምቶ አለመቅራት የሚያመጣው ክፍተት ነው። የብዙ ተማሪዎች አያያዝ የለብ ለብ ነው። አንዱን ኪታብ ጥንቅቅ አድርገን ሳንይዝ ከፍ ወዳለው ለመግባት ያለን ጉጉት ብዙ ቀርተናል የሚል ጉጉታችንን ከማርካት ባለፈ ብስለት እንዳይኖረን ሊያደርገን ይችላል።
ይህንን ክፍተታችንን ለመድፈን ከሚያግዙ መንገዶች ውስጥ ሶስቱን ላንሳ፦
1- ቃላት ለቀማ
2- መልእክቱን መጨበጥ
3- ነጠብጣቦችን ማገናኘት

ላብራራቸው።
1- ቃላት ለቀማ፦
ከምንቀራው ኪታብ ውስጥ አንድ የማናውቀው ቃል መኖር የለበትም። በተቻለ መጠን ሁሉንም ልቅም አድርገን ልንይዝ ይገባል። በዚህ መልኩ ስንሄድ ደርስ በጣም እየቀለለን ነው የሚሄደው። ቃላት በቅጡ ሳንይዝ የምንጓዝ ከሆነ ግን ወደላይ በገፋን ቁጥር ይበልጥ እየከበደን ይሄዳል። በዚያ ላይ ቃላት የማንይዝ ከሆነ አጠቃላይ የደርሱን ጭብጥ የመያዝ እድላችን እያነሰ ነው የሚሄደው።

2- መልእክቱን መጨበጥ:-
ከኪታብ ትምህርት ዋናው የሚፈለገው አላማ መልእክቱን መጨበጥ ነው። ቁርኣን የወረደው፣ ሐዲሥ የተላለፈው የቃላት ትርጉም ለማስተማር ሳይሆን ለሰዎች የሚበጃቸውን መልእክት ለማስተላለፍ ነው። በብዛት በሃገራችን የተለመደው የቃል በቃል ትርጉም የማስተማር ዘዴ በዚህ በኩል ጉልህ ክፍተት አለበት። ስለዚህ ለመልእክት በቂ ትኩረት መስጠት ይገባል።
እዚህ ላይ አንድ ወሳኝ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። "የተማርነውን ኪታብ በበቂ ሁኔታ እንደተገነዘብነው መለኪያው ምንድነው?" የሚል። መለኪያው የተማርነውን ኪታብ ለሌላ ማስተማር በሚያስችል መጠን ይዘነዋል ወይ?" ብለን ራሳችንን መጠየቅ ነው። ለራሳችን እውነተኛ ሆነን እንመልስ። አንዳንዴ አስተማሪዎች ሲሳሳቱ "ማግኘታችን" የራስ ሽንገላ ውስጥ እንዳይከተን ልንጠነቀቅ ይገባል። የእውነት ኪታቡን በስርአት ቁጭ ብለን ማስተማር እንችላለን? ካልሆነ ወደሌላ ኪታብ ለመቀጠል ከመጓጓታችን በፊት አጥርተን እንማር። "ይህንን ኪታብ ቀርተነዋል፤ ሌላ ይሁንልን" ከማለታችን በፊት ራሳችንን እንገምግም።

3- ነጠብጣቦችን ማገናኘት:-
በዚህ ክፍል ሁለት ነጥቦችን ነው መጠቆም የፈለግኩት።
1ኛ፦ ማስረጃን ከነጥቡ ጋር፣ በአንድ ባብ (ርእስ) ስር የተደረደሩ የቁርኣን አንቀፆችንና ሐዲሦችን ከርእሱ ጋር ማገናዘብ። እየነጠሉ መረዳት በቂ አይደለም። ይሄ ሐዲሥ እንዴት ነው ማስረጃ የሚሆነው? ይሄ መልእክት ከርእሱ ጋር እንዴት ነው የሚናኘው? እያልን ማስተዋል ይኖርብናል።
2ኛ፦ ከራሳችንና ከህዝባችን ተጨባጭ ጋር ማገናኘት። ይህም የምንማረው ትምህርት ራስንም ወገንንም ለመለወጥ እንዲያግዘን ይረዳናል።

ወላሁ አዕለም

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
ያ አላህ ደስሲል አልሃምዱሊላህ
ሴት ልጅ ከምንም በላይ እራሷንም ሌሎችንም እህቶቿንም የወደፊት ልጆቿንም ጥሩና መልካም በሆነ መልኩ ማነጽ ትችል ዘንድ የመጀመሪያዋ እርምጃዋ ሊሆን የሚገባዉ እዉቀትን መፈለግ መማር ማወቅ ነዉ።

አንድት እህት እራሷን ወደ እዉቀት ወደኢልም ባስጠጋች ቁጥር ከራሷ ላይ ጅህልናን አላዋቂነትን እየገፈፈች እራሷን በእዉቀት ብረሀን እየገነባች ወደተሻለ ደረጃ ተሸጋግራ ለሌሎች አራአያ ተምሳሌት መካሪ ሆና ከራሷ አልፋ ሌሎችን የምጠቅም የምታንጽ  የምትቀይር መሆን ትችላለች።

✍️
t.me/https_Asselfya
ኑ እንተዋወስ!!
ተጋብዛችኋል

ሁላችንም እንዘልቃለን
በአላህ ፍቃድ

✍️
ተውሂድን ያልየዘ ሰው ጥላውን ይፈራል።

✍️
ውዷ እህቴ !!

🔍ከሰዎች ተማሪ እንጅ አትኮርጂ
🔍ኩረጃና ትምህርት ይለያያሉና!!


✍️
ድናቸዉን ለመማር ያወቁትን በማሳወቅ ደፋ ቀና በሚሉ ሁሉ ላይ የአላህ እዝነት አይለያችሁ በርቱ ።
የኢማን ጥፍጥና ከማር ይበልጣል ግን ለቀመሰው

ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተዘገበው ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:–

ሶስት ባህሪዎች የተገኙለት ሰው የኢማንን ጥፍጥና አገኘ

👉አላህና መልዕክተኛውን ከማንም ይበልጥ የወደደ!
👉አንድን ሰው ለማንም ሳይሆን ለአላህ ብቻ ብሎ የወደደ!
👉አላህ ከክህደት ካዳነው በኃላ ዳግም ወደ ክህደት መመለስን እሳት ውስጥ እንደመወርወር የጠላ!

📚 [ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል]

🍃
ኹጥባ ለስራ ተቀባይነት መስፈርቶቹ
አቡ ረይስ ኢብኑ ኢማም
﴿خطبة الجمعة﴾
【የጁሙዓ ኹጥባ】

❍ شرطا قبول العمل ...!!

۞ለስራ ተቀባይነት ሁለት መስፈርቶቹ !!

🕌 ደቡብ ወሎ ገርባ ሰላም መስጂድ

🎙በአቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/8230
t.me/abu_reyyis_arreyyis/8230