💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
«ይኸ ይሁን ምርጫሽ»
➭➭➭➭➭➭➭➭➭

መልካም ተናጋሪ አንደበቱ እሩቱ፣
ቁጭ ብሎ የቀራ በግዜ በወቅቱ፣
ኢልምን የተማረ በወጣትነቱ፣
ዝርክርክ ያልሆነ ለድን ለእምነቱ፣
አለሁ ብሎ እሚቆም ለተዉሂድ ለሱና፣
በዉቀት የሚናገር ቆራጥና ጀግና፣
ሊቢድዓ ሰወች የሆነ ገናና፣

ከዉሸት የራቀ ለእዉነት ያደረ፣
በተዉሂድ ጉዳይ ላይ ያልተደራደረ፣
የተውሂድ የሱና ጠባቂ የሚሆን
ካዘዙበት ሁሊም የሚሞሏ ቃሉን
ጠማማውን ሁሉ በሁጃ አንበርካኪ፣
በጣፋጭ አንዴበት እውነትን ሰባኪ፣
ከጠላቶች ሴራ ቃሉ ጋሻ ሁኖ፣
በዴሊል ሲናገር ሰው ሁሉ አምኖ፣

አንተን የሚዘምር በጧትም በማታ፣
ሰወች ካልበዙበት ጭር ካለ ቦታ፣
ሀጥያቱን አስቦ የሚያለቅሰውን፣
ባሪያ በመሆኑ እሚዴሰተውን፣
አሏህን በማዉሳት ነፍሱን ያጠረዉን፣
አይኑን ላክ አድርጎ ወዴ ግዙፍ ሰማይ፣
እባውን ዘርግፎ በሰውነቱ ላይ፣
እባክህ የሚልህን ጭቀቱን እንድ ታይ፣
በጠፊዋ አለምም የሚታገል ለምነቱ፣
ለተውሂድ ለሱና የሚሆን መሰዋቱ፣

ሸሂድ ሁኖ የሚሞት የሚሆን ምኞቱ፣
እዉነት ተናገሪ በተግባር በምነቱ፣
ከመረጥሽስ አይቀር እደዚክ አይነቱ፣


✍️ሶላሁዲን አቡ ዑበይዳህ

𝐓𝐞~ t.me/selahudin_Islamic_knowlages
👍1
ብቻ አንተ ጎበዝ ሁን በሱና ላይ ትጋ
እየዋልክ  እያደርክ  ታወጣለህ ዋጋ


✍️
☑️ በቁርአን እንተዋወስ !!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️
📍ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًۭا لِّلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱمْرَأَتَ نُوحٍۢ وَٱمْرَأَتَ لُوطٍۢ ۖ كَانَتَا تَحْتَ عَبْدَيْنِ مِنْ عِبَادِنَا صَٰلِحَيْنِ فَخَانَتَاهُمَا فَلَمْ يُغْنِيَا عَنْهُمَا مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًۭٔا وَقِيلَ ٱدْخُلَا ٱلنَّارَ مَعَ ٱلدَّٰخِلِينَ
♦️አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑሕን ሴትና የሉጥን ሴት ምሳሌ አደረገ፡፡ ከባሮቻችን ከኾኑ ሁለት መልካም ባሪያዎች ሥር ነበሩ፡፡ ከዱዋቸውም፡፡ ከአላህም (ቅጣት ኑሕና ሉጥ) ከሚስቶቻቸው ምንም አልገፈተሩላቸውም፡፡ ከገቢዎቹም ጋር «እሳትን ግቡ» ተባሉ፡፡

📍وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًۭا لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱمْرَأَتَ فِرْعَوْنَ إِذْ قَالَتْ رَبِّ ٱبْنِ لِى عِندَكَ بَيْتًۭا فِى ٱلْجَنَّةِ وَنَجِّنِى مِن فِرْعَوْنَ وَعَمَلِهِۦ وَنَجِّنِى مِنَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

♦️ለእነዚያ ለአመኑትም የፈርኦንን ሴት አላህ ምሳሌ አደረገ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለእኔ ቤትን ገንባልኝ፡፡ ከፈርዖንና ከሥራውም አድነኝ፡፡ ከበደለኞቹ ሕዝቦችም አድነኝ» ባለች ጊዜ፡፡

📍وَمَرْيَمَ ٱبْنَتَ عِمْرَٰنَ ٱلَّتِىٓ أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَٰتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِۦ وَكَانَتْ مِنَ ٱلْقَٰنِتِينَ
♦️የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን (ምሳሌ አደረገ)፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡


📚ሱረቱል ተህሪም 10_12
=
👍1
ሼኸ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

ነጃ መውጣት (መዳን) የምትፈልግ ከሆነ እነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ አደራ፦
①) የአላህን ኪታብ "ቁርአን" አጥብቀህ ያዝ
②) ቅናቻውን "የመልእክተኛው መንገድ" ተከተል
③) ቢድአ "በዲን ላይ ጭማሬ" ተጠንቀቅ።

📚 شرح المنظومة الحائية (ص٥٦)
t.me/https_Asselfya
👍1
ምንም ያክል ዉድ የሆነ ምግብ ልትበላ ትችላለህ !
ግን እመነኝ ከእናትህ ምግብ የበለጠ የሚጣፍጥ የትም አታገኝም

✍️
ድናቸዉን ለመማር ደፋ ቀና በሚሉ ሁሉ የአላህ እዝነት አይለያቸዉ

«እውቀትን ተማሩ እውቀትን መማር ዒባዳ ነውና  ሰውየው እውቀትን በመማር ላይ እስከሆነ ድረስ ጂሀድ ላይ ነው ያለው»።

ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል

📚መዳሪጁ ሳሊኪን (246-3)

t.me/https_Asselfya

በርቱ ጠንክሩ ማለቴ እንጠንክር!
👍1
04-شرح السنة للبربهاري
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም
🔖 አዲስ ተከታታይ ትምህርት

📚 شرح السنة للبربهاري - ٠٢

✸| ክፍል 04

🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም

👉የኪታቡን pdf ለማግኘት
t.me/https_Asselfya/6108
ما نصيحتكم لرجل يريد يتزوج الثانية ومقصده تطبيق السنة فقط ؟
للشيخ العلامة / عبدالعزيز البرعي حفظه الله
☑️ ሁለተኛ ማግባት ሱና እንደሆነ ብዙዎች ሲናገሩ ይሰማል !?

ነገር ግን ሼኩ ሱና መሆኑን የሚጠቁም ማስረጃ አላውቅም ይሉናል

🎙الشيخ عبد العزيز بن يحيى البرعي حفظه الله

በደንብ እናድምጠው ከመልሱም ባሻገር ምክራቸዉም በጣም ልብ አርስ ነዉና እንመከርበት

https://t.me/https_Asselfya
« ሙዕሚን»
☞የተግባር ሰው ነው፡፡
☞ በንግግሩም ቁጥብ ነው፡፡
☞ሲናገር እፍረት (ሀያእ) አለው፡፡
☞ከተናገረም የሚናገረው መልካምን ብቻ ነው፡፡
አሏህም (ሱብሃነሁ ወተዓላ )እንዲህ ይላል

وَقُل لِّعِبَادِى يَقُولُوا۟ ٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ

ለባሮቼም በላቸው፡- ያችን እርሷ መልካም የኾነችውን (ቃል)ይናገሩ፡፡

📚[አል-ኢስራእ ፣53

t.me/https_Asselfya
የሙናፊቆች ባህሪያት


« ክፍል   ⓸»

🍁ሪያእ(እዩልኝ) ማለት፦አንድ ሰዉ የአምልኮን ተግባር ሲፈጽም  ሰዎች አይተዉ እንድያደንቁት  እንድያወድሱት እና እንድያሞግሱት በመፈለግ ግልፀ አድርጎ  መስራት ማለት ነዉ።

🍁ሱምዓ(ስሙልኝ)ማለት፦ደግሞ አንድ ሰዉ የአምልኮን ተግባር ሲፈጽም ሰዎች ሰምተዉ  እንድያደንቁት እንድያወድሱት እና እንድያሞግሱት በመፈለግ መናገር ማለት ነዉ።

🍁ሪያዕ እና ሱሙዓ ከትነሹ ሺርክ አይነት የሚመደብ ሲሆን ከትልቁ ሽርክ አይነት ዉስጥም ሊካተት የሚችልበት አጋጣሚ አለ። እሱም

1◅እዩልኝ እና ስሙልኙ መሰረታዊ እምነት ላይ ሲሆን። በልቡ ዉስጥ የሌለን እምነት ህይወቱንና ንብረቱን ለመጠበቅ ሲል በግልፀ የሚናገር እና የሚተገብር ከሆነ።

2◅እዩልኝ እና ስሙልኙ  ከስራዉ ከበለጠ።
3◅በሚሰራዉ ስራ በሚናገረዉ ንግግር ከአላህ ፊት ይልቅ የዱንያን ጥቅም የሚያስበልጥ እና የሚያስቀድም ከሆነ።

       የንፍቅና  ፍርድ/ብይን
      ➬➮➬➮➬➮➬➮➬

ንፍቅናዉ በዓቂዳ ላይ የተመሠረተ ከሆነ ትልቁ የንፍቅና አይነት ሲሆን እሱም ባለቤቱን ከእስልምና  ሃይማኖት  የሚያስወጣ ግልፀ ክህደት ነዉ።

ከዚህ ንፍቅዉ ሳይፀፀት ከሞተ ከገሃነብ  አዝቅጥ ዉስጥ ዘዉታሪ  ይሆናል።

በዱኒያ ላይ መልካም ስራ ቢሰራ ስራዉ  ንፍቅናዉ ያጠፋበታል(ያብስበታል)። ሰረቶ እንዳልሰራ ይሆናል።

قال تعالى: { إِنَّ ٱلۡمُنَـٰفِقِینَ فِی ٱلدَّرۡكِ ٱلۡأَسۡفَلِ مِنَ ٱلنَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمۡ نَصِیرًا }

አላህ  እንድህ ይላል፦ሙናፍቃን በእርግጥ ከእሳት ከታችኛዉ አዘቅት ዉስጥ ናቸዉ። ለእነርሱም ረዳት አታገኝላቸዉም። ( አን_ኒሳእ:145)

قال تعالى:{ وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡمُنَـٰفِقِینَ وَٱلۡمُنَـٰفِقَـٰتِ وَٱلۡكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَـٰلِدِینَ فِیهَاۚ هِیَ حَسۡبُهُمۡۚ وَلَعَنَهُمُ ٱللَّهُۖ وَلَهُمۡ عَذَابࣱ مُّقِیمࣱ }

አላህ እንድህ ይላል፦ ወንድ እና ሴት ሙናፊቆች፤ከሐድዎችንም አላህ የገሀነብን እሳት በዉስጧ ዘዉታሪዎች ሲሆኑ ቃል ገብቶላቸዋል። እርሷ በቂያቸዉነት።አላህም ረግሟቸዋል።እነርሱም ዘዉታሪ ቅጣት አላቸዉ። (አት_ተዉባህ :68)

🍁ከእዚህች አያህ ዉስጥ ሙናፊቆች፦

1➛በገሃነም እሳት ዉስጧ ዘዉታሪዎች መሆናቸዉ።
2➛ለእነርሱ ገሃነም በቂያቸዉ እንደሆነች።
3➛አላህም እንደረገማቸዉ እና
4➛እነርሱም  ዘዉታሪ ቅጣት እንዳላቸዉ ተጠቅሷል።


✍️አላህም አንድን ስራ የሚቀበለዉ በሁለት መስፈርቶች ነዉ።

1▻ለአላህ ብሎ ጥርት ተደርጎ የተሰራ ስራ ሲሆን፤
2▻የመልእክተኛዉን ፈለግ መከተል (የእሳቸዉን ትእዛዝ መሰረት በማድረን)የተሰራ ሲሆን ነዉ። ከእዚህ ዉጭ ያለን ስራ አላህ አይቀበልም።

📔 ይቀጥላል ኢንሻ አላህ................

➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
▪️قال ابن القيم رحمه الله تعالى

➷‏"القلب كلما اشتدت به الغفلة؛‏اشتدت به القسوة،‏فإذا ذكر الله ذابت تلك القسوة،‏كما يذوب الرصاص بالنار"…
‏…
☑️ ኢብኑል ቀይም  አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል።
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
➡️አንድ ሰው አላህን ከማውሳት (ከዚክር) በራቀ ቁጥር የቀልብ ድርቀት እየጨመረ እና ቀልቡ እየደረቀ ይሄዳል።

♦️ነገር ግን አላህን በሚያወሳ (በሚዘክር) ጊዜ  ሊድ የተባለው ማእድን በእሳት እንደሚቀልጠው ያቺ የቀልብ ድርቀት እንደዛ ቀልጣ ትጠፋለች።
📚[‏الوابل الصيب (١٤٦)]
t.me/https_Asselfya